ru
Feedback
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

Открыть в Telegram

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Больше
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
44 133
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
-21530 день
Архив постов
በቬትናም በጣለዉ የማያቋርጥ ዝናብ ቢያንስ የ41 ሰዎች ህይወት አለፈ በማዕከላዊ ቬትናም ካለፈዉ ሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ ያልተቋረጠ ዝናብ እና ጎርፍ የተነሳ ቢያንስ የ41 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።የጎርፍ አደጋው ከ52,000 በላይ ቤቶች በዉሃ እንዲጥለቀለቁ ያደረገ ሲሆን ግማሽ ሚሊዮን አባወራዎችንና የንግድ ቤቶችን ያለኤሌክትሪክ ኃይል እንዳሳጣው ዘገባዎች ጠቁመዋል። ባለፉት ሶስት ቀናት የዝናብ መጠኑ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡በቅርብ ወራት ውስጥ የዝናብ አደጋዉ ቬትናምን ክፉኛ አጥቅቷል። ካልማጊ እና ቡአሎይ የተባሉ ሁለት አውሎ ነፋሶች ካስከተለዉ አደጋ በኃላ በሳምንታት ውስጥ ሞትና ውድመት አስከትሏል።ካለፈዉ ዓመት ከጥር እስከ ጥቅምት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ በቬትናም የደረሱ የተፈጥሮ አደጋዎች 2 ቢሊዮን ዶላር ጉዳት አድርሰዋል ሲል መንግስት ግምታዊ አሃዝን አስቀምጧል። በአገር ውስጥ ሚዲያዎች የተሰራጩ ፎቶግራፎች እንዳሳዩት ሰዎች ጎርፍ ወደ ቤታቸው ሲገባ በጣሪያ ላይ ታግተው ያሳያሉ፡፡በላም ዶንግ ግዛት ውስጥ የተንጠለጠለ ድልድይ መልህቁን ሲነቅል አመላክተዋል።የመሬት መንሸራተት በዋና ዋና መንገዶች እና አውራ ጎዳናዎች ላይ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ግዛቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
11😢 1
1
የተመረዘ ምግብ በልተዉ ከታመሙ 8 የአንድ ቤተሰብ አባላት  ዉስጥ የ7ቱ  ህይወት አለፈ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በጋራ  እራት ተመግበዉ በጠና ከታመሙ   ስምንት የአንድ ቤተሰብ አባላት ዉስጥ የሰባቱ ህይወት ማለፉን ፖሊስ ተገልጿል ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ም/ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬድዮ እንደገለፁት በወረዳዉ ወገራም ቀበሌ ዳሾ ቆቶ  ተብሎ በሚጠራዉ መንደር  ህዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 1:00 ሰዓት ስምንቱ የቤተሰብ አባላት   አብረዉ እራት ከተመገቡ በኋላ በድንገት መታመማቸዉ የገለፁት። እራት በአብሮነት እንደተመገቡ  ብዙም ሳይቆዩ ከፍተኛ ለሆነ ህመም መዳረጋቸዉን መረጃ የደረሳቸዉ  የአካባቢዉ ነዋሪዎች  የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ   ተረባርበዉ ወደ ሆስፒታል ማድረሳቸዉ ነዉ የተነገረዉ። ቢሆንም ከተጎዱ የቤተሰቡ አባላት የ5  ዓመቱ መንግስቱ ኃይሌ ፣የ7 ዓመቱ መክብነ ኃይሌ እና የ17 ዓመቱ  ተክሉ ኃይሌ  የተባሉት ሶስቱ ወንድማማቾች በዕለቱ ሆስፒታል እንደደረሱ  ህይወታቸዉ ማለፉን ነዉ  የተገለፀዉ።  የተቀሩ ተጎጂዎችን ህይወት በህክምና ለማትረፍ ሀኪሞች ያልተቋረጠ ጥረት ቢያደርጉም  የ14 ዓመቷ  መቅደስ ኃይሌ እና   የ15 ዓመቱ ገብሬ ኃይሌ የሁለቱ እህትና ወንድም ህይወት ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም  ምሽት 11:00 ሰዓት ሲያልፍ  የሟቾች ቁጥር ወደ  አምስት ሊጨምር ችሏል። ከተቀሩት ተጎጂዎች ደግሞ  የ1ዓመት ከ7 ወሩ ህፃን  ሲሳይ ኃይሌ  ህዳር  9 ቀን 2018 ዓ.ም ጥዋት 2:00 ሰዓት ላይ ህይወቱ ሲያልፍ  የስድስቱ  ሟች ልጆች አባት የሆነዉ አቶ ኃይሌ  አበራ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት ላይ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። የባለቤቷንና  የስድስት ልጆችዋን ህልፈት ምክንያት ያላወቀችው ዳመነች ደንበል በሚኒሊክ ሆስፒታል  ዉስጥ ሆና በህክምና እየተረዳች በህወት መኖሯን ተገልጿል። ፖሊስ ተጎጂዎች  የተመገቡት ምግብ የተመረዘዉ  በማንና እንዴት ነው የሚለዉን   ለማረጋገጥና የተፈፀመዉን ድርጊት አጣርቶ   ከምስራቅ ጉራጌ ዞን እና ከመስቃን ወረዳ  የተወጣጣ የምርመራ አጣሪ ግብረ ኃይል አዋቅሮ ምርመራ የማጣራቱን  ስራ የተጀመረ ሲሆን  በድርጊቱ የተጠረጠሩ አስር ሰዎች በቁጥጥር ስር  ዉለው  ምርመራ እየተጣራባቸው  ይገኛል ሲሉ  ም/ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል። በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
💔 92 14😭 8 2
የተመረዘ ምግብ በልተው ነበር የተባሉ 7 የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወት ማለፉን ፖሊስ ገለጸ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ መሰረተ ወገራም ቀበሌ ዳሾ ቆቶ  ተብሎ በሚጠራዉ መንደር ህዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 1:00 ሰዓት አብረዉ እራት የተመገቡ 8 የቤተሰብ አባላት መካከል 7ቱ ህይወታቸው አልፏል። የክልሉ ፖሊስ የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ምክትል ኮማንደር ያለዉ ተመስገን እንደገለፁት በአብሮነት እራት እንደተመገቡ ብዙም ሳይቆዩ ከፍተኛ ለሆነ ህመም መዳረጋቸዉን መረጃ የደረሳቸዉ  የአካባቢዉ ነዋሪዎች  የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ  ተረባርበዉ ወደ ሆስፒታል አድርሰዋቸዋል። ቢሆንም ከተጎዱ የቤተሰቡ አባላት ሦስቱ ማለትም የ5 ዓመቱ መንግስቱ ኃይሌ ፣የ7 ዓመቱ መክብነ ኃይሌ እና የ17 ዓመቱ  ተክሉ ኃይሌ የተባሉት ወንድማማቾች በዕለቱ ሆስፒታል እንደደረሱ ህይወታቸዉ አልፏል። የተቀሩት ተጎጂዎችን ህይወት በህክምና ለማትረፍ ያልተቋረጠ ጥረት ቢያደረግም የ14 ዓመቷ መቅደስ ኃይሌ እና የ15 ዓመቱ ገብሬ ኃይሌ የሁለቱን እህትና ወንድም ህይወት ማትረፍ ሳይቻል ቀርቶ ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም  ምሽት 11:00 ሰዓት ህይወታቸው አልፏል። የ1ዓመት ከ7 ወሩ ህፃን ሲሳይ ኃይሌ ህዳር  9 ቀን 2018 ዓ.ም ጥዋት 2:00 ሰዓት ላይ ህይወቱ ሲያልፍ የስድስቱ  ሟች ልጆች አባት የሆነዉ አቶ ኃይሌ አበራ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት ህይወታቸው አልፏል። የልጆቿን ህልፈት ያላወቀችው ወ/ሮ ዳመነች ደንበል በሚኒሊክ ሆስፒታል [በጽኑ ህሙማን] ክፍል ዉስጥ ሆና በህክምና እየተረዳች እንደሆነ አስታውቋል። ተጎጂዎች የተመገቡት ምግብ የተመረዘዉ  በማንና እንዴት? የሚለዉን እዉነታ ለማረጋገጥና የተፈፀመዉን ድርጊት አጣርቶ እዉነታዉ ለማረጋገጥ ከምስራቅ ጉራጌ ዞን እና ከመስቃን ወረዳ  የተወጣጣ የምርመራ አጣሪ ግብረ ኃይል ተዋቅሮ ምርመራ መጀመሩ ተገልጿል። ኮማንደር ያለዉ ተመስገን የምርመራ ግብረ ኃይሉ በድርጊቱ የሌሎች እጅ ሊኖር ይችላል በሚል ጥርጣሬ 10 ሰዎችን በቁጥጥር ስር  አዉሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልፀዋል። ተጎጂዎች በዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል ህክምና መከታተላቸውን የገለጸው ፖሊስ የሟቾች የአስክሬን ምርመራ ዉጤት እየተጠበቀ መሆኑንና ውጤቱም ስለጉዳዩ የተሻለ ፍንጭ የሚሰጥ መረጃ ሊገኝ እንደሚችል ጠብቋል።  መረጃው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ነው። #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የተመረዘ ምግብ በልተዉ ከታመሙ 8 የአንድ ቤተሰብ አባላት ዉስጥ የ7ቱ ህይወት አለፈ ምግቡ በማንና እንዴት ተመረዘ? በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በአብሮነት እራት ተመግበዉ በጠና ከታመሙ ስምንት የአንድ ቤተሰብ አባላት ዉስጥ አባወራዉ ከስድስት ልጆቹ ጋር ሰባት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸዉ ማለፉን ፖሊስ ገልጿል። የክልሉ ፖሊስ የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ምክትል ኮማንደር ያለዉ ተመስገን እንደገለፁት በወረዳዉ መሰረተ ወገራም ቀበሌ ዳሾ ቆቶ ተብሎ በሚጠራዉ መንደር ህዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 1:00 ሰዓት ስምንቱ የቤተሰብ አባላት አብረዉ እራት ከተመገቡ በኋላ በድንገት መታመማቸዉ ተናግረዋል። በአብሮነት እራት እንደተመገቡ ብዙም ሳይቆዩ ከፍተኛ ለሆነ ህመም መዳረጋቸዉን መረጃ የደረሳቸዉ የአካባቢዉ ነዋሪዎች የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ ተረባርበዉ ወደ ሆስፒታል ማድረሳቸዉ ነዉ የተነገረዉ። ቢሆንም ከተጎዱ የቤተሰቡ አባላት የ5 ዓመቱ መንግስቱ ኃይሌ ፣የ7 ዓመቱ መክብነ ኃይሌ እና የ17 ዓመቱ ተክሉ ኃይሌ የተባሉት ሶስቱ ወንድማማቾች በዕለቱ ሆስፒታል እንደደረሱ ህይወታቸዉ ማለፉን ነዉ የተገለፀዉ። የተቀሩ ተጎጂዎችን ህይወት በህክምና ለማትረፍ ሀኪሞች ያልተቋረጠ ጥረት ቢያደርጉም የ14 ዓመቷ መቅደስ ኃይሌ እና የ15 ዓመቱ ገብሬ ኃይሌ የሁለቱ እህትና ወንድም ህይወት ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 11:00 ሰዓት ሲያልፍ የሟቾች ቁጥር ወደ አምስት አሻቀበ። ከተቀሩት ተጎጂዎች ደግሞ የ1ዓመት ከ7 ወሩ ህፃን ሲሳይ ኃይሌ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ጥዋት 2:00 ሰዓት ላይ ህይወቱ ሲያልፍ የስድስቱ ሟች ልጆች አባት የሆነዉ አቶ ኃይሌ አበራ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በሰመመን ዉስጥ ሆኖ ከእንቅልፉ ሳይነቃ ህልፈቱ እዉን ሆኖ ልብ ሰባሪና አሳዛኝ የሆነ ዜና ተደመጠ። የባለቤቷንና የስድስት ልጆችዋን ህልፈት ለማወቅ ያልታደለችዉ ወይዘሮ ዳመነች ደንበል በሚኒሊክ ሆስፒታል በከፍተኛ የጥንቃቄ ክፍል ዉስጥ ሆና በህክምና እየተረዳች በህወት መኖሯን ነዉ ፖሊስ የተገለፀዉ። ተጎጂዋ ቤተሰቡን በጅምላ ወደ ሞት ያወረደዉን ጉዳይ ልትተርክ በህይወት ትተርፍ ይሆን?ወይስ እሷም የባለቤቷና የልጆችዋ እጣ ገጥሟት ከቤተሰቡ መሀል አንድም ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ በጅምላ እቺን አለም የመሰናበታቸዉ አሳዛኝ ዜና ይደመጣል? የሚለዉን ለመገመት ይከብዳል። ፖሊስ ተጎጂዎች የተመገቡት ምግብ የተመረዘዉ በማንና እንዴት?የሚለዉን እዉነታ ለማረጋገጥና የተፈፀመዉን ድርጊት አጣርቶ እዉነታዉ ለማረጋገጥ ከምስራቅ ጉራጌ ዞን እና ከመስቃን ወረዳ የተወጣጣ የምርመራ አጣሪ ግብረ ኃይል አዋቅሮ ምርመራ የማጣራቱን ስራ መጀመሩን የተናገሩት ኮማንደር ያለዉ ተመስገን የምርመራ ግብረ ኃይሉ በድርጊቱ የሌሎች እጅ ሊኖር ይችላል በሚል ጥርጣሬ አስር ሰዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልፀዋል። ተጎጂዎች በዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል ህክምና ተከታትለዋል ያለዉ ፖሊስ የሟቾች የአስክሬን ምርመራ ዉጤት እየተጠበቀ መሆኑንና ስለጉዳዩ የተሻለ ፍንጭ ሊሰጥ እንደሚችል መረጃ ሊገኝ እንደሚችል ይገመታል። የክልሉ ፖሊስ ሚድያ ክፍል ይህ ዜና በሚድያ ይፋ እስካደረገበት ሰዓት ድረስ ከስምንቱ ተጎጂዎች ዉስጥ አንዷ የሆነችዉ የቤቱ እማወራ በአዲስ አበባ ምንሊክ ሆስፒታል በህክምና እየተረዳች መሆኑን አረጋግጧል። በተለያየ ጊዜ እቺን አለም የተቀላቀሉት ከ46 ዓመቱ አባት እስከ 1 ዓመት አ7 ወር እድሜ ያለዉ ህፃን እቺን አለም በተመሳሳይ ሰአት ለመሰናበት የተገደዱበት ተግባር የተለየ ግኝት ካለ መረጃዉን ለህዝብ ይፋ የምናደርግ ይሆናል። (ኮማንደር ታጁ ነጋሽ -ማ.ኢ.ፖ.ኮ) #ዳጉ_@zena24now
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ደቡብ አፍሪካ ለቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ በጎዳናዎች ላይ ያለውን የጸጥታ ጥበቃ አጠናከረች የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እና ጦር ሃይሎች በጆሃንስበርግ በሚካሄደው የቡድን 20 የአለም መሪዎች ጉባኤ ዙሪያ ሊደረጉ ከሚጠበቁት ሰልፎች አስቀድሞ በሄሊኮፕተሮች እና በሞተር ሳይክሎች ላይ መኮንኖችን ያሳተፈ የጸጥታ ጥበቃ አድርገዋል።ረቡዕ የተካሄደው የውትድርና ለውጥ ባለሥልጣናቱ 3,500 የፖሊስ መኮንኖችን እና ሠራዊቱን በብሔራዊ የጋራ ኦፕሬሽን እና ኢንተለጀንስ መዋቅር ስር ያጠቃለለ ነበር፡፡ የፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ሌተና ጄኔራል ቴቤሎ ሞሲኪሊ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ባለስልጣናቱ በጆሃንስበርግ እና በሌሎች ትላልቅ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎችን እየጠበቁ ነው።“የመቃወም መብቱ እንዲተገበር እንፈቅዳለን” ሲሉ ሌተና ጄኔራል ቴቤሎ ሞሲኪሊ ተናግረዋል። ነገር ግን በተገቢው መመሪያ እና የህግ ገደቦች ውስጥ ሰልፎቹ ይካሄድዋል። የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በሀገሪቱ ትልቁ የእግር ኳስ ስታዲየም አጠገብ በሚገኘው የኤግዚቢሽን ማዕከል አቅራቢያ በሚገኘው የመሪዎች ጉባኤ አቅራቢያ ተቃዋሚዎች የሚሰበሰቡባቸው ቦታዎችን መለየቱን ገልጿል።ለሁለት ቀናት የሚቆየው የመሪዎች ጉባኤ ቅዳሜ የሚጀመር ሲሆን ከ40 በላይ ሀገራት መሪዎች እና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች እንዲሁም እንደ የተባበሩት መንግስታት ያሉ አለምአቀፍ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ነገር ግን ዩናይትድ ስቴትስ በጉባኤዉ እንደማትገኝ አስታዉቃለች፡፡ ሰልፎች ከፀረ-ካፒታሊስቶች፣ ከአየር ንብረት ተሟጋቾች፣ ከሴቶች መብት ተሟጋቾች፣ ፀረ-ስደተኛ ቡድኖች እና ሌሎችም ተቃዉሞ ይገጥመዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
24👍 3👏 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ ሁለት ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
20😢 8😁 5👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
በአፋር ክልል በአምስት ዓመታት ውስጥ 6 የነበረውን የሆስፒታል ቁጥር ወደ 10 ማሳደግ ተቻለ ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ ክልሉ የጤና ስርአቱ ተስተጓጉሎ የነበረ ሲሆን በተሰራው ሰፋፊ ስራዎች ችግሮችን መቅረፍ መቻሉን የአፍር ክልል የጤና ቢሮ አስታውቋል ። የክልሉ የጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ያሲን ሃቢብ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በወቅቱ የወደሙ ጤና ተቋማትን ወደ ቦታ የመመለስ እነሱን የማደስ የሰው ሀብቱንም በዛ ልክ ደግሞ በማደራጀት ሰፋፊ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን ውጤትም አስገኝቷል ተብሏል። የክልሉ ማህበረሰብ  አርብቶ አደር እንደመሆናቸው የጤናው ስርዓት ሲታቀድ እና ሲሰራ የአኗኗር ባህላቸውን ተከትሎ መሆኑን የተናገሩት አቶ ያሲን በክልሉ የጤና ተቋማትን በመጨመር የሰው ኃይል በመጨመር ሰፋፊ ስራዎችን የተሰሩ ሲሆን ወደ 88 የነበሩ ጤና ጣቢያዎችን ወደ 110፣ 6 የነበሩት ወደ 10 ሆስፒታል፣ ስፔሻሊቲውንም በተመሳሳይ ደረጃ ከፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ በእያንዳንዱ ፕራይመሪ ሆስፒታል ከአራት እና ከዛ በላይ የሆኑ ስፔሻሊስቶችን በመመደብ ሰፊ ስራ ተሰርቷል ብለዋል። በትግስት ላቀዉ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
👍 16 10👌 2👎 1
በዌስት ባንክ ፍልስጥኤማዉያንን በማፈናቀል እስራኤልን በጦር ወንጀል ተከሰሰች ሂውማን ራይትስ ዎች እስራኤል በያዘችው ዌስት ባንክ 32,000 ፍልስጤማውያንን ከሶስት የስደተኞች ካምፖች በሃይል በማፈናቀል የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ፈጽማለች ሲል ከሷል።የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ባለ 105 ገጽ ሪፖርቱን አውጥቷል፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ኢዝራኤል ካትስን ጨምሮ በእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል። ግኝቶቹ ሂዉማን ራይትስ ዎች በጃንዋሪ 21 በጀመረው በዌስት ባንክ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ ወቅት የዘር ማፅዳት ብሎ የገለፀውን ሰነድ አያይዟል።የሂዉማን ራይትስ ዎች የእስራኤልና ፍልስጤም ዳይሬክተር ኦማር ሻኪር በኤክስ ላይ በለጠፉት መልዕክት ድርጊቱን "ሁለተኛ ናክባ" ብለዉ ሰይመዋል፡፡ ይህም ማለት ከ 1967ቱ የፍልስጤማውያን መፈናቀል  በኋላ ሁለተኛው ግዙፍ መፈናቀልን ለመግለጽ ናክባ የሚለዉ ስያሜ ጥቅም ላይ ዉሏል፡፡ በሌላ በኩል የእስራኤል ጦር ትናንት በጋዛ ላይ ከባድ የአየር ድብደባ በጋዛ ሲቲ እና በካን ዮኒስ ፈጽሞ ቢያንስ 30 ሰዎችን ገድሏል፤ ሃማስ ዉጥረቱን ያባብሳል ሲል ገልጾታል፡፡እስራኤል ጥቃቱ የተፈጸመው የሐማስ ተዋጊዎች በደቡባዊ ጋዛ በሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች ላይ ለተተኮሱት የአጸፋ ምላሽ ነው ስትል ሃማስበበኩሉ  “እየተፈፀመ ያለውን ወንጀላቸውን እና ጥሰቶቻቸውን ለማስረዳት የተደረገ ሙከራ ነው” ሲል ውድቅ አድርጎታል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
👍 29 10😁 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
🤔 4 2
የመድፈር ጥቃትን በመፈፀም እና እንዲፈፀም በማመቻቸት ተግባር ላይ የተሠማሩ ወንድማማቾች በእስራት ተቀጡ በሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ የመድፈር ጥቃት በመፈፀምና እንዲፈፀም በማመቻቸት ተግባር ላይ የተሰማሩ ወንድማማቾች በእስራት መቀጣታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የሴቶች እና ሕፃናት ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር  አስናቀች ወልዴ እንደገለፁት 1ኛ ተከሣሽ ቶለሣ ታምሩ የአስራ ዘጠኝ ዓመት ወጣት፣ 2ኛ ጫላ ታምሩ የአስራ ስምንት አመት ወጣት  ወንድማማቾች  በመቀናጀት የአስራ አምስት ዓመቷ ልጅ ላይ የመደፈር ጥቃት በመፈፀም እና ሁኔታዋችን በማመቻቸት ተከሰው በእስራት መቀጣታቸውን ገልፀዋል። አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሣሾች ታላቅና ታናሽ ወንድማማቾች ሲሆኑ ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም ከምሽቱ አንድ ሠዓት ተኩል ላይ የመደፈር ጥቃት የተፈፀመባት የአስራ አምስት አመትን ልጅ ሁለተኛው ተከሣሽ በመጥራት ታላቅ ወንድሙ የመድፈር ጥቃት እንዲፈፅምባት ማድረጉ በማስረጃ ተረጋግጧል። ታላቅ ወንድሙ የአስራ አምስት ዓመቷን ልጅ ላይ የመድፈር ጥቃት ሲፈፅም ታናሽ ወንድም ደግሞ ቤተሠቦቹ እና ሌሎች ሠዎች እንዳይመጡ በር ላይ ሆኖ በመጠበቅ ሁኔታዎችን ሲያመቻች ነበር። ታዳጊዋ የደረሠባትን ጥቃት ወዲያው ለቤተሠቦችዋ በማሳወቋ ቤተሠቦች ሁኔታውን ለፖሊስ ገልጸዉ ድርጊቱ የፈፀሙ ታላቅ እና ታናሽ ወንድማማቾች ከተሸሸጉበት በቁጥጥር ስር በማዋል ጥቃት የተፈፀመባትን ልጅ ለምርመራ ወደ ጤና ጣቢያ ተልካለች።ፖሊስ በታናሽ እና በታላቅ ወንድማማቾች ላይ የምርመራ መዝገቡን ከሕክምና ተቋም በተገኘ ማስረጃ እና በሌሎች በማጠናከር ለአቃቤ ሕግ የላከ ሲሆን አቃቤ ሕግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በሁለቱ ወንድማማቾች ላይ በወንጀል ሕግ ቁጥር 627 በሕፃናት ላይ የሚፈፀም የግብረ ስጋ ድፍረት እና በደል ክስ መስርቷል። በአቃቤ ሕግ የተመሠረተውን ክስ የተመለከተው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለቱ ወንድማማቾች ላይ ሕዳር 4ቀን 2018ዓ.ም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሣሽ ቶለሣ ታምሩ በሠባት አመት ሁለተኛ ተከሣሽ ጫላ ታምሩ በአንድ አመት እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ምክትል ኢንስፔክተር አስናቀች ወልዴ ጨምረው ገልፀዋል። በሰመሀር አለባቸው #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
🤬 29 16👍 10👎 8
Фото недоступноПоказать в Telegram
1
ለቻይና ስትሰልል ነበረ የተባለች የቀድሞ የፊሊፒንስ ከንቲባ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣች ቻይናን በመሰለል የተከሰሱት የቀድሞ የፊሊፒንስ ከንቲባ የማጭበርበሪያ ማዕከልን በመምራት በፈጸሙት ሚና በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።ሐሙስ ዕለት በተላለፈዉ ዉሳኔ እሷ እና ሌሎች ሶስት ሰዎች የእድሜ ልክ እስራት እና የ2 ሚሊዮን ፔሶ ቅጣት ተፈርዶባቸዋል። ባለሥልጣናቱ በባምባን ውስጥ ከሀገሪቱ ትልቁ የማጭበርበር ማዕከላት አንዱን ካገኙ በኋላ የቀድሞ ከንቲባ አሊስ ጉኦ ጉዳይ በፊሊፒንስ ለዓመታት ተይዞ ቆይቷል። ለሳምንታት በመሸሸግ ከቆየች በኋላ ባለፈው አመት ተይዛ የነበረችው የ35 ዓመቷ ሴት፣ የተከሰሰችባቸዉን ክሶች በሙሉ ውድቅ አድርጋለች። ይግባኝ ማለት ትችል እንደሆነ ግን እስካሁን ግልፅ አይደለም።በጉዎ ላይ አሁንም አምስት በመታየት ላይ ያሉ ክሶች አሉ፣ አንደኛውን በገንዘብ ማጭበርበር የተከሰሰችበትን ነዉ።እ.ኤ.አ በ2022 ጉኦ ከዋና ከተማው ማኒላ በስተሰሜን የምትገኘው የባምባን ከንቲባ ሆና ተመርጣለች፡፡ የባምባን ነዋሪዎች ቀደም ሲል ለቢቢሲ እንደተናገሩት ተቆርቋሪ እና ሩህሩህ መሪ ነበረች ብለዋል።በጊዜ ሂደት ግን ከንቲባዋ ሰፊ የማጭበርበር መረብ ዘርግታ ትንቀሳቀስ እንደነበር ሊታወቅ ችሏል፡፡ በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
13👍 3
5
በአዲስ አበባ የሞቱ ዶሮዎችን በማረድ እና በማሸግ ለተለያዩ ሱቆችና ሆቴሎች ለማከፋፈል ሲዘጋጁ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ በአዲስ አበባ ከተማ በሾላ ገበያ የሞቱ ዶሮዎችን በማረድ እና በማሸግ ለተለያዩ ሱቆችና ሆቴሎች ለማከፋፈል ሲዘጋጁ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ። ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከሰላም ፀጥታ ፅ/ቤት እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ በመሆን  ባደረገዉ ድንገተኛ ዘመቻ ነው። በተደረገው ክትትልና የተቀናጀ ኦፕሬሽን ግለሰቦቹ የሞቱ ዶሮዎችን በማረድ እና በማሸግ ለተለያዩ ሱቆችና ሆቴሎች ለማከፋፈል ሲዘጋጁ በነበረበት ሁኔታ መያዛቸው ተጠቁሟል። በዚህም የታሸገ ዶሮ በቁጥር መቶ 100 ተበልቶ ለመታሸግ የተዘጋጀ አርባ ሁለት 42 መያዝ መቻሉን ብስራት ሬዲዮ ከባለሥልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
😁 17 8🤔 3👀 2👍 1😭 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጀልባ ተገልብጦ 70 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ተባለ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በካሳይ ግዛት ውስጥ በአንድ ወንዝ ውስጥ ጀልባ ተገልብጦ ወደ 70 የሚጠጉ ሰዎች መጥፋታቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ጀልባዋ ከ800 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ላይ ከምትገኘው ቤና ዲቤሌ ወደብ ወደ ዋና ከተማ ኪንሻሳ በማቅናት ላይ የነበረች ሲሆን በሳንኩሩ ወንዝ ላይ በደረሰባት አውሎ ንፋስ መስጠሟን የተባበሩት መንግስታት ራዲዮ ዘግቧል። "ጀልባው በግምት 120 ሰዎችን አሳፍራ ነበር፣ እስካሁን 50 ያህሉ መትረፋቸውን እና የጠፉትን የማፈላለግ ጥረቱ ቀጥሏል" ሲል የአካባቢው አስተዳዳሪ ፍራንሷ አሆካን ተናግረዋል። አሆካ የነፍስ አድን ቡድኖች ያጋጠሟቸውን ችግሮች በማንሳት የተረፉትን እና የተመለሱትን አስከሬኖች ለመለየት ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር እንዲገናኙ ቤተሰቦችን ጠይቀዋል።በኮንጎ በአብዛኛው ባለዉ ደካማ መሰረተ ልማት የተነሳ ምክንያት የውሃ ትራንስፖርት የተለመደ ነው። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показать все...
😢 8 6🤔 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
3
ሚኪያስ ጎማ ፣ ባትሪና ከመነዳሪ አከፋፋይ  #ለቪትስ #ለያሪስ #ለዲዛየርና ስዊፍት #ለኮሮላ #3L & 5L እንዲሁም ለከባድ ተሽከርካሪዎች የሚሆኑ ጎማዎች እና ባትሪዎችን ይዘዙን ካሉበት እናደርሳለን 👉የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎማዎች (ትሪያንግል ፣ ስፖርትራክ ፣ ኮምፈርሰር ፣ አፖሎ ፣ ብሪጅስቶን እና ሌሎችም) 👉አሮጌ ባትሪ እንገዛለን 👉 የተገለገሉበት ጎማ ን ዋጋ ተምነን በአዲስ እንቀይርሎታለን 👉 በስልክ ቁጥር 📞...+251-913-701702 / +251-975293297 ይደውሉልን አልያም ተክለሀይማኖት ከሚገኘው ሱቃችን ይምጡ በደስታ እናስተናግድዎታለን
Показать все...
8👍 2🔥 1