ru
Feedback
"ኡማ ቲቪ " Tv

"ኡማ ቲቪ " Tv

Открыть в Telegram

ለበለጠ ወቅታዊ መረጃወችን ለማገኘት የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇 https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

Больше
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
46 287
Подписчики
-624 часа
-1027 дней
-56430 день
Архив постов
በኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ተመሰረተ። EMYC|| ታህሳስ 18/ 2018 በኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንሰል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የምስረታ በዓል ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ እና የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተወካይ አቶ አብዱ ሰኢድ፣ የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ፕሬዝደንት ኡስታዝ ሀይደር ከድር፣ የካውንስሉ ዋና ፀሀፊ ኡስታዝ ከማል አረብ፣ ዋና ስራ አስኪያጁ ነብዩ አያሌው፣ የደቡብ ምዕራብ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ሸይክ አደም መሐመድ፣ የደቡብ ምእራብ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ሐጅ ናስር ጊዲ፣ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች የተመራው የልኡካን ቡድን በቦንጋ ከተማ የክልሉን ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ምስረታ አበስሯል። የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ህዝበ ሙስሊሙን በአንድ ጥላ ስር የማስተሳሰር፣ ወጣቶችን በትምህርት እና ስልጠና የማጎልበት፣ አንድነትን የማጠናከር እና የሀገር ኢኮኖሚን የማሳደግ አላማን ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ የየክልል ቅርንጫፎች ምስረታም ይህንን አላማ ለማሳካት ጉልህ ሚና እንደሚወጣ ይታመናል።
Показать все...
👍 6 5
Фото недоступноПоказать в Telegram
ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ154.4773 ብር ተሸጠ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ማክሰኞ ታኅሣሥ 18/2018 ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ154.4773 ብር እንደተሸጠ ይፋ ባደረገው የዋጋ መግለጫ አሳውቋል፡፡ ማዕከላዊ ባንኩ በልዩ ሁኔታ ባወጣው ጨረታ ለሽያጭ ያቀረበው 150 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ነው፡፡ የባንኩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የተከናወነው ከአንድ ቀን በፊት ካሠራጨው አጭር ማስታወሻ በኋላ ነው፡፡ ማዕከላዊ ባንኩ ከዚህ ቀደም 13 ባንኮችን ያሣተፈ ጨረታ አውጥቶ፣ አንድ ዶላር አማካይ ዋጋ 154.7747 ብር ተሽጦ ነበር። የአሁኑ የጨረታ ዋጋ ከቀደመው ጋር ሲነፃፀር የ0.2974 ሣንቲም ቅናሽ የተመዘገበበት ነው። ባንኩ በቀጣይ በተመሣሣይ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚያወጣ አስታውቋል።
Показать все...
6🤣 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሶማሊላንድ የእስራኤልን እውቅና መቀበሏን የተቃወሙት ታዋቂው የእስልምና ምሁር ሸይኽ ዶ/ር መሐመድ ካርዬ በሀርጌሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ! - ሀሩን ሚዲያ ፥ ታኅሣሥ 19 ቀን 2018 ዓ.ል በትላንትናው ዕለት በሀርጌሳ የሚኖሩት ታዋቂው የእስልምና ምሁር ሸይኽ መሐመድ ካርዬ፣ ሶማሊላንድ ከእስራኤል ጋር የመሠረተችውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እና የተቀበለችውን ዕውቅና በይፋ በመቃወማቸው በሶማሊላንድ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘግቧል። እስራኤል ዓርብ ዕለት (ታኅሣሥ 18 ቀን 2018 ዓ.ል) ሶማሊላንድን እንደ ገለልተኛ ሀገር እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሀገር መሆኗን በይፋ አስታውቃለች። የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዱራህማን መሐመድ አብዱላሂ (ኢሮ) እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የጋራ የዲፕሎማሲ ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ፣ ሸይኽ መሐመድ ካርዬ ይህ ስምምነት "የእስልምናን መርህ የሚጻረር እና የፍልስጤማውያንን መብት የሚጋፋ ነው" በሚል በይፋ ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር። ምሁሩ ሸይኽ መሐመድ ካርዬ ትላንት ምሽት በሀርጌሳ ከቤታቸው ተወስደው በቁጥጥር ስር የዋሉት፣ ማኅበረሰቡ መንግሥት ከእስራኤል ጋር የጀመረውን ግንኙነት እንዲቃወም ቅስቀሳ አድርገዋል በሚል ክስ መሆኑን የእሳቸው የቅርብ ምንጮች ለሚዲያዎች ገልጸዋል። ይህ የእስር እርምጃ በሀርጌሳ እና በሌሎች የሶማሊላንድ ከተሞች በሚኖሩ የእስልምና ምሁራን እና ወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። የሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግሥት እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን ዕውቅና "የሉዓላዊነት ጥሰት" በማለት በጽኑ አውግዟል። በተመሳሳይ ግብፅ፣ ቱርክ እና ጅቡቲ የእስራኤልን እርምጃ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፣ ጉዳዩ በቀጠናው ላይ አዲስ የፖለቲካ ቀውስ ሊፈጥር እንደሚችል ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል። ሸይኽ መሐመድ ካርዬ ቀደም ሲል በአሜሪካ ፖርትላንድ ኦሪገን በሚገኘው አል-ሳቢር መስጂድ በኢማምነት ሲያገለግሉ የነበሩ ሲሆን፣ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ በማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ባላቸው ጠንካራ አቋም ይታወቃሉ። የእሳቸው መታሰር በሶማሊላንድ መንግሥት እና በሃይማኖታዊ ማኅበረሰቡ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ሊያሻክረው እንደሚችል ተነግሯል። © ሀሩን ሚዲያ
Показать все...
25😢 6
ውድና የተከበራቹህ የቻናላችን ቤተሰቦች ዛሬ አንዲት ጀግኒት እናት ጋር ቤተሰብ ሁኑ በታማኝነት በጥሩ መስተንግዶ በእናትነት ስሜት የቤት እቃወችን ከፈለጉ ወደሷ ጎራ ይበሉ ። ዘመናዊ የኪችን እቃ ከLG  በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱ። አላማችን ዘመናዊ እቃዎች ጉልበት ፣ ወጪ እና ጊዜ ቆጣቢ እቃዎች ከነፃ ደሊቨሪ ጋር ወደናንተ ማቅረብ ነው። Tg: @Lulusha25 Tel: +251908303332 አድራሻ፦ ጀሞ 1  ወደ ለቡ በሚወስደው መንገድ  የአዳማ ታክሲ መጫኛ ጋር ያገኙናል ። https://t.me/+vlfOW0fCWPQyMDc0
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
በፍርስራሽ ላይ የበቀለ ተስፋ፥ በጋዛ በፈራረሰው አል-ሺፋ ሆስፒታል ውስጥ የሐኪሞች ምርቃ ተካሄደ! በእስራኤል ከባድ ድብደባ ወደ ፍርስራሽነት በተቀየረው የጋዛው ትልቁ አል-ሺፋ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ፣ አስገራሚ እና ስሜት ቀስቃሽ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል። በጦርነቱ ምክንያት ትምህርታቸው ተቋርጦ የነበሩ የሕክምና ተማሪዎች፣ ሆስፒታሉ በፈራረሰበትና አሁንም የጭስ ሽታ ባልተለየው ስፍራ ላይ የሐኪምነት መሐላ ፈጽመዋል። ይህ የምረቃ ፕሮግራም የተከናወነው ሆስፒታሉ ሙሉ በሙሉ ወድሞ ባለበት እና በዙሪያው የፈራረሱ ሕንጻዎች ባሉበት ሁኔታ ነው። ተመራቂ ሐኪሞቹ ነጭ ጋውናቸውን ለብሰው በፍርስራሹ መካከል ቆመው የታካሚዎችን ሕይወት ለማዳን ቃለ-መሐላ ሲፈጽሙ የሚያሳዩ ምስሎች በዓለም አቀፍ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሰፊ ትኩረት አግኝተዋል። ይህ እርምጃ ፍልስጤማውያን ለማንኛውም ጥፋት እጅ እንደማይሰጡ የሚያሳይ ትልቅ የጽናት መልዕክት ተደርጎ ተወስዷል። በጋዛ ያለው የጤና ሥርዓት ሙሉ በሙሉ በፈረሰበት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የሕክምና ባለሙያዎች በጦርነቱ ሕይወታቸውን ባጡበት በዚህ ወቅት፣ እነዚህ አዳዲስ ሐኪሞች መመረቃቸው ለቀሪው የጤና ተቋም ትልቅ አቅም እንደሚሆን ተገልጿል። ተመራቂዎቹ "ሕንጻዎቹ ቢፈርሱም የእውቀትና የአገልግሎት መንፈሳችን አይፈርስም" በሚል መሪ ቃል አገልግሎታቸውን ለመጀመር ቆርጠው ተነስተዋል። ይህንን ኩነት የዘገበው አልጀዚራ እንደገለጸው፣ በምረቃው ላይ የተገኙት የጤና ባለሙያዎችና የተማሪዎቹ ቤተሰቦች በደስታና በሐዘን መካከል ሆነው ሥነ-ሥርዓቱን ታድመዋል። ብዙዎች ይህንን ትዕይንት "በጨለማ ውስጥ የበራ ሻማ" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባለሙያዎችም የተማሪዎቹን ድፍረትና ቁርጠኝነት አድንቀዋል። አል-ሺፋ ሆስፒታል በአንድ ወቅት የጋዛ የሕክምና ማዕከል የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን የወደመ ህንጻ ሁኗል። ሆኖም የዛሬው ምርቃ ሆስፒታሉ አሁንም የሕይወት እና የተስፋ ምንጭ መሆኑን ዳግም ያረጋገጠበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኖ ተመዝግቧል።
Показать все...
25🥰 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
ባንግላዴሽ ከፓኪስታን ጋር የነበረባትን የነፃነት ጦርነት አጠናቃ በ1971 ነፃ ሀገር መሆኗን ካወጀች በኋላ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ለማግኘት በምትጥርበት ወቅት ነበር እስራኤል ባልተጠበቀ ሁኔታ እጇን የዘረጋችው። እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር የካቲት 4 ቀን 1972 እስራኤል ባንግላዴሽን እንደ ነፃና ሉዓላዊት ሀገር እንደምትቀበል በይፋ ያስታወቀች ሲሆን፣ ይህም እስራኤልን ባንግላዴሽን ከቀበሉ የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሀገራት ተርታ እንድትመደብ አድርጓታል። ይሁን እንጂ አዲስ የተመሰረተው የባንግላዴሽ መንግስት ለዚህ እውቅና የሰጠው ምላሽ በታሪክ ውስጥ የሚጠቀስና ቆራጥ ነበር። በወቅቱ የነበረው አመራር የእስራኤልን የእውቅና ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ እንደማይቀበሉት አስታወቁ። ይህ ውሳኔ በወቅቱ ለነበረው የባንግላዴሽ መንግስት ከጥቅም ይልቅ መርህን የማስቀደም ጉዳይ ነበር። ባንግላዴሽ ከፍልስጤም ህዝብ ጎን መቆሟን በግልጽ ለማሳየትና ከአረብ ሀገራት ጋር ያላትን ወንድማማችነት ለማጠናከር ስትል የእስራኤልን እውቅና ወደ ጎን ትታለች። ይህ በ1972 የተጀመረው አቋም ለግማሽ ክፍለ ዘመን ሳይለወጥ እስካሁንም ድረስ ቀጥሏል። እስከ ዛሬ ድረስ በሁለቱ ሀገራት መካከል ምንም ዓይነት ይፋዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት፣ የንግድ ልውውጥም ሆነ ቀጥታ የትራንስፖርት ትስስር የለም። የባንግላዴሽ ፓስፖርትም ለረጅም ዓመታት ዜጎች ወደ እስራኤል እንዳይጓዙ የሚከለክል ማሳሰቢያ ይዞ ሲታተም ቆይቷል። ©Yahyanuhe
Показать все...
27
Фото недоступноПоказать в Telegram
የዚህ ሰው በህይወት መኖር ምን ይጠቅም ይሆን? ሐያ አምስት አመት ፍርድ?
Показать все...
😡 26 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
🇵🇸💔 18 ሺህ ሸሒዶች ሰማዕታትን ቀብሪያለሁ፣ ዕረፍት አልባው የጋዛ መቃብር ቆፋሪው ዩሱፍ አቡ ኻጣብ ከኦክቶበር 15,2023 ጀምሮ ከ18 ሺህ በላይ ሙታኖችን ጉድጓድ እየቆፈርኩ ቀብሪያለሁ፣ይላሉ የ65 ዓመቱ አዛውንት ሁሉም በእስራ Hell የዘር ማጥፋት Genocide የተፈጁ ነበሩ ይላሉ አዛውንቱ ዩሱፍ፤ ቀኑን ሙሉ መቃብር ስቆፍር ነው የምውለው፣አንዳንዴ የወራሪዎቹ IOF ሀይሎች የቀበርኳቸውንና ጉድጓዱን ጭምር በቦምብ ይደበድቡታል።"በማለት ዓለም ይህን ድርጊት ያቆመው ዘንድ ይማፀናሉ። በወራሪዎቹ ጥቃት ወንድምና ልጃቸውን ያጡት አቡ ኻጣብ ዛሬም ጉድጓድ እየቆፈሩ የወገኖቻቸውን አስከሬን ከመቅበር አልቦዘኑም። ኢላህ በቃ ይበላቸው ይበለን!🤲🤲🤲🤲🤲🤲
Показать все...
33😭 20
Фото недоступноПоказать в Telegram
በአሜሪካ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ የፖለቲካ ተፅዕኖ እና የተሳትፎ አቅጣጫ አዲስ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተገለጸ! ሀሩን ሚዲያ፥ ታኅሣሥ 19 ቀን 2018 ዓ.ል በአሜሪካ የሚኖሩ ሙስሊም ዜጎች በሀገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ላይ ያላቸው ተሳትፎና ተፅዕኖ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየጎላ መምጣቱን የተለያዩ ዓለም አቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። እንደ አልጀዚራ ዘገባ ከሆነ፣ ማኅበረሰቡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጋዛ እና በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የዋሽንግተን የውጭ ፖሊሲ እንዲቀየር የሚያደርገው ግፊት አዲስ መልክ ይዟል። ይህ የፖለቲካ ንቅናቄ በዋናነት "ድምፅህን አትስጥ" (Uncommitted) በሚል መርህ የሚመራ ሲሆን፣ ሙስሊም መራጮች ድምፃቸውን እንደ ትልቅ የፖለቲካ መደራደሪያ መሣሪያ በመጠቀም ላይ መሆናቸውን ሮይተርስ በትንታኔው አመልክቷል። የአሜሪካ-እስልምና ግንኙነት ምክር ቤት (CAIR) እና ሌሎች የሲቪል መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ለሚድል ኢስት አይ እንደገለጹት፣ ሙስሊም አሜሪካውያን አሁን ላይ በምርጫ ወቅት ድምፅ ከመስጠት ባለፈ በውሳኔ ሰጪነት ደረጃ ለመሳተፍ ያላቸው ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ለቀጣዩ የ2026 የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ራሳቸውን እያዘጋጁ ያሉ ሙስሊም እጩዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ነው። ቢቢሲ እንደዘገበው፣ ወጣቱ የሙስሊም ትውልድ በከተማ አስተዳደር፣ በክልል ምክር ቤት እና በፌዴራል ደረጃ በሚገኙ የፖለቲካ መዋቅሮች ውስጥ በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል። ይህ ንቁ ተሳትፎ በዋናነት ትኩረት ያደረገው እንደ ኢስላሞፎቢያ ያሉ የጥላቻ ድርጊቶችን የሚከላከሉ ሕጎች እንዲወጡ፣ የሲቪል መብቶች እንዲከበሩ እና አሜሪካ ከሙስሊሙ ዓለም ጋር ያላት ግንኙነት በፍትሃዊነት ላይ እንዲመሰረት ለማድረግ ነው። ቱርክዬ አናዶሉ ኤጀንሲ እንደዘገበው፣ ሙስሊም መራጮች እንደ ሚቺጋን፣ ፔንሲልቬንያ እና ጆርጂያ ባሉ ወሳኝ ግዛቶች ያላቸው የድምፅ ብልጫ ማንኛውንም የምርጫ ውጤት የመቀየር አቅም እንዳለው ተረጋግጧል። ይህም ትላልቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ እያስገደዳቸው መሆኑን ዘ ጋርዲያን በዘገባው ጠቁሟል። በአጠቃላይ፣ የአሜሪካ ሙስሊሞች ከሌሎች አናሳ ማኅበረሰቦች ጋር በመቀናጀት የሚፈጥሩት አዲስ የፖለቲካ ጥምረት፣ በሀገሪቱ የወደፊት ፖሊሲዎች ላይ የራሱን አሻራ እንደሚያሳርፍ ይጠበቃል። ይህ እንቅስቃሴ ማኅበረሰቡ ከዳር ተመልካችነት ወጥቶ የፖለቲካው ንቁ ተዋናይ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን ሚድል ኢስት ሞኒተር በሰፊው ዘግቧል። © ሀሩን ሚዲያ
Показать все...
29