ru
Feedback
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

Открыть в Telegram

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Больше
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
44 133
Подписчики
Нет данных24 часа
-747 дней
-34830 день
Архив постов
Фото недоступноПоказать в Telegram
በፓኪስታን እና በአፍጋኒስታን መካከል የድንበር ጦርነት ተቀሰቀሰ በፓኪስታን እና በአፍጋኒስታን ታሊባን ሃይሎች መካከል የድንበር ግጭት እንደገና ተቀስቅሷል ፣እያንዳንዱ ወገን ሌላኛውን አካል ደካማ የነበረውን የተኩስ አቁም ስምምነቱን አፍርሷል በሚል እየተካሰሱ ይገኛሉ። በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው 2,600 ኪሜ ድንበር ላይ የምትገኘውን የአፍጋኒስታን ከተማ ስፒን ቦልዳክን  ነዋሪዎች ጥቃትን ፈርተው ተሰደዋል። በአቅራቢያው በምትገኘው የካንዳሃር ከተማ የህክምና ሰራተኛ ለቢቢሲ ፓሽቶ አገልግሎት እንደተናገሩት አራት አስከሬኖች በአካባቢው ወደሚገኝ ሆስፒታል ገብተዋል። ሌሎች አራት ሰዎች ቆስለዋል። በፓኪስታን በኩል ደግሞ 3 ሰዎች ቆስለዋል ተብሏል። ባለፉት ወራት በሁለቱ ሀገራት መካከል አልፎ አልፎ ጦርነት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፥ የአፍጋኒስታኑ የታሊባን መንግስት ፓኪስታን በሀገሪቱ ውስጥ የአየር ድብደባ ትፈጽማለች ሲል ከሷል። ሁለቱም ወገኖች የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ቢያረጋግጡም ለአራት ሰአታት የፈጀውን ጦርነት በተመለከተ አንዳው ሌላኛውን ለጥቃቱ ወቅሰዋል። የፓኪስታን ጠቅላይ ሚንስትር ሸህባዝ ሻሪፍ ቃል አቀባይ ሞሻራፍ ዛዲ ታሊባንን “ያለምክንያት ተኩስ ከፍቷል” ሲሉ ከሰዋል። ይህንኑ ተከትሎ “አፋጣኝ፣ ተገቢ እና ጠንከር ያለ ምላሽ በታጣቂ ሃይሎቻችን ተሰጥቷል ብለዋል። ፓኪስታን ግዛቷን እና የዜጎቻችንን ደህንነት ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነች ሲሉ አክለዋል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
8💔 5👍 2😭 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሚኪያስ ጎማ ፣ ባትሪና ከመነዳሪ አከፋፋይ  #ለቪትስ #ለያሪስ #ለዲዛየርና ስዊፍት #ለኮሮላ #3L & 5L እንዲሁም ለከባድ ተሽከርካሪዎች የሚሆኑ ጎማዎች እና ባትሪዎችን ይዘዙን ካሉበት እናደርሳለን 👉የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎማዎች (ትሪያንግል ፣ ስፖርትራክ ፣ ኮምፈርሰር ፣ አፖሎ ፣ ብሪጅስቶን እና ሌሎችም) 👉 የተገለገሉበት ጎማ ን ዋጋ ተምነን በአዲስ እንቀይርሎታለን 👉 በስልክ ቁጥር 📞...+251-913-701702 / +251-975293297 ይደውሉልን አልያም ተክለሀይማኖት ከሚገኘው ሱቃችን ይምጡ በደስታ እናስተናግድዎታለን
Показать все...
9
Фото недоступноПоказать в Telegram
የአራት ወር ህፃን ላይ የፈላ ውሃ በመድፋት ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንሶ ዞን በካራት ከተማ ሚሊኒየም ሰፈር በአቶ ኩሲያ ካላሌ መኖርያ ቤት ግቢ ውስጥ የወንጀል ድርጊቱ ተፈፅሟል። ሊባን ኤርሚያስ የተባለች የ4 ወር ዕድሜ ያላት ህፃን በእናቷ ወይዘሮ ካይሎቴ አማሬ ታቅፋ እያለ ተከሳሽ የፈላ ውሃ በብረት ድስት በማድረግ እናት በታቀፈቻት ልጅ ፣በእናትየው እና በሌላ በ3 ዓመት ከ5 ወር ልጅ ላይ በመድፋት ጉዳት ማድረሷ ተገልፆል፡ በዚህም የአራት ወር እድሜ ያለት ህፃን ወዲያኑ ህይወቷ ሲያልፍ የ3 ዓመት ከ5 ወር ህፃን  እና ወላጅ እናት በህክምና ህይዉታቸው ማትረፍ ተችሏል ሲሉ በኮንሶ ዞን የቀና ወረዳ ፍትህ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ገመቹ ገለገሎ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ በዚህም ፖሊስ ተከሳሽን በቁጥጥር ስር በማዋል በወንጀለኛ  ህግ አንቀጽ 27/1 58/1/ሀ እና  539/1 ጠቅሶ ክስ መሰርቷል፡፡ተከሳሽ የወንጀሉን ድርጊት አምና ተበዳይ ስለምትሰድባትና ስለምታንቋሽሻት ወንጀሉን የፈፀመች መሆኗን ገልፃ ችሎቱም የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ከሰማ በኋላ በክስ አንድ በወንጀል ህግ አንቀጽ 58/1/ለ እና 540 ስር እና በክስ 2 እና 3 በወንጄል ህግ አንቀጽ 58/1/ለ እና 555/ሀ እንድትከላከል ብይን ሰጥቷል። ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ እንደሌላት ለችሎት የገለፀች በመሆኑ ችሎቱም እንዲትከላከል ብይን በሰጠበት የህግ አንቀጽ ስር ጥፋተኛ በማድረግ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ መወሰኑን በኮንሶ ዞን የቀና ወረዳ ፍትህ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ገመቹ ገለገሎ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
💔 50 26😱 10👎 8👍 5🤬 3
የመጀመሪያ ባለቤቱን ከአዲሷ ሚስቱ ጋር በመተባበር ገድለዉ  ለአራት ዓመታት ተሰዉረዉ የነበሩ ጥንዶች ወደ ማረሚያ ቤት ወረዱ ሰይድ አደም የተባለው የሀምሣ አንድ አመት ግለሠብ ነዋሪነቱ በምስራቅ ባሌ ዞን  ጐሎልቻ ወረዳ ድሬ ጉዶ ቀበሌ ነዋሪ ነው።ሰይድ በተለያዩ የንግድና ግብርና ስራ ተሰማርቶ ቆይቷል፡፡በወጣትነት ዘመኑ ሳምሺያ ሳና ከተባለች ሴት ጋር በሀገር ባሕልና ወግ መሠረት ሽማግሌ በመላክ በጋብቻ ትዳር መስርቷል።ሰይድ ከሳምሺያ ጋር ትዳር መስርቶ ልጆች ወልዶ እያለ በሒደት  ሌላ ትዳር ይመሠርታል። በዚሕም ሁለተኛ ትዳር ሰይድ ሳምሺያ ሲያገባ የሚቆርጥላትን መተዳደርያ ለሁለተኛ ሚስቱ መቁረጥ ይጀምራል።የሰይድ ሁለተኛ ሚስት ፋጡማ መሐመድ የተባለችውም ሳምሺያ ያላት መሬት ቀምታ ስታሳርስ ፣ ባለቤትዋን ና ፋጡማን በመክሰስ ፍርድቤት ችሎት ላይ እንደ አቀረበቻቸው የምስራቅ ባሌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ገልጸዋል። ሰይድና ፋጡማ በዚሕ ቂም በመያዝ መስከረም ወር 2014 ዓም ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ላይ ሳምሺያ በተኛችበት እንቅልፍ ላይ እያለች ፋጡማ ስለታም ሳንጃ በመያዝ ሰይድ ደግሞ በማነቅ ፋጡማ በእንቅልፍ ላይ ያለችው ሳምሺያን የተለያዩ ሰውነቷ ክፍል ላይ በስለታማ ሳንጃ በመዉጋር ህይወቷ እንዲያልፍ ካደረጉ በኃላ ከአካባቢው ተሰዉረዋል።በነጋታው የሣምሺያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደልን ተመልክቶ ከአካባቢው ነዋሪዎች ሪፖርት እንደደረሠ ፖሊስ በስፍራው በመገኘት አስክሬኑን በማንሳት ወደ ሆስፒታል ልኳል፡፡ የምርመራ ሂደቱንም ለዚህ ወንጀል መነሻ ምክንያትና የድርጊት አፈፃፀም በተለያዩ ማስረጃዎች ሲያጣራ ሰይድና ፋጡማ ድርጊቱን ስለ መፈፀማቸው  በበቂ ማስረጃ በማጣራት ክትትሉን እንደቀጠለ ዋና ኢንስፔክተር አሻግሬ ጥላሁን ተናግረዋል።በፖሊስ በኩል አስፈላጊው የምርመራ መዝገብን በአስክሬን የምርመራ ውጤት ፡ በማስረጃ ተጣርቶ ለአቃቢ ሕግ በመላኩ አቃቢ ሕግ ከባድ ና ጭካኔ የተሞላበት በመሆኑ ተከሣሾች በሌሉበት  ክስ መስርቷል፡፡ በአቃቢ ሕግ የተከፈተውን ክስ ተከሳሾችቀርበው እንዲከራከሩ ፍርድ ቤት በጋዜጣ ጥሪ ማቅረቡን ዋና ኢንስፔክተር አሻግሬ ጥላሁን ጨምረው ገልፀዋል። ተከሳሾቹ በቀረበላቸው ጥሪ መሠረት ቀርበው መከራከር ባለመቻላቸው የምስራቅ ባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታሕሣስ 19 ቀን 2014 ዓም በዋለው ችሎት በሌሉበት የሀያ ፣ሀያ አመት እስራት ወስኖባቸዋል፡፡ ከአራት አመት በፊትም ፍርድ ቤቱም ተከሣሾችን  ፖሊስ ተከታትሎ ለማረሚያ ቤቶች አስተዳደር እንዲያስረክብ ትፅዛዝ መስጠቱን ዋና ኢንስፔክተር አሻግሬ ጥላሁን ገልፀዋል።ፖሊስም በሁለቱ ተከሣሾች ላይ ከፍተኛ ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ ከአራት አመት በኃላ ተከሳሾቹ ሁሉ ነገር ተረስቷል የሚጠይቀን የለም በማለት ያላቸውን ንብረት ለመቆጣጠር ወደ ወንጀል የፈፀሙበት ስፍራ ሲመለሱ ፖሊስ በደረሠው መረጃ መሠረት ተከታትሎ ከአራት አመት በኃላ  ሁለቱንም በቁጥጥር ስር አውሎ የተሰጣቸውን ቅጣት እንዲፈፅሙ ወደ ጊኒር ማረሚያ ቤት አስተላልፏቸዋል። በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
27😢 14💔 9👍 4👏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
3
Фото недоступноПоказать в Telegram
የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ የገደለው ግለሰብ የሟች ቤተሰብን ይቅርታ ጠየቀ የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በመግደል ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀድሞ መሪውን ቤተሰብ ይቅርታ ጠይቋል።ቀደም ሲል በግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ነኝ ብሎ የተናገረው ያማጋሚ ለፍርድ ቤቱ በአቤ ሞት ለተጎዳችዉ የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት አኪ “በጣም አዝኛለሁ” ይቅርታ ብሏል። ያማጋሚ እ.ኤ.አ. ጁላይ 8 ቀን 2022 በምእራብ ናራ ከተማ በተደረገ የፖለቲካ ዘመቻ ዝግጅት ላይ አቤ ላይ ለመተኮስ በቤት ውስጥ የተሰራ ሽጉጥ ተጠቅሟል። በዚያው ቀን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በሆስፒታል ውስጥ እየረዱ ህይወታቸዉ አልፏል፡፡የአቤ ሞት በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሯል። በሕዝብ ዘንድ “አቤኖሚክስ” እየተባለ በሚጠራው የውጭ ፖሊሲ እና የኢኮኖሚ ስትራቴጂ ፖለቲከኛዉ ይታወቁ ነበር። "ቤተሰቡን ለሦስት ዓመታት ተኩል ለስቃይ ዳርጌያለሁ ለዚህ ጥፋቴ ምንም ምክንያት የለኝም" ሲል ያማጋሚ ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል ሲሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ያማጋሚ እናቴን እና ሰፊውን ቤተሰቤን አጥፍቷል ያለውን የአንድነት ቤተ ክርስቲያንን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ማገዛቸዉን በመወንጀል አቤ ላይ ጥቃት እንደፈፀመ ለመርማሪዎች ተናግሯል።የያማጋሚ ወንጀል በደቡብ ኮሪያ በጅምላ ሰርግ እንዲፈጸም በማድረግ በሚትታወቀው አንድነት ቤተክርስትያን ላይ ምርመራ እንዲካሄድ አስገድዷል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
14
Фото недоступноПоказать в Telegram
በሀዲድ ገበያ የደረሰው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል ዛሬ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 9:45 ሰአት ላይ ሀዲድ ገበያ  እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በንግድን መኖሪያ ቤቶች ላይ  ተከስቶ የነበረዉ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል ። የእሳት አደጋው የተከሰበት ቦታ ለአደጋ መቆጣጠር ስራ ምቹ ያልሆነ ፣ ቤቶቹ የተገነቡበት ግብዓቶች ፈጣን ተቀጣጣይ ከሆኑ ከቆርቆሮና ከእንጨት የተገነቡ በመሆኑ እሳቱ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በፍጥነት  መቆጣጠር ተችሏል። የእሳት  አደጋው መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ ሲሆን  አደጋው በሠው ላይ ያስከተለው ጉዳት የለም ። አሁን ያለንበት ሞቃታማና ነፈሻማ የአየር ንብረት ለእሳት መከሰትና መባባስ አስተዋጾኦ የሚያደርግ በመሆኑ ህብረተሰቡ እሳትና የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጮችን ሲጠቀም ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል ። #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
13
Фото недоступноПоказать в Telegram
🏡🌴ከቴምር ሪልስቴት ፒያሳ አድዋ 00 ፊት ለፊት ሱቅ ሽያጭ ግራውንድ ላይ 👉 20ካሬ 👉ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን 👉ሙሉ ክፍያ 7ሚሊዮን ብር 👉በ 18 ወር ውስጥ የሚረከቡት ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇👇 +251937341286 +251714558361 📲👇በ WhatsApp ማግኘት ከፈለጉ https://wa.me/251937341286 📲Channel: https://t.me/TemerRealEstateSalesAdvisor 📲Telegram : t.me/AbrhamTemerSales
Показать все...
8👍 1
የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ዓብይ ጉባኤ ለ117 ዳኞች ሹመት ለክልሉ ምክር ቤት ኡቀረበ 👉 የሁለት ዳኞች ያለመከሰስ ከለላ ተነስቷክ የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ዐቢይ ጉባኤ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔ መስጠቱ ተገልጿል። በዚህም 169 የወረዳ ፍርድ ቤት ረዳት ዳኞች እና 5 የአዲስ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች በድምሩ የ174 ዳኞች ሹመት ለክልሉ ምክር ቤት እንዲቀርብ መወሰኑ ተገልጿል፡፡ አራት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ሸሪዓ ዳኞች እና 25 የወረዳ ፍርድ ቤት ሸሪዓ ዳኞች ሹመት ሰጥቷል። እንዲሁም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሴ እና ጎንደር ምድብ ችሎት አስተባባሪዎች ከኃላፊነት እንዲነሱ ወስኗል። የአንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የተጠረጠሩበትን ሃሰተኛ ሰነድ እና የአንድ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ የተጠረጠሩበትን የአካል ጉዳት ማድረስ እና ዛቻ ወንጀል መነሻ በማድረግ ከተወያየ በኋላ ያለመከሰስ ከለላቸዉን ማንሳቱ ተገልጿል። እንዲሁም የፀባይ እና የስነስርዐት ጉዳዮችን መርምሮ ሁለት የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች ከኃላፊነት እንዲነሱና ውሳኔው በክልሉ ምክር ቤት እንዲጸድቅ የውሳኔ ሀሳብ መስጠቱ ተገልጿል፡፡ እንዲሁም በሌሎች የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ መክሮ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ሌሎች የቅሬታ ይግባኞችን መርምሮ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ተጨማሪ ማጣራት የሚያስፈልጋቸው የዲሲፒሊን ጉዳዮች በቀጣይ ጉባኤ ተጣርተው እንዲቀርቡ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ በተጨማሪም የቀረበለትን የዝውውር መረጃ መርምሮ ለኅብረተሰቡ የተሻለ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ሲባል በጥናት ላይ የተመሰረተ የመመሪያ ማሻሻያ ተደርጎ እስኪተገበር ድረስ መደበኛ ዝውውር ለጊዜዉ ታግዶ እንዲቆይ እና በሚወጣው መመሪያ መሰረት ውድድር ተደርጎ እንዲተገበር ሆኖም እንደአስፈላጊነቱ በልዩ ዝውውር የሚቀርቡ የዝውውር ጥያቄዎች እንዲስተናገዱ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ በሰመሀር አለባቸው #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
10👎 1🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቬንዙዌላ ከአሜሪካ የተባረሩ ስደተኞችን መቀበል ትቀጥላለች ሲሉ ማዱሮ ተናገሩ የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ሀገራቸው በጥር ወር በተደረሰው ስምምነት ከአሜሪካ በአየር የተባረሩ ስደተኞችን መቀበሏን ትቀጥላለች ብለዋል።የቬንዙዌላው መሪ 266 የቬንዙዌላውያን ስደተኞችን አሳፍሮ ከአሜሪካ የመጣ አይሮፕላን ማይኬቲያ ሲሞን ቦሊቫር አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሱን ተከትሎ ይህንኑ መናገራቸዉን ቴሌሱር ዜና ወኪል ዘግቧል። ባለፉት ሁለት ቀናት ወደ ቬንዙዌላ የተመለሱት ስደተኞች ቁጥር 525 ደርሷል።ማዱሮ በሚቀጥለው ቀን ሌላ በረራ እንደሚመጣ እና ሂደቱ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ቬንዙዌላ የሚመለሱ ስደተኞችን በዋሽንግተን ጥያቄ መሰረት እንደምትቀበል ገልጸው፣ በቅርብ ጊዜ መስተጓጎል እንደነበር ጠቁመዋል።ማዱሮ እቅዱን ከአሜሪካ አውሮፕላኖች ጋር ለመቀጠል ቀጥተኛ ጥያቄ እንደደረሳት እና እንዳጸደቁት ተናግረዋል። ቬንዙዌላ ረቡዕ እለት በአሜሪካ መንግስት ጥያቄ መሰረት ለስደተኞች የመመለሻ በረራዎችን እንደምትጀምር ተናግራለች።የዩናይትድ ስቴትስ እና የቬኔዙዌላ ግንኙነት በእጅጉ የሻከረ ቢሆንም በስደት ላይ ያለው ትብብር ቀጥሏል። ዩናይትድ ስቴትስ ባለፉት ወራት በላቲን አሜሪካ ወታደራዊ ዘመቻዎችን በማስፋፋት የጦር መርከቦችን፣ ተዋጊ ጄቶች እና ሌሎች ንብረቶችን ወደ ካሪቢያን አካባቢ አሰማርታለች። ትራምፕ በቅርቡ የቬንዙዌላ የአየር ክልል ሙሉ በሙሉ እንደሚዘጋ በማወጅ የቬንዙዌላ ባለስልጣናትን እና የወንጀል ኔትወርኮችን እንደ የውጭ አሸባሪ ድርጅቶች ፈርጃለች፡፡ ካራካስ የአሜሪካን ዛቻን ማጣጣሏ ይታወሳል፡፡ በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
18👍 4😁 3
በሸዋሮቢት እና አካባቢው 90 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ተደረገላቸው በሸዋሮቢት ከተማ እና በዙሪያው ለሚገኙ ከ90 በላይ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ተደርጎላቸው ለነበሩ የማህበረሰብ ክፍሎች የህክምናው ውጤታማነት የተረጋገጠበት የድህረ-ህክምና ክትትል አገልግሎት ተሰጥቷል። ከሳምንት በፊት የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ከደብረብርሃን ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ባከናወኑት ዘመቻ፣ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸውን ወገኖች በመለየት የቀዶ ህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ ይታወሳል።የቀዶ ህክምናው የተደረገላቸው ታካሚዎች በአሁኑ ሰዓት ያሉበትን የጤና ሁኔታ ለመገምገም ከደብረብርሃን ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የመጡ ከፍተኛ የአይን ህክምና ስፔሻሊስቶች በቦታው በመገኘት የክትትል አገልግሎት ሰጥተዋል። የህክምና ክትትል የተደረገላቸው ከ90 በላይ ታካሚዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እና የቀዶ ህክምናው ስኬታማ እንደነበር ባለሙያዎቹ ማረጋገጣቸውን ብስራት ከሸዋሮቢት ኮሙኒኬሽን ያገኘው መረጃ ያመላክታል።የክትትል ህክምናው የተደረገላቸው ታካሚዎች በሰጡት አስተያየት ከዚህ በፊት በአይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት ተጋርዶባቸው የነበረው ብርሃን በመመለሱ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። የህክምና ባለሙያዎቹ በበኩላቸው፤ በቀጣይም ከአራት ወራት በኋላ ተመሳሳይ የአይን ህክምና አገልግሎት በድጋሚ እንደሚሰጥ ቃል ገብተዋል። #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
15👍 12👌 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
የቀድሞው የሠላም ሚኒስትር ዴኤታ  አቶ ታዬ ደንደአ ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ የ7 ዓመት ከ2 ወር እስር ተፈረደባቸው። አቶ ታዬ ዛሬ አርብ ኅዳር 26/2018 ዓ.ም. የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት ጥፋተኛ በተባሉበት ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ነው። የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን እና የክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ታዬ ሕገ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት እንዲሁም ፍቃድ ሳይኖራቸው በቤታቸው ውስጥ አንድ ታጣፊ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ60 ጥይቶች ጋር ተገኝቷል በሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር። #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
💔 29👎 21👍 5 4
ሩሲያ እና ህንድ የንግድ ልዉዉጣቸዉን ወደ 100 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ ተስማሙ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት የንግድ እና የምዕራቡ ዓለም ማዕቀብን በተመለከተ በህንድ ዋና ከተማ የአንድ ቀን ስብሰባ በዛሬዉ እለት አካሂደዋል፡፡የዓርቡ ስብሰባ በ 2022 ሩሲያ ሙሉ ጦርነት በዩክሬን ላይ ከጀመረ በኋላ የፑቲን ህንድ የመጀመሪያ ጉብኝት ሲሆን ህንድ ከሩሲያ ነዳጅ ዘይት ግዢ ጋር በተያያዘ የዩናይትድ ስቴትስ የታሪፍ ቅጣት እፎይታን እየፈለገች ትገኛለች። "ህንድ ገለልተኛ አይደለችም፤ ህንድ አቋም አላት፤ እናም ይህ አቋም ለሰላም ነው" ሲሉ ሞዲ ከፑቲን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ተናግረዋል፡፡"ለሰላም የሚደረገውን ጥረት ሁሉ እንደግፋለን፣ እናም ለሰላም በሚደረግ ማንኛውም ተነሳሽነት ጎን እንቆማለን ሲሉ አክለዋል።ፑቲን በምላሹ ሞዲ ግጭቱን ለመፍታት ለሰጡት ትኩረት እና ጥረት አመስግነዋል።የፑቲን ይህ ጉብኝት የተደረገዉ የሩሲያ የጦር መሳሪያዎች ከፍተኛ ገዢ ከሆነችው ህንድ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሳደግ ተስፋ በማድረግ ነው፡፡ በ2030 ከህንድ ጋር ያለውን የንግድ ልውውጥ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ማሳደግ እንደሚፈልጉ ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል፡፡ በ2024 ዓመት የሀገራቱ የንግድ ግንኙነት ወደ 68 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ያለ ነበር። ፑቲን እ.ኤ.አ. በ 2023 ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ባካሄደችው ጦርነት የዩክሬን ህጻናትን በህገ-ወጥ መንገድ ማፈናቀላቸውን ተከትሎ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የአለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ማዘዣ ቢያወጣባቸዉም በህንድ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ህንድ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባል ሀገር አይደለችም፡፡ በስምምነቱም ሆነ በህጎቹ አትገዛም። ፑቲን ምንም አይነት የእስር ፍርሃት ሳይኖርባቸዉ ወደ ህንድ መጓዝ ችለዋል፡፡ በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
12
Фото недоступноПоказать в Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ 25 የትራፊክ ፍሰት ችግር ያለባቸዉ መንገዶች ፣አደባባዮች ፣ተርሚናሎች እና መጋጠሚያዎች ተለዩ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በከተማዋ የትራፊክ ፍሰት ችግር ባለባቸዉ 25 መንገዶች ፣አደባባዮች ፣ተርሚናሎች እና ማጋጠሚያዎች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል ።በከተማዋ በተለይም በስራ መግቢያና መዉጪያ ሰዓት የትራፊክ መጨናነቅ በሚታይባቸው ቦታዎች ላይ ፍሰትን መሠረት ያደረገ ስምሪት በመስጠት ጠንከር ያለ የማስተባበር ስራ እያከናወነ መሆኑን በባለስልጣን መስሪያቤቱ የትራፊክ ቁጥጥርና ኩነት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አያሌዉ ኢቲሳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። የትራፊክ ፍሰት ችግር አለባቸው ብለዉ ከተለዩ አከባቢዎች መካከል በለሚኩራ ክፍለከተማ በተለምዶ 72 ፣ሲኤምሲ መሪ ሳይት እና አያት መሪ ፣በአቃቂ ቃሊቲ ቶታል ማደያ እስከ አደባባይ እና ከማሰልጠኛ አቦ መብራት እንደሚገኙበት ተገልጿል ።በተጨማሪም በየካ ክፍለ ከተማ ከላምበረት እስከ ዲያስፖራ አደባባይ እና ከጉርድ ሾላ እስከ መገናኛ ተርሚናል ፣በኮልፌ ክፍለ ከተማ ከዘነበወርቅ እስከ ቶታል እና ከካራ እስከ አየር ጤና ፣በቦሌ ክፍለ ከተማ ከቦሌ ሚካኤል  እስከ ጊዮርጊስ መብራት ፣ከኤድናሞል አዉራሪስ ጉላጉል 22 እና በሌሎችም አከባቢዎች የትራፊክ ፍሰቱን የማስተካከል ስራ ተጠናክሮ ቀጥላል ተብሏል ። በቀጣይ በጥናት ላይ በመመስረት የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ፍሰት ማስተካከል የሚያስችሉ የምህንድስና ማሻሻያዎች ስራዎች ተግባራዊ እንደሚደረጉ ዳይሬክተሩ ለጣቢያችን ጨምረዉ ተናግረዋል ። በመባ ወርቅነህ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
16🙏 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ 25 የትራፊክ ፍሰት ችግር ያለባቸዉ መንገዶች ፣አደባባዮች ፣ተርሚናሎች እና መጋጠሚያዎች ተለዩ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በከተማዋ የትራፊክ ፍሰት ችግር ባለባቸዉ 25 መንገዶች ፣አደባባዮች ፣ተርሚናሎች እና ማጋጠሚያዎች ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል ።በከተማዋ በተለይም በስራ መግቢያና መዉጪያ ሰዓት የትራፊክ መጨናነቅ በሚታይባቸው ቦታዎች ላይ ፍሰትን መሠረት ያደረገ ስምሪት በመስጠት ጠንከር ያለ የማስተባበር ስራ እያከናወነ መሆኑን በባለስልጣን መስሪያቤቱ የትራፊክ ቁጥጥርና ኩነት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አያሌዉ ኢቲሳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። የትራፊክ ፍሰት ችግር አለባቸው ብለዉ ከተለዩ አከባቢዎች መካከል በለሚኩራ ክፍለከተማ በተለምዶ 72 ፣ሲኤምሲ መሪ ሳይት እና አያት መሪ ፣በአቃቂ ቃሊቲ ቶታል ማደያ እስከ አደባባይ እና ከማሰልጠኛ አቦ መብራት እንደሚገኙበት ተገልጿል ።በተጨማሪም በየካ ክፍለ ከተማ ከላምበረት እስከ ዲያስፖራ አደባባይ እና ከጉርድ ሾላ እስከ መገናኛ ተርሚናል ፣በኮልፌ ክፍለ ከተማ ከዘነበወርቅ እስከ ቶታል እና ከካራ እስከ አየር ጤና ፣በቦሌ ክፍለ ከተማ ከቦሌ ሚካኤል  እስከ ጊዮርጊስ መብራት ፣ከኤድናሞል አዉራሪስ ጉላጉል 22 እና በሌሎችም አከባቢዎች የትራፊክ ፍሰቱን የማስተካከል ስራ ተጠናክሮ ቀጥላል ተብሏል ። በቀጣይ በጥናት ላይ በመመስረት የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ፍሰት ማስተካከል የሚያስችሉ የምህንድስና ማሻሻያዎች ስራዎች ተግባራዊ እንደሚደረጉ ዳይሬክተሩ ለጣቢያችን ጨምረዉ ተናግረዋል ። በመባ ወርቅነህ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
እስራኤል በጋዛ የተኩስ አቁም ቢደረስም የ2026 የመከላከያ በጀት 34 ቢሊየን ዶላር መሆኑን አስታወቀች የእስራኤል የመከላከያ በጀት ለቀጣዩ አመት 112 ቢሊዮን ሼክል ወይም 34 ቢሊየን ዶላር ተብጅቷል ሲል የመከላከያ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ቀደም ሲል በወጣው ረቂቅ በጀት ከያዘው 90 ቢሊዮን ሼክል ወይም 27 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። የመከላከያ ሚኒስትሩ ኢዝራኤል ካትስ እና የገንዘብ ሚኒስትሩ ቤዛሌል ስሞትሪች በመከላከያ ወጪ ማዕቀፍ ላይ ተስማምተዋል፤ምክንያቱም ካቢኔው በሚቀጥለው ዓመት በጀት ላይ መወያየት የጀመረ ሲሆን ይህም እስከ መጋቢት ወር ድረስ መጽደቅ አለበት ወይም ወደ አዲስ ምርጫ እንዲደረግ ሊያስገድድ ይችላል ።ካትዝ ወታደሮቹ የተፋላሚዎቹን ፍላጎት ለመሸፈን እና በተጠባባቂ የሰራዊቱ ኃይል ላይ ያለውን ሸክም እንደሚቀንስ ተናግረዋል ። የስሞትሪች ቢሮ እንደገለጸው የ 2026 የመከላከያ በጀት በጦርነቱ ዋዜማ ከ 2023 ጋር ሲነፃፀር የ 47 ቢሊዮን ሼክል ወይም 14 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል ።በጋዛ ያለው የዘር ማጥፋት ጦርነት እና በሊባኖስ ሂዝቦላህ ላይ የሚፈጽመዉ ጥቃት እ.ኤ.አ. በ2024 እስራኤል ከያዘችዉ 31 ቢሊየን ዶላር ጨምሯል፡፡ በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
16😁 10👎 5
የተረጋጋ የገበያ ግብይት እንዲኖር ምግብና አላቂ የፅዳት መገልገያ ቁሳቁሶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ መሆኑን የኢትዮጲያ  የኢንዱስትሪ  ግብአቶች ልማት ፍቼ ቅርንጫፍ አስታወቀ በህብረተሠቡ ውስጥ ያለውን የምግብ እና አላቂ የፅዳት መገልገያ ቁሣቁሶችን የሕብረተሠቡን ተጠቃሚነትን እና ፍላጐት መሠረት ባደረገ መልኩ በተመጣጣኝ ዋጋ ለሕብረተሠቡ እያቀረበ እንዳለ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት ፍቼ ቅርንጫፍ አስታወቀ፡፡ የድርጅቱ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሐላፊ አቶ ጂብሪል ቲልሞ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት በአሁኑ ሰዓት በምግብ እና በአላቂ የፅዳት ቁሳቁሶች ላይ የተጠቃሚ ማሕበረሰብ መብዛት ጋር ተያይዞ ያለውን የገበያ እና የአቅርቦት ውስንነት ለመፍታት የገበያ ማረጋጋት  ስራ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በዚሁ መሠረት ዘይት ባለ አምስት ሊትር በውጭ ገብያ እስከ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ብር የሚሸጠውን በአንድ ሺህ ስድስት መቶ ሶስት ብር፣ ፖስታ በውጭ አስከ አንድ መቶ አስር ብር የሚሸጠውን በሰማንያ ስምንት ብር፣የውጭ ሀገር ሩዝ  በኪሎ አንድ መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር የሐገር ውስጥ ሩዝ በኪሎ በሐምሣ ስምንት ብር ከሐምሳ ሳንቲም፣ ሞከሪኖ በኪሎ መቶ አስራ ስድስት ብር እንዲሁም ዱቄት በኪሎ በአንድ መቶ አስር ብር በመሸጥ የገብያ ማረጋጋት ስራ እየተሠራ እንዳለ ገልፀዋል። የፅዳት አላቂ እቃዋች እንደየ አካባቢው ሕብረተሠብ በተመጣጣኝ ዋጋ በመሸጥ ማሕበረሠቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ሲሆን የፍቼ ከተማ ነዋሪዎች አራት አራት ሆኖ በመደራጀት እየገዛ መሆኑን ገልፀዋል። የአካባቢው የመንግስት ሠራተኛው  ሆነ የተለያዩ ድርጅት ሠራተኞች, የሆቴል ቤት ድርጅቶች,፣ ሕበራት እና ዩኒየኖች በሕጋዊ መንገድ ሕጋዊ የድጋፍ ደብዳቤ በማምጣት ምርቶችን እየገዙ መሆኑን አቶ ጅብሪል ጠቅሰው በቀን ከአንድ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተጠቃሚዎች ምርቶችን ማከፋፈል መቻሉን ገልፀዋል። በሰመሀር አለባቸው #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
22😁 21👎 5
6