Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ
Открыть в Telegram
እንኳን ደህና መጡ‼ 📌ማስታወቂያ ለማሰራት👉 @WasuMohammed 📌 ቻናሉን ለመቀላቀል 👉 @Wasulife ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏
Больше2025 год в цифрах

242 600
Подписчики
+8 09224 часа
+10 6267 дней
+19 67430 день
Архив постов
ደሴ - መንበረ ፀሃይ‼
"ሁለቱ ታዳጊዎችን አብረው ገደል ገብተዋል" ነዋሪዎች
ደሴ ከተማ መንበረፀሃይ አካባቢ ዛሬ ታህሳስ 17/2018ዓ.ም የከተማው ደረቅ ቆሻሻ የሚወገድበት ቦታ ተደርምሶ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።
"አንዱ አቶ አለነ ይባላል በህይወት ተርፏል ድምፅን ልከንልሃል።ሁለቱ ታዳጊዎች ግን የቆሻሻው ክምር ሲደረመስ ወደ አዝዋ ገደል ይዟቸው ወርዷል።በህይወት አይተርፉም።ከ5:00 ጀምረን ሞከርን የሚቻል አልሆነም"ሲሉ ነዋሪዎቹ ነግረውኛል።አቶ አለነ ሞላ ከአደጋው የተረፉ ናቸው የዓይን ምስክርነታቸው በድምፅ ተያይዟል።
በጉዳዩ ላይ የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ጥላሁን ታደሰን በስልክ ጠይቂያቸው በሰጡኝ ማብራሪያ <<ክስተቱ ትክክል ነው አጋጥሟል።በቆሻሻ ክምሩ ላይ ለምን እንደወጡ ባናውቅም ሁለት ወጣቶች ቆሻሻው ወደታች ሲደረመስ አብረው ወርደዋል።ህይወታቸው አልፏል።ዛሬ የሚቻለው ሁሉ ተሞከረ ማውጣት ግን አልተቻለም።በሁኔታው አዝነናል።ነገ ተጨማሪ አማራጮችን ተጠቅመን ለማውጣት አስበናል።>>ብለዋል።ኮማንደር ጥላሁንን ለፈጣን ምላሻቸው እያመሰገንኩ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ።
17.04 MB
❤ 37😢 23💔 8😱 1🙉 1
ሹመት‼
የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ‼
በዚህም መሠረት፦
1ኛ, አህመዲን ሙሐመድ (ዶ/ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማ ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ፣
2ኛ, ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የገጠር ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ፣
3ኛ, ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ፣
4ኛ, አማኑኤል ፈረደ (ዶ/ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የአሥተዳደር ዘርፍ አሥተባባሪ፣
5ኛ, መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ፣
6ኛ, አቶ ደረጀ ማንደፍሮ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ፣
7ኛ, አቶ ጥላሁን ወርቅነህ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣
8ኛ, ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
9ኛ, ኢንጅነር ዳኝነት ፈንታ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጅ ቢሮ ኃላፊ፣
10ኛ, አቶ አታላይ ጥላሁን የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ፣
11ኛ, ጋሻው ሙጨ (ዶ/ር) የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
12ኛ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ እና
13ኛ, አቶ ዓባይ መንግሥቴ የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሹመታቸው በምክር ቤቱ ጸድቋል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በአቶ ዓለምአንተ አግደው የቀረቡ 174 የወረዳ ዳኞችን ሹመትም ተቀብሎ ማጽደቁን ኢዜአ ዘግቧል።
Wasu Mohammed - ዋሱ መሐመድ -
Page
❤ 112🤣 23👍 12👏 9😱 5🙏 3😍 3🍌 3🤪 3🏆 1
ሰበር መረጃ‼
እስራኤል ለሶማሊያላንድ ይፋዊ እውቅና ሰጠች‼
እስራኤል ለሶማሊላንድ የሉዓላዊ ሀገርነት እውቅና መስጠቷን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታንያሁ አስታውቀዋል።
❤ 65👍 30😱 8💩 7🔥 4🥰 3😁 3🕊 3🙏 2
ዱዓና ፆለት ለማስተር አብነት‼
📌የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ከወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን ዛሬ ወንድማችን ማስተር አብነትን በሆስፒታል ተገኝተው ጠይቀዋል።
በጉብኝታቸው ወቅት ለወንድማችን ማስተር አብነት ያላቸውን አጋርነት የገለጹ ሲሆን፣ የሚገኝበት የጤና ሁኔታ ፈጥኖ እንዲሻሻልና ወደ ቀድሞ ጤንነቱ እንዲመለስም ልባዊ ዱዓ አድርገውለታል።
📌በተመሳሳይ ማስተር አብነትን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለገብርኤል አማካኝነት በዛሬው ዕለት የጸሎትና የመጽናናት ጉብኝት ተደርጎለታል።
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ወክለው ልዩ ጸሐፊው በመገኘታቸውና በማጽናናታቸው፣ ትልቅ መንፈሳዊ ጥንካሬ እንደሰጠው ገልጾ ልባዊ ምስጋናውን አቅርበዋል።
❤ 136👏 19🙏 11😍 6😭 6😁 5🕊 3🙉 3🙊 2👍 1🔥 1
ኤርትራ ጀመረች‼
የኤርትራ ጦር ድንበር ተሻግሮ በቡሬ ድንበር ትንኮሳ እየፈጸመ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ከስፍራው ወጥቷል፡፡
📌 ጦሩ ወደ አፋር ክልል በመግባት ትንኮሳ እያደረገ ነው ተብሏል፡፡
የኤርትራ ጦር ወደ አፋር ክልል ድንበር አካባቢዎች ሰርጎ በመግባት ወታደራዊ ትንኮሳ እየፈጸመ መሆኑን አዲስ ሪፖርተር ድህረ ገጽ ዘግቧል። ዜናው ሕውሓት “ትዕግስቴ አልቋል” በማለት መግለጫ ከማሰራጨቱ ጋር የተናበበ እንደሆነ ተመልቷል።
የሻብያ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ ትንኮሳ እፈጸመባቸው ካሉ አካባቢዎች መሀል
📌ቡሬ፣
📌ደናክል፣
📌ጋረቦ እና
📌አዋላ ይጠቀሳሉ፡፡
ዘገባው እንዳለው፣ በተለይም በቡሬ አፋር ድንበር አቅጣጫ የኤርትራ ጦር ከፍተኛ ወታደራዊ ንቅናቄ እያደረገ ነው ብሏል፡፡
የኤርትራ ወታደሮች በአካባቢው ሰላማዊ የአፋር ዜጎችን በማዋከብና የክልሉን ድንበር ለመዳፈር ሙከራ ማድረጉን ተከትሎ ክልሉ ድርጊት በአስቸኳይ ካልቆመ ራሱን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ እንዲሁም የፌዴራል መንግስት ጉዳዩን በቅርበት እንዲከታተል በአሰራሩ አግባብ ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል።
❤ 164😁 44👍 27🕊 21😢 12😱 9🤣 7🙏 6🙈 4🫡 4🏆 3
00:28
Видео недоступноПоказать в Telegram
#ቤትየመግዣው ምርጡ ጊዜ ትላንት ነበር ቀጣዩ ምርጥ ጊዜ አሁን ነው
#ቴምርሪልስቴት ሱቅ ሽያጭ የተንጣለለ ዘመናዊ ሞል በቃሊቲ(ገላን ኮንዶሚኒየም)
‼️ቃሊቲ ሱቅ ሽያጭ
👉2.4ሚሊዮን 22ካሬ ቅድመ ክፍያ500,000ብር 4ተኛ
👉2.5ሚሊዮን 25ካሬ ቅድመ ክፍያ 600,000ብር 3ተኛ
👉2.7ሚሊዮን 25ካሬ ቅድመ ክፍያ 800,000 ብር 2ተኛ
👉3.2ሚሊዮን 31ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 1ኛ
👉4.5ሚሊዮን 26ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን ግራውንድ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Telegram :@KalTemerRealEstate
10.03 MB
❤ 14👏 2
ፀማይ ወረዳ‼
በደቡብ ኦሞ ዞን በበና ፀማይ ወረዳ ጎልድያ በተባለ ቀበሌ በቁም እንስሳት ላይ ድንገተኛ በሽታ መከሰቱ ተሰምቷል።በበሽታው በርካታ የቤት እንስሳት መሞታቸው ተዘግቧል።በአካባቢው ለተከሰተው ለዚህ በሽታ አፋጣኝ መፍትሄ ካልተሰጠው ወደተለያዩ አካባቢዎች የመዛመት እድሉ ሰፊ መሆኑም ተሰምቷል።
😭 41❤ 24😱 13😢 4🎉 2
" በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ የጸጥታ ግምገማ እንዲቀርብልን ጠይቀናል" የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን ለመወሰን፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ይፋዊ የጸጥታ ሁኔታ ግምገማ እየጠበቀ መሆኑን አስታወቀ።
ምርጫ ቦርድ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጸው፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የምርጫ ወረዳዎችን በጸጥታ ሁኔታቸው ላይ በመመስረት በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀጠናዎች በሚል በመለየት ሪፖርት እንዲያቀርብ በይፋ ጠይቋል። ቦርዱ ይህ መረጃ ሳይደርሰው በትግራይ ክልል ምርጫ ስለማካሄድ ምንም ዓይነት ውሳኔ ላይ መድረስ እንደማይችል ገልጿል።
የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጄኔራል ታደስ ጥያቄው እንደቀረበላው ገልፀዋል። በክልሉ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ወይስ አይቻልም በሚለው ጉዳይ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተን ምላሽ እንሰጣለን ያሉት ጀነራል ታደሰ ፣ ምላሹም በዚህ ሳምንት ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
❤ 54😍 7🎉 4🥴 3💩 2🕊 2🏆 2🙊 2🔥 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
" በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ የጸጥታ ግምገማ እንዲቀርብልን ጠይቀናል" የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን ለመወሰን፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ይፋዊ የጸጥታ ሁኔታ ግምገማ እየጠበቀ መሆኑን አስታወቀ።
ምርጫ ቦርድ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጸው፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የምርጫ ወረዳዎችን በጸጥታ ሁኔታቸው ላይ በመመስረት በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀጠናዎች በሚል በመለየት ሪፖርት እንዲያቀርብ በይፋ ጠይቋል። ቦርዱ ይህ መረጃ ሳይደርሰው በትግራይ ክልል ምርጫ ስለማካሄድ ምንም ዓይነት ውሳኔ ላይ መድረስ እንደማይችል ገልጿል።
የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጄኔራል ታደስ ጥያቄው እንደቀረበላው ገልፀዋል። በክልሉ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ወይስ አይቻልም በሚለው ጉዳይ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተን ምላሽ እንሰጣለን ያሉት ጀነራል ታደሰ ፣ ምላሹም በዚህ ሳምንት ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
❤ 1
