352 777
Підписники
-4824 години
+967 днів
+1 45930 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ማስታወሻ
በ2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርታችሁን በመከታተል ላይ የምትገኙ ተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ማውጣት ይጠበቅባችኋል።
የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ያላደረጋችሁ በከተማዋ የምትገኙ ተማሪዎች ቅዳሜ እና እሑድ በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች በመገኘት ምዝገባ በማድረግ መታወቂያውን መውሰድ ትችላላችሁ።
@tikvahuniversity
❤ 42👎 21😱 5👍 3😢 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ጥቆማ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተወሰኑ ቦታዎች ላይ “ምርጫ የሚያስፈፅሙ” ተጨማሪ የምርጫ ክልል አስፈጻሚዎችን ለመመልመልና በጊዜያዊነት ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል።
በዚህም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ “በምርጫ ክልል በአስፈጻሚነት” መስራት የምትፈልጉ አመልካቾች ይህን ሊንክ https://nebe-election.org/registration_co በመጠቀም ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።
የማመልከቻ ጊዜ፦ ከህዳር 12-15/2018 ዓ.ም
መስፈርቶች፦
➫ ዕድሜ ከ21 ዓመት በላይ የሆነ/የሆነች
➫ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ያልሆነች
➫ የትምህርት ዝግጅት፦
የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ
➫ የሥራ ቦታ፦ በሁሉም ክልሎች
➫ የሥራ ቆይታ፦ ለሰባት ወር
➫ ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ
@tikvahuniversity
❤ 46👍 9👎 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Advanced Graphic + Video Editing + Motion Graphic + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 52👍 3👎 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#AssosaUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ትምህርት ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ ስምንት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ (National ID)፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
@tikvahuniversity
❤ 124👎 47👍 33🙏 12😢 7🥰 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#WolloUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በኮምቦልቻ ግቢ
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በደሴ ግቢ
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ አራት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ፡፡
@tikvahuniversity
❤ 107👎 7🙏 4👏 1😢 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#BuleHoraUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 29 እና 30/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ትምህርት ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል፡፡
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ ስምንት 3x4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ (National ID) ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
@tikvahuniversity
❤ 166👎 46👏 10🙏 10👍 6
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የበሽ ጥቅል እየገዛን እስከ 1 ሚልዮን ብር እንሸለም! ከቀሩት 8 ሚሊዬነሮች አንዱ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ!
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በ M-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፦
https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን 👇🏽
https://t.me/official_safaricomet_bot
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#besh
❤ 38👏 4🙏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#Update
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎችን ዛሬ ህዳር 11/2018 ዓ.ም መቀበል ጀምሯል።
ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት ባደረገው ጥሪ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የምዝገባ ቦታ በዘንዘልማ ግቢ ተብሎ የተገለፀ ቢሆንም፤ የምዝገባ ቦታው ከዘንዘልማ ግቢ ወደ #ፔዳ_ግቢ የተቀየረ መሆኑን ተቋሙ ገልጿል።
@tikvahuniversity
❤ 118👏 26👎 10😢 6🙏 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ETA
የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ተገምግሞ ተቀባይነት ያገኘን ስርዓተ ትምህርት በመከተል ትምህርት እንዲሰጡ አሳስቧል፡፡
ማንኛውም ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሀገሪቱን የትምህርት ፖሊሲ ተከትሎ በተዘጋጀ ስርዓተ ትምህርት ተማሪ መቀበል፣ ማስተማር እና ማስመረቅ እንዳለበት ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡
ይህን የተላለፈ ተቋም በትምህርት መስኩ ለሁለት ዓመት አዲስ ተማሪ እንዳይቀበል ቅጣት እንደሚጣልበታል እና ስርዓተ ትምህርቱን ያልተከተለ የትምህርት መስክ እንዲዘጋ እንደሚደረግም ተመላክቷል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 49👍 2🙏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል የዩኒቨርሲቲው መደበኛ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ2018 ዓ.ም የሳምንት መጨረሻ ፕሮግራም አስጀምሯል።
ፕሮግራሙ መደበኛ ተማሪዎች የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ (STEM) ክህሎቶች እነዲያጎለብቱ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል።
ሰልጣኝ ተማሪዎቹ ከዩኒቨርሲቲው ኮሌጆች/ትምህርት ቤቶች የተመለመሉ ሲሆኑ፤ መሰረታዊ የኮምፒውተር፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ ሮቦቲክስ እና ኮዲንግ ክህሎቶች ለማጎልበት የሚያስችሉ ስልጠና እንደሚሰጣቸው ተገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 44👏 4😱 3🙏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የ45 ቀን የቲያትር አርት (Theatrical Art) ስልጠና በፒያሣ ካምፓስ የፊታችን ሰኞ ህዳር 15/2018 ዓ.ም ይጀመራል!
👉 የቲያትር ድርሰት አፃፃፍ (Script Writing)፣ የቲያትር ዝግጅት (Directing) እና የቲያትር ትወና (Acting) ስልጠናን በአንድ ላይ አካቶ የሚሰጥ
👉 በተቋማችን አዳራሽ የቲያትር ዝግጅቶችን በማቅረብ ራስዎትን በበለጠ የሚያስተዋውቁበት
👉 በታዋቂ የቲያትር ባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 60👎 2👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#AmboUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አምቦ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 29 እና 30/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
@tikvahuniversity
❤ 205👍 50👎 29😢 16🥰 3😱 1🙏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በኅብረተሰብ ጤና ትምህርት የማስተርስ ፕሮግራም (MPH) በመደበኛ እና በእረፍት ቀናት ለመማር ያመለከቱና የመግቢያ የፅሑፍ እና የቃል ፈተና የወሰዱ አመልካቾች የመጨረሻ ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡
ቅበላ ያገኛችሁ አመልካቾች ዝርዝር ለመመልከት የኮሌጁን ድረ-ገፅ (https://sphmmc.edu.et/) ይጎብኙ፡፡
የምዝገባ ጊዜ፦
ከህዳር 11-13/2018 ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ፦
በኮሌጁ የሬጅስትራር ቢሮ በአካል
ትምህርት የሚጀምረው ለመደበኛ ተማሪዎች ህዳር 15/2018 ዓ.ም እና ለእረፍት ቀናት ተማሪዎች ህዳር 13/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 60👎 8🙏 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ጥቆማ
በ2026 የዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚ እና አስትሮፊዚክስ ኦሎምፒያድ ኢትዮጵያን በመወከል መወዳደር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ያመልክቱ!
ማን ማመልከት ይችላል?
➫ ከ20 ዓመት በታች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች
➫ የ2ኛ ደረጃ እና የ1ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
➫ በ STEM፣ አስትሮኖሚ እና ፊዚክስ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች
➫ ችግር ፈቺ እና ሳይንሳዊ ክህሎት ያላቸው ተማሪዎች
🚀 ሀገር አቀፍ ስልጠናና ሜንቶርሺፕ በአስትሮኖሚ እና ፊዚክስ የሚያገኙ ይሆናል፡፡
🚀 በ2026 በሚካሔደው ዓለም አቀፍ ኦሎምፒያድ ኢትዮጵያን የሚወክሉ 5 ተማሪዎች ይለያሉ፡፡
ተወዳዳሪዎች እንዴት ይለያሉ?
1️⃣ የመግቢያ ፈተና – ሒሳብ፣ ፊዚክስ እና አጠቃላይ አስትሮኖሚ
2️⃣ ደረጃ 1 ስልጠና – በአስትሮኖሚ እና ችግር ፈቺ መሰረታውያን ላይ
3️⃣ የአጋማሽ ፈተና – ከፍ ያለ መረጣ
4️⃣ ደረጃ 2 ስልጠና – ሙሉ የአስትሮኖሚ እና አስትሮፊዚክስ ኦሎምፒያድ ሴለበስ
5️⃣ ሀገር አቀፍ ፍጻሜ – የመጨረሻዎቹ 5 ተወዳዳሪዎች ይለያሉ
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ህዳር 18/2018 ዓ.ም
ያመልክቱ፦
https://tally.so/r/w49B7O?updated=1 ወይም በምስሉ ላይ ያለውን QR ኮድ ስካን ያድርጉ
ለተጨማሪ መረጃ፦
0929103870 / eskcssgi@gmail.com
@tikvahuniversity
❤ 69👎 3👍 2👏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
39ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና ነገ ሐሙስ ህዳር 11/2018 ዓ.ም በመገናኛ ካምፓስ ይጀመራል!
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 መሠረታዊ የአካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 ስልጠናው ከፒስቺሪ በተጨማሪ በ Excel፣ Word እና ተግባራዊ ዶክመንቶች ታግዞ የሚሰጥ ነው።
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 53👏 5😱 1🙏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰራተኞች ቅነሳ ሊያደርግ ነው የሚለው መረጃ 'ትርጉም የማይሰጥ' ነው። - ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት አልማዝ ኢዮቤልዩ አከባበርን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የተቋሙ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፤ የሰራተኞች ምደባና ስምሪት ማስፈፀሚያ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶና ውይይት ተደርጎበት ወደ ሥራ መግባቱን ገልፀዋል።
በዚህም ምደባ የሚከናወንበት የጊዜ ሰሌዳ ፀድቆ ለሚመለከታቸው አካላት መላኩ ተገልጿል።
የሰራተኞች መመዝገቢያና የመረጃ ማጥሪያ ኦንላይን ፎርም ተዘጋጅቶ ምዝገባ ተከናውኗል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ከደረጃ 08 በላይ ለሆኑ 1,500 ለሚደርሱ የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች ፈተና በመስጠት ብቃትና ውጤታማነትን ማዕከል በማድረግ ምደባ ይሰጣል ብለዋል፡፡
ከደረጃ 08 በታች ለሚገኙ የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች በሰነድና በነበራቸው የግምገማ ውጤት በውድድር ምደባ እንደሚሰጥ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ አመላክተዋል፡፡
የአካዳሚክ ሰራተኞች፣ ተመራማሪዎች፣ የአካዳሚክ ቴክኒካል ረዳቶች እና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጤና ሙያተኞች በውድድር ላይ የተመሰረተ ልየታ ተደርጎ ስምሪት እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
ተጨማሪ የሰው ኃይል በሚያስፈልግበት ቦታ ላይ በተዘጋጀው ስትራቴጂ መሰረት ወደ ሥራ የማስገባት ተግባር እንደሚከናወን አስረድተዋል።
ዩኒቨርሲቲው የሰራተኞች ቅነሳ ሊያደርግ ነው በሚል የተሰራጨውን መረጃ “ትርጉም የማይሰጥ” ነው ሲሉ ሐሰት መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው 4 ሺህ የአስተዳደር ሰራተኞች ያሉ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ፤ በሁሉም መዋቅሮች “በቂ ሰራተኛ አለ ማለት፥ ሁሉም ይቀጥላሉ ማለት አይደለም። በቅድሚያ ብቃት ያላቸው ሰራተኞች ቦታውን መያዝ አለባቸው” ብለዋል፡፡ #ኢፕድ
@tikvahuniversity
❤ 214👎 59😢 12👏 9👍 4🥰 3🙏 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#AAU
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዩቤልዩ በዓሉን ለማክበር ዝግጅት አጠናቋል።
ክብረ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 75 ዓመታት ያበረከተውን አስተዋፅኦ በመጽሐፍ ተሰንዶ ይፋ የሚደረግ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
ዘጋቢ ፊልም፣ የአካዳሚክ ሴሚናሮች፣ የፓናል ውይይቶች እና የበጎ ፈቃድ ሳምንት መርሐግብሮች እንደሚካሔዱም ጠቅሰዋል፡፡
በሌላ በኩል የዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ የመሆን ሒደት እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር የሚያግዘውን ከ2024 እስከ 2028 ዓ.ም የሚመራበትን የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ሥራ መግባቱን አስረድተዋል፡፡
የተለያዩ መመሪያዎች፣ ሰነዶች እና ፖሊሲዎች ፀድቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡
500 በላይ የነበሩ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ወደ 418 እንዲሸጋሸጉ መደረጋቸው ተገልጿል።
@tikvahuniversity
👎 92❤ 86🙏 7👍 6
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ማን ያውቃል ቀጣይ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ!
በትናንትናው ዕለት የ12ኛው ዙር ዕድለኞች ዕጣ አወጣጥ በቲክቶክ እና በፌስቡክ ገፃችን ላይ በቀጥታ ስናስተላልፍ በነበረው መሰረት የ1,000,000 ብር ዕድለኛ ከሶዶ ሆነዋል! እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵
የበሽ ጥቅል እየገዛን እንንበሽበሽ! 🥳🎉🎉
ሌሎች የ100 ብር አሸናፊዎች #Besh100Winner በመጠቀም ኮሜንት ላይ ወይም Story ላይ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ታግ በማድረግ ያሳውቁን።
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፦ https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን 👉🏽 https://t.me/official_safaricomet_bot
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#besh
❤ 34😢 4🥰 1👏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#MoE
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለመማር የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ #ተጠባባቂ ከተባሉ ተማሪዎች መካከል የተወሰኑ ተማሪዎችን መቀበሉን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ተጠባባቂ የነበራችሁ ተማሪዎች በመጀመሪያ በተመዘገባችሁበት ሊንክ (sbs.moe.gov.et) በመግባት የተመደባችሁበትን ትምህርት ቤት በማየት ምዝገባ ማከናወን የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 91👎 63👏 10👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት ይስጡ!
የትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ ቡድን ባዘጋቸው ሁለት ረቂቅ ደንቦች ላይ የትምህርት ማኅበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡
1. በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ ረቂቅ ደንብ፦ https://forms.gle/HisAZoyTpmo1ZFCA6
2. የተማሪዎች የሥነ-ምግባር መመሪያ (የመጀመሪያ ረቂቅ)፦
https://forms.gle/R72ai6EiMnzZtGsC6
ሊንኮቹን በመጫን ከዛ በመቀጠልም ማስፈንጠሪያ (Link) የሚለውን በመጫን ሰነዶቹን ማግኘት ይችላሉ፡፡ ሁለቱንም ሰነዶች ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (Submit) የሚለውን በመጫን አስተያየትዎን መላክ እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 65👎 34🥰 1

