TIKVAH-ETHIOPIA
Відкрити в Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
Показати більше2025 рік у цифрах

1 572 093
Підписники
-51224 години
-2 3697 днів
-3 44030 день
Архів дописів
አሜሪካ በየዓመቱ የምታካሂደውን የዲቪ ሎተሪ አቆመች።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በብራውን ዩኒቨርሲቲ በተፈጸመ የጅምላ ጥቃት ሁለት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የአሜሪካን ግሪን ካርድ ሎተሪን (ዲቪ) አገዱ።
ጥቃቱን ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረው እና ሐሙስ ዕለት ሞቶ የተገኘው ፖርቹጋላዊው በአውሮፓውያኑ 2017 ዲቪ ሎተሪ አሸንፎ ወደ አገሪቱ የገባ ሲሆን ግሪን ካርድም ተሰጥቶታል።
የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትር የሆኑት ክሪስቲ ኖም " በዚህ አስከፊ ፕሮግራም አሜሪካውያን ከእንግዲህ እንዳይጎዱ ለማረጋገጥ " በሚል ትራምፕ በሰጡት መመሪያ መሠረት የቪዛ መርሃ ግብሩን ለጊዜው እንዲቋረጥ መደረጉን ተናግረዋል።
የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተጠርጣሪው የ48 ዓመቱ ክላውዲዮ ኔቭስ ቫለንቴ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም ፕሮፌሰር ኑኖ ሉሬሮንም ገድሏል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
የዲቪ ሎተሪ ፕሮግራሙ በአሜሪካ በስደተኝነት በቂ ድርሻን ላላገኙ አገራት ዜጎች በየዓመቱ 50 ሺህ ቪዛዎችን ይሰጣል። ይህ ደግሞ የአሜሪካ ዜግነትን ለማግኘትም በር ከፋች ነው።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ ነው።
@tikvahethiopia
😭 2 478❤ 1 026👏 319💔 91🤔 77🙏 71😢 50😡 45🕊 43😱 37🥰 31
00:11
Відео недоступнеДивитись в Telegram
የንግድ ሥራውን ሰልጠን አርጉት!
የንግድ ሥራችንን እና የምርት አያያዛችንን ጨምሮ ሁሉንም ከምርት ሥራ ጋር የተያያዙ ተግባሮችን በቀላሉ በዙሪያ ቢዝነስ አውቶሜሽን ሰልጠን እናድርጋቸው!
በኢትዮ ቴሌኮም ከኢታ ሶሉሽንስ እና ዳሸን ባንክ ጋር በአጋርነት የቀረበ
#Zoorya
#Ethiotelecom #ETTASolutions #DashenBank #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
Zoorya.mp429.22 MB
❤ 198🙏 14😡 6😱 4🥰 3
#MoH
ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ17 የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በታህሳስ 2018 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና እንደሚሰጥ አሳውቋል።
አዲስ እንዲሁም ነባር የመንግሥት እና የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hpe.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።
የኦንላይን ምዝገባ ጊዜ እሑድ ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም እንደሚያበቃ ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ፥ ከተጠቀሰው የምዝገባ ጊዜ በኋላ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጾ ተመዛኞች በተጠቀሱት ቀናት እንዲመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣቸውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ Print አድርገው መያዝ እንዳለባችሁ አስገንዝቧል።
ተመዛኞች ሲመዘገቡ በመረጡት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንዲገኙ ማሳሰቢያ ተለልፏል።
ተመዛኞች ምዝገባውን ለማካሔድ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ግዴታ መሆኑን አውቀው የፋይዳ መለያ ልዩ ቁጥር (FIN) በትክክል እንዲያስገቡ ተብሏል።
Via @tikvahuniversity
❤ 776😡 45👏 39😭 30🙏 19🕊 15🥰 12😱 11🤔 9😢 5💔 4
" ሕዝቡን ያስቆጣ ተግባር የፈፀሙት ከንቲባ ከስልጣን ወርደዋል" - የሺንሽቾ ከተማ ነዋሪዎች
በባሳለፍነው ሳምንት በከንባታ ዞን ሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ለሰርግ መልስ በሚል የፌዴራል መንገድ በሁለቱም በኩል በድንኴን ተዘግቶ ነበር።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎች ሰርግ ደጋሹ ግለሰብ በአከባቢው ባለሃብትና የባለስልጣናት ዘመድ በመሆኑ ከሌሎች ነዋሪዎች የተለየ ሰርግ ለመደገስ በማሰብ ሁለት ግዙፍ ድንኳኖችን በግራና በቀኝ በመተከል ሺሽቾን ከወላይታ ሶዶ ፣ ከዱራሜ ፣ ወራቤና ሆሳዕና ቡታጅራ የሚያገናኘው የፌዴራል መንገድ በሁለቱም አቅጣጫ መዝጋቱን ገልጸዋል።
በዚህ ምክንያት አንድ ተሽከርካሪ በውስጥ ለውስጥ ልዋጭ መንገድ ሲሄድ ከኤሌክትሪክ መስመር ጋር ተነካክቶ መቃጠሉን አክለዋል።
ለአንድ ባለሃብት ልጅ ተብሎ መንገዱ እንዲዘጋ የሆነው በከተማዉ ከንቲባ በነበሩት አቶ ታርኩ ተስፋዬ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ሰጪነት ነው ያሉት ነዋሪዎች ይኸው ህዝብን ያስቆጣ ተግባር የፈጸሙት ከንቲባ ከስልጣን መነሳታቸውን ተናግረዋል።
የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ጊዜያዊ የሽግግር አማካሪ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ከከንቲባቅን ከስልጣን እንዳነሳ ነው ያስረዱት።
የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ጊዜያዊ የሽግግር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዙር 12 ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የከተማዋ ከንቲባ የነበሩትን አቶ ታሪኩ ተስፋየን ከስልጣን በማንሳት አቶ መለሰ ገብሬን በቦታቸው መሾሙንም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።
" በከንቲባውና አስተዳደራቸው ሕዝቡ ደስተኛ አልነበረም " ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ " በምክር ቤቱ ዉሳኔ ደስተኛ ነን " ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈ ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደዉ አስቸኳይ ጉባኤ ሌላች የስልጣን ማሰናበትና ሽግሽግ አድርጓል።
በዚህም መሠረት፦
➡️ አቶ መለሰ ገብሬ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ
➡️ ወ/ሮ ባንቺ ማቴዎስ የሺንሽቾ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ
➡️ ኢ/ር ቢኒያም ጴጥሮስ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ
➡️ አቶ አድማሱ ወልዴ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግምባታ ዘርፍ ኃላፊና የመንግስት ረዳት ተጠሪ
➡️ ወ/ሮ አጥናፏ ታዴዎስ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የመንግስት ረዳት ተጠሪ
➡️ አቶ ሽመልስ ተስፋዬ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ መሾሙን ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
@tikvahethiopia
❤ 1 408👏 372🤔 41🙏 31🕊 17🥰 10😭 8😡 6😢 5
" ልጃችንን አፋልጉን ! "
የ10 ዓመቷ ተማሪ ከቤት እንደወጣች አልተመለሰችም።
ሰላም ጥበብ እድሜዋ 10 ዓመት ሲሆን በቀን 06-04-2018 ቃሊቲ ወረዳ 06 ' ህብረት ችቦ ' ትምህርት ቤት ብላ እንደወጣች እንዳልተመለሰች ቤተሰቦቿ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።
ወላጆቿ ጭንቀት ላይ በመሆናቸው ያያችኋት ወይም ያለችበትን የምታውቁ እንድትጠቁሙ በፈጣሪ ስም ተማፅነዋል።
ስልክ:-
0924873829 አበበች ቀና
0919149785 ተስፋለም ወንድሙ
መኖርያ ሳሪስ ሃና ማርያም
🔔
" አባታችንን አፋልጉን ! "
አቶ ካሳ ኡንቱኮ የ85 ዓመት አዘውንት ሲሆኑ በቀን 05/04/18 ዓ/ም ከሚኖሩበት ሸገር ከተማ ከታ ለኩ ሚካኤል አካባቢ ለሽምግልና ጉዳይ በወጡበት አልተመለሱም።
ስልክ የሌላቸው እንደሆኑ የገለጹት ቤተሰቦች ያያቸው ወይም ያሉበትን የሚያውቅ በስልክ ቁጥር፦
0940444236
0911458834 ላይ በመወደወል እንድታሳውቋቸው ተማፅነዋል።
🔔
" ልጃችንን አፋልጉን ! "
ሚልኪ ረቡማ ሰኞ ወደ 8 ሰአት ትምህርት ቤት ለመሄድ እንደወጣች እስከዛሬ እንዳልተመለሰች ቤተሰቦቿ ገልጸውልናል።
በዕለቱ ከላይ እስኩዌር ሸሚዝ እና ከታች ኦሞ ከለር ሱሪ ቦርሳና ዩኒፎርም ይዛ ነበር።
ቤተሰብ ጭንቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን ያያችኋት በስልክ ቁጥር ፦
+251904063201
+251916248741 ላይ በመደወል ጠቁሙ።
➡️ ከቀናት በፊት ጠፍተው የነበሩት አባታችን ሹሚ ኢዳ መገኘታቸውን ቤተሰቦቻቸው ከምስጋና ጋር አሳውቀዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ልጃችንን አፋልጉን ! "
የ10 ዓመቷ ተማሪ ከቤት እንደወጣች አልተመለሰችም።
ሰላም ጥበብ እድሜዋ 10 ዓመት ሲሆን በቀን 06-04-2018 ቃሊቲ ወረዳ 06 ' ህብረት ችቦ ' ትምህርት ቤት ብላ እንደወጣች እንዳልተመለሰች ቤተሰቦቿ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።
ወላጆቿ ጭንቀት ላይ በመሆናቸው ያያችኋት ወይም ያለችበትን የምታውቁ እንድትጠቁሙ በፈጣሪ ስም ተማፅነዋል።
ስልክ:-
0924873829 አበበች ቀና
0919149785 ተስፋለም ወንድሙ
መኖርያ ሳሪስ ሃና ማርያም
🔔
" አባታችንን አፋልጉን ! "
አቶ ካሳ ኡንቱኮ የ85 ዓመት አዘውንት ሲሆኑ በቀን 05/04/18 ዓ/ም ከሚኖሩበት ሸገር ከተማ ከታ ለኩ ሚካኤል አካባቢ ለሽምግልና ጉዳይ በወጡበት አልተመለሱም።
ስልክ የሌላቸው እንደሆኑ የገለጹት ቤተሰቦች ያያቸው ወይም ያሉበትን የሚያውቅ በስልክ ቁጥር፦
0940444236
0911458834 ላይ በመወደወል እንድታሳውቋቸው ተማፅነዋል።
🔔
" ልጃችንን አፋልጉን ! "
ሚልኪ ረቡማ ሰኞ ወደ 8 ሰአት ትምህርት ቤት ለመሄድ እንደወጣች እስከዛሬ እንዳልተመለሰች ቤተሰቦቿ ገልጸውልናል።
በዕለቱ ከላይ እስኩዌር ሸሚዝ እና ከታች ኦሞ ከለር ሱሪ ቦርሳና ዩኒፎርም ይዛ ነበር።
ቤተሰብ ጭንቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን ያያችኋት በስልክ ቁጥር ፦
+251904063201
+251916248741 ላይ በመደወል ጠቁሙ።
➡️ ከቀናት በፊት ጠፍተው የነበሩት አባታችን ሹሚ ኢዳ መገኘታቸውን ቤተሰቦቻቸው ከምስጋና ጋር አሳውቀዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Assosa
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ወርቅ እና ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ይዘው በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ከእነኤግዚቢቱ በአሶሳ ከተማ አምባ አንድ በሚባል ቦታ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል፡፡
ወርቅና ጥሬ ገንዘቡ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተደረገ ክትትል ነው ብሏል።
የተጠርጣሪዎቹ ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ይፋ ባይደረግም በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እያጣራባቸው እንደሆነ አሳውቋል።
የተያዘው ወርቅና ጥሬ ገንዘብ ለአሶሳ ከተማ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ገቢ መደረጉን ተመላክቷል።
@tikvahethiopia
❤ 822😱 197😭 72😢 59👏 55😡 40🕊 24🤔 16💔 14🙏 9🥰 5
አራተኛው የኢንቨስትመንት ባንክ በዛሬው ዕለት በይፋ ስራ መጀመሩን ገልጿል።
አዋሽ ካፒታል አ.ማ. በኢትዮጵያ ከሚንቀሳቀሱ እና ከካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ ከተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ባንኮች አራተኛው ሆኖ ስራ መጀመሩን በዛሬው ዕለት ተገልጿል።
የአዋሽ ካፒታል አ.ማ. የቦርድ ሰብሳቢ እና የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው የአዋሽ ባንክ ተቀጥላ ኩባንያ የሆነው አዋሽ ካፒታል አ.ማ ህጉ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶችና መመዘኛዎች በሟሟላት ሙሉ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መቀበሉን አሳውቀዋል፡፡
አዋሽ ካፒታል አ.ማ የተቋቋመው በሁለት መቶ ሚሊዮን ብር ካፒታል መሆኑንም ተገልጿል።
የአዋሽ ካፒታል 95 በመቶ ባለድርሻ አዋሽ ባንክ ሲሆን ቀሪው 5 በመቶ በተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተያዘ ነው።
አዋሽ ካፒታል አክስዮን ማህበሩ:-
• በድርጅት ፋይናንስ እና የማማከር አገልግሎት፤
• በዋስትና ንግድ እና የማገናኘት ስራ፤
• በምርምር እና የገበያ ኢንተሊጀንስ ፤
• በአረንጓዴ ፋይናንስ እና የESG (ከባባዊ፣ ማህበራዊና አስተዳዳራዊ) የማማከር አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
❤ 756🙏 54🤔 25😢 19😡 13👏 11🕊 7🥰 6😭 5😱 1
ጉቦ በተቀበሉ ዐቃቤ ሕግ እና ግብረ አበሮቹ ላይ የወንጀል ክስ ቀረበ።
በፍትሕ ሚኒስቴር ዐቃቤ ሕግ የነበረ እና ግብረ አበሮቹ ከባለጉዳይ በተሰጠ ጥቆማ መሰረት በጉቦ መቀበል ወንጀል ተጠርጥረው በሕግ ቁጥጥር ሥር ውለው የወንጀል ምርመራ ሲጣራባቸው ቆይቶ ታሕሳስ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በሙስና ወንጀል ክስ ቀረበባቸው።
ስማቸው ይፋ ያለተደረጉት ተጠርጣሪዎቹ በወንጀል ተጠርጣሪ የነበሩ ግለሰብ ላይ " የወንጀል ክስ እንዳይቀርብ እናደርጋለን " በማለት 1 ሚሊየን ብር እንዲከፍሏቸው ሲደራደሩ ይህንን ድርጊት ጠቋሚዎች ለፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በማሳወቃቸው በተጠርጣሪዎቹ ላይ ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በቅንጅት ክትትል በማድረግ ሕዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከግለሰቡ ቤተሰቦች 500,000 ብር ለጊዜው ባልተያዘ ግብረ አበራቸው የባንክ ሒሳብ እንዲገባ አድርገው የጉቦውን ገንዘብ ያስገቡበትን ደረሰኝ ሲሰጡ እጅ ከፍንጅ ሊያዝ ችሏል።
ይህንን ተከትሎ አስፈላጊ እና አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች በማሰባሰብ የወንጀል ምርመራ ሥራውን በማጠናቀቅ ታሕሳስ 8 ቀን 2018 ዓ.ም የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) (ሀ) እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 10 (1) እና (2)ን በመጥቀስ በተከሳሾቹ ላይ የወንጀል ክስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦባቸዋል።
ፍትሕ ሚኒስቴር ይህንን ጥቆማ በመስጠት ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ላገዙ አካላት ምስጋና አቅርቧል።
ሚኒስቴሩ በሠራተኞቹ የሚፈጸሙ ተመሳሳይ የሙስናና የሌብነት ተግባራትን ተከታትሎ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ተጠሪነቱ ለሚኒስትሩ የሆነ ልዩ ቡድን በማቋቋም ወደ ሥራ እንደገባ ገልጿል።
" እንዲህ አይነት ተግባራትን በሚፈፅሙ ሠራተኞች ላይ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነኝ " ያለው ሚኒስቴሩ " በፍትሕ አካላት የሚፈጸም የሙስና ተግባር ከየትኛውም በላይ አስከፊ በመሆኑ ማንኛውም ሀገር ወዳድ ዜጋ ተመሳሳይ ተግባራትን አስመልክቶ ማንኛውም መረጃ ሲኖረው መረጃውን ለፍትሕ ሚኒስቴር በስልክ ቁጥር +251115584819 ወይም +251952 66 66 11 በማሳወቅ የፍትሕ ሥርዓቱን በመጠበቅ እንዲያግዘን እንጠይቃለን " ብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
❤ 766👏 168🙏 23🕊 21😭 20🤔 18😡 7😱 4😢 4
የኢትዮጵያን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት "የኢትዮጵያ የስንዴ ትራንስፎርሜሽን ጉዞ" የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት (ATI) በዛሬው ዕለት አግሪለርን የተሰኘ ፕላትፎርም እና "የኢትዮጵያ የስንዴ ትራንስፎርሜሽን ጉዞ" የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ይፋ አድርጓል።
"የኢትዮጵያ የስንዴ ትራንስፎርሜሽን ጉዞ" የተሰኘው ዘጋቢ ፊልም 41 ደቂቃ ርዝመት ያለው ሲሆን ሌስ አንጀለስ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰራ ነው።
ፊልሙ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች እየተከናወኑ ያሉ እና ኢትዮጵያን በአፍሪካ ግንባር ቀደም የስንዴ አምራች አድርጎ ያስቀመጣትን ዋና ዋና ጥረቶች የሚያስገነዝብ ነው።
ኢንስቲትዩቱ በተጨማሪም "አግሪ ለርን" የተሰኘ በግብርና ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ፕላትፎርም (Learning Management System) ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ስር የሚገኘው አደይ ፕሮጀክቶች ከ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በጋራ በመሆን ያቀረበው ይህ ፕላትፎርም "ወጣቶች እና ሌሎችም በግብርና ዙሪያ እውቀት ተኮር ግንዛቤ ማግኘት የሚፈልጉ አካላት ራሳቸውን የሚያስተምሩበት ነው" ተብሏል።
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ኢኖቬሽን ዳይሬክተር አቶ ግሩም ከተማ ለቲክቫህ በሰጡት ቃል መጠይቅ ምን አሉ ?
" የአደይ ፕሮጀክት አንዱ አላማ ወጣቶች ለግብርና ዘርፍ ስራ እንዲሰሩ ማመቻቸት ነው ፣የእዚህ ፕሮጀክት አንዱ አካል ደግሞ በጉዳዩ ዙሪያ እውቀት እንዲያገኙ ማስቻል ነው ።
የአግሪ ለርን ፕላትፎርም አላማውም ለምሳሌ አንድ ወጣት በንብ ማነብ ወይም በአቮካዶ እርሻ ላይ መሰማራት ቢፈልግ ከአስተሳሰብ ለውጥ ፣ቢዝነሱን እንዴት መምራት እንዳለበት እና በስራውም ሲሰማራ ምን ሊያስፈልገው ይችላል የሚለውን ጨምሮ ካመረተም በኋላ እንዴት እንደሚሸጥ ያሳየዋል።
ብድር ከየት እንደሚያገኝ በምን መልኩ ለብድር ማመልከቻ ያስገባ የሚለውንም ግንዛቤ እንዲያገኝ ይረዳዋል።
በውስጡ አግሮ ኢኮኖሚክስ ላይ አምስት ኮርሶች፣ የአስተሳሰብ ለውጥ (Mindeset) የመሳሰሉ ስልጠናዎች ሦስት ኮርሶች ፣ ማርኬቲንግ እና ፋይናንሻል ማኔጅመንት የመሳሰሉት ላይ ደግሞ ሁለት ኮርሶች አሉት።
በኮርሶቹ ማጠናቀቂያ ወቅት ሰርተፍኬት ይሰጣል ሰርተፍኬቱን ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችል QR ኮድ ያለው ነው።
አንድ ኮርስ ለመጨረስ 60 ሰዓት የሚፈጅ ቢሆንም እንደየሰው አቅም ከዛም ባነሰ ጊዜ ሊያጠናቅቁት ይችላሉ። " ብለዋል።
ይህንን ፕላትፎርም https://agrilearn.ati.gov.et/ በመግባት በነጻ መግኘት እንደሚቻል የቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ኢኖቬሽን ዳይሬክተር አቶ ግሩም ከተማ ጠቁመዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
16.17 MB
❤ 409😡 125🤔 32👏 9🙏 7😭 6😢 4🕊 3💔 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
❤ 73🤔 13😡 9🥰 6💔 5🙏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#MPESAEthiopia
ፈጣን የክፍያ መንገድ ከM-PESA!
የM-PESAን መተግበሪያ በመጠቀም የትኛውንም QR Scan በማድረግ እንዲሁም ከየትኛውም የክፍያ መፈፀምያ መተግበሪያ የM-PESAን QR Scan በማድረግ ክፍያችንን እንፈፅም።
መተግበሪያውን ለማውረድ ይህንን ይጫኑ
https://onelink.to/ewsb22
ለተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ያግኙን፥
https://t.me/MPesaETCustomerCare
#MPESAEthiopia
❤ 96👏 6🙏 3😭 1😡 1
00:18
Відео недоступнеДивитись в Telegram
ወደ አቢሲንያ ባንክ የሚወስዳችሁ ብዙ ምክንያት አለ! ሁሉም ምክንያቶች ያሸልማሉ!
ከእርስዎ የሚጠበቀው የባንካችን ቤተሰብ በመሆን፣ በቅርንጫፍም ሆነ በዲጂታል አማራጮቻችን አዲስ ሂሳብ መክፈትና ተቀማጭ ማድረግ ፣ ነባር ሂሳብዎ ላይ ተጨማሪ ገቢ ማድረግ ፣ በፊት ገፅታዎ እና በጣት አሻራዎ የደንበኝነት ምዝገባ ማካሄድ፣ በባንካችን የውጭ ምንዛሬ መመንዘር ወይም ገቢ ማድረግ እንዲሁም ከባንካችን ጋር በአጋርነት ከሚሠሩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በአቢሲንያ ባንክ በኩል ክፍያ መፈጸም ብቻ ነው!
ያን ጊዜ የሚያስሸልሙ ኩፖኖችን ወዲያውኑ ያገኛሉ!
እነዚያ ኩፖኖች ደግሞ፦ አዲስ ሀዩንዳይ ኤሰንት መኪና፣ ቲቪና ላፕቶፕ፣ ጨምሮ ሌሎች በየ15 ቀኑ ፍሪጅ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን እና ሌሎችም አጓጊ ሽልማቶችን አሸናፊ ያደርግዎታል፡፡
ያስታውሱ—የብዙ ኩፖኖች መኖር የሽልማት ዕድልን ይጨምራል
ለበለጠ መረጃ :የባንካችንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፤
👉 https://t.me/+llUA1MmaoxgxM2Y0
ABISIANIA Campaign Social Media 1.mp497.62 MB
❤ 240😡 7😭 6👏 5😱 3🥰 2🕊 2😢 1
" የማህበራዊ ሚዲያ ' አንቂ ነን ' ባዮችን አልታገስም " - የአዲስ አበባ ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያም የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ሙያዊ ክብርን የሚያዋርዱ፣ ከህብረተሰቡ ባህል፣ እምነትና ሞራል ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ የነበሩ " የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪዎች ነን " (Social Media Influencers and Content Creators) የሚሉ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ ይገኛል፡፡
የመጀመሪያዎቹ ተጠርጣሪዎች ዛሀራ መሀመድና ፈቲያ ኤልያስ የተባሉ ነዋሪነታቸው በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቦሌ ቡልቡላ ሲሆን የቲክቶክ ፕላትፎርምን በመጠቀም የሀገሪቱን ባህል፣ ወግ፣ እምነትና ሞራል በማይመጥን መልኩ "Illuminant" ወይም " የሠይጣን ማህበርተኞች አባላት ነን እኛን ምሰሉ፤ በርካታ ገንዘብ ታገኛላችሁ" የሚሉ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ሦስተኛው ተጠርጣሪ ደግሞ ለታ ደረጄ ተረፋ የተባለ ነዋሪነቱ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ልዩ ቦታው ጀሞ ሦስት የሆነ " የተከበረውን የመምህርነት ሙያና የመምህራንን ክብር በሚያንቋሽሽ መልኩ" ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እየሰራ በቲክቶክ ፕላትፎርም ሲያሰራጭ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
ተጠርጣሪው በሚለቃቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎች የተማሪ የደንብ ልብስ ለብሶ የመማሪያ ወንበሮች ላይ ቆሞ መጨፈር፣ በመምህራን ላይ የማሾፍ፣ ከተማሪ ኪስ ገንዘብ የመስረቅና የመሳሰሉ ይዘቶችንም ይሰራ እንደነበር ፖሊስ አረጋግጧል፡፡
አራተኛው ተጠርጣሪ ኤዶም ሚሊዮን ሲሆን ነዋሪነቱ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ካምቦሎጆ እንዲሁም የሽመልስ ሀብቴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሲሆን እርሱም የቲክቶክ ፕላትፎርምን በመጠቀም ከወገቡ በላይ ልብሱን በማውለቅና ራቁቱን በመሆን "ሰግጥ ፈምስ" በማለት በየመንገዱ ህብረተሰቡን የማስደንገጥ፣ ራቁቱን ምግብ በትሪ በመያዝ ህብረተሰቡን ካላጎረስኳችሁ የማለትና የማስደንገጥ ይዘቶችን ሲሰራ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋሉ ግለሰቦች ወይም " የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪዎች ነን" (Social Media Influencers and Content Creators) በሚሉ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን የወንጀል ምርመራ ስራ የጀመረ ሲሆን በቀጣይም ተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ የሚገቡ የማህበራዊ ሚዲያ "አንቂ ነን" ባዮችን እንደማይታገስም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያሳስባል፡፡
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopi
#NewsAlert
የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወቅታዊ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ ላይ መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም መግለጫው ፥ ለፀጥታ ስራ ተመድበው ከሚሰሩ የሰራዊት አባላት ውጪ የትኛውንም የጦር መሳሪያ ይዞ የሚገኝ እና የሚንቀሳቀስ ግለሰብ ወይም ቡድን ላይ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስዱ መሆኑን አስገንዝቧል።
@tikvahethiopia
❤ 553🕊 122🙏 65👏 43😡 26🤔 13🥰 12💔 11😱 9😢 3😭 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#Gambella : በዛሬው ዕለትም በጋምቤላ ከተማ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተኩስ እሩምታ ሲሰማ እንደዋለ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
" ተኩስ በተለያዩ አቅጣጫዎች ቀጥሎ እየተሰማ ነው የዋለው " ያሉን ነዋሪዎቹ " ሁኔታዎቹ የሚያስፈሩ ናቸው ፤ ከቤት ለመውጣትም ከፍተኛ ስጋት ነው ያለው " ብለዋል።
" አሁንም ያለው ሁኔታ ከዚህ እጅግ ሳይከፋ አንድ ነገር ሊደረግ ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።
አንድ የጤና ተቋም ምንጭ " ዛሬ ቀን ሙሉ ተኩስ ነበር የተጎዱ ሰዎችም ወደ ጤና ተቋም ሲመጡ ነበር " ብለዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
😢 452❤ 332😭 115🕊 76💔 48🤔 23👏 19😡 19😱 15🙏 10🥰 5
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#Tigray
በፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) የሚመራ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ልኡክ ወደ አዲስ አበባ አቅንቷል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ዛሬ ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም ባጋራው አጭር መረጃ ፥ ልኡኩ ወደ አዲስ አበባ ያቀናው በክልሉ አሁናዊ ሁኔታ ከፌደራል መንግስት ለመወያየት ነው።
በልኡክ ቡድኑ ፕሬዜዳንቱና ምክትላቸው እንዲሁም ሌሎች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መካተታቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
@tikvahethiopia
🕊 424❤ 293😡 41🙏 34👏 24😭 13🤔 10😢 6🥰 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵
ሰኞ ታህሳስ 6/2018 16ኛው እና የመጨረሻው ዙር ዕጣ አወጣጥ በቲክቶክ እና ፌስቡክ ገፃችን ላይ በቀጥታ ስናስተላልፍ በነበረዉ መሰረት የ1000,000 ብር ዕድለኞች ከሮቤ እና ሎጊያ ሆነዋል።
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡ https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን👉🏽 https://t.me/official_safaricomet_bot
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#besh
❤ 149😡 17🙏 8😱 3🤔 2🕊 1
#Ethiopia🇪🇹 #India🇮🇳
" የተማሪዎችን ነፃ የትምህርት ዕድል (scholarship) በእጥፍ ለማሳደግ ወስነናል " - የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ሰፊ ውይይት ማካሄዳቸውን አሳውቀዋል።
ከ105 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ባለው የX ገጻቸው ላይ በአማርኛ ቋንቋ ባሰራጩት መልዕክት ፥ " የህንድ እና የኢትዮጵያን ትስስር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ከፍ ለማድረግ ወስነናል " ብለዋል።
የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር ሶስት ቁልፍ ሀሳቦች ተነስተዋል ያሉ ሲሆን እኚህም ፦
- በምግብ ዋስትና እና በጤና ደህንነት መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር። ይህም በዘላቂ ግብርና፣ በተፈጥሮ እርሻ እና በግብርና ቴክኖሎጂ ላይ ያለውን ትብብር ያካትታል።
- የአቅም ግንባታን ማሳደግ። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ውስጥ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለማስተዋወቅ እና የተማሪዎችን ነፃ የትምህርት ዕድል (scholarship) በእጥፍ ለማሳደግ ተወንሷል። ይህ ብዙ ተጨማሪ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በህንድ ውስጥ የከፍተኛ ትምህርት እድሎችን እንዲያገኙ እና ወጣቶች ከወጣቶች ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ያስችላቸዋል።
- በዲጂታል የህዝብ መሠረተ ልማት (DPI) ላይ በስፋት ስለ መስራት ናቸው።
በሌላ በኩል፥ ትላንት ምሽት ጠ/ሚ ናሬንድራ ሞዲ ‘የኢትዮጵያ ታላቅ ክብር ኒሻን’ ተበርክቶላቸዋል።
" ኒሻኑን ላበረከቱልኝ የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ምስጋናዬን አቀርባለሁ " ብለዋል።
" በዓለም ላይ ካሉት ጥንታዊ እና ሀብታም ስልጣኔዎች አንዱ በሆነ ሀገር መከበር፤ እጅግ በጣም ኩራት የሚንጸባረቅበት ጉዳይ ነው። ይህ ክብር ባለፉት ዓመታት አጋርነታችንን ለቀረጹ እና ላጠናከሩት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ህንዳውያን ነው " ሲሉ በአማርኛ ቋንቋ ባሰራጩት መልዕክት ገልጸዋል።
" ህንድ ተቀያያሪ የሆኑ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና አዳዲስ እድሎችን ለመፍጠር ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ ሆና ትቀጥላለች " ብለዋል።
ናሬንድራ ሞዲ ዛሬ ጥዋት በህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ያጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውንም አጠናቀው ተሸኝተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
❤ 1 747😡 129👏 99🙏 64😭 23🕊 13😱 11🤔 10🥰 8😢 4
#Ethiopia🇪🇹#Algeria 🇩🇿
ኢትዮጵያ እና አለጀሪያ በፍትህ ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የፍትህ ሚኒስቴር ገልጿል።
የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በላይሁን ይርጋ ከአልጀሪያ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጋር በአለጄሪያ ዋና ከተማ አልጀርስ ተገናኝተው መክረዋል።
ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል በፍትህ ዘርፍ ያለውን ትብብር እና ቅንጅት የበለጠ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።
ሁለቱም አመራሮች ቀጣይ በፍትህ ዘርፍ ያለውን ግንኙነት ወደተሻለ ደረጃ ማሳደግ የሚቻልባቸውን ጉዳዮች አንስተው ተወያይተዋል።
አቶ በላሁን ይርጋ ከአልጀሪያ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር በተጨማሪ ፦
- ከፍትህ ሞድረናይዜሽን ተቀም /Justice modernization directorate General/ ፣
- ከህግና ዳኝነት ጥናት ማዕከል /Legal and Judicial research center/ ፣
- ከዳኝነት ጉዳይ ተቋም/Judicial affairs directorate General/ ፣
- የማረሚያ ቤት ሰራተኞት ማሰልጠኛ ተቋም /National School for prison administration staff / እና የማጂስትሬሲ ከፍተኛ ትምህርት ቤት /Higher school of magistracy/ አመራሮች ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት የፍትህ ተቋማት መካከል ስለሚኖር ግንኙነት እና ትብብር ውይይት ማድረጋቸውን የፍትህ ሚኒስቴር አሳውቋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
❤ 329😡 55🤔 14😭 12👏 4🙏 4🕊 4😢 2
