ru
Feedback
️ ንስር አማራ🦅

️ ንስር አማራ🦅

Открыть в Telegram

የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ። 💚💛❤️ እኛን በውስጥ ለማናገር @NISIREamhra2 @NISIREamhraa_bot 👈 ይችን አድራሻ ይጠቀሙ🦅 ንስር ዐማራ🦅 #የግፉአን_ድምፅ t.me/NISIREamhra

Больше
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
63 130
Подписчики
-2124 часа
-2237 дней
-78730 день
Архив постов
🔥#አፈሳና_የንፅሀን_ጭፍጨፋ‼️ #የንፁሀን_ግድያ- የአገዛዙ ኃይል በዛሬው ዕለት ወሎ ቀጠና መቅደላ ላይ ተማሪዎችንና ወጣቶችን ፋኖ በማለት ጭፍጨፋ ፈፅመዋል ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች ገልፀዋል‼️ #አፈሳ- አገዛዙ ወደ ጦርነት የሚማግደውን ወጣት በግዴታ እያፈሰ እንደሆነ በተደጋጋሚ የተዘገበ ሲሆን በዛሬው ዕለት በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ደብረብርሀን ከተማ በተለያዩ ቀበሌዎች አፈሳ ሲካሄድ የነበረ ሲሆን ወጣቶቾ አልባሌ ቦታና ከመገኘት በመቆጠብና እንቅስቃሴን በመግታት ራሳችንን ከወታደራዊ አፈሳ እንጠብቅ ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች ገልፀዋል‼️ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 17/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
61👍 14😢 11🙏 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
🔥#የጥንቃቄ_መልዕክት‼️ #የጦር_ጀቱ_ቀጠናውን_እየቃኘ_ነው‼️ ዛሬ ህዳር 17/2018 ዓ/ም መነሻውን ከአፋር ሱልጣን አሊሚራህ ሐንፍሬ አየር ማረፊያ ያደረገ ሚግ አውሮፕላን በራማ ገብርኤል ተራራና በቀዩ ጋሪያ በኩል አቆራርጦ በመብረር ሙሉ የራያ ቀጠና ላይ አሰሳ ሲያደርግ አርፍዷል። የጦር ጀቱ በራያ ግምባር፦ አማያ፣ ጨፌ መንደር፣ ሸወይማርያም፣በዋጉሥጋሌ፣ ጠበለት፣ አረፋ ጊዮርጊስ፣ ቀመሌ ተክለሐይማኖት፣አሣ መምቻ፣ ተኩለሽ፣ አራዱም፣ ሮቢት፣ ጎብየ፣ በላጎ፣ ቃሊም ዙሪያ ላይ ቅኝት ሲያደርግ ያረፈደ ሲሆን በመጨአሻም በወልድያና ፀሐይ መውጫ አድርጎ ወደ ኮምቦልቻ ማቅናቱን የመረብ ሚዲያ የምስራቅ አማራ ግንባር ዘጋቢዎች ተመልክተዋል። ሚግ አውሮፕላኑ ዛሬ ህዳር 17/2018 ዓ/ም ከማለዳው 12:00 ጀምሮ ለሁለት ሰዓታት ያህል እየተመላለሰ ቅኝት ሲያደርግ ቆይቷል። መነሻውን ከሰመራ የሚያደርገው ተዋጊ አውሮፕላኑ፡ ሰሞኑን በተከታታይ እኩለ ለሊት ገደማ ላይ የዞብል፣ የቀዩ ጋሪያ፣ የራማ ተራሮችን ይዞ እስከ ተኩለሽ፣ ቆቦ ዙሪያ፣ አባሆይ ጋሪያ፣ ግዳን ዙሪያና በላጎ ተራራ እንዲሁም አላማጣን አልፎ ከፊል የትግራይ አከባቢዎች ላይ ቅኝት አድርጎ እንደሚመለስ ጣቢያችን መረብ ሚዲያ በህዳር 15/2018 ዓ/ም የምሽት ዜና እወጃው ዘግቦ እንደነበር ይታወቃል። አገዛዙ በርከት ያለ የሰዎች ስብስብ ካገኘ ጥቃት ከመፈፀም ወደኋላ እንደማይል ከዚህ ቀደም በፈፀማቸው ጥቃቶች ያሳየ ሲሆን፡ ስለሆነም ማሕበረሰቡ እንደ ገበያና የሐይማኖት ስፍራዎች እንዲሁም መሠለ መሰባሰቢያ ስፍራዎች ላይ ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መረጃውን ላልሰሙት አሰሙ። ©መረብ ሚዲያ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 17/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
96🙏 14👍 10
🔥#ቁልፉ_የመረጃ_ሰው_ተሸኝቷል‼️ የፋሽስቱ አገዛዝ ቁልፍ የመረጃና ደህንነት ሰው ቆቦ ከተማ ላይ እርምጃ ተወሰደበት:: የቆቦ ከተማ መረጃ እና ደህንነት የሆነው የፋሽስቱ አገዛዝ ቁልፍ ሰው አቶ ጥጋቡ ደርቤ ከነ አጃቢዎቹ በሰማዕቶቹ ጀግኖች በነ አርበኛ አለሙ ገብሩ በነ አርበኛ ዋሴ ከበደ በነ አርበኛ ፍሬው አለና እና ሌሎች አርበኞች ልጆች በምስራቅ አማራ ኮር 2 ቃኝ አባሎች ወደማይቀረው ተሽኝቷል:: ከአማራ ህዝብ ተፈጥሮ ከፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ጋር በመተባበር የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ የኖረው ሆድ አደሩ አቶ ጥጋቡ ደርቤ ከነ አጃቢዎቹ ህዳር 16/2018 ዓ.ም ምሽት ቆቦ ከተማ ላይ በምስራቅ አማራ ኮር 2 ቃኝ አባሎች እርምጃ ተውስዶበታል:: በቀጣይም እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 17/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
115👏 15🎉 13💔 9👍 2🏆 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
🔥ህዳር አስራ ሰባት (17) ቀን ሺህ ስምንት መቶ ሰባ ዘጠኝ (1879) ዓመተምህረት‼️ #ዝክረ_ታሪክ ከአንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ (139) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት ታሪክን የኋሊት!! ከአንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ (139) ዓመታት በፊት በዛሬዋ ዕለት #አዲስ_አበባ ከተማ በዳግማዊ አጼ ምኒልክና በእቴጌ ጣይቱ በፍል-ውሃ ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ አጥር አሳጠረውበት በነበረው ሥፍራ አካቢብ ላይ እቴጌ ጣይቱ ፍልውሃ ወደ በሚፈልቅበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተው ስለወደዷት ቦታውን “አዲስ አበባ" በማለት ከአንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ዓመታት በፊት የሰየሙበት ዕለት ነበር። #የኋላው_ከሌለ_የለም_የፊቱ‼️ #ይህ_የኛ_የኢትዮጵያውያን_ታሪክ_ነው‼️ 17/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
88👍 16🙏 12
🔥ከአፍብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር-11ኛ ክፍለ-ጦር  የተላለፈ  ጥብቅ ማሳሰቢያ‼️ **** 1. ባህር-ዳር እና  አካባቢው ላይ ጠላት ብዛት ያላቸው የስለላ ሃይሎችን የላከ መሆኑ የውስጥ መረጃ ደርሶናል። በመሆኑም ከቀን 16/03/2018 ዓም ጀምሮ በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ የሚንቀሳቀስ የትኛውም የታጠቀ ሃይል (በአማረ መንጌ ወይንም በላይ ዘለቀ) የተረጋገጠ ህጋዊ ጊዜያዊ መታወቂያ የመያዝ ግዴታ አለበት። 2. ጠላት የመሣሪያ ኮንትሮባንድ የሚሠሩ ነጋዴዎችን አሰማርቶ መሣሪያ ግዠ (ሽከፍ) ላይ መሆኑን ደርሰንበታል።በባህር ዳር እና አካባቢው ላይ የመሣሪያ ሽያጭ ፈፅሞ የተከለከለ ነው።ከዛሬ ጀምሮም (ከቀን 16/03/2018 ዓም ጀምሮ) ቀጠናው ላይ በንግድ መልክ  ሲሸጥ ሲለውጥ የተገኘ አካል በተጨባጭ ከተገኘ ንብረቱ በክ/ጦሩ ውርስ ይሆናል። መሣሪያውንም ክ/ጦሩ ለአባሉ ትጥቅ ያውላል። 3. ለጠላት ቅርብ በሆኑ አካባቢዎች የአርሶ አደር መሣሪያ የሚያስወርዱ፤ በፍኖ ስም የሚነግዱ የጠላት ሃይሎች ተሠማርተዋል።በባህርዳር እና አካባቢው ላይ የምትገኙ ማህበረሰባችንም መሣሪያችሁን በጥንቃቄ እንድትይዙ ።ከዛሬ ጀምሮ ትጥቁን ለየትኛውም አካል በሰላም አሳልፎ ከሰጠ ፤ተገቢውን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል።(በፍኖ ስም እየደወለ የሚያስወርድ አካል ካለም፤ ፍኖ አለመሆኑን ለማሣሰብ እንወዳለን) 4. ህገ-ወጥ የለቅሶ ላይ ተኩስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው። 5. ባህርዳር እና አካባቢው ላይ ኑሯቹህን እና ጎጇቹህን ቀልሳችሁ የምትኖሩ የመንግስት የሚኒሻ አካላት በአስቸኳይ እስከ ታህሳስ 1/04/2018 ዓም ወደቀደመ ኑሯቹህ ትመለሡ ዘንድ እናሳስባለን።ከመንግስት የምታመጡት መሣሪያ የግላችሁ መሆኑን እና አካባቢውን በሚያስተዳድረው ፍኖ የማትጠየቁ መሆኑን እንገልፃለን። 6. የአርበኛ ዘመነ ካሴን ጥሪ አክብራችሁ አሁንም ከመንግስት ተቋም አድማ ብተና፣ፓሊስ እና መከላከያ ወጣችሁ ለምትመጡ ከነሙሉ ትጥቃችሁ የትራንስፓርት ጨምረን ወደየመጣችሁበት አካባቢ የምንልካችሁ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን። ..................                  ............. አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፍ!!            ክፍት ለማንም በጎነት ለሁሉም!! ©አፍብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር፣11-ኛ ክ/ጦር #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 16/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
65🙏 18👍 11
🔥#Stop_Amhara_Genocide ‼️     #ስዊዘርላንድ‼️ በብልፅግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ፆታዊ ጥቃት እንደጦር መሳሪያ በመጠቀም ፣ በሴቶች ላይና በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት ዘር-ማጥፋት (Genocide ) ፣ የሚያጋልጥ ሰልፍ በንስር አማራ ሚዲያና በጀግናዋ እህታችን አስተባባሪነት ሰላማዊ ሰልፍ፣ የሻማ ማብራትና አበባ የማስቀመጥ ስነ-ስርዓትና #በሲዊዘላንድ በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ በአራቱም የአማራ ቀጠናዎች በነበሩ ሴት ታጋዮች የተፈፀመው ኢ- ሰብዓዊ ድርጊትና በጎጃም ሰከላ በአገዛዙ ሰራዊት ተደፍራ የተገደለችዋን የ14 አመት ህፃን ቃልኪዳን አዲሱና መሰል ወንጀሎች እየተወገዙ ይገኛል‼️ ዝርዝር መረጃውንና ቪዲዬውን ፕሮግራም ሲጠናቀቅ ይዘን የምንመለስ ይሆናል። #የአማራ_ጭፍጨፋ_ይቁም‼️ #Stop_Amhara_Genocide ‼️ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 16/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
123👍 29🙏 10😢 4🎉 1
🔥በደብረ ኤልያስ ከተማ የበርካታ ዜጎች መኖሪያ ቤት እንዲፈርስ ሀገር አፍራሹ የብልጽግና ስብስብ ወስኗል‼️ በስሁት የፖለቲካ ትርክት ሰክሮ አማራን ከነሁለንተናው ለማጥፋት ደፋ ቀና ለሚለው የኦሕዴድ መር ሥርዓት የሚያጎበድደው  የአማራ ካድሬ ለምስር ወጥና ለርካሽ ስልጣን ሲል የገዛ ሕቡን ለጨፍጫፊዎቹ በማመቻቸትና የእኩያንን ዓላማ ተፈጻሚ በማድረግ በአማራ ሕዝብ ታሪክ የማይረሳው ግፍና መከራን እያደረሰ ይገኛል። ከነዚህም መካከል "በመልካም አንገት ላይ እንቅርት እንዲሉ"  ሁለንተናዊ ልዕልናና ኃያልነትን አስተባብራ በኖረችና ባለችዋ በደብረ ኤልያስ ከተማ የተወሸቀው ጸረ ሕዝቡ የብልጽግና ስብስብ ይገኝበታል። ከተማውን ከወረረበት ዕለት ጀምሮ በንጹሐን ላይ የመከራ ቀንበር ሲያወርድ የከረመው ገዳይ ስብስብ ዛሬ ደግሞ ሌላ ጆሮን ጭው የሚያደርግ የጥፋት ዜናን ለደብረ ኤልያስ ከተማ ነዋሪዎች አሰምቷል። ይህም በፋል(FAL) የመንገድ ተቋራጭ በሚሰራው ሀገር አቋራጭ መንገድ ምክንያት ቤታቸው ከሙዛ ጀምሮ እሰከ አበሸብ በግምት በ3KM ርዝመት ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ያለምንም የካሳ ክፍያ ቤታቸውን እንዲነሱ ነው ዛቻ አዘል ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው። በወቅቱ (ከ3 ዓመት በፊት) ለባለ ቤቶቹ የካሳ ክፍያ ጸድቆላቸው በሚፈጸምበት ወቅት በፈነዳው የፋኖ አብዮት ሥራው በመቋረጡ ምክንያት የካሳ ክፍያ የቀረ ሲሆን ዛሬ ግን እንዳዲስ ውሳኔዎች ተገልብጠው ያለምንም ካሳ አፍርሰው እንዲነሱ ተነግሯቸዋል። ቅሬታ ያቀረቡ የከተማው ነዋሪዎችም "አርፋችሁ ተቀመጡ ምንም አይነት ቅሬታም ሆነ ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም፤ እንኳን ቤታችሁ ይቅርና እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም፤ የማታርፉ ከሆነ እናንተንም እናፈርሳችኋለን..." በማለት ነዋሪዎችን አንገታቸውን አስደፍተው መልሰዋቸዋል። የብልጽግናው ሌባ ስብስብ ይህንን የክህደት ተግባር የፈጸመውም የተለመደ የዘረፋ ተግባሩን ለመፈጸም ነው። ነገሩ እንዲህ ነው! የበረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ ወረዳውን ሙሉ በመሉ ከተቆጣጠረበት ከሐምሌ 27/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለ1 ዓመት ከ6 ወር ያክል ራሳቸውን የወረዳው አመራር አድርገው በመሰየም ደብረ ማርቆስ ከተማ የተወሸቁ ሆዳም ባንዳዎች ያለምንም መምሪያ በአየር ላይ እየተወራረደ ከ9000,000 (ዘጠኝ ሚሊዮን) ብር በላይ ተበልቶ በመገኘቱ ሁሉም የብልጽግና ካድሬዎች ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተው ሰንብተዋል። ይህንንም የተበላ ገንዘብ ለማካካስ  የካሳ ክፍያውን  ወደ ራሳቸው በማዞር ካሳ ጸድቆላቸው ነገር ግን የመንገድ ተቋራጩ ስራ በማቆሙ ምክንያት ክፍያ ያልተፈጸመላቸው የቤት ባለይዞታዎች ያለምንም የካሳ ክፍያ ቤታቸውን አፍርሰው እንዲነሱ ዛቻ የተሞላበት መምሪያ አውርደዋል። ይህ ስብስብ አስቀድሞም የደብረ ኤልያስንና ማቻክል ወረዳዎችን ለማገናኘት ጌደብ ወንዝ ሊሰራ ከታቀደው የድልድይ ማሰሪያ ገንዘብ በመቀበል ይህንን የተዘረፈ ገንዘብ ለመሙላት አስቦ እንደነበርም መረጃዎች ደርሰውናል። ድል ለአማራ ፋኖ! ክብር ለሕዝባችን! ©ፋኖ ዘመን ባሳዝነው የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 16/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
59👍 10💔 7🙏 3😢 1
🔥#እውነት እያደረች ትጠራለች ተደብቃ አትቀርም‼️ አገዛዙ ወደ ፋኖ አስርጎ ያስገባውን ግለሰብ በተለየዬ መንገድ ፖለቲካ ሊሰራበት ሞክሯል 1ኛ. ፅንፈኛው (በእነሱ አጠራር) የሰላም አማራጭን እየተቀበለ እንደሆነ 2ኛ. የሰላም አማራጭ ተጠቅመው ወደ አገዛዙ ገቡ የተባሉትን ግለሰቦች በፋኖ ማልያ አሰቃቂ ተግባር እንዲፈፅሙ አድርጎ በመቅረፅ ህዝባችንና አለም አቀፉ ማህበረሰብ  #የአማራ_ፋኖን ከሌሎች አሸባሪዎች ተርታ እንዲያስቀምጡትና ከህዝብ ለመነጠል ነበረ ግን እኛ የሰባዊነት ውኃ ልክ ከሆነው የአማራ ህዝብ አብራክ የወጣናንና የአፄ ምኒልክ እና #እትጌ_ጣይቱ_ብጡል ልጆች ነንና ይህ ተግባር የምንታገለውና የምንፀየፈው ተግባር ነው‼️ ተግባሩም የአገዛዙ እንደሆን ትናት የተለቀቁ screenshots መረጃዎች ምስክሮች የሚሆኑ ሲሆን የድራማው ደራሲና ተዋናይ በውይይት ጊዜ የነበረውን ሁነት በዚሁ ፎቶ ማዬት ይቻላል። ፎቶው ከAI የፀዳ እንደሆነ ደግሞ የAI ምርመራን 100% ያለፈ መሆኑንም አብረን አየይዘናል!! #እውነት እያደረች ትጠራለች ተደብቃ አትቀርም‼️ በጦር ሜዳ ያጣውን ድል በሚዲያው ሞክሮ ነበረ አልተሳካም!! #ፋኖ_ይችላል💪 #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 16/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
124👍 29🙏 10💯 3💔 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የቀስተ ደመና ሻለቃ ደጎልማ በሚባል ቦታ ላይ በወራሪው የብልጽግና ሠራዊት ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ሀለንተናዊ ጥፋትን በሕዝባችን ላይ እየፈጸመ የሚገኘው ወራሪው የብልጽግና ሠራዊት የአርሶ አደሩን መኸር ለማውደምና ለመዝረፍ በመጣበት ደጎልማ ቀበሌ ላይ ጀግኖቹ የቀስተ ደመና ሻለቃ ፋኖዎች በአመሻሹ ሲለበልቡት አምሽተዋል። ጀግኖቹ ጠላትን በጥይት አረር እየገረፉት ባለበት ሰዓት ለመቁረጥ የገባውን ጠላት በመልሶ መቁረጥ ድባቅ በመምታት በአመሻሹ ሙትና ቁስለኛውን አስታቅፈውታል። ድል ለአማራ ፋኖ! ክብር ለሕዝባችን! ፋኖ ዘመን ባሳዝነው የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
Показать все...
85👍 39🏆 5
🔥ማረጉ ተማረ ክፍለጦር ከ20 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት በመደምሰስና ከ35 በላይ በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፀፉ‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ስር የሚገኘው ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ባደረገው አውደ ዉጊያ ከ20 በላይ የአገዛዙ ጦር ሲደመሰስ የጠላት ኃይል 35 ቁስለኛውን ይዞ ወደመጣበት እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል። የብርሃኑ ጁላ 12ኛ ክፍለ ጦር ሁለት ሬጅመንት፣የ65ኛ ክፍለ ጦር ሁለት ሬጅመንት ኃይልና የ65ኛ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድ በጥምረት አንድ ዙ-23 እና አራት ዲሽቃ በመያዝ መነሻውን ከላስታ ወረዳ ብልባላ ከተማ በማድረግ ሌሊቱን በመጓዝ የማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ቃኝን፣ሦስተኛ ሻለቃንና የኮሩን ዘመቻ መምሪያ ኃላፊን አርበኛ ፋኖ ታዘበው ሻምበልንና ስልጠና መምሪያ ኃላፊውን አርበኛ ፋኖ አምሳ አለቃ መልካሙ ገበየሁን አፍናለሁ በሚል ቀቢፀ ተስፋ ወደ 01 ቀበሌ ይምርሃነ ክርስቶስ በመጓዝ ላይ እንዳለ ክፍለ ጦሩ ቀድሞ በደረሰው መረጃ መሠረት ዛዚያ ስላሴ፣ዳቢያና አሞራ ደብር ደፈጣ በመያዝ ህዳር 16/2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12:30 ሰዓት እስከ አመሻሽ 12:00 ሰዓት ለሙሉ ቀን በተደረገ ትንቅንቅ ከ20 በላይ የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ከ35 በላይ ቆስሏል። በዚህ አውደ ዉጊያ ጠላት የማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ቃኝን፣3ኛ ሻለቃንና ከላይ የተጠቀሱ የኮር አመራሮችን ለማፈን አቅዶ የመጣ ቢሆንም ጠላት ባላሰበውና ባልጠበቀው ራሱ ታፍኖ የማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ቃኝንና ሁሉንም ሻለቃዎች በማሳተፍ ጠላት በወገን ክንድ ሲቀጠቀጥ ውሎ ወደመጣበት ፈርጥጧል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 15/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
81👍 24👏 5
🔥‎የምኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የጎፍ ክ/ጦር በሳልመኔ ከተማ በመግባት አስደናቂ ኦፕሬሽን ሰራ‼️ ‎ ‎========== ‎የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የጎፍ ክ/ጦር በአልብኮ ወረዳ መቀመጫ ሳልመኔ ከተማ በመግባት በብልጽግና የጸጥታ አካላት ላይ ርምጃ ወስዷል:: ‎ ‎በዚህም ድንቅ ኦፕሬሽን የአልብኮ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አመራር የሆኑት አልይ አሰን የሚኒሻ ጽ/ቤት አመራር ካሳው እና ሌሎች ጋሻ አጃግሬዎቻቸው ላይ በተወሰደ እርምጃ ከባድ ቁስለኛ ሁነው ሆስፒታል ገብተዋል ሲል የልጅ እያሱ ኮር የየጎፍ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አርበኛ ሱልጣን የሱፍ ለንስር አማራ በላኩት መልዕክት ገልፀዋል። ‎ ‎ ህልውናችንን በተባበረ ክንዳችን እናረጋግጣለን!!! #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 15/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
105🙏 14👍 9🫡 5💯 1
🔥#አትፈልጉት‼️ ኮሎኔል ረሺድ ከደብረ ማርቆስ በርካታ አባላት እና መሳሪያ ይዞ ከድቷል። ብርሐኑ በቀለ ፍለጋውን እያጧጧፈው ነው ። ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን ። ድል ለጀግናው ፋኖ !! ©አረበኛ ማርሸት ፀሐው #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 15/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
164👍 54🙏 14🏆 13🫡 6😡 2
🔥#ሸዋ_አማራ‼️ የመናገሻችን እምብርት ሸዋ ቀጠና አናብስት (አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ) ውስን ነበልባሎች💪 #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 15/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
92👍 34💔 2
🔥#ሰበር_ዜና‼️ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለጦር ጀነራል ተፈራ ማሞ  ብርጌድ በአገዛዙ ሰራዊት ላይ  መብረቃዊ ጥቃት ሰነዘረ። ጀነራል ተፈራ ማሞ ብርጌድ በከተማ ኦፕሬሽን በተደጋጋሚ በመስራት አመርቂ ውጤት እያስመዘገበች ያለቺው ባለፈው ሳምንት ናደው ሻለቃ የተሳካ የደፈጣ ስራ በአሮጌ ምንጃር መፈፀሟ ዘግበን ነበር። ትላንት ህዳር 16, 2018 ዓ.ም ማታ በ2:00 ሰዓት በአረርቲ ከተማ በአሮጌው ከብት ተራ ካሉ መጠጥ ቤት በሚገኙበት የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ሚኒሻና ኮማንዶ መከላከያ በየአረቄ ቤቱ ተወሽቀው እንደገቡ መረጃ የደረሳቸው መብረቁ ሻለቃ በብርሃን ፍጥነት ከቦታው በመድረስ በወረፋ ሱሳቸውን ሲያጣጥሙ የነበሩትን የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ኮማንዶ እና ገረዶቹ ሚኒሻዎች ቅንድብ ቅንድባቸው በማለት ስያጋድሟቸው አምሽተው በሰላም ወደ ቀጠናቸው ተመልሷል። በዚህ የተደናገጠው የአገዛዙ ሰራዊት በአካባቢው ከሚገኙ መጠጥ ቤት ሰራተኛ አንቺ ነሽ ያስገደልሽን በማለት እንደረሸኗት አረጋግጠናል። አረርቲ ሆስፒታል በርካታ ቁስለኛና ሙት እንደታየ በመረጃ ምንጮቻችን አማካኝነት ማረጋገጥ ችለናል። መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።      " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ©‎አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።     #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 15/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
77👍 4🏆 3🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
🔥የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ እና አሳምነው ዕዝ አሃዶች በጥምረት በተለያዩ ግንባሮች ታላቅ ድል ተጎናፀፉ‼️ ምኒልክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር አሃዶች እና አሳምነው ዕዝ የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኮር ብሩኬ ደምሴ ክፍለጦር አሃዶች በጥምረት የብልፅግና አራዊት ሰራዊት ላይ በተለያዩ ግንባሮች ድል ተጎናፅፈዋል:: ህዳር 15/2018 በሶስት ግንባር ወደ ማጥቃት የገቡት የእምዬ ምኒሊክ እና የአሳምነው ፅጌ ልጆች በአካድ ግንባር ብቻ የስርዓቱ ወታደር አብዛሀኛው ተከቦ ሲደመሰስ ከፊሎቹ ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነዋል። በዚሁ ግንባር ከ10 በላይ ክላሽ እና በርካታ ተተኳሽ የተማረከ ሲሆን ምሽጉ በጀግኖቹ ተሰብሮ ጠላት ሲፈረጥጥ እየተከታተሉ እንደ ንብ እየነደፉት ነው። በሌላኛው በነጋሽ ግንባር ያለው ምሽግም በመክት ሻለቃ የተደረማመሰ ሲሆን ጥላት ሬሳውን እያዝረከረከ ፈርጥጧል:: በሌላኛው በፉርሴ ግንባርም ስበር ሻለቃዎች የአብይን ሆድ አደር ውሃ ውሃ እያስባሉት ሲሆን ነውር ጌጡ የሆነው የዘረኛና ጨፍጫፊ ቡድን ከደሴ ተጨማሪ ሃይል የጨመረ ቢሆንም ኬላ ቦታዎችን በመያዝ በደፈጣ እያበራዩ ወደ መጣበት መልሰውታል:: በዚህ የተበሳጨውና በእግረኛ ሰራዊቱ ብሎም በመካናይዝዱ ውጤት ማምጣት የተሳነው ፋሽስቱ አገዛዝ አየር ሃይሉን በመጠቀም በድሮን ጥቃት የንፁሃኖችን ህይወት ቀጥፏል:: በተጨማሪም ቤትና ንብረትም አውድሟል ሲል የየጎፍ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ ሱልጣን የሱፍ ገልጿል‼️ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 15/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
63🙏 15👍 2🏆 2
🔥#የልዩ_ኮማንዶዎች_የምረቃ_ቪዲዬ‼️ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለጦር ለስድስት ወራቶት ያሰለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ‼️ የምረቃውን ወታደራዊ ትርዒት በዩቱዩብ አድራሻችን ይመልከቱ👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/pxFt4LxwuS0?si=ILjg1o1plBaxXG_0
Показать все...
44👍 24🏆 4🎉 1
🔥"ድርጊቱ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ" እንደሚባለው ነው‼️ ------------------------------------------------- ከቀናት በፊት ዲጅታል ኢትዮጵያ በሚል የአገዛዙ ዲጅታል ሳይበር -እነሱ ፅንፈኛ ብለው የሚጠሩት በትክክለኛ ስሙ ከፋኖ ወደ መንግስት የሰላም ጥሪ ተቀብሎ እጅ ሰጠ ብለው መዘገባቸው ይታወሳል። ማስረጃውን በፎቶ ከታች በፎቶ የተመላከተ ሲሆን ደቡብ ወሎ ወረኢሉ ወረዳ በአንድ ግለሰብ የተፈፀመው ድርጊት የብልፅግናዎች የእጅ ስራ ውጤት ነው።የአማራ ህዝብ ትግልን በሰይጣናዊ ዕሳቤ ለመክሰስ መሞከር በፍፁም ተቀባይነት የለውም!! " #ጅራፍ_ራሱ_ገርፎ_ራሱ_ይጮሃል" እንዲሉ አበው ከታች በምስሉ ላይ የሚዘዋወረው ግለሰብ ፈፀመው በተባለ ድርጊት ላይ የብልፅግና የሚዲያ ሰራዊት እና ጀሌዎቻቸው የሚያሰራጩት አሉባልታ የአማራ ፋኖን አይመለከትም። ድርጊቱንም ሆነ ግለሰቡን በፍፁም እናወግዛለን!! ሰራዊታችን ምስጉንና ህዝባዊ ሃላፊነቱን የሚወጣ እንጅ በባንዳ ስም የብልፅግና ተልዕኮ ተሸካሚዎች በሚፈፅሙት አሉታዊ የዕለት ከዕለት ተግባር ፋኖ ሊከሰስ አይገባውም!! እንደሚታወቀው ፀረ-ሰው የሆነው የብልፅግና ስርዓት በአማራ ህዝብ ላይ በርካታ ወንጀሎችንና ኢ-ሰብአዊነት መገለጫ የሆነው አገዛዙ በትግላችን ላይ ጥላሸት ለመቀባት ያደረገውን ያልተገባ ስም ማጥፋት በቀላሉ የምንመለከተው አይደለም!! የብልፅግናው ተልዕኮ ተቀባይ የአማራ ፋኖን ትግል ከህዝባችን ስነ ልቦናዊ ዕሴት ጋር ይነጥላል ብሎ በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ በተባለ ወረዳ የተፈፀመው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የአማራ ፋኖን የማይመለከት እና ግለሰቡ ድርጊቱን በፈፀመበት ቅፅበት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ውሏል በሚል መገለፁ የድርጊቱ ባለቤቶች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ነው። የአማራ ፋኖ ሰራዊታችን ከራስ በፊት ለህዝብ የሚኖር እና ህዝባችንን ከተጋረጠበት ብሔራዊ የህልውና አደጋ ጠላቶቹን በአግባቡ የሚከላከል ሃይል እንጅ በመሰል አረመኔያዊ ድርጊቶች ከቶ የሚጠረጠር እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል። በግለሰቡ አማካኝነት የተፈፀመውን ነውረኛ ድርጊት እኛም እንደ ታጋይ እና ድርጅት የምንቃወመው  እንድሁም በዚህ እኩይ ድርጊት ላይ የተሳተፉ አካላትን ጭምር ተጠያቂ የምናደርግ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ዓላማችን የአማራን ብሔራዊ የህልውና አደጋ በመመከት ፀረ-ሰው የሆነውን የብልፅግና ስርዓት በመደምሰስ ለሁሉም ዜጎች የምትሆን የጋራ ሃገር መስራት እንጅ ለርካሺ ፓለቲካ በሚሆኑ ነውረኛ ድርጊቶች ላይ ፍፁም ሃላፊነት በጎደለው ተግባር ውስጥም የማንሳተፍ መሆኑን መላው የኢትዮጲያ ህዝብ የሚያውቀው መሆኑን በምናደርጋቸው ተግባራት የሚታወቅ ነው። ሰራዊታችን እንኳን ለራሱ ህዝብ ለጠላት ሰራዊት ጭምር ርህራሄ ያለው እና የተስተካከለ ስብዕና እና ስነ ምግባር ያለው መሆኑን የተረጋገጠ ነው። ትግላችንን ሰው ሰራሺ እና ተልዕኮ ተቀባይ ሰራጊ አካላት ከቶ አይደናቀፍም!! መዳረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሸንፋል። ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ ህዳር 15-03-2018
Показать все...
166👍 29🎉 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
🔥#አይ_አተኳኮስ_እናቴዋ💪 #ፋኖ_ይችላል💪 ዛሬ ቀን ላይ ሰሜን ጎጃም፣ ሰሜን አቸፈር ወረዳ ሊበን ከተማ ውስጥ በተሰራው ፈጣንና ቀልጣፋ ኦፕሬሽን ጠቋሚ ጣታቸውን ( መተኮሻዋን ) ጭምር እያንጠባጠቡ ያመለጡም አሉ። #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 15/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
👍 66 33❤‍🔥 20🫡 5🏆 4🙏 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ከአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር የተሰጠ ማስጠንቀቂያ! የመካነሰላም ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ካድሬዎች መሬት እየቆረሱ ለባለሀብቶች በጫረታ መልኩ አቅርበው ገንዘቡን የፋሽስቱ አብይ አህመድን ስርዓት እድሜ ማራዘሚያ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን የውስጥ ምንጮች ካደረሱን ጥቆማ ለመረዳት ችለናል:: ካድሬዎች በፕሮፓጋንዳ ብዛት አደናግረው እና በሆድ እየገዙ ከጎናቸው ያሰለፏቸው የፀጥታ ኃይል አባላት ፍላጎት በየጊዜው እያደገ በመምጣቱ የተነሳ እነሱን በሆዳቸው እየገዙ ለማቆየት አስበው የወጣቶች መዝናኛ ስፍራን እና የቀበሌ መኖሪያ ሰፈርን ለባለሀብት በጫረታ ለመሸጥ ካቢኔው አቋም መያዙ ተደርሶበታል:: ከተማይቱ ክልል ውስጥ 03 ቀበሌ የሚገኘው የወጣቶች መዝናኛ ማለትም የስፓርት ቦታ የሆነውን እና የክፍለ ከተማይቱ ውበት ተደርጎ የሚቆጠረውን ሜዳ ለጫረታ አቅርበውታል:: ይህን ብቻ ሳይሆን 02 ቀበሌ በተለምዶ ቲቲአይ ሰፈር ንጋት ፋርማሲ ፊት ለፊት የሚገኘውን ቦታ እና ቀበሌ 01 ጤና ጣቢያ አቅራቢያ ደግሞ የቀበሌ መኖሪያ ቤቶችን ነው ለጫረታ ያሰቧቸው:: በዚህ ምክንያት የቀበሌ ቤት ይኖሩ የነበሩ የድሀ ድሀዎች ልቀቁ ተብለው ከተማይቱ ዳር ወደሚገኘው ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሄደው በቅጥር ግቢው ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ነው ለማረጋገጥ የቻልነው:: የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር እንዲህ አይነት የመሬት ችርቻሮን በጥብቅ የሚያወግዝ ሲሆን በተጫራቾች ላይ ጭምር እርምጃ ከመውሰድ እንደማይቆጠብ ከወዲሁ ያሳስባል:: ስለዚህ በጫረታው ላይ ለመሳተፍ ያሰባችሁ ባለሀብቶች ከወዲሁ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እያሳሰብን ይህን ማስጠንቀቂያ ችላ ብላችሁ በጫረታው ብትሳተፉ ለሚሊሻ ቀለብ እንደሰፈራችሁ ቆጥረነው በእናንተ ላይ ጭምር የማያዳግም እርምጃ እንደምንወስድ እንድታውቁት ይሁን:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም
Показать все...
70👍 10
🔥206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ እና የጅበላ ሙተራ ሻለቃ ባደረጉት ታላቅ ተጋድሎ ጀብድ ተሰርቷል‼️ ህዳር 15/ 2018 ዓ.ም  የአረመኔው ሰራዊት ከደብረ ኤሊያስ፣ደብረ ማርቆስ እና አማኑኤል ከተሞች በመነሳት ወደ ተርቸከል ሊባኖስ በሶስት አቅጣጫ 8 ዲሽቃ በያዘ ኃይል በመድፍ የታገዘ ጥቃት ለመሰንዘር ቢንቀሳቀስም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በተደረገበት የደፈጣ ጥቃትና መደበኛ ውጊያ በርካታ የሰራዊት አባላት ተደምስሰዋል። የማዕከላዊ ዕዝ 602ኛ ኮር 32ኛ ክ/ጦርን በተወርዋሪነት የተጠቀመው የአረመኔው ሰራዊት ተጨማሪ ድጋፍ ሰጭ ይዞ ቢንቀሳቀስም በሁለት ግንባር በተከፈተበት ውጊያ ትስስሩ ተቋርጦ ወደኋላ አፈግፍጓል። ጨለማን ከለላ በማድረግ ስምሪቱን ያደረገው  ጠላት በቴዎድሮስ ዕዝ በ206 ኮር የ14ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ ቸርተከል ላይ ባደረገችው የደፈጣ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ ሲሆን በሊባኖስ ግምባር ደምባ ላይ ከፍተኛ ትንቅንቅ የፈፀመችው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ አስደናቂ ጀብድ ፈፅማለች። በቸርተከሉ ውጊያ ጠላት ተቀጥቅጦ ወደ ኋላ ሲመለስ አስክሬኑን ቀብሮ በአንድ አምቡላንስ እና ፓትሮል ቁስለኛውን ተሸክሞ ፈርጥጧል። የወገን ኃይል ታላቅ ጀብድ የፈፀመበት ደምባ እስከ ምሽት 12:00 አውደ ውጊያው ቀጥሎ የጠላት ሁለት የጦር አመራሮች ተደምስሰዋል ። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! ©የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 15/ዐ3/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Показать все...
85👍 35😡 4🙏 3🏆 3