Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
Відкрити в Telegram
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Показати більше2025 рік у цифрах

228 794
Підписники
-18824 години
-1 0407 днів
-4 59130 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 2:00 ሲሆን በዘመድ ቴቪ መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።
• ቲክቶክ 👉 tiktok.com/@zemedkun.b
• ZemedTv 👉 zemedtv.com/live.html
• በትዊተር (×) 👉 x.com/i/broadcasts/1vOGwdZNPnRJB
• በራምብል 👉 rumble.com/v730dta--zemede-december-14-2025.html?e9s=src_v1_cbl%2Csrc_v1_upp_a
• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Yahsat 52.5° East
11977 H 27500 ...ላይ ይከታተሉን።
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!
01:28
Відео недоступнеДивитись в Telegram

2.70 MB

“…አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፤ ተመልከት ስድባችንንም እይ። ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ። ድሀ አደጎችና አባት የሌለን ሆነናል፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆነዋል። ውኃችንን በብር ጠጣን እንጨታችንን በዋጋ ገዛን። አሳዳጆቻችን በአንገታችን ላይ ናቸው፤ እኛ ደክመናል ዕረፍትም የለንም። ሰቆ 5፥ 1-5
"…እነሆ፥ ዛሬ ባሪያዎች ነን ፍሬዋንና በረከትዋን ይበሉ ዘንድ ለአባቶቻችን በሰጠሃት ምድር፥ እነሆ፥ በእርስዋ ባሪያዎች ነን፥ ስለ ኃጢአታችንም ለሾምህብን ነገሥታት በረከትዋን ታበዛለች፤ ሰውነታችንንም ይገዛሉ፥ በእንስሶቻችንም የሚወድዱትን ያደርጋሉ፥ እኛም በጽኑ መከራ ላይ ነን። ነሀ 9፥ 36-37
"…ባሪያዎች ሠልጥነውብናል፤ ከእጃቸው የሚታደገን የለም። ከምድረ በዳ ሰይፍ የተነሣ በሕይወታችን እንጀራችንን እናመጣለን። ከሚያቃጥል ከራብ ትኩሳት የተነሣ ቁርበታችን እንደ ምድጃ ጠቈረ።…የልባችን ደስታ ቀርቶአል፤ ዘፈናችን ወደ ልቅሶ ተለውጦአል። አክሊል ከራሳችን ወድቆአል፤ ኃጢአት ሠርተናልና ወዮልን! ስለዚህ ልባችን ታምሞአል፤ ስለዚህም ነገር ዓይናችን ፈዝዞአል፤
"…አቤቱ፥ አንተ ለዘላለም ትኖራለህ፤ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ? አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ። ሰቆ 5፥ 8-21
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እሺ ወገን ቅምሻ ርእሰ አንቀጿ ይህን ትመስላለች። አጭር ናት ግን ደግሞ ጣፋጭ። በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ የተሰበውን ሴራ በጋራ እናፈርሰዋለን። እስከዚያው ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ የደብሩን ካህናት ማስደብደብ፣ ማሸማቀቅ፣ ከደብሩ ማስቀየር ወዘተ ገታ ቢያደርጉ ጥሩ ነው። የቅዱስ ላሊበላ ካህናት እንባ አይጠቅምዎትም።
"…ጉድ ነው ዘንድሮ። በየዘርፉ ትንቅንቅ። ውጊያው መንፈሳዊ ነው። አሸናፊው ግን እግዚአብሔር ነው።
• ትዝብታችሁን ✍✍✍
👆②✍✍✍
3. ሰባቱ የጌታ ቃላት (እኔ ነኝ)
ሀ. የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ
ለ. የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ
ሐ. እኔ የበጎች በር ነኝ
መ. መልካም እረኛ እኔ ነኝ
ሠ. ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ
ረ. እኔ መንገድ እና ህይወት ነኝ
ሰ. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ
4. ሰባቱ ሰማያት
ሀ. ጽርሐ አርያም
ለ. መንበረ መንግሥት
ሐ. ሰማይ ውዱድ
መ. እየሩሳሌም ሰማያዊት
ሠ. ኢዮር
ረ. ራማ
ሰ. ኤረር
5. ሰባቱ ሊቃነ መላአክት
ሀ. ቅዱስ ሚካኤል
ለ. ቅዱስ ገብርኤል
ሐ. ቅዱስ ሩፋኤል
መ. ቅዱስ ራጉኤል
ሠ. ቅዱስ ዑራኤል
ረ. ቅዱስ ፋኑኤል
ሰ. ቅዱስ ሰቂኤል
6. ሰባቱ አቢያተ ክርስቲያናት
ሀ. የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
ለ. የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን
ሐ. የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
መ. የትያጥሮስ ቤተ ክርስቲያን
ሠ. የሴርዴስ ቤተ ክርስቲያን
ረ. የፊልድ ልፍልያ ቤተ ክርስቲያን
ሰ. የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን
7. ሰባቱ ተአምራት
ጌታ እየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተአምራት
ሀ. ፀሐይ ጨልሟል
ለ. ጨረቃ ደም ሆነ
ሐ. ከዋክብት ረገፉ
መ. አለቶች ተሰነጣጠቁ
ሠ. መቃብራት ተከፈቱ
ረ. ሙታን ተነሡ
ሰ. የቤተ መቅደስ መጋረጃ
8. ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት
ሀ. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ
ለ. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
ሐ. ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ
መ. እነሆ ልጅሽ እናትህ እነሆት
ሠ. ተጠማሁ
ረ. ተፈፀመ
ሰ. አባት ሆይ ነብሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ
9. ሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን
ሀ. ምስጢረ ጥምቀት
ለ. ምስጢረ ቁርባን
ሐ. ምስጢረ ክህነት
መ. ምስጢረ ሜሮን
ሠ. ምስጢረ ተክሊል
ረ. ምስጢረ ንሰሃ
ሰ. ምስጢረ ቀንዲል
10. ሰባቱ አፅዋማት
ሀ. ዐብይ ፆም
ለ. የሐዋርያት ፆም
ሐ. የፍልሰታ ፆም
መ. ፆመ ነቢያት
ሠ. ፆመ ገሀድ
ረ. ፆመ ነነዌ
ሰ. ፆመ ድህነት
11. ሰባቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ነገሮች
ሀ. ትዕቢተኛ አይን
ለ. ሐሰተኛ ምላስ
ሐ. ንፁህ ደምን የምታፈስ እጅ
መ. ክፉ ሐሳብ የምታፈልቅ ልብ
ሠ. ለክፋት የምትፈጥን እጅ
ረ. የሐሰት ምስክርነት
ሰ. በወንድማማቾች መካከል ፀብን የምታፈራ ምላስ
12.ሰባቱ የጸሎት ጊዜያት
ሀ. ነግህ (የጠዋት ፀሎት)
ለ. ሰለስት (የ 3 ሰዓት ፀሎት)
ሐ. ቀትር (የ 6 ሰዓት ፀሎት)
መ. ተሰዓቱ (የ 9 ሰዓት ፀሎት)
ሠ. ስርክ (የ 11 ሰዓት ፀሎት)
ረ. ነዋም (የመኝታ ፀሎት)
ሰ. መንፈቀ ሌሊት (የሌሊት ፀሎት)
13. ሰባቱ ዕለታት
ሀ. እሁድ
ለ. ሰኞ
ሐ.ማክሰኞ
መ. ረቡዕ
ሠ. ሐሙስ
ረ. አርብ
ሰ. ቅዳሜ
"…ጻድቁ ቅዱስ ላሊበላም ይሄን ፍፁም ቁጥር በመውሰድ የግዕዙን ፯ ቁጥር በማጠላለፍ በአራት ማዕዘን ውስጥ በመክተት በደብረ ሮሃ በቤተ ማርያም ቤተ መቅደስ ህንፃ መስኮት ላይ ቀረፀው። የጀርመኑ የናዚ ፓርቲ የወሰደው ይህንን ቅዱስ ምልክት አይደለም። የጀርመኑ የወሰደው የላቲኑን S ፊደልን በZ ፊደል መልክ S ን ቀርፆ ነው። እንደዚያ ነው። አንዳንድ የወሀቢያ እስላሞች ይናዚን ምልክት ከእኛ ጠልሰም ጋር በማምታት ኢሉሚናቲ ምናምን ሲሉ ይታያሉ። ነፈዝ ሁላ። ይከብዳችኋል። የቤተ ክርስቲያን ረቂቅ ትምህርት በጣም ነው የሚጠጥርባችሁ። ወድጄ መስዬሃለሁ ኢትዮጵያ፣ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ የምለው። የቀመስኩትን ስለቀመስኩ፣ ያገኘሁትን ስለማውቅ፣ ያየሁትን ስላየሁ ነው። ከአፍራሾች ጋር ጉረሮ ለጉረሮ የምተናነቀው ለዚያ ነው። የቀመስኩትን ስለማውቅ። ገባችሁ ኣ…? እንጂ እኮ እንደ ሌላው በላየ ባልሰማ ዝም ብዬ አውሮጳም አይደል ያለሁት ቧልት እያወራሁ፣ በአንዱ ፋብሪካ እየተጠገረርኩ፣ ወይም ጸዴ የምትሉት ቀማቴ፣ አልያም ቧልተኛ ዩቲዩበር፣ ኮተታም ቲክቶከር ሆኜ መኖር እችል ነበር።
"…ፍጥረት ሁሉ ቁጥር አለው። ቀመር አለው። በጥበብ የበለፀጉ፣ በምስጢር የተራቀቁ ሊቃውንት በሙሉ ሁሉንም ነገር በጥበብ፣ በቁጥር ነው የሚያዋቅሩት። ፯ × ፯ = ፵፱ ነው የሚመጣው። (7×7 = 49) ይሄ ቁጥር በሙሴ መጻሕፍት በተለያየ መልክ ተገልጿል። ቁጥሩን ሰፍረን ቆጥረን የማንጨርሰው በገሀዱ ዓለም የሚታዩትንና የማይታዩትን ፍጥረታት በሙሉ የፈጠረ የእግዚአብሔር አብ ቀመር ነው። አብ የሚለው ቃል በቀመር ሲገለጥ…
አ = ፵ (40)
ብ = ፱ (9)
በድምሩ ፵፱ (49) ይሆናል።
"…ቅዱስ ላሊበላ በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ ጻድቅ ስለነበረ ነው ሰማያዊቷን የብርሃን ዓለም ኢየሩሳሌምን በምድር ላይ ያነጸው። የገነባው። ደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ዳግማዊ እየሩሳሌም ተብላ የምትጠራውም ለዚህ ነው። በምድራዊቷ ኢየሩሳሌም የምናገኛቸውን ቅዱሳት መካናት በሙሉ በአንድ ስፍራ ያዘጋጀልን ነው ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ። የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ቀራንዮን፣ የሲኦልና የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌን፣ የአዳም መካነ መቃብርን ምሳሌ ሁላ የምናገኘው በደብረ ሮሃ ነው። በቅዱስ ላሊበላ። የሚደንቀው ደግሞ እነዚህ አስደናቂ ጥበብ የፈሰሰባቸው ህንፃዎች ከተሠሩ በኋላ አፈሩ የት እንደደረሰ፣ ህንፃዎቹ የተፈለፈሉበት መሳሪያዎች ለናሙና እንኳ ያለመገኘታቸው ነው። በባህር ላይ የታነፀ ሕንጻ የምታገኘው ቅዱስ ላሊበላ ብቻ ነው።
"…እደግመዋለሁ ‼ አሁን ይሄ ረቂቅ ምስጢር የተሞላ የቅዱስ ላሊበላ ቅዱስ ስፍራ ፈተና እንደተጋረጠበት ነው የሚሰማው። የፈተናው አምጪ፣ የችግሩ ፈጣሪ ደግሞ ቤተ ክህነቱ መሆኑ ነው የሚነገረው። ለዚህ ደግሞ የፈረንሳይ መንግሥትን ጨምሮ የኦሮሙማው አገዛዝ በተለይ አብይ አሕመድ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። የቀድሞዎቹም ሆነ የአሁኑ የቅዱስ ላሊበላ አስተዳደሮችም የወቀሳው በትር ያርፍባቸዋል። ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ በዋነኝነት በዚህ ምስጢራዊ ቅዱስ ስፍራ ውድመት ተጠያቂም እንደሆኑ ይገልጻሉ ሊቃውንተ ኢትዮጵያ።
"…የሊቃውንተ ኢትዮጵያን ሙሉ ስጋት፣ ጥሪ፣ ማስጠንቀቂያና ጥያቄ በሙሉ ማክሰኞ ከምስጋና በኋላ በሰፊው እንመለስበታለሁ።
"…በደብረ ሮሀ ቅዱስ ላሊበላ የምትገኙ የመከራው ገፈት ቀማሾችም ያላችሁን የቃል ስጋት በመረጃ እና በማስረጃ እንድትልኩልኝ ከወዲሁ እነግራችኋለሁ። በቅዱስ ላሊበላ ደብር እና በፈረንሳይ መንግሥት፣ በኢትዮጵያም አገዛዝ መካከል የተፈረመውን ስምምነት የሚያሳይ ሰነድ በቅርብ የምታገኙ ካላችሁ ብትልኩልኝ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው የሚሆነው። አባ ጽጌ ሥላሴ ከአሜሪካ እና እነ ቀሲስ መንግሥቱ ጎበዜ እና ቀሲስ ኃይለማርያም ከስዊድን በጥብቅ እፈልጋችኋለሁ። አቤት አለን ዘመዴ በሉኝ። ፍጠኑ።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ ከራየን ወንዝ ማዶ።
"ርእሰ አንቀጽ"
"…መርበብተ ፡ ሰሎሞን ፡ ሰሎማዊ ፡ አርበምን ፡ አርክምን ፡ ፍልቸልሚኤል ፡ ፍልፍል ፡ ሜሎስ ፡ ገጸ ፡ ፍርቃና ፡ ሜሎስ ፡ ገጸ ፡ ፍርቃና ፡ ሜሎስ ፡ ጋዴን ፡ ስሙ ፡ ዘያደነግጾሙ ፡ ለአጋንንት ፡ ለደስማ ፡ ወለማሪት ፡ ዳዊና ፡ ሐርናቂ ፡ _ ዝንቱ ፡ ማዕሰሮሙ ፡ ለአጋንንት ፡ ለባርያ ፡ ወሌጌዎን ፡ ለደስክ ፡ ወሌጌዎን ፡ ለደስክ ፡ ወለማሪት ፡ ያይቅርናሃ ፡ ሽርኵሽ ፡ አሕርኩሽ ፡ _ አወግዘከ ፡ አንተ ፡ ሰይጣን ፡ በ፸ወ፮ ፡ ጳጳሳት ፡ በ፸ ፡ ቀሳውስት ፡ በ፸ወ፯ ፡ መነኮሳት ፡ በ፸ወ፫፯ ፡ ዲያቆናት ፡ በ፸ወ፮ ፡ ነገሥታት ፡ ተአሰር ፡ ወተወገዝ ፡ ከመ ፡ ኢትግበር ፡ ሕሱመ ፡ በላዕለ ፡ ገብርከ ፡ ___። ይሄ ቅምሻ ነው።
"…የእግዚአብሔር ሕቡዕ ስም ያለበት የንጉሥ ሰሎሞን የጣት ቀለበት ከሀገረ እስራኤል ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በኢትዮጵያ ነው የሚገኘው የሚለው እምነት በምዕራባውያኑ ዘንድ ከታመነ ቆይቷል። ይህ የንጉሥ ሰሎሞን ቀለበት የአክሱም ሃውልት የተሠራበት፣ ድንጋይ የሚያለዝብ፣ ጸሎቱ ከባድ፣ ረቂቅ፣ ምስጢራዊ የሆነ ቀለበት ነው። ጻድቅ እና ንጉሥ የሆነው ቅዱስ ላሊበላም በላስታ ደብረ ሮሃ ከአንድ ወጥ ዓለት እነዚያን አስደናቂ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናትን የፈለፈለበት ጸሎት ያለበት የንጉሥ ሰሎሞን ቀለበት መገኛው ኢትዮጵያ ነው ብለው በማመናቸው ነው በጥብቅ እየፈለጉ ያሉት።
"…መንግሥቱ ኃይለማርያም ቀለበቱ በጣና ሀይቅ በዳጋ እስጢፋኖስ ነው የሚገኘው ተብሎ ተነግሮት በብዙ ደክሞ እንደ ነበር ነው የሚነገረው። ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴም በቅዱስ ላሊበላ የሆነ ምስጢር ባገኝ ብለው በብዙ እንደደከሙም ይነገራል። ዛሬም ላይ ኮሎኔል አብይ አሕመድም ዳንኤል ክብረትን ይዞ ልክ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ዳጋ እስጢፋኖስ እንደባዘነው እሱም ዳጋ እስጢፋኖስ ላይ በብርቱ እየደከመ ነው። ከዳጋ ፍንጭ ያጡት እነ አቢይ ዳንኤል በመርጦ ለማርያም እና በሌሎች የኢትዮጵያ ገዳማት እና አድባራትም እንደደከሙ ነው የሚነሰማው።
"…በትግራዩ ጦርነት ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ፣ በወሎ በቤተ ዐማራ በላስታ፣ በሰሜን ጎንደር እና በደቡብ ጎንደር አንዳንድ ገዳማትና አድባራት በጦርነቱ ሰበብ ተመዝብረዋል። ፍተሻም ተደርጎባቸዋል። በተለይ ከሦስተኛው ቤተ መቅደስ የመታነጽ ዜናን ተከትሎ ታቦተ ጽዮን የምትገኘው ኢትዮጵያ ያውም ትግራይ አክሱም ነው ተብሎ መታመኑ በዚያ አካባቢ ከባድ ውድመት ያደረሰ ጦርነት ተካሂዷል። በጦርነቱ ወቅት ኢንተርኔት ተዘግቶ፣ ስልክ ተቋርጦ፣ መብራት ጠፍቶ ነበር ጦርነቱ የተካሄደው። አሜሪካና አረቦቹ በእስራኤልም ፈቃድ ሥልጣን ላይ ያለው የኦሮሙማው አገዛዝ መሪ የሆነው አቢይ አሕመድን ወደ ሥልጣን ካመጡት በኋላ እርሱም በሰጣቸው በሀገሪቷ ላይ በነፃ የማንቧቸር ፈቃድ፣ ባቀረበላቸውም ግብዣ መሠረት በላይ በኤርትራ በኩል በሻአቢያ መሪነት የሱማሌ እና የዓረብ ወታደሮች፣ በህወሓት በኩል ደግሞ ዜግነታቸው ያለተገለጹ ነጮች እና ጥቁሮች እንዲሁም በደብረ ታቦር ግንባር በዐማራ ፋኖና በኤርትራ ወታደሮች ከተደመሰሰው የወያኔ ጦር ጋር ተደምስሰው የተረፉት ሲማረኩ 400 የኦነግ ጦር እርምጃ ይወሰድባቸው ሲባል የኦሮሙማው ጀነራሎች ጣልቃ ገብተው አይ በሕግ ነው እንጂ በደቦ ፍርድ መገደል የለባቸውም የሚል ምክንያት በማቅረብ ተጨመሪ ምርመራና ምስጢር እንዲያወጡ መደረግ አለባቸው በማለት ከወያኔ ጎን ተሰልፈው በተለየ ሁኔታ የዐማራ ክልልን ያወደሙትን ኦነጎች የኦሮሙማው ጀነራሎች ታድገዋቸዋል። በጭና ተክለሃይማኖት የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ትግሬዎቹ ብቻቸውን ያን አረመኔያዊ ድርጊት እንዳልፈጸሙትም መታመን የተጀመረው ከዚያ በኋላ ነው። የፈለገ አረመኔ ቢሆን አንድ ትግሬ ያውም ኦርቶዶክስ የሆነ የቤተ ክርስቲያን ካህን አርዶ፣ የካህኑን ሚስት ደፍሮ ከዚያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በግ አርደው በቤተ መቅደሱ ውስጥ ተመግበው፣ መቅደሱን አቆሽሸው ይወጣሉ የሚል እምነት የለኝም። የሆነው ሆኖ በተቀነባበረ የርስ በእርስ ጦርነት ኦርቶዶክሱ ዐማራና ትግሬ ወድሟል። ውድመቱን ተከትሎ ፈረንጅ ዱቄት ይዞ ትግሬን ማዕተቡን ማስበጠስ ሲጀምር ጎንደርን የኦሮሞ ፓስተር ጎንደር ላይ መሬት ላይ እያንደባለለ መሳቂያ፣ መሳለቂያ ሲያደርገው ታይቷል። ዐማራም ትግሬም ተርበው ማዕተባቸውን ለጠኔያቸው ማስታገሻ ዱቄት ሲሉ እንዲበጥሱ እየተደረገ ነው።
"…ፍጻሜ ያላገኘው የታቦተ ጽዮን ጉዳይ እስከአሁን ሁሉንም እንዳወዛገበ ሲሆን የታቦተ ጽዮን ጉዳይ መቋጫ እስኪያገኝ ድረስ ተብሎ የምዕራቡ ዓለም ፊቱን ወደ ቅዱስ ላሊበላ ለማዞር ተገድዷል። ቅዱስ ላሊበላ ማለት ረቂቅ የኢትዮጵያውያን ቀደምት አባቶች የምስጢር ካዝና የሆነ ስፍራ ነው። ደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ እና አከባቢው ታች እስከ አባዮሴፍ ተራራ፣ እመኪና መድኃኔዓለም፣ ገነተ ማርያም ድረስ በምስጢር የታጨቀ ምድር ነው። የሥነ ከዋክብት አጥኚዎች እንደሚሉት፣ እንደሚናገሩት ከሆነ ለሥነ ፈለክ ጥናት በምድራችን ላይ ካሉ ሥፍራዎች ላሊበላ ዋነኛና ቀዳሚ ሥፍራ እንደሆነ ነው የሚናገሩት። እነ መምህር ሮዳስ ታደሰ ባለፈው ጊዜ የተከሰተውን የፀሐይ ግርዶሽ በተመለከተ ሁኔታውን ለዓለም ለማስረዳት ያደርጉ በነበረው እንቅስቃሴ ወቅት የፀሐይ ግርዶሹ በትክክል በነጥብ ሙሉ ለሙሉ የሚጋረደው ፀሐይ በቅዱስ ላሊበላ አናት ላይ ባረፈች ጊዜ ነው በማለት ሲናገሩ ከርመው፣ ነጭም፣ ጥቁርም፣ ምሑራንና ተማሪዎችን ይዘው ላሊበላ ሄደው የተባለውም ድርጊት ተፈጽሞ እነ ሮዳስም ታዋቂነትን አግኝተውበት የተመለሱበት ክስተት የተፈጠረው በቅዱስ ላሊበላ ነው። ቅዱስ ላሊበላ ዝም ብሎ ፍልፍል ህንፃ ብቻ አይደለም።
"…ኋላ ላይ የጀርመኑ ናዚ ገለባብጦ የተጠቀመት የስዋስቲካ ምልክት አርማው ከዘመናት በፊት በሌላ ገጽ በግዕዙ ፯ ቁጥር ተቀርጾ አስቀድሞ የተቀመጠበት ነው የቅዱስ ላሊበላ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን። መነሻው መጽሐፍ ቅዱስ የሆነ ጥበብ የተገለጸበት ነው ቅዱስ ላሊበላ። ይሄ ምልክት የሚገኝበት ቤተ ማርያም ውስጥ ያለው አንደኛው አምድም ጥብቅ ምስጢር የያዘ ስለሆነ ዓምዱ አይገለጽም። ቤተ ገብርኤልም ሌላው አስደናቂ ስፍራ ነው። እነዚህ ሁሉ አሁን ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦባቸዋል። ካህናት ተባረው፣ ምዕመናን ተባርረው፣ ከአዲስ አበባ መነኮሳት መጥተው ያስተዳድሩት፣ ይቀደስበትም እየተባለም ነው።
"…ስለስዋስቲካ ካነሳን አይቀር እስቲ ፯ ቁጥርን መነሻ አድርገን ጥቂት እንንገራችሁ። "…ሰባት ጊዜ ሰባት አድርገህ የዓመታትን ሰንበት ሰባት ቍጠር፤ የሰባት ዓመታትም ሰንበት ዘመን አርባ ዘጠኝ ዓመት ትቈጥራለህ። ዘሌ 25፥ 8። በማለት ራሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ለሊቀ ነቢያት ሙሴን ሲያዘው እናያለን። እዚህ ላይ ሰባት ቁጥርን፣ ሰንበትን፣ ሰ ፊደል ራሷን እናገኛታለን። ሀለሐመሠረሰ ብለን ፊደላቱን ወደታች ስንቆጥር ፊደል ሰ 7ተኛ ተራ ቁጥር ላይ እናገኛታለን። ሰባት ቁጥር ደግሞ ፍፁም ቁጥር ነው። ስለ 7 ቁጥር ካነሳን እግረ መንገዳችንን ሰባት የሆኑ ምስጢራትን በሙሉ ዓይተን ብናልፍ ምን ይለናል? ምንም።
1. ሰባቱ አባቶች
ሀ. ሰማያዊ አባት እግዚአብሔር
ለ. የነብስ አባት
ሐ. ወላጅ አባት
መ. የክርስትና አባት
ሠ. የጡት አባት
ረ. የቆብ አባት
ሰ. የቀለም አባት
2. ሰባቱ ዲያቆናት
ሀ. ቅዱስ እስጢፋኖስ
ለ. ቅዱስ ፊልጶስ
ሐ. ቅዱስ ጵሮክሮስ
መ. ቅዱስ ጢምና
ሠ. ቅዱስ ኒቃሮና
ረ. ቅዱስ ጳርሜና
ሰ. ቅዱስ ኒቆላዎስ
"…👇①✍✍✍

❤ 31🙏 12👍 6🤯 1

🙏 26❤ 20👍 6
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መልካም…!
"…ከምስጋናው ቀጥሎ ለዛሬ ከሊቃውንተ ኢትዮጵያ ጋር በነበረን ሳምንታዊ ውይይት ወቅት በቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ስለተጋረጠው ከባድ እና አስፈሪ አደጋ የሚያወሳ ርእሰ አንቀጽ ውይይቱን ወደ ጽሑፍ ቀይሬ በርእሰ አንቀጽ መልክ በማዘጋጀት ለዛሬ እንደምለጥፍላችሁ ቀጠሮ በመያዝ ነበር የተለያየነው።
"…ነገርየው ከባድ ነው። እንዴ እንቅልፍ ሁላ ነው ያሳጣኝ። አዘጋጅቼውም አላልቅ ነው ያለኝ። የተጠቀሱት የግለሰብ ስሞችም ራሳቸውን የመከላከል መብት አልነፍጋቸውም። በአብያተ ክርስቲያናቱ ላይ ለተጋረጠው አደጋ በስም ተጠቅሰው የተወቀሱት በሙሉ እኛም ምላሽ አለን ቢሉ በሬ ክፍት ነው። አቡነ ኤርሚያስን ጨምሮ ማለት ነው።
"…ለዛሬ ግን እንደ ቅምሻ፣ እንደ መግቢያ አፒታይዘር ነው የምትሉት? እንደዚያ የሆነ የመንደርደሪያ የርእሰ አንቀጽ ቅምሻ እለጥፍላችኋለሁ። ሙሉውን ግን ጥንቅቅ አድርጌ ፈጽሜ ማክሰኞ ከምስጋና በኋላ እለጥፍላችኋለሁ። እንግዲህ ምን ይደረግ? የምጽፈው በእጅ ስልኬ ነው። ከ1ሺ አጀንዳዎች መሃል እየመረጥኩ የምተጋተገው በእጅ ስልኬ ነው። ከባድ አጀንዳ ሲሆን ጥንቃቄ፣ ጊዜም ይፈልጋል። ለዚያ ነው ኦጎኖቼ።
"…በነገራችን ላይ የአዶልፍ ሂትለር የፓርቲው ምልክት እና በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ በቤተ ማርያም መስኮት ላይ ያለው ምልክት አንድ አይነት አይደለም። የእኛው ፍፁም የሆነው ፯ ቁጥር ሲሆን የሂትለር ፓርቲ አርማ ስዋስቲካው ግን የላቲኗ S ፊደል በዜድ ፊደል ቅርጽ ተሠርታ ነው። የእኛ ሰባት፣ ሰንበት፣ ፊደል ሰ ራሱ 7ተኛ ረድፍ ላይ ነው የሚገኘው። ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ 7 ፍጹም ቁጥር ነው። ሰባቱ ሰማያት፣ ሰባቱ ዕለታት ወዘተ በሰፊው እመጣበታለሁ።
• እናስ ጎበዝ የሊቃውንተ ኢትዮጵያን የርእሰ አንቀጽ ቅምሻ ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…?
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"…እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፡— ሥራህ ግሩም ነው፤ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ። መዝ 66፥3
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
• ሁለት ነገር…!
• አንደኛው ሕልም ነው።
"…በሕልሜ ይመስለኛል። እንዴት እዚያ እንደተገኘሁ አላውቅም ግን በሀገረ አማሪካ በዋሽንግተን ዲሲ ሮጲላ ማረፊያ ተርሚናል ውስጥ ቆሜ ይመስለኛል። ከፊቴ ከሀገረ አማሪካ ወደ አውሮጳዊቷ ኔዘርላንድ አመስተርዳም ከተማ ለመብረር በKLM አየር መንገድ ጠያራ ለመሳፈር በዋሽንግተን ዲሲ ዳላስ አውሮጵላን ጣቢያ ሻንጣውን እየገፋ ሱክሱክ እያለ ሮጲላ ለመሳፈር ሱክሱክ እያለ የሚሄድ ሰው አያለሁ። መጀመሪያ ላይ ይሄን ሰው የት ነው የማውቀው ብዬ የምወዛገብ ይመስለኛል። ወዳያው ግን አባ ሜንጫው ሃጂ ጃዋር መሀመድ መሆኑን አውቅና ላናግረው አላናግረው እልና ከውሳኔ ሳልደርስ ሆሆይ ኋላ ደግሞ በሰው ሀገር በሜንጫ ካልኩህ ብሎ በሰው ሀገር ቀውጢ ፈጥሮብኝ መንግሥታችን ተነካ ብለው ከሚኒሱሉልታ፣ ከሚኒሱታሱታ ሁላ ግርር ብለው መጥተው ቢከቡኝስ በማለት ማነገሩን ትቼ በዓይን መከተሉን ተያያዝኩት።
"…ጃዋር ሄደ ሄደና አውሮጵላኑ ጋር እንደደረሰ አንዳች የሰማይ ስባሪ የሚያክሉ የአማሪካ የፀጥታ ኃይሎች ያስቆሙታል። እኔም ራቅ ያለ ስፍራ ላይ ስለቆምኩ የሚነጋገሩት አይሰማኝም። መጀመሪያ ግን አድናቂህ ነን እባህን ፎቶ እንነሳ የሚሉት ነበር የመሰለኝ። ቆይቶ ግን ቀጥል ብለው ወደ ጠቋቁር መኪና እየመሩ ወንበዴ፣ ሌባ፣ አሸባሪ እንደሚይዙት አይነት ይዘውት ሲሄዱ አያለሁ። ወደ አመስተርዳም የሚሄደውም ሮጲላ ጠብቆት፣ ጠብቆት ተነሥቶ ወደ ሆላንድ ሲበር ብንን ብዬ ተነሳሁ።
"…አሁን ይሄ ከአሩሲ ኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋ ጋር ምን ያገናኘዋል? …እንዴት እንደ ደነገጥኩ አትጠይቁኝ። ክው ነው ያልኩት። ከሚኒሶታ ሶማሌዎች ጋር የሚያገናኘው ነገር ያለም አይመስለኝም። ብቻ ሕልም መሆኑን በግድ ነው ራሴን ያሳመንኩት።
• ሁለተኛው ጥያቄ ነው?
"…በጎጃም የአርበኛ ዘመነ ካሤ የግል ጠባቂው እንደሆነ የማውቀው ሰው በፌስ ቡክ ገፁ ጥቁር የኀዘን መጋረጃ ያለምን መግለጫ ለጥፎ በማየቴ ምክንያት በጎጃም የደረሰ አደጋ አለ እንዴ? ለማለት ነበር። ግሩም ምሳሌም በሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ማኅተም የተጻፈ ከድሮን ተጠንቀቁ የሚል መልእክት በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ስም አውጥቶ አይቻለሁ።
"…ደግሜ ደጋግሜ እናገራለሁ። በጎጃም ያላችሁ ፋኖዎች ግን በዚህ በበጋ ያውም በጠራራ ፀሐይ እነ አስረስ መዓረይን፣ እነ ጥላሁን አበጀን፣ እነ ማርሸትን አምናችሁ በየአደባባዩ ላያዋጉአችሁ ምረቃ ምንትስዬ እያሉ እንዳያስፈጇችሁ ጥንቃቄ አድርጉ። ተናግሬአለሁ። ባንዳ የፋኖ መሪዎች እንደሆነ ድሮንም፣ ጥይትም አይነካቸውም። በጥቅሴ ሲያስፈጇችሁ፣ ሲያዘርፏችሁ፣ ሲዘርፏችሁም ከርመው መጨረሻ ላይ ከጫካ ሲወጡ ቢሊየነር ሆነው ነው የሚወጡት። ሥልጣን ሁሉ ነው የሚያገኙት። እናም ተጠንቀቁ። ምክሬን ስሙ። ወዳጆቼ እየተፋለሙ በውጊያ መሞት ጀግንነት ነው። እንዲያው ዝም ብሎ ለሾው ሲባል አደባባይ ተሰብስቦ በጅምላ በአቢይ አሕመድ ድሮን መጨፍጨፍ እንዝህላልነት ነው።
"…በጎጃም ያን የመሰለ የጀግና ጀግና ወንድ የአባቱ የበላይ ዘለቀ ምትክ አንበሳ የሆነ የፋኖ ሠራዊት የዋንኬ በግ የመሰሉ ሾተላዮች እየመሩት ነው አሳርደው የጨረሱት። ያውም የጎጃም ፋኖ የሚሰለጥነው፣ የሚመረቀውም ሞንታርቦ እያጮኸ፣ ለድሮኗ እይታ ነጭ ቲሸርት እና ቀይ ቦኔት ደፍቶ ነው ለጥ ያለ ሜዳ ላይ ተመቻችቶ የሚጠብቀው። ወታደር ጭቃ ተቀብቶ፣ ቅጠል ለብሶ፣ ከየትኛውም የእይታ መነፅር ርቆ ነው የሚሰለጥነው። በጎጃም ግን ይሄ አይታሰብም። ጭራሽ በቀጥታ ሁላ ነው በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ፣ በቴሌግራም የሚያስተላልፉት። እባካችሁ ተጠንቀቁ።
"…እነ አስረስ እንደሁ በቅርቡ እጅ ይሰጣሉ። የአፋሕድ እና የአፋብኃን የንግግር ውጤት ነው የሚጠብቁት። ዝርዝሩን ጊዜው ሲደርስ በሰፊው እመጣበታለሁ። እናም የጎጃም ፋኖዎች እባካችሁ ተጠንቀቁ። የአስረስ መዓረይ ቲሸርት፣ የአርበኛ ዘመነ ፎቶ ያለበት ነጭ ቲሸርት ለብሳችሁ ለድሮን አመቻችተው ሲሰጧችሁ እሺ አትበሉ። ማስረሻ ሰጤ፣ አስረስ መዓረይ፣ ማርሸት ፀሐዩ፣ አረጋ ከበደ፣ ተመስገን ጥሩነህ ቤተሰብ ናቸው። ጌታቸው ረዳ አቢይን እንደዚያ ሞልጮ፣ ሰድቦ በመጨረሻ እኮ አማካሪ ነው የሆነው። እና አስረስ መዓረይ አቢይን ሲሰድበው ስላያችሁ ሚንስትርነት የሚከለክለው ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል። ጥንቃቄ።
"…የጎጃም ፋኖ ሪፎርም ያስፈልገዋል። በባለሙያ ይመራ። ጦርነት በወታደሮች እንጂ በጠበቆች እና በጋዜጠኞች፣ በአውርቶ አደሮች አይመራም። ጦርነት በካድሬ፣ በቤተሰብ አይመራም። ጦርነት በሆቴል፣ በካፌ ባለቤቶች፣ በአውቶቡስ ተራ ጫኝና አውራጆች አይመራም። ጦርነት በአክቲቪስቶች ብዛት አይመራም። ማርያምን አይመራም። ይመርራል ግን እውነቱ ይሄው ነው። ዋጡት።
• ይህቺን ለማለት ነው የመጣሁት።
00:28
Відео недоступнеДивитись в Telegram
• ጎበዝ… አዳኖይ ተፈታ እንዴ…?
"…እናንት የአውቶቡሷ ኢትዮጵያ ተሳፋሪ መንገደኞች ከዛሬ ጀምሮ ልታርሙት የሚገባችሁን ነገር የተከበሩት የአውቶቡሷ ሹፌር በዚህ መልኩ እያሳሰቧችሁም እያስጠነቀቋችሁም ነው። ልብ ብላችሁ በፅሞና ስሙት።
"…እናም በሹፌሩ መልእክት መሠረት የነዳጅ ዋጋው ጨመረ፣ ከሥራ ተባረርኩ፣ ግብር በዛብኝ። መኖር አቃተኝ፣ ትራንስፖርት ተወደደ፣ ሸቀጣ ሸቀጥ ጨመረ፣ የመብራት፣ የውኃ ቆጣሪው ናላዬን አዞረው፣ ምን ልሁን፣ ደኸየው፣ አጣሁ ነጣሁ። ታገትኩ፣ በመዋጮ ተበዘበዝኩ፣ ትራፊኩ፣ ፖሊሱ፣ ሚሊሻው ግጦ ጨረሰኝ፣ እንቁላል 25 ብር፣ እንጀራ 40 ብር፣ ዳቦው ውስጡምን ቀፎ ሆነብኝ ኧረ ኡኡኡ፣ ልጆቼን ምን ላብላ? የቤት ኪራይ ተቆለለብኝ ምናምን አትበሉ። ኔጌቲቭ ኢነርጂ ወደ ራሳችሁ አትሳቡ፣ አትጎትቱ። የምትደኸዩት በእኔ በሹፌሩ ምክንያት አይደለም። የምትደኸዩት፣ ዶላር የሚጨምረው፣ ኑሮ የሚንረው ችግር ስለምታወሩ ነው እየላችሁ ነው።
"…ፓስተር ምህረት ደበበ፣ ዳዊት ድሪምስ፣ ማንያዘዋል እሸቱ፣ አዶናይ እግዚአብሔር ይይላችሁ። ኔጌቲቭ ኢነርጂ፣ ፖዘቲቭ ኢነርጂ ብላ ብላ እያላችሁ ሰውዬውን የሌለ ፍልስፍና በምክር መልክ ሞልታችሁት ይኸው ጨልሎ አጨለለን። ሌላ ምንም አልልም የእጃችሁን ይስጣችሁ እያላችሁ ፀጉራችሁን ብትነጩ፣ ብትፈርጡ ወፍ የለም።
• በቃ ኑሮ ከበደኝ አትበሉ። ሃላስ…!
3.33 MB
01:54

6.31 MB
01:54
Відео недоступнеДивитись в Telegram
• የባሱን ሹፌር አድምጠን እንመለስ…
• ተማሪዎች…!
"…በዚህ ተንቀሳቃሽ ፊልም ላይ የባስ ሹፌሩን ዲስኩር ደጋግማችሁ በመስማት የዲስኩሩን ሰምና ወርቅ በማውጣት ከዲስኩሩ የተረዳችሁትን ሓሳብ በጥንቃቄ መርምራችሁ የራሳችሁን ግምት በአስተያየት መስጫ ሳጥኑ ውስጥ አስቀምጡ።
• ለኢትዮጵያ ስለተከፈተው የሰማይ በርና መስኮቶች በሮች ዓይነት አናጢዎች አስተያየት ብትሰጡ መልካም ነው።
• የላዳና የባስ ሹፌሮች፣ መካኒኮች፣ ተጠቃሚዎች፣ ደንበኞች በሙሉ ከደስኳሪው ዲስኩር የቀረ፣ የጎደለ፣ የተዘለለ ሓሳብ አለ ብላችሁ መጨመር፣ አይ ኤጭ አሁንስ አበዛው ብላችሁ የምትቀንሱት ሓሳብ ካለ በጨዋ ደንብ ሓሳባችሁን በአስተያየት መስጫ ሰንዱቁ ውስጥ ማስቀመጥ ትችላላችሁ።
• የባሱ ሹፌር ግን በጅምላ…
• ማስጠንቀቂያ ‼
"…ለዛሬ በዚህ ባለ ሕልም ዕልም ፖስት ላይ ዘመዴ ነዳጅ ጨመረ፣ የትራፊክ፣ የቀበሌ፣ ወዘተ ቅጣት በዛብን፣ ሸቀጥ ተወደደ፣ ከሥራ ተባረርን፣ ከሥራ ተቀነስን፣ መኖር አልቻልንም፣ የቤት ኪራይ ጨመረ፣ ውኃ የለችም፣ የመብራት ክፍያ ናረ፣ ግብር ናላችንን አዞረው፣ ሸቀጥ ጨመረ፣ እገታ በዛብን ወዘተረፈ የሚሉ አስተያየቶችን የማናስተናግድ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን።
• ቢቻላችሁ የተከፈተውን የሰማይ መስኮትና በር እያያችሁ ሓሳባችሁን ለመስጠት ሞክሩ።
6.31 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"…አሄሄ ወዴት ወዴት…? እኮ ወዴት…? "…የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም። ሉቃ 8፥17
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
• የትኛው ነው አሳሳቢ፣ አስጨናቂ ጉዳይ…?
"…በአንድ ጊዜ 129 ብር የገባው የነዳጅ ጉዳይ ነው የሚያስጨንቅህ፣ የሚያሳስብህ፣ የሚያስለቅስህ፣ የሚያስተክዝህ፣ እንቅልፍ የሚነሳህ ወይስ የአንድ መረን የለቀቀ፣ ጋለሞታ፣ ባህል፣ እምነት፣ ግብረ ገብነትን የሚያጠፋ ቲክቶከር መታሰር…?
"…የአዶናይ እናት ታልቅስ፣ ታንባ፣ እሪሪ ትበል ምክንያቱም ዘጠኝ ወር አርግዛ፣ አምጣ የወለደችው ልጇ ስለሆነ። እሷ ብታለቅስ ደንብ ነው፣ ተፈጥሮአዊም ነው። የሚገርመው የኩታራው፣ የፈላዎቹ ፍንዳታ ወጠጤዎቹ መነፋረቅ ነው። አባት እናትዋ ወር እስከወር መድረስ አቅቷቸው በጭንቀት ሊፈነዱ ነው አለሌዋ ፍንዳታ ቲክቶከሩ ታሰረ ብላ እናት አባቷ ቢሞቱ የማታፈሰውን እንባ ታንዠቀዥቀዋለች። ጉድ እኮ ነው።
"…አገዛዙ ያሰራቸውን ነገ ይፈታቸዋል። ለታሰሩት ቲክቶከሮች ደረት መድቃትህን ትተህ ስላጎበጠህ ኑሮ ማሰብ ጀምር። ነፍሰ በላውን የትግሬ ነፃ አውጪ መስራች አቦይ ስብሃትን በነፃ ፈትቶ የለቀቀው ኦሮሙማ ቲክቶከሮቹን ምን ያደርጋቸዋል ብለህ ነው የምታላዝነው። ፍንዳታ ሴቶቹስ እሺ ያልቅሱ ደንባቸው ነው። በድራማው፣ በፊልሙ ሲነፋረቁ የሚውሉ ናቸውና አይፈረድባቸውም። አንተ ምንአባህ ሆነህ ነው በል?
"…ነዳጁ በመላ ኢትዮጵያ ነው ወይ የተጨመረው? ትግራይ አንድ ሊትር ስንት ነው? ነዳጅስ በትግራይ አለ? ጎንደር፣ ወሎ ጎጃም፣ አፋር ወለጋ፣ ሶማሌ፣ ሀረር ድሬደዋ፣ ደቡብ፣ ቤኒሻንጉል ጋምቤላ ነዳጅ ዋጋው ስንት ነው?
"…ነዳጁ ሲጨምር የቤት ኪራዩ፣ ትራንስፖርቱ ጨመረ ወይስ ቀነሰ? ምግብ እና ሸቀጣ ሸቀጡስ ጨመረ ቀነሰ? የመብራት እና ውኃው ቀነሰ ጨመረ? እንዴት እያደረጋችሁ ነው? እዚህ ላይ ብታወጉ አይሻላችሁም? ጃኒ ጂኒ አትበልብኝ ጂኒ ይስፈርብህና።
"…ዘመዴ ኦዳ አዋርድ ላይ የነበሩትም እኮ አለባበሳቸው ያስጠላል። ለምን ዝም ተባሉ ይለኛል እንዴ? ድፍረትህ እኮ አይጣል ነው። እና በሻቱን ይክሰስልህ? ኦሮሞ ኦሮሞን ይክሰስልህ? ጋምቤላ፣ ስልጤ፣ ትግሬ ዐማራው እያለ ይክሰስልህ? ኧረ አቅምህን ዕወቅ አባቴ። ተንቀሳቀስ። እነሱ የ150 ዓመት እድፍ በትግላችን አጠራን፣ በደማችን አጠራን እያሉ እየዘመሩ እኮ ነው ያደጉት። አንተ ተዘፍዝፈህ እኚኝ ትልብኛለህ። አሁን ማን ይሙት የጩሉሌ ፓርቲ ፕሬዘዳንት ማሜን ኦሮሙማው ሊያስረው መስሎህ ነው? 😂
"…ቆይ በነገራችን ታች…
• እራት በልተሃል ግን…?
• ምሳስ በልተሃል?
• ነገ ቁርስ ትበላለህ?
• አፋሕድ እጅ ሰጠ፣ ዐማራ ባንክ ተዘረፈ፣ እስክንድር እጅ ሊሰጥ ነው፣ እና አንተ ምን አገባህ? ምንአገባህ ነው የምልህ? ይልቅ ዘይት ስንት ገባ? መቶ ብር ምን ይገዛልሃል? እሱ ላይ ተወያይ፣ ለመፍትሄው ታገል። ታሰረ፣ ተፈታ አትበልብኝ። የታሰረው ይፈታል። የማይፈታው የተጫነብህ አዚም ነው።
• የምለው ይገባሃል ግን…?
03:15
Відео недоступнеДивитись в Telegram
"…በዚህ አነጋገሬስ ትስማማላችሁ…? …ተቃዊሚ ካለ ይቅረብ…? ዋሸሁ እንዴ…?
28.50 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
• ጀመርኩት…?
"…ብልጽግና ነዳጅ ሊጨምር፣ ታክስና ግብር ሊጨምር፣ ኑሮ ሊያንር፣ ሰዉን ሊያጦዝ ሲፈልግ አስቀድሞ አጀንዳ ይቀርጻል። አጀንዳው ሕዝቡ አገዛዙ ባቀደው ነገር ላይ ትኩረት እንዳያደርግና እሱ በፈጠረው አጀንዳ ላይ ሰፍሮ እዚያ ሲራኮት ውሎ እንዲድር ለማድረግ ነው።
"…የኦሮሞ ብልጽግና አጀንዳ ሲፈጥር ሁለቴ አያስብም። መጀመሪያ መርጦ መርጦ በሰንዱቁ ያስቀምጥ ይከዝን እና ከዚያ ባስፈለገው ግዜ መዥረጥ በማድረግ ሻሞ ብሎ በአፎቹ፣ በምላሶቹ፣ በበቀቀኖቹ በኩል ይበትነዋል ከዚያ አዳሜና ሄዋኔ ኦሮሙማው ሻሞ ብሎ የበተነለትን አጀንዳ ተጋፍቶ ተራክቶ ሲለቃቅም ይገኛል።
"…ብልፅግና ሕዝብን እንደ ቁጫጭ ነው የሚቆጥረው። እንደ ጉንዳን ነው የሚመለከተው። ሕዝቡን ይንቀዋል። እንደ እንስሳ ነው የሚያየው። አእምሮ እንደ ጎደለው እንስሳ። ከነ ሲጠራው እንኳ ሾርት ሚሞሪያም ሕዝብ ነው ብሎ እየሰደበ፣ እያዋረደ የሚጠራው። እንደ ውሻ ደረቅ አጥንት በአጀንዳ መልክ ይወረውርለታል ሕዝቤ ለሃጩን እያዝረበረበ ኡኡ፣ ውዉዉ ነው። እንደ ጉንዳን ቁራጭ ስጋ፣ እንደ አይጥ ቅቤ የነካው አጀንዳ ይወረውለታል አዳሜና ሔዋኔ ማነሽ ስንቄ ነጠላዬን አቀብዪኝ እያለ መትመም ነው ወደተዘጋጀው አጀንዳ። ያነዜ ሕዝቤ በተወረወረለት አጀንዳ ሲራኮት ብልፄ አምጥታ ትቆልልበታለች። ሕዝቤ ከተወረወረለት ደረቅ አጥትንት አጀንዳ ደክሞት ሲመለስ…
• ቤንዚን 1ሊትሩ 129 ብር ገብቶ ይጠብቀዋል።
• ሸቀጣ ሸቀጥ ሰማይ ተቆልሎ ይጠብቀዋለ።
• ትራንስፖር እሳት ሆኖ ይጠብቀዋል።
• ሕክምና በሽታ ላይ ጥሎ ይጠብቀዋል።
• የትምህርት ቤት ወጪ ፍዝዝ፣ አድርጎ ይጠብቀዋል።
• መብራት እና ውኃ ቡዝዝ አድርጎ ይጠብቀዋል።
በላዩ ላይ…
• የኮቴ፣ መዋጮ፣ እርዳታ፣ የልማት፣ የሚኒሻ፣ የኮሬ ነጌኛ፣ የኦሮሚያ ዜግነት፣ የቱቦ ማስከፈቻ፣ የመንገድ መብራት፣ የደንቦች ዩኒፎርም ማሰፊያ፣ ከጅቡቲ እስ አዲስ አበባ 37 ኬላ ላይ የኮቴ፣ የትራፊክ ቅጣት፣ ስብሰባ የቀረ ቅጣት፣ የድጋፍ ሰልፍ የቀረ ቅጣት ወዘተረፈ አምጥቶ መተንፈሻ ያሳጣዋል። ሕዝቤም ኧረ በዛ፣ ኡኡ ብሎ መጮህ ሲጀምር…
"…በናትናኤል መኮንን፣ በጉርሻ ፔጅ፣ በጌጡ ተመስገን ፔጅ በኩል ሌላ አጀንዳ ይዞ ከች ይላል። በናቲ በኩል ቀይ ባህር ልንዘምት ነው። እነ ደብረ ጽዮን ጓ አሉ። ትግሬ ሊያምጽ ነው ብላ ብላ፣ በጉርሻ ፔጅ በኩል ሚስትየው ቧሏን ብልቱን ቆረጠችው፣ ቆንጅዬው ልጅ ጠፍቷል፣ ሕጻኗ ታረደች፣ በጌጡ በኩል የ95 ዓመቱ ሽማግሌ የ8 ዓመቷን ሕፃን ደፈሩ ብላ ብላ ብሎ አጀንዳ ያመጣል። ሕዝቤም አንደዜ አእምሮው ሾርት ነው ተብሏልና መከራውን ረስቶ መራኮት ይጀምራል።
"…ሲብስ ደግሞ ማስረሻ ሰጤን ከላከበት ተቀብሎ ፋኖ ተደራደረ ይላል ሕዝቤ ይራኮታል። የማስረሻ ሲነቃ፣ አንገቱን ሲያስደፋው ደግሞ በአያሌው መንበር በኩል ጎጃሜን መጎንተል፣ ማበሳጨት ይጀምራል። ሕዝቤ እየዬ ሲል እሱ ሥራውን ይሠራል።
"…ዋነኛው ወሴ፣ ዋነኛው ወንድ የሚተሻሸው ጠቅላዩ እያለ የእነ ማስረሻ አጀንዳ ሲፈርስ፣ የእነ አያሌው ሲከሽፍ ከመሬት ብድግ ብሎ ጋጠወጥ የትግሬ አክቲቪስቶችን በማሰር የሞራል ሰባኪ ሆኖ ይከሰታል። በዚያው ሰዓት ግን ትግሬዎቹ በታሰሩበት ወንጀል ኦሮሞዎቹ ኦዳ ሽልማት ብለው የወንድ ለወንድ ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያበረታታ ማስታወቂያ፣ ፋሽን ሾው ሲያሳዩ ይታያሉ። ድንቄም ኡኡቴ አልቀረበትም እኮ።
"…ቤንዚን ጨምሯል። ደሞዝ እዚያው ነው። ሸቀጣ ሸቀጥ ጨምሯል። የቤት ኪራይ ጨምሯል። ትራንስፖርት በድብቅ ጨምሯል፣ ብልፄ ደግሞ ወንድ የሆነ ይጨምር እያለች ነው። ሕዝቡ አብዛኛው በሆዱ ያጉረመርማል ካሜራ ፊት እና በየስብሰባ አዳራሹ ግን ተአምር እንደወረደለት ይበጠረቃል።
• ጎረቤት ሀገር ኬንያ መንግሥታቸው ጥቂት ሳንቲም ልጨምር ነኝ ብሎ በተናገረ በማግሥቱ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ፣ ፓርላማ ውን ሰብሮ ገብቶ ሞተን ነው ቆመን ብሎ በመቃወም መንግሥታቸው እሺ ይቅርታ ከቃላችሁ አልወጣም በማለት አቁሞታል። በዚህ አያበቃም፣ አልረካንም በማለቱም ካቢኔው እንዲበተን እንፈልጋለን በማለቱ ካቢኔውም ተበትኗል። ይሄ ጎረቤት ሀገር ኬንያ ነው።
• እስቲ በዚህ ዙሪያ እንወያይ። በቤንዚን ጭማሪው ዙሪያ እንወያይ። ቀጥሎ ምን የሚከሰት ይመስላችኋል? ሌላ አጀንዳ ሳይወረውርላችሁ በፊት እስቲ በዚህ ዙሪያ ለሰከንድም ቢሆን እንወያይ።
• ኑሮ እንዴት ይዟችኋል…?
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መልካም…
"…እኔ የምለው በነገራችን ታች… ከምስጋናው በኋላ አሁን ደግሞ በዚህ ሰዓት የብልጽግናው አገዛዝ ጨርሶ በፍጹም እንዲነሳበት የማይፈልገውን አጀንዳ አንስተን እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በጨዋ ደንብ በግልጽ መወያየት ብንጀምር ምን ይመስላችኋል…? ኣ…?
• ዘመዴ ጀምረው፣ እንጀምር ብቻ በሉኝ።