መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿
Открыть в Telegram
☑ ከጥንት አባቶቻች በተቸረን ሰሎሞናዊ ጥበብ ተፈጥሮ ያበቃላቸው የእፅዋት መድሀኒቶችን በመጠቀም ክፉ ዓይነ ጥላ ፣ በቤተሰብ ወይም በዘር የሚተላለፉ መናፍስት መፍትሔዎቻቸው ይተነተናሉ። ☑ አድራሻ ቁጥር 1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ቁጥር 2 አ/አ አየር ጤና እንዲሁም በተለያዩ የክልል ከተሞች እንልካለን 📞#0918834904 📞#0915310455 መልዕክት ካለዎት @merigetaamedeberhan
Больше2025 год в цифрах

118 255
Подписчики
-13124 часа
-9867 дней
-4 53730 день
Архив постов
መፅሄተ መንፈስ ቅዱስ.pdf2.45 MB
መፍትሔ ሥራይ ቆጵርያኖስ.pdf67.26 MB
ቱላዳን.pdf65.16 MB
👍 1
እጮኛሞች ሆይ እናንተ ተፋቅራችሁ፣ተዋዳችሁ አላውቅበት ብላችሁ የምታበላሹት የነገ የትዳር ሕይወት ስንቶቹ የሚመኙት እና እግዚአብሔርን የሚማጸኑበት ሕይወት ነው፡፡ እናንተ ሳተውቁ የምታበ
ላሹ አጋጣሚ ሌላ ሰው ቢሆን ኖሮ ተጋብተው ወልደው ይከብሩበት ነበር፡፡ እናንተ ትዳር ሰልችቷች ስትለየዩ የሚበተኑት የሚንከራተቱት ልጆች ስንት መሐኖች እግዚአብሔርን ‹‹እባክህ የዓይኔ ማረፍያ አንድ ልጅ ስጠኝ›› ብለው የሚጸልዩት ነው፡፡
ባለ ትዳሮች ሆይ እናንተ መኖር መፋቀር አቅትዋችሁ ሕይወቱ ሰልችቷችሁ የምታፈርሱት ትዳር ስንቶቹ ለመኖር የሚጓጉት ነው፡፡ እግዚአብሔር በአንድም በሌላ የሰጣችሁ እጮኛ እና ትዳር በዓይነ ጥላ ተንኮል የሚኮላሻው ስላላወቃችሁበት ነው፡፡ ግን ቁጭት ውስጥ የምትገቡት በእጃችሁ ያለውን እድል ስታጡት አሳልፋችሁ ለሌላ ስትሰጡት ነው፡፡ ዓይነ ጥላው እናንተን በመቆጨት ለማቃጠል ካለፈ በኃላ ‹‹ያኔ ምን ሆኜ ነው፣ለምን እንደዛ አደረኩ›› እያስበላ የጸጸት ዘመናትን እንድታሳልፉ ያደርጋችኃል፡፡ ታጋሹ ኢዮብ በሕይወቱ ላይ የደረሰበት ታላቅ ፈተናና መከራ በሥጋው ስልችት ስላለ ‹‹ነፍሴ ሕይወቴን ሰለቸቻት›› በማለት ተናግሯል፡፡ /ኢዮ 10÷1/
ዓይነ ጥላ እጮኛሞችንና በላትዳሮችን በነገሮች ሁሉ እያሰለቻቸው ሌላ ሰውን እያስመኛቸው ለዝሙት ያጋልጣቸዋል፡፡ ወዳጆቼ የተጠናወተን ዓይነ ጥላ እንኳን ሥጋዊ የእጮኝነት እና የትዳር ሕይወትን ቀርቶ የነፍሳችንን መንፈሳዊ ሕይወት ያሰለቸናል፡፡ ጸሎት እንድንሰለች ያደርገን የለ? ጸሎት ስንሰለች እኮ መጨረሻችን ጸሎቱን መተው ነው፡፡ ልክ እንደ ጸሎቱ ፍቅር እና ትዳር ሲሰለቸን መጨረሻ መለያየት ነው፡፡ የዓይነ ጥላው አጋንንታዊ ግቡ የእኛን ሕይወት ማበላሸት እና ማኮላሸት ነው፡፡
ወዳጆቼ አንዳንዶች ‹‹መኖር ሰለቸኝ›› ሲሉ የምትሰሙት ዓይነ ጥላቸው መኖር ሲያሰለቻቸው ነው፡፡ ዓይነ ጥላ መኖር ሲያሰለቸን እረሳችንን እንድናጠፋ ነው የሚገፋፋን፡፡ መኖር መሰልቸት ለአጋንንቱ በቁም መሞት፡፡ በእጮኝነት መኖር መሰልቸት ለአጋንንቱ እጅ መስጠት ነው፡፡ በትዳር መኖር መሰልቸው በአጋንንቱ ተንኮል ስር መውደቅ ነው፡፡
ዛሬ ወጣቱን ዓይነ ጥላው ሕይወትን ስላሰለቻቸው በሱስ መጠመድ፣በስካር ሌሊቱን ሁሉ ማበድ ምንም አይመስላቸውም፡፡ ቀድሞ በማሰልቸት ስለገባባቸው መኖር የሚለው ነገር ለእነሱ ትርጉም የለውም፡፡
ዓይነ ጥላ እራሳችንን እንድንሰለች ያደርገናል፡፡ እራሳችንን ስንሰለች ለምን እንደምንኖር፣ለማን እንደምንኖር ስለማናውቅ የባዶነት ስሜት ውስጥ ይከተናል፡፡ ስለዚህ እጮኛሞች፣ባለትዳሮች የያዛችሁት ሕይወት የመሰልቸት ስሜት ከተሰማችሁ ቆም ብላችሁ አስቡ፡፡ በጸሎትም ወደ ፈጣሪ ጩኹ፡፡ ካልሆነ ግን በእጃችሁ ያለውን ሕይወት እያያችሁት ከእጃችሁ በማውጣት የሙሉ ጎዶሎ ያደርጋችኃል፡፡ ዓይነ ጥላው ሕይወታችንን በማሰልቸት ሳይቀማን ልንነቃበት እና ልናውቅበት ይገባል፡፡ ዛሬ የስንቱ የፍቅር እና የትዳር ሕይወት ባላታወቀ ግን በዓይነ ጥላ ስውድ ደባ ሕይወት አልባ ሆኗል፡፡ ላለፈ ክረምት ቤት ባይሰራም ዓይነ ጥላ በማሰልቸት ብዙ ነገራችንን ቢያበላሽም ካለፈ ሕይወት በመማር በአጋንት ሴራ የራሳችን የሆነ ነገርን እንዳንነጠቅ መጠንቅ አለብን፡፡
አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎች ሼር በማድረግ ያቋድሱ፡፡
ክፍል ስድስት
በመጥፎ የሰውነት ጠረን እና ሽታ የሚመሰል ዓይነ ጥላ
/ወንዶች በተለይ ሴቶች የሚቸገሩበት/
ይቀጥላል …
👍 2
ክፍል አምስት
እጮኛሞችንና ባለ ትዳሮችን የሚያሰለች ዓይነ ጥላ
/ብዙዎች የታከቱበት አስከፊ ሕይወት/
በቀሲስ መ/ር ሄኖክ ወ/ማርያም
ተወዳጆች ሆይ በክፍል አራት ዓይነ ጥላ እንዴት ባለ ስውር እና ግልጽ ፈተና በሰዎች ዘንድ እንድንጠላና እንዳንወደድ እንደሚያደርገን አይተናል፡፡ አሁን ደግሞ በዚህ ክፍል የራሳችንን ሕይወት በማሰልቸት እንዴት እንደሚጫወትብንና እንደሚያሰለቸን እናያለን፡፡ የአብርሃም እና የሳራ አምላክ ይርዳን፡፡
ዓይነ ጥላ የእኛን ሕይወት በማሰልቸት ከርኩሳን መናፍስት የሚወዳደረው የለም፡፡ ምክንያቱን የዓይነ ጥላ መንፈስ ውጊያ ሕይወታችንን ማጨናገፍ ላይ ያተኮረ ስለሆነ ነው፡፡ ብዙዎች ሳያውቁ ሳይነቁ ጥሩ አእምሮ ኖሮአቸው ዓይነ ጥላቸው መማርን ያሰለቻቸዋል፡፡ ተምረው ስራ ይይዙና ዓይነ ጥላቸው ስራን ያሰለቻቸዋል፡፡ እጮኛ ይይዙና ፍቅር ይሰለቻቸዋል፣ትዳር ይይዙና ትዳሩ እስር ቤት እየመሰላቸው ስልችት ይላቸዋል፡፡
ወዳጆቼ ብዙዎች እጮኛ ወይም ጓደኛ ለመያዝ ያስቡና ከያዙ በኃላ ብዙም ሳይቆዩ ግንኑነታቸው ይሰለቻቸዋል፡፡ ግን ለምን እንደሆነ አያውቁም፡፡ እየወደዱ የመጥላት አባዜን ዓይነ ጥላው ያጠናውታቸዋል፡፡ ስንቶች በራሳቸው ጥላቻ እየመሰላቸው የራሳቸውን እጮኛ ወይም ጓደኛ ለሰው አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ ዓይነ ጥላቸው እነሱ ላይ ሆኖ ፍቅረኛቸውን እንዲጠሉ ያላቸውን የፍቅር ሕይወት እንዲሰለቹ ያደርጋቸዋል፡፡
አንዳንዶቹን ደግሞ ዓይነ ጥላቸው የፍቅር ሕይወታውን ለማጨለም አብሮአቸው ያለውን ፍቅረኛ ሰልችተው ከሌላ ሰው ጋር የሰመረ ፍቅር የሚኖራቸው አድርጎ በማሳሰብ ይለያያቸዋል፡፡ ብዙ ሴቶች ወንድ ለምን እንደሚሰለቹ አያውቁም፡፡ ወንዶቹም ዓይነ ጥላቸው የወደዳትንና በተለይ የወደደችውን ሴት ስልችት እንዲል ያደርጋቸውና ሴት መቀያየር የተሻለ ፍቅር እና ሴት ማግኘት እያስመሰለባቸው አመንዝራ ያደርጋቸዋል፡፡ ወዳጆቼ ዓይነ ጥላ በእጮኝነት ሕይወት ማሰልቸት ከጀመረ ከማንም ጋር ደስተኛ አያደርገንም፡፡
ሌሎቹም ደግሞ ዓይነ ጥላው እጮኛ ይዘው ነገን በትዳር እንዳይኖሩ ገና ሲያስቡት የእጮኝነት፣የትዳር ሕይወት እንዲሰለቻቸው ያደርጋቸዋል፡፡ የሚያሳዝነው አንዳንዶች እውነተኛ እጮኛ መያዝ ይፈልጋሉ ግን ገና ሲያስቡት ይሰለቻሉ፡፡ ዓይነ ጥላቸው ነገሮችን አግዝፎ እያሳያቸው ፈሪ ያደርጋቸዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሴቶች የእጮኝነትን ሕይወት በመሰልቸት ስለሚጀምሩ ስኬታማ አይሆኑም፡፡ ስልክ መደዋወል፣መጠያየቅ፣አብሮ መብላት፣ሻይ ቡና ማለት ያስጠላቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላቸው ውስጥ ሆና አሸምቆ የመከላከል ሥራ ይሠራል እነሱንም ያሰለቻል፡፡
ባለትዳሮችን የሚያሰለች ዓይነ ጥላ ደግሞ መዓተኛ ነው፡፡ እስኪጋቡ ያስቸኩላቸዋል፣ተጋብተው አንድ እስኪሆኑ ፍቅር በፍቅር ያደርጋቸዋል፡፡ ግን በእውነተኛ ፍቅር መዋደድ ሲጀምሩ ከመላከድ ወደ መሰላቸት ውስጥ ይገባሉ፡፡ ባለ ትዳሮች እና ፍቅረኛሞች ከሁለት አንዳቸው ባላቸው ሕይወት መሰላቸት ሲጀምሩ ማኩረፍ፣መነጫነጭ፣መጣላት ብሎም መሰዳደብ ሲብስም ጸያፍ ስድብን በንቀት መሳደብ ይጀምራሉ፡፡
አቅደው ተዋደው የተጋቡት ባለትዳሮች ከውስጥ አሸምቆ ተደብቆ የነበረው ዓይነ ጥላ ብቅ ይልና ለምን እንደተጋቡ ግራ እስኪጋቡ ድረስ፣ማግባታቸው ልክ እንዳልሆነና፣አሁን አብሯቸው የሚኖረው የትዳር ተጣመሪያቸው እጣ ክፍላቸው፣እህል ውኃቸው እንዳልሆነ ወይም እንዳልሆነች በማሳሰብ የስልችት ሕይወት ውስጥ ይከታቸዋል፡፡
ዓይነ ጥላ ፍቅረኛሞችንና ባለትዳሮችን ባማሰልቸው ብዙ ነገር ይጠቀማል፡፡ አንደኛ የነበራቸው ፍቅር ተቀዛቅዞ መሰላቸታቸውን ለመለያየት ይጠቀምበታል፡፡ በዚህም የራሳቸው ውሳኔ እንጂ የዓይነ ጥላው ስውር ሴራ አይመስላቸውም፡፡ ሁለተኛ ከወደዱት ሰው ተሰላችተው ከተለያዩ ፍቅርና ትዳርን ይፈራሉ፡፡ በዚህም ነገም የትላንቱ የስልቹነት ሕይወት ይደገማል ብለው እንዲያስ ያደርጋቸዋል፡፡ ሦስተኛ የመሰልቸው ሕይወት ተስፋ የመቁረጥን ክፍ ሕይወት ስለሚያመጣ ፍቅር እና ትዳርን እንዳያምኑ ያደርጋቸዋል፡፡ አራተኛ ከፍተኛ ጥላቻ ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል፡፡
ወዳጆቼ ዓይነ ጥላ የዛሬን የፍቅር እና የትዳርን ሕይወት የሚያሰለቸን ነገና ተነገ ወዲያ ያለውን ሕይወታንን በማሰብ ነው፡፡ የዛሬን የእጮኝነት እና የትዳር ሕይወትን በመሰለቸት ከለያየን ነገን በፍቅር እና በትዳር እኖራለሁ ብለን ስለማናስብ በቀላሉ የነገ ሕይወታችንን በዛሬ ተንኮሉ ያበለሽብናል፡፡
ዓይነ ጥላ የባለ ትዳሮችን ሕይወት ለማበላሸት ከሚጠቀምባቸው ዘዴ አንዱ ሩካቤን ማሰልቸት ነው፡፡ ትላንት ተስማምተው ተፈቃቅደው ጓጉተው የሚፈጽሙት ሩካቤ የፍቀር መግለጫ ሳይሆን የባርነት ሕይወት አድርጎ ሩካቤ ጠል ያደርጋቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላው ትላንት የነበራትን የሩካቤ ፍላጎት ላይ የስሜት ቅዝቃዜ በመድፋት ስሜትዋን ይገላል፡፡ በዚህም ሩካቤ ይሰለቻል፡፡ ሲሰለች ደግሞ ጥላቻ ይከተላል፡፡ ከጥላቻ በኃላ ፊቺ ይቀጥላል፡፡
እግዚአብሔር የሰጠንን የተፈጥሮ ጸጋ እንደ አልባሌ ነገር እንደ ነውር በማሳየት የመሰልቸት ሕይወት ውስጥ ይከተናል፡፡ ለዚህም ነው ብዙዎች ፍቅር፣መወዳድ ሳያንሳቸው መሰልቸት ተጭኗቸው የሚለያዩት፡፡ ሲጠየቁም ለምን እደሆነ አያውቁም፡፡ዓይነ ጥላው ባልን ሚስቱን ሲያሰለቸው የሩካቤ ፍላጎቱን ያጠፋል፡፡ ሚስት ግድ ስትለው ‹‹ደክሞኛል፣ዛሬ ጥሩ አይደለውም›› በማስባል ስልቹነትን በማለማመድ ወደ መለያየት መንገድ ይመራቸዋል፡፡
ዓይነ ጥላ ባለትዳሮችን ሲያሰለች ፍቅራቸውን በመጋረድ ኑሮአቸውን፣ችግራቸውን፣ፈተናቸውን አግንኖ በማሳየትና በማሳሰብ ትዳራቸውን ያሰላቻል፡፡ ለዚህም ነው አንዳንዶች ለምንድነው የተለያያችሁት ሲባሉ ‹‹ተደባበርን›› እያሉ ዓይነ ጥላቸው በአፋቸው ላይ የሚናገረው፡፡ የተረገመው ዓይነ ጥላ እንኳን ሕይወታችንን የምንኖርበትን ቤት እንድንሰለች ያደርገናል፡፡ ጥሩና ምቹ ቤት ውስጥ እየኖርን ዓይነ ጥላው ደስታችንን ለመንጠቅ ቤታችንን እንድንጠላ ያደርገናል፡፡ አንዳንዶች ‹‹ቤቴ ያስጠላኛል፣ጪሂ ጪሂ ይለኛል›› የሚሉት አጋንንቱ በገሃድ ሲዋጋቸው ነው፡፡
ወዳጆቼ የዛሬ አስር ዓመት ያነበብኩትን የአንድ የዶክተር ሕይወት ላካፍላችሁ፡፡ ዶክተሩ በጥቁት አንበሳ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና ክፍል ኃላፊና ጎበዝ ባለ ሙያ ነው፡፡ ይህ ዶክተር አጋንንት ያሰለቸውን ሕይወት እንዲህ በማለት ነበር የገለጸው፡፡ ‹‹የከብት ኑሮ ሰለቸኝ፡፡ ከብት ጠዋት አተላውን ጭዱን ይበላና ወደ እርሻ ይሄዳል በዛም ተጠምዶ ሲያርስ ይውላል፡፡ እኔም ጠዋት ቁርሴን በልቼ ወደ ሆስፒታል ሄጄ ሳክም እውላለሁ፡፡ በሬው መማሻውን ወደ በረቱ ይመለሳል፡፡ እኔም መምሻዬን ወደ ቤቴ እመለሳለሁ፡፡ ቀን ሲያርስ የዋለው በሬ አተላና ጭድ ይቀርብለታል ይበላልም፡፡ ለእኔም ማታ እራት ይቀርብልኛል እበላለሁ፡፡ በሬው ከበረቱ ውስጥ ያለችውን ላም ያጠቃል፡፡ እኔም ከሚስቴ ጋር እተኛለሁ፡፡ ለእኔም ለበሬው ይነጋል፡፡ እርሱም ወደ እርሻው እኔም ወደ ሥራዬ እሄዳለሁ›› በመማለት ተናግሯል፡፡
አጋንንት ሕይወታችንን ሲያሰለች እንደዚ ባላ ነገር ነው እራሳችንን በማሳመን የመሰልቸት ሕይወት ውስጥ የሚከተን፡፡ ወገኖቼ ሰው ሲሰለች እንደ ሰው ሳይሆን እንደ እንስሳ ነው የሚሆነው፡፡ ሰው ሲሰለች እንደ ሰው ሳይሆን እንደ እንስሳ ነው የሚያስበው፡፡ ሰው ሕይወትን ሰለቸ ማለት ለአጋንንት ውጊያ ተመቸ ማለት ነው፡፡
❤ 2
ሰላም ለኩሉ እንዴት ከረማችሁ እንዴት አመሻችሁ ሰሞኑን ስለ አይነጥላ ሴራ በሂወታችን ለይ ስለሚያደርሰው ተፅኖ የምፅፈውን በድምፅ ለመስማት የምትፈልጉ በ tik tok ገብተው ያገኙታል። 👇👇👇
✳️የቲክቶክ ቻናላችን
http://tiktok.com/@mergetaamdebrhan
ሰላም ለኩሉ እንዴት እንዴት ከረማችሁ እንዴት አመሻችሁ ሰሞኑን ስለ አይነጥላ ሴራ በሂወታችን ለይ ስለሚያደርሰው ተፅኖ የምፅፈውን በድምፅ ለመስማት በ tik tok ገብተው ያገኙታል። 👇👇👇
✳️የቲክቶክ ቻናላችን
http://tiktok.com/@mergetaamdebrhan
ቸገራሉ ያንቀላፋሉ፡፡ ዓይናቸው ይሞጨሙጫል፣ዙርያውን ቆሻሻ ይይዛል፡፡ በሕፃናት ላይ ደግሞ ገና በልጅነታቸው የእይታ ችግር በመምሰል ለዓይን ሕመም ይዳርጋቸዋል፣ነገሮችን አጥርተው ስለማያዩ እኛም ዓይነ ጥላውን በመነጽር በመሸፈን ችግሩ የሌላ ይመስለናል፡፡ በዚህ መልኩ ያጠቃን ያላወቅነው ዓይነ ጥላ አብሮ በማደግ፣ችግሩን ወደ ሌላ ጥግ በመውሰድ በስውር እንደተተናኮለን ይቀጥላል፡፡
ዓይነ ጥላ በሰዎች ዓይን ላይ ሲቀመጥ ወንዶች መልከኛ ሴቶች ሲያዩ፣ሴቶች መልከኛ ወንዶችን ሲያዩ የራሳቸው ሰው እያላቸው በማየት በመመኘት ይቅበዘበዛሉ፣ሲያዩ ድንገት የመደንገጥ እና የልብ ትርታቸው ሲጨምር ይሰማቸዋል፣መልኳ፣ቁመናዋ ያማረ፣ዳሌዋ የተሰደረ ሴት ሲያዩ ለማናገር ይጓጓሉ፣አይተው ከዓይናቸው ርቀውም ሲሄዱ በዓይናቸው ይከተሏቸዋል ይሸኟቸዋል፡፡ የዚህ መንፈስ አንዱ ብልግናው እና አለማፈሩ በቤተክርስትያን ውስጥም በምኞት ያቅበዘብዛል፣ዓይን ያንከራትታል፡፡
ከላይ ያየናቸው ምልክቶችም የዝሙት መንፈስ ዓይን ላይ ሲቀመጥ የሚገለጥበት ሰውን የሚያቅበዘብዝበት ጠባዩ ነው፡፡ የዝሙት መንፈስ ዓይን ላይ ሲቀመጥ ከዓይነ ጥላ የሚለይበት ጠባዩ የዝሙት መንፈስ ያየናትን ሴት ወይም ያየነው ወንድ ያለ ምንም ምክንያት እና ያለ ተግባቦት ያስወድደናል፡፡ በማየት ብቻ በፍቅር እንወድቃለን በቀላሉ ለዝሙት እንዳረጋለን፡፡ ዓይነ ጥላ ግን ዓይን አዋጅ በማድረግ ፍጥጫ እንጂ ምርጫ እንዳይኖረን በማየት ፍላጎት ብቻ ያቅበዘብዘናል፡፡
ዓይን ላይ የተቀመጠው የዝሙት መንፈስ ጥቃቱ ያየናቸውን በማስወደድ ለዝሙት መጋበዝ ሲሆን ዓይነ ጥላ ግን ያየነውን ግን የማናገኘውን የእኛ ሊሆን የማይችለውን በማስመኘት በዓይን አምሮት ማቅበዝበዝ ነው ሥራው፡፡
ሴቶቹም ዓይነ ጥላው ዓይናቸው ላይ ከተቀመጠ እጮኛ፣የትዳር አጋር እያላቸው ሌላ ወንድ በማየት በምኞት እንዲቅበዘበዙ ያደርጋቸዋል፡፡ ዓይናቸውን መቆጣጠር፣ልባቸውን መግዛት አይችሉም፡፡ የሚገፋው ሌላ ነውና፡፡ ሁለት የሚዋደዱ እጮኛሞች አብረው ሻይ ቡና እያሉ አንዱ አጠገቡ ያስቀመጣትን ትቶ ሌላ አሻግሮ የሚያየው ዓይን ላይ በተቀመጠ አቅበዝበዥ ዓይነ ጥላ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ መሰሪ፣ሕይወት ቀባሪ ዓይነ ጥላ ስንቱ ተጣልቶ ተለያይቶ ቀርቷል፡፡
ቅዱስ ወንጌል ‹‹ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል›› ይላል ዓይነ ጥላ ደግሞ ዓይንና ልብ ላይ ሆኖ በምኞት ያቅበዘብዘናል፣በምኞት በሐሳብ በፍትወት ያቃጥላል፡፡ /ማቴ 5÷28/ እዚህ ላይ ልብ ልትሉት የሚገባው አይቶ መመኘት በዓይን ምክንያት የሚመጣ የምኞት ኃጢአት ነው፡፡ ስለዚህ ሰው በዓይን ዓይቶ መመኘት በሥጋዊ ጠባይ እና በዓይነ ጥላና በዝሙት መንፈስ ምክንያት ከመመኘት አልፎ በልቡ ሊያመነዝር ይችላል፡፡
እንደ ቅዱስ ወንጌሉ ማየት ኃጢአት አይደለም፡፡ አይቶ በልብ ተመኝቶ በፍትውት ሲቃጠል ነው ማመንዘር የሚሆነው፡፡ በዚህ በምኞት ፍትወት የምንሰቃየው ሰዎች ይህን ችግር ለመቅረፍ ከራሳችን ጋር ብዙ ሞክረናል ግን አልሆን ይለናል፡፡ አንዳንዶቻችን እራሳችንን ነፃ ለማውጣት ‹‹መልክ አየሁ እንጂ ምን አደረኩ›› እያልን ለመንፈሱ ሽፋን እንሰጠዋለን፡፡
ተወዳጆች ሆይ ዓይነ ጥላ ዓይናችን ላይ እየተቀመጠ፣እያቀላወጠ የዓይን ተቅበዝባዥ ስለሚያደርገን በጊዜ ካልነቃንበት፣በጾም በጸሎት በስግደት ካልተዋጋነው መልሰን የማናገኛቸውን ነገሮችን በማበላሸት እና በማኮላሸት የጨለማ ሕይወትን ያጎናጽፈናል፡፡ ሳንቀደም ልንቀድመው ይገባል፡፡ ከተቀደምንም ከእግዚአብሔር ጋር ድሉ የእኛ ስለሆነ ልንበረታበት ይገባል፡፡
ዓይን ላይ ለሚቀመጥ ዓይነ ጥላ አንዱ ፍቱን መድሃኒቱ ካህናት አባቶቻችን ጋር በመሄድ ንጹህ ቅብዓ ቅዱስ ብንቀባ መንፈሱ ከዓይናችን ላይ ይነሳል፡፡ ከተቻለ በበጋ ላይ አትገኝም ወይም አትመነጭም እንጂ ጻድቃኔ ማርያም የዓይን ጸበል አለ እሱን ዓይናችን ላይ በመቀባት መፍትሔ እናገኛለን፡፡ እንደውም አባቶቻችን በትውፊት እንደሚነግሩን ጻድቃኔ ማርያም ያለው የዓይን ጸበል እመቤታችን ‹‹በስደቴ ጊዜ ያለቀስኩት እንባ ትሁን›› ብላለች፡፡ እኔም እዛ በነበርኩበት ዓመታት በዓይን ጸበልዋ ብዙ ሰው ከዓይን ሕመምና ከዓይነ ስውርነት ሲድኑ አይቻለሁ፡፡
‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› ት.ኢሳ 53÷8
አንብበው ሲጨርሱ በችግሩ ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሼር በማድረግ ያዳርሱ፡፡
ክፍል አሥራ አምስት
ዓይነ ጥላ እና ግለ ወሲብ በወንዶች እና በሴቶች ላይ
/ኃጢአተ አውናን/
/ያልተቀሰፈው አግዚአብሔር የታገሰው ትውልድ/
ይቀጥላል …
👍 1
ክፍል አራት
ዓይን ላይ ተቀምጦ በፍትወት ምኞት የሚያቅበዘብዝ ዓይነ ጥላ
/ፍጥጫ እንጂ ምርጫ እንዳይኖረን የሚያደርግ የወጣቱ ችግር/
ተወዳጆች ሆይ በክፍል ሦስት ዓይነ ጥላ የራሱን ባሕርይ ከእኛ ጋር በማጣባት እኛን በመምሰል የማንፈልገውን በመናገር በመተግበር እንዴት እንደሚዋጋን በዝርዝር አይተናል፡፡ አሁን ደግሞ የብዙዎች ችግር የሆነውን እንመለከታለን፡፡
እስኪ ዓይን ላይ ስለሚቀመጥ ዓይነ ጥላ ከማየታችን በፊት የቀድሞ የውድቀት ታሪካችን ከዓይን ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ እንመልከት፡፡ ሰይጣን ሔዋንን ከጣለበት ዋነኛው ስልቱ በእግዚአብሔር አትብሉ የተባሉትን ዕፀ በለስ ለሔዋን ዓይኗ ላይ ቁጭ ብሎ የሞት ሞት ትሞታላችሁ የሚለውን ሕግ አስረስቶ፣እግዚአብሔርን የመሆን ምኞትን አጉልቶ በማሳየት ነው፡፡ ሰይጣን ምን ያህል ዓይኗ ላይ ቁጭ ብሎ እንድትበላ ያጓጓት፣ ይገፋፋት እና ያቅበዘብዛት እንደነበር ሙሴ በኦሪቱ ላይ ‹‹ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፣ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፣ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች›› ይላል፡፡ /ዘፍ 3÷6/
እዚህ ላይ ካስተዋልን ሰይጣን የሔዋን ዓይን ላይ ቁጭ ብሎ የሞት ዕፀ በለስን የሕይወት አድርጎ በማሳየት ብሎም በመጓጓት እንዳስበላት ነው፡፡ ሰይጣን ዓይኗ ላይ ቁጭ ብሎ የሞት አዋጅ የታወጀበትን ዕፀ በለስን መልካም እንደሆነ በማሳየት ለሞት ዳርጓቸዋል፡፡ ‹‹ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ›› የተባለው ሰይጣን ዓይኗ ላይ ቁጭ ማለቱን የሚገልጥ ነው፡፡
ስለዚህ ሰይጣን አሁን እኛ የምንኖረውን የውድቀት ሕይወት ዓይን ላይ ተቀምጦ፣ዕፀ በላስን አሸምጥጦ በማስበላት ያመጣብን ጣጣ ነው፡፡ ሁል ጊዜ ሰይጣን ነገሮችን ገልብጦና አጉልቶ በማሳየት ነው ለውድቀት የሚዳርገን፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ‹‹ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች›› ያለው ኃጢአት ብሎም ሞት የሚመጣው በዓይን ፈተና ስለ ሆነ ነው፡፡ /ያዕ 1÷15/ የአብዛኛው ኃጢአት መነሻው በዓይን ከማየት ነው፡፡
ወዳጆቼ ዓይን ለአብዛኞቹ ርኩሳን መናፍስት መግቢያና መውጫ ነው፡፡ በተለይ እንደ ቡዳ፣የዛር ቡዳ እና የዝሙት መንፈስ ዓይንን ማዕከል በማድረግ ነው ጥቃት የሚሰነዝሩት የሚተናኮሉት፡፡ በሰው ውስጥም ሲገቡ መግቢያቸው ዓይን ነው፡፡
ከዚህ በፊት እንዳየነው ዓይነ ጥላ ዓይናችን ላይ ሲቀመጥ ከውስጥም ከውጭም ለመተናኮል ይቀለዋል፡፡ ዓይን ላይ የሚቀመጥ ዓይነ ጥላ በተለይ ወጣቶችን፣እጮኛሞችንና በላ ትዳሮችን ያጠቃል፡፡ ለምሳሌ ዓይናችን ላይ ዓይነ ጥላ ሲቀመጥ ከውጭ የምናያቸው ነገሮች ለሰዎች መልካም ናቸው ለእኛ ግን መናኛ መስለው ይታዩናል፡፡ የሰዎች በተለይም የቅርብ ያልናቸው ሰዎች፣እጮኛችን፣የትዳር አጋራችን ያላቸው ተክለ ሰብዕና፣ቁመና፣ቁንጅና፣መልካም ጠባይ ወዘተ ለእኛ በዓይነ ጥላው ምክንያት ተገልብጦ ስለሚታየን አንደሰትበትም፣አይጥመንም፡፡ ይባስ ብለን ያልሆነ አቃቂር በማውጣት ማጥላላት እንጀምራለን፡፡
ዓይነ ጥላችን መልካም ሰዎችንና መልካም ነገሮችንና መልካም እዕድሎችን በመጥፎ መልኩ ገልብጦ ስለሚያሳየን አእምሮችን ከዓይነ ጥላው የተቀበለውን የተሳሳተ እይታ፣በመጥፎ ግንባታ ስሎ ያሳስበናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰውን ቀርባችሁ ስታዩት ፊቱን ወይም የፊቱን ቅርጽ ብቻ በማየት ሙልጭ ያለ ነገረኛ፣ሌባ ሊመስላችሁ ይችላል፡፡ አንዲትን ሴት ስታይዋት ሴሰኛ/ወንድ አውል/ ልትመስላችሁ ትችላለች፡፡ አንድን ሴት ስታይዋት ስለ እሷ የሌላትን ክፉና ነውረኛ ጠባይ ያላት ይመስላችኃል፡፡ ወንዱንም እንደዛው፡፡
ዓይነ ጥላ ዓይናችን ላይ ሲቀመጥ ስለ ሰዎች ያለ ምንም እውቀት እና ምክንያት ሰውን በመጥፎ ስነ ምግባረቸው ልንስላቸውና ልንጠላቸው እንችላለን፡፡ አንዳንዴ አንድ ሰውን ስናየው ዓይነ ውኃው ደስ ስለማይለን እንኳን ልናናግረው ለማየት እንጠየፋለን፡፡ ብዙ ሴቶች ለእጮኝነት የሚጠይቃቸውን ወንድ ያለ ምክንያት የሚጠሉት ዓይናቸው ላይ ባለው ዓይነ ጥላ ምክንያት ነው፡፡ ዓይናቸው ላይ ቁጭ ብሎ ‹‹ኤጭ..ሲናገር፣ሲያየት፣ሲራመድ፣ምኑም አይጥምም፣ሲያስጠላ›› የሚሉት ዓይናቸው ላይ ያለው ዓይነ ጥላ ሰውዬውን ሲጠላ ነው፡፡ በዚህም ዓይነ ጥላው ወደ እነሱ ለትዳር የሚመጣውን ሰው በስውር የመከላከልና የማባረር ሥራን ይሠራል፡፡
ወንዶቹ ላይ የሚቀመጠው ዓይነ ጥላም መልከኛዋን እንደ መልከ ጥፉ፣ትዕግስተኛና መልካምዋን ሴት እንደ ነገረኛ እና እንደ ነውረኛ በማስመሰል ሲለሚያሳያቸው ከሴት ወደ ሴት በምኞት እና በተግባር ያቅበዘብዛቸዋል፡፡
ተወዳጆች ሆይ መጽሐፍ ቅዱስ ዓይንን የሰውነት መብራት በማለት ነው የሚገልጸው፡፡ እንዲህ ይላል ‹‹የሰውነትህ መብራት ዓይን ናት፡፡ ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፡፡ ዓይንህ ታማሚ ብትሆን ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል፡፡ እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፣ጨለማውስ እንዴት ይበረታ›› በማለት ያስቀመጠልንን ከዓይነ ጥላ አንፃር እንይ፡፡ /ማቴ 6÷22-23/ ወንጌሉ እንደሚነግረን የሰውነት መብራት የሆነው ዓይን ላይ ዓይነ ጥላ ከተቀመጠ ሕይወታችንና ሁሉንም ነገራችንን ያጨልማል፤ ጨለማውንም ያበረታብናል፡፡
ዓይን የሰውነታችን መብራት ስለሆነ ሁሉንም ነገር በቀላሉ ማከናወን እንችላልን፡፡ ግን በዓይናችን ላይ ዓይነ ጥላው ሲቀመጥ ብርሃን የሆኑ የሕይወት መንገዳችን የቀን ጨለማ ይሆንብናል፡፡ ለሰው ብርሃን የሆኑት ነገሮች ሁሉ እኛ ጋር ሲደርሱ ጨለማ ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ ዓይናችን ለዓይነ ጥላ የመዋግያ ጥሩ ይዞታ ይሆንለታል፡፡ ከዓይናችን ላይ በመነሳት አጥፍቶ ጠፊ ይሆናል፡፡ እኛንም ያጠቃል የእኛ የሚሆኑትንም መልካም ነገሮች ያርቃል፡፡ በሴቶች እህቶቻችን ዓይን ላይ ሲቀመጥ ለትዳር የሚሆናቸውን ወንዶች ለመምረጥ ዓይናዋጅ ያደርግባቸዋል፡፡ ለምርጫ ይቸገራሉ፡፡ በወንዶቹም ላይ ሲቀመጥ እንደዛው ይሆናሉ፡፡
ተወዳጆች ሆይ እስኪ ዓይነ ጥላ ዓይናችን ላይ ሲቀመጥ የመገለጫ ባሕሪውን እንመልከት፡፡ ዓይናችንን ያለ ሕመም ያለቅሳል/እንባ ይፈሰዋል/፣ያቃጥለናል፣ዓይናችን ባልታወቀ ምክንያት ይደፈርሳው በሚገርም ሁኔታ ውበቱን ያጣል፣ይቀላል፣ይደፈርሳል፣የእይታ ችግር ይኖርብናል/ ሰው፣ፊደል፣ቁስ፣በቅርቡ ያሉ ነገሮችን መለየት አንችልም/፣ ዓይናችን ሳናስበው ፍጥጥ ይላል፣መቀቆጣጠር የማንችለው እርግብግቢት ይኖረዋል፣አባቶችን ማየት እንጠላለን፣እንንቃለን፣ለሰው የማይታይ ግን ለራሳቸው የሚታይ ምስል ለምሳሌ ለየት ያለ፣የሚያስፈራ ሰው ወይም አውሬ መሰል ነገር እናያለን፣የማናውቀው ነገር ውልብ ሲል እናያለን/ይህም ዓይነ ጥላው ፍራቻ ውስጥ ለመክተት የሚጠቀምበት ስልቱ ነው/፣ዓይናቸው ከተፈጥሮ ውጪ ፈጦ ወደ ውጭ የሚወጣ ይመስላል በዚህም ዓይነ ጥላው የአስፈሪነት ፊትን ያላብሳናል፣የተረጋጋ እይታ የለንም ከሰው ጋር ቁጭ ብለን እያወራን በደቂቃ የተለያየ ቦታ እናማትራለን በዚህም ዓይነ ጥላው በሌላ ሰው የመጠርጠርንና የማፈንገጥን ስሜት ለማሳደር ይጠቀምብናል፣እንዳንታመን ያደርገናል፡፡ ይህ ስልቱ እጮኛሞች የተዋወቁና አብረው ቁጭ ብለው በሚነጋገሩበት ጊዜ አንድነታቸውን ከጅምሩ ለማኮላሸት የሚጠቀምበት ዘዴው ነው፡፡ በዚህም በቀበዝባዛነት እና በሴሰኝነት ምስል ለማሳየት ይጠቀምበታል፡፡
ዓይነ ጥላ ተማሪዎች ላይ ዓይናቸው ላይ ሲቀመጥ ደብተራቸው፣ብላክ ቦርድ ላይ ያለውን ፊደል መለየት አይችሉም፣ፊደል ሲያዩ በከፍተኛ ሁኔታ ዓይናቸውን ይቆጠቁጣቸዋል፣ያስለቅሳቸዋል፣ያቃጥላቸዋል፡፡ ትምህርት ሲማሩ በክፍል ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በእንቅልፍ ይ
👍 1
Repost from መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿
በኃላ ጥፋት ያለውን ፍንትው አድርጎ የሚያሳያቸው፡፡ እየተዋደዱ በፍጹም በነገሮች መግባባት የማይችሉት የዛሬን ፍቅር እና የነገን ትዳር በማይወደው በዓይነ ጥላው ምክንያት ነው፡፡
ይህ ዓይነት ባሕርይ ዓይነ ጥላው በባለትዳሮች መሐል፣ለጠብ ብሎም ለመለያየት ይጠቀምበታል፡፡ ሚስት ለባል አንድ ነገር ከነገረችው ባል ሆዬ ሚስት ባላሰበችው ሳይሆን ፍጹም ባልገመተቸው መንገድ ተርጉሞ ለጭቅጭቅ እና ለጠብ ያደርገዋል፡፡ በባል ውስጥ ያለው ዓይነ ጥላ የሚስትን ንግግር እንደ ሕንድ ፊልም ተርጓሚ ገልብጦ ያሳየዋል፡፡ ሚስቱን እንዳያምናት እንዲጠራጠራት ያደርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ ለዓይነ ጥላው ለመለያየት መሠረት የሚጥልበት አደገኛ መንገዱ ነው፡፡
ሚስት ላይ ያለው ዓይነ ጥላ ደግሞ ባል ገና ቤቱ ገብቶ ሰውነቱን እንኳን በአግባቡ ሳያሳርፍ ዓይነ ጥላዋ እሳት ልሶ እሳት ጎርሶ ይጠብቀዋል፡፡ በማግባትዋ የተበሳጨው አጋንት በመለያየት ለመደሰት ትንታግ ምላሱን ባል ላይ ይዘረጋል፡፡ ባልም ይናገራል አልያም ይመታታል፡፡ አብሮን በስውር የኖረው ዓይነ ጥላ በትዳራችን መሐል በጠብ በጭቅጭቅ የፍቅር ጠንቅ ይሆናል፡፡ ዓይነ ጥላ ያለባቸው ባለትዳሮች በጠብ ጊዜ ተናግረው አይወጣላቸውም ወይም ተሳድበው አይረኩም፡፡ እየተርገፈገፉ ስሜታቸውን ቁጣቸውን መቆጣጠር አይችሉም፡፡ አባቶች ‹‹ቁጡ እና ኃይለኛ ሰው ሙት ቢያስነሳም አይደነቅም›› ይላሉ፡፡
ወዳጆቼ ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ የትዳር ፍቺ በዘመናችን በዝቷል፡፡ የማያረጋጋ መንፈስ ተሸክመን የተረጋጋ የትዳር ሕይወት መኖር አልቻልንም፡፡ ብዙዎች የትዳር አጋራቸውን ችግር ዓይነ ጥላቸው ከፍ አድርጎ እያሳያቸው፣ቢፋቱ የተሻለና ሰላማዊ ሕይወት የሚኖሩ አስመስሎ እያሳሰባቸው ለፍቺ ይዳርጋቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላ እርስ በእርስ አላግባባ ብሎን ቢያፋታን ምን ዓይነት ዓይነ ጥላዊ ጥቅም ያገኛል? ብንል፡፡ አንድ ትዳራችንን በማፋታት ይለያየናል፡፡ ሁለት በቅዱስ ቁርባን ካገባን ቅዱስ ቁርባናችንን ያፈርሳል፡፡ ሦስት ልጆቻችንን ይበታትናል፡፡ አራት ቤተሰብ ከቤተሰብ በመለያየት ያራርቀናል፡፡ አምስት የትዳር በረከታችንን ያሳጣናል፡፡ ስድስት በትዳር ፍቺ ምክንያት መንፈሳዊ ሕይወታችንን ችግር ውስጥ ይከታል፡፡ ሰባት ግላዊ ሕይወታችንን ያቃውሳል፡፡ ስምንት ሌላ ትዳር እንድንይዝ በማድረግ ሰማያዊ ክብራችንን ያሳጣናል፡፡ ዘጠኝ ለዘላለም ትዳር ጠል ሆነን እንድንኖር ያደርገናል፡፡ አሥር የተስፋ መቁረጥ ሕይወት ውስጥ ይከተንና ዘማዊ ጠጪ ሰካራም በማድርግ ለተመሰቃቀለ ሕይወት ይዳርገናል፡፡ አሥራ አንድ ልጆቻችንን በአግባቡ እንዳናሳድግ ያደርገናል፡፡ አሥራ ሁለት የትዳራችንንና የልጆቻችን ደስታ በማሳጣት ለከፋ ሕይወት ይዳርገናል፡፡ ወዳጆቼ ይህ ሁሉ የሕይወት ጣጣ ባለመግባባት የሚመጣ ነው፡፡ የትዳር ጠንቅ የሆነው ዓይነ ጥላ የጣላቸው ብሎም ያለያያቸው እንኳን ሽማግሌ ጳጳስ ቢመጣም አይታረቁም፡፡ ጸጸቱና ቁጭቱ የሚመጣው ትዳሩ ሲፈርስ፣ልጆች ሲበተኑ ነው፡፡
በአንድ ወቅት ከሚስታቸው ጋር በመጣላት ሰላማቸውን ያጡ ካህን የቤት ጠባቸው ወደ ውጭ ወጥቶ ዘመድ ጎረቤት ተሰብስቦ አስታርቁዋቸው፡፡ ግን ሳምንት ሳይሞላ ተመልሰው ተጣሉ፡፡ ነገሩ እየከረረ ጠባቸው ከሳምንት ወደ እለት ተእለት ተቀይሮ ለሸምጋይ አስቸገረ፡፡ ታድያ በሚስታቸው ጭቅጭቅ የመራራቸውን ካህን ሽማግሌዎች ሊያስታርቋቸው ሲመጡ ‹‹አባቶቼ በሽምግልናው አትድከሙ እናንተ አስታርቃችሁን ስትሄዱ አጅሬ ሹልክ እያለ እየገባ ነው ሰላሜን የሚነሳኝ፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ሚስቴን ሳይሆን ያን ስመ አይጠሬ መናጢውን ታግሼ እኖራለሁ እንጂ ሌላ ምን አደርጋለሁ›› አሉ ይባላል፡፡ እኚህ ካህን ቢያንስ የትዳራቸውን ጠንቅ በማወቅ እግዚአብሔር አንድ መፍትሔ እስኪሰጣቸው መታገሳቸው በራሱ አንድ መፍትሔ ነው፡፡ ይህ ዓይነት ብልሃት በእኛ ዘንድ ስለሌለ መፋታት እንደ መፍትሔ ተወሰደ፣ትዳሩም ተናደ፡፡
ሌላው አብሮን አሸምቄ ተደብቆ የኖረው ዓይነ ጥላ ደህና ሥራ ጀመርኩ ብለን ሥራ መሥራት ስንጀምር በተለያየ ምክንያት ከአለቃችን ከሥራ ባልደረባችን ጋር ማጨቃጨቅ፣ማነታረክ ይጀምራል፡፡ በዚህ ብስጭት ወይ ሥራውን እንተዋለን አልያም እንደ ተጠማመድን እንቀጥላለን፡፡ ፍቅርን፣አንድነትን የሚጠላው ዓይነ ጥላ እኛ ላይ አልያም አሠሪያችን ላይ በመሆን በሰውዬው ባሕርይ ግልጽ ጥላቻውን ይጀምራል፡፡ ተግባብተን መሥራት ሞት እስኪመስለን ድረስ ያከብድብናል፡፡ በዚህ ዓይነ ጥላ ጠባይ በሥራ ባልደረቦቻችን ዘንድ መጠላትን እናተርፋለን፡፡ በሥራ ታታሪ ብንሆንም አንመሠገንም፡፡ ዓይነ ጥላው በሥራ ምክንያት የሚመጣልንን የእድገት፣የሥልጣን፣የትምህርት እድል ባለመግባባታችን ያሳጣናል፡፡
አንዳንዶቻችን በትምህርት ሕይወታችን ከተማሪዎች ጋር መግባባት እንዳይኖረን ከሰው በማራቅ የብቸኝነት ሕይወትን እንድንመርጥ ያደርገናል፡፡ ይህ ጠባያችን ሲያድግ በነገ ሕይወታችን ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል፡፡
ዓይነ ጥላው እጅግ ክፉ ከመሆኑ የተነሳ ከወላጅ እናት አባታችን ከወንድም እህቶታችን ጋር በፍጹም ላያግባባን ይችላል፡፡ ወላጆቻችንን እንደ በዳይ አድርጎ በማሳየት፣በአስተዳደጋችን ምንም ውለታ እንደሌለብን አድርጎ በማሳየት ቤተሰባችንን እንድንጠላ ያደርገናል፡፡ ቁም ነገር ቦታ ስንደርስ ቤተሰባችንን እንዳንረዳ በድለው እንዳሳደጉን እያሳሰበ ከቤተሰብ ያርቀናል፡፡ በእንዲህ ዓይነት ክፉ ጥንውት ውስጥ ገብተን ነገ አግብተን ብንወልድም ዓይነ ጥላው የዘራነውን በልጆቻችን ያሳጭደናል፡፡
ወዳጆቼ በየትኛውም ሕይወታችን ከተፈጥሮ ባሕርያችን ያፈነገጠ ድንገተኛ የባሕርይ ለውጥ በራሳችን ላይ ስናይ ቆም ብለን እናስብ፡፡ ዓይነ ጥላው ከሰዎች ጋር እንዳንግባባ በማድረግ ከሰው ተገልለን፣ተለይተን ‹‹እኔ ከሰው ጋር መኖር አልችልም›› ወደሚል እሳቤ ውስጥ ይከተንና ሰው በሚኖርበት ዓለም እየኖርን ሰው አልባ ያደርገናል፡፡ ሕይወታችንንም ባዶ ያደርግብናል፡፡ ከሰው ተግባብተው መኖር ያቃታቸው ሰዎች ብቸኝነትን እንደ መደበቅያ ዋሻ ያደርጉታል፡፡ ብቸኝት ሲብስ ለአእምሮ ህመም፣ለስነ ልቦና ችግር ብሎም ለእብደት እና እራስን ለማጥፋት ይዳርጋል፡፡ ስለዚህ ባለ ትዳሮች፣እጮኛሞች፣ጓደኛሞች በመሃላችሁ ውሃ የማያነሳ አለመግባባት ሲፈጠር ቆም ብሎ ማሰብ፣መታገስ፣ነገሩን በመንፈሳዊ ዓይን በመቃኘት ማጤን አለብን፡፡ እራሳችንን መግዛት፣የቁጣ፣የንጭንጭ ባሕርያችንን ለመግታት ከሞከርን ዓይነ ጥላው ወደ ከፋ ደረጃ አይደርሰንም፡፡ መንፈሳዊ ሰው መሆን አንዱና ትልቁ ጥቅም መለኮታዊ ዋስትና ጥበቃ ማግኘት ነውና በመንፈሳዊ ሕይወታን ከበረታች ሠልፉ የእኛ ነው ድሉ የእግዚአብሔር ነው፡፡
ክፍል አራት
በሰው እንድንጠላ፣የሚያደርግ ዓይነ ጥላ!
/ነገአችንን የሚበለሽ የሚያኮላሽ/
ይቀጥላል ….
Repost from መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿
ክፍል ሦስት
ከሰው የማያግባባ ዓይነ ጥላ
/ሰው አልባ፣ሕይወት አልባ የሚያደርግ/
የእጮኛሞች፣የባለ ትዳሮች፣የጓደኛሞች ፈተና
ወዳጆቼ በክፍል ሁለት ሴቶችን በተለይ መልከኞችንና ወንዶችን ዓይነ ጥላ እንዴት ባለ የፈተና ስልት ትዳር አልባ በማድረግ ከትዳር ዓለም እንደሚያርቃቸው፣ለትዳር የሚጠይቃቸውን ሰው እንዴት እንደሚመልስባቸው ተመልክተናል፡፡ በዚህ በክፍል ሦስት ደግሞ ሰውን ከሰው ስለማያግባባው፣ሰውን ከሰው ስለሚያጣላው፣በመጨረሻም ሕይወት አልባ ስለሚያደርገው ዓይነ ጥላ እንመለከታለን፡፡ የአባቶቻችን አምላክ ምስጢሩን ይግለጥልን፡፡
ብዙዎች ‹‹ይህን ያህል በአጋንንት ለምን እፈተናለሁ፣አጋንንትማ በእኔ ላይ ስልጣን የለውም›› ይላሉ፡፡ አጋንንት በንስሐ ተወስኖ የማይኖር ሰው ላይ፣በጸሎት ተግቶ የማይኖር ሰው ላይ፣በቅዱስ ቁርባን መለኮታዊ ጸጋ የማይኖር ሰው ላይ በጾም በስግደት ያልበረታ ሰው ላይ ሁሌም አጋንንታዊ የበላይነት አለው፡፡ አጋንንት አይዘናጋም፣የተንኮል ሥራውን በአግባቡ ያውቃል፡፡ እኛ አንድ ሳምንት ብንጸልይ ለአንድ ወር ጸሎት እንተዋለን፡፡ ጸሎታችንም በሥጋዊ ሥራ ምክንያት ‹‹እግዚአብሔር የማያውቀው የለም›› እያልን ጸሎት የማንጸልይ ሰነፎች ነን፡፡
እግዚአብሔር የሚያውቀን ስንጸልይ ነው፡፡ እግዚአብሔር መከታ ከለላ የሚሆነን በጸሎት ወደ እርሱ ስንጮህ ነው፡፡ ይህንን ባላደረግንበት አግባብ፣አጋንንት የሕይወት ግብግብ ቢገጥመን አይደንቅም፡፡ አጋንንት እኛን በተለያየ ነገር በመዋጋት የእግዚአብሔር ሰው እንዳንሆን፣መንፈሳዊ ጸጋዎችን እንዳናገኝ፣በተሰጠን እንዳንጠቀም የማበላሸት እና የማኮላሸት ሥራ ይሠራል፡፡ ምክንያቱም አጋንታዊ ጥንታዊ ሥራው ነውና፡፡
ወዳጆቼ አጋንንት እኛን ማሰቃየት፣ሕይወታችንን ማበላሸት በእኛ አልጀመረም፣መተናኮልን በእኛ እየተለማመደ አልኖረም፡፡ ይልቁንም በሰማይ ቤት የአዳምና የሔዋንን የሰማይ ሕይወት የማጨለም ልምዱን ይዞ ነው ወደ ምደር መጥቶ በእኛ በአዳምና በሔዋን ልጆች አጋንንታዊ የበቀል መከራውን የሚያሸክመን፡፡ ከዚህ ጥንታዊ ክፉ ጠላታችን ጋር ለመዋጋት የፈተና ስልቱንና ተንኮሉን ማወቅ ለእኛ የማንቅያ ደውል ስለሆነ የክፋት ጠባዩን ስናውቅ ነው ለመዋጋት የምንችለው፡፡ ተንኮሉን ስናውቅ ነው የሕይወታችንን መሠረታዊ ችግር የምናውቀው፡፡ ተንኮሉን ስናውቅ ነው አጋንንትን ከስም በላይ በሆነ የተንኮል ተግባሩን የምናውቀው፡፡ ስለ አጋንንት ውግያ ስጽፍላችሁ ገድሉን ሳይሆን ተንኮሉን እንድታውቅ መሆኑን እወቁ፡፡ እንግዲህ ይህንን ክፉ የሕይወት ጠላት ይዘን ነው ተዘናግተን የምንኖረው፡፡
ተወዳጆች ሆይ ከዓይነ ጥላ አስከፊ እና መጥፎ ጠባይ አንዱ ሰዎችን ከሰዎች ጋር ያለማግባባት ተንኮሉ ነው፡፡ በተለይ ከቤተሰቦቻችን ጋር፣ከትዳር አጋራችን ጋር፣ከሥራ ባልደረባችን ጋር፣ከእጮኛችን ጋር፣ከጓደኛችን ጋር በምክንያት እና ያለ ምክንያት እንዳንግባባ ያደርገናል፡፡ ካልተግባባን ደግሞ መስማማት አንችልም፡፡ ካልተስማማን ደግሞ አብረን መቀጠል አንችልም፡፡ ስለዚህ መራራቅን መለያየትን እንደ መፍትሔ እንወስዳለን፡፡ ይህ በውስጣችን አሸምቆ የኖረው ዓይነ ጥላ አንዳንዱን እንኳን ከሰው ከራሱም አያግባባውም፡፡ ወዳጆቼ ስንት ሰዎች አለን የራሳችንን ባሕይር የማናውቅ፡፡ ስንት አለን ወጥ የሆነ ባሕርይ ሳይሆን እንደ በጋና እንደ ክረምት ለሰው የሚሞቅ እና የሚቀዘቅዝ ያልታወቀ ባሕርይ ያለን፡፡
ዓይነ ጥላው በሰዎች ውስጥ ያለመግባባትን ሴራ የሚሠራው በሁለት መንገድ ነው፡፡ አንድኛው ከማኅፀን ወይም ከልጅነታችን በመዋረስ ጠባያችንን በማቃወስ የሚጠቀምብን ሲሆን፡፡ ሁለተኛውና የብዙዎቻችን ችግር የሆነው ከጊዜ በኃላ የመጣብን አላስፈላጊ የባሕርይ መገለጫችንን በመጠቀም ነው፡፡
ወዳጆቼ እግዚአብሔር ከሰጠን ጸጋዎች ውስጥ አንዱ የባሕርይ ጸጋ ነው፡፡ ይህም ከሰው ተግባብተን ተስማምተን የምንኖርበት ትልቅ ጸጋ ነው፡፡ ሰው ይህን ጸጋ ሲያጣ ከማንም ጋር መግባባት አይችልም፡፡ የሰው ልጅ ባሕርይ እንኳን ሰው ግሩማን የሚሆኑ የሚያስፈሩትን አራዊትን ማግራት መግዛት ብሎም አብሮ መኖር ያስችለዋል፡፡ ይህንን የቅድስና ጸጋችንን ያኔ በገነት ጸጋችን ሲገፈፍ ጥለነው ስለመጣን ዛሬ በራሳችን መልካም ባልሆነ ባሕርይ ተጠቅተን ተሰቃይተን ሰውንም ስናሰቃይ እንታያለን፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ለሰው ልጆች ‹‹ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ›› ብሎ የቅድስና ባሕርይን እንድንላበሰ አክብሮ ሰጥቶናል፡፡ / ዘሌ 19÷2/
ከልጅነታን የሚዋረሰን ዓይነ ጥላ ለወደፊት ተንኮሉ እንዲመቸው ከልጅነታን የጭቅጭቅ፣የጠብ፣የኩርፊያ፣የእልከኝነት፣የእንቢተኝነት፣የአልሸነፍ ባይነት፣እኔ ያልኩት ካልሆነ በማለት የራሱን የጠባይ መገለጫ ውስጣችን በማስረጽ ነውጠኛ ሰው ያደርገናል፡፡ እነዚህን ያልተወደዱ ባሕርይ ይዘን እናድግና ከፍ ስንል ለራሳችን የራሳችን ባሕርይ ግራ እስኪገባን ድረስ ከሰው ጋራ ጥሩ ተግባቦት እናጣለን፡፡ ለዚህም ነው አንዳንዶቻችን ጥሩ መንፈሳዊ ሰው ለመሆን እንፈልግና መንፈሳዊ ጠባይ ግን አይኖረንም፡፡
ዓይነ ጥላው በስውር የራሱን የክፋት ባሕርያት በእኛ ውስጥ ያሳድጋል፡፡ ቤተሰቦቻችን ‹‹ጠባዩ ነው፣እሱ/እሷ ከልጅነት ኃይለኛ ነው/ናት›› እያሉ ስለተስማሙ ለባሕርያችን እውቅና እየሰጡን እናድጋለን፡፡ እራሳችንን ችለን ከሰዎች ጋር፣ከጓደኛና ከቤተሰቦቻችን ጋር በፍጹም መግባባት አንችልም፡፡ የእኛ በሚመስል ግን በዓይነ ጥላው ባሕርይ ስም ይሰጠናል፡፡
ሁለተኛው ድንገት የባሕርይ ለውጥ እናመጣለን፡፡ ሳናውቀው የኃይለኝነት፣የቁጣና እኔ ያልኩት ወደሚል አደገኛ የባሕርይ ጥንውት ውስጥ እንገባለን፡፡ ከዛማ በሆነው ባልሆነው መቆጣት፣መነጫነጭ የዘወትር ሥራችን ይሆናል፡፡
ይህ የባሕርይ አስከፊ ገጽታችን ወደ እኛ የሚመጡትን መልካም ነገሮችን ያሳጣናል፡፡ ዓይነ ጥላው እኛ ላይ ቁጭ ብሎ በቁጣ መንፈስ፣ማሕበራዊ ተግባቦታችንን ማቃወስ ይጀምራል፡፡ የሚያሳዝነው ዓይነ ጥላው ሰዎች የተናገሩንን መልካም ነገሮች ገልብጦ በማሰማት፣በሌላ አቅጣጫ በመተርጎም ለጠብ ይጋብዘናል፡፡ ለዚህም ነው አንዳንዶቹ ‹‹አንቺ ነገር ማጣመም ነው የምትችይው›› የሚባሉት፡፡
እጮኛሞችን ደግሞ ገና በጓደኝነት ጊዜያቸው ከሁለት አንዱ ላይ ያለው ዓይነ ጥላ በቃላት፣በንግግር፣በፍላጎት፣በምርጫ እንዳይግባቡ እንዳይስማሙ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህ አለመግባባት እየዋለ ሲያድር ብሎም ሲከር በቀላሉ ያለማንም ግን በዓይነ ጥላው ጣልቃ ገብነት መለያየት ውስጥ ይገባሉ፡፡ እየተዋደዱ፣እየተላመዱ በባሕርይ በሚመስል አለመግባባት ስንቱ ለመለያየት በቅቷል፡፡ የስንቱ የእጮኝነት ሕይወት በዓይነ ጥላ ስውር ደባ ፍቅር አልባ ሆኖ ተቀጭቷል፡፡
የሚያሳዝነው በእጮኝነት ጊዜ የሚፈጠረው አለመግባባት፣ጭቅጭቅ ለሁለቱም ልክ እና አሳመኝ የሆነ ምክንያት አድርጎ ያሳያቸዋል፡፡ ታረቁ ሲባሉ እንቢኝ አሻፈረኝ ይላሉ፡፡ እጮኛሞችን ዓይነ ጥላው ማለያየት ሲፈልግ ከሁለት አንዱን ድንገት ባሕሪውን ይቀይራል፡፡ ያልተለመደና አዲስ የሚመስሉ ነገሮችን ያሳያል፡፡ በዚህን ጊዜ መደባበር፣መናናቅ፣መቀዛቀዝ መበሃላቸው ይፈጠርና ወደ ሌላ የጥርጥር ድምዳሜ ውስጥ ከትዋቸው ይለያያቸዋል፡፡
የሚዋደዱ የሚፋቀሩ እጮኛሞች ለሰው ግራ እስኪሆን ድረስ ለምን እንደማይግባቡ፣ለምን እንደሚጨቃጨቁ አይውቁም፡፡ በተለይ ዛሬ ጥሩ ጊዜ እናሳልፋለን ብለው ከተቀጣጠሩ በመሃል ድንገተኛ አለመግባባት ይፈጠርና ተጨቃጭቀው ይለያያሉ፡፡ ነገሩ ካለፈ በኃላ ነው ከሁለት አንዳቸው ጥፋታቸው የሚታያቸው፡፡ ዓይነ ጥላው የልቡን ካደረሰ
👍 3
ከንቱ መመካት ያሳልፍባቸዋል፡፡ እንዲህ ያሉ መራጮችን እግዚአብሔር ‹‹ነገር ግን በውበትሽ ታምነሻል›› ይላቸዋል፡፡ /ሕዝ 16÷15/ አንዳንዶቹን በመልካቸው የተፈላጊነት ስሜት እንዲሰማቸው በማድረግ አመንዝራ ያደርጋቸዋል፡፡ ውበታቸው ፍቅራቸው እየሰመላቸው ለማመንዘር ቅርብ ናቸው፡፡ ‹‹ውበትሽን በጊዜ ተጠቀሚ›› በሚል ዓይነ ጥላዊ ፈሊጥ በዝሙት መርመርመጥ ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ እንደዚህ የሚሆኑትን ሴቶች ነብዩ ሕዝቅኤል ‹‹በየመንገዱ ራስ ከፍ ያለውን ቦታሽን ሠራሽ፣ውበትሽንም አረከስሽ፣ለመንገድ አላፊም ሁሉ እግርሽን ገለጥሽ ግልሙትናሽንም አበዛሽ›› በማለት ይወቅሳል፡፡ /ሕዝ 16÷25/
ወዳጆቼ ዓይነ ጥላው ውበታቸውን ለትዳር ሕይወት ሳይሆን ለዝሙት ያደርግባቸዋል፡፡ ዝነኞችንና ታዋቂዎችን ደግሞ ዓይነ ጥላቸው መልካቸውን ለትዳር ሳይሆን ለከንቱ ነገር እንዲያውሉት ያደርጋቸዋል፡፡ ስምና ዝናቸውን ተጠቅመው በትዳር ከመኖር ይልቅ የማመንዘር ሕይወትን እያዳበሩ በውበት እና በዝናቸው እየኮሩ እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡ እነዚህም ‹‹ስለ ዝናሽ አመንዝረሻል፣ምንዝርናሽንም ከመንገድ አላፊ ሁሉ ጋር አበዛሽ›› ተብለዋል፡፡ /ሕዝ 16÷15/
ዓይነ ጥላ ያለባት መልከኛ ሴት ምናልባት አንድ ወንድ ወድዋት ተግባብቷት፣ተቀራርቧት ማውራት ሲጀምሩ ዓይነ ጥላው ፊትዋ ላይ፣ዓይኗ ላይ ግንባርዋ ላይ ጠቀምጦ ለሚወዳት ወንድ ኃይለኛ፣ነገረኛ፣ቁጡ ሴት አድርጎ ያሳየዋል፡፡ የሚገርመው እሷ ግን ጤናማ ፊት ይዛ የምታወራው ነው የሚመስላት፡፡ ወንዱ ነገ ቢያገባት ሊመጣበት የሚችውን የትዳ ተግዳሮት በማሰብ ይርቃታል፡፡ ደግሞ ከአንዱ ጋር የጓደኝነት ሕይወት ትጀምራለት፣የፍቅር ሕይወት ውስጥ ከገባች በኃላ የወደደችው ወንድ ያለ ምንም ምክንያት ይርቃታል፡፡
አንዳንዱ ወንድ ደግሞ አንሶላ ከተጋፈፋት በኃላ ይሸሻታል፡፡ በዚህም ወንድ መጥላት ይጀምራሉ፣ወንድ አያምኑም በዚህ የተነሳ ሳያገቡ ይቀራሉ፡፡ እጅግ የሚገርመው ደግሞ ለሴቶች ለትዳር መልካምና መንፈሳዊ ናቸው የተባሉ ወንዶች በአንድም በሌላም ይመጣላቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላው ግን የመገርገር ሥራ እየሠራ የሚመጡትን ወንዶች ከሕይወት መንገዳቸው ላይ ይመልስባቸዋል፡፡ ወንዶች ለትዳር ይመጣሉ ቁም ነገሩ ላይ ግን ባዶ ይሆናሉ፡፡
ዓይነ ጥላው የሴትችን የትዳር እድላቸውን በተለያየ መንገድ ማጨናገፉ ምን ዓይነ ጥላዊ የክፋት ጥቅም ያገኛል? ካልን፡፡ አንደኛ ከትዳር ዓለም ያርቃቸዋል፡፡ ሁለት ካገቡ ዘር ይተካሉ ስለዚህ የልጅ ጸጋ እንዳይኖራቸው ያደርጋቸዋል፡፡ ሦስት የቤተሰባቸው ጥገኛ እና ተጧሪ ያደርጋቸዋል፡፡ አራት የሰውን ሕይወት እያዩ በቅናት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡ አምስት ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ ስድስት ተስፋ ስለሚቆርጡ ለዝሙት ሕይወት ይዳርጋቸዋል፡፡ ሰባት በእግዚአብሔር እና በእምነታቸው ተስፋ የማስቆረጥ ሥራ ይሰራባቸዋል፡፡ ስምንት ወንድ ጠል ያደርጋቸዋል፡፡ ዘጠኝ ሕይወታቸውን የቀን ጨለማ አድርጎ በማሳየት በሥራቸው ውጣታማ እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ አስር ለምን እና ለማን እንደሚኖር ግራ እያጋባቸው ከራሳቸው፣ከቤተሰባቸው እያጣላቸው ያኖራቸዋል፡፡
ተወዳጆች ሆይ ትዳር ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ በረከት ነው፡፡ ከእግዚአብሔር መልካም ስጦታዎች ውስጥ አንዱ ትዳር ነው፡፡ የትዳር ሕይወት በምድር ሳይሆን በሰማይ ቤት በእግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃድ የተጀመረ የቅድስና ሕይወት ነው፡፡ አዳም እና ሔዋን የተጋቡት በምድር ሳይሆን በሰማይ ነው፡፡ አዳምና ሔዋን በሰማይ የጀመሩትን የበረከት የቅድስና ሕይወት ነው እኛ በምድር የምንኖረው፡፡
ስለዚህ ይህንን የቅድስናና የበረከት ሕይወት ዓይነ ጥላው ስለሚጠላ የትዳር መልካም አጋጣሚያችንን፣ጥሩ እድላችንን የራሳችን ሐሳብ በሚመስል ውስጣዊ ተንኮል ሲከላከል ይኖራል፡፡ እኛም ወደ እኛ የሚመጡትን የትዳር ፈቃዶችን በራሳችን ምዘና ‹‹አይሆነኝም፣አይመጥነኝም›› በማለት በመግፋት እንኖራለን፡፡ በመጨረሻ የመራጭ ነገር ተመራጭም የመሆን እድል ስለማይኖረው ዓይነ ጥላው የእሱን ፍላጎት በእኛ ሕይወት በማጎልበት የባዶነት ኑሮን ያስታቅፈናል፡፡
አንዳንዶችን ደግሞ ለትዳር ሲጠየቁ ዓይነ ጥላቸው ከትዳራቸው ትምህርታቸውን እያስቀደመ ‹‹ቆይ የጀመርኩትን ትምህርት ዳር ላድርስ ልጨርስ፣ማስተርሴን ልያዝ›› እያሉ የወጣትነት ዘመናቸውን በትምህርት ያሳልፉና ትዳር በሚፈልጉበት ጊዜ ዓይነ ጥላው ለሚፈልጋቸው ሰው ትልቅ ሰው፣ጎልማሳ በማስመሰል እያሳየ ወንድ እንዲርቃቸውና ትዳር እንዳይዙ ያደርጋቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላው አግብተው መማር እንደማይችሉ እያሳሰባቸው ለፍቅር፣ለትዳር ሕይወታቸው ሳይሆን ለትምህርታቸው ቅድሚያ እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል፡፡ ተምረው ጥሩ ደገጃ ከደረሱ በኃላ ያለ ፍቅር፣ያለ ትዳር መኖር ባዶነት መሆኑን ሲረዱ ሞራላቸው እየከሰመ፣የመኖር ትርጉሙ እየመነመነ ሲመጣ ‹‹ለማን ነው የምለፋው፣ለማነው የምኖረው፣ለአንድ ራሴ ምን አስጨነቀኝ›› በማለት የሕይወት ውድቀት ውስጥ ይገባሉ፡፡
ይህ የሴቶች ብቻ ሳይሆን የወንዶችም ትልቅ ችግር ነው፡፡ ወንዶቹ ‹‹ተምሬ፣ሠርቼ ከብሬ፣አንድ ነገር ይዤ ነው የማገባው›› እያሉ እድሜአቸውን ያለ ትዳር እንዲገፉ ያደርጋቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላው የኑሮን ውድነት እያሳሰባቸው፣ገና ለገና በቤት ኪራይ ልኖር ነው እያስባላቸው ከትዳር በማዘግየት፣የትዳር ሕይወታቸውን መቅጨት፣ እድሜአቸውን ማሳለፍ ይጀምራል፡፡
በተለይ በዚህ ዘመን የተጠናወተን ዓይነ ጥላ በዘር በብሔር ከለላ ግብቶብን ‹‹የራሴ ዘርና ብሔር ካልሆነ አላገባም›› እያስባለን ሰውን ሳይሆን እንደ ገበሬ ዘርን እንድንመርጥ ያደርገናል፡፡ ገነት በየብሔራችን የምንገባ ይመስል መንፈሳዊ ነን የምንለውም ከትዳር መሠርት ውስጥ ሃይማትን ሳይሆን ዘርን መርጠን ትዳር አልባ እንሆናለን፡፡
ተወዳጆች ሆይ ከዚህ ቀደም የጠፋው ጠፍቷል ከዚህ በኃላ ትዳር እና ልጅ ጠል በሆነው በዓይነ ጥላ መንፈስ፣የነገ ሕይወታችን እንዳይቃወስ ቆም ብለን እናስብ፡፡ በአንድም በሌላም ወደ እኛ የሚመጡትን የትዳር መልካም አጋጣሚዎችን ዓይነ ጥላችን እየገፋ፣የሚመጡትን እያስከፋ ከሚኖሩት በታች ከሞቱት በላይ አድርጎ እንዳያስቀረን ተንኮሉን ልንነቃበት እና ልናውቅበት ይገባል፡፡
ደግሞ ገና ለገና የትዳር እድሌን ዓይነ ጥላ ሳያበላሽብኝ ብላችሁ ዘው ብሎ ከመግባት ሁነኛውን ሰው በጸሎት መለየት ያስፈልጋል፡፡ ግን ‹‹በውበትም ፋንታ ጠባሳ ይሆናል›› እንደተባለው ውበታችን የሕይወት መጥፎ ጠበሳ እንዳይሆን ልናስብበት ይገባል፡፡ / ኢሳ 3÷24/
ክፍል ሦስት
ከሰው የማያግባባ ዓይነ ጥላ
/ሰው አልባ፣ሕይወት አልባ የሚያደርግ/
ይቀጥላል ….
👍 7👏 1
ክፍል ሁለት
ሴቶችን በተለይ መልከኞችን ትዳር አልባ የሚያደርግ ዓይነ ጥላ
/ወንድ አርቅ/
ወዳጆቼ በክፍል አንድ ገርጋሪው ዓይነ ጥላና የዛር አጋንንት ከማኅፀን ጀምሮ በመጠናወት፣ሕይወታችንን እንዴት እንደሚያበላሽ አይተናል፡፡ በዚህ በክፍል ሁለት ደግሞ ዓይነ ጥላ ለሴቶች እህቶታችን የትርዳር ጠንቅ፣ለወንዶች ደግሞ ከትዳር ለመራቅ ምክንያት እንዴት እንደሚሆን እንመለከታለን፡፡ የቅዱሳን አምላክ ምስጢሩን ይግለጥልን፡፡
ማሳሰብያ ፦ ይህን ትምህርት ስታነቡ ውስጣችሁ ሊበሳጭ እና ዓይነ ጥላው ሊያጉረመርም ስለሚችል በትዕግስት አንብቡ፡፡
ተወዳጆች ሆይ ዓይነ ጥላ በባሕሪው ትዳር አይወድም፡፡ ለዚህም ነው ትዳር እንዳንይዝ፣የተለያየ የሕይወት መዘዝ የሚያመጣብን፡፡ ዓይነ ጥላ ልጅ አይወድም ለዛም ነው ልጆችን ከማኅፀን የሚያጨናግፈው፣ከተወለዱ በኃላ ደግሞ ሕይወታቸውን የማበላሸት ሥራ ከልጅነታቸው የሚሠራው፡፡
ብዙ ሴቶች በተለይ መልከኞች ትዳር እንዳይዙ ዓይነ ጥላው ከፍተኛ የማደናቀፍ ሥራ ይሠራል፡፡ መልክና ቁመናቸውን ይዘው ቆመው እንዲቀሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ አንድ መልከኛ ሴትን ከቤተሰቦችዋ፣ከጓደኞችዋ ጀምሮ ‹‹አንቺ ለምን አታገቢም፣ይሄ ውበት እኮ ይረግፋል፣ሁሉም በጊዜው ነው የሚሆነው ይልቁንስ ተጠቀሚበት›› እያሉ ምክር ይሁን የቃል መውገር ይለግሷቸዋል፡፡
እነሱም ግራ እስኪገባቸው ድረስ ለምን እንዳላገቡ፣ወንዶች ለምን ለትዳር እንዳልፈለግዋቸው አያውቁም፡፡ ግን ዓይነ ጥላው በውስጥ እና በውጭ ሆኖ ይገረግርባቸዋል፡፡ የውስጥ ዓይነ ጥላው ውስጣቸው አሸምቆ ተደብቆ ለወንዶች አቃቂር በማውጣት የማጥላላት የመናቅ ሥራን ይሠራል፡፡ በዚህም የሚመጡትን ወንዶች ያባርራል፡፡
ዓይነ ጥላው መልከኛ ስለሆኑ የኩራት፣የትዕቢት፣የበላይነት፣የትፈለግያለሽ ስሜት እያሳደረባቸው ለትዳር የሚመጡትን ወንዶች በራሳቸው እየመዘኑ እንዲጠሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ምርጫቸውን በማብዛት አንዱ ላይ እንዳይረጉ ያደርጋቸዋል፡፡ዓይነ ጥላው ውስጣቸው ሆኖ ለትዳር የመጣውን ወንድ ‹‹አይመጥንሽም፣ይህንን ነው የምታገቢው፣ቤተሰብ ምን ይላል›› እያለ በሚወዳት ወንድ እንድታፍር፣እንድትሳቀቅ ያደርጋል፡፡ ዓይነ ጥላው ተመራጭ እና መራጭ እንድትሆን በኩራት መንፈስ ጠስቆ ይይዛታል፡፡ በመልኳ በቁመናዋ፣በዳሌዋ እንድትመካ እያደረጋት ወንዶችን ወደ ታች እንድታይ ይደረጋታል፡፡
ሴቶች ልብ የማይሉት ዓይነ ጥላው በውበታቸው፣በቁመናቸው፣በደም ግባታቸው እራሳቸውን ከፍ አድርገው እንዲያዩ በማድረግ የትዳር ሕይወታቸውን ከባለ ጠግነት ጋር ያያይዝባቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላ ያለባቸው መልከኛ ሴቶች ወንዶችን በመልካም በሕርያቸው፣በተክለ ሰብዕናቸው፣በውስጥ ውበታቸው፣በቀናነታቸው በታማኝነታቸው ሳይሆን በእውቀታቸው፣በሥልጣናቸው፣በዝናቸው በመመዘን የራሳቸውን ሰው እንዳይመርጡ ያደርጋቸዋል፡፡ ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ ‹‹አንቺ ልጅ እባክሽ አግቢ›› ሲላት ዓይነ ጥላው የሐብት መሻት፣የባለ ጠግነት ስሜት እንዲሰማት በማድረግ ‹‹ሀብታም ካልሆነ አላገባም፣ቤት የሌለው፣መኪና የሌለው ባል ምን ይሠራልኛል›› እያሉ በዓይነ ጥላው እየታለሉ ያለ ባል ይቀራሉ፡፡ ሀብታም ባል ቢያገቡም ለባላቸው ፍቅር ከመለገስ ይልቅ በውበታቸው በመኮፈስ ትዳራቸውን ዓይነ ጥላው መረበሽ ይጀምራል፡፡
አብዛኞችን ደግሞ ዓይነ ጥላቸው የወደዱትን ሰው ጥቃቅን የስህተት ምክንያት እየፈለገ ያጨቃጭቃቸዋል፣የወደዱትን ሰው የፍቅር ምቶች ይነሳባቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላቸው እጅጉን ከመክፋቱ የተነሳ በምንም ተአምር ለተበደሉበት ነገር ይቅርታ እንዳያደርጉ ልባቸውን ያደነድናል፡፡ በተለይ ጥፋትን በቅርበት ካዩ ይቅርታ ቢጠየቁም አሻፈረኝ በማለት ወደ ሌላ ሰው እንዲሄዱ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህ ሂደት የቀናቸው መልካም ሰው ላይ ይወድቃሉ፣ያልቀናቸው ደግሞ ከወንድ ወንድ ይንከራተታሉ፡፡ ፍቅር እና ጸጋ እግዚአብሔር የሚጠነቀቅለትን ነው የሚፈልገው፡፡ እነሱ መጠንቀቅ ሳይሆን መጨቃጨቅ እንደ ባሕርይ ያጣባቸውና ሕይወታቸውን መና ለማስቀረት ዓይነ ጥላቸው ይታትራል፡፡
የውጭ ዓይነ ጥላው ደግሞ በሚፈልጋት ወንድ ላይ ተቀምጦ እንደ ተራራ አግዝፎ እንዲያያት፣ትበዛብኛለች ብሎ እንዲያስባት ቢያገባት እንኳን ለትዳሩ የፍቅር ስንቅ ሳትሆን ጠንቅ አድርጎ ያሳየዋል፡፡ በዚህም የወደፊቱን ትዳር በመገመት በመፍራት ‹‹እኔ ለእሷ አልሆንም›› በማለት ወንዱን ተስፋ በማስቆረጥ ያርቀዋል፡፡ ከእሷ ጋር መኖር በእሳት ተቃጥሎ እንደ ማረር አድርጎ ያሳስበዋል፡፡ እሷም ላይ እሱም ላይ ያለው ዓይነ ጥላ የመፈላለግ ድንበራቸውን በማፍረስ፣የጀመሩት ፍቅር ገና በጅምሩ በምክንያት በማቃወስ ያራርቃቸዋል፡፡ የሚያሳዝነው ዓይነ ጥላው ለጊዜው ልክ አድርጎ ያስወሰናቸውን ውሳኔ ካለፈ በኃላ፣ነገሮች ከተበላሹ በኃላ፣ሌላ ሕይወት ውስጥ ከገቡ በኃላ በጸጸት አለንጋ ይገርፋቸዋል፡፡ ‹‹ምን ሆኜ ነው? ለምን እንደዛ አደረኩ? ልክ አላደረኩም›› በማለት ባለፈ ነገር እንዲቆጩ ያደርጋቸዋል፡፡ ነገሮች ተመልሰው መስተካከል ወደማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ከገቡ በኃላ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማን ያደርገናል፡፡ መበደላችን የሚታወቀን ካለፈን በኃላ ነው፡፡ ይህ አንዱ የመንፈሱ መሰርይ ጠባይ ነው፡፡ እድላችንን ከማሳጣት በኃላ በጸጸት ማሰቃየት፡፡
ልክ እንደ ሴቶቹ ወንዶቹም የዚህ እኩይ መንፈስ ሰለባ ናቸው፡፡ ወንዶቹን ደግሞ መራጭ፣ተፈላጊ አድርጎ በማስቀመጥ ሴት አውል ያደርጋቸዋል፡፡ ከሚወድዋቸው ሴቶች ጋር ከትዳር በፊት በመዘሞት በሩካቡ ሥጋ ብቻ በመመዘን እየናቅዋቸው ይሸሿቸዋል፡፡ ይህ የዓይነ ጥላ ባሕርይ የተጣባቸው ወንዶች ለትዳር ክብር ስለማይኖራቸው ዓይነ ጥላው ያለ ሚስት ያስቀራቸዋል፡፡
በተለይ ወንዶች አይነ ጥላው ብዙ ሴቶችን በማስመረጥ ብሎም በማማገጥ ያለማምዳቸውና ትዳር የሚለውን ክቡር ሕይወት ዋጋ ቢስና ከንቱ ያደርግባቸዋል፡፡ ትዳር ሲባሉ ያባለጋቸው ዓይነ ጥላ ሕይወቱን ያከብድባቸዋል፡፡ አንዳንድ ውዶች ደግሞ ትዳር የሚባለውን በትዳር ኖረው የተፋቱትን በማሰብ ለማግባት ይፈራሉ፡፡ አጋንንት የእኛን እንዳንኖር የሰው እያሳየ መጥፎ ስዕል ይስልብንና ከትዳር ዓለም እንድንርቅ ያደርገናል፡፡
ዓይነ ጥላ ያለባቸው ሴቶች በመልካቸው ይመካሉ፣ወንድ ይንቃሉ፣ወንድ ይፈራሉ፣ትዳር ይፈራሉ፣ይኮራሉ፣ፊታቸው የተቆጣ ይመስላል፣ከኩስትርና አልፎ የተከሰከሰ ፊት ይኖራቸዋል፣ሲያይዋቸው ተናጋሪና ኃይለኛ ሴት ይመስላሉ ወዘተ እነዚህ ሴቶች እንደዚህ ዓይነት የፊት ገጽታ የሚይዙት ወደው ሳይሆን ዓይነ ጥላው ወንድ እንዲርቃቸው፣ወንድ እንዳይቀርባቸው ለመተናኮል ነው፡፡
ወዳጆቼ ሰው እንዴት በአፈር ይመካል? መልክ ደስ ቢል እንጂ አያስመካም፡፡ የዛሬ መልክ ነገ በእርጅን ውበቱን አጥቶ ተቆራምቶ የሚለወጥ ነገር ነው፡፡ ግን ዓይነ ጥላው ምን ሠርቶ ይኑር? በተሠጠን ነገር ከመጠቀም ይልቅ እንዳንጠቀምበት የማባከን ሥራ ይሠራል፡፡ ጥበበኛው ሰለሞን ‹‹ውበት ሐሰት ነው፣ደም ግባትም ከንቱ ነው›› ይለናል፡፡ ሰለሞን ውበት ሐሰት ነው ያለው የማይቆይ የማይዘልቅ መሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡ ደም ግባት ከንቱ ነው ያለው ደም ግባት በህመም፣በአደጋና ከጊዜ በኃላ በሚመጣ ነገር እንዳልነበር ስለሚሆን ነው፡፡ /ምሳ 31÷30/ እንግዲህ ሐሰት እና ከንቱ የሆነ ነገር ይዘን ነው የምንኮፈሰው፣የምንመካው፡፡ እንዲህ የመኮፈስ፣የመኩራት የትዕቢት መንፈስ የሚያሳድርብን ዓይነ ጥላው ነው፡፡
ዓይነ ጥላ ሴቶችን ወንድ እያስመረጣቸው፣እያስናቃቸው፣እያስመካቸው የወጣትነት እድሜቸውን ያባክናል፡፡ የተፈላጊነታቸው ጊዜ በ
ጆቹ የአጋንት ውግያ ውስጥ ይገባሉ፡፡
ወደጆቼ መልካም ስንዴን በሚያበቅል እርሻ ላይ አረም እየዘራን ነው፡፡ የተባረከ ልጅ በምንወልድበት ማኅፀን የአጋንንት የተንኮል አረም የበቀለባቸው ልጆች የምንወልደው ከእግዚአብሔር በአምልኮ ስለተለየን ነው፡፡ መንገዱን የሳተ ተጓዥ ሌባና ሽፍታ ይዘርፈዋል፣ያጠቃዋል ብሎም ሊገለው ይችላል፡፡ ከእግዚአብሔር መንገድ ርቀን፣በባዕድ አምልኮ ተጉዘን አጋንንት የማያጠቃበት፣ሕይወታችንን ከማኅፀን ጀምሮ የማያበላሽበት ምክንያት የለም፡፡
ዓይነ ጥላ ከማኅፀን ጀምሮ እኛን መዋረሱ ምን ጥቅም ያገኛል? ካልን ብዙ አይነ ጥላዊ ጥቅም ያገኛል፡፡ አንደኛ በሕፃንነታችን ስለሚዋረስ እኛን በራሱ መንገድ በመቀየስ እንድንጓዝ ያደርገናል፡፡ ሁለተኛ ገና በጠዋቱ በሕይወታን ጣልቃ ስለገባ የተበላሸ ሕይወትን እያለማመደን እንድናድግ ያደርገናል፡፡ ሦስተኛ ከባሕርያችን ጋር በመዋሃድ የእኛ በሚመስሉ ግን በእሱ የተንኮል ባሕርይ ውስጥ እንድናድግ ያደርገናል፡፡ አራተኛ ጥሩ ዜጋ እንዳንሆን የብልሹነት መንገድ ውስጥ ይከተናል፡፡ አምስተኛ የተፈጥሮ መክሊታችንን/ስጦታችንን ቀብሮ፣ሰውሮ፣በራሱ ልክ ወቅሮ ያለ ሕይወታችን አፈንግጠን እንድንኖር ያደርገናል፡፡ ስድስተኛ የሕይወታችን አዛዥ በመሆን ለጥፋት እና ለኃጢአት እያዘጋጀን ከፍ ስንል እያሠራን ይኖራል፡፡ ሰባተኛ የእኛ የሆነውን ነገር ለማበላሸት፣ለማኮላሸት ይመቸዋል፡፡ አብሮን በስውር ኖሯልና፡፡ ስምንተኛ የሕይወት ተስፋችንን፣የነገ ብሩሃችንን ከልጅነት ጀምሮ ለማጨለም ይጠቀማል፡፡ ዘጠነኛ አእምሮአችንን በመቆጣጠር ላልፈለግነው ተግባር እንድንውል ያደርገናል፡፡ አሥረኛ የእኛ ባልሆነ ባሕርያችን በቤተሰባችን እንድንጠላ፣ትምህርታችንን በእንጭጩ በመቅጨት የቤተሰብ መዛበቻ በማድረግ ከቤተሰብ እንድናፈነግጥ፣በራሱ የክፋት መንገድ እንድንሮጥ ያደርገናል፡፡ አሥራ አንደኛ አጋንንቱ ገና በልጅነታችን የቅዱሳን ጸጋ ወደ እኛ እንዳይጠጋ እኛን በኃጢአት ያረክሰናል፡፡ አሥራ ሁለተኛ ተዋግቶን፣ተስፋ አስቆርጦን ከያዝነው እምነት ያስወጣናል፣ከእግዚአብሔር እንድንለያይ ያደርገናል፡፡
ተወዳጆች ሆይ እንግዲህ በቤተሰቦቻችን መንፈሳዊ ሕይወት አልባነት የገባው ዓይነ ጥላ ከፍ ስንል እራሳችንን ስናውቅ፣ተምረን ለመሥራት፣ትዳር ይዘን ለመውለድ ፣ሰርተን ለመክበር ለመኖር ስንጀምር ያኔ ነው ግልጽ እና ስውር ውግያውን የሚጀምረው፡፡ የእኛ የሆነውንና የእኛ ልናደርገው ያሰብነውን ነገሮች ማበላሸት ይጀምራል፡፡ ለዚህም ነው በጸበል ቦታ ልቀቅ ሲባል ‹‹አሳድጌ አሳድጌ›› እያለ የሚያላዝነው፡፡
ወዳጆቼ በማኅፀን የሚጠናወተን ዓይነ ጥላ እና ዛር ከላይ ከዘረዘርናቸው በላይ አደጋ ሊያደርሱብን ይችላሉ፡፡ ከማኅፀን ጀምሮ የአእምሮ እድገት ውሱንነት፣የአእምሮ ዘገምተኝነትን ይዘው የሚወለዱት ልጆች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ችግራቸው ከመንፈሱ ጥቃት ጋር ይገናኛል፡፡ በሳይንሱ ግን ብዙ ስያሜ ይሰጠዋል፡፡ አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት ዛር አንጋሽ ቤት፣ጠንቋይ ቤት ለማስጠንቆል ሄዳ ታማሚ ልጅ ብትወልድ አይደንቅም፡፡
ከማኅፀን ጀምሮ በልጆች ላይ ለሚያድረው ገርጋሪው ዓይነ ጥላና ለምቀኛው የዛር አጋንንት መፍትሔው ቶሎ ቶሎ ልጆችን ቅዱስ ቁርባን እንዲቀበሉ ማድርግ ነው፡፡ በሰውነታቸው ላይ ያደረው ዓይነ ጥላ ቅዱስ ቁርባን ሲቀበሉ በሰውነታቸው ላይ የሚያድረውን ጸጋና የመለኮት እሳትን መቋቋም ስለማይችል ጥሏቸው ይሄዳል፡፡ እንዲሁም በእረፍታቸው ጊዜ ጸበል እንዲጠመቁ ማድረግ ደግሞ አንዱና ሁነኛ መፍትሔ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን አብሮን በማደግ ለሌላ ችግር ይዳርገናል፡፡
በዚሁ አጋጣሚ በእኛው በቤተክርስትያኒቱ የቴሌቪዥን ስርጭት ‹‹ወቅታዊ ጉዳይ›› በሚል ፕሮግራም ላይ ስሙን መጥቀስ የማልፈልገው መምህር ‹‹ሥጋ ወደሙ ለልጆች በረከት ነው፡፡ ከኃጢአት ንጹህ ስለሆኑ ባይቆርቡም ችግር የለውም›› ብሎ ሲናገር ስሰማ ስለ እውነት ነው የምላችሁ ግራ እስኪገባኝ ድረስ ነው የደነገጥኩት፡፡ ይህን ውይይት የሰማ ቤተሰብ ቅዱስ ቁርባን መንፈሳዊ ኃይልን፣ጸጋ መለኮትን የሚያሰጥ ሳይሆን እንደ ዝክር በረከት ነው የሚለውን ሰምተው ልጆችን ከማቁረብ ይቆጠባሉ ብሎም ይተዋሉ፡፡ ዛሬ እንኳን ልጆቻችንን ሳናቆርብ ቀርቶ እያቆረብናቸውም ፈተናቸው ብዙ ነው፡፡
ወላጆችም ልጆቻችን ከርጉማን መናፍስት ጋር የተቆራኙ ልጆች እንዳንወልድ በንስሐ ጸድተን፣ቅዱስ ቁርባን እየተቀበልን ብንኖር እና ብንወልድ የእኛ መንፈሳዊ ጸጋ ያደረባቸውና የተባረኩ ልጆች እንወልዳለን፡፡ ግን እኛ ውስጥ የሌለነን ነገር ለልጆቻችን መስጠት ስለማንችል ከእኛ ያጡትን፣ከአጋንንት ያገኙትን ይዘው መወለድና ማደግ ይጀምራሉ፡፡ ይህ የትውልድ አመጣጣችን፣የመወለድ ሂደታችን በዚህ መንገድ እንድናልፍ ሆነናል፡፡ የቤተሰባችንን የመናፍስቱን ዕዳ እኛ በስቃይ፣በመከራ፣በፈተና በስኬት አልባ ሕይወት እንከፍላለን፡፡
ለዚህም ነው ገና በጨቅላነታችን ዘመን ባልፈለግነውና ባላሰብንበት የሕይወት መስመር ውስጥ እየዳከርን ዛሬን በስቃይ የምንኖረው፡፡ ለዚህም ነው በልጅነታችን የት ይደርሳሉ ተብለን ተተንብዮልን መንታ መንገድ ላይ ቆመን የቀረነው፡፡ ለዚህም ነው በልጅነታችን በትምህርት ክህሎታችን ተመስክሮልን ድንገት የመፍዘዝ የመደንዘዝ እና የሰነፍነት ባሕርይ ተጣብቶን የምናውቀው ያጠናነው ትምህርት መልሶ አልገባ እያለን የምንቸገረው፡፡
ለዚህም ነው ጠባይ መልክና ቁመና ሳያንሰን ትዳር አልባ የሆነው፡፡ ለዚህም ነው ተምረን እንዳልተማረ ሰው ማስተዋላችን ጠፍቶን ግራ ገብቶን የምንኖረው፡፡ ለዚህም ነው ያየን የማይወደን፣ያለ ሥራችን ስም ተሰጥቶን የኛ የምንላቸው ሰዎች ጠልተውን የምንኖረው፡፡ ለዚህም ነው እንኳን ሳቃችን ቁም ነገር ንግግራችን ለሰው አልጥም እያላቸው፣እራሳችንን በመጥላት የምንኖረው፡፡ ለዚህም ነው የቱንም ያህል መልካም ሰው ብንሆንም ሰዎች መልካምነታችን ሳይሆን የሌለንን መጥፎ ገጽታችንን ለማየት የሚጥሩት፡፡ ለዚህም ነው ፍርሃትን፣በራስ መተማመንን አጥተን፣አድገን ሰው ፊት እንደ ሰው መናገር፣ማማከር እያቃተን የደፋር ፈሪዎች የሆንነው፡፡
ለዚህም ነው ሁለት ያልተግባቡ ሰዎች የምንሆነው፡፡ በቤተሰባችን ያለን ሰብዕና፣በመስሪያ ቤት፣በትምህርት ቤት፣በትዳራችን፣በማህበራዊ ሕይወታችን ሌላ ሰው ሆነን የምንኖረው፡፡ ለዚህም ነው ደግ ሆነን እንደ ንፉግ እና እንደ ክፉ የምንታየው፡፡ የሠራነው ውሃ የሚበላው፣የጨበጥነው አመድ የሚሆነው፣ያቀድነው በሐሳብ ጠንጠልጥሎ የሚቀረው፣እጄ ገባ ያልነው እንደ ሰማይ የሚርቀን፣ሩቅ አስብን ቅርብ የምናድረው … እግዚአብሔር ዘግቶብን ሳይሆን ዓይነ ጥላው እያጨናገፈብን፣ራዕያችንን እየጋረደብን ነው፡፡ አብሮን ያደገው፣ከልጅነታችን የተጠናወተን ዓይነ ጥላ የሕይወታችን ደንቃራ እና ኪሳራ ይሆናል፡፡
ተወዳጆች ሆይ እስኪ ቆም ብላችሁ ከልጅነታችሁ ጀምሮ እያጣችሁት የመጣችሁትን ነገሮች አስቡዋቸው? ስኬት በሚመስል ጥሩ ነገር ጀምራችሁ ዛሬ የት ጋር ነው የቆማችሁት? በምትፈልጉት ሳይሆን ባላሰባችሁት መንገድ ዛሬ የት ጋር ነው ያላችሁት? ሕይወታችንን ገለጥለጥ አድርገን፣መለስ ብለን ካየነው ዓይነ ጥላው ምን ያህል ሕይወታችን እንደተጫነን፣በሕይወታችን ምን ያህል ጣልቃ በመግባት ያላሰብነው የመከራ ጉድጓድ ውስጥ እንደከተተን እናያለን፡፡
ወዳጆቼ የችግራችን መፍትሔዎች ዝርዝር ነገር ስለሚፈልጉ በማጠቃለያ ትምህርታችን እንመለከታቸዋለን፡፡ እስከዚያው ትምህርቱን ተከታተሉ፡፡
ክፍል ሁለት
ሴቶችን በተለይ መልከኞችን ትዳር አላባ
የሚያደርግ ዓይነ ጥላ
/ወንድ አርቅ/ይቀጥላል.
👍 4❤ 2🥰 2
