Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
Відкрити в Telegram
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Показати більше2025 рік у цифрах

228 775
Підписники
-18824 години
-1 0407 днів
-4 59130 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መልካም…
"…ለዛሬ የሚቀርብ ከሊቃውንተ ኢትዮጵያ ጋር በነበረን ሳምንታዊ ውይይት ወቅት ሊቃውንቱ "…የአምስት መቶ ዓመት የጥፋት ፍጻሜ የመጨረሻው ምዕራፍ ❌⛔️ እና የአምስት መቶ ዓመት የውድቀት ትንሣኤ የመጀመሪያው ምእራፍ ግብግብ ✝ ✅" በሚል ርእስ ደም ግፊት፣ ልብድካም የሚያስነሣ፣ የሚያበሳጭ፣ የሚያስቆጭ፣ ትንፋሽ የሚያሳጥር አስደማሚ ትንተናና ገለጻ እያደረጉ ለዚህ ጉባኤ ተመርጠን ከተለያዩ ክፍለዓለማት የተሰባሰብን ኢትዮጵያውያንን ሲያስደምሙን ነበር ያመሹት። ተስፋ ባይኖረው ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ እንድተወው የሚያስወስነኝ ነበር ውይይቱ። ከምር ዕድለኛ ነኝ።
"…ውይይቱን ከድምፅ ወደ ጽሑፍ ቀይሬዋለሁ። አንዳንዱ ቃላት ስለከበደኝ፣ ስለጠጠረብኝ መልሼ ሊቃውንቱ ያዩት ዘንድ ልኬላቸዋለሁ። በእርግጠኝነት ዛሬ ማታ አረጋግጠው መልሰው ይልኩልኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። እናም እንደተለመደው ነገ ረቡዕ ከምስጋና በኋላ ሁላችሁም ታነቡት ዘንድ እለጥፍላችኋለሁ። የነገ ሰው ይበለን። ሊቃውንቱን ያብዛልን። ረጅም ዕድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን። ነጭ ነጯን ብቻ። ሃቅ ሃቋን።
"…እስከዚያው እስከ ነገ ማለት ነው ዛሬ ምሽቱን በሙሉ አጫጭር የሆኑ ርእሶችን እያነሣን በቴሌግራም ገጻችን ስንውያይ እናመሻለን።
• አላችሁ አይደል…?
"…እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ ማቴ 24፥15
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
ከወደ ዋሽንግተን የምሥራች አለ…
"…በብፁዕ አቡነ ሉቃስየተመራ እና መልአከ ጥበባት አባ ገብርኤል (ዶር)ን፣ መጋቤ ጥበብ ቀሲስ ሳሙኤል ግዛው (ኢትዮ ቤተሰብ)ን፣ እና ዲያቆን ፋሲካው ካሳውን ያካተተ አንድ ጠንካራ አይሰበሬ ባለማዕተብ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ልዑክ በዛሬው ዕለት በሀገረ አሜሪካ በዋሽንግተን ከተማ በአሜሪካ የሚኖሩ፣ እዚያው ተወልደው ባደጉ፣ ዜግነትም ባላቸው ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆች ያላሰለሰ ተጋድሎና ጥረት በኋላ ከአሜሪካ መንግሥት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግሥቱ ባለሥልጣናት ጋር ታሪካዊ የሆነ የመጀመሪያ ደረጃ ፍሬያማና ውጤታማ ውይይት መደረጉን የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።
"…የአሩሲ ኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋ በምስል፣ በቪድዮ ጭምር እየዘገነናቸውም ቢሆን እንዲታይ ተደርጓል። በትግሬ፣ ዐማራና ኦሮሞ፣ በሸኔና በኦነግ፣ በፋኖና በቲዲኤፍ ተሸፍኖ፣ ተከድኖ፣ በድብቅ እየተጨፈጨፉ ስለሚገኙት ኦርቶዶክሳውያን ሰዓታትን የፈጀ ውይይት ተደርጓል። መሪዎቹ የኦሮሞ እስላሞች፣ ገዳዮቹም የኦሮሞ እስላሞች፣ ዳኞች፣ ፖሊሶች፣ ሚሊሻና ሊቃነ መናብርቱ ሳይቀሩ የኦሮሞ እስላሞች በሆኑበት በአሩሲ ክርስቲያኖች ያለ ከልካይ በጅምላ እየተጨፈጨፉ መሆናቸውን የሚያሳይ ዘግናኝ የምሥልና የቪዲዮ ማስረጃም ቀርቧል።
"…ብፁዕ አቡነ ሉቃስ አወያዮቹን እና ባለ ሥልጣናቱን አስፈቅደው፣ ቪድዮው፣ ፎቶው፣ ዘግናኙ መረጃ ይታይልን በማለታቸው በዚያው በአዳራሹ ተከፍቶ መታየቱንና ተመልካቾቹም ማየት፣ መመልከት እስኪቸገሩ ድረስ መደንገጣቸውም ተሰምቷል። ፕሬዘዳንት ትራምፕ ጋር በመቅረብ የናይጄሪያ ክርስቲያኖች በቦኮ ሀራም እንዴት እንደሚጨፈጨፉ በማሳየት የአሜሪካ መንግሥት አቋም እንዲይዝ ያደረጉም ናይጄሪያዊ እህት ይህ የእኛም የአሩሲ ጭፍጨፋ በአሜሪካ መንግሥት እንዲታይ ግፊት ማድረጋቸውና የዛሬው አሩሲ የተዋሕዶ ልጆች ጭፍጨፋ በአሜሪካ መንግሥት ዓይን ሞገስ አግኝቶ እህ ብሎ እንዲያዳምጥ በማስደረጉ በኩል የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዙም ተነግሯል።
"…ይሄም በዚሁ አያበቃም። ነገም እንድትመጡ ተብለው ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ለነገም ወደ አሜሪካ መንግሥት ቢሮዎች መጠራታቸውን የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል። አጀንዳዬን አልቀይርም ያሉ፣ የአሩሲ ኦርቶዶክሳውያንን ጉዳይ ያለመታከት ይዘው ችክ ብለው ሲወተውቱ የከረሙት እነ ዲያቆን ፋሲካው፣ እነ ዲያቆን ዘአማኑኤል፣ እነ ቀሲስ ሳሙኤል፣ እነ አባ ገብርኤልና ብፁዕ አቡነ ሉቃስም የድካማቸውን ውጤት እያየሁ በመሆናቸው እግዚአብሔር ይመስገን። ዝርዝር ጉዳዩን በዘመድ ቴሌቭዥን፣ በቲክቶክ እና በኢትዮ ቤተሰብ ጭምር ልዑካኑን ይዤ በመቅረብ በሰፊው እመለስበታለሁ።
"…እስከዚያው ድረስ ግን የአሩሲ ኦርቶዶክሳውያን እግዚአብሔርን በመያዝ አረመኔ፣ ጨካኝ፣ አራጁን የኦሮሞ የወሃቢያ እስላም ገዳይን በመመከት፣ አራጅን በማነከት የወንድነት፣ የጀግንነት ሥራ እየሠራችሁ በጽናት፣ በተጋድሎ ትቆዩ ዘንድ ትመከራላችሁ።
• ደኅና እደሩልኝ።
• ይሄ ነገር በፈረንሳይኛ ይሆን በስፓንሽኛ…? ETHIOPIE ???? …መቸም የተባበሩት መንግሥታትን ያህል ግዙፍ ተቋም በዚህ መጠን ፊደል ይስታል ብዬም አላምንም። እዚያው በተመድ አዳራሽ ጠረጴዛ ላይ ETHIOPIA ተብሎ የተጻፈም ስላየሁ ነው።
• ETHIOPIE ግን በምንኛ ነው?
👍 403❤ 105🤔 55😡 17🙏 15💔 11🕊 6✍ 4🔥 4🤯 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
• ስለዚህ… ማርበርግ የሚባለው አደገኛ ቫይረስ በደቡብ ኢትዮጵያ ተከስቷል፣ ሀኪሞችን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ ዜጎችን፣ በደቡብ ጂንካ፣ በአዋሳ፣ በምሥራቅ አሩሲና በአዲስ አበባ ቅዱስ ጳውሎስ ደም እያስተፋ ዜጎችን ገድሏል። በጂንካ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፣ ትራንስፖርትም ተቋርጧል ብላብላ ተብሎ የተነገረን ሁሉ ውሸት፣ ሐሰት፣ ቀደዳ፣ የብላኔ ወሬ ነው ማለት ነው…?
"…አልገብቶኝም…! እኔ ደግሞ ተጨንቄ ልቤ ውልቅ ማለቱ 😂😂😂 … ነገ ቫይረሱ ተስፋፋ ብትለኝ አልሰማህም።
"…ቫይረሱ ትኩረት አልተሰጠውም ብላችሁ ዘመዴ እባክህ በቴሌቭዥን ጊዜ ሰጥተህ ሕዝቡ እንዲጠነቀቅ አድርግ ብላችሁ የሸወዳችሁኝ፣ የቅርብ ሰዎቼ ወዳጆቼ የምላችሁ ሃኪሞች ሠራችሁልኝ። አጃጃላችሁኝ። እናንተን አምኜ ስዘበዝብ መክረሜ ቆጨኝ።
"…በሌለ ቫይረስ ስለምን ክትባት ነው የምታወራው። በል ራስህን ቻል። ቤር ቤረሰብ አትረብሹ። ዘና ፈታ ይበሉበት። ነገርኩህ ነገ መጥተህ ቫይረሱ፣ ክትባቱ ብትል አልሰማህም።
"…አሁንማ እንኳ ውሸት መሆኑን እያወቅኩ። ከምር ሸወዱኝ እኮ ፍሬንዶቼ። እኔ እዚ በጭንቀት ልፈነዳ ነው ደቡብ ሆዬ ሆሳዕና ላይ ደመራ፣ ችቦ ሆኖ ቤር ቤረሰብ በዓልን እየተሻሸ ያከብርልኛል። ያውም ኢትዮጵያ በዘር፣ በሃይማኖት የተከፋፈለችበትን ቀን፣ የገዳይ ሾተላዩን፣ ፀረ ዐማራው መርዞ ለትግሬ ሴት ጭን ሲል ነገዱን ለሞት፣ ለእልቂት አሳልፎ የሰጠውን፣ ከጀርባው ሆነው በመዘወር ኢትዮጵያውያን በሙሉ ዐማራን ጨቋኝ ብለው ባገኙበት እንዲቀጠቅጡት ያደረገውን ማርቡርግ ቫይረስ የሆነውን የዋለልኝ መኮንንን ሙት ዓመት እየጨፈረ ያከብርልኛል።
• ዝም ብለህ ተከተብ፣ ቫይረስ ምናምንትስዬ እንዳትለኝ።
❤ 558👍 235🙏 48🤔 36✍ 8😱 6🔥 4🤯 4👌 4🏆 3😡 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"…ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ፡— የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል። 2ኛ ጴጥ 2፥22
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
01:53
Відео недоступнеДивитись в Telegram
"…ሾተላዮች ቶሎ ቢወጡ ሸጋ ነበር…
"…ዛሬ ጠዋት ትንሿ አፍሪካዊት ሀገር ቤኒንም ወጉ ደርሷት መፈንቅለ መንግሥት ማድረጓ ተሰምቷል። ደስ ሲል። ተራብን፣ ሥራ አጣን የሚሉ ዜጎች በፌስ ቡክ፣ በቲክቶክ ማለቃቀስ መጀመራቸውን ያየው ወታደሩ ክፍል አገዛዙን ገልብጦት አደረ። ይኸው መፈንቅለ መንግሥት አድራጊው ደርግ በኢቲቪአቸው መግለጫ እየሰጠ ነው። እስከአሁን ፕሬዝዳንቱ ያለበት አልታወቀምም ተብሏል።
"…ወደ እኛ ሀገር ስንመጣ ቲክቶከሩ ሁሉ በትግሬና በኦሮሞ ቲክቶከሮች የተሞላ ነው። ስለ ጭን፣ ስለ ባት፣ ስለ ጡት፣ ስለዳሌ፣ ስለ ወሲብ፣ ስለ ዱቄት መቀባት፣ ስለ ግልሙትና የሚያነቁ፣ የሚያበረታቱ ወሴ ሉጢዎች የተሞላ ስለሆነ እስከ አሁን የሕዝብን ብሶት፣ ችግር የሚያጋራ ቲክቶከር በለው ዩቲዩበር ፌስቡከር አልነበረም።
"…አሁን ግን በደል ችግሩ ገንፍሉ ስለወጣ በየፌስቡክና በየቲክቶኩ የሚለቀቁ አንዳንድ ቪዲዮዎች የሚያሳዩት ተራብን፣ መሥራት አልቻልንም፣ መኖር አልቻልንም፣ መረረን በሚሉ በአንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ዋይታ ከተሞሉ ሰነባብተዋል። ቆነጃጅት፣ ሸመረን ወጣቶች፣ ነጋዴዎች፣ መካከለኛ ገቢ የነበራቸው መኪና የሚነዱ ሴቶች፣ ታክሲ ነጂው ሹፌር፣ ባለሱቁ ነጋዴ የሆኖ ናቸው እየወጡ ራበን የምንበላው አጣን፣ ልጆቻችን ተራቡ እያሉ ቪዲዮ መልቀቅ የጀመሩት። ፈረንጅ middle Class የሚላቸው በኛ ሀገር ግን ያውም upper class የሚባሉት ናቸው እዬዬ እያሉ ያሉት።
"…በጅማም ሳይቀር በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የመረረው ሕዝብ በግልፅ አደባባይ ወጥቶ down down አቢዩ ማለት ጀምሯል። ሰሞኑንና ትናንት ቪዲዮዎችን እያጋሩ ነው ያሉት። በቃ፣ ቀስ በቀስ፣ ሰልፍ እየተጀመረ ነው። ወያኔ ልትወድቅ አካባቢ ያለ ነፋስ በኢትዮጵያ" እየነፈሰ ነው።
"…በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ፣ ባለቀ ሰዓት እነ አርበኛ ዘመነ ካሤ የሚፍረከረኩት። በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ በራሱ ችግር ራሱ በስብሶ ሊወድቅ ከጫፍ በደረሰ ሥርዓት የሚፍረከረኩት። 😂 በዚህ ጊዜ ነው ፈሪ ሾተላዩ ሁሉ እጅ ሊሰጥ የሚያኮበክበው። ያውም ባለቀ ሰዓት። ፈጣሪ እንክርዳዱን በጊዜ በቶሎ ከፋኖ ላይ ይንቀል። እነዚህ ተፈጭተው ተጋግረው ከስንዴው ጋር ዳቦ ሆነው ቢቀርቡ ለጤና ጠንቅ ነው የሚሆኑት። እነ እስክንድር፣ እነ አስረስ በቶሎ ወጥተው ፋኖ ጤናውን ባገኘ።
• ቤኒኖች እንኳን ደስ አላችሁ።
9.98 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
• ነጭ ነጯን ጀምረናል።
• ገባ ገባ በሉማ…!
• አላችሁ አይደል…?
👍 375❤ 113🙏 49😡 19🔥 7👌 6🏆 6✍ 4🕊 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 2:00 ሲሆን በዘመድ ቴቪ መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።
• ቲክቶክ 👉 http://tiktok.com/@zemedkun.b
• ZemedTv 👉 zemedtv.com/live.html
• በትዊተር (×) 👉 x.com/i/broadcasts/1OwxWeEmdLpGQ
• በራምብል 👉 rumble.com/v72pw5c--zemede-december-07-2025.html?e9s=src_v1_cbl%2Csrc_v1_upp_a
• በሳታላይት ቴሌቭዥን
👉 Yahsat 52.5° East
11977 H 27500 …ላይ ይከታተሉን።
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"…አንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ በዜግነት እስራኤላዊ የሀገረ እስራኤል የስለላ መሥሪያ ቤት ሰው በተደጋጋሚ ጊዜ ይደውልልኛል። የእመቤታችንን ስም እየጠራም ያወራኛል። ምንም የተለየ እና የተደበቀ አጀንዳ ስለሌለኝ በነፃነት ነው የማወራው።
• በነገራችን ታች… እኔ ዘመዴ በስልክም ብታወራኝ፣ በአካልም ብታወራኝ፣ በቴክስትም ብታወራኝ፣ በግልም፣ በኮሚቴም፣ በጉባኤም ብታወራኝ ምንም የተለየ አጀንዳ፣ የተደበቀ ነገር ስለሌለኝ የማወራህ በቴሌግራም የምጽፈውን፣ በቲክቶክና በቴሌቭዥን መርሀ ግብሬ በነጭ ነጯን የምነግርህን ነው መልሼ የምነግርህ። እንደዚያ ነው። 😁
"…እናም ይሄ ወዳጄ ይለኛል… ዘመዴ ኮሎኔል ሙሀባውን እና አቶ መስፍንን ላገናኝህና አውራቸው ይለኛል። መስፍን የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ አይደል እንዴ የላከው? ምን ይሁነኝ ብዬ ነው የማወራው እለዋለሁ። አይደለም አንድነቱ እንዴት እንደፈረሰ እኛም ለዘመዴ የምንነግረው አለን ስላሉ ነው ይለኛል። ምን ገዶኝ እለዋለሁ። ከዚያም ደወለ የእስራኤሉ ሰው።
• ሃሎ አሉኝ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀቤ እና አቶ መስፍን ከፈለኝ። ከዚያ የእኔ ነገር…
• በኋላ ነጭ ነጯን ላይ እጨርስላችኋለሁ። አሁን መስፍኔም ይኸው የተወለወለ መስታወት መስሎ፣ ተልእኮውንም ጨርሶ ወደ እናት ክፍሉ ወደ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ቢሮው ተመልሷል።
• በነገራችን ላይ ይሄ ሰው ቀላል አይምሰላችሁ። ከጌታቸው አሰፋ መመሪያ እየተቀበለ… ኬኒያ ላይ ግንቦት ሰባት እና ሻአቢያን… 😁 … አቶ ልደቱ አያሌውን ከጨዋታ ውጪ …
• በኋላ ያገናኘን…
Фото недоступнеДивитись в Telegram
• ሃሉ… ይሰማል…?
"…ዛሬ ምሽት በዘመድ ቴቪ ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር በተሰኘው መርሀ ግብራችን ጎጃም እናመሻለን። በዚያውም መራር ሃቅ እየጎመዘዘን አጣጥመን እንውጣለን።
• ይሄ አንደኛው ነው… !
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"…ሰንበታቴን ጠብቁ፥ መቅደሴንም አክብሩ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ዘሌ 19፥ 30
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
መልካም…!
"…የየነታ ይባቤ ሞት ተፈጥሮአዊ ነው ወይስ ሰው ሠራሽ? በሚል ርእስ ከሊቃውንተ ኢትዮጵያ ጋር በነበረን ውይይት ላይ የያዝኩትን ማስታወሻ ነበር ያቀረብኩላችሁ።
"…እንዳነበባችሁት ሊቃውንቱ በውይይታችን ወቅት ሰፊ እና ጥልቅ የሆነ ምልከታቸውን አስቀምጠዋል። ስለ አርበኛ ዘመነ ካሤም፣ ስለ እነ ብፁዕ አቡነ አብርሃምም፣ ስለነ ሮዳስ ወዘተረፈ የተነሣውም ሓሳብ መራር ነው ነገር ግን እንወያይበት ዘንድ ግድ ነው። አይደለም እንዴ?
"…የማኅበራዊ ሚዲያ ጥቅሙ፣ ተፈጥሮውም ለእንዲህ ያለ ውይይት፣ ሙግት፣ ክርክር የተፈጠረ ነው። ቴክኖሎጂ፣ ሳይንስ፣ ፖለቲካ፣ ስፖርት፣ ሙዚቃ፣ ፊልም፣ ሃይማኖት ጭምር በአግባቡ የሚሠሩበት ይጠቀሙበታል። እምቢኝ ያሉ ደግሞ ማኅበራዊ ሚዲያቸውን ዮኒ ማኛ፣ ሞጣ ቀራንዮ ያደርጉታል። ቀውጢ ማለት ነው።
"…የእኛ ቤት ይለያል። በጣም ይለያል። ማንም የማይሞክረው ደፈር ያለ ሓሳብ ይነሣበታል። ሲጀመር ጫጫታው ይበዛል። የሚደነግጠው፣ ደም ግፊቱ የሚጨምረው፣ ልብ ድካም የሚይዘውም የትየለሌ ነው። እየቆየ ሲሄድ ነው አሃ ለካስ ዘመዴ ልክ ነበር የሚለው ሰው የሚበዛው። እንደዚያ ነው።
"…በእኛ ቤት የትኛውም ሓሳብ ይነሣል። ተነሥቶም ሓሳቡ በጨዋ ደንብ በነፃነት ይንሸራሸራል። ታዲያ በጨዋ ደንብ ነው። አልያ ባለጌ ባለጌ የሚጫወት ይቀሰፋል።
"…ብዙ ሚልዮን አንባቢ እንዳለኝ የማውቀው እኔ አንድ ነገር በለጠፍኩ ጊዜ ጦማሩን ተከትሎ የሚጎርፍልኝ መረጃ ነው። ይሄ ነገር ይገርመኛል።
• በሉ መልካም ምሽት…? እናንተስ የኔታ የሞቱት በተፈጥሮአዊ መንገድ ነው ወይስ በሠውሠራሽ መንገድ?
13.46 MB
"…አስረስ በጎሳ አገውነቱ፣ በሃይማኖት ቅባትነቱ፣ በፖለቲካዊ ዕይታው ብአዴንነቱ፣ በአሽከርነት አሜሪካና አቢይ ይበልጡበታል። አቡነ አብርሃም በአንድ ቪዲዮ ንግግራቸው ላይ "አባቴ አሩሲ ነው ኖሮ፣ ሞቶም የተቀበረው" ያሉአትን ነገር ስናይና ከአስረስ ጋር በሥጋ የአንድ አያት ልጅ መሆናቸው ሲታይ ዐማራና ጎጃሜነት ለአስረስ ቅንጦት ነው የሚሆነው የሚሉም አሉ። የጎጃም ሕዝብ፣ የጎጃም ፋኖ፣ ውጭ ሀገር ያለህ የጎጃም ዲያስፖራ ተባብራችሁ ቢቻላችሁ ዘመነን ድረሱለት፣ ከአስረስ መንጋጋ አውጡት። ካልቻላችሁ ቁርጣችሁን አውቃችሁ ለዘመነ አልቅሱለት። የንታ ይባቤ የተቀበሩት ሞተው ነው። ዘመነ የሞተው ግን በቁሙ ነው። በቁሙ የቀበረው፣ ገንዞ የቀበረው አስረስ መዓረይ ነው። የፋኖ መሪ ሆኖ እንዳይመረጥ፣ ይሄንና ያን ተናገር እያለ ዘመነን ነጥብ አስጥሎ አርበኛ ዘመነ ካሴን በሁሉ ዘንድ እንዲናቅ ያደረገው መዓረይ ነው። ይህ ሁሉ ሆኖም ሳለ ዘመነን ምን ለጎመው? አሁን ማን ይሙት በየትኛው የጎጃም ቀጠና፣ በየትኛው የፋኖ አደረጃጃት ነው ዘመነ ተጽዕኖ ያለው? ዘመነ ሰብስቦ ያነጋገረው ፋኖ ምን ያህል ነው? እስኪ ይናገር። በጎጃም ፋኖ ውስጥ አሁን ላይ ዘመነ አለ? በላይ ዘለቀን አንቀው የገደሉት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ናቸው። ዘመነን በቁሙ የሰቀለው አስረስ መዓረይ ነው። ዘመነ መኖሩን እንጃ። ጎጃምን እየመራሁ ነው ካለ እስኪ ይውጣና ይናገር። ከአጋቹ አስረስ መዓረይ ነጻ ሆኖ መግለጫ ያውጣ። የዘመነ ደጋፊ ይሆናል ተብሎ የተገመተ ፋኖ፣ መነኩሴ፣ ቄስ፣ መምህር፣ ሊቅ የተባለ ሁሉ በባትሪ ተፈልጎ ይመነጠራል። አስረስ ሲፈልግ ጦር ሰብቆ የመንደሩን ፋኖ ልኮ ይመነጥራቸዋል። ሲነቃበት ደግሞ መከላከያን መንገድ መርቶ ሸኝቶ ያስጨፈጭፋቸዋል። ይህን ሲሰሙ ይመርራል፣ ይጎመዝዛል ነገር ግን እውነት ነው፣ ጥሬ ሃቅ ነው። ዋጡት።
"…ኦሮሙማው ጎጃም ላይ አስረስን በማግኘቱ ያሳካው ድል አቢይ ኦሮማራ ብሎ ገዱን አለቃ አድርጎ፣ ብአዴንን አሞኝቶ፣ ዶ/ር አምባቸውንና ጀነራል አሳምነው ጽጌን እንደቀረጠፈው ያለ ነው። አሁን ከሸዋ እስክንድርን፣ ከጎንደር እነ ጌታ አስራደን፣ በጎጃም አስረስ መዓረይን ይዞ እየሠራ ነው። ጎጃም ዘመነን ለመብላት፣ ጎንደር ሀብቴ ወልዴንና ሳሙኤል ባለድልን ለመብላት አሰፍስፏል። በሸዋ ቀደም ብሎ አርበኛ አሰግድ ተቀርጥፏል። ለኢ/ር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ እግዚአብሔር ይሁነው። የጎጃሙ ከሁሉም ይከፋል፤ ጎጃም ተጨምድዶ ተይዟል። ተመስገን ጥሩነህ፣ ቀንድ አውጣ አረጋ ከበደ፣ አስረስ መዓረይ፣ ማስረሻ ሰጤ፣ አቡነ አብርሃም በመጠቃቀስ ጎጃምን እንቅ አድርገው ይዘውታል፤ ከባድ ነው። ዘሜ በእነዚህ ተተብትቦ ነው ሕልውናውን ያጣው።
"…ስለዚህ ዘመነ ያለው አማራጭ እውነተኛ ፋኖዎችን ይዞ ሴራውን በጣጥሶ ከዐማራ ፋኖ ጋር በአንድነት ሕልውናውን ማስቀጠል ነው፤ ካለ ማለቴ ነው። አልያ በቀደመ ስሙ፣ በሰበካውና በቀደመ የፖለቲካ ካፒታሉ ሕዝቡ ያን እየመነዘረ ይበላል እንጂ ዘመነም ከእነ አስረስ ጋር ተባባሪ፣ የምክራቸውም ተሳታፊ፣ የጥፋታቸውም ተካፋይ ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል። ምክንያቱም የጎጃም ፋኖ መሪ ዘመነ እያለ አስረስ መዓረይን ነጥሎ መውቀስ ተገቢነት ስለሌለው ማለት ነው። ይሄ መታረም ይኖርበታል። እስከዛሬ በአርበኛ አስረስ ተጽዕኖ ስር ነበር ቢባል እንኳ አሁን አርበኛ ዘመነ ካሤ በጎጃም ውስጥ ስለሌለ እውነታውን ለማውጣት፣ ለመናገር ይቸግረዋል ተብሎ አይገመትም። ምንአልባት እኛ የማናውቀው እሱ ብቻ የሚያውቀው የከፋ ጉዳይ ካልገጠመው በቀር አርበኛ ዘመነ ካሤ ከጠበቃ አስረስ መዓረይ እስራት የመፈቻ ጊዜው አሁን ነው የሚሉም አሉ።
"…አርበኛ ዘመነ ካሤ በፍጥነት አቋሙን ለይቶ የጎጃምን ፋኖ ካልሰበሰበ ያለበለዚያ ሦስት ነገሮች ይጠብቁታል ተብሎ ይገመታል።
• አንደኛው አማራጭ፦ የአርበኛ ዘመነ ካሤ በብዙ መልክ የነበረው ፖለቲካዊ ቁመናው በራሱም እንዝህላልነት፣ በእነ አስረስም ሴራ ስለሞተ ቢያንስ ሌላው ቢቀር ሕይወቱን ለማትረፍ በኤርትራ ወይም በሱዳን አድርጎ ወደ ኡጋንዳ ወይም ወደ ሌላ የውጪ ሀገር መውጣት። ከዛም እንደ ጃዋር መሀመድ፣ እንደ ልደቱ አያሌው፣ እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ እንደ ገዱ አንዳርጋቸው ጥርስ የሌለው ያረጀ አንበሳ ሆኖ ሰሚም ባይኖር በእነ መሳይ መኮንን እና በእነ መዓዛ መሐመድ መድረክ ብቅ እያለ ስብከት ጩኸቱን ማሰማት•።
• ሁለተኛው አማራጭ፦ በአስረስ መዓረይ አቅራቢነት፣ በአቢይ ፈቃደኝነት ለአገዛዙ እጅ ሰጥቶ፣ "በአፍሪካ ሕብረትና በኢጋድ አደራዳሪነት ዐፋብኃ የሰላም ስምምነት ፈጸመ" ተብሎ በሰበር ዜና ፕሮፖጋንዳ ተሠርቶለት ጌታቸው ረዳ የያዘውን ቦታ መተካት አሊያም ተመጣጣኝና ለሌላውም አስተማሪ የተባለ ሥልጣን ላይ መቀመጥ የሚሉ ቢኖሩም አርበኛ ዘመነን የተመስገን ጥሩነህ ዘመድ የሆነው ማስረሻ ሰጤ ያገኘውን ክብር ያህል ስለማግኘቱ እንጃ ነው የሚሉም አሉ።
• ሦስተኛው አማራጭ፦ ያው እንደተለመደው እንደ ብዙዎቹ የጎጃም ጀግና ፋኖዎች ወይ በድሮን አልያም በሰርጎ ገብ ባንዳ እንደ አባቱ እንደ የኔታ ይባቤ የማይቀረውን ሞት መጎንጨት ነው። ይህ እንዳይሆን የጎጃም ፋኖ ሓላፊነቱን መውሰድ አለበት። አስረስ እያለ ግን ከሦ።ስት አንዱ ዘመነ ላይ መፈጸሙ አይቀርም። ትንቢቴን እውነት አያድርገው። አሜን
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ ከራየን ወንዝ ማዶ።
• የየኔታ ይባቤ ሞት ተፈጥሯዊ ወይስ ሰው ሠራሽ?
“…የኔታ ይባቤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካፈራቻቸው ብርቅዬ ልጆቿ አንዱ ነበሩ። በጎጥ በብሔር ያልተበረዙ፣ የሥልጣን ጥማት ያላነቀዛቸው፣ እስከ አምስት ሚልዮን ብር ጉቦ ተከፍሎ ደጅ የሚጠናውን ጵጵስና በነጻ ከእጃቸው ሲገባ አሽቀንጥረው የጣሉ፣ የሐዋርያትን ፈለግ የተከተሉ፣ ደቂቀ እንጦንስ፣ እውነተኛ መናኝ፣ አራት ዐይና ሊቅ ፕሮፌሰር፣ ጎጃም ያበቀላቸው፣ የጎጃም ሕዝብ የሥነ አዕምሮ መለኪያ፣ የጎጃምን ሕዝብ ልዕልና የምናይባቸው መነጽር፣ የቤተክርስቲያን መብራት፣ ወላዴ አርድእት፣ ገዳሙን ፈትቶ ጉባኤውን በትኖ ሁሉም ወደ ከተማ በሚጎርፍበት በዚህ ዘመን በበአታቸው ጸንተው ተጋድሏቸውን የፈጸሙ፣ ወንበራቸውን እስከ መጨረሻው ሕቅታ ድረስ ያላስታጎሉ፣ ሩጫቸውን፣ ገድላቸውን በመልካም የፈጸሙ፣ የዘመናችን አቡነ ጴጥሮስ፣ በኢንጀክሽን ጥይት ተደብድበው የሞቱ ዳግማዊ ጴጥሮስ ናቸው።
“…ዳንኤል ክብረት ልጅ በመምሰል የቤተክርስቲያንን ምስጢር አሳልፈው እንዲሰጡት ጠይቆ ማንነቱን ተረድተው እምቢ በማለታቸው ቂም ቋጥሮ ሲኖር ዐማራው ላይ የታወጀው ጦርነት ሲጀምር የሚበቀልበትን ዕድል አገኘ። በአስረስ ማረ አማካኝነት ዕድሉን ተጠቀመ። የንታ ይባቤ ከዘመነ ጋር ወዳጅ ናቸው፣ ለዘመነ ጥይት የማያስመታ፣ ሹመት የማያሽር ሰጥተውታል የሚል ወሬ ሲነዛለት አስረስ መዓረይ እውነት መስሎት፣ ለቅባት አስተምህሮ ያላቸውን ጥላቻ ሲያውቅ እንደ ይሁዳ ለዳንኤል ክብረት አሳልፎ ሰጣቸው። ዳንኤልም የፋኖ ደጋፊ ናቸው ብሎ አቢይን በመዘብዘብ ተባብረው ዘብጥያ እንዲወርዱ አደረጓቸው። ቀስ በቀስ ሥራውን የሚሠራ ኢንጀክሽን ወግተው ለቀቋቸው። ኢንጀክሽኑ ሥራውን ሲጨርስ አረፉ። አስከሬናቸው እንዳይመረመርና እንዳይታወቅ በቶሎ ተቀበሩ። አለቀ። የሆነው እንዲህ ነው የሚባለው።
“…አቢይ እሳቸውን በማሰሩ ምክንያት ከሚደርስበት ውግዘት ለመላቀቅ በዚህ መልኩ ሸኛቸው። ማን ይጠይቀዋል? ሲኖዶሱ የእሱ ነው፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሳዊሮስን አስቀምጧል፤ ባሕር ዳር አባ አብርሃምን አስቀምጧል፤ ወሎ ላይ አባ ኤርምያስ አሉለት፤ ምን ቸገረው? ለአባ ኤርምያስ ውለታ የአቡነ ቄርሎስን ሀገረ ስብከት ሰሜን ወሎን፣ ምርቃት አድርጎ ደግሞ የአቡነ አትናቴዎስን ሀገረ ስብከት ደቡብ ወሎን፣ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚሏትን ከሚሴን ጭምር አሰጥቷቸዋል። አሁን ላይ በዚህ ዘመን አቢይ ማን ተው ባይ አለው? ማንስ ይገላምጠዋል? ማንም?
"…አቢይ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚፈጽመው ፕሮጀክት ስኬት ከውጭ እኒህ አባቶች አሉለት። አጀንዳ ያስቀይሳሉ፤ ሕዝብ በአገዛዙ ላይ እንዳይነሳ ያፍናሉ፤ ከጠናም ቀውስ ይጠምቃሉ። ለምሳሌ ያህል የላሊበላን ካህን እርስ በእርስ ጦር እንዲማዘዝ ያደረጉት አቡነ ኤርምያስ ናቸው። ካህኑ ከሕዝቡ እንዳይመክር ለራሱ አጀንዳ ፈጥረው ካህኑን በመቋሚያና በጸናጽል የሚያፈራካክሱት ለዚህ ነው። የፈረንሳይና የአቢይ የቅርስ ዘረፋ ፍላጎት እንዳይጨናገፍ ካህኑ አጀንዳ ማግኘት፣ ተጣልቶ እስከ መከሳከስ መድረስ አለበት። በተጨማሪም ለአቢይ አቡነ ዲዮስቆሮስም አሉለት። በራያ፣ በአላማጣ፣ በኮረም፣ በዖፍላ ላይ ወያኔ የሚያደርሰው የካህናት እልቂትና ፍጅት፣ የአቡነ ሰላማ የጨረቃ ጳጳሳት የሚያደርሱት ፍጅት ጆሮ እንዳያገኝ የኮረሙን አቡነ ዲዮስቆሮስን አሹሞ ይዟል።
"…ከውስጥ ደግሞ አጠገቡ እነ ዳንኤል ክብረትን፣ እነ ሮዳስ ታደሰን እና ሄኖክ ኃይሌን ይዟል። ሄኖክ ኃይሌ ወጣቱን በማስጨፈርና በማስጨብጨብ እውነተኛ የቤተክርስቲያን እውቀት እንዳያገኝ እና ለእውነተኛ መምህራን ጆሮና ጊዜ እንዳይሰጥ በደንብ አድርጎ ይዞለታል። ለዚህ ውለታውም ክርስቲያኖች ሲታረዱ፣ ሲፈናቀሉ፣ አብያተ ክርሲቲያናት እንደ ጧፍ ሲነዱ ዘግበው የማያውቁት ኢቢሲ፣ ኢዜአ፣ ዋልታ እና ፋና ለሄኖክ ኃይሌ የገጽታ ግንባታ እንዲሆንና ተቀባይነት እንዲያገኝ ሠርጉን የጋብቻ ሥነ ሥርዓቱ ሳይቀር የአየር ሰዓት ወስደው አስተላልፈውለታል። ዳንኤል ክብረት እውነተኛ መምህራንን፣ ጳጳሳትን እና ገዳማውያንን ጠንቅቆ ስለሚያውቃቸው በመጠቆም እንደ የንታ ይባቤ እንዲገደሉ፣ እንዲሳደዱ፣ ከሀገረ ስብከታቸው እንዲፈናቀሉ በማድረግ በምትካቸው ሆዳሞችን፣ መተተኞችንና አጨብጫቢዎችን ይሰበስብለታል የሚሉም መተርጉማን አሉ። እንደ ሮዳስ ታደሰ ያለው የነጮችን ተልእኮ በመቀበል ከዚህ ቦታ እንዲህ አይነት ዓውደ ነገሥት፣ ከዚህ ገዳም እንዲህ ያለ ምሥጢር አዘል መጽሐፍ አለ እያለ ቅርስ ይመዘብርለታል። በሐዋርያት ትምሕርትና ተጋድሎ የተደመሰሰውን የቬነስና የአርጤምስን የኮከብ ቆጠራ ከመለኮታዊ እውቀት በማዳለብ የሔርሜቲክንና የግኖስቲኮችን ፍልስፍና በቤተክርስቲያን ስም ለትውልዱ ይግትለታል። ከፀረ ዐማራዋ፣ ከፀረ ኦርቶዶክሷ ከኦሮሙማዋ ሃኪም አበበች ከተባለች ጠንቋይ ስር ማሽ ቅጠል በጣሽ ስር በማደር፣ የእሷን ትእዛዝ በመቀበል ትውልዱን ያደነዝዛል። እኒህን የመሳሰሉ ወንበር አስጠባቂዎች እና የስልጣኑ ዘቦች እያሉ የአቢይን መንበር ማን ይነቀንቀዋል? አጀንዳ ሰጪና አጀንዳ ተቀባዩ እንደ ግሪሳ ወፍ እንደ አሸንም የፈላ ስለሆነ ለጊዜው ሽግር ነው።
"…በዚህ የሁለት ዓመቱ የዐማራ ጦርነት በጎጃም እንደተገደሉት ሊቃውንት በሌላ በየትም ስፍራ የተገደለ የለም። በጎጃም አጠባ፣ ጠረጋ ነው የተደረገው። ገሚሶቹ ለጊዜው ባይሸሸጉ፣ ዞር ባይሉ አይቀርላቸውም ነበር። አንድ ጥንቅቅ ያለ በሁሉ መስክ የተሟላ የቤተ ክርስቲያን መምህር ለማፍራት 20 ሰላሳ ዓመት ነው የሚፈጅ። እንዲህ በበብዙ ድካም የተገኘን ሊቅ ለመግደል ግን አንድ ጥይት ብቻ ነው የሚበቃው። በዚህ መንገድ በጎጃም የዓለማዊም ሆነ የመንፈሳዊው ዓለም ሊቃውንት አልቀዋል፣ ተጨፍጭፈዋል ማለት ነው የሚቻለው። ሊቃውንቱ እየጸዱ ያሉት በፋኖ ተብየው የእነ አስረስ ዘመነ ፋኖዎች እና በኦሮሙማው የመከላከያ ሠራዊት ነው። ብልታቸውን የማይታወቅ መርፌ ተወግተው ፈነዳድተው የሞቱትን የደብረ ማርቆስ የአብነት ተማሪዎችን ማስታወሱ በቂ ነው። ዶር አንዳለም የተባለን ባለ ምጡቅ አእምሮ የህክምና ሊቅ የገደሉት ፋኖዎች መሆናቸውን ሁለቱም አምነዋል። አገዛዙ አንዱን ገዳይ ይዤ ሁለቱ ዐማለጡኝ በማለት መግለጫ ሲያወጣ፣ ፋኖ ማርሸትም ሁለቱን ገዳዮች ይዘን አንደኛው አምልጦናል ብሎ ያለን በተመሳሳይ ቀን ነው። የአገዛዙ ፖሊስ ያዝኩት ያለውን ነፍሰ ገዳይ ፍርድ ቤት አቅርቤ አስፈርጄበታለሁ ሲል እነ ማርሸት፣ እነ አስረስ፣ እነ ዘመነ፣ እነ ፓስተር ዳዊት፣ እነ ፓስተር ተሰማ ያዝናቸው ያሉትንና ለፍርድ እናቀርባቸዋለን ብለው ያሏቸውን ወንጀለኛ ፋኖዎች እስከዛሬ ድረስ አላቀረቡም። እናም በጎጃም ለተፈጸመው የካህናት፣ የአብነት ተማሪዎች፣ የየኔታ ይባቤ፣ የጎጃም የዘመናዊ ትምህርት ቤት መምህራን ወዘተ ሁሉ ሞት ዋና ተጠያቂው አስረስ ማረ ዳምጤ ነው። ቢመርህም ዋጠው። እኔ ዘመዴ ለማንም አላዳላም እውነቱን ነው የምግትህ። ነጭ ነጯን ነው የማለብስህ። ከፈለግክ ጀሮህን ድፈን፣ ዓይንህን ጨፍን፣ ቴሌቪዥንህን ጠርቅም፣ ስልክህን መቆለፍ ትችላለህ፣ የፈለግከውን በል። አቀናባሪው። መሪው አስረስ መዓረይ ነው።
02:15
Відео недоступнеДивитись в Telegram
•ልብ በሉ… አሁን የምንወያየው በእንዲህ ያለ ታላቅና ብርቱ በሆነ ኀዘን፣ የሕዝብም ፍቅር ሥርዓተ ቀብራቸው ስለተፈጸመው ሊቅ ጉዳይ ነው።
• ዳንኤል ክብረት ሲከሳቸው።
• ፓስተር ምስጋናው ሲወቅሳቸው።
• አያሌው መንበር በሞታቸው ስለተሳለቀባቸው እና የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የአስረስ መዓረይ የሥጋ ዘመድ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና አቡነ ቶማስ በቀብራቸው ላይ ስላልተገኙት፣ በወፍራም ሀብታም ላይ ሳይቀር የሚገኙት ቅባቴው እነ አቡነ ማርቆስማ ተገላገልን ሳይሉ ይቀራሉ። በቀብራቸው ላይ የተገኙት የፍኖተ ሰላሙ የተዋሕዶ ጠበቃ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ብቻ መሆኑ ሲታይ አሟሟታቸውን መጠየቅ ግድይላል።
• አላችሁ አይደል…?
13.46 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
• ለዛሬ ቀጠሮ ነበረን አይደል…?
"…በረከታቸው ይደርብንና ሰሞኑን ሲከነክነኝ ስለከረመው የታላቁ ሊቅ የየኔታ ይባቤ ሞት ተፈጥሯዊ ወይስ ሰው ሠራሽ…? በሚል ርእስ ዙሪያ ከሊቃውንተ ኢትዮጵያ ጋር አስደማሚ የውይይት ጊዜ እንደነበረን እና እኔም ከሊቃውንቱ የሰማሁትን በሙሉ በራሴ የአጻጻፍ ስልት ቅምም አድርጌ አቀርብላችኋለሁ ተባብለን ነበር ትናንት የተለያየነው።
"…ትናንት ምሽት ደክሞኝ የቴሌግራም ቤቴን ደጃፍ ሳልዘጋው አድሬ ጠዋት ስነሳ ቤቴ ብልሽትሽት ብሎ አድሮ አገኘሁት። የተደረጃው ቅባቴ ሸንጎና የወሀቢያ መዓት ወደ 3 ሺ የፖርኖግራፊ ሊንክ በቤቴ በመበተን ሲንበጫበጩ አድረዋል። መሸ ነጋ። ሁሉንም ቀሰፍኳቸው። ቤቴም ጸዳ።
• ማሳሰቢያ፦ ማንኛውም ሊንክ ሲላክላችሁ ዘላችሁ አትክፈቱት። በተለይ ጸያፍ፣ ነውረኛ ሊንክ ስታገኙ ደልቱት። ከከፈታችሁት ቴሌግራማችሁን፣ ፌስቡካችሁን፣ ቲክቶካችሁን ሁሉ ነው የምታጡት። ረብሻው ከእንቅልፌ እስክነቃ ብቻ ነበር። ከዚያ በኋላ ይኸው ፀጥ፣ ረጭ። እንክርዳዱን ለቅሜ ወደ እሳት። ቻዎ።
"…አሁን ወደዚያወው ወደ ቀጠሮ መርሀ ግብራችን እንገባለን በጉዳዩ ላይ ብንወያይ ሽግር የለውም አይደል?
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"…ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ። …ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ። የባለቤቱም ባሮች ቀርበው፡— ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ? አሉት። እርሱም፡— ጠላት ይህን አደረገ፡ አላቸው። ባሮቹም፡— እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን? አሉት። እርሱ ግን፡— እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም። ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን፡— እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ፡ አለ። ማቴ 13፥ 25-30
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
🙏 877❤ 272👍 117🕊 11✍ 7⚡ 6😡 6🤯 5🤔 3💔 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"…ነገ ቅዳሜ ከምስጋና በኋላ… ሲከነክነኝ ስለከረመው የታላቁ ሊቅ የየኔታ ይባቤ ሞት ተፈጥሯዊ ወይስ ሰው ሠራሽ…? በሚል ርእስ ዙሪያ ከሊቃውንተ ኢትዮጵያ ጋር በነበረን አስደማሚ የውይይት ወቅት ከሊቃውንቱ የሰማሁትን በሙሉ በራሴ የአጻጻፍ ስልት ቅምም አድርጌ አቀርብላችኋለሁ።
"…በነገራችን ላይ የአስረስ መዓረይ የሥጋ ዘመድ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በሊቁ ሥርዓተ ቀብር ላይ አልተገኙም የሚሉ አሉ? በሰላም ነው?
• በጉዳዩ ላይ ብንወያይ ሽግር የለውም አይደል?
