352 742
Підписники
-9324 години
+37 днів
+1 19630 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ሎርካን_ሜዲካል_ኮሌጅ
የበርካታ ዓመታት ልምድ ባላቸው ሐኪሞችና ምሁራን ባለቤትነት የሚመራው ሎርካን ሜዲካል ኮሌጅ ምዝገባ ጀምሯል❗️
BSc Fields of Study:
→ Doctor of Medicine
→ Doctor of Dental Medicine
→ Bachelor of Dental Science
→ Nursing
TVET Programs:
→ Dental Therapy
→ Nursing
→ Medical Laboratory
→ Pharmacy
→ Radiography
የ CPD ማዕከል አገልግሎት
☎️ 0913398780 / 0911596059
አድራሻ፦
CMC አደባባይ ከፀሐይ ሪል እስቴት ጀርባ ከ ICMC ጠቅላላ ሆስፒታል አጠገብ
Addis Ababa, CMC square, Behind Tsehay Real Estate, next to ICMC General Hospital
Facebook: https://www.facebook.com/Lorcanmedicalcollege
❤ 21
Фото недоступнеДивитись в Telegram
10ኛ ዙር የጋዜጠኝነት ስልጠና ቅዳሜ ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም ይጀመራል፡፡
ስልጠናው ያካተታቸው፦
👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆች
👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት እና የዶክመንተሪ ዝግጅት
👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና YouTube Journalism አካቷል፡፡
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 53👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ምደባ ተለቋል፡፡
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት 👇
በድረ-ገፅ፦ https://student.ethernet.edu.et
በቴሌግራም ቦት፦ @moestudentbot
@tikvahuniversity
❤ 403👎 122👍 65🙏 42👏 35😢 33😱 10
#TVTI
በ2018 የትምህርት ዓመት በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በደረጃ 6 (የመጀመሪያ ዲግሪ) ስልጠና ለመጀመር የተመዘገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ወስደዋል፡፡
ኢንስቲትዩት በዚህ ዓመት በደረጃ 6 (የመጀመሪያ ዲግሪ) ሰባት አዳዲስ ፕሮግራሞች እንደሚከፍት መግለፁ ይታወሳል፡፡
ባዮሜዲካል ቲክኖሎጂ፣ ሳይበር ሴኩሪቲ ቴክኖሎጂ፣ አርቲፊሻል ኢንተሌጀንስ ቴክኖሎጂ፣ ሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ፣ ኒው ኢነርጂ ቪሄክል ቴክኖሎጂ፣ ፕላስቲክ ቴክኖሎጂ እና ሆርቲካልቸር በደረጃ 6 (የመጀመሪያ ዲግሪ) አዲስ የሚከፈቱት ፕሮግራሞች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 49👍 11👎 3🙏 2
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን ጥያቄውን ለትምህርት ሚኒስቴር በይፋ አቅርቧል፡፡ - የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ትምህርት ሚኒስቴር ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች ለማሟላት እየተሠራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ለሚ ጉታ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
ፖሊሲና መመሪያዎች፣ ስትራቴጂክ ዕቅድ እና ተቋማዊ የግምገማ ሰነድ የመሳሰሉት ዝግጅት መጠናቀቁን ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል።
የመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ በከፍተኛ ትኩረት እየተሠራ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የምርምር ፓርክ ግንባታ ባለፈው ዓመት መጠናቀቁን አስታውሰዋል።
በምርምር ፓርኩ ውስጥ ለሚገኙ አምስት የልህቀት ማዕከላት 30 ቤተ-ሙከራዎችን የማደራጀት ስራ ተጀምሯል ብለዋል።
ዘመናዊ የዳታ ማዕከል፣ የ10 ኪሜ አስፋልት እና የአራት ኪሜ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና ሌሎችም ግንባታዎች እየተገባደዱ ይገኛሉ ብለዋል። #ኢዜአ
@tikvahuniversity
❤ 56👎 10👍 4
በባዮሜዲካል ቴክኖሎጂ ዘርፍ በደረጃ 6 (የመጀመሪያ ዲግሪ) ስልጠና ለመስጠት ስምምነት ተፈረመ፡፡
ስምምነቱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ጋር በባዮሜዲካል ቴክኖሎጂ ዘርፍ በደረጃ 6 (የመጀመሪያ ዲግሪ) ስልጠና በትብብር ለመስጠት የሚያስችላቸው ነው፡፡
ስምምነቱን የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) እና የቅዱስ ጳውሎስ ሚሌኒየም ሚዲካል ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሙሉቀን ተስፋዬ ተፈራርመዋል፡፡
ኮሌጁ የተግባር ማሰልጠኛ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፤ ከስልጠና ባሻገር በቴክኖሎጂ ኢንኩቤሽን ፕሮግራምች የህክምና ቁሳቁሶችን የመፍጠር ሥራ በጋራ እንደሚሠራ ይጠበቃል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 26
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ፓዩኒየር ኮሌጅ (ጀርመን አደባባይ ካምፓስ)
⭐️ የእውቅና ፈቃድ ያለው!
🔔 ምዝገባ ላይ ነን!
በዲግሪ ፕሮግራም
➢ በሜዲስን
➢ በዴንታል ሜዲስን
➢ በፋርማሲ
➢ በሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ
በሪሚዲያል ፕሮግራም
➢ በተፈጥሮ ሳይንስ ፕሮግራሞች
በCPD እና ሌሎች አጫጭር ስልጠናዎች
አድራሻ፦
ከጀርመን አደባባይ ወደ ለቡ መብራት በሚወስደው መንገድ በግራ በኩል 550 ሜትር እንደተጓዙ ያገኙናል
ለበለጠ መረጃ፦ 0902443344 / 0902442244 / 0903222233
❤ 20
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መስራት ማህበር ለኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች ተግባራዊ ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ ነው፡፡
✅ በንግድ፣ በፋይናንስ፣ በማርኬቲንግ፣ በኢንቨስትመንት፣ በገበያ ማፈላለግ እና በህግ ጉዳዮች ዙርያ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተዘጋጁ ጽሁፎችን ማጋራት
✅ የንግድ ስራችሁን ለማስተዳደር የምትጠቀሙበት መመሪያዎችንና ሃሳቦችን ማጋራት
✅ በናንተ የስራ ፈጠራ መንገድ ቀድመው ካለፉና ብዙ ልምድ ማካፈል ከሚችሉ ጋር ሃሳብ የምትለዋወጡበት መድረክ
✅ በስራችሁ ወደፊት ለመራመድ የሚያግዟችሁን የተለያዩ ሃሳቦች ማጋራት እንዲሁም ጠቃሚ ግንኙነቶችን የምትፈጥሩባቸው ኩነቶችን መጠቆም
የንግድ ስራችሁን አሳድጉ 👇
https://mahber.mesirat.org/wp-login.php?loggedout=true&wp_lang=en_US
❤ 16😱 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#MoE
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ ያለፋችሁና ጋምቤላ የተመደባችሁ ተማሪዎች ባላችሁበት ሆናችሁ በተመዘገባችሁበት ሊንክ በመግባት በኦንላይን እስከ ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም ድረስ ምዝገባ እንድታከናውኑ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 70👏 13😱 12👍 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#Y12HMC
በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜድካል ኮሌጅ በPublic Health የድኅረ-ምረቃ መርሐግብር (General Public Health, Epidemiology, Health Care Quality, and Reproductive Health) ለመማር ያመልከታችሁ የመግቢያ ፈተና ቅዳሜ ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም ጠዋት 2:30 እንደሚሰይጥ ኮሌጁ አሳውቋል፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፦ በየካቲት 12 ሆስፒታል ቅጥር ግቢ
ተፈታኞች የNGAT ማለፊያ ውጤታችሁንና ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ ይዛችሁ በመቅረብ ፈተናውን እንድትወስዱ ኮሌጁ አሳስቧል፡፡
ውጤት የሚለጠፈው ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም ሲሆን፤ ያለፉ ተፈታኞች ምዝገባ ጥቅምት 29 እና 30/2018 ዓ.ም ይካሔዳል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 32😱 2👍 1👏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በቅርቡ ይፋ የተደረገው የሚዲያ ልህቀት ማዕከል የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠን ጀምሯል፡፡
ስልጠናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መሰጠት የተጀመረ ሲሆን፤ ሰልጣኞች በጋዜጠኝነት ሙያ የፕሮፌሽናል ሰርቲፊኬት ለማግኘት ስልጠና መውሰድ ጀምረዋል፡፡
ከተለያዩ መገናኛ ብሁሃን የተውጣጡና ማዕከሉ ያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና ወስደው ያለፉ ሰልጣኝ ጋዜጠኞች የመጀመሪያ ዙር ስልጠናውን እየተከታተሉ መሆናቸው ታውቋል፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በፈረሙት የመግባቢያ ስምምነት መሰረት ፕሮፌሽናል ሰርቲፊኬት የሚሰጥባቸው የስልጠና ፕሮግራሞች፦
➫ Hydro Journalism (የውሃ ጋዜጠኝነት)
➫ Health Journalism (የጤና ጋዜጠኝነት)
➫ Climate Journalism (የአየር ንብረት ጋዜጠኝነት)
➫ Data Journalism (የዳታ ጋዜጠኝነት)
➫ AI-Driven Journalism (የኤ.አይ. ጋዜጠኝነት)
@tikvahuniversity
❤ 34👏 1😱 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሰቨን ስታር ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ
የበርካታ ዓመታት የማስተማር ልምድ ባላቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሐኪሞች የተመሰረተ ኮሌጅ!
🔔 ለ2018 ዓ.ም ምዝገባ ጀምረናል!
በዲግሪ የጤና መርሐግብሮች
➫ ነርሲንግ ➫ ፐብሊክ ሄልዝ
➫ ፋርማሲ ➫ ሚድዋይፈሪ
➫ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ
➫ ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ
በዲግሪ የቢዝነስ መርሐግብሮች (በቀን እና በማታ)
➫ አካውንቲንግና ፋይናንስ
➫ ማርኬቲንግ ማኔጅመንት
➫ ቢዝነስ ማኔጅመንት
➫ ሰው ሀብት አስተዳደር
በጤና በደረጃ-4 መርሐግብሮች
➫ በፋርማሲ ➫ በላብራቶሪ
➫ በነርሲንግ ➫ በሚድዋይፈሪ
➫ በሜዲካል ራዲዮሎጂ
በቢዝነስ በደረጃ-4 መርሐግብሮች
➫ በአካውንቲንግና ፋይናንስ
➫ በማርኬቲንግና ሴልስ ማኔጅመንት
በሪሚዲያል መርሐግብር
⏩ ፈጥነው ይመዝገቡ!
አድራሻ፡-
አዲስ አበባ፣ ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን፣ ከባቡር ትኬት መቁረጫው ፊት ለፊት
☎️ 0982373737 / 0965686819
❤ 20
Фото недоступнеДивитись в Telegram
10ኛ ዙር የኢንቴሪየር ዲዛይን (Interior Design) ስልጠና የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ይጀመራል።
👉 AutoCAD, Revit, እና 3D Max ሶፍትዌሮችን በአንድ ላይ
👉 ከንድፈ ሀሳብ እና ሶፍትዌር ስልጠና በተጨማሪ በተግባር በወርክሾፕ የሚሰጥ
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 40🥰 2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 ዓ.ም በከተማዋ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ከ500 በላይ ውጤት ካስመዘገቡ 1,321 ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ላመጡ 336 ተማሪዎች ዕውቅና ሰጥቷል።
በአዲስ አበባ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 31 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት አምጥታዋል። ይህም በ2016 ዓ.ም ከነበረው 23 በመቶ መሻሻል የታየበት ነው።
በመላ ሀገሪቱ ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ካሳለፉ 50 ትምህርት ቤቶች መካከል 17 ትምህርት ቤቶች በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ናቸው። በተጨማሪ በከተማዋ የሚገኙ ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ አሳልፈዋል።
ለእነዚህ ተቋማት እና ተማሪዎች ዕውቅና የሰጠ መርሐግብር በዛሬው ዕለት በከተማ አስተዳደሩ ተከናውኗል። ለአይነ ስውራን እና መስማት ለተሳናቸው ውጤታማ ተማሪዎችም ዕውቅና ተሰጥቷል። 👍👏
@tikvahuniversity
❤ 195👍 41👎 27👏 12😱 5😢 1🙏 1
#Post_Graduate_Studies
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በ2018 ዓ.ም በመደበኛው እና በኤክስቴንሽን መርሐግብር የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ለመከታተል ፍላጎት ያላቸውን አመልካቾች በመቀበል ላይ ይገኛሉ፡፡ ተቋማቱ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት የምዝገባ ጊዜን አራዝመዋል፡፡
በቅርቡ የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ አመልካቾች በምትፈልጉት ቅበላ ባላጠናቀቀቀ ተቋም ምዝገባ ማድረግ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 107👎 12👍 8🙏 2👏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በህ/ተ/ም/ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ የትምህርት ዘርፉን በተመለከተ ከተናገሩት፦
"በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት የተዘጋጁ ከ43 ሚሊዮን በላይ የሁለተኛ ደረጃ መፅሐፍት ታትመውና ተከፋፍለው ለተማሪዎች አንድ ለአንድ ደርሰዋል።"
"ኢትዮጵያ ውስጥ 2.4 ሚሊዮን ወጣቶች ነጻ የኮዲንግ ስልጠና ወስደዋል።"
@tikvahuniversity
👎 108👍 35❤ 24😢 8
Фото недоступнеДивитись в Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵
በትላንትናው ዕለት የዘጠነኛው ዙር ዕድለኞች ዕጣ አወጣጥ በቲክቶክ እና ፌስቡክ ገፆቻችን ላይ በቀጥታ ስናስተላልፍ በነበረው መሰረት የ1,000,000 ብር ዕድለኞች ከጅማ እና ከባህር ዳር ሆነዋል።
ማን ያውቃል ቀጣይ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! የበሽ ጥቅል እየገዛን እንንበሽበሽ! 🥳🎉🎉
ሌሎች የ100 ብር አሸናፊዎች #Besh100Winner በመጠቀም ኮሜንት ላይ ወይም Story ላይ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ታግ በማድረግ ያሳውቁን።
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፦ https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን 👉🏽 https://t.me/official_safaricomet_bot
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#besh
❤ 26🙏 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#FellowshipOpportunity
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ብቁ አመልካቾችን ለ2018 ዓ.ም Intensive Care Medicine Fellowship ፕሮግራም አወዳድሮ መቀበል ይፈልጋል።
ለዚህ ዓመት አራት (4) የፌሎውሺፕ ዕድሎች መኖራቸውን ኮሌጁ ገልጿል።
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም
የቅበላ መስፈርት
በህክምና ዲግሪ ያለው ያላት እና በ Emergency and Critical Care Medicine ወይም በ Anesthesiology, Critical Care and Pain Medicine ወይም በ Internal Medicine ስፔሻሊቲ ያለው/ያላት እና የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ
የማመልከቻ ቦታ፦
በ Intensive Care ህክምና ትምህርት ክፍል ወይም በ ሬጅስትራር ቢሮ ወይም በኢሜል አድራሻ negest.tesfaye@sphmmc.edu.et
አመልካቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ፦
➫ የማመልከቻ ደብዳቤ
➫ የቅርብ ጊዜ CV
➫ የድጋፍ ደብዳቤ (2)
➫ የድኅረ ምረቃ ፈተና ውጤት
➫ የትምህርት ማስረጃዎች (ዲግሪ እና የውጤት መግለጫ)
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ
ለበለጠ መረጃ 👇
Dr. Mahilet Mitiku:
malidmitik@yahoo.com or
Negest Tesfaye:
negest.tesfaye@sphmmc.edu.et
@tikvahuniversity
❤ 67👍 11👎 2👏 1🙏 1
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በቀን 200 ሲሊንደር ኦክስጂን ማምረት የሚችል የኦክስጂን ፕላንት ሥራ አስጀምሯል፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከጤና ሚኒስቴር እና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የኦክስጂን ፕላንትን ጨምሮ ያስገነባቸውን የተለያዩ ፕሮጀክቶች አስመርቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የኦክሲጅን ፍላጎቱን ለመሟላት በዓመት ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ሲያስወጣ መቆየቱን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
አዲስ የተመረቀው የኦክስጂን ፕላንት ከተቋሙ ባሻገር የሌሎች የጤና ተቋማት ፍላጎት የሚያሟላ መሆኑን ገልፀዋል።
@tikvahuniversity
❤ 69👍 9
#ጥቆማ
የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS) በቀጣይ ወር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡
ብሪቲሽ ካውንስል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ'IELTS' ፈተና ህዳር 13/2018 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ይሰጣል፡፡
በዕለቱ ሁለት አይነት የ'IELTS' ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) የሚሰጡ ሲሆን፤ ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች ምዝገባ ተጀምሯል።
ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts
ለተጨማሪ መረጃ፦ 0925629589
@tikvahuniversity
❤ 31😱 1

