ru
Feedback
"ኡማ ቲቪ " Tv

"ኡማ ቲቪ " Tv

Открыть в Telegram

ለበለጠ ወቅታዊ መረጃወችን ለማገኘት የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇 https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

Больше
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
46 279
Подписчики
Нет данных24 часа
-877 дней
-54930 день
Архив постов
Фото недоступноПоказать в Telegram
የሳውዲ አረቢያ ፍርድ ቤት በሽተኛ ምንም እንኳን ህገወጥ ነዋሪ ቢሆንም አስቸኳይ ህክምና ሊከለከል እንደማይችል ወሰነ። አንድ የግል ሆስፒታል ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የለለውን ግለሰብ በህክምና እየረዳ ሳለ ህይወቱ አለፈ የግል ሆስፒታሉ ለህክምና ያወጣውን ወጭ መንግስት እንዲከፍለው ወደ ፍርድቤት አቀና ፍርድ ቤቱ የህክምና ክፍያውን የመንግስት ባለስልጣን እንዲከፍል ወሰነ።
Показать все...
68👍 25😁 1🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የዘንድሮ ዓመት ሐጅ በረራ የሚከናወንበት የመጀመሪያ ቀን ታወቀ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፤ የዘንድሮ የሐጅ ሥነ ሥርዐትን የመሄጃና የመመለሻ ቀናትን ይፋ አድርጓል። ምክር ቤቱ ይህን ያሳወቀው ዛሬ ሐሙስ ታኅሣሥ 9/2018 ነው። በዚህም የሀገር ውስጥ የሐጅ መስተንግዶ ሲገባደድ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ የሚደረገው በረራ ሚያዝያ ወር ማገባደጃ እንደሚጀምር ተገልጿል። በመረጃው መሠረት የመጀመሪያው በረራ ሚያዝያ 24/2018 ይደረጋል ተብሎ የጊዜ ሠሌዳ የተቀመጠለት ሲሆን፣ ግንቦት 13/2018 ደግሞ ወደ ሳዑዲ የሚደረግ በረራ የመጨረሻ ቀን ይሆናል። መመለሻ ጊዜን በተመለከተ ከግንቦት 25 ጀምሮ እስከ ሰኔ 8/2018 እንደሚሆን ገልጿል። ከፍተኛ ምክር ቤቱ አያይዞም ለዘንድሮው የሐጅ አገልግሎት በግል ትኬት በመቁረጥ ለሚጓዙ ሑጃጅ ቀድሞ በተመኑ ላይ ከተቀመጠው ዋጋ ላይ 176 ሺሕ 420 ብር ቅናሽ እንደሚያደርግ አስታውቋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለዘንድሮ የሐጅ አገልግሎት ክፍያ የተተመነው የብር መጠን 740 ሺሕ መሆኑን ያስታወቀው ኅዳር 22/2018 ነበር።  ትኬታቸውን በግል የሚያዘጋጁ ሑጃጅ፤ ምዝገባ ጣቢያ በመሄድ ምዝገባ ማድረግ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከምዝገባ በኋላ የሚከፍሉት ክፍያ 563 ሺሕ 580 ብር ይሆናል ተብሏል። ከፍተኛ ምክር ቤቱ በግል ትኬት የሚጓዙ ምእመናን በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ትኬታቸውን እንዲያዘጋጁ እንዲሁም የተቀመጡ የሕክምና ማስረጃ ሠነድ እንዲያሟሉ ጥሪ አስተላልፏል።
Показать все...
18
Фото недоступноПоказать в Telegram
ዓለም አቀፍ የዐረቢኛ ቋንቋ ቀን ዛሬ ሐሙስ እ.አ.አ ዲሴምበር 18/2025 ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕለቱን የዐረቢኛ ቋንቋ ቀን በሚል ሠይሞታል። ዐረቢኛ ቋንቋ የተባበሩት መንግሥታት ቀድሞ ይጠቀምባቸው ከነበሩት አምስት የሥራ ቋንቋዎች መካከል ስድስተኛው ሆኖ የተካተተው በ1973 ነው። ከ2012 ጀምሮ ቀኑን ታስቦ እንዲውል ያደርጋል። ቀኑ በየዓመቱ በተለያየ መሪ ቃል ይከበራል። አምና ከአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ጋር ተቆራኝቶ የነበረው ክብረ በዓል፤ ዘንድሮ መሪ ቃሉ ከፈጠራ (Innovation) ጋር ተገናኝቷል። በዚህ መሪ ቃል ሲታሰብ ዓላማው በትምሕርት፣ በመገናኛ ብዙኃን፣ በቴክኖሎጂ እና በፖሊሲዎች አማካኝነት ዐረቢኛን ይበልጥ ተደራሽ፣ ተለዋዋጭ እና ማኅበራዊ መፍትሔ ሰጪ በሆነ መንገድ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ማሣየት ነው። ዐረቢኛ ቋንቋ በመላው ዓለም 450 ሚሊዮን ተናጋሪ ያለው መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት መረጃ ያመለክታል። ቋንቋው ለዕውቀት ልውውጥ፣ ለሥልጣኔ፣ ለሥን እና ኪን ጥበባት፣ ፍልስፍና ወዘተ ጉልሕ ድርሻ አበርክቷል። ከሴማዊ ቋንቋዎች ውስጥ ከፍተኛ የተናጋሪ ቁጥር ያለው ዐረቢኛ፤ ለዘመናት በኅብረተሰቦች እና በሌሎች ቋንቋዎች ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን የቋንቋ ሊቃውንት ይናገራሉ። ሊቃውንት የዐረቢኛ ቃላት በሌሎች ቋንቋዎች ውስጥ የገቡት በንግድ፣ በትምህርት እና በባሕል ልውውጥ አማካኝነት መሆኑን ይገልፃሉ። እንግሊዝኛ፣ ስፓኒሽ፣ ፈረንሣይኛ፣ ቱርክኛ እና ሌሎች በርካታ ቋንቋዎች በሺሕዎች የሚቆጠሩ ቃላትን ከዐረቢኛ ተውሰው በዕለት ተዕለት ግንኙነት መጠቀሚያ አድርገዋል። ዐረብኛ ለዓለም ካበረከታቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦዎች መካከል የሒሳብና ሣይንስ መስክ ያሣረፈው አሻራ ተጠቃሽ ነው። በመስኮቹ የሚታወቁ አንዳንድ ቃላት መሠረታቸው ዐረቢኛ ቢሆንም በጊዜ ብዛት ከእነዚህ ቃላት መካከል አንዳንዶቹ ተቀያይጠውና ተለውጠው አመጣጣቸው ተዘንግቷል። በምሣሌነት ከሚጠቀሱት ውስጥ በሒሳብ የሚታወቀው “አልጄብራ” ይገኝበታል። ቃሉ የመጣው ከዐረቢኛው “አልጃብር” ሲሆን፣ ትርጉሙ መመለስ ወይም መገናኘት እንደ ማለት ነው።  ከሣይንስና ከሒሳብ ባሻገር በዕለት ተዕለት ቃላቶች ውስጥ ተመሣሣይ ሒደት ሊስተዋል ይችላል። “አልጎሪዝም” (algorithm) የሚለው ቃል የተገኘው ደግሞ በዘጠነኛው መቶ ዘመን በባግዳድ ይኖር በነበረው የፋርስ ምሑር በሙሐመድ ኢብኑ ሙሳ አል ኸዋሪዝሚ ከተጻፈው የእኩልዮሽ መፍትሔ የሚሰጥ ሥራውን አርእስት በመዋስ ነው። “ካራት” (Carat) የሚለው የከበሩ ድንጋዮች ክብደት መለኪያም መነሻው “ቂራጥ” قيراط የተባለው የዐረብኛ ቃል ነው። አንዳንድ ቃላት ደግሞ ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር ሲቀያየጡ ድምጸታቸው ይቀየራል። ለአብነት የእንግሊዝኛው “ጂራፍ” (giraffe) [በአማርኛ ቀጭኔ] የመጣው ከዐረቢኛው “ዘራፋ” زرافة ሲሆን፣ እንግሊዝኛና ሌሎች የአውሮፓ ቋንቋዎች ተመሣሣይ ቃላትን ከራሳቸው ድምጸት ጋር እንዲጣጣም ለማድረግ የመጀመሪያዎቹን ድምጾች በመቀየር ለውጥ አድርገውበታል። አንዳንድ ቃላት በንግድ አማካኝነት ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር ተቀያይጠዋል። ለዚህ ተጠቃሹ “ታሪፍ” (Tariff) የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ነው። ቃሉ “ታዕሪፍ” تَعْرِيف ከሚለው የዐረብኛ ቃል የተወሰደ ነው። ትርጉሙ “ማሳወቅ” እንደማለት ነው። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዐረቢኛ ቋንቋ ቀን ዋንኛ አስተባባሪ በስሩ የሚገኘው የትምሕርት፣ የሣይንስና የባሕል ድርጅት (UNESCO) ነው።
Показать все...
16👍 7
Фото недоступноПоказать в Telegram
27 አመት የፈጀው ረጅሙ የእግር ጉዞ ታሪክ ======================= ➣ ለ27 አመት በእግሩ የተጎዘው የብሪታንያዊው ጀብደኛ ካርል ቡሽቢ ታሪክ ስለ ሰው ልጅ ጽናት፣ ብርቱ ምኞት እና ከወትሮው የተለየ ቆራጥነት የሚተርክ ነው። ይህ ሰው በዘመናዊው ዘመን ከታዩት እጅግ አስገራሚ ጉዞዎች አንዱን ጀምሮ የዓለምን ትኩረት ስቧል። ➣ መነሻው በሀገረ እንግሊዝ ከምትገኘው ትንሽዬ ከሃል ከተማ እስከ ላቲን አሜሪካዋ ቺሊ:: ______ ካርል ቡሽቢ ጉዞውን የጀመረው በ1998 ዓ.ም. ነበር። ትንሿ ብሪታንያዊት ከተማ ሃል (Hull) የሚገኘውን ቤቱን ለቆ፣ ወደ ደቡብ አሜሪካ ጫፍ በረረ። የጉዞው መነሻ ደግሞ በቺሊ የሚገኘው ደቡባዊ ጫፍ ከተማ ፑንታ አሬናስ ነበር። የእሱ ብቸኛና የማይቀየረው ሕግ፡- ወደ ሃል ተመልሶ ለመግባት በእግሩ ብቻ ይሄዳል፤ በሞተር የሚንቀሳቀስ ማንኛውንም ተሽከርካሪ፣ ጀልባ ወይም አውሮፕላን መጠቀም ፈጽሞ አይፈቀድለትም! ➣ የማይቻሉትን መሻገር ____ የቡሽቢ ጉዞ በምድር ላይ ካሉት እጅግ አስቸጋሪ እና አደገኛ ቦታዎች አቋርጧል። • የዳሪየን ጋፕ (The Darién Gap): ጉዞው ከመካከለኛው አሜሪካ እስከ ኮሎምቢያ በሚዘልቀው፣ በዓለም ላይ እጅግ ጥቅጥቅ እና አደገኛ በሆነው ጫካ፣ በዳሪየን ጋፕ መሀል በእግር እንዲያልፍ አስገድዶታል። • የቤሪንግ የባሕር ወሽመጥ (The Bering Strait): እጅግ አደገኛው ፈተና ደግሞ ሰሜናዊውን ምድር ሲያቋርጥ ገጠመው። እ.ኤ.አ. በ2006፣ ከሩሲያ ወደ አላስካ መግቢያ የሆነውን የቀዘቀዘውን የቤሪንግ ወሽመጥ በእግሩ (በበረዶ ላይ) መሻገር ችሏል—ይህም እስካሁን ጥቂት ሰዎች ብቻ የሞከሩት እብደት የሚመስል ድርጊት ነው። ➣ ጽናት ከጊዜ ጋር _____ ጉዞው ከሩብ ምዕተ ዓመት በላይ የዘለቀ ሲሆን፣ በውስጡም የሚከተሉትን አካቷል:: • አህጉራት: ደቡብ አሜሪካን፣ መካከለኛው አሜሪካን፣ ሰሜን አሜሪካን፣ እስያ እና አሁን ደግሞ አውሮፓን አቋርጧል። •የጉዞው የቆይታ ጊዜ በጣም ረጅም የሆነበት ምክንያት በሩሲያ ውስጥ የተከሰቱ ከባድ የቪዛ እና የቢሮክራሲ ችግሮች፣ በአሰቃቂ ጉዞዎች የደረሱ ጉዳቶች፣ እና እንደ ኮቪድ-19 ያሉ ዓለም አቀፍ ክስተቶች ናቸው። • የግል መስዋዕትነት: ካርል በእንቅስቃሴው ውስጥ ህጉን ለመጠበቅ ሲል ለምሳሌ ጠባብ የውሃ መንገዶችን ለመሻገር አንዳንዴም መዋኘት የግድ ይሆንበት ነበር ። ➣ የመጨረሻው ምዕራፍ:: _____ ከአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች በኋላ እና ከ27 ዓመታት ገደማ በኋላ፣ ካርል ቡሽቢ አሁን 'የጎልያድ ጉዞ' ብሎ የሰየመውን ታሪካዊ ጉዞ ወደ ማብቃት ተቃርቧል። አሁን በአውሮፓ ውስጥ የመጨረሻውን የጉዞውን ክፍል እያከናወነ ሲሆን፣ የመጨረሻው ግቡ ደግሞ ጉዞውን ወደ ጀመረበት ወደ ትውልድ ከተማው ሃል መመለስ ነው። ➣ የካርል ቡሽቢ ታሪክ የሰው ልጅ አካል እና መንፈስ መታገስ የሚችለውን ወሰን በግልጽ ያሳያል። የሰውልጅ የሚጓዘው ቦታ ለመድረስ ብቻ ሳይሆን፣ አንድ ሰው የፈለገውን ህልም ለመፈጸም የቱንም ያህል ጊዜ ቢወስድበትም ወይም ቢከብድ ፈጽሞ ተስፋ አለመቁረጥ እንደማሳያ ይሆናል ብዬ አምናለሁ :: ©Seid ebrahim
Показать все...
31👍 12🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንኳን ደስ አልዎ!! አዲሱ ኢ ፓስፖርት በሁሉም የሃገራችን  ክልሎች አገልግሎቱን ጀመረ! ካሉበት ሆነው አስፈላጊ ሰነዶችን በኦንለይን(በቴሌግራም) በመላክ ብቻ  ቀጠሮ አሲዘው፤ በቀጠሮ ቀን ወዳመለከቱበት ቅርንጫፍ ሄደው አሻራ በመስጠት በመደበኛ እና በአስቸኳይ (2 ቀን ወይም 5 ቀን) ፓስፖርቶን በእጅዎ ያድርጉ። አስፈላጊ ሰነዶች   አዲስ ፓስፖርት 1. የታደሰ የቀበሌ /የመስራ ቤት መታወቂያ 2. የተረጋገጠ የልደት ሰርተፊኬት ከ 41 አመት በታች ለሆኑ ፓስፖርት እድሳት 1. የቀድሞ ፓስፖርት የመረጃ ገጽ 2. ፓስፖርት መጠን (3*4) ቅርብ ግዜ የተነሱት ፎቶ   ለተበላሸ/ለጠፋ ፓስፖርት 1. የታደሰ የቀበሌ /የመስራ ቤት መታወቂያ 2. ለፖሊስ ያመለከቱበት መረጃ (ከጠፋ)   ለህጻናት (ከ 18 አመት በታች) 1. የአመልካች አባት ወይም እናት ወይም ሞግዚት የታደሰ መታወቂያ 2. የልጅ የልደት ካርድ 3. ልጅ ከ 5 አመት በላይ ከሆነ ፋይዳ መታወቂያ   ፓስፖርት ለመቀበል 1. የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ 2.ፋይዳ መታወቂያ 3. ኦንለይን ያመለከቱበት ፕሪንት አውት 4. ክፊያ የፈጸሙበት ደረሰኝ (CBE birr, CBE mobile banking, Tele birr) እጅግ ተመጣጣኝ ዋጋ!!! ይደውሉ፤ያማክሩን!!! ለበለጠ መረጃ; 0940958895 ይደውሉ። Join telegram group https://t.me/Urgentpassport157
Показать все...
9💯 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
🇿🇦💔 إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ የታዋቂው የደቡብ አፍሪካ የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ጠበቃ የነበሩት እስማኤል ሙሐመድ አዩብ በ83 ዓመታቸው ወደ አኺራ ሔደዋል አላህ ጀናቱል ፊርደውስ ይስጣቸው!🤲 ለኔልሰን ማንዴላ በእስር ሮቢን አይላንድ ደሴት ላይ ታስረውም ከተፈቱም በኋላ ለረጅም ጊዜ በጥብቅና ከጎናቸው የቆሙ ስመጥር ሰው ነበሩ። ሚስተር አዩብ ለማንዴላ ብቻ ሳይሆን በፀረ አፓርታይድ ትግሉ ጊዜ ለሌሎች በርካታ ታጋዮችም ጠበቃ በመሆንና አፓርታይድን በመታገል ሰፊ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። የቀብር ስነስርዓታቸው ትናንት ረቡዕ ከዙህር ብኋላ በዌስበሪ መካነ መቃብር ተፈፅሟል። We ask Allah to forgive him, have mercy on him, and grant him Jannatul Firdaus. اللهم اغفر له وارحمه #IsmailAyob #NelsonMandela #InMemoriam
Показать все...
36😢 9
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጎንደር ከተማንና ሰሜን ጎንደር ዞን ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ገመገመ بسم الله الرحمن الرحيم የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የጎንደር ከተማን እና የሰሜን ጎንደር ዞንን የዞኑን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የሥራ አፈጻጸም በዝርዝር ገምግሟል። ከፍተኛ ምክር ቤቱ ግምገማውን ያካሄደው አስቀድሞ በተዘጋጁ መመዘኛ ቼክ ሊስቶች (Checklists) ላይ በመመስረት ሲሆን፣ ባለፉት 3 ወራት የተከናወኑ ተግባራትና የተመዘገቡ ውጤቶች ላይ ትኩረት አድርጓል። በውይይቱም የዞኑ ምክር ቤት ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ የቀጣይ እቅዶችም ላይ ጥልቅ ምክክር ተካሂዷል። በግምገማው የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ ✅ ጠንካራ ጎኖችን ማስፋት፦ በግምገማው ወቅት የታዩ ጠንካራ አፈጻጸሞች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና በሌሎች አካባቢዎችም ተሞክሮ እንዲሆኑ አቅጣጫ ተቀምጧል። ✅ እቅዶችን ማሳካት፦ የተቀመጡ እቅዶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብና ጥራት ልክ እንዲሳኩ የላቀ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተመላክቷል። ✅ ተከታታይ ድጋፍና ክትትል፦ የክልሉ ከፍተኛ ምክር ቤት በየሦስት ወሩ በዞኖች በመገኘት መሰል የግምገማና የድጋፍ ስራዎችን በቋሚነት ለማከናወን ከስምምነት ላይ ደርሷል። ይህ የግምገማና የድጋፍ መድረክ በክልሉ የሚገኙ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቶችን ተቋማዊ አቅም ለመገንባት፣ አሰራርን ለማዘመንና ለሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል። Amhara Region Islamic Affairs Higher Council/የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
Показать все...
18
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኻሊድ ቢን ሙህስን ============ እ.ኤ.አ. በ 2013 የካሊድ ቢን ሙህሰን አል ሻሪ ስም ተራ ዜና ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የሰው ልጅ ያናወጠ ክስተት ነበር። የሃያ ሁለት አመት ወጣት የነበረው ይህ የሳውዲ ወጣት 610 ኪሎ ግራም ይመዝናል። ይህም በወቅቱ በዓለም ላይ ካሉት ሁሉ ከባዱ ሰው አድርጎታል። ካሊድ በአልጋው ላይ መንቀሳቀስም ሆነ መዞር እንኳን አልቻለም መራመድ አይችልም። መተንፈስ በዝምታ የተካሄደ ከባድ የዕለት ተዕለት ጦርነት ነበር። ከአልጋው ሳይወጣ በሰውነቱ ውስጥ ተይዞ የማይቀር የሚመስለውን እጣ ፈንታ እየጠበቀ ዓመታት አለፉ።ነገር ግን በዚህ ከፍተኛ የተስፋ መቁረጥ ስሜት መካከል ያልተጠበቀ ነገር ተፈጠረ። የካሊድ ታሪክ ለሟቹ የሳውዲ ንጉስ አብዱላህ ቢን አብዱላዚዝ በደረሰ ጊዜ ምላሹ አስተዳደራዊ ትእዛዝ ብቻ ሳይሆን፣ የካሊድን ህይወት ሙሉ በሙሉ የለወጠው ሰብአዊ ውሳኔ ነበር።አንድ ትልቅ የሕክምና ቡድን በጂዛን ክልል ወደሚገኘው ቤቱ ተዛወረ። የበሩን ፍሬም አውጥተው የክፍሉን ወለል ማጠናከር ነበረባቸው፣ከዚያም ካሊድ በመደበኛ ዝርጋታ ላይ ሳይሆን በሰው ሰራሽ ክሬን ከቤቱ ወጣ። ይህ ትዕይንት እንግዳ እና የሚያም ነበር፣ ነገር ግን ወደ መትረፍ መንገድ የመጀመሪያው እርምጃ ነበር። ካሊድ በሪያድ ወደምትገኘው ወደ ንጉስ ፋሃድ የህክምና ከተማ በአየር ተወሰደ። እዚያም ከ 30 በላይ ዶክተሮች እና ስፔሻሊስቶች ትልቅ ፈተና ገጥሟቸዋል። ይህንን ሰው እንዴት ወደ ህይወት ይመልሱት? ከባድ ጥያቄያቸው ነበር።ካሊድ የጨጓራ ማለፊያ ቀዶ ጥገና ተደረገለት፣ ከዚያም በጣም ጥንቃቄ የተሞላበት አመጋገብ፣ አድካሚ የአካል (አካላዊ) ህክምና እና ረጅም የመልሶ ማቋቋም ክፍለ ጊዜዎች እንቅስቃሴውን ወደነበረበት ይመልሳል እና ሰውነቱ እንደጠፋ ተስፋ አድርጓል። በእያንዳንዱ ኪሎ ግራም ክብደቱን በመቀነሱ ሰውነቱ ብቻ ሳይሆን ስቃዩ እየቀነሰ፣ ፍርሃቱ እየጠፋ፣ ፈቃዱም እየጠነከረ መጣ። በአራት ዓመታት ውስጥ ያልተለመደ የሕክምና እና የሰው ተአምር ተገኝቷል. ካሊድ ክብደቱ በመጨረሻ 63 ኪሎ ግራም እስኪደርስ ድረስ በታሪክ ከተመዘገበው ትልቁ የክብደት መቀነስ 542 ኪሎ ግራም ያህል አጥቷል። ከመጠን በላይ ቆዳን ለማስወገድ ተጨማሪ ቀዶ ጥገናዎችን አድርጓል. ከሁሉም በላይ ግን በነፃነት መተንፈስ የማይችል ሰው መቆም, መራመድ እና ፈገግ ማለት ችሏል። ዛሬ ካሊድ ቢን ሙህሰን አል ሻሪ"ፈገግታ ያለው ሰው" በመባል ይታወቃል። የእሱ ታሪክ ከአሁን በኋላ ስለ ውፍረት ተረት ብቻ ሳይሆን ስለ ርህራሄ ሃይል፣ ባልንጀራውን የመርዳት አስፈላጊነት እና የህይወት ችግሮች ምንም ያህል ከባድ ቢሆኑም ተስፋ አለመቁረጥን በተመለከተ ጥልቅ ትምህርት ነው። ካሊድ ከእስር ቤት ከሆነው አካል ወደ ነፃ የወጣች ነፍስ ተለወጠ መደነቅን፣ ሀዘንን እና ተስፋን የሚቀሰቅስ እና ተስፋ በአንድ ታማኝ ውሳኔ ሊጀምር እንደሚችል የሚያስተምረን ታሪክ ነው፣ ነገር ግን ውሳኔው ሙሉ ህይወትን ሊያድን ይችላል።
Показать все...
76👍 17
ኢዜማ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የራሱን ፖሊሲ ሲያስፈጽም መቆየቱን ገለጸ! የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ ያለማንም ጣልቃ ገብነት የራሱን የፓርቲ ፖሊሲ ሲያስፈጽም መቆየቱን በይፋ አስታውቋል። ፓርቲው ማክሰኞ ታኅሣሥ 7 ቀን 2018 ዓ.ል ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ፤ የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው በተሾሙባቸው ባለፉት አራት ዓመታት የኢዜማን የትምህርት ፖሊሲ ተግባራዊ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጿል። የፓርቲው ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢዮብ መሣፍንት እንደተናገሩት፤ ሚኒስትሩ "ያመኑበትን ሲሰሩ ነው የቆዩት" ያሉ ሲሆን፣ ይህም ለቀጣዩ ምርጫ ቅስቀሳ የሚጠቀሙበት ትልቅ ስኬታቸው መሆኑን ገልጸዋል። ይህ የኢዜማ ይፋዊ መግለጫ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ስጋትና ጥያቄን ቀስቅሷል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሚኒስቴሩን በመሩባቸው የእነዚህ ዓመታት ጊዜያት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዲሁም ኒቃብ እንዳይለብሱ ተከልክለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ እያሉ ሰላት እንዳይሰግዱ/የሰላት ስነ-ስርዓት እንዳያከናውኑ/ በመከልከላቸው ከትምህርት ገበታቸው የተሰናበቱና ለእንግልት የተዳረጉ በርካታ ናቸው። በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የእምነቱ ተከታዮች "ለእምነታችን ነጻነት ይከበር" በማለታቸው የአካልና የሞራል ጥቃት ደርሶባቸዋል። ፓርቲው "ያለማንም ጣልቃ ገብነት የራሳችንን ፖሊሲ አስፈጽመናል" ማለቱ፤ ባለፉት ዓመታት በሙስሊም ተማሪዎች ላይ ሲፈጸም የነበረው አድልዎ እና የሀይማኖት ነጻነት መገፈፍ የፓርቲው እቅድ አካል ነበርን? የሚል መሠረታዊ ጥያቄ አስነስቷል። ኢዜማ በምርጫ 2018 እንደሚሳተፍና እነዚህን ስራዎቹን ለቅስቀሳ እንደሚጠቀምባቸው ቢገልጽም፤ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ግን ይህ "የፓርቲ ፖሊሲ" የተባለው አካሄድ የእምነት ነጻነትን የሚጋፋና ዜጎችን ከትምህርት ገበታ የሚያፈናቅል መሆኑን በተደጋጋሚ ሲያመለክት ቆይቷል። ባለፉት ዓመታት በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የደረሰው የሂጃብ እና የሰላት እገዳ ከፓርቲው እቅድ ጋር ስለመያያዙ የገለጸው ነገር የለም!
Показать все...
25😡 11👍 5
Фото недоступноПоказать в Telegram
42🥰 27😭 11👍 5💯 3😢 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
በሕንድ የቢሃር ግዛት ዋና አስተዳዳሪ የአንዲትን ሙስሊም ዶክተር ኒቃብ መግፈፋቸው ሊወገዝ የሚገባው ድርጊት ነው - አምነስቲ በሕንድ የቢሃር ዋና አስተዳዳሪ ኒቲሽ ኩማር፤ በዚህ ሣምንት በይፋዊ የሹመት መርኀ ግብር ላይ የአንዲት ሙስሊም ዶክተርን ኒቃብ ሲያወልቁ የሚያሳይ ቪዲዮ ከተሠራጨ በኋላ ከፍተኛ ነቀፌታ ተሠንዝሮባቸዋል። ድርጊቱን ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሊወገዝ የሚገባው ነው ብሎታል። የ74 ዓመቱ ኒቲሽ ኩማር፤ ኑስራ ፐርቪን ለተባለች ዶክተር የሹመት ደብዳቤዋን በሰጡበት ወቅት ኒቃቧን ከፊቷ ላይ ዝቅ አድርገው ሲገፏት ታይተዋል። ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ሳምራት ቹድሪ ከኋላ ቆመው የአስተዳዳሪውን ድርጊት ለማስቆም ጣልቃ ለመግባት ሙከራ ቢያደርጉም የጤና ኃላፊው ማንጋል ፓንዴ እና የአስተዳዳሪው ዋና ጸሐፊ ዲፓክ ኩማር ሲስቁ ይታያሉ። ስለ ጉዳዩ የተናገሩት በሕንድ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የቦርድ ሊቀመንበር አካር ፓቴል፤ ድርጊቱን የኑስራ ፐርቪንን ክብር፣ ነፃነትና ማንነት የሚነካ ነው ሲሉ አውግዘውታል። አንድ የሕዝብ አስተዳዳሪ የሴቶችን ሒጃብ በኃይል ማወለቁ ድርጊቱ ተቀባይነት እንዳለው የሚያስመስል መልዕክት ለኅብረተሰብ ያስተላልፋል ያሉት ኃላፊው፤ ማንም ይህን የማድረግ መብት እንደሌለው ገልፀዋል። እንዲህ ዐይነት ድርጊቶች ፍርሃትን በማናር መድልዎን መደበኛ የማድረግ አቅም እንዳላቸውና የእኩልነትና የሃይማኖት ነፃነት መሠረቶችን የሚሸረሽሩ መሆናቸውንም አስረድተዋል። ጥሰቱን በግልጽ በማወገዝ ተጠያቂነት እንዲሰፍንም ጠይቀዋል። አክለውም ማንም ሴት እንደዚህ ዐይነት ክብርን የሚያዋርድ ድርጊት ሰለባ እንዳትሆን አስቸኳይ ርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል። ኒቲሽ ኩማር በዋና አስተዳዳሪነት በሚመሯት ቢሃር ግዛት፤ የሙስሊሞች ቁጥር 17 ነጥብ 5 ሚሊዮን እንደሚገመት ይፋዊ መረጃዎች ያመለክታሉ።
Показать все...
39😭 23👍 5😢 1
Repost from TgId: 2594327312
ቢስሚላህ #አልሀምዱሊላህ ትናንት ማታ የአንድ መስጅድ የማይክና አጠቃላይ የድምፅ ችግር አለበትና እንቅረፍ ብያቹሁ ነበር ። አልሀምዱሊላህ በአላህ ፍቃድ በእናንተ የኸይር ወዳጅ ቤተሰቦች በተባበረ ክንድ በአጭር ጊዜ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለመሰብሰብ ተችሎል አልሀምዱሊላህ ። በቀጣይ ቀናት እቃወቹ ተገዝቶ ለሚመለከተው አካል ሲደርስ አሳውቃቹሀለሁ ። የዳሩር ኡማ ቤተሰቦች በሙሉ በዱንያ ላይ በመልካም ስራ እንዳሰባሰበን ሁሉ ነገ በጀነተል ፊርደውስ ይሰብስበን የቻናሌ ቤተሰቦች አላህ ያቆይልኝ ትለያላቹህ አላህ ይጨምርላቹህ ። በቀጣይ ቀናት መጪው ረመዷን ስለሆነ የተለያዩ የመልካም ስራ ጥሪወች ስለሚኖሩኝ ተዘጋጁ ። የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ ። https://t.me/darulOmah https://t.me/darulOmah
Показать все...
31🥰 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
🥰 6 2👍 1
የተመረጡ 13 ሰወች እያንዳንዳቹህ 1ሺ ብር ነይቱ እስኪ?
Показать все...
3
13ሺ ብር ቀናቶናል የሚሸፍን ?
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
አንድ ወንድም ሀላሌ ላደርጋት የምፈልጋት አንዲት ልጅ አለች እሺ እንድትለኝ ዱዓ አድርጉልኝ ተብላቹሀል ። አላህ ይቀበልህ ያሰብከው ነገር ባማረ መልኩ ይሳካልህ አላህ ይውደድህ ። አላህ በዱንያም በአኼራም በትዳርህ ላይ ይደሰትብህ ልጆቶም እሺ ትበልህና ያማረ ህይወትን አላህ ይወፍቃቹህ እስከ ጀነተል ፊርደውስ የሚዘልቅ ትዳርን አላህ ይወፍቃቹህ ።
Показать все...
30😁 10🥰 1
15ሺ ብር ይቀረናል እቅዳችንን ልንጨርስ ማነው የተመረጠ የሚሸፍነው ?
Показать все...
6
ከ200 ብር እስከ 10ሺ ብር የአላህ ባሪያወች እየተሳተፉ ነው ። አላህ ይቀበላቹህ አላህ ይጨምርላቹህ አላህ የሁለት አለምን ስኬት ይወፍቃቹህ እጣቹህ ይመር ለአላህ ቤት ጉዳይ እንደቆማችሁት አላህ በጉዳዬቻቹህ ላይ ይቁምላቹህ ። ሌሎቻችሁም ወደ መጨረሻ ምዕራፍ ስለደረስን ተሳተፉ
Показать все...
🥰 10 2👍 2
አልሀምዱሊላህ የ120ሺ ብሩ ዘመቻ ሊሳካ 30 ሺ ብር ብቻ ይቀረናል ተሳተፉ ከዝሁር በፊት እንጨርስ ። 1000429906737  መሀመድ ጁድ
Показать все...
10
የ120ሺ ብሩ ዘመቻ ሊሳካ የሚቀረን 40ሺ ብር ብቻ ነው ። ይህ እንዲሳካ በዚህ ዘመቻ ይሳተፉ 4 ሰወች እያንዳንዳቹህ 10ሺ ብር 40 ሰወች እያንዳንዳቹህ 1ሺ ብር 80 ሰወች እያንዳንዳቹህ 500 ብር እንዲሁም አቅም ያላቹህ ሰወች ተሳተፉና እንጨርስ የጁመዓ ኹጥባ በእስፒከራቹህ ይሰማ
Показать все...
6