ግጥም ብቻ 📘
Відкрити в Telegram
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch @shiyach_bicha ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1
Показати більше2025 рік у цифрах

65 786
Підписники
-324 години
-397 днів
-30130 день
Архів дописів
እልፍ አዕላፍ ሰዎች.....
ይኖሩ ይመስል በምድር ዘላለም፤
ዳግም ላይፋቱ ተጋብተው ከአለም፤
የጊዜን ምንነት ወርቅነት ሳያዉቁ፤
ከእድሜያቸዉ ላይ ዘመናት ሰረቁ።
............................................
✍ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤ 37🔥 14😢 2
ቀን የለም
------------
የጨረቃ ግማሽ
ሰማይ ላይ ተስላ፣
ግማሹ መጥፋቱን
ከዜና ስሰማ።
ድንገት አንቺን አየሁ፣
አገኘኋት ብዬ
መናገርን ፈራሁ።
ከየት ልደብቅሽ
እንዴትስ ልውሰድሽ፣
በምን ውስጥ ቆልፌ
ደግሞ ልከልልሽ።
አለሙን ታውቂያለሽ
ጨለማ ካልሆነ ወዳንቺ አያይም፣
ከደመኖች እኩል
ቀን አንቺን ቢያደርግም፣ አይገርምም፣
ለምን ያልሽ እንደሆን
ዋጋሽን አያውቅም።
እሺ ካልሽኝ ይኸው
አገኘሁኝ ቦታ፣
ትንሽ የጨለመ
ማይገኝ ስጦታ።
ገብተሽ ተደበቂ
ልቤ ይሁን መኖሪያሽ፣
እኔ እየጨለምኩ
አንቺ እያበራሽ።
@abela_black
@getem
@getem
@getem
❤ 35👍 1🔥 1😁 1
[ነጋ እንዴ እላታለሁ]
₁ ብዙ ነገር አይቻለሁ
ከኖርኩም ያለሁት ለሷ ነው ለራሴማ ሞቻለሁ።
ለራሴ?
ሳቅም ለቅሶም ቀምሻለሁ ይመሰክራል ትራሴ።
አንድ ጎኔ በእንባ
አንደኛው በፈገግታ
ባንዱ ብርሃን ስትገባ
ባንዱ ስትበራ ነግታ
እንደዚህ ነው ስሪቴ
እንደዛ ነው ህይወት ያዋቀረኝ
ያላየሁት የሷ ደስታ ብቻ ቀረኝ።
₂ ብዙ ነገር አይቻለሁ!
በቅቶኛል
አቅቶኛል
የዚህ ዐለም ሸክም ጉዝጓዝ
ምን ይደክማል እራስን ተሸክሞ እንደመጓዝ?
ይከብደኛል
እከብዳለሁ
ምን ትመስላለች ፀሐይ?
ምን ይቆላታል ጨረቃዋ?
ቻለችኝ ዐለም እንደምን?
ያዘችኝ በምን ጫንቃዋ?
₃ እከብዳለሁ
ለምድሩም ለሰማዩም
ይከብደኛል ሰማዩና ምድሩ
የምስማው የማየውም
በቅቶኛል
የምነካው የማልነካው
የኔ መኖር
አንዱን ማጣት ባንደኛው ነው የሚተካው!
በቅቶኛል!
ባበቃ ነገር ላይ እንዳላበቃ መወስለት
አልመለስም ወደዚህ መቀስቀስ ያቆመች እለት።
₄ ዐለም ግን አላወቀችኝም
እሷን እስከጥግ አውቃታለሁ
እና መኖር እንደሚመኝ ስትቀሰቅሰኝ እነቃላታለሁ።
ነጋ እንዴ? እላታለሁ
የፊቷ ብርሃን ደብዝዟል
የኔስ ጉዳይ አከተመ፣ መኖር ለሷ ምን ይዟል?
ነጋ እንዴ? ፊቷ ታዲያ ምነው ጨለመ
አላደረም መዋል እያለመ?
ለምን ቀሰቀሰችኝ ታዲያ?
እንጃ!
ነጋ እንዴ እላታለሁ
ቢነጋም ለርሷ ነው የሚነጋው
"ተነስ ተነስ" ትለኛለች እሺ አንዴ መቃብሬን ልዝጋው!
By Yadel Tizazu
@getem
@getem
@paappii
❤ 49😢 5🔥 2
Показати все...
❤ 41🔥 8👍 5
ምንድን ነው እውነት!?
ምንድን ነው እውቀት!?
ምንድን ነው እምነት!?
በምን ይሻላል ካንቺ ሰውነት !?
ምንድን ነው ቦታ !?
ምንድን ነው ጊዜ !?
ምንድን ነው ሕይወት!?
በምን ይለያል ከገላሽ ሙቀት!?
ምንድን ነው አምላክ!?
ምንድን ነው ጥበብ !?
ምንድን ነው ኪነት !?
በምን ይበልጣል ከዐይኖችሽ ውበት!?
ምንድን ነው ሎጂክ !?
ምንድን ነው ሳይንስ !?
ምንድን ነው ፍልስፍና !?
በምን ይሻላል ከአንገትሽ ቃና !?
ልልሽ እልና . . .
አንቺ ለራሱ ምድንነሽና !?
By Tewodros Kassa
@getem
@getem
@paappii
😁 82❤ 41👎 10😱 4😢 1🤩 1
ልቡ ግን ምን አለ
አዳም ሄዋንን ልክ እንዳያት፣
ተዋት አታግኛት
ወይ ደግሞ አፍቅራት፣
ትሂድ ወይ ልቀቃት
ወይስ ደግሞ ሳማት፣
ሂድ እቅፍ አድርጋት
ወይንስ ትሁንክ ሚስት።
እንጃ ምን እንዳለክ፣
አንተ ግን ተናገርክ።
እቺ አጥንት ከአጥንቴ፣
ስጋሽ ከስጋዬ፣
የአካሌ ክፋይ
የህይወት አጋሬ። አለ፣
ሴት፣ የማያውቀው አዳም
ሚስቱን ሄዋንን አወቃት፣
የዘመኑ አዋቂ፣
እናውቃለን ብለን ከስንቱ ስንዘሙት፣
ያቺን ሄዋን፣
እናግኛት ብለን ስንማማል ከስንት።
ግን፣
ያኔ አዳም እያለ
ሌላ ሴት ያልኖረው፣
የወንድ ልጅ አመል
እግዜሩ ገብቶት ነው።
እንጃ፣
ብቻ አዳም ያውቃል፣
በአንድ ሚስት መደሰት
በአንድ ሚስት መቃጠል፣
ብቻ አዳም ያውቃል
አንድ አሀዝ ወይ ፊደል፣
ሺ አመት እንዲፀኑ
ከእግዜር ነው መታደል።
@abela_black
@getem
@getem
@getem
❤ 50👍 3😁 3
ልምጣ ይሆን እደርሳለሁ
ባላገኝሽ አይሻለው፣
ካለሽበት ልሳለምሽ
ባታይኝም አይሻለው፣
የበደልኩሽ የሳትኩት ግን
በእጄ እያለሽ ስተውሽ ነው፣
ክንፋም መልአክ የነገረው
ትንቢት ይኖር ልቤ ያወቀው።
ስታመልጪኝ ከእጄ ሳጣሽ
ያኔ ሰጋሁ እንዳላጣሽ፣
ልራመድ ወይ ወደትላንት
እንዳገኝሽ በትዝታሽ።
የጠፋ አለም የከደንኩት
በጨለማ ያዳፈንኩት፣
እንደ እንጀራ በስሎስ ቢሆን
ለማ ይሆን እኔ የተውኩት።
ባለሽበት አይሻለሁ
ልምጣ ልይሽ ጓጉቻለው፣
የጥፋት ጣር የአርፋጅ እግር
እየገፋኝ ደርሻለው፣
ይቅር በይኝ ተምሬአለሁ
ባንቺ ብቻ እፀናለሁ፣
ልምጣ ይሆን እደርሳለው?
@abela_black
@getem
@getem
@getem
❤ 29🔥 10😢 5😁 2
ቅንድቧን እንደ ሴት ፥ ኩል አልተኳለችው
ፀጉሯ ቢንጨባረር ፥ ጉዳዬ አላለችው
ከንፈሯን በቀለም ፥ አልለቀለቀችው
እንደነገሩ ነው ፥ ልቤን የረታችው ።
እንደ ነገሩ ናት
ካፈር የተሰራች ፥ አመለ ውሃ ናት
እንደ ነገሩ ናት
ባያምር ባይደምቅ ፥ ልብሷና ቀሚሷ
እግረመንገዷን ነው ፥ የምታምረው እሷ
እንደ ነገሩ ናት
በደበዘዘ መልክ ግልገል ፀሐይ አዳይ
ያለ ጋሻና ጦር በዝምታ ገዳይ
እንደ ነገሩ ናት
በጭብጨባ ብዛት የማትደናበር
በተቺ ዘለፋ የማትሰባበር
እንደ ነገሩ ናት
የገዛ ክንፎቿን አጣጥፋ የምትበር ።
By Habtamu Hadera
@getem
@getem
@paappii
❤ 107🤩 16🔥 11🎉 3
ልብሱ
ጫማው
ጌጡ ቀርቶ
እህል እንኳን ሳልገዛልሽ ፤
ስለ ዐይኖችሽ
ስለ እጆችሽ
ስለ እግሮችሽ ሳልፅፍልሽ ፤
ሳልጎበኝሽ
ሳልሰልልሽ
የኾንሽውን ሳልጠይቅሽ ፤
እንዲሁ . . . እንዲያው . . . እንደማንም ፤
እንደ ተራ . . . እንደ ምንም ፤
ድምፄን ውጬ ዝም ስልሽ ፤
ረስቼሽ እንዳይመስልሽ ።
፡
ባይልልኝ ነው አበባዬ ፤
ባይሆንልኝ
ባይሞላልኝ ፤
ከዕንባ በቀር በልቤ ላይ
ሌላ ገንዘብ ባይቆይልኝ ፤
እንጅማ አንቺን ፤
እመቤቴን ፤
እንዴት ብዬ እረሳለሁ !?
ቀን በውኔ
ሌት በሕልሜ
ትዝ እያልሽኝ አለቅሳለሁ ፤
ብቻ አንድ ቀን
ሞት ካልለየኝ ፤
ያ ጨለማ ካልቀደመኝ ፤
ዕምባ አርግዤ ብቅ እላለሁ፤
እጆችሽን
እግሮችሽን
ዐይኖችሽን እስማለሁ ፤
ከአንቺ ርቄ የሆንኩትን
አንድ በአንድ ነግርሻለሁ ፤
ወድሻለሁ
ወድሻለሁ
ወድሻለሁ
። ። ። ። ።
By Tedros kassa
@getem
@getem
@paappii
❤ 72🔥 13😢 8👎 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ና ገነትን እንኑራት…………..
ከርምጃህና እርምጃዬ
ከትከሻህና ትከሻዬ
ከሸባበተዉ ፀጉርህና ጠጉሬ መሀል
የመላዕክት ዝማርያቸዉ ይሰማሀል?
ምርኩዝህን አይተሀዋል እንደሙሴ…………
ድካምህን
ወንድነትህን
ማጣትና ማግኘትህን
አሉባልታ ስሜትህን
ከፈልክበት
ተሸለምከዉ ተደገፍከዉ።
ማርያምን ስወደው ሽብሽብ ገፅህን
የፈዘዘዉ ቅንድብህን
የጐደጐደዉ አይንህን
እኔልሙት……..
ስትስቅ እኮ ምድር ቀዉጢነዉ ምትሆነዉ
ደመና ሳቋን - መቆጣጠር አቅቷት
ዝናቧንም የምትለቀዉ።
ና ገነትን እየኖርናት
ነፋሴና ነፍስህ ይሙቃት
ትዝታ ወልዴ✍️
@Tizita21
@getem
❤ 73🔥 10👍 3🤩 1
Показати все...
❤ 22😢 19🔥 7😁 2
