2025 рік у цифрах

107 316
Підписники
-4624 години
-3747 днів
-2 08430 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት የአፋር ክልል ወሰንን ተሻግሮ በመግባት ስድስት መንደሮችን “በጉልበት ተቆጣጥሯል” ሲል የክልሉ መንግስት ወነጀለ።
የአፋር ክልል መንግስት ምሽቱን ባወጣው መግለጫ የህወሓት ቡድን ከድርጊቱ “በአስቸኳይ ካልተቆጠበ”፤ ራሱን “ከውጫዊ ጥቃት” የመከላከል ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አስጠንቅቋል።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
😭 27❤ 26😁 4👎 2🔥 2👀 2
ለውይይት የቀረበው አዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ተእታ/ቫት) ተመላሽ ረቂቅ ረቂቅ መመሪያ በርካታ ለውጠችን መያዙ ተነገረ
ከአመት በፊት ለፀደቀው የቫት አዋጅ ማስፈጸሚያ እንዲሆን የረቀቀው እና ከስድስት አመት በፊት ወጥቶ የነበረውን መመሪያ እንደሚከልስ የተነገረለት አዲሱ መመሪያ ከተመላሽ ጋር ያሉ ጥያቄዎችን ቅድመ ሁኔታ ይበልጥ ጠበቅ የሚያደርግ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በተጨማሪ “ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ወጪ ያለው ፕሮጀክት” በሚለው ስር የሚገኙ እሳቤዎችን ቀይሯል የሚሉት ረቂቅ መመሪያውን የተመለከቱ ባለሞያዎች በተለይ ለአገር ውስጥ ባለሃብት ተለቅ ያሉ ስራዎችን እንዲወጥን ሊያበረታታ ይችላል ሲሉ ነው የገለፁት፡፡
በረቂቅ መመሪያው የትርጉም ክፍለ “ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ወጪ ያለው ፕሮጀክት” የሚለውን ሃሳብ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ 100 ሚሊየን ዶላር ወይም ከአንድ መቶ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበት መሆኑ የተረጋገጠ ፕሮጀክት ሲል እንደሚገልጸው ካፒታል ከረቂቁ መመልከት ችላለች፡፡
ይህም ከቀደመው መመሪያ ከፍተኛ ለውጥ ያለው ነው የሚሉት ባለሞያዎች ምናልባት ሃሳቡ መመሪያው ከውይይት በኋላ ተግባራዊ ሆኖ ሲወጣ የበለጠ ግልጽ የሚሆኑ ሃሳቦች እንደሚኖሩት ገልጠዋል፡፡
በስራ ላይ ባለው መመሪያ “ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ወጪ ያለው ፕሮጀክት” ከ 100 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ የሚደረግበት እነደሆነ ይጠቅስ ነበር፡፡
አዲሱ መመሪያ በወጪ ንግድ ላይ የሚኖሩ ተመላሽ ሁኔታዎች ላይ ለውጥ ያለበት ሆኑ ነው የተገለፀው፡፡ በዚህም ቀደም ሲል ቫት ከተከፈለበት ግብይት 25 በመቶን ወደ ውጭ የላከ ተላሽ መጠየቅ ይችል ነበረ ሲሆን በረቂቁ ይህ መቶኛ ወደ 50 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡
Capital Newspaper
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 18
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ምትኩ ካሳ፣ ባለቤታቸው ወ/ሮ ሶፊያ ጀማል እና ልጃቸው በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንደተሰጣቸው ተዘግቧል።
ውሳኔው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ችሎት የተላለፈ ሲሆን፣ የፍትህ ሚኒስቴር ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ ተከሳሾቹ የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን ከፍተኛ መጠን ያለው የእርዳታ እህል ከመጋዘን ወጪ በማድረግ ለተረጂዎች ሳይደርስ ለዱቄት ፋብሪካዎችና ለሌሎች ግለሰቦች በመሸጥ ለግል ጥቅም ማዋላቸው ተገልጿል።
በክሱ ላይ እንደተመላከተው፣ በህገ ወጥ መንገድ ከኮሚሽኑ በድጋፍና በብድር ስም በ100 ሚሊየን ብር የሚገመት ገንዘብ ለግል ጥቅም የዋለ ሲሆን፣ ከ601 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴን ጨምሮ ሌሎች የእርዳታ እህሎች ተዘዋውረዋል።
በተጨማሪም፣ ተከሳሾቹ በሕገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ምንጩን ደብቆ ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ (በስማቸው ንብረቶችን በመግዛት) ወንጀል ተሳትፎ ማድረጋቸው በፍርድ ቤቱ መረጋገጡ ተገልጿል።
ክሱ በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም. የተመሰረተባቸው የሚታወስ ሲሆን ተከሳሾቹ በእምነት ክህደት ቃላቸው ወንጀሉን አለመፈጸማቸውን ቢገልጹም፣ ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግን የሰው ምስክር እና የሰነድ ማስረጃዎች መርምሮ ውሳኔውን መስጠቱ ነዉ የተዘገበው።
Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 14😭 11👍 5😁 1
በክልሎች የደመወዝ ጭማሪ በጀት ጉድለት ያጋጠመው ኮሚሽኑ በፈጠረው የቀመር ሥሌት አረዳድ ችግር ነው ተባለ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ያጋጠመው የደመወዝ ጭማሪ በጀት ጉድለት፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በሠራው የቀመር ሥሌት ላይ በተፈጠረ የአረዳድ ችግር ምክንያት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በገንዘብ ሚኒስቴር የበጀት ዝግጅትና አስተዳደር መምርያ ኃላፊ አቶ ፍሬው ኃይሌ፣ አምስቱ ክልሎች የበጀት ጉድለት እንዳጋጠማቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኃላፊዎችና የክልሎቹ ተወካዮች በተገኙበት በተደረገ ውይይት፣ ችግሩ የተፈጠረው ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሠራው የደመወዝ ጭማሪ ወይም ማስተካከያ ቀመር ሥሌትን በአግባቡ ካለመረዳት በመነጨ
ምክንያት እንጂ፣ ባጋጠመ የበጀት እጥረት ወይም በሌላ ምክንያት አለመሆኑንና መግባባት ላይ መደረሱን አስረድተዋል፡፡
በውይይቱም ክልሎች በአማካይ፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ደግሞ በእርከን ሒሳቡን መሥራታቸውን መናገራቸውን ያወሱት ኃላፊው፣ በዚህም ሒሳብ የሠሩበት መንገድ አንድ ዓይነት እንዳልሆነ መተማመናቸውንም ጭምር ጠቅሰው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ኮሚሽኑ ባቀረበው ሥሌት መሠረት የበጀት ምደባ ማድረጉን ገልጸዋል።
ጉዳዩን በምሳሌ ሲያስረዱ፣ ‹‹የበጀት ጉድለት ያጋጠመባቸው ክልሎች ደመወዛቸው 4,6ዐዐ ብር የነበሩ ሠራተኞች በቀጥታ 6,9ዐዐ ብር ይሆንላቸዋል›› ተብሎ በሰው ቁጥር እንደተባዛ ጠቁመው፣ ይህ ግን መሀል ላይ ያሉትን ወደ ዘጠኝ የሚደርሱ ደረጃዎች ወይም እርከኖች መሠረት ያደረገ አይደለም ብለዋል፡፡ ሆኖም በእርከኑ መሠረት የተሠራው ሒሳብና የሠራተኛው ቁጥር አንድ እንደሚሆን አቶ ኤፍሬም አስረድተዋል፡፡
ሦስት ሚሊዮን ብር፣ አሥር ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም እስከ አሥር ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት አጋጥሞናል ብለው ጥያቄ ያቀረቡ ክልሎች መኖራቸውን የጠቀሱት ኃላፊው፣ ሆኖም ሲቪል ሰርቪስ የሰጠው ምላሽ የአንድ ወይም የሁለት ሚሊዮን ብር የበጀት ልዩነት ሊፈጠር ይችላል እንጂ ይኼን ያህል አይሆንም የሚል መሆኑን፣ ይህም ከሆነ ደግሞ ክልሎች በራሳቸው ገቢ መሙላት የሚችሉ መሆኑን እንደተነገራቸው አስታውሰዋል፡፡
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ቀመሩን የሠራው እስከ 2016 ዓ.ም. ሰኔ ወር ባለው የመንግሥት ሠራተኛ ቁጥር መሠረት መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፣ ከዚያ በኋላ ቅጥር የፈጸሙ ክልሎች ላይ የሠራተኛ ቁጥር ልዩነት መምጣቱንና ይህንንም በጥያቄ መልክ ቀርቦ ነበር ብለዋል፡፡
ነገር ግን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ቅጥር በማድረጉ ለእነዚህ ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በጀት ከፌዴራል መንግሥት ሊደለድል እንደማይችል፣ ራሳቸው ክልሎች ኃላፊነቱን እንዲወስዱ እንደተነገራቸው አስረድተዋል።
ለ12 ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የሚለቀቀው በጀት በየሦስት ወራት ለሦስት ጊዜያት ያህል ተከፋፍሎ ከግምጃ ቤት እንዲደርሳቸው እንደሚደረግ፣ በዚህም የመጀመሪያው ሦስት ወራት ማለትም የመስከረም፣ የጥቅምትና የኅዳር ወራት ደመወዝ መሠራጨት መጀመሩን ጠቁመዋል።
በኅዳር አጋማሽ፣ የታኅሳስ፣ የጥርና እንዲሁም የየካቲት፣ በየካቲት አጋማሽ ደግሞ፣ የመጋቢት፣ የሚያዝያ፣የግንቦትና የሰኔ ወራት እንደሚለቀቅ ተናግረዋል።
Via:- Reporter
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 19
Repost from YeneTube
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👉 እስከ 35% ታላቅ ቅናሽ👈
- ባለ 2 መኝታ =5.4 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ክፍያ
- ባ 3 መኝታ =6.5 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ክፍያ
👉ቴምር ሪል እስቴት የመኖሪያ አፓርትመንት እና የንግድ ሱቆች
👉ከ20% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ ያግኙ።
ከባለ 1 መኝታ እስከ 3 መኝታ በተለያየ የካሬ አማራጮቾ
👉ከ63 ካሬ – 146 ካሬ
👉 በ10% ቅድመ ክፍያ
👉በፒያሳ
👉በአያት ሎሚያድ እና በአያት ፈረስቤት
👉በጋርመንት እና
👉በተክለሀይማኖት
👉የንግድ ሱቆች በፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ ፊት ለፊ።
ለበለጠ መረጃ :- 0901504245
0923579248 ይደውሉ።
❤ 5
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሩሲያ አዳዲስ የኒውክሌር ሃይል የሚሸከሙ ክሩዥ ሚሳኤሎችን ማምረት ጀምራለች ሲሉ ፑቲን ተናገሩ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዋና ከተማዋ ሞስኮ በተካሄደው የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ በተሳተፉበት ወቅት እንደተናገሩት ቀጣዩን ትውልድ የተሰኘውን በኒውክሌር ኃይል የሚንቀሳቀሱ የክሩዝ ሚሳኤሎችን ማምረት ሩሲያ ጀምራለች ብለዋል። "የሚቀጥለው ትውልድ በኑክሌር ኃይል የሚንቀሳቀሱ የክሩዝ ሚሳኤሎች ልማት ተጀምሯል፤ ፍጥነታቸው ከድምጽ ፍጥነት ከሶስት እጥፍ በላይ ይሆናል እናም ለወደፊቱ እንዲያውም ሃይፐርሶኒክ ይሆናሉ "በማለት ፑቲን በክሬምሊን ውስጥ ተናግረዋል።የሩሲያው ፕሬዝዳንት የሀገሪቱን የኑክሌር ኃይል ያለው ቡሬቬስትኒክ ሚሳይል እና ፖሲዶን ሰው አልባ የውሃ ውስጥ ተሽከርካሪ ለሚሰሩ ገንቢዎች የመንግስት ሽልማቶችን ሰጥተዋል።
በተጨማሪም በቡሬቬስትኒክ እና በፖሲዶን ውስጥ ጥቅም ላይ ከዋሉት ጋር በሚመሳሰሉ የኃይል አማራጮች ላይ የተመሰረተ "አዲሱ የጦር መሣሪያ" በሩሲያ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቀዋል ። ፑቲን በሽልማት ስነ ስርዓቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር የቡሬቬስትኒክን እድገት ለሩሲያ ህዝብ “ታሪካዊ” ጠቀሜታ እንዳለው እና “ለሚመጡት አስርት ዓመታት ደህንነትን እና ስትራቴጂካዊ እኩልነትን ማረጋገጥ ያስችላል” ሲሉ ገልፀውታል። የሚሳኤሉን ዝርዝር ሁኔታ በማስታወስ፣ ፑቲን በጥቅምት 21 ቀን ቡሬቬስትኒክ በተሞከረበት አካባቢ የኔቶ መርከብ እንዳለ እና ሞስኮ ጣልቃ አልገባችም ሲሉ ተናግረዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 28🔥 6
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
እስከ 30% ባነሰ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
❤ 9😁 5👎 1🔥 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገበት መሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
የሚከለሰው ሥርዓተ ትምህርትም በ2018 የትምህርት ዘመን ዩኒቨርስቲ የገቡ ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ተልዕኮ መሰረት ባደረገ መልኩ ስርዓተ ትምህርቱን የመከለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ክለሳው ያስፈለገው የቀድሞዎቹ ሥርዓተ ትምህርቶች ዘመኑን ያልዋጁና ከ21ኛው ክፍለ ዘመን ጋር በአግባቡ ያልተቃኙ በመሆናቸው ነው ብለዋል።አዲሱ እየተከለሰ ነው የተባለው የከፍተኛ ትምህርት፣ ሥርዓተ ትምህርት ተመራቂዎች በትምህርት ፕሮግራሞቹ ከተማሩ በኋላ ሊኖራቸው የሚገባውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት በአግባቡ የፈተሸ መሆኑን መሪ ሥራ አስፈጻሚው አስረድተዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ትምህርት ፕሮግራሞች ዴስክ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ነገዎ በበኩላቸው የሚከለሰው ሥርዓተ ትምህርት ሙያና ተግባር ተኮር መሆኑን ጠቅሰው ስራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ ምሩቃንን ማፍራት እንደሚያስችል ተናግረዋል።
በሁለት ዙሮች እስካሁን 55 የትምህርት ፕሮግራሞች መከለሳቸውን አንስተው እስከ ዓመቱ መጨረሻም ከ80 የሚበልጡ ፕሮግራሞች እንደሚከለሱ ጠቅሰዋል፡፡አዲስ የተከለሱት የትምህርት ፕሮግራሞች በ2018 የትምህርት ዘመን ዩኒቨርስቲ የገቡ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ወይም ከመጭው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረጉም ተጠቅሷል።
Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 18👎 4👍 3👀 2
መንግስት በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ አርሲ ዞን፣ በተደጋጋሚ “ ለተፈጸሙት ግድያዎች ኃላፊነት መውሰድ እንደሚገባው “ የፓርላማ አባሉ አበባው ደሳለው አሳሰቡ፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አበባው ደሳለው በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ አርሲ ዞን የተፈጸሙትን ግድያዎች በጽኑ አውግዘው፣ “ የአካባቢው አመራሮችና የፌደራሉ መንግስት ኃላፊነት መውሰድ እንዳለባቸው” ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡
“ ኃይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃት እንዲቆም እኔም ብሆን ቀደም ብዬ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ጥያቄ አቅርቤ ነበር ” ሲሉ ያስታወሱት የምክርቤት አባሉ ይህን መሰል ጥቃት በአካባቢው በተደጋጋሚ እንደሚፈጸም ገልጸዋል፡፡
ለዚህም ዋነኛው ምክንያት “ የአካባቢው አመራሮች ችግሩን ለመቅረፍ ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ስለሌላቸው ነው ” ባይ ናቸው፡፡
ጥቃቱን በሚፈፀሙት አካላት ላይም ተጠያቂነትን አለማረጋገጥና እርምጃ ሲወሰድ አለመታየቱ ችግሩ እንዲባባስ ሌላኛው ምክንያት መሆኑን አመላክተዋል፡፡
አበባው አክለውም በኢትዮጵያ የነበረው የመተሳሰብና አብሮ የመኖር እሴት በዚህ መሰል ድርጊት እንዲሸረሸር ያደረገዉ የህግ የበላይነትን ማስከበር አለመቻል መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን “ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ላይ ከመጡበትና ከዚያ ጥቂት ጊዜያት ቀደም ብሎ እስካሁን ድረስ እንደ ፖሊስና መከላከያ ” ሲሉ የዘረዘሯቸው የመንግስት የጸጥታ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ አለመሆናቸው ችግሩን አባብሶታል ብለዋል፡፡
የፓርላማ አባሉ አሁንም ቢሆን ገለልተኛ አካል በስፍራው ገብቶ በማጣራት ጥፋተኞቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አበባው በቀጣይ ግን መንግስት ችግሩን መፍታት ካልቻለ “ ሰዎች ተፈጥሯዊ የሆነውን ራሳቸውን የመከላከል መብት ተጠቅመው ራሳቸውን እንዲከላከሉ ሊያስታጥቃቸው ይገባል አልያም በራሳቸው እንዲታጠቁ ማድረግ ይኖርበታል ” ሲሉ አሳስበዋል፡፡
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
👍 38❤ 28⚡ 5😁 3😭 2🔥 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ምያንማር ውስጥ የሳይበር ማጭበርበሪያ ካምፖችን በመምራት የሚታወቀው ቤተሰብ አባላት በቻይና የሞት ፍርድ ተላለፈባቸው!
የቻይና ፍርድ ቤት ምያንማር ውስጥ የበይነ መረብ ማጭበርበር ተግባር ላይ ተሰማርተው በነበሩ አምስት ዋና የውንብድና ቡድን አባላት ላይ የሞት ፍርድ አስተላለፈ።ባይ የተባለው ቤተሰብ አባላት እና አጋሮች የሆኑ 21 ሰዎች በማጭበርባር፣ በነፍስ ማጥፋት፣ በሰዎች ላይ ጉዳት በማድረስ እና በሌሎች ወንጀሎች የጥፋተኝት ውሳኔ እንደተላለፈባቸው የቻይና መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ያመለክታል።
ይህ ቤተሰብ በአውሮፓውያኑ 2000ዎቹ ላይ ኃይላቸውን እያጎለበቱ ከመጡ በጣት የሚቆጠሩ የውንብድና ቡድኖች መካከል አንዱ ነው።ቤተሰቡ፤ በድህነት እና ኋላ ቀርነት ትታወቅ የነበረችውን የምያንማሯን ላውካኢንግ ዞንን ዋነኛ የቁማር እና የወሲብ ንግድ መናኸርያ አድርጓታል።ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ ከተዘዋወሩ በኋላ በኦንላይን የማጭበርበር ተግባር ላይ እንዲሰማሩ ተገድደዋል።
በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በሚገኝበት የማጭበርበር ሥራ ላይ በግዳጅ ሠራተኛ ከሆኑት ውስጥ አብዛኛዎቹ ቻይናውያን ናቸው።በቻይና ፍርድ ቤት የፍርድ ውሳኔ ከተላለፈባቸው አምስት ዋነኛ ሰዎች መካከል የውንብድና ቡድኑ አለቃ ባይ ሱቸንግ እና ልጁ ባይ ዩንግካንግ ይገኙበታል። ያንግ ሊ ቺያን፣ ሁ ሲያውጃንግ እና ቼን ግዋንዩ ቀሪዎቹ ፍርደኞች ናቸው።
ከቤተሰቡ አባላት ውስጥ ሁለቱ የሞት ፍርድ ከተላለፈባቸው በኋላ የቅጣት ውሳኔው ታግዷል። አምስት ሰዎች በዕድሜ ልክ እስራት የተቀጡ ሲሆን ዘጠኝ ሰዎች ከሦስት እስከ 20 ዓመት የሚደርስ እስራት ተፈርዶባቸዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 37👍 6👀 3🔥 1
በአሜሪካ በጭነት አውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአሜሪካ ኬንታኪ ግዛት ትናንት ምሽት በደረሰ የዩፒኤስ ጭነት አውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
የጭነት አውሮፕላኑ ከሉዊስቪል ሙሐመድ አሊ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መብረር በጀመረ ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ መከስከሱ ተመላክቷል፡፡
የኬንታኪ ግዛት አስተዳዳሪ አንዲ በሺዬር÷ የጭነት አውሮፕላኑ ከተነሳ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የመፈንዳት አደጋ እንዳጋጠመው አስረድተዋል፡፡
በተከሰተው አደጋም እስካሁን የ7 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ÷11 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል፡፡
የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ጠቁመው÷ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
አደጋውን ተከትሎ የተፈጠረውን የእሳት አደጋ በፍጥነት መቆጣጠር መቻሉን ገልጸዋል፡፡
የበረራ ቁጥሩ 2979 የሆነው የጭነት አውሮፕላን 38 ሺህ ጋሎን ነዳጅ ጭኖ ወደ ሆኖሉሉ ሊያቀና እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 14😭 8
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ዞህራን ማምዳኒ የኒውዮርክ የመጀመሪያው በአፍሪካ የተወለደ ሙስሊም ከንቲባ ሆኖ ተመረጠ
ዞህራን ማምዳኒ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ትልቁን ከተማ ለመምራት በተካሄደው ውድድር አሸንፏል፣ አሶሺየትድ ፕሬስ ማክሰኞ መገባደጃ ላይ የተነበየው ይህ ውጤት፣ የምርጫ ጣቢያዎች የዓለምን ትኩረት የሳበው የጦፈ ውድድር ከተጠናቀቀ በኋላ ነበር። የእሁዱ ድል ከ 8.4 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለሚኖርባት ከተማ በታሪክ ውስጥ ትልቁ ውጤት ሲሆን ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ኃይል ያለው ዓለም አቀፍ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
ማምዳኒ የመጀመሪያው ሙስሊም፣ የመጀመሪያው የደቡብ እስያ ዝርያ ያለው እና በአፍሪካ ውስጥ በዩጋንዳ ካምፓላ የተወለደ የኒውዮርክ ከተማን ለመምራት የመጀመሪያው ሰው ነው። ሰኞ እለት ማምዳኒ "በዚች ከተማ ታሪክ ለመስራት ወደዚህ ደረጃ ላደረሱኝ ደጋፊዎቼ አመስግናለሁ" ብሏል።
የቀድሞው የኒውዮርክ ግዛት ገዥ ኩሞ ማምዳኒ ምርጫውን ስላሸነፍክ እንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላልፈዋል። እራሱን ዲሞክራሲያዊ ሶሻሊስት ሲል የሚገልፀው ማምዳኒ ከወራት በፊት በአንፃራዊነት የማይታወቅ ነበር ።ለማህበራዊ ፕሮግራሞች በገባው ቃል መሰረት የመራጮችን ቀልብ በመግዛት ወደ ድል አምርቷል።
#ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 38👍 6
Repost from YeneTube
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🔥በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ
🌟ለ15 ቤቶች ብቻ ተደደርጎ የነበረው ታላቅ ቅናሽ ሊያበቃ ውስን ቀናት ብቻ ቀሩት‼️
🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት
💎ባለ 1 መኝታ በ 441,000 ሺ ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 720,000 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 1,035,000 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ
🔥እንዲሁም የቤቱን 70% ሲከፍሉ 30% በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል (30% ቅናሽ)
-በግንባታ ላይ የሚገኙ
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelMERITRealtor)
❤ 5
Repost from YeneTube
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Amharic Capiton:
መስራት ማህበር ለኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች ተግባራዊ ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ ነው:
Ø በንግድ፣ በፋይናንስ፣ በማርኬቲንግ፣ በኢንቨስትመንት፣ በገበያ ማፈላለግና በህግ ጉዳዮች ዙርያ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተዘጋጁ ጽሁፎችን ማጋራት
Ø የንግድ ስራችሁን ለማስተዳደር የምትጠቀሙበት መመሪያዎችንና ሃሳቦችን ማጋራት
Ø በናንተ የስራ ፈጠራ መንገድ ቀድመው ካለፉና ብዙ ልምድ ማካፈል ከሚችሉ ጋር ማህበረሰብ የምትፈጥሩበትና ሃሳብ የምትለዋወጡበት መድረክ
Ø በስራችሁ ወደፊት ለመራመድ የሚያግዙአችሁን የተለያዩ ሃሳቦች ማጋራት እንዲሁም ጠቃሚ ግንኙነቶችን የምትፈጥሩባቸው ኩነቶችን መጠቆም
የሚከተሉትን የመረጃ ምንጮች በመጠቀም የንግድ ስራችሁን አሳድጉ https://mahber.mesirat.org/wp-login.php?loggedout=true&wp_lang=en_US
❤ 4
🫵አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ
☎️ 09 80 81 37 86
🫵የስራ መደብ:-NGO በሁሉም
🌸የት/ ደረጃ:- 10-12 /ዲግሪ/ ድፕሎማ
🌸 ልምድ፦ 0 አመት ጀምሮ
🌸ፆታ:- ወ/ሴ
🌸 ደሞዝ :- 25,000+
🫵የስራ መደብ:- ሆስተስ
🌸የት/ ደረጃ :- 10+12
🌸ልምድ፦ 0አመት
🌸ፆታ :- ሴ
🌸ደሞዝ:- 15,000+
🫵የስራ መደብ:- ማስታወቂያ ለጣፊ
🌸የት/ ደረጃ :- አይጠይቅም
🌸 ልምድ፦ 0አመት
🌸ፆታ :- ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:-12,000
🫵የስራመደብ፦ እረዳት H&r
🌸የት/ደረጃ:-በማንኛውም ድግሪ
🌸ልምድ፦ 1አመት
🌸ፆታ:- ሴ/ወ
🌸ደሞዝ:- 16,5000
🫵የስራ መደብ:- መምህር በሁሉም ዘርፍ
🌸የት/ደረጃ:- ዲግሪ/ዲፕ
🌸ልምድ፦0አመት
🌸ፆታ:- ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:-15,000
🫵የስራ መደብ:- ውሀ ላይ ሽያጭ
🌸የት/ደረጃ:- 8/10
🌸ልምድ፦ 0አመት
🌸ፆታ:- ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:- -13,000
🫵የስራ መደብ:- ሁለገብ ፋብሪካ ላይ
🌸የት/ደረጃ:-8/10
🌸ልምድ፦0አመት
🌸ፆታ:- ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:- 12,500
🫵የስራ መደብ:- ባስ ትኬተር
🌸የት/ደረጃ:- 8/10+
🌸ልምድ፦0አመት
🌸ፆታ:-ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:- 14,000+ ጥቅማጥቅም
🫵የስራ መደብ:- መረጃ ሰብሳቢ
🌸የት/ደረጃ:- 8/10ኛ
🌸ልምድ፦ 0አመት
🌸ፆታ:- ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:- 15,000 +ትራንስፖርት
🫵የስራ መደብ:- ቡና ማሸግ አጠቃላይ
🌸የት/ደረጃ:- አይጠይቅም
🌸ልምድ፦0አመት
🌸ፆታ:- ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:- 13,500
🫵የስራ መደብ:- የመስክ ሰራተኛ
🌸የት/ደረጃ:- ዲግሪ/ ዲፕ
🌸ልምድ፦0አመት
🌸ፆታ:- ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:- 30,500
🫵የስራ መደብ:-ደንበኞች አገልግሎት
🌸የት/ደረጃ:- ዲግሪ
🌸ልምድ፦0አመት
🌸ፆታ:- ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:- 20,500
🫵የስራ መደብ:፦ቢራ ፈብሪካ አጠቃላይ
🌸የት/ደረጃ:- 8/10
🌸ልምድ፦0አመት
🌸ፆታ:- ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:- 13,300
🫵የስራ መደብ፦ብስኩት ፋብሪካ
🌸የት/ደረጃ፦8/10
🌸ልምድ፦0አመት
🌸ጾታ፦ወ/ሴ
🌸ደሞዝ ፦13,500
🫵የስራ መደብ:- ባንክ ቤት ፅዳት/ተላላኪ
🌸የት/ደረጃ:- 8ኛ
🌸ልምድ፦0አመት
🌸ፆታ:- ሴት
🌸ደሞዝ:- 8,500+
🫵የስራ መደብ:- መኪና ሸያጭ
🌸የት/ደረጃ:- 10+
🌸ልምድ፦ 0አመት
🌸ፆታ:- ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:- 15,500+
🫵የስራ መደብ:- ሽያጭ
🌸የት/ደረጃ:- 10+
🌸ልምድ፦0አመት
🌸ፆታ:- ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:- 8,000+
🫵የስራ መደብ:- ሹፋር
🌸የት/ደረጃ:- የሰራ
🌸ልምድ፦0አመት
🌸ፆታ:- ሴት
🌸ደሞዝ:- 12,000 +
🫵የስራ መደብ:- ጉዳይ አስፈፃሚ
🌸የት/ደረጃ:- 10+
🌸ልምድ፦ 0አመት
🌸ፆታ:- ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:- 15.500
🫵የስራ መደብ:- ርሴብሽን /እንግዳ ተቀባይ
🌸የት/ደረጃ:- 12ኛ/ዲፕ
🌸ልምድ፦0አመት
🌸ፆታ:-ወ/ሴ
🌸ደሞዝ:- 10,000-15,000
🫵የስራመደብ ፦ ስልክ ኦፕሬተር
🌸የት/ደረጃ ፦10+
🌸ፆታ፦ ሴ/ወ
🌸የስራ ልምድ ፦0አመት
🌸ደሞዝ ፦13,500
🫵ሌሎችም ተጨማሪ ስራዎችን ዘወትር በቴሌግራም ይመልከቱ 👇👇👇👇
Telegram channal
👇👇👇👇
https://t.me/hopeworkvacancy
🔕ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇
☎️ 09 33 95 94 56
☎️ 09 80 81 37 86
አድራሻ ፦🔷መገናኛ ሾላ መብራት ወደ ሲግናል በሚወስደው መንገድ መብራቱን አለፍ ሲሉ M/ ማስታወቂያ ያለበት ህንፃ 1ተኛ ፎቅ ቢ.ቁ 115/A
❤ 8👍 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የ12 ዓመቷን የእንጀራ ልጃቸዉ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸሙት የ75 ዓመቱ አዛዉንት በእስራት ተቀጡ
የወንጀል ድርጊቱ በጅማ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ጅሬን ቀበሌ መፈጸሙን ፖሊስ አስታዉቋል። የጅማ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ፖሊስ ፅህፈት ቤት የሴቶች እና ሕፃናት የወንጀል ምርመራ መርማሪ ሣጅን ሲፍቱ በላይ እንደገለፁት ተከሣሽ ናስር አባ ቡልጉ የተባሉት የ75 ዓመት አዛዉንት ድርጊቱን በ12 ዓመቷ የእንጀራ ልጃቸዉ ላይ ፈጽመዋል፡፡
መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓም ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ ጥቃቱን ሊፈጹሙ የቻሉት የታዳጊዋ እናት ጎረቤት ለቅሶ ለማስተዛዘን ባመሹበት ወቅት በነዉ።ወላጅ እናት ከለቅሶ ቤት ሲመለሱ ታዳጊዋ ልጅም በደረሠበት ጥቃት ደም በደም ሆና በመመልከታቸው ወዲያው ጎረቤት ጠርተው ጉዳዩን ለፖሊስ አሳዉቀዋል፡፡
ታዳጊዋ ጥቃቱን ማን እንፈጸመባት ለፖሊስ በሰጠችው መረጃ መሠረት ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡ በተጨማሪም በሕክምና ምርመራ ተደርጎላት ውጤቱን ፖሊስ በማያያዝ መዝገቡን ለአቃቤ ሕግ ልኳል።ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ የተመለከተው አቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ በወንጀል ሕግ ቁጥር 627 መሠረት ክስ መስርቷል።
በአቃቤ ሕግ የተመሠረተውን ክስ የተመለከተው የጅማ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ናስር አባ ቡልጉ ጥፋተኛ በማለት በ18 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል።
Via:- ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
😭 47❤ 34👎 5😁 4
" ድጋፍ ማድረግ በምትፈልጉበት ወቅት ተገቢውን ማጣራት አድርጉ " - ፖሊስ
ያልታመመ ሰው ታማሚ በማስመሰል ተሽከርካሪ ውስጥ አስተኝተው ከህብረተሰቡ ገንዘብ ሲለምኑ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
አንድን ወጣት የኩላሊት ታማሚ በማስመሰል በተከራዩት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 26734 ኦሮ የሆነ ሚኒባስ ውስጥ አስተኝተው በእርዳታ ስም ከህብረተሰቡ ገንዘብ ሲሰበስቡ የነበሩት ተጠርጣሪዎች ሊያዙ የቻሉት አያት አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ክትትል እንደሆነ ገልጿል።
በተሽከርካሪው ውስጥ በተደረገ ፍተሻ ፦
- በዕርዳታ ስም የተሰበሰበ 23 ሺህ 325 ብር
- በሃሰት የተዘጋጀ የህክምና ሰነድ እና የድጋፍ ደብዳቤ ተገኝቷል።
በሰነዶቹ ላይ በተደረገው ማጣራት ሃሰተኛ መሆናቸው እንደተረጋገጠ ፖሊስ ገልጿል፡፡
ገንዘብ በመሰብሰብ ስራ ላይ ለተሰማሩት ግለሰቦች በቀን 300 ብር የሚከፈላቸው ሲሆን ተሽከርካሪውን በቀን 3000 ሺህ ብር እንደተከራዩት እና ለአሽከርካሪው 1 ሺህ ብር እንደሚከፈለውም አረጋግጫለሁ ብሏል።
በወንጀሉ በቀጥታ የተሳተፉ እና የተባበሩ በአጠቃላይ 9 ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝም አሳውቋል።
ህብረተሰቡ በየመንገዱ የሚካሄዱ እንዲህ አይነት ህገ ወጥ ተግባራትን በመከላከል ረገድ የድርሻውን እንዲወጣ ፤ ድጋፍ ማድረግ በሚፈልግበት ወቅት ተገቢውን ማጣራት እንዲያደርግና አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲሰጥ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
#AddisAbabaPolice
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 25
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በቦንጋ ከተማ 800 ሺህ ብር የሚያወጣ ህገወጥ የአረቄ ምርት ተወገደ
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ብርሃኑ እንደገለፁት በህብረተሰብ ጥቆማ የተያዘው ህገወጥ የአረቄ ምርት የተወገደው የሚመለከታቸዉ አካላትን ያቀፈ ግብረ ኃይል በተገኙበት መሆኑን ገልጸዋል።
ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት የአረቄ ምርት ተብለው በቀረቡ የታሸጉ ሃይላንዶች ላይ በተደረገው ፍተሻ ፈሳሽ ሳሙና ፣ ሳኒታይዘር እና ውሃ የሚመስል ፈሳሽ በውስጣቸው መገኘቱን ብስራት ሬዲዮ ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
የተወገደው ህገወጥ ምርት ግምታዊ ዋጋው 800 ሺህ ብር እንደሚያወጣ ተገልጿል ።
የምርቱን ይዘትና የአምራቹን ድርጅት የሚገልፅ መረጃ በታሸጉባቸው ዕቃዎች ላይ አለመገኘቱ ተነግሯል። የከተማው ጤና ጽህፈት ሃላፊው አረቄን መሰል ተመሳስለው የሚመረቱ የመጠጥ ምርቶች በጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትሉ ጠቁመዋል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግና እንደወትሮው መረጃ በመስጠት እንዲተባበር የቦንጋ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒዩኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት መልዕክቱን አስተላልፏል።dagu
@Yenetube @Fikerassefa
👎 26😁 12❤ 10👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በ #ሳዑዲ_ዓረቢያ ሁለት #ኢትዮጵያውያን አንድ #ህንዳዊ ግለሰብን ገድለዋል በሚል ተጠርጥረው መታሰራቸው ተገለፀ
የሳዑዲ ዓረቢያ ባለሥልጣናት በጂዳ ከተማ አንድ ህንዳዊ ግለሰብን በሕገወጥ ግብይት ምክንያት በተነሳ አለመግባባት ሳቢያ በጥይት ተመቶ ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ዜጎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተገለፀ።
የጂዳ ከተማ ፖሊስ እንደገለጸው፣ ክስተቱ የተፈጠረው በከተማዋ አቅራቢያ በሚገኝ ተራራማ አካባቢ ሕገ-ወጥ ዕፅ በመገበያያት ላይ በነበሩ ወንዶች መካከል በተፈጠረ የገንዘብ አለመግባባት ነው። ከተጠርጣሪዎቹ አንዱ ጥይት በመተኮስ ህንዳዊውን ሰው በከፍተኛ ሁኔታ ማቁሰሉ የተገለፀ ሲሆን፣ ግለሰቡም በአቅራቢያ ወደሚገኝ ሆስፒታል ቢወሰድም በደረሰበት ጉዳት የተነሳ ሕይወቱ ሊያልፍ መቻሉን ገልፍ ኒውስ ዘግቧል።
ሁለቱም ተጠርጣሪዎች በአካባቢው በዕፅ እና በኮንትሮባንድ ዝውውር ውስጥ ተሰማርተው ነበር ያለው ፖሊስ በተጨማሪም የድንበር ደህንነት ደንቦችን በመተላለፍ ተይዘው ለተጨማሪ ሕጋዊ ሂደት ወደ ዐቃቤ ህግ መተላለፋቸውን አመልክቷል።
የሳውዲ አረቢያ ባለሥልጣናት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የድንበር ተሻጋሪ የህገወጥ የሸቀጦች ዝውውር እና ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች ዒላማ ያደረጉ ሥራዎችን ማጠናከራቸው ተዘግቧል።
ቀደም ሲል በሳዑዲ አረቢያ ከአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ ቢያንስ 37 ኢትዮጵያውያን የሞት ቅጣት ይጠብቃቸዋል ሲሉ 31 የሲቪል ማህበረሰብ እና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 15🔥 3😭 1
