ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
Открыть в Telegram
The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man
Больше2025 год в цифрах

44 133
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
-22730 день
Архив постов
የኢንዶኔዢያ ዋና ከተማ ጃካርታ ቶኪዮን በመብለጥ ከፍተኛ ህዝብ የሚኖርባት የዓለማችን ትልቁ ከተማ ተባለች
አዲስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት እንዳመለከተው የኢንዶኔዥያ ዋና ከተማ ጃካርታ 41.9 ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩባት በዓለም ትልቋ ከተማ ስትሆን የባንግላዲሿ ዳካ ደግሞ 36.6 ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩባት ሁለተኛዋ ግዙፍ ከተማ ሆናለች፡፡ በ2000 የታተመው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ለዓመታት በአለም ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የሚኖርባት ከተማ የነበረችዉ ቶኪዮ ወደ ሶስተኛ ደረጃ ወርዳለች፡፡የጃፓን ዋና ከተማ በአንጻራዊ ሁኔታ የተረጋጋ 33.4 ሚሊዮን ህዝብ ብዛት ያላት ከተማ ስትባል የባንግላዲሽ ዋና ከተማ ዳካ ከዘጠነኛ ደረጃ ወደ ሁለተኛ ደረጃ መጥታለች፡፡
አሁን ባለዉ እድገት የዳካ ህዝብ ብዛት ከቀጠለ በ2050 ጃካርታን በመብለጥ የዓለማችን ከፍተኛ ህዝብ የሚኖርባት ከተማ እንደምትሆን ይገመታል ።የዓለም የከተሞች ተስፋ የ2025 የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳይ ዲፓርትመንት ሪፖርት እንዳመለከተው ከ10 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ያሉባቸው የከተማ አካባቢዎችደ ብዛት ወደ 33 ከፍ ብሏል፡፡ በ1975 በዓለም ዙሪያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የሚኖሩባቸዉ ከተሞች ስምንት ብቻ የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ በአራት እጥፍ ጨምሯል።
ከዓለም 33 ሜጋ ከተማ 19 ያህሉ እና በደረጃ ከ10ሩ ዘጠኙ በእስያ ውስጥ ይገኛሉ ። ከጃካርታ ፣ ዳካ እና ቶኪዮ በተጨማሪ 10 ከፍተኛ ህዝብ የሚኖርባቸዉ የእስያ ከተሞች መካከል የህንድ ዋና ከተማ ኒው ዴሊና ኮልካታ ፣ የቻይናዎቹ ሻንጋይና ጓንግዙ ፣ የፊሊፒንስ መዲና ማኒላ እንዲሁም የደቡብ ኮሪያ መዲና ሴኦል ይጠቀሳሉ፡፡32 ሚሊዮን ህዝብ ያላት የግብፅ መዲና ካይሮ ከ 10 ከእስያ ውጪ ከፍተኛ ህዝብ የሚኖርባት ከተማ ነችሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያሳያል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 19🤔 4👍 2
የገዛ መንታ ልጆቹን ከ7 ዓመታቸው ጀምሮ የመድፈር ጥቃት የፈፀመባቸው አባት በእስራት ተቀጣ
በአሰላ ከተማ አስተዳደር ቡርቂቱ ቀበሌ ውስጥ የአስራ ሁለት ዓመት መንታ ልጆች ላይ በ2013 ፣ በ2015 እና በ2017 ዓ.ም የመድፈር ጥቃት የፈፀመው አባት ላይ የእስራት ውሳኔ መተላለፉን የአርሲ ዞን አቃቢ ህግ እና የኮሙኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ደረጀ ወርቁ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል::ተከሣሽ አቡ ናፎ ቢፍቱ የተባለው ግለሠብ የአስራ ሁለት ዓመት መንታ ልጆቹን እናታቸው በሌለችበት የመድፈር ጥቃት በመፈፀሙ በእስራት እንዲቀጣ የተወሠነበት መሆኑ ተገልፅዋል።
ተከሳሹ አባት እጅግ ነውረኛና የማህበረሰቡን ወግና ልማድ በተፃረረ መልኩ በእድሜ አነስተኛ ና ራሣቸውን መከላከል በማይችሉ የአስራ ሁለት አመት ልጆቹ ላይ ወላጅ እናት በሌለችበት የወላጅነት ሐላፊነቱን ወደጎን በመተው የመድፈር ጥቃት መፈፀሙ በሕክምና ማስረጃ ሙሉ በሙሉ በመረጋገጡ በፖሊስ የምርመራ መዝገቡ ሲጣራ ቆይቷል፡:አቃቢ ሕግ ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ሕግ ቁጥር 627 በሕፃናት ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረ ስጋ በደል እና በወንጀል ሕግ ቁጥር 654 በዘመዳሞች መካከል የሚፈፀም የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል በመጥቀስ ክስ መስርቷል፡፡
በአቃቢ ሕግ የተመሠረተውን ክስ ሲከታተል የቆየው የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሕዳር 16 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት ተከሣሽ አቡ ናፎ ቢፍቱ የተባለው ተከሣሽ የፈፀመው የወንጀል ድርጊት ከአንድ ወላጅ አባት የማይጠበቅ ነውረኛ እና አፀያፊ ተግባር ከመሆኑ ባሻገር በዘመዳሞች መካከል በመልካም ፀባይ ተቃራኒ በሆነ መልኩ የፈፀመው የብልግና ድርጊት በልጆቹ ላይ ከፈጠረውከባድ ሐዘን፣ጭንቀት ና ሕፍረት ጋር ተዳምሮ የፈፀመው ተግባር በመንታ ልጆቹ ላይ ያስከተለውን የአእምሮ ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት በሀያ አንድ አመት እስራት እንዲቀጣ የተወሠነበት መሆኑ የአርሲ ዞን አቃቢ ህግ እና የኮሙኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ደረጀ ወርቁ ለብስራት ሬዲዮ ጨምረው ተናግረዋል::
በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል
🤬 63❤ 19👎 8😭 7👍 1💔 1
የገዛ መንታ ልጆቹን ከ7 ዓመታቸው ጀምሮ የመድፈር ጥቃት የፈፀመባቸው አባት በእስራት ተቀጣ
በአሰላ ከተማ አስተዳደር ቡርቂቱ ቀበሌ ውስጥ የአስራ ሁለት ዓመት መንታ ልጆች ላይ በ2013 ፣ በ2015 እና በ2017 ዓ.ም የመድፈር ጥቃት የፈፀመው አባት ላይ የእስራት ውሳኔ መተላለፉን የአርሲ ዞን አቃቢ ህግ እና የኮሙኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ደረጀ ወርቁ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል::ተከሣሽ አቡ ናፎ ቢፍቱ የተባለው ግለሠብ የአስራ ሁለት ዓመት መንታ ልጆቹን እናታቸው በሌለችበት የመድፈር ጥቃት በመፈፀሙ በእስራት እንዲቀጣ የተወሠነበት መሆኑ ተገልፅዋል።
ተከሳሹ አባት እጅግ ነውረኛና የማህበረሰቡን ወግና ልማድ በተፃረረ መልኩ በእድሜ አነስተኛ ና ራሣቸውን መከላከል በማይችሉ የአስራ ሁለት አመት ልጆቹ ላይ ወላጅ እናት በሌለችበት የወላጅነት ሐላፊነቱን ወደጎን በመተው የመድፈር ጥቃት መፈፀሙ በሕክምና ማስረጃ ሙሉ በሙሉ በመረጋገጡ በፖሊስ የምርመራ መዝገቡ ሲጣራ ቆይቷል፡:አቃቢ ሕግ ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ሕግ ቁጥር 627 በሕፃናት ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረ ስጋ በደል እና በወንጀል ሕግ ቁጥር 654 በዘመዳሞች መካከል የሚፈፀም የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል በመጥቀስ ክስ መስርቷል፡፡
በአቃቢ ሕግ የተመሠረተውን ክስ ሲከታተል የቆየው የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሕዳር 16 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት ተከሣሽ አቡ ናፎ ቢፍቱ የተባለው ተከሣሽ የፈፀመው የወንጀል ድርጊት ከአንድ ወላጅ አባት የማይጠበቅ ነውረኛ እና አፀያፊ ተግባር ከመሆኑ ባሻገር በዘመዳሞች መካከል በመልካም ፀባይ ተቃራኒ በሆነ መልኩ የፈፀመው የብልግና ድርጊት በልጆቹ ላይ ከፈጠረውከባድ ሐዘን፣ጭንቀት ና ሕፍረት ጋር ተዳምሮ የፈፀመው ተግባር በመንታ ልጆቹ ላይ ያስከተለውን የአእምሮ ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት በሀያ አንድ አመት እስራት እንዲቀጣ የተወሠነበት መሆኑ የአርሲ ዞን አቃቢ ህግ እና የኮሙኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ደረጀ ወርቁ ለብስራት ሬዲዮ ጨምረው ተናግረዋል::
በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል
Фото недоступноПоказать в Telegram
አሜሪካ በጣም ታዋቂ የሆኑትን ብሄራዊ ፓርኮቿን ለመጎብኘት ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎችን 100 ዶላር ማስከፈል ልትጀምር ነዉ
ዩናይትድ ስቴትስ በአሜሪካ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎችን 100 የአሜሪካን ዶላር የሚያስከፍል አዲስ የ"አሜሪካ-ትቅደም" የመግቢያ ክፍያ ፖሊሲ በመተግበር ላይ ነች።ይህዉ መረጃ ይፋ የሆነው የብሔራዊ ፓርክ ስርዓትን በሚቆጣጠረው የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲሆን በ2026 የክፍያ እቅድ አካል ነው። በአሜሪካ ነዋሪ ላልሆኑ ሰዎችን ዓመታዊ የፓርኮች መግቢያ ዋጋ ከ80 ወደ 250 ዶላር ይጨምራል ብሏል።
የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ዳግ ቡርጉም በሰጡት መግለጫ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከክፍያ ጭማሪ ጋር “የአሜሪካን ዜጎችን ለማስቀደም” ዓላማ አድርገዋል ብለዋ። "እነዚህ ፖሊሲዎች የብሔራዊ ፓርክ ስርዓትን የሚደግፉ የአሜሪካ ግብር ከፋዮች በተመጣጣኝ ዋጋ መጠቀማቸውን ሲቀጥሉ አለም አቀፍ ጎብኚዎች ፓርኮቻችንን ለመጠበቅ እና ለመጪው ትውልድ ለማሻሻል የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንደሚያበረክቱ ያረጋግጣሉ" ሲሉ ቡርጉም አክለዋል፡፡
በክፍያ ጭማሪው ከሚጎዱ ፓርኮች መካከል በቴነሲ እና በሰሜን ካሮላይና የሚገኘው የታላቁ ስሞኪ ተራራ ብሄራዊ ፓርክ፣ በዩታ የሚገኘው የጽዮን ብሔራዊ ፓርክ እና በአሪዞና የሚገኘው ግራንድ ካንየን ብሄራዊ ፓርክ ይገኙበታል።እ.ኤ.አ. በ2024 በብዛት የሚጎበኘው የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ ፓርክ የሆነው ታላቁ ስሞኪ ተራራ፣ ቀደም ሲል ለሁሉም ጎብኝዎች በነፃ መግቢያ ጥሪ አቅርቧል፣ መግቢያዉ ነጻ ቢሆንም በቀን 5 ዶላር፣ በሳምንት 15 ዶላር፣ ወይም ለፓርኪንግ በዓመት 40 ዶላር ያስከፍል ነበር።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 17😁 9👏 1
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዕድሜያቸዉ ከ10 እስከ 24 ዓመት ለሆኑ ሴቶች የቤተሰብ ዕቅድ ተጠቃሚነት 27 በመቶ ብቻ ነዉ ተባለ
👉 የልጅነት እርግዝናን ማስቆም አልተቻለም
የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ጤና ቢሮ አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የጤና ተቋማትን ለአፍላ ወጣቶች ምቹ ማድረግ እንዲሁም ወጣቶች በሚበዙባቸዉ በተለይም ከትምህርት ቤቶች ጋራ በመስራት እና ለጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ዋና ተግባር መሆኑን አስታውቋል።
ባለፋት 3 ወራት የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት የአፍላ ወጣቶችና ወጣት ሴቶች ተጠቃሚነትን 50 በመቶ ለማድረስ ፣ፍትሃዊነትንና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መሠራቱ ተጠቁሟል ።
የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ካገኙ ከ400ሺህ ተጠቃሚዎች መካከል 27 በመቶ የሚሆኑት ከ10 እስከ 24 የዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ሴቶች መሆናቸዉን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የቤተሰብ ዕቅድ ፣የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች የጤና ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አብረሀም ወንድሙ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
72 በመቶ የሚሆኑ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከ25 እስከ 49 የዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ሴቶች መሆናቸዉን የገለፁት አስተባባሪው ከ10 እስከ 24 የዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ አፍላ ወጣቶችና ወጣት ሴቶች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚነት ዝቅተኛ ነዉ ብለዋል ።ብስራት ሬዲዮ ከዚህ ቀደም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልጅነት እርግዝናን ማስቆም አልተቻለም መባሉን መዘገባችን የሚታወስ ነዉ ።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 17
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሩሲያ የናይጄሪያን የፀረ-ሽብርተኝነት ጥረቶችን ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች
ሩሲያ ናይጄሪያ በሽብርተኝነት ላይ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የተናገሩ ሲሆን አቡጃ ፅንፈኛ ቡድኖችን ለመከላከል የምታደርገዉን “ከባድ ጥረት” አወድሰዋል።ዛካሮቫ የሞስኮ አቋም "ያልተለወጠ ነው" በማለት ሽብርተኝነት ዓለም አቀፋዊ ስጋት መሆኑን በመጥቀስ ሩሲያ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች እና የአፍሪካ ህብረት ጋር በማስተባበር እርዳታ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
"ሩሲያ ለናይጄሪያ አጋሮች አስፈላጊውን እርዳታ መስጠቷን ለመቀጠል ተዘጋጅታለች" ስትል ዛካሮቫ አክላለች፡፡የናይጄሪያ የጦር ሃይሎች እና የህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች "የሽብር ስጋቶችን በብቃት በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ልምድ እንዳካበቱ ተናግራለች።"ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ ሰላማዊ ዜጎች ከመንግስት እና ከደህንነት አባላት ጋር በጥቃቱ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጻለች።
እ.ኤ.አ. ከ2002 ጀምሮ በቦርኖ ግዛት ሲንቀሳቀስ የቆየው ቦኮ ሃራምን ጨምሮ ታጣቂ ቡድኖች በናይጄሪያ የማያቋርጥ ጥቃት እየፈጸሙ ይገኛል፡፡ በ 2015 የናይጄሪያ ጦር ከፍተኛ ኪሳራ ቢያደርስበትም አሁንም ንቁ ሆኖ ቆይቷል ።በትምህርት ቤቶች ላይ የቀጠሉ ጥቃቶች ባለሥልጣናቱ በተለያዩ ግዛቶች የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን እንዲዘጉ አስገድዷቸዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኒዩ በጸጥታ ስጋት ምክንያት ለቡድን 20 ስብሰባ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ እንዲሰርዙ ተገደዋል፡፡
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 15
Фото недоступноПоказать в Telegram
በማርበርግ ቫይረስ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ
👉 የሟቾች ቁጥር 6 ደርሷል
ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በሽታው የመያዝ እድላቸውን ለመቀነስ የሚያግዝ Remsedevir የተባለ የፀረ ህዋስ መድኃኒት ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የመጀመሪያው የበሽታው ታማሚ ከተገኘበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 17 ድረስ በበሽታው ለተጠረጠሩ ለ73 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ መደረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። 11 በሚሆኑ ግለሰቦች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘ መረጋገጡን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል። እነዚህ ታማሚዎች አስፈላጊው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ቢሆንም የ6ቱ ህይወት ያለፈ ሲሆን የተቀሩት 5ቱ ደግሞ በህክምና ጣቢያ ወስጥ ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡
የበሽታው ምልክቶች ከታየባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 119ኙ የክትትል ጊዜያቸውን ጨርሰው ከለይቶ ማቆያ እንዲወጡ ተደርጓል።
ከዚህ በተጨማሪም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ከነበራቸው የማህበረሰብ አካላት ጋር በበሽታው የመያዝ እድላቸውን ለመቀነስ የሚያግዝ Remsedevir የተባለ የፀረ ህዋስ መድኃኒት ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት እስካሁን 16 ለሚሆኑ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ተብለው ለታሰቡ የህክምና ባለሙያዎችን እና ለታማሚዎች ለማድረስ ስለመቻሉ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 11🙏 4👍 2
ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመደቡ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት ኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሀገር ሆና መመረጧ ይታወሳል፡፡
ይህን ተክትሎም የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዚዳንት አድርጎ መመደቡን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
በዚህ መሰረትም ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከሀገር ውስጥ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተባበሩት መንግሥታት አካላት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር የኮፕ 32 ዝግጅትን የሚመሩ ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ኮንቬንሽን አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ የማዘጋጀት ኃላፊነት በመስጠታቸው ምስጋና አቅርቧል፡፡
በቀጣይም በጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) አስተባባሪነት ከዓለም የአየር ንብረት ጥበቃ ማኅበረሰብ ጋር በቅርበት ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል፡፡
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 21👎 2
ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመደቡ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት ኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሀገር ሆና መመረጧ ይታወሳል፡፡
ይህን ተክትሎም የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዚዳንት አድርጎ መመደቡን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
በዚህ መሰረትም ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከሀገር ውስጥ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተባበሩት መንግሥታት አካላት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር የኮፕ 32 ዝግጅትን የሚመሩ ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ኮንቬንሽን አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ የማዘጋጀት ኃላፊነት በመስጠታቸው ምስጋና አቅርቧል፡፡
በቀጣይም በጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) አስተባባሪነት ከዓለም የአየር ንብረት ጥበቃ ማኅበረሰብ ጋር በቅርበት ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 2
ሀሰተኛ የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን ይዘው ሲቀሳቀሱ የነበሩ 4 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ዋሉ
ተጠርጣሪዎቹ በርዋ ከበደ፣ ሙላት አባይ፣ ሳሙኤል ሙሉጌታ እና ጃኮ ፔንዞ የተባሉ ሲሆን የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ጥቅምት 30 ቀን 2018ዓ/ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ6 ልዩ ቦታው ልዩ ሆቴል አካባቢ ነው።
ሙላት አባይ የተባለው ተጠርጣሪ የተበደረውን ገንዘብ ልመልስልህ በማለት ሀሰተኛ መቶ ዶላር ለጓደኛው እንደሰጠው የገለፀው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግለሰቡም ከጓደኛው የተቀበለውን ዶላር ወደ ባንክ በመሄድ ለመመዘር ሲሞክር ሀሰተኛ መሆኑ ስለተረጋገጠ ለፖሊስ ጥቆማ ሠጥቷል።
ፖሊስም ጥቆማውን መነሻ በማድረግ በወንጀሉ አንደኛውን ተጠርጣሪ ከነአባሪው በመያዝ በተደረገ የአካል ፍተሻም 1ሺህ ሀሰተኛ ዩሮ ሊገኝበትም ችሏል።
ፖሊስ ባደረገው ምርመራ የማስፋት ተግባር ሳሙኤል ሙሉጌታ የተባለው ተጠርጣሪ እንደሰጣቸው ለፖሊስ መረጃ በመስጠታቸው የተጠቀሰው ግለሰብ በቁጥጥር ስር በሚውልበት ጊዜም 1400 ሀሰተኛ ዶላር እንደተገኘበትም የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል።
ምርመራው የማስፋት ስራውን ያላቆመው ፖሊስ 3ተኛ ተጠርጣሪ ሀሰተኛ ዶላሩን ከየት እንዳመጣው ሲጠየቅ የውጭ ሀገር ዜጋ ወደሆነው አራተኛ ተጠርጣሪ ጃኮ ፔንዞ መምራቱን ያስታወሰው ፖሊስ መምሪያው የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው አራተኛው ተጠርጣሪም 5600 ሀሰተኛ ዶላር መገናኛ አካባቢ ይዞ ሲቀሳቀስ በቁጥጥር ስር ሲውል በአጠቃላይ ከ8ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ገንዘቦች መያዛቸውን ፖሊስ ገልጿል።
ህብረተሰቡ ሐሰተኛ የውጭ ሀገርም ሆነ የሀገር ውስጥ የገንዘብ ኖቶችን ስርጭት ለመከላከል የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በመሆን መከላከል ይኖርበታል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
ምንጭ:- አአ ፖሊስ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 12👏 5
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማህፀን መንሸራተት አሳሳቢ የጤና ችግር መሆኑ ተጠቆመ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በእናቶች ዘንድ እየታየ ያለው የማህፀን መንሸራተት ትኩረት የሚሻ የጤና ችግር መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።ይህን ችግር ለመፍታት በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የማህጸን መንሸራተት ነጻ የህክምና አገልግሎት በዘመቻ መልክ እየተሰጠ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል ።
በቢሮው የእናቶች እና ህጻናት ጤና ባለሙያ ወ/ሮ ወርቅነሽ አሰጌ በዘመቻ መርሃ ግብሩ የማህጸን መውጣት በአንዳንድ እናቶች ላይ የሚታይ የጤና ችግር ነው ማለታቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል ። በሽታውን ለማከም ከፍተኛ የሙያተኛ አቅም እና ግብዓቶችን የሚጠይቅ እንደሆነ የጠቁሙት ባለሙያዋ ቢሮው ከጎንደር ዩኒቨርሲቲና ከዊንግስ ኦፍ ሂሊንግ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ዘመቻውን እያካሄደ ነዉ።
በመጀመሪያ ዙር የዘመቻ ቀናት ከ60 በላይ እናቶችን በሆስፒታሉ ማከም ተችሏልል።ከአከባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ችግሩ አሳሳቢ ነው ያሉት ወ/ሮ ወርቅነሽ በቀጣይ በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገው እንቅስቃሴ ውጤታማ እንዲሆን ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል። በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህጸንና ጽንስ ህክምና ስፔሻለስት ዶ/ር አለሙ ተሻለም የማህጸን መውጣት በስፋት በወሊድ ወቅት በእናቶች ላይ የሚከሰት መሆኑን አብራርተዋል።
ከፍተኛ ህመምን የሚያስከትል መሆኑን ጠቅሰው ከግንዛቤ እጦት የተነሳ ለረጅም ጊዜ ብዙዎቹ እናቶች በህመሙ እንደሚሰቃዩ ገልጸዋል፡፡የክልሉ ጤና ቢሮው ያቀረበላቸውን ጥሪ ተከትሎ በመርሀ ግብሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እናቶችን በጥንቃቄ በማከም ጤንነታቸውን መመለስ ተችሏል፡፡ የተለያዩ የስራ ጫናዎች የማህጸን መንሸራተትን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን ዉሃ ሽንት እና ሰገራን ያለመቆጣጠር፣ በዳሌ እና በወገብ አከባቢ ከፍተኛ የህመም ስሜት መኖር ከበሽታው ምልክቶች መካከል ይጠቀሳሉ ።
በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 13🙏 11
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በዓመት 3ሺህ ቶን በላይ የማር ምርት ለገብያ ቀርቧል
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በዓመት 3ሺህ2መቶ 79 ቶን የማር ምርት ለገበያ ማቅረብ መቻሉን የዞኑ ግብርና ልማት ፅ/ቤት አስታውቋል።በፅ/ቤቱ የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ቡድን መሪ አቶ ግዛቸው ነጋሹ ለብስራት ሬዲዮ እንደ ገለጹት በሰሜን ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች በዓመት ሁለት ጊዜ የማር ምርት እንደሚሰባሰብ ነግረውናል። በዘንድሮ የምርት ዘመን በባህላዊ መንገድ 3 መቶ 25 ሺህ 9 መቶ አራት ኪሎ ፣ በዘመናዊ ዘዴ ደግሞ 44 ሺህ 9መቶ አርባ ስምንት ኪሎ የማር ምርት ተሰብስቧል።
በአካባቢው ሶስት አይነት የማር ምርት እንደሚሰበሰብ የገለጹት የቡድኑ መሪ ከአደይ አበባ እንዲሁም ከጦስኝ እና ኩሳዬ የሚመረተው ቢጫ ማር፣ ከግራዋ ዛፍ የሚመረተው ጥቁር ማር፣ ከዋንዛ እና የተለያዩ ዛፎች የሚመረት ነጭ ማር ከጥቅምት አስራ አምስት እስከ ህዳር ሰላሳ ድረስ ተቆርጦ ለገብያ እና ለተጠቃሚው ማህበሰብ ይቀርባል።ሁለተኛው የማር ምርት በተለይ ጥቁር ማር ከግንቦት እስከ ሰኔ ወር አጋማሽ እንደሚቆረጥና ለገበያ እንደሚቀርብ የተናገሩት አቶ ግዛቸው ነጋሹ ይህ የማር ምርት ለመድሃኒት የሚፈለግ በመሆኑ በገብያ ላይ ተቀባይነቱ የጎላ ነዉ።
በማር ምርት ላይ የተሰማሩ ዘጠና የህብረት ስራ ማህበራት ፣ አምስት የማይክሮ ማህበራት እና ለ ሶስት መቶ አርባ ስድስት በባሕላዊ ቀፎ ማር በማምረት ላይ ላሉ አምራቾች እንዲሁም በፖኬጅ የተደራጁ ስድስት ሺህ አስራ ሁለት አርሶ አደሮች አንድ ሺህ ዘመናዊ የማር ቀፎ፣የማር ማጣርያና የማር እንጀራ መጋገርያ በመከፋፈሉ በዘንድሮ የምርት ዘመን ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሠባ ዘጠኝ የተጣራ የማር ምርት አዲስ አበባ እና አዳማ ለሚገኙ የማር ምርት ተቀባይ ነጋዴዎች ማስረከብ ተችሏል።
በባህላዉ ቀፎ የሚመረት የማር ምርት በአንድ ቀፎ አስር ኪሎ ሲሆን በዘመናዊ ቀፎ ደግሞ ሰላሳ ኪሎ ድረስ ስለሚመረት በርካታ የሽግግር ስራ ከባህላ ወደ ዘመናዊ ቀፎ መከናወኑንም ገልፀዋል።በማር ምርት ላይ የሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎች እና ሕገወጥ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር ከኢትዮዽያ የምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በማቀናጀት የሚሰራ ስራ ቢኖርም አሁንም የማር ምርትን ከሌሎች የባዕድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል ለሽያጭ ማቅረብ የሚስተዋል ስለሆነ ሕብረተሰቡ ህገወጦችን ተከታትሎ ለህግ አካላት እንዲያቀርብ አቶ ግዛቸው ነጋሽ ጨምረው ገልፀዋል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 15👎 5👍 3🤔 1
አብሮት የሚጠብቀውን ጓደኛውን በመግደል ከሚሰራበት ባንክ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የዘረፈ ወንጀለኛ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ።
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 6 ቀን 2015 ዓ/ም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ልደታ ኮንዶሚኒየም አቢሲንያ ባንክ ባልቻ ቅርንጫፍ ውስጥ ነው።
ወንጀል ፈፃሚው ጌታሁን ሙላት አብሮት የሚሰራውን ጓደኛውን ሟች ዘገዬ ቸሩን በተኛበት ጭንቅላቱ እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሉን በፌሮ ብረት በመምታት በመግደል የባንኩን የብር ካዝና በብረት ፈልቅቆ 2ሚሊየን 460ሺ ብር ዘርፎ ይሰውራል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የምርመራና ክትትል አባላትና አመራሩ ወንጀሉ ከተፈፀመ ዕለት ጀምሮ በርካታ ፖሊሳዊ ቴክኒኮችን በመጠቀም ባሰባሰበው መረጃ ወንጀል ፈፃሚውን በቁጥጥር በማዋል በተደረገበት ምርመራ ግለሰቡ ሁለት ተመሳሳይ ወንጀሎችን መፈፀሙን እና አማረ ደሳለኝ በሚል ሃሰተኛ ስም እና በሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የጥበቃ አገልግሎት በሚሰጥ ተቋም በጥበቃ ሰራተኛነት መቀጠሩን አረጋግጧል፡፡
ግለሰቡ በሥራ ባልደረባው ላይ የግድያ ወንጀል ፈፅሞ ለመሰወር ቢሞክርም በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ወንጀሉን እንዴት እንደፈጸመው መርቶ አሳይቷል፡፡
ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ከባድ ውንብድና 2ተኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ ጌታሁን ሙላት ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጡ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት የሚቀጥሯቸውን ሰራተኞች ማንንነት፣ የተያዦቻቸው ህጋዊነትና የሚያቀርቡትን ሰነድ ትክክለኛነት የማረገጋጥ ግዴታ እንዳለባቸውና ይህንን ግዴታቸውን ካልተወጡ ለሚያጋጥም ማንኛውም አይነት ችግር ፈቃዳቸው መሰረዝን ጨምሮ በህግ እንደሚጠየቁ ፖሊስ አሳስቧል።
ምንጭ:- አአ ፖሊስ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 25😢 14👏 6🤔 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኢትዮጵያ የተቀቀለ የበግና የፍየል ስጋን ወደ ቻይና ልትልክ ነው
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያሏትን ውስን የስጋ ምርት ተቀባይ ሀገራትን ቁጥር ለመጨመር እና ከዘርፋ ያላትን ተጠቃሚነት ለማሳደግ አቅዳ እየሰራች ትገኛለች ሲል የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዮት አስታውቋል።በኢንስቲትዮቱ የማህበራዊ ኢኮኖሚክስና እሴት ሰንሰለት አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ሳህሉ ሙሉ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በአብዛኛዉ የስጋ ምርቷን ጥቂተ በሆኑ የገልፍ ሀገራት ላይ ለሽያጭ ታቀርባለች።
ይህም ሊሆን የቻለዉ የእነዚህን ሀገራት የምርት ጥራትና ደህንነት መስፈርትን ብቻ በማሟላቷ እንደሆነ ተናግረዉ ችግሩን ለመፍታት ሌሎች ሰፋፊ የገበያ መዳረሻዎችን ለማፈላለግ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።በአሁኑ ወቅት ይህን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ሲሉ የተናገሩት ዶክተር ሳህሉ በተለይም እንደ ቻይና ወደሚገኙ የሩቅ ምስራቅ ሀገራት ምርቱን ለመላክ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ከአምናና ካቻምና ጀምሮ የተቀቀለ ስጋን ወደ ቻይና ለመላክ የሚያስችሉ አካሄዶችን በመከተል የተለያዪ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የገለፁት ዶክተር ሳህሉ ይህ ሂደት ከጫፍ መድረሱን አብራርተዋል። በያዝነው ሳምንት የመጨረሻው የፕሮቶኮል ፊርማ ወይንም ስምምነት ከተደረገ በኋላ ምርቶቹን ወደ ቻይና ገበያ መላክ እንደሚቻል ተገልጿል።የተቀቀለ የበግና ፍየል ስጋ ለጊዜው ወደ ቻይና ለመላክ የተፈቀደ ሲሆን አምራቾችንና ላኪዎችን የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡በዘርፋ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች በማቀነባበር ሂደት ውስጥ አስፈላጊውን ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ኢንስቲትዮቱ አስታውቋል።
በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
👎 26❤ 15😁 10👍 3😭 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
በሚዛን አማን ከተማ የወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ 102 ሴቶችን በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ ለማሰማራት እየተሰራ ነዉ ተባለ
በሚዛን አማን ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣዉን በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶችን ቁጥር ለመቀነስ የከተማዉ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት 102 በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶችን በመለየት በተለያዩ የስራ መስኮች ለማሰማራት እየሰራ መሆኑን ገልጿል ።
የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግስት ለማ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት በከተማዉ በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ 102 ሴቶችን በመለየት ወደ 40 የሚጠጉ ሴቶችን የስራ ፍላጎት የመለየት ስራ ተሠርቷል ።
ለዚህም የሚያስፈልገዉ በጀት ከፍተኛ ሲሆን ይህም በመንግስት ፣በማህበረሰብ እና በጎ ፍቃደኛ ባለሀብቶች ትብብር የሚሸፈን ነዉ ያሉት ኃላፊዋ 25 ሴቶች ተለይተዉ በሻይ ቡና ስራ ላይ እንዲሰማሩ አንድ ባለሀብት የገንዘብና የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ እንዲያደርግ እየተመቻቸ መሆኑ ተገልጿል ።
በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ አብዛኞቹ ሴቶች ከ25 እስከ 30 የዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ሲሆን በኢኮኖሚ ችግር እና ቤተሰቦቻቸውን በሞት በማጣታቸዉ ምክንያት ወደ ስራዉ መግባታቸዉን ወይዘሮ ትግስት ለጣቢያችን ተናግረዋል ።
ሴቶቹ በጎዳና ላይ በመቆምና በሆቴሎች ዉስጥ ይህን ስራ የሚሰሩ ሲሆን ጤናቸዉን እንዲከታተሉ እና የኤችአይቪ ምርመራ እንዲያደርጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ እየተሰጠ መሆኑ ተጠቁሟል ።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 31👍 8🔥 1
