ru
Feedback
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

Открыть в Telegram

Journalist-at-large

Больше
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
133 743
Подписчики
-4624 часа
-1437 дней
-61730 день
Архив постов
Фото недоступноПоказать в Telegram
ፋና ብሮድካስቲንግ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በኦሮሚያ ክልል የታፈሱበት ሰሞንኛ ድርጊት "ሀሰት" መሆኑን ሊነግረን ቀጠሮ ይዟል ማስረጃዬን ላቀርብ አሰብኩና ለካ እነዚህ ሚድያዎች "ውሸት ነው" ብለው ከዘገቡት "እውነት ነው ማለት ነው" የሚለው ትዝ አለኝ እና ተውኩት። ቢያንስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ኮመንት ላይ የሰጡትን አስተያየት አንብቡ። ከተመሠረተ ሶስት ወር እንኳን ያልሞላው መሠረት ሚድያ ከዚህ በተሻለ መረጃዎችን ከነማስረጃቸው ለህዝብ አቅርቧል። #አትዋሹ #StopFakeNews @EliasMeseret
Показать все...
👍 1 521😁 189 116🙏 37🤔 35😢 14😱 10🕊 10
በአዲስ አበባ እና አዳማ የጀመረው አፈሳ እና የገንዘብ ድርድር ወደ ሻሸመኔ እና ሌሎች ከተሞች ተስፋፍቷል ሻሸመኔ 010 ቀበሌ ስታድየም ዋናው በር ፊት ለፊት ባለው መጋዘን ውስጥ እና 02 ቀበሌ ምክር ቤት ጀርባ (ብሔራዊ ትምህርት ቤት ጎን ባለው አዳራሽ) በርካታ ወጣቶች ታጭቀው እንደሚገኙ የሚደርሱኝ ጥቆማዎች ያሳያሉ። "ዙሪያ ገባው በሚሊሻ ተከቧል፣ ቤተሰብ አይደለም መጠጋት ለራስም ያሰጋል። ግን ምን እየሆነ ነው ያለው?" ብለው የሚጠይቁት ነዋሪዎች ከመሸ መንቀሳቀስ ከባድ እንደሆነባቸው እና የሚሊሻው አፈሳ ተባብሶ እንደቀጠለ ተናግረዋል። "ስልክህን ይፈተሻል ብለው መንገድ ላይ ይቀበሉህና ጠዋት ሚሊሻ ቢሮ ና ይላሉ። ስትሔድ ለማነው የሰጠኸው ተብለህ ወንጀለኛው አንተው። መሮናል። እኔም አንድ የኦሮሞ ወጣት ነኝ የታገልኩት ግን ለዚህ አልነበረም" በማለት መልዕክቱን ያደረሰኝ ደግሞ አንድ የከተማው ወጣት ነው። @EliasMeseret
Показать все...
😢 751👍 231😁 54 25🤔 23🕊 18🙏 12😱 10
ከሰሞኑ በስፋት ህዝብን እያስጨነቁ ያሉ፣ ብዙም ትኩረት ግን ያላገኘው የወጣቶች አፈሳ ነው። በአዲስ አበባ እና እንደ አዳማ ባሉ ከተሞች ድርጊቱ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ሚድያዎቻችን ሽፋን እንኳን እየሰጡት አይደለም። የሚገርመው በአዳማ በፋብሪካዎች እና በአዋሳኝ ቦታዎች ባሉ ኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ጭምር ታፍሰው ተወስደው በገንዘብ እየተለቀቁ ነው። በግልፅ እገታ እንዲህ ተጀመረ ማለት ነው? እስቲ ህዝብ የሚለውን ተመልከቱ: - "ሰላም ኤሊያስ፣ በአዳማ ወጣቶች ከቤት መውጣት አልቻልንም፣ አፈሳ በሚል ምክንያት መታወቂያ ያለውም የሌለውም በሚሊሻ ይያዝና የቀበሌ አዳራሽ ውስጥ ይታጎራል፣ የኔ ሰፈር አዳማ ቦሌ የሚባለው ቦታ ነው፣ አንድ ጓደኞዬ የግል ዩኒቨርስቲ የሚማር በ 16/02/2017 ቀን 10:00 ሰአት የተያዘ  ከተያዘ ዛሬ 14 ኛ ቀኑ ነው።  ታፍሰው nafyad ት/ቤት ያለዉ ቀበሌ ገብተው ከቤተሰብ ጋር እንኳን መገናኘት አይቻል፣ ቤተሰብ በዱላ ነው ሚያባሩት ሊጠይቅ የሄደን ሰው ። ብር ያለው 50 ሺህ ብር ከፍሎ ይወጣል፣ እሱም የትኛው ቀበሌ እንደገባክ ከታወቀ ነው፣ ስልክ ይነጠቃል ዛሬም በጠራራ ፀሀይ በማፈስ ላይ ናቸው፣ ሁሉም ነገር በጣም ነው ሚያስጠላው።" - "ሰላም፣ ባለፈው ወንድሜ በኦሮሚያ ፖሊስ ቡራዩ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አሸዋ መዳ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ገብርኤል ሰፈር ፖልስ ጣቢያ ነበር እዛው አከባቢ በነበረው ስውር ቤት እስከ 1,400 ልጆች ታፍነው ነው ያሉት እና እኔም እግዚአብሔር ረድቶኝ 15,000 ብር ከፍዬ ወንድሜን አስፈትቻለሁ። ካልሆነ ይዘውት እንደምሄዱ ስያስፈራሩኝ ነው ሄጄ  ያስፈታሁት። ብዙ ታፍነው ነው ያሉት ቤተሰብ እንኳን የት እንዳሉ የማያውቃቸው እና በደላላ ጥበቃ ትሆናላችሁ ተብለው እና በ10 ቀን ውስጥ 7,000 ብር እንደሚከፈላቸው ተነግሮ ነው የሸወዷቸው እና ደላላው 5 ልጆች ካመጣላቸው 10,000 ብር ይከፍላል።" - "አዳማ ከአዲስ አበባ በባሰ መታወቂያ ኖረህም አኖረህም በቃ እየታፈስክ ነው የምትወሰደው ። በአሁን ሰዓት ሰዎች ያውም ምንም የስራ እንቅስቃሴ በጠፋበት ጊዜና ኑሮ እንዲህ እንደ እብድ ለየብቻ ማስወራት በጀመረበት ጊዜ ተንቀሳቅሶ የተገኘውን ለቤተሰብ ይዞ ለመግባት የአፈሳው ነገር ከባድ በመሆነ ብዙ ሰው በፍራት ረሃቡን ተጋፍጦ ከቤት ከመውጣት እየታቀበ ነው።" - "አዳማ ላይ እናቶች ምነው ወንድ ልጅ ባልኖረኝ የሚሉበት ዘመን መቷል መንገድ ላይ የተገኘ ሁሉ እየታፈሰ ነው" - "እንዴት አደርክ? ጓደኛዬ ወደ ውጭ የሚልከው ምርት አምጥቶ አዳማ ማበጠሪያ እያስበጠረ 10 ሰራተኞችን እዛው ድርጅቱ ውስጥ ያሉትን በአፈሳ ወሰዷቸው ትናንት" ይሄ ከብዙ በጥቂቱ ነው፣ ፈጣሪ ይሁነን። መልካም ቀን። @EliasMeseret
Показать все...
😢 828👍 304 39🤔 36🕊 21😁 18🙏 7😱 6
Фото недоступноПоказать в Telegram
የትብብር ጥያቄ፣ ትናንት ምሽት 1:10 ገደማ ከጎሮ ወደ ፍየል ቤት በሚወስደው መንገድ ታክሲ የተሳፈሩ ግለሰቦች ሶስት ፓስፖርት ጥለው ወርደዋል (ታክሲው ሱዙኪ)፣ ፓስፖርቶቹ ቪዛ የተመታባቸው ሲሆን ዛሬ ምሽት 4 ሰአት ወደ አሜሪካ ጉዞ እንዳላቸው ነግረውኛል። የቪዛዎቹ ባለቤቶች እሸቱ ኢሳያስ፣ ሜሮን ናጆ እና የህፃን ንፅሀፍቅር እሸቱ ነው። ፓስፖርቱን ያገኛችሁ ወገኖቻችን በዚህ ቁጥር ደውላችሁ ብትሰጡን ወረታውን እንከፍላለን ብለዋል 0935497085 0945306045
Показать все...
😱 190👍 158 44😢 44🙏 32😁 10
Фото недоступноПоказать в Telegram
#FactCheck በተቃራኒ ጎራ የቆመ አካልን መቃመም አንድ ነገር ነው፣ ነገር ግን እንዴት አንድ 'የተማረ' የተባለ ሰው ያውም የወጣበት ማህበረሰብ ላይ የድሮን ጥቃት ተፈፅሞ ህጻናት እና ነፍሰ ጡር ሴቶች ተገደሉ ተብሎ በሚድያዎች ሲዘገብ ውሸት ነው ለማስባል ሀሰተኛ መረጃ ያሰራጫል? ጌትነት አልማው የተባለው እና ብዙ ግዜ ብሔራዊ ቴሌቭዥን (EBC) ላይ ጭምር እየቀረበ ትንታኔ የሚሰጥ ግለሰብ ቢቢሲ በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ህጻናትን እና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን በተመለከተ ዛሬ የሰራውን ዘገባ በማንሳት "ስትዋሹም እየተናበባችሁ" በማለት ቢቢሲ ለአማራ ክልል ዜናው የተጠቀመበት ምስል በትግራይ ጦርነት ወቅት ትግራይ ቴሌቭዥን የተጠቀመበት የቆየ ምስል ነው ብሏል። ይሁንና ትግራይ ቴሌቭዥን በወቅቱ፣ ማለትም ኦክቶበር 24/2022 ባወጣው ዘገባው ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት የተጠቀመውን ምስል ሳይሆን ሌላ የድሮን ጥቃትን ያሳያል የተባለ መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል (ምስሉ ላይ በስተቀኝ ተያይዟል)። ስለዚህ ግለሰቡ ቢቢሲ ለአማራ ክልል ዘገባው የቆየ የትግራይ ምስል እንደተጠቀመ አድርጎ ያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ተረጋግጧል። በንፁሀን ደም እንዲህ መሳለቅ ያሳዝናል! Via ኢትዮጵያ ቼክ @EliasMeseret
Показать все...
👍 752😢 316🙏 40 37🤔 23😁 6😱 2🕊 2
Показать все...
😢 353👍 32😱 26 8🕊 7🤔 2
😢 395👍 82🙏 22 18🤔 8😱 8😁 3
አንዳንዴ የሀገራችን መሪዎች ለጥቂት ደቂቃ በኢንቦክስ የሚላኩ ቅሬታዎችን፣ ጥቆማዎችን፣ የእርዱኝ ተማፅኖን እና የድረሱልኝ ጥሪን አብረውኝ ቁጭ ብለው ባዩት ብዬ እመኛለሁ ይሄ ከባለፈው አንድ እና ሁለት ቀን በጥቂቱ ነው። @EliasMeseret
Показать все...
😢 280👍 102 21🤔 6😱 3🙏 1
#Update ቅድም ለፍለጋ ያጋራሁትን የህፃን ልጅ ፎቶ ተከትሎ በርካታ በዱባይ እና በኢትዮጵያ የሚገኙ ሰዎች መረጃ ሰጥተዋል እናት ልጇን ካለ ጋብቻ ዱባይ ውስጥ ከወለደች በኋላ ለአንድ አመት በክፍሏ በመደበቅ (ክትባትም ሳታስከትብ) አቆይታት ነበር። አባትም ስላልታወቀ ፓስፖርቷን ተነጥቃ በአንድ የመውጫ (exit) ዶክመንት ወደ ኢትዮጵያ ከሶስት ቀን በፊት ተጠርዛ ተላከች። ከዛም ነው ትናንት ምሽት ልጇን ሆሳዕና ውስጥ የጣለቻት። "ቤተሰቦቼ ይገሉኛል ስትል ሰምተናል" ብለው ከዱባይ አንዳንድ ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎች ተናግረዋል። ከዚ በሁዋላ ጉዳዩ እና የተገኘው ዶክመንት ለፖሊስ ይተላለፋል፣ የግለሰቧም ማንነት ስለታወቀ የሆሳዕና ፖሊስ በቅርቡ እንደሚያሳውቀን ተስፋ አረጋለሁ። መልእክቱን አይታችሁ ላስቀመጥኳቸው ቁጥሮች (ለሚሚ እና ለምስክር ሺበሺ) በመደወል ላሳወቃችሁ ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ። @EliasMeseret
Показать все...
👍 590😢 143 36🙏 32🤔 10😁 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ይህች ህፃን ትናንት ምሽት 3:30 ላይ በሆሳዕና ከተማ መንገድ ላይ ተጥላ እንደተገኘች የደረሰኝ ጥቆማ ያሳያል። ምናልባት ከቤተሰቦቿ ተነጥቃ ተወስዳ ሊሆን ስለሚችል የልጅቷን ወላጆች የምታውቁ ወይም ወላጅ የሆናችሁ በዚህ ስልክ ደውላችሁ ከመንገድ ዳር ያነሱትን ግለሰቦች እንድታገኙ መልእክት አድርሰውኛል (ጉዳዩን ለፖሊስ እንዳሳወቁም ተናግረዋል): ሚሚ: 0977742511 ወይም 0947689074 ምስክር: 0910742028
Показать все...
👍 344😢 195 40🙏 18😱 9🤔 2
ከጋዜጠኛ ቃለየሱስ በቀለ ጋር መልካም ቆይታ አርገናል https://youtu.be/MgxvrzAzI0Y?si=JcJKvWKTqTxTeSuZ
Показать все...
👍 75 13😁 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ከሰሞኑ እንኳን በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ከ40 በላይ ንፁሀን ዜጎች በግፍ ሲገደሉ፣ በደራ ወረዳ አንድ የመስጂድ ኢማም የሆኑ ሼይህ ከነ12 ቤተሰባቸው ሲረሸኑ፣ ዜጎች በየስፍራው ሲታገቱ እና ወጣቶች በአዲስ አበባ እና አዳማ እየታፈኑ ወደ ካምፕ ዚጓዙ ትንፍሽ ያላለ ሚድያ... @EliasMeseret
Показать все...
😢 1 245👍 423😁 75 60🤔 39😱 7🕊 4
በቤተመንግስት ተገኘ ስለተባለው 400 ኪ/ግ ወርቅ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ፓርላማ ላይ "ባደረግነው የቤተመንግስት ዕድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገብተናል" ማለታቸው ይታወሳል። "ይህ ወርቅ ምን ይሆን ብዬ?" አንዳንድ ማጣራቶችን ለማድረግ ሞክሬ ነበር። ያገኘሁት መረጃ አስደንጋጭም፣ አሳሳቢም ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ይህ ወደ ብሄራዊ ባንክ ተላከ የተባለ ወርቅ በኢትዮጵያ የንጉሳዊ ስርዐት ወቅት ለበርካታ መቶ አመታት ነገስታት ሲገለገሉባቸው የነበሩ በወርቅ እና በሌሎች የከበሩ ማዕድናት የተሰሩ ቁሳቁሶች፣ ከሌሎች ሀገራት በስጦታ የተሰጡ ቅርሶች እንዲሁም በርካታ በነገስታቱ ታዘው የተሰሩ እና የተገዙ ናቸው። "ታድያ እነዚህ ወደ ሙዚየም እንጂ ለሽያጭ ወይም ለወርቅ ክምችት ወደ ባንክ እንዴት ሊላክ ይችላል?" ብዬ ጥያቄ ያቀረብኩላቸው ጉዳዩን የሚያውቁ ግለሰቦች ምላሻቸው "ማን ሰምቶን?" ነው። ቅርስ ጥበቃ፣ ብሄራዊ ባንክ፣ የጠ/ሚር ፅ/ቤት እንዲሁም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚህ ዙርያ መክሮ እነዚህን የኢትዮጵያ ታሪክ የሆኑ ንብረቶች ወደነበሩበት ቦታ ወይም ወደ ሙዚየም እንዲመለሱ ማድረግ አለባቸው። እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው! @EliasMeseret
Показать все...
👍 1 546😢 426😁 165 93🤔 79😱 47🙏 11🕊 8
Фото недоступноПоказать в Telegram
የሚድያ ሰራዊት...?! በዚህ መልኩ የሚገኝ ላይክ፣ ኮመንት እና ሼር ጥቅሙ ምን ይሆን? @EliasMeseret
Показать все...
😁 1 725😢 175👍 159🤔 78 42😱 40🙏 10🕊 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
በትምህርት ተቋማት፣ በኢንደስትሪ ፓርኮች ወይም በግል የስራ ቦታ ሊገኙ የሚገባቸው ወጣቶች እየታፈሱ ወደ ወታደር ካምፕ እየተላኩ ነው የሚገርመው ደግሞ አፍሰው የሚወስዱ ሚሊሺያዎች ወደ ካምፕ የሚወስዷቸው ወጣቶች ኮታ ተሰጥቷቸዋል። Back to the Derg era... back to square one! ዜናውን መሠረት ሚድያ ላይ ያንብቡ: https://t.me/meseretmedia/496 @EliasMeseret
Показать все...
😢 673👍 122😁 40🤔 29😱 24 19
#ሁለቱግፎች በቅርብ ቀናት ከሰማኋቸው የግፍ ድርጊቶች ሁለቱን ላጋራችሁ: አንደኛው ጀሞ አካባቢ በሚገኛው ሳውዝ ዌስት አካዳሚ የተፈፀመ ነው። የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘው ሲዘምሩ እና የጥላሁንን "ኢትዮጵያ" ዘፈን ሲዘፍኑ የነበሩ ከ30 በላይ ታዳጊዎች (ከ10- 12ኛ ክፍል ተማሪዎች) ታፍሰው ተወስደው ክፉኛ ተደብድበዋል። ሁለቱ ላይ የደረሰው ድብደባ እጅግ የከፋ ነበር የተባለ ሲሆን፣ የልጆቻቸውን ከእስር መፈታት ሊማፀኑ ወደ 'ማርያም ሰፈር' የሚገኝ ፖሊስ ጣብያ የሄዱ ወላጆች "ከፈለጋችሁ በክላሽ እናናግራችሗለን" እንደተባሉ ነግረውኛል። ሁለተኛው ደግሞ በከምባታ ዞን ፉንጦ ከተማ የተፈፀመ ሲሆን ከሁለት ሳምንት በላይ መብራት በመጥፋቱ በኮሚቴ ሆነን መንግስትን እንጠይቅ ብለው ሲመክሩ የነበሩ ወጣቶች በደቡብ ምዕራብ ክልል ልዩ ሀይል ተይዘው ክፉኛ ተቀጥቅጠዋል፣ የድብደባውን መጠን የሚያሳይ ቪድዮም ተለቋል። ሙሉ መረጃውን መመልከት ከፈለጉ: https://youtu.be/4-mTXuOxJjg?si=TU42M6bYuv3cqgGE #StopAtrocities
Показать все...
😢 449👍 106🤔 29 18🙏 9😁 5😱 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
ይሄ ቁጭት ሲንጋፖርን እና ማሌዥያን መምሰል እና አለመምሰል ሳይሆን እንዴት በዚህ ክፍለ ዘመን አንድ የሀገሬ ዜጋ ምግብ አጥቶ ይራባል፣ ፖለቲከኞች በሚቆሰቁሱት እሳት ይለበለባል፣ በልማት ስም ከቤቱ ተጎትቶ ወጥቶ መንገድ ላይ ይጣላል... ወዘተ ቢሆን በወደድኩ። እኔ እንኳን እንደ አንድ ተራ ግለሰብ ምናልባት ድምፅ ከሆነን በሚል ከህዝብ የሚደርሰኝ አሰቃቂ እና ዘግናኝ ሁኔታ እንቅልፍ ይነሳኛል። አያውቁትም ወይስ አያገባኝም? ወይስ ሌላ? @EliasMeseret
Показать все...
975👍 527😢 218🙏 87🤔 43😁 33😱 5🕊 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
ያለንበት ሁኔታ በጨረፍታ! @EliasMeseret
Показать все...
😢 1 455👍 119🤔 31😱 26 22😁 16🙏 10🕊 9
በየቀኑ ከሚደርሱኝ አሳዛኝ መልእክቶች መሀል ⤵️ ሰላም ኤልያስ፣ ከኑሮ ውድነት ጋር በተገናኘ አንድ መረጃ ላጋራ ወደድኩ። ለደህንነት ስባል ስሜ ለጊዜው ይቆይና የምሰራው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነዉ ከተቀጠርኩ አንድ አመት ከሰባት ወር ሆኖኛል፤ የማገኘው ደሞዝ የተጣራ 12 ሺህ ብር አከባቢ ነው። ይሄ ማለት ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ባንኮች ሁሉ ዝቅተኛ ደሞዝ ከፋይ ንግድ ባንክ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ ከማይክሮ ፋይናንስነት ወደ ባንክነት የተሸጋገረው ኦሞ እንኳ በቅርቡ የተስተካከለው ደሞዝ ስኬላቸው ከንግድ ባንክ ይበልጣል። ንጽጽረ በእኛ ደረጃ ካሉት ጋር ነው። ወደ ዋናው ሀሳቤ ስመለስ ወጭዬን በዚህ መልክ ነው የምመድበው: ለቤት ክራይ=2000 በወር ለታክስ=1040 በወር ለመጠጥ ውሃ=1400 በወር ለምጦራት እናቴ=1500 በወር ሌሎች ወጪዎች=1000 በትንሹ የቀረው 5060 ለምግብ ሲሆን የምግብ ወጪዎቼ እንዲህ ነው: ቁርስ በቀላሉ አምባሻ በሻይ=40 ምሳ በቀላሉ ሽሮ/አታክልት/አቦካዶ/አይነት/ፓስታ እና የመሳሰሉ ምግቦች ከበላው=80 እራትም እንደዛው=80 በአጠቃላይ በቀን በትንሹ ለምግብ 200 ብር ይወጣል ይሄ ደግሞ በወር ስሰላ 6000 ብር ነው። ከላይ ባስቀመጥኩት ዝርዝር መረጃ መሠረት ሌሎች ወጪዎችን መቀነስ ስለማልችል ምግብ በቀን 2 መመገብ ጀምሬያለሁ። ሌላው ደግሞ የጤና ሁኔታ ስሆን ምንም እንኳ ባንኩ የሕክምና ወጪ እሸፍናለሁ ብለው ብያወራም ያለው እውነታ ሌላ ነው። እርግጥ እውነት ነው ባንኩ የሕክምና ውጪ ይሸፍናል፣ የሚሸፍነው ግን በመንግሥት ሆስፒታል ከታከምክ ብቻ ነው። በመንግሥት ሆስፒታል ውስጥ ደግሞ ሌላው ቀርቶ ጓንት እንኳ ከውጭ ገስታችሁ አምጡ እንባላለን፣ ከዚህ ውጭ ያለው ነገር ለተመልካች ግልጽ ነው። ከላይ በዘረዘርኩት ወጪ ውስጥ "ውሃ ግዴታ ነው ወይ?" ካልከኝ አዎ ያለንበት አከባቢ ንጹሕ የመጠጥ የሌለበት ነው። ብዙ ልብ የሚሰብር ነገሮች አሉ! @EliasMeseret
Показать все...
😢 1 261👍 322 56🤔 35😱 29😁 23🕊 6🙏 5