ru
Feedback
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

Открыть в Telegram

Journalist-at-large

Больше
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
133 780
Подписчики
-1024 часа
-1197 дней
-58130 день
Архив постов
Фото недоступноПоказать в Telegram
ለዘመናት በመንግስት ነዳጅ ላይ ሲደረግ የነበረው ድጎማ ተነስቶ አልቋል፣ ከዚህ በኋላ በአለም አቀፍ ገበያ ሂሳብ ይመራል ተባለ። አሁን ደግሞ አዲስ የ30 በመቶ ግብር ነዳጅ ሊጣል ነው እየተባለ ነው። የዛሬ አመት ደግሞ ሌላ አዲስ ግብር ይመጣል፣ ከዛም ሌላ... ህዝብን የሚያራቁት አዙሪት! @EliasMeseret
Показать все...
😢 1 063👍 130 102😱 65🙏 25🤔 22😁 21🕊 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
ከሶስት ሳምንት በላይ እስር ላይ የቆዩት የሸገር ኤፍኤም ጋዜጠኞች በዋስ ተለቀዋል እንኳን ለቤታችሁ አበቃችሁ! https://tinyurl.com/3m2zd7ch @EliasMeseret
Показать все...
👍 394 118🙏 42🤔 12🕊 12😁 5😱 3
መሠረት ሚድያ ላይ ከሚሰጡ በርካታ አስተያየቶች አንዱ መረጃዎች በፕሪሚየም አባልነት በመሆናቸው ማንበብ አልቻልን፣ አማራጭ ይፈለግ የሚል ነው። ይህ የፕሪሚየም አገልግሎት ባይጀምር ኖሮ ሚድያው በአንድ ሰው ጫና ላይ ወድቆ እስካሁን መቀጠል መቻሉን እጠራጠራለሁ። ለዚህ ግዜያዊ መፍትሄ ተደርጎ የተወሰደው አንዳንድ ዜናዎችን ለሁሉም ክፍት ማድረግ፣ በሳምንት አንድ ቀን (አርብ) ጠርቀም ያሉትን የሳምንቱን ዜናዎች በዩትዩብ ለህዝብ ማቅረብ እና የ30% የፕሪሚየም አባልነት ቅናሽ ማድረግ ነው። ሌላ መፍትሄ እስኪበጅ በዚህ ሊንክ አማካኝነት በ30% የፕሪሚየም አባል ይሁኑ፣ በስምንት ሪፖርተሮቻቸን ከመላው ኢትዮጵያ የሚሰናዱትን እና የትም ቦታ የማያነቧቸውን ሀገራዊ መረጃዎች ይከታተሉ ⤵️ https://meseretmedia.substack.com/30pcoff
Показать все...
👍 223 114😁 79🙏 33😢 18🤔 10
Фото недоступноПоказать в Telegram
መሠረት ሚድያ ከመፍረስ የታደገው ትምህርት ቤት! መሠረት ሚድያ ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም በሰራው አንድ ዘገባው አራት ኪሎ የሚገኘው የምኒሊክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በአሁን አጠራሩ ደግሞ የኮተቤ ዩኒቪርሲቲ የሳይንስ ካምፓስ (STEM Academy) ሊፈርስ መሆኑን መረጃ ለህዝብ አቅርቦ ነበር። ዜናው ከቀረበ ብዙ ቀናት ቢያልፉትም ዛሬ መንግስታዊው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) መረጃው 'ሀሰት ነው' ብሎ ብቅ ብሏል። የሚገርመው ግን እዛው የኢፕድ መረጃ ላይ የመሠረት ሚድያ መረጃ ትክክል እንደነበር ይጠቁማል። ቦታው በመንግስት ስለተፈለገ ትምህርት ቤቱ ሌላ ቦታ እንዲፈልግ በደብዳቤ ተጠይቆ እንደነበር፣ አሁን ላይ ጥያቄው በመቅረቱ ትምህርት ቤቱ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውን በዚሁ ግቢ መጀመሩን ያስነብባል (በምስሉ ላይ በቀይ ይታያል)። ባለፉት ጥቂት ቀናት የደረሰኝ መረጃ እንደሚያሳየው ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ታሪካዊው ትምህርት ቤት ሊፈርስ መሆኑን የሚድያ ዘገባውን አይተው ጣልቃ በመግባት ትምህርት ቤቱን እንደታደጉት ነው። ስለዚህ መሠረት ሚድያ ትምህርት ቤቱን ከመፍረስ ታድጎታል፣ መረጃውም ትክክል እንደነበር ራሱ የመንግስት ሚድያው አረጋግጧል። ታድያ የሌባ አይነ ደረቅ ነገር ካልሆነ ውሸቱ የቱ ነው? #መሠረትሚድያ
Показать все...
👍 599 257🙏 69😁 60😱 5
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንደ ሸገር ኤፍኤም የጋዜጠኞቹን እስር ችላ ያለ ሚድያ እስካሁን አላየሁም! ሁለት ጋዜጠኞቹ ከታሰሩ 17 ቀን የሞላቸው ቢሆንም ሚድያው አንድ ነገር ሳይተነፍስ ቆይቷል። ትናንት መሠረት ሚድያ ሸገር ኤፍኤም ለራሱ ጋዜጠኞች እንኳን ድምፅ ሊሆን አልቻለም የሚል ዜና ማውጣቱን ተከትሎ ዛሬ "በቁጥጥር ስር ከዋሉ 17 ቀን ሆናቸው" የሚል ዜና ይዘው ብቅ ብለዋል። ለራስህ ጋዜጠኛ ድምፅ ካልሆንክ እንዴት ለሌላው ህዝብ ድምፅ ልትሆን ትችላለህ? ሁለቱ ታታሪ ጋዜጠኞች ትግስት ዘሪሁን እና ምንተአምር ፀጋው የታሰሩት በጤና ባለሙያዎች ዙርያ በሰሩት ዘገባ ነው፣ ጥፋት ካለባቸው እንኳን በሚድያ ህጉ መጠየቅ እየተቻለ አሁንም ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ማቆያ ተይዘው ይገኛሉ። @EliasMeseret
Показать все...
436😢 248👍 75😁 15🤔 13
Фото недоступноПоказать в Telegram
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ አርቲስት ችሮታው ከልካይ፣ አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ ወዘተ... እባካችሁ ይህን ህዝብ አታዘርፉ! "ያለ ምንም ኤምባሲ ኢንተርቪው ሰዎች ወደ ጣልያን እና ካናዳ እየሄዱ መሆኑን ሰምታችኋል? ወደነዚህ ሀገራት ለመሄድ የኤምባሲ ኢንተርቪ ሳይሆን ፓስፖርት እና የእኛ እጅ ብቻ ነው የሚያስፈልጋችሁ" (ቪድዮ: https://www.facebook.com/share/v/16iWpRzpFp/) "ካናዳ በፓስፖርት ብቻ ኑልኝ እያለች በአዲስ ዓመት እዚህ ልታሳልፉ ነው? (ቪድዮ: https://www.facebook.com/share/v/19xypxrE9b/) ይህ እንግዲህ ከሰሞኑ 'Fly Addis' በተባለ ድርጅት ዝነኛ ግለሰቦችን በመጠቀም እያሰራጨ ያለው የተሳሳተ፣ አንዳንዴም ነጭ የማጭበርበር ተግባር ነው። በዚህ ድርጊት ላይ ከላይ ከተጠቀሱት ግለሰቦች በተጨማሪ ሌሎች እውቅ ግለሰቦችን በማሳየት ህዝብን በዚህ መልኩ እያሳሳቱ ገንዘብ እየተቀበሉ ነው። የሚያስተዋውቁት ስልክ የማይሰራ ሲሆን በአካል የሚሄዱትን ግን ገንዘብ እየተቀበሉ ይገኛሉ፣ አብረናቸው እንሰራለን የሚሏቸውን ተቋማትም ለማናገር ሞክሬ 'ፍፁም ውሸት' የሚል ምላሽ ነው ያገኘሁት። መች ይሆን ይህ ህዝብ እንዲህ አይነት ድርጊት ሀሰተኛ መሆኑን አውቆ የሚጠነቀቀው? የመንግስት አካላትስ እንዴት ቁጥጥር ማድረግ ተሳናቸው? ታዋቂ አርቲስቶች/ግለሰቦችስ ለምን እንዲህ አይነት ድርጊት ላይ ይሳተፋሉ። በተመሳሳይ 'ፊን ቴክ' የተባለው ድርጅት የሰራው ስራም ተጋልጧል (ሊንክ: https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/c6d?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7) ከዚህ በፊትም ብዬዋለሁ፣ ብራንድ አምባሳደር ምናምን እየተባለ ታዋቂ ግለሰቦችን በካሜራ እያሳዩ ህዝብን መዝረፍ በጣም ተለምዷል፣ ለዚህ ደግሞ የፕሮግራም አዘጋጁ አብርሀም ግዛው ብዙዎቹ ላይ በአንድም በሌላ መልክ እየተሳተፈ ነው። ህዝቡን አትዝረፉ፣ አታዘርፉ፣ ካልሆነ በስም እየጠራን ማጋለጥ እንቀጥላለን። @EliasMeseret
Показать все...
515👍 128😢 104🙏 28🤔 9😱 4🕊 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ልብ ያለው ልብ ይበል 😀 ኧረ ተከርባቹን የቀድሞ ሚኒስቴር ዴኤታ እየሰማችሁት፣ ከባድ attention ይፈልጋል። #useless @EliasMeseret
Показать все...
😁 923👍 113 85🙏 15😢 14🤔 2😱 2🕊 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ህዝቡምንይላል "ከሚከተሉት ግለሰቦች ውስጥ ለህዳሴ ግድብ ዕውን መሆን 'በአንፃራዊነት' ከፍተኛውን ድርሻ የተወጡት ማን ናቸው?" ለሚለው ጥያቄ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ በ6 ሰዓት ውስጥ ብቻ 24,500 ሰው ድምፅ ሰጥቷል። ውጤቱም የሚታየው ነው፣ መልካም አዳር! @EliasMeseret
Показать все...
642👍 268😁 64🙏 56😢 18🤔 8😱 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
ከ585,882 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች መሀል ያለፉት 48,920፣ የወደቁት ደግሞ 536,962 ሆነዋል። በሌላ አገላለፅ 91.6% ተማሪዎች ወድቀው 8.4% ብቻ አልፈዋል ነው። ለዚህ የትምህርት ስርዐቱን የሚመሩት አካላት በዋነኝነት፣ መንግስትም በየደረጃው ሀላፊነት ወስዶ ምን እየሆነ እንደሆነ ለህዝብ ሊያስረዱ ይገባል። ይህ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ትውልድ ምን ሊሆን ነው? ከሰሞኑ እየታፈሰ ወደ ጦር ማሰልጠኛ እንደሚገባው ትውልድ እጣ ፈንታቸው ይሆን? ያሳዝናል! @EliasMeseret
Показать все...
😢 943 129😁 115👍 62🤔 61😱 35🙏 14🕊 5
#ህዝቡምንይላል ከሚከተሉት ግለሰቦች ውስጥ ለህዳሴ ግድብ ዕውን መሆን "በአንፃራዊነት" ከፍተኛውን ድርሻ የተወጡት ማን ናቸው?Anonymous voting
  • አፄ ኃይለ ላሴ
  • ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ
  • ጠ/ሚር ሐይለማርያም ደሳለኝ
  • ጠ/ሚር አብይ አህመድ
  • ኢ/ር ስመኘው በቀለ
0 votes
1 447👍 343😁 334🙏 100🕊 77🤔 46😢 18😱 17
ትናንት ምሽት እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ታዳጊዎች ለዛሬ ጠዋቱ ፕሮግራም በመስቀል አደባባይ ልምምድ እያረጉ በነበረበት ወቅት የመድረክ መደርመስ አደጋ አጋጥሟቸው ተጎድተዋል፣ በርካታ ቤተሰብ ለሊቱን ሙሉ በየሆስፒታሉ በዋይታ እና ለቅሶ ሲንከራተት ነው ያደረው። ትናንት ምሽት ተጎጂዎቹን ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በየሆስፒታሉ እየዞሩ የጎበኙ ቢሆንም የመንግስት ሚድያዎች እንዲዘግቡ አልተፈቀደላቸውም፣ ባለስልጣናቱም እንደተለመደው በማህበራዊ ገፆቻቸው እንኳን አላጋሩትም። የሚያሳዝነው ደግሞ ከየትምህርት ቤቱ ጎበዝ ተማሪዎች ተብለው የተመረጡት እነዚህ ታዳጊዎች የአዲስ አመት በዓልን ጨምሮ ለበርካታ ቀናት ከቤተሰብ ተለይተው ስድስት ኪሎ ካምፓስ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገው የቆዩ ነበሩ። በአደባባይ የደረሰ አደጋን በዚህ ደረጃ መሸፈን ምን ያስፈልጋል? ለማንኛውም ለታዳጊዎቻችን ፈጣሪ ይድረስላቸው፣ በቶሎ ይማራቸው። መሠረት ሚድያ ላይ ለሁሉም ክፍት ተደርጎ የቀረበውን ይህን መረጃ ያንብቡ ⤵️ https://tinyurl.com/4s2tz2ju
Показать все...
😢 420 143👍 30😁 12😱 11🕊 11🤔 6
የ 'ብራንድ አምባሳደር' በሚል የምትሰየሙ አርቲስቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች በስማችሁ የሚደረግ አላግባብ ነገር ካለ ቀድማችሁ ንቁ፣ ባይሆን እንኳን ዘግይታችሁ ስታውቁ ለህዝብ አሳውቁ። እዚህ ጋር አንድ እና ሁለት ሚሊዮን ብር እያሳየ በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚጫወት ስላለ ተጠያቂነት ስለሚይመጣ ይታሰብበት። በዚህ ዙርያ የመሠረት ሚድያ ዘገባ ⤵️ https://tinyurl.com/2ckvm8ba
Показать все...
👍 212 73😁 42🤔 13😱 8
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፣ አደረሰን! መልካም አዲስ ዓመት! @EliasMeseret
Показать все...
🙏 444 175👍 57🕊 33
Фото недоступноПоказать в Telegram
አንዳንድ ሰው በዛሬው ዕለት ሊሰማው የማይፈልገው ግን ጥሬ ሀቅ! በያዝነው የ2017 ዓ.ም ብቻ የኤሌክትሪክ ደንበኞች ላይ 400 ፐርሰንት እና ከዛ በላይ የሆነ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ተደርጓል፣ ለዚህ ደግሞ አይ ኤም ኤፍ (IMF) የሰጠው ብድርን አያይዞ ያስተላለፈው ቀጭን ትዕዛዝ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። የትውልድ ቅብብሎሽ የሆነው ህዳሴ ዛሬ ተመርቋል፣ ይሁንና የሚያመነጨው ሀይል ወደ ህዝብ ደርሶ ሀይል ወደየገጠሩ እና መንደሩ ካልገባ እና በተቃራኒው የዋጋ ጭማሪ ከገጠመው ህዝቡ 'ለምን?' የሚል ጥያቄ ማንሳት ብቻ ሳይሆን 'ግድቡ የኔ ነው' ማለት ማቆሙ አይቀርም። በተመሳሳይ ዳንጎቴ ይገነባዋል የተባለው የማዳበርያ ፋብሪካ ለገበሬው ዋጋ ከመቀነስ ይልቅ ይባስ ከጨመረበት ብሎ እንደማሰብ ነው። ህዳሴ 'ዳግማዊ አድዋ ነው' ከተባለ ከአበዳሪዎቹ የሚደርስ ጫናን በተቻለ መጠን ለማስቆም ባይቻል ለመቀነስ መጣር አለብን። ከእነሱ በሚመጣ ጥያቄ ዜጎች ከዓመት በፊት ለኤሌክትሪክ ከሚከፍሉት አሁን አራት እና አምስት እጥፍ ሲከፍሉ ማየት ከእንደዛሬው ካለ የደስታ ዜና ጋር አብሮ ሲታሰብ ይከብዳል። አሁን ላይ በኤሌክትሪክ እየተንበሸበሹ ያሉት እንደ ቻይና እና ኤምሬትስ ካሉ ሀገራት የሚመጡ የክሪፕቶ ማይኒንግ (crypto mining) ኩባንያዎች እና ለእነሱ ኤሌክትሪክ ሲሸጥ ሞቅ ያለ የድለላ እና የኪስ ገንዘብ የሚያገኙት የመንግስት ሀላፊዎች ናቸው (በዚህ ዙርያ መሠረት ሚድያ ላይ በቅርቡ ዘገባ ይኖራል)። መልካም አዳር! @EliasMeseret
Показать все...
1 071👍 424🙏 90😢 28🤔 25🕊 10😱 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
በህዳሴ ግድብ ዙርያ የኢትዮጵያን ድምፅ ካሰማንባቸው አለም አቀፍ ዜናዎች በከፊል! ከሁሉም 'Ethiopia to fill disputed dam, deal or no deal' የሚለው ልዩ ዘገባ ኢትዮጵያ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር ስምምነት ላይ ባይደረስም ውሀ ሙሌት ልትጀምር እንደሆነ የታወቀበት የመጀመርያው አለም አቀፍ ዜና ነበር፣ የግብፁ ፕሬዝደንት በብስጭት በቀጥታ ምላሽ የሰጡበትም ነበር። #ItsMyDam
Показать все...
👍 420 206🙏 27😁 23😱 5🤔 2🕊 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
በትውልድ ቅብብሎሽ እውን የሆነ ድንቅ የሀገር ኩራት! #ItsMyDam
Показать все...
764👍 163🙏 30🕊 9😁 1😱 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኮንፈረንስ በተካሄደ ቁጥር ይህ ድርጊት ለምን? በየአመቱ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባን ጨምሮ በጣም ብዙ አለም አቀፍ ኮንፍረንሶችን ከ10 ዓመት በላይ አዲስ አበባ ላይ በጋዜጠኝነት ተካፍያለሁ። ታድያ በዚህ ሁሉ ወቅት የከተማዋ ነዋሪዎች መንገድ ሲዘጋ በትራንስፖርት እጥረት ይንከራተቱ ይሆናል እንጂ ካለፈው አንድ እና ሁለት ዓመት ወዲህ እንደሚደረገው ዘግናኝ የሆነ አፈሳ እና ወደ ማጎሪያ ቦታ መጣል ሰምቼም፣ አይቼም አላውቅም። ከሰሞኑ በርካቶች በአዲስ አበባ ይካሄዳል የተባለውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ፣ የአፍሪካ-ካሪቢያን ስብሰባ እና የግድቡ ምርቃት ተብሎ የዚህ ድርጊት ሰለባ እየሆኑ ነው። መሠረት ሚድያ እንደዘገበው አንዳንዶቹ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ውሃ ልማት አካባቢ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኝ 'ማቆያ' በሚባል መጋዘን ውስጥ ተይዘው ይገኛሉ። ብትሩ በተለይ የኔ ብጤዎች እና በመንገድ ዳር ስራ ላይ የተሰማሩት ምስኪን ዜጎች ላይ ማረፉ ያሳዝናል። ለምሳሌ ዛሬ አዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር እንግዳ ይመጣል ተብሎ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ያሉ የኔ ብጤዎች በሙሉ ተጭነው ተወስደዋል። አንድ የአይን እማኝ እንዳለኝ "በአሁን ሰአት በአራት ፓትሮል በተኙበት እየቀጠቀጡ እንደ ኩንታል ማዳበሪያ እየጫኗቸው ነው፣ አካለ ጎዶሎ አልቀረ፣ የልጅ እናት አልቀረ።" ሌላ የደረሰኝ ምስክርነት እንዲህ ይላል: "አንድ የልጅ እናት ጨቅላ ልጇን አዝላ ከፀጥታ ሀይሎች ለማምለጥ  ስትሞክር ህፃኑ ወድቆ ጭንቅላቱ ተሰንጥቆ ደም በደም ሆኖ ፊቱ በደም ተሸፍኖ ነበር። ምስሉን በስልኬ ላስቀር ሞክሬ ፍርሀት ስላለ ተውኩት፣ ሰውን በተኑት።" ታድያ ኮንፈረንስ በተካሄደ ቁጥር ይህ ድርጊት ለምን? @EliasMeseret
Показать все...
😢 709 192👍 51😁 21🤔 9🕊 8😱 6
ስለ ህዳሴ ግድብ ሲነሳ የታላቁ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ አባት አባ በቀለ ትዝ ይላሉ! በአንድ ወቅት አባ በቀለ ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ ሰምቼ  "ምን እናግዝዎ?" ስላቸው "አሁን አቅሜም እየደከመ ነው፣ ልጄ ስመኘው በህይወት ቢኖር ኖሮ ማረፊያዬ መካነ መቃብር እና የዲያቆናት መፅሀፍ ማንበብያ ትንሽ ዳስ ስራልኝ እለው ነበር" አሉኝ። አስቡት፣ የህዳሴ ግድብን የሚያክል ፕሮጀክት የሚመራ ኢንጂነር ወላጅ አባት! ያንን ተከትሎ መረጃውን እዚሁ ማህበራዊ ሚድያ ላይ አጋርቼ በሁላችሁም በተደረገ ርብርብ ከግማሽ ሚሊየን ብር ተሰባብስቦ ያሰቡትን ሁሉ አሰርተው በ96 አመታቸው አርፈዋል። የኢ/ር ስመኘውን ህይወት ባይመልስም ቢያንስ ህዝብ አባታቸውን በዚህ መልኩ መካሱ ደስ ያሰኛል። @EliasMeseret
Показать все...
🙏 835 358👍 100😢 33🕊 13😱 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
የ #ItsMyDam ታሪክ! ጉዳዩ የሆነው የዛሬ አምስት አመት ገደማ ነው። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በስካይላይት ሆቴል በግድቡ ዙርያ ውይይታቸውን አድርገው እኩለ ለሊት ገደማ ላይ ካለ ስምምነት ጨረሱ። የውሀ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ከስብሰባው መጠናቀቅ በሁዋላ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አንዲት ለውጭ ሀገር ሚድያ የምትሰራ ጋዜጠኛ "ግድቡን ማነው የሚያስተዳድረው?" የሚል ጥያቄ ሰነዘረች። ኢ/ር ስለሺ በመገረም "ሌላ ማን ያስተዳድረዋል? ግድቡ የኔ ነው... It's my dam" የሚል መልስ ሰጡ። ከመሸ የተጠናቀቀው ይህ ጋዜጣዊ መግለጫ አልቆ ወደ ቤት እየተመለስኩ የኢ/ር ስለሺ "ግድቡ የኔ ነው... It's my dam" የሚለው አባባል በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ። ሀሳቤ የነበረው ይህ ድንቅ አባባል በሌሎች ሚድያዎች ባይቀርብ ተረስቶ እንዳይቀር ነበር። ከዛም ንግግሩ ያለበትን ቪድዮ በፌስቡክ፣ ትዊተር እና ቴሌግራም አካውንቶቼ ላይ ከቀናት በኋላ ለቀቅኩት፣ በርካታ ሰዎችም ንግግሩን ሼር እና ሪትዊት አደረጉት። ከዛ በሁዋላ ያለው ታሪክ ነው! በቅርብ አንድ የመንግስት ሀላፊ እንዳሉት ንግግሩ "ታግሎ ማታገያ" ከመሆኑም በላይ #ItsMyDam የኢትዮጵያውያን ሶሻል ሚድያ ተጠቃሚዎች በግድቡ ዙርያ መነቃቂያ፣ ለግድቡ የሎተሪ ሽያጭ ማካሄጃ፣ የቴሌቭዥን ማስታወቂያዎች ማጀብያ፣ የቲሸርቶች እና ማስኮች ማጌጫ፣ ለግብፅ ሚድያዎች አጭር መልስ መስጫ...ወዘተ ሆኗል። #ItsMyDam @EliasMeseret
Показать все...
851👍 218🙏 52😁 30🕊 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ከሰሞኑ ኦቪድ በተባለው ድርጅት ዙርያ በተለያዩ ሚድያዎች መረጃ ሲወጣ ፋናዬ 'ኦቪድ የማነው?' ብሎ ማርከሻ እና ማደንዘዣ መሰል ቪድዮ ለቋል። ኧረ እንከስሀለን ብለው ሲዝቱብኝም ነበር፣ የት ደርሶላቸው ይሆን? @EliasMeseret
Показать все...
😁 290🤔 53 36👍 18😢 1🕊 1