ru
Feedback
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

Открыть в Telegram

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot 🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Больше
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
221 160
Подписчики
-9624 часа
-6127 дноК
-2 66330 день
Архив постов
Фото недоступноПоказать в Telegram
በኢራን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ‼️ በኢራን ሴምናን ከተማ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 5.2 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተገልጿል። የኢራኑ ታስኒም የዜና ወኪል የመሬት መንቀጥቀጡን መጠን 5.2 እንደሆነ ሲያሳውቅ፤ የአሜሪካ የጂኦሎጂ ጥናት ማዕከል (USGS) በበኩሉ ክስተቱ 5.1 በሬክተር ስኬል መመዝገቡን አስታውቋል። የመሬት መንቀጥቀጡ ከሴምናን ከተማ በስተደቡብ ምዕራብ 37 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተ ሲሆን፤ 10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት እንዳለው ታውቋል። የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሰውና በንብረት ላይ ስላደረሰው ጉዳት እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ኢራን በጂኦሎጂያዊ እንቅስቃሴ በሚታወቀው የአልፓይን-ሂማሊያን ላይ የምትገኝ በመሆኗ በዓለም ላይ ለመሬት መንቀጥቀጥ በጣም ከተጋለጡ ሀገራት አንዷ ነች። እንደኢኮኖሚክ ታይምስ ዘገባ ኢራን በዓመት በአማካይ 2ሺ 100 የመሬት መንቀጥቀጦችን የምታስተናግድ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ከ15 እስከ 16 የሚሆኑት ከባድ የሚባሉ ናቸው። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 219😭 72👍 26😁 18🔥 11🙏 5😱 3
በኢራን እና በእስራኤል መካከል የተጀመረው ጦርነት ማንም ወደማይቆጣጠረው እሳት ሊሸጋገር ይችላል‼️ 🗣ተመድ በኢራን እና በእስራኤል መካከል የተጀመረው ጦርነት አፋጣኝ እልባት ከላገኘ ማንም ወደማይቆጣጠረው እሳት ሊያመራ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አስጠነቀቁ። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግጭት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ የንፁሃን ሞት እና መፈናቀል፣ በመኖሪያ ቤቶች እና በሲቪል ማኅበረሰብ መሠረት ልማቶች ላይ ውድመት፣ በኒውክለር ተቋማት ላይ ጉዳት እያስከተለ ነው ብለዋል። "ጦርነቱ በዚሁ ከቀጠለ ማንም ሊቆጣጠረው የማይችለው እሳት ሊፈጥር ይችላል፤ ያንን መፍቀድ አይገባም" ሲሉ አሳስበዋል ዋና ጸሐፊው። ቆም ብለን በጥሞና በማሰብ እና ትክክለኛ ውሳኔ መወሰን የወደፊት የጋራ ብሩህ ተስፋዎችን መዘየድ እንደሚገባም በኤክስ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስገንዝበል። የሁለቱ ሀገራት ግጭት ውድመት እያደረሰ እንዲቀጥል ከማድረግ በጋራ በኃላፊነት ስሜት በመንቀሳቀስ ቀጠናውን ብቻ ሳይሆን ዓለምን ከቀውስ ገደል አፋፍ እንታደግ በማለት ጥሪ አቅርበዋል። በግጭቱ ተዋናዮች እና ግጭቱ ውስጥ ለመሳተፍ በመንደርደር ላይ የሚገኙ አካላትም ለሰላም ዕድል እንዲሰጡ ጠይቀዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 211😁 19👍 14👏 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
📍አድራሻ - በመሀል ከተማ ለቡ ማብራት-ሀይል ⚡️ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ወጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!! ➤ ስቱዲዮ (56,57 ካሬ) ➤ ባለ አንድ መኝታ (69,77,85,90 ካሬ) ➤ ባለ ሁለት መኝታ (99,104,133,145,150.. ካሬ) ➤ ባለ ሦስት መኝታ(118,139,144,150,155 ካሬ) ➤ ባለ አራት መኝታ (175,177,185,193 ካሬ) የንግድ ሱቆች - 28.3 - 900 ካሬ 💸8% / 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ 👉 በተጨማሪም ከ 8% - 30%  እንደ አከፋፈሎ ቅናሽ ይደረግሎታል 🏢 ሁሉም ቤቶች  ከስቱዲዮ እና ከ ባለ አንድ መኝታ ውጭ ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል, ስቶር እና የ ላውንድሪ ክፍሎች ያሏቸው። የጋራ መገልገያዎች 🔘 አራት የመንገደኞች እና አንድ የእቃ አሳንሰር 🔘 አምስት የዋና ገንዳዋች 🔘 አስተማማኝ ና ደህንነቱ የተጠበቀ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ 🔘 የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ 🔘 ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ 🔘 የቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter) 🔘 ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች ለበለጠ መረጃ 📞  0903723507
Показать все...
❤ 33😱 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ግጭት ስምንተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን፣ ዓለም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀጥሎ የሚያደርጉትን ለማየት በጉጉት እየጠበቀ ነው‼️ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ እስራኤል ከኢራን ጋር በምታደርገው ጦርነት ውስጥ ለመሳተፍ ወይም ላለመሳተፍ ውሳኔ እንደሚሰጡ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል። የዋይት ሐውስ የፕሬስ ሴክሬታሪያት (ካሮሊን ሌቪት) ባነበቡት መግለጫ ላይ ትራምፕ ከኢራን ጋር “ትልቅ የመደራደር እድል አለ” ብለዋል። ትራምፕ ኢራንን የማጥቃት ዕቅዳቸውን ያጸደቁ ቢሆንም ከእስራኤል ጎን ለመሰለፍ ወይንም ላለመሰለፍ አልወሰኑም ሲሉ ምንጮች ለቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ ተናግረዋል። ትራምፕ በፎርዶ በሚገኘው የኢራን የምድር ውስጥ የዩራኒየም ማበልፀጊያ ተቋም ላይ ጥቃት የመፈጸም ብርቱ ሃሳብ እንዳላቸው ሲቢኤስ ዘግቧል። የምድር ውስጥ የኒውክለር ተቋሙን ለማጥፋት የሚያስችል ትልቅ ቦምብ እንዳላት የሚታሰበው አሜሪካ ብቻ ናት። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 260😁 41👍 26😱 20🕊 10🔥 5😡 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
📍አድራሻ - በመሀል ከተማ ለቡ ማብራት-ሀይል ⚡️ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ወጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!! ➤ ስቱዲዮ (56,57 ካሬ) ➤ ባለ አንድ መኝታ (69,77,85,90 ካሬ) ➤ ባለ ሁለት መኝታ (99,104,133,145,150.. ካሬ) ➤ ባለ ሦስት መኝታ(118,139,144,150,155 ካሬ) ➤ ባለ አራት መኝታ (175,177,185,193 ካሬ) የንግድ ሱቆች - 28.3 - 900 ካሬ 💸8% / 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ 👉 በተጨማሪም ከ 8% - 30%  እንደ አከፋፈሎ ቅናሽ ይደረግሎታል 🏢 ሁሉም ቤቶች  ከስቱዲዮ እና ከ ባለ አንድ መኝታ ውጭ ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል, ስቶር እና የ ላውንድሪ ክፍሎች ያሏቸው። የጋራ መገልገያዎች 🔘 አራት የመንገደኞች እና አንድ የእቃ አሳንሰር 🔘 አምስት የዋና ገንዳዋች 🔘 አስተማማኝ ና ደህንነቱ የተጠበቀ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ 🔘 የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ 🔘 ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ 🔘 የቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter) 🔘 ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች ለበለጠ መረጃ 📞  0903723507
Показать все...
❤ 35
Фото недоступноПоказать в Telegram
የጸጥታው ምክር ቤት በእስራኤል እና ኢራን ግጭት ዙሪያ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ‼️ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በእስራኤል እና ኢራን ግጭት ላይ ለመወያየት ለዓርብ ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን ቢቢሲ ዘግቧል። ስብሰባው በኢራን፣ ሩስያ፣ ቻይና፣ ፓኪስታን እና አልጄሪያ ጥያቄ አቅራቢነት የተጠራ ሲሆን፤ የእስራኤል አምባሳደር ዳኒ ዳኖን በስብሰባው እንደሚገኙ ዘገባው ጠቅሷል። የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ ከሳምንት በፊትም በኢራን ጥያቄ አቅራቢነት የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በኒውዮርክ መምከሩ ይታወሳል። በስብሰባው ላይ የእስራኤልን ጥቃት ያወገዙት የኢራን ተወካይ ሰኢድ ራቫኒ የጸጥታው ምክር ቤት ድርጊቱን እንዲያስቆምና እስራኤልን ተጠያቂ እንዲያደረጋት ጠይቀው እንደነበር ዘገባው አስታውሷል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 225👍 23👏 23😁 20🕊 15
ሕዝበ ሙስሊሙ ለመጅሊሱ ምርጫ ከነገ ጀምሮ የመራጭነት ካርድ እንዲወስድ ጥሪ ቀረበ‼️ ሕዝበ ሙስሊሙ ለኢትዮጵያ እስልም ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ ለማድረግ ከነገ ጀምሮ በየመስጅዱ የመራጭነት ካርድ እንዲወስድ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ላለፉት 5 ወራት ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው ቦርዱ በ2017 ዓ.ም ለሚካሄደው የመጅሊስ ምርጫ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጾ በነገው እለት ምዝገባ እንደሚጀመር ይፋ አድርጓል። ቦርዱ ምርጫውን አሳታፊና አካታች በሆነ መልኩ ለማካሄድ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል፡፡ በመሆኑም ሕዝበ ሙስሊሙ መታወቂያውን በመያዝ ከነገ ጀምሮ ለ12 ቀናት በየመስጅዱ በሚደረገው የመራጮች ምዝገባ ተመዝግቦ የመራጭነት ካርድ እንዲወስድ ቦርዱ ጥሪ አቅርቧል። በምዝገባው ሂደት ለሚያጋጥሙ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በየመስጅዱ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ መቋቋሙም በመግለጫው ተጠቁሟል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 169😁 34👏 11👍 9😱 7🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
እስራኤል በቴህራን የሚገኘውን የሐገር ውስጥ ደህንነት መስሪያቤት ማውደሟን አስታወቀች። የእስራኤል ሰራዊት ዛሬ ባሰራጨው መረጃ «የሐገር ውስጥ የደህንነት መስሪያቤቱን ያወደምኩት በጦር አውሮፕላኖች ድብደባ ነው» ብሏል‼️ ሰራዊቱ ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ በኢራን ላይ የሚካሄዱ ጥቃቶች አላማ የኒኩለር ማብለያ ተቋማትን ማውደም ብቻ ሳይሆን «አምባገነን» ያለውን የኢራንን መንግስታዊ መዋቅሮችንም እንደሚያካትት ገልጾ ነበር ሲል አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 148😁 36👍 30😡 27😭 11👌 10😱 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
📍አድራሻ - በመሀል ከተማ ለቡ ማብራት-ሀይል ⚡️ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ወጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!! ➤ ስቱዲዮ (56,57 ካሬ) ➤ ባለ አንድ መኝታ (69,77,85,90 ካሬ) ➤ ባለ ሁለት መኝታ (99,104,133,145,150.. ካሬ) ➤ ባለ ሦስት መኝታ(118,139,144,150,155 ካሬ) ➤ ባለ አራት መኝታ (175,177,185,193 ካሬ) የንግድ ሱቆች - 28.3 - 900 ካሬ 💸8% / 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ 👉 በተጨማሪም ከ 8% - 30%  እንደ አከፋፈሎ ቅናሽ ይደረግሎታል 🏢 ሁሉም ቤቶች  ከስቱዲዮ እና ከ ባለ አንድ መኝታ ውጭ ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል, ስቶር እና የ ላውንድሪ ክፍሎች ያሏቸው። የጋራ መገልገያዎች 🔘 አራት የመንገደኞች እና አንድ የእቃ አሳንሰር 🔘 አምስት የዋና ገንዳዋች 🔘 አስተማማኝ ና ደህንነቱ የተጠበቀ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ 🔘 የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ 🔘 ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ 🔘 የቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter) 🔘 ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች ለበለጠ መረጃ 📞  0903723507
Показать все...
❤ 38👏 1🙏 1
አያቶላ ኻሚኒ አሜሪካ ኢራንን ብታጠቃ ከባድ መዘዝ የሚያመጣ ዘላቂ ጉዳት እንደሚያጋጥማት አስጠነቀቁ‼️ የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ ዩናይትድ ስቴትስ ኢራንን ብታጠቃ ከባድ መዘዝ የሚያመጣ ዘላቂ ጉዳት እንደሚያጋጥማት አስጠነቀቁ። የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ለኢራን መሪዎች በተለይም ለአያቶላ ኻሚኒ ኢራን ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ እጅ መስጠት አለባት የሚል መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ፣ የኢራንን ህዝብና ታሪኳን የሚያውቁ አስተዋዮች ኢራንን በዚህ መልኩ ዛቻ በተሞላበት ቃላት አይናገሯትም ብለዋል፡፡ ምክንያቱም ኢራናውያን ለጠላት የሚንበረከኩ ህዝቦች አይደሉም ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። መንፈሳዊ መሪው አያይዘውም፤ ዩናይትድ ስቴትስ ከእስራኤል ወግና ኢራንን ማጥቃት ከጀመረች ከባድ እና ዘላቂ ጉዳት እንደሚደርስባት አስጠንቅቀዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 367😁 62👍 52👏 16🕊 11🙏 6😭 4
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኢራንን የአየር ክልል ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረነዋል አሉ‼️ የጂ7 ስብሰባን አቋርጠው ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማምሻውን ትሩዝ በተሰኘ ማህበራዊ ገፃቸው ባጋሩት ጽሁፍ፥ የኢራንን የአየር ክልል ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረነዋል ብለዋል። ትራምፕ አያይዘውም ኢራን ጥሩ የተባለ የአየር ክልል መቆጣጠሪያ እና ሌሎች ወታደራዊ መሳሪያዎች በብዛት አሏት፤ ነገር ግን አሜሪካ ከሰራቻቸው አይበልጡም ብለዋል። ማንም ሀገር አሜሪካ ከምትሰራቸው የላቁ ወታደራዊ መሳሪያዎች ሊሰራ አይችልም፤ የአሜሪካ ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎች የትኛውም ሀገር ከሚሰራቸው የተሻሉ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
😁 249❤ 186👍 69😡 39🕊 20👏 6😱 6
Фото недоступноПоказать в Telegram
የኢራን እና የእስራኤል ግጭት አሜሪካ እሳቱን በማራገብ እያባባሰች ነዉ ስትል ቻይና ከሰሰች‼️ የዩናይትድ ስቴትስ መሪ የቴህራን ነዋሪዎችን "ወዲያውኑ ለቀው እንዲወጡ" ካስጠነቀቁ በኋላ ቻይና በኢራን እና በእስራኤል መካከል እየተባባሰ ባለው ግጭት ላይ "እሳት በማቀጣጠል" ትራምፕን ከሰሰች ። “እሳቱን ማቃጠል፣ ነዳጅ ማፍሰስ፣ ማስፈራራት እና ግፊት መጨመር የሁኔታውን መባባስ ለማርገብ አይረዳም ነገር ግን የበለጠ እንዲባባስና ግጭቱን ያሰፋዋል” ሲሉ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉኦ ጂያኩን በመደበኛ የዜና ኮንፈረንስ ላይ ስለ ትራምፕ አስተያየት ሲጠየቁ ተናግረዋል ።በእስራኤል የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ማክሰኞ እስራኤል እና ኢራን ከባድ ጥቃት ዉስጥ መግባታቸዉን ተከትሎ ዜጎቹ “በተቻለ ፍጥነት” ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳስቧል። "በእስራኤል ውስጥ ያለው የቻይና ተልእኮ ቻይናውያን በተቻለ ፍጥነት በመሬት ድንበር ማቋረጫዎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳስቧል፣ ይህም ለግል ደህንነታቸው ዋስትና እንዲሰጡ ቅድመ ሁኔታ ነው" ሲል ኤምባሲው በዊ ቻት ላይ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።"በዮርዳኖስ አቅጣጫ መሄድ ይመከራል" ሲል አክሏል፡፡የቤጂንግ ኤምባሲ ማክሰኞ እለት ግጭቱ “መባባሱን ቀጥሏል” ብሏል። "በርካታ የሲቪል መሰረተ ልማቶች ተበላሽተዋል፣ የዜጎች ጉዳት እየጨመረ ነው፣ የጸጥታው ሁኔታም አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል" ብሏል።የኢራን እና እስራኤል ጥቃቱ ከበፊቱ ያነሰ ቢሆንም ለአምስተኛ ቀን የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ከመካከለኛው ምስራቅ የሚወጡ ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡እስራኤል በምዕራብ ኢራን ውስጥ በርካታ “ወታደራዊ ኢላማዎች” በአንድ ሌሊት የመታች ሲሆን ከምሽት ወደ ላይ የሚተኮሱ ሚሳኤሎች እና የድሮን ማከማቻ ቦታዎችን ደብድባለች፡፡ @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 201👍 14🎉 10🔥 6😱 3😁 2💔 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
በሀይፋ የሚገኘው ትልቁ የእስራኤል የነዳጅ ማጣሪያ ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ ሥራ አቆመ‼️ በቀን ከ200 ሺህ በርሜል በላይ ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት የሚያጣራው በሀይፋ የሚገኘው ትልቁ የእስራኤል የነዳጅ ማጣሪያ እሁድ ምሽት በኢራን ባለስቲክ ሚሳይል መመታቱ ይታወሳል። እስራኤል በኢራን የሚገኙ ሁለት የነዳጅ ማጣሪያዎችን ቅዳሜ ዕለት በቦንብ መደብደቧን ተከትሎ እሁድ ምሽት ኢራን የሀይፋ የነዳጅ ማጣሪያን በባለስቲክ ሚሳኤል መትታለች። ማጣሪያው 60 ፐርሰንት የሚሆነውን ነዳጅ ለእስራኤል ያቀርብ የነበረ ሲሆን፤ ጥቃቱን ተከትሎ በደረሰበት ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ሥራ ማቆሙን ሮይተርስ ዘግቧል። በሌላ በኩል በኢራን ሚሳይል ጉዳት ከደረሰባቸው ከተሞች አንዷ በሆነችው በሀይፋ በኢራን የሚሳይል ጥቃት የወደሙ ቦታዎችን በመቅረፅ ላይ የነበሩ የቲአርቲ ጋዜጠኞች ተይዘው ካሜራቸው እንደተቀማ የዜና አገልግሎቱ አስታውቋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 283😁 55👍 44😭 36👏 18🕊 13🔥 5
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የላከው መልዕክት‼️ ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እየተባባሰ የመጣውን የእስራኤል እና ኢራንን ጦርነት አስመልክቶ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ የ5 ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሀገራቱ መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ ሰላም ለዓለም የሚል መልዕክት ማስተላለፉ ይፋ ሆኗል፡፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ጨዋታ ለሰላም” የሚል ያልተጠበቀ ስጦታ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ እንደተላከላቸውም አሳውቀዋል፡፡ ሮናልዶ የፈረመበትን የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን መለያ ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አንቶኒዮ ኮስታ እጅ የተረከቡት የሪፐብሊካኑ ተወካይ በአሁኑ ሰዓት ለቡድን ሰባት ስብሰባ ካናዳ ይገኛሉ፡፡ @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 405👍 65😁 31👏 6🙏 4🔥 3🎉 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ትናንት ሌሊት ኢራን በእስራኤል ላይ በፈጸመችው ጥቃት አራት ሰዎች መሞታቸውን የእስራኤል ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አገልግሎት አስታወቀ‼️ ይህም በእስራኤል ከአርብ ዕለት ጀምሮ የተገደሉትን ሰዎች ቁጥር 19 አድርሶታል። የብሔራዊ ድንገተኛ ጊዜ አገልግሎቱ በ70ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሁለት ሴቶች እና ሁለት ወንዶች መገደላቸውን አስታውቋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 197😁 46😭 42🕊 35👏 26👍 23🔥 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኢራን ለእስራኤል ሲሰልል አግኝቼዋለሁ ያለችውን ዜጋዋን በሞት ቀጣች‼️ ኢራን ለእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ ሲሰልል ነበር በማለት በቁጥጥር ስር አውላው የነበረውን ዜጋዋን ዛሬ በሞት መቅጣቷን የኢራን መንግሥት የዜና አውታር ኢርና ዘግቧል። ኢስማኢል ፌክሪ፥ አሚር ከተባለ የሞሳድ ወኪልና ከሌላ የእስራኤል ሰላይ ጋር በመገናኘት ምስጢራዊ የሆኑ የኢራን ቦታዎችን የሚመለከትና ሌሎች ቁልፍ መረጃዎችን ለእስራኤሉ የስለላ ድርጅት በማቀበል ተጠርጥሮ በዲሴምበር 2023 በቁጥጥር ስር ውሎ ነበር። እንደ ኢርና ዘገባ፥ ተጠርጣሪው በኢራን መንግሥት የቀረበበትን ክስ ከማመኑም በተጨማሪ ለዚሁ ሥራው በክሪፕቶከረንሲ ክፍያ መቀበሉ በማስረጃ ተረጋግጧል። ተጠርጣሪው በጠላትነት የተፈረጀች ሀገርን በመርዳትና የኢራንን ብሔራዊ ደህንነት አደጋ ላይ በመጣል ተከሶ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በዛሬው ዕለት በስቅላት መቀጣቱን ዘገባው ጠቅሷል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 342👍 80😁 31😭 28💔 26😱 11🔥 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኢራን ወደ እስራኤል ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን ተከትሎ እስራኤል ዜጎቿን ወደ ጥብቅ መጠለያ እንዲያመሩ መልዕክት አስተላለፈች‼️ @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 331😁 147👍 58🙏 38🕊 28😱 16💔 6
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኢራን በእስራኤል ላይ በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ በርካታ ውድመቶች ማድረሷ ተገለጸ‼️ በትላንትናው ምሽት የእስራኤል ጦር በፈጸመው የአየር ጥቃት፣ የኢራን የነዳጅ ዘይት ማከማቻዎች መምታቱን ተከትሎ ኢራን በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ በርካታ ውድመቶች ማድረሷ ተገልጿል። እስራኤል የፈጸመችው የአየር ጥቃት የኢራን የሚሳኤል ማከማቻ ዋሻዎችን እና ማስወንጨፊያ ቦታዎችን ኢላማ ያደረገ መሆኑን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል። በኢራን ዋና ከተማ የሚገኘው ሻህራን የነዳጅ ዘይት ማከማቻ (ዴፖ) በእስራኤል የአየር ጥቃት መመታቱን ተከትሎ፣ ኢራን በቴላቪቭ ላይ በርካታ ሚሳኤሎችን በማዝነብ ከ9 በላይ ህንጻዎችን አውድማለች። እስራኤልም በኢራን ላይ በፈጸመችው ጥቃት፣ ከዚህ በፊት 3 መቶ ሚሳኤሎች ወደ ቴላቪቭ እንዲወነጨፉ ያዘዙትን የጦር አዛዥ ጨምሮ የኢራንን እንቁ የኒውክሌር ሳይንቲስቶች በመግደሏ ከወዳጆቿ ውዳሴ እየጎረፈላት መሆኑ ተጠቅሷል። እስራኤል የኢራንን የጦር አዛዦች እና የኒዩክለር ሳይንቲስቶች በአንድ ምሽት የአየር ጥቃት መግድሏ ያንገበገባት ኢራን፣ በትላንትናው ምሽት ሚሳኤሎችን ወደ ቴላቪቭ በማዝነብ የበቀል እርምጃዎችን ወስዳለች። የቴህራን የነዳጅ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው መረጃም የኢራን የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ በእስራኤል የምሽቱ የአየር ጥቃት መውደሙን ገልጿል። እስራኤል ከዚህ ድርጊቷ ካልተቆጠበች ኢራን ከእስካሁኑ የከፋ ጥቃት በእስራኤል ላይ ልትሰነዝር እንደምትችል የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሶድ ፔዜሽኪያን ማስጠንቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው፣ በኢራን የፈጸሙት የአየር ጥቃት በእስራኤል እና በአጋር ሀገሮች ላይ በኢራን ሊሰነዘር የነበረውን ጥቃት ያመከነ ነው ብለዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 425👍 43🕊 25😁 23👏 21😡 13🤝 8
Фото недоступноПоказать в Telegram
እስራኤል ኢራናውያን ከወታደራዊ ተቋማት እንዲርቁ አሳሰበች‼️ የእስራኤልመከላከያ ሠራዊት ኢራናውያን ከወታደራዊ ተቋማት አካባቢ እንዲርቁ አሳሰበ። መከላከያ ሠራዊቱ በኤክስ ገጹ ላይ በለጠፈው ጽሑፍ “በወታደራዊ የጦር መሣሪያ ማምረቻ ፋብሪካዎች ውስጥም ሆነ በአካባቢውእንዲሁም የድጋፍ ተቋሞቻቸው አካባቢ የሚገኙ ሰዎችወዲያውኑ ለቅቀው እንዲወጡ እና ተጨማሪ መግለጫ እስኪሰጥ ድረስ እንዳይመለሱ” ብሏል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 164😁 44👍 13😱 8🔥 6🎉 5
Фото недоступноПоказать в Telegram
እስራኤል የአየር ክልሏን እና ዋነኛ አየር ማረፊያዋን ዘጋች‼️ በተጨማሪም የአገሪቱ ዋነኛ አየር ማረፊያ ቤን ጉሪዮን ለየትኛውም በረራ ዝግ መሆኑን አክሏል። የአየር ክልሉም ሆነ የአየር ማረፊያው ከሚኒስቴሩ ትዕዛዝ እስካልመጣ ድረስ ዝግ ሆነው ይቆያሉ ተብሏል። የቤን ጉሪዮን የአየር ማረፊያ ድረ-ገጽ ዛሬ ጥዋት እየሰራ አልነበረም። ሚኒስቴሩ አርብ፣ ሰኔ 6/ 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ለመጓዝ ያቀዱ መንገደኞች “የአገሪቱ አየር ክልል እንደገና ከመከፈቱ ቢያንስ ከስድስት ሰዓታት በፊት” መረጃው በመገናኛ ብዙኃን ይደርሳቸዋል ብሏል። እስራኤል በኢራን እየፈጸመችው ያለውን ጥቃት ተከትሎ የአየር ክልሏን ዘግታ የነበረችው ዮርዳኖስ ከአንድ ቀን በኋላ መክፈቷን አስታውቃለች። በአገሪቱ በረራዎች ተቋርጠው የነበረ ሲሆን ዛሬ በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር 1፡30 የአየር ክልሏን መክፈቷን የዮርዳኖስ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን አስታውቋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1
Показать все...
❤ 245😁 73👍 21🔥 16💔 15🙏 3