68 961
Підписники
Немає даних24 години
-137 днів
-96730 день
Архів дописів
የሚያሳስበኝ
(በእውቀቱ ስዩም)
ዶስተየቨስኪይ የተባለ የሩስያ ደራሲ ልቦለድ ውስጥ የሚገኝ ኢቫን የተባለ ገጸባህርይ ” ሰውን አውሬ ብሎ መጥራት አራዊትን እንደ መስደብ ይቆጠራል ይላል ፤” ሰው የበጎነት አቅም ያለውን ያህል ፥ በጭካኔ የሚወዳደረው የእንስሳ ዝርያ የለም፤ አንበሳ ሚዳቆን የሚገድለው በልቶ ማደር ስላለበት ነው፤ ሳይቸግረው ያለ አላማ መሰሉን፥ የሚገድል፥ ብጤውን በማሰቀየት የሚደሰት ፍጡር ሰው ብቻ ነው፤
ልጅ ሆኜ በጎችን አሰማራ ነበር፤ ግልገል በግ የሚደፍር ትልቅ በግ አይቼ አላውቅም ፤ ወንዱ በግ ፥ደረሰች በግ ላይ ለመውጣት ራሱ ወቅት ይጠብቃል፤ ለርቢ መድረሷን አሽትቶ ካላረጋገጠ በቀር አይደርስባትም፤
የሰባት አመትዋን ሄቨንን ለመስማት በሚገዘገንን ጭካኔ ደፍሮ የገደላትን ሰውየ “ እንስሳ ፥ወይም አውሬ” ብሎ መጥራት ፍትሀዊ የማይሆነው ለዚህ ነው፤ እንዲህ አይነቱ ቀፋፊ ፍጡር የሚገልጽ ሌላ ቅጽል ተፈጥሮ መዝገበቃላት ውስጥ መካተት አለበት፤
ህግ ካለ ይህ ወንጀለኛ እንደ ምግባሩ ፍዳውን መቀበል ይገባዋል፤ እሱ ብቻ ሳይሆን ወንጀሉን ለመሸፋፈን የሞከሩ እና የዶለቱ ሁሉ ከቅጣቱ ድርሻቸውን ማንሳት አለባቸው፤
አስገድዶ ደፈራ በዋናነት የወሲብ ጉዳይ አይደለም፤ የፈሪዎች እና የግፈኞች “ሀይል “ መግለጫ ነው፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሰባ ምናምን አመት ሴት የደፈረ ጎረምሳ በአስራት መቀጣቱን የሚገልጽ ዜና ማንበቤ ትዝ ይለኛል ፤ የሰባ አመት ባልቴት እና የሰባት አመት ሴት ሁለቱም ለሩካቤ የሚያሳስብ ነገር የላቸውም፤ ግን ሁለቱም አንድ የሚያደርጋቸው አቅም አልባ መሆናቸው ነው፤ ራሳቸውን ከደፋሪው መከላከል አይችሉም፤ ደፋሪዎች ብዙ ጊዜ ፈሪዎች ናቸው፤ ከሚበልጣቸው ጋራ ወይም ከእኩያቸው ጋራ ጉልበት እንደማይፈታተሹ ያውቁታል፤ በጉልበት የሚያንሳቸውን፤ ሀብት ስልጣን ወይም ወገን የለውም ብለው የሚያስቡትን ከማጥቃት ግን አይመለሱም፤ ብዙ ጊዜ የጥቃት ሰለባዎችን ስናይ ህጻናት፥ የቤት ሰራተኞች፥ እንግዶች፥ የመንገድ ዳር ተዳዳሪዎች ወይም በጦርሜዳ ላይ ያለ ታዳጊ የቀሩ ሴቶች ናቸው፤
ለወላጆች አንድ የጭንቅ ቀን ምክር አለኝ፤ ጨካኝ ፤ጭቦኛና ቀፋፊ ባህርይ ያላቸው ሰዎች
የትም እና መቼም ይኖራሉ፤ሰርሲ ላንስተር እንደተናገረችው Everywhere in the world they hurt little girls ."
ፈታኝ አለም ውስጥ እንደምንኖር አንርሳ፤ ሁሌም በህግ በፈሪሀ እግዚአብሄር እና በባህል በጭምት ፊት ተማምነህ መዘናጋት የለብህም፤የልጆችህ ወታደር መሆን አለብህ ፤ ልጆችሽን እንደ አይንሽ ብሌን ጠብቂ ! ቀላል እንዳልሆነ አውቃለሁ፤ግን ሌላ ምን አማራጭ አለ?
#share
👍 39❤ 1
እርስ በርሱ የሚጠላለፍ ማህበረሰብ!!
ይኸ ታሪክ የዛሬይቱን ኢትዮጵያ በከፊል የሚያሳይ ሳይሆን አይቀርም
***
“የአንድን ሰው እውነተኛ መለኪያው ማየት ከፈለክ የሚበልጡትን ሰዎች ሳይሆን አቻዎቹንና እንዲሁም የበታቾቹን ሰዎች በምን መልክ እንደሚቀርብ (እንደሚያስተናግድ) ተመልከት” – J. K. Rowling ቶም ራዝ (Tom Rath) እና ዶናልድ ኦ. ክሊፍተን (Donald O. Clifton) “ሃው ፉል ኢዝ ዩር በከት” (How Full Is Your Bucket?) በተሰኘው በጋራ በጻፉት መጽሐፋቸው ውስጥ በርካታ አስገራሚና አስተማሪ ታሪኮችን አስፍረዋል፡፡
ከእነዚህ ተቃሚ ታሪኮች መካከል የኮሪያንና የአሜሪካንን ጦርነት አስመልክቶ ለምሳሌነት የተጠቀሙበት ታሪክ ይገኝበታል፡፡ በኮሪያና በአሜሪካ መካከል የነበረው ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ ዊልያም ሜጀር ኢ. ሜየር (Major William E. Mayer) የተሰኙ የአእምሮ ሃኪም (Psychiatrist) አንድ ሺህ በሚሆኑ በሰሜን ኮሪያ እስር ቤት በነበሩ አሜሪካዊ የጦር ምርኮኞች ላይ አንድን ጥናት አካሄዱ፡፡ ሃኪሙ በተለይም ለማወቅ የፈለጉት ኮሪያኖች በምርኮኞቻቸው በአሜሪካኖች ላይ በውጤታማነት የተጠቀሙበትን ስነ-ልቦናዊ የጦርነት ስልት ለማወቅ ነበር (How Full is Your Bucket, 2005, P. 7-9)፡፡
የአሜሪካ የጦር ምርኮኞች ታስረው የነበሩት የጦር ካምፕ እስር ቤት የአኗኗር ደረጃ ያን ያህል መጥፎ እንዳልነበረ ይታወቃል፡፡ ምርኮኞቹ በቂ ውኃና ምግብ፣ እንዲሁም መሰረታዊ ነገሮች ይሰጣቸው ነበር፡፡ ለምንም አይነት ግርፊያም ሆነ አካላዊ ስቃይ አልተዳረጉም ነበር፡፡ እንደውም በታሪክ ውስጥ እስካሁን ከሚታወቁት የጦር ምርኮ እስር ቤቶች እንደዚያን ጊዜው ያለ እስረኞቹ ምንም አካላዊ ስቃይ ያልደረሰባቸው እስር ቤት አይገኝም ይባላል፡፡
አንድ አንገብጋቢ ጥያቄ ግን የሰውን ሁሉ አእምሮ ወጥሮ ይዞት ነበር፡፡ ለምን ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ የአሜሪካ የጦር ምርኮኞች ካለምክንያት ሞቱ? እስር ቤቱ ምንም አይነት አደገኛ አጥር አልነበረውም፣ በወታደሮችም አልተከበበም ነበር፤ ሆኖም አንድም አሜሪካዊ እስረኛ የማምለጥ ሙከራ እንኳ አድርጎ አያውቅም፡፡ ነገር ግን እነዚህ ተማራኪ ወታደሮች ካለማቋረጥ የአለቃዎቻቸውን ትእዛዝ ይጥሱ ነበር፡፡ እርስ በርሳቸውም ከመጠን በላይ ይጣሉ ነበር፡፡ አንዳንዴ እንደውም ከራሳቸው ወገን ይልቅ ከማረኳቸው ከኮሪያ ወታደሮች ጋር የጠበቀ ወዳጅነትን በመመስረት እርስ በርሳቸው ይበዳደሩ ነበር፡፡
የሞቱት ሞተው የተረፉት ሰዎች ጃፓን የሚገኘው የቀይ መስቀል ጣቢያ ሲረከባቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ስልክ እንዲደውሉ እድሉ ሲሰጣቸው አንዳቸውም እንኳ ስልክን የመደወል ፍላጎት አልነበራቸውም፡፡ ምንም እንኳን በነበሩበት እስር ቤት ምንም አይነት የከፋ አካላዊ ስቃይ ባይደርስባቸው፣ 38 በመቶው እስረኛ እንዲሁ ካለምንም አካላዊ ምክንያት እንደሞተ ይነገራል፡፡
ምክንያቱ ሲመረመር ኮሪያኖቹ የተጠቀሙበትን የመጨረሻና የከፋ የጦር ስልትና መሳሪያ ደረሱበት፡፡ ይህ የመጨረሻ የጦር ስልትና መሳሪያ “አንዱ ከሌላው ጋር ከነበረው የእርስ በርስ ትስስርና ግንኘኙነት የተነሳ ሊያገኝ የሚችለውን የስሜት ድጋፍ መንፈግ” ነበር፡፡ ይህንን ለማድረግ የተጠቀሙባቸው ስልቶች አራት ናቸው፡፡
1.አንዱ በሌላው ላይ መረጃን የማቀበል ስልት
አንድ የአሜሪካ ምርኮኛ የፈጸመውን ጥፋት የራሱ አገር ሰው ለኮሪያኖቹ ሲያሳብቅበት፣ ለአሳባቂው ምርኮኛ እንደ ሲጃራና የመሳሰሉትን ነገሮች በመስጠት ኮሪያኖቹ ያበረታቱት ነበር፡፡
አሳባቂውም ለምን ይህንን የሰው ነገር አሳበክ ተብሎ አይጠየቅም፣ የተሳበቀበትም አሜሪካዊ ለምን ይህንን አደረክ ተብሎ አይቀጣም፡፡ ኮሪያኖቹ ይህንን ያደረጉበት ምክንያት ምርኮኞቹ እርስ በርሳቸው አንዲናናቁ፣ እንዲባሉና ወዳጅነታቸው እንዲበላሽ ለማድረግ ነው፡፡
2.ራስን የመውቀስ ስልት
ይህንን ስልት ለመጠቀም ኮሪያኖቹ ከአስር እስከ አስራ ሁለት የሚሆኑ ምርኮኞችን በአንድ ላይ በማድረግ እያንዳንዱ ምርኮኛ በሌሎቹ የራሱ ሃገሩ ሰው ፊት እየቆመ፣ ከዚህ በፊት ስላደረጋቸው ክፉ ነገሮች፣ እንዲሁም ከዚህ በፊት ማድረግ ሲገባው ስላላደረጋቸው መልካም ስራዎች እንዲናገር ያደርጉት ነበር፡፡
የዚህ ስልት ዋነኛ አላማ ምርኮኞቹ ለኮሪያኖቹ እንዲናገሩ ሳይሆን የራሳቸው ሃገር ሰዎች ክፉ ክፉውን ብቻ እንዲሰሙባቸውና እርስ በርስ እንዲናናቁ፣ ግንኙነታቸው እንዲበላሽና አንዱ በሌላው ላይ ያለው ግምት እንዲወርድ ማድረግ ነው፡፡
3.ለመሪዎቻቸውና ለሃገራቸው ያላቸውን ታማኝነት የማፍረስ ስልት
ይህንን ስልት ተግባራዊ ለማድረግ ኮሪያዎቹ ካለማቋረጥ አንድ የአሜሪካ ምርኮኛ ወታደር አብሮት ለተማረከው አዛዡ ያለውን መታዘዝና አክብሮት የመሸርሸር ዘይቤ ተጠቅመዋል፡፡ ይህ ስልት ስኬታማ እንደነበር የሚያሳዩ በርካታ ሁኔታዎች ተከስተዋል፡፡
ለምሳሌ፣ አንድ ጊዜ አንድ ኮሎኔል ለወታደሮቹ ሩዝ በሚያድግበት ረግረግ መሬት ላይ ያለው ውኃ አደገኛ ባክቴሪያ እንዳለው በመጥቀስ ከዚያ እንዳይጠጡ አዘዛቸው፡፡ አንዱ ወታደር እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “ወዳጄ ሆይ፣ አንተ እኮ አሁን ኮሎኔል አይደለህም፣ እንደ እኔው ተራ እስረኛ ነህ፡፡ አንተ ለራስህ ተጠንቀቅ እኔ ደግሞ ለራሴ አውቅበታለሁ”፡፡ ይህንን ብሎ ውኃውን በጠጣ በጥቂት ቀናት ውስጥ በተባለው ባክቴሪያ ተመርዞ ሞተ፡፡
አንድ ጊዜ ደግሞ 40 የሚሆኑ ምርኮኞች በራሳቸው ጓዶች ከጎጇቸው ተገፍተው ውጪ እንዲሞቱ ሲጣሉ ማንም ምርኮኛ ምንም ነገር ለማድረግ አልሞከረም፣ ምክንያቱም የእርስ በርስ ግንኙነት ተበላሽቶ መናናቅ ስለነገሰ፣ “እኔን አያገባኝም” በሚል ስሜት ተይዘው ስለነበር ነው፡፡
4.አዎንታዊ ስሜትን የሚሰጥን ማንኛውንም ነገር መከልከል
ይህንን ስልት ለመጠቀም ኮሪያዎቹ ያደረጉት ከምርኮኞቹ ምንም አይነት አዎንታዊ ዜናን በመንፈግና አሉታዊውን ብቻ እየመረጡ በማሰማት ነው፡፡ ጥሩ ዜና የያዘ ደብዳቤ ከአገራቸው ሲላክላቸው በፍጹም አይሰጧቸውም ነበር፡፡
የሞተን ዘመድ፣ እሱን ከመጠበቅ ተስፋ ቆርጣ የተወችው የፍቅረኛ ደብዳቤ፣ ያልተከፈለ እዳን አስመልክቶ የሕግ ጥያቄና የመሳሰሉት ተስፋ አስቆራጭ መልእክቶች ግን በፍጥነት እንዲደርሳቸው ይደረግ ነበር፡፡ ምርኮኞቹ ምንም አይነት ተስፋ እስኪያጡ ከመድረሳቸው የተነሳ አንዳንዶቹ ብርድ ልብሳቸውን ተከናንበውና አቀርቅረው በመቀመጥ በዚያው ይሞቱ እንደነበር ይነገራል፡፡
እነዚህ የአሜሪካ ምርኮኞች ያለቀላቸው እርስ በርሳቸው የተናናቁ ጊዜ ነው፡፡ ምንም እንኳ የነበሩበት ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም፣ እርስ በርስ ከመናናቅና ከመጨካከን አንድነታቸውን፣ መከባበራቸውንና መደጋገፋቸውን የበለጠ ሊያጠናክሩ የሚገባቸው ሁኔታ ውስጥ ነበር ያሉት፡፡
በማንኛው ጊዜ፣ ከመለያየት አብሮ መሆን፣ ከመናናቅ መከባበር፣ ከመጨካከን ደግሞ መደጋገፍ ይመረጣልና፡፡ ሆኖም፣ እርስ በርሳቸው ከመናናቃቸው በፊት ሁሉም በመጀመሪያ ራሳቸውን መናቃቸው ግልጽ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ በራሴ ላይ ያለኝ አመለካከት ሲወድቅ በሃገሬ ሰው ላይ ያለኝ አመለካከትም አብሮ ይወርዳል፡፡ ራሴን ያየሁበት እይታዬ ወገኔን በዚያው መልክ እንዳይ የማስገደድ ባህሪይ አለው፡፡
“የማንነትህ መለኪያ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተወሰደ
ምንጭ-news .et ገፅ
#share
👍 43❤ 10👏 6
የመኖር ጥበብ
በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። ታዲያ ይህ ሰው፣ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በኑሮው ከሚገጥመው ችግር የተነሳ፣ ሁልጊዜም በህይወቱ ደስተኛ አልነበረም።
አንድ ቀን ግን ከሚኖርበት ሥፍራ በቅርብ ርቀት የምትገኝ ከተማ ዘንድ፣ አንድ ታላቅ የኃይማኖት አባት ከአጃቢዎቻቸው ጋር እንደመጡ ይሰማል። ይህን ጊዜም እኚህን አባት ማግኘት አለብኝ ብሎ ይወስናል።
በመሸም ጊዜ እኚህ አባት ያሉበት ሥፍራ ይደርስና፡ እሳቸውን ለማግኘት ቁጭ ብሎ መጠባበቁን ይይዛል። ከረጅም ቆይታ በኋላም እኒያን አባት ያገኝና ጥያቄውን ይጀምራል።
"አባቴ፥ በህይወቴ ፍፁም ደስተኛ አይደለሁም፤ በቃ ሁሌም በችግር የተከበብኩኝ ሰው ነኝ... በዚህ በኩል የሥራ ጭንቀት፣ በዚህ ደግሞ የጤና ቀውስ፣ በዛላይ የቤቴ ውስጥ ችግር... ብቻ ተደማምሮ እረፍት ነስቶኛል፣ ደስታም ርቆኛል፤ እባክዎትን አንዳች የመፍትሄ ሀሳብ ይስጡኝና፡ ደስተኛና የሰላም ኑሮ እንድኖር ይርዱኝ!"
ሽማግሌውም ፈገግ ብለው "ልጄ፥ ለችግርህ ነገ ጠዋት ላይ መፍትሄ እሰጥሃለሁ፤ ነገር ግን አሁን ባዝህ፣ ጥቂት የኔን ሥራ ልትሠራልኝ ትችላለህን?" አሉት። ሰውዬውም በዚህ ይስማማል።
እሳቸውም ቀጥለው፦ "በጉዞአችን የያዝናቸው መቶ ግመሎች በዚህ ይገኛሉ፤ እናም ዛሬ ምሽት የነርሱን ነገር አደራውን ላንተ ሰጥቻለሁ፤ ሁሉንም ግመሎች እመሬት ላይ ካስቀመጥክ በኋላ ወደ መኝታ መሄድ ትችላለህ"። አሉት።
ይህንንም ብለው ወደ ድንኳናቸው ሲያቀኑ፣ ሰውዬውም የታዘዘውን ሊያደርግ ምሽቱን ግመሎቹ ዘንድ አመራ።
በቀጣይ ቀንም ሽማግሌው ማልደው ወደ ሰውዬው በማቅናት "ልጄ፥ ሌሊቱን ጥሩ ተኝተህ አደርክ?" ብለው ይጠይቁታል።
ሰውዬው ግን ኅዘን በተሞላበት ስሜት ሆኖ "አባቴ፥ ለዐፍታ እንኳን እንቅልፍ ሳይወስደኝ ነው ሌሊቱ የነጋው። ብዙ ለፋሁ፣ ብዙም ጣርኩኝ፡ ይሁንና በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች እንዲቀመጡ ማድረግ አልቻልኩም። አንዳንዶቹ ራሳቸው ይቀመጣሉ፤ አንዳንዶቹ ግን ላስቀምጣቸው ብሞክርም እንኳን አይቀመጡም፤ አንዱ በዚህ በኩል ሲቀመጥ፡ በሌላ በኩል ያሉት ይነሣሉ"።
ይህን ጊዜ ሽማግሌው ፈገግ እያሉ እንዲህ አሉ፦ "ካልተሳሳትኩኝ፡ ይህ የሆነው ትላንት ማታ ነው አይደል?"
- ራሳቸውን በራሳቸው ያስቀመጡ ብዙ ግመሎች ነበሩ!?
- ብዙዎቹ ደግሞ በአንተ ጥረት ሊቀመጡ ችለዋል!?
- ቀሪዎቹ ልታስቀምጣቸው ሞክረህ እንኳን አልተቀመጡም፤ ከቆይታ በኋላ ግን በጊዜ ውስጥ ራሳቸውን አስቀምጠው አግኝተሃቸዋል!?
ሰውዬውም፦ "አዎ! አዎ!...ትክክል!" ብሎ መለሰ።
ሽማግሌውም ቀጠሉና፦
"ስለዚህ አሁን አንድ ነገር ተረዳህን?፤ በህይወት ያሉም ችግሮች እንዲሁ ናቸው...
- አንዳንዶቹ በራሳቸው መፍትሄ ያገኛሉ።
- አንዳንዶቹ በአንተ ጥረት መፍትሄ ያገኛሉ።
- አንዳንዶቹ ደግሞ በአንተ ጥረት እንኳን አይፈቱም፤ እነዚህን ችግሮች ለጊዜ ተዋቸው። ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ በራሳቸው ይፈታሉና/መፍትሄ ያገኛሉና/።
ትላንት ማታ፣ ምን ያህል ብትሞክር በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች ማስቀመጥ እንዳልቻልክ ትምህርት ወስደሃል። አንዱን ግመል በዚህ ጋር ስታስቀምጥ በሌላ በኩል ያሉት ይነሣሉ። ልክ እንዲሁ፤ እዚህ ጋር አንዱን ችግር ፈታሁ/ተፈታ ስትል እዛ ደግሞ ሌላ ችግር ተነስቶ ይጠብቅሃል። ህይወት እንዲህ ነውና!። ችግሮች የህይወት አካል ናቸው፤ አንዳንድ ጊዜ ጥቂት፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ በርካታ ችግሮች ይኖራሉ። ይሄ ማለት ግን ስለነሱ ሁሌ ማሰብ አለብህ ማለት አይደለም። እነሱን ለጊዜ እየተወክ ወደፊት ተጓዝ። በእያንዳንዱ እርምጃም ወደ ዓላማ-ህይወት (Purpose of life/self- realization/) ማደግን ተማር።
ልብ በል፤
• አንዳንድ ጊዜ፤ ደስታን ለማወቅ በኅዘን፣ ዝምታን ለማድነቅ በጩኸት፣ የመኖርን ዋጋ ለማወቅ ባለመኖር መንገድ ልታልፍ ግድ ነው።
ይኸውልህ፤ ህይወት በተቃርኖ የተሞላች ነች። እያንዳንዱ ስኬት ከሸክም ጋር ነው የሚመጣው። ትልቅ ቤት ማግኘት ስኬት ሲሆን፣ ብዙ የሚጸዳ መኖሩ ሸክም ነው። ልጅ መውለድ ስኬት ሲሆን፣ በእኩለ ሌሊት መነሳቱ ሸክም ነው። ባለስልጣን መሆን ስኬት ሲሆን፣ የህዝብን ጩኸት ማስተናገዱ ሸክም ነው።
ብዙ ጊዜ የምንሠራው ስህተት- ስኬቱን ያለ ሸክም ከመፈለግ የሚመጣ ነው። ይህ ግን እውነታው አይደለም። የሚመጡት በጥቅል (package) ነው። ዋናው ነገር፣ ሸክሙም እያለ በስኬቱ/በበረከቱ መደሰትን መማሩ ላይ ነው!!
(በሳሙኤል ገዳ)
👍 73❤ 39👏 8🙏 8
ውድ እወድሻለሁ!
ጋሽ ገ/ ክርስቶስ ደስታን ውድ እወድሻለሁ በሚል የፃፈው ግጥም እልፍ ዘመን አልፎም አይጠገብም። ሚካኤል በላይነህ በዜማ አዋዝቶ አሰምቶናልም፣ በውቀቱ ስዩምም በራሱ መንገድ ስራውን ተንተርሶ በማለዳ ድባብ መድብሉ ውስጥ አካቶ ዘናጭ ስራ አስነብቦናል። ታዲያ ለምን እንደየሃሳባችን አንቀጥልበትም?
እናንተም በራሳችሁ መንገድ ልት ቀጥሉበት ትችላላችሁ።
---
እኔ እወድሻለሁ
እንደ ብራና ፅሁፍ
ጥልቅ ምስጢር ይዞ
የተማሪውን አይን
ሌት ተቀን አፍዝዞ
እንደሚይዝ ቅኔ
እኔ እወድሻለሁ !
እንደ ግሩም ቃላት
እንደ ስኬታቸው
እንደመግጠማቸው
ስሜትን ሰብስበው
ቀልብን ሁሉ ስበው
ንጉስ ከዙፋኑ
እንደማውረዳቸው
ሎሌውን ከትቢያ
እንደማንሳታቸው
እኔ እወድሻለሁ!
እንደ ጥሩ መፅሃፍ
ካ‘ለም ነውጥ የሚያርቅ
ከዱኒያ ጋራ የተጣላ ነፍስን
በውል የሚያስታርቅ
ኢማን ቀሊል ውሎን
በትኖ እንደጉም
አውድና ህይወትን
መልሶ ሚገጥም
ልክ እንደዚያ ጥራዝ
ላነብሽ እሻለሁ
ስወድሽ …ስወድሽ…
ውድ እወድሻለሁ!
----
👍 64❤ 21👏 1😢 1
ችግር ላይ የማላገጥ ፖለቲካ....
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
በዘጠናዎቹ መጀመሪያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ መንግስት የታጠቀ ሰራዊት አስፍሮ ነበረ። ተማሪዎች ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ ግቢ ውስጥ በሰፈረው የመንግስት ሃይል ተደበደቡ። የጥቃት ኢላማ ሆኑ። ይህም ቁጣ ቀስቅሶ ገነት ዘውዴ የምትመራው ስብሰባ በዩኒቨርስቲው ተካሄደ። ይሄኔ መንግስት ለየት ያለ ድራማ አዘጋጀ።
ተማሪዎች ቁጣቸውን በአግባቡ እንዳይገልጡ የሚያደርጉ ሰዎች ተመለመሉ። የምልምሎቹ ዋነኛ ሃላፊነት የነበረው ትልልቅ ጥያቄዎችን በፌዝ መልክ ማለዘብ ነው። በስብሰባው ላይ አስተያየት እንዲሰነዝሩ እድል ሲሰጣቸው በአጀንዳው ዙሪያ ቀልድ አዘል ንግግር ያደርጋሉ።
ብርሃኑ ደቦጭ 'የድንቁርና ጌቶች' በተሰኘ መፅሐፉ ይህን የሚያሳይ ምሳሌ አካቷል። አንድ ተማሪ እንዲናገር እድል ሲሰጠው "ታህሳስ ላይ ፖሊሶች ደበደቡን። በሚያዚያም ድጋሚ ደበደቡን። ድብደባ እንደ አንድ ኮርስ መስጠት ቢጀመር'' አይነት ወሬ አወራና ታዳሚው ሳቀ።
የዚህ አይነቱ ድርጊት ዋነኛ አለማ ትልቁን አጀንዳ በቀልድና ፌዝ በማለዝብ የተማሪዎቹ ጥያቄ ተገቢውን ትኩረት እንዳያገኝ ማድረግ ነበረ። በወቅቱ በትልቁ ችግር ዙሪያ የመቀለድ ስውር ተልእኮን ከመንግሥት በመቀበል ከተማሪዎቹ ጋ ተመሳስለው ወደ ስብሰባው የገቡ ልጆች ግዴታቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል።
ዛሬ ላይ የኑሮ ውድነቱ ላይ እጅግ የተጋነነ ማላገጥ በሶሻል ሚዲያ እየተመለከትን ነው። በችግር መቀለድ ጥሩ ነው። ሰው ሞቶ በድንኳን ውስጥ እንኳ ሳቅ እና ጨወታ አለ። ሀዘንን የሚያለዝብ ፥ ብሶትን የሚያስታግስ ጨወታ ያስፈልጋል። ሲበዛ ግን አግባብነት አይኖረውም።
እስከመቼ በቁስላችን እንስቃለን? በገዛ ሀዘናችን እየተሳለቅን የምንዘልቀው እስከምን ድረስ ነው? ከእንባችን ሳቅ መቅዳት የምናቆምበት ቀን አይናፍቀንም?
አንገብጋቢና አሳሳቢ የሆኑ ብሔራዊ ችግሮቻችን እንደ ተራ ጉዳይ እየተቀለደባቸው ክብደታቸውን እያጡ ነው። ይህ እንዴት ሆነ ብሎ ለመጠየቅ ጊዜው አሁን ነው
@Tfanos
👍 74👏 5❤ 3
ወዴት ነህ ይለኛል፣
ሊያሳፍረኝ ታክሲ፣
ሊጭነኝ ወያላ፤
እኔና ሀገሬ፣
እኔድበት መንገድ፣
ግብ እንዳለን ሁላ!
/ይስማዕከ ወርቁ/
👍 58🔥 5👏 2🤔 2😢 1
ፓሊሲው ማሻሻያ ተግባራዊ ከሆነ ሳምንት ተቆጥሯል።
ስጋቶች ከየአካባቢው እየተነሱ ነው።
አንዱ የስጋት ምንጭ የሆነው በገቢ እቃዎች ላይ የታየው የዋጋ ንረት ነው።
የችግሩ ምንጭና መፍትሔውን በጋራ እንመልከተው።
ነጋዴው ድሮም እቃ የሚያስመጣው በጥቁር ገበያ ተመን ነበር። እንዲያውም አሁን ላይ ከጥቁር ገበያ ባነሰ የዶላር ተመን የማስመጣት እድል እየተፈጠረለት ነው።
የምንዛሪ ዋጋ ለውጥ ከሌለ የእቃ ዋጋ ለምን ይጨምራል ? የሚል መከራከርያ በስፋት እየተሰማ ነው።
ይህ አቀራረብ ሁለገብ ምልከታ የጎደለው ስለሆነ ወደ ተረጋጋ መፍትሔ የሚወስድ አይመስለኝም።
በመጀመርያ ነጋዴው የሚያስመጣው ቁሳቁስም ሆነ ሸቀጥ 100% ከጥቁር ገበያ በሚገኝ የውጭ ምንዛሪ የሚገዛ አይደለም።
ሁለተኛ ነጋዴው ሚያስመጣው እቃ ዋጋ የሚወሰነው ጉምሩክ ባዘጋጀው የእቃዎች የዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ተመስርቶ ሲሆን ቀረጥ የሚከፍለው ደግሞ የብሔራዊ ባንክ የእለቱን የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት በማድረግ ነው።
ይህ ማለት ነጋዴው ከሳምንት በፊት በ100 ዶላር ለጫነው እቃ ቀረጥ የሚከፍለው በወቅቱ በነበረው የብሔራዊ ባንክ የአንድ ዶላር ተመን ብር 57.5 ተሰልቶ ሲሆን ዛሬ ላይ ቢጭን ደግሞ በባንኮች በሚያወጡት የውጭ ምንዛሪ አማካይ ተመን ላይ ተመስርቶ በሚሰላ ዋጋ 100 ብር ገደማ ነው።
ይህ ማለት የቀረጥ መጣያ ዋጋው በእጥፍ ጨምሯል ማለት ነው። ' ዋጋ ቀንስ ' ብቻ ሳይሆን ነጋዴው በተመን ለወጥ ምክንያት የተፈጠረበትን የቀረጥ ጭማሪ እንዴት ይሸፍን የሚለው ጥያቄ መመለስ ይስፈልጋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊታሰብበት የሚገባው ፦
° የአውሮፕላን ትኬት፣
° ኢንሹራንስ፣
° የጭነት ዋጋ፣
° የኮንቴይነር ኪራይ በእቃዎች ዋጋ ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም።
ቀስ በቀስ በደሞዝና በድጎማ መልክ ወደ ኢኮኖሚው የሚፈሰው ገንዘብም አቅርቦትና ፍላጎትን በማዛባት ግሽበትና የዋጋ ንረት ማስከተሉ የሚጠበቅ ነው።
ሌላው የውጭ ምንዛሪ ግብይት በነጻ የገበያ ውድድር የሚመራ ከሆነ የእቃ ዋጋም ያለማንም ጣልቃ ገብነት ገበያው ውስጥ በሚኖረው አቅርቦት፣ ፍላጎትና የመተኪያ ዋጋን መሰረት አድርጎ መመራት አለበት። ይህ የተሻለው የዋጋ ማረጋጊያ መንገድ ነው።
በተቃራኒው በመመርያና በአስተዳደራዊ እርምጃ የሚተመን ዋጋ የግብይትና የአቅርቦት ስርዓትን በማፋለስ፣ የጥራት ጉድለትና የዋጋ ንረት በአጠቃላይ የገበያ ውጥቅጥን ማባባሱ የሚጠበቅ ነው።
በአስተዳደራዊ ውሳኔ አከፋፋዩም ሆነ ቸርቻሪው ዛሬ እጁ ላይ ያለውን ምርት በውሳኔው ዋጋ አጣርቶ ሊሸጥ ይችላል።
እጁ ላይ ያለው ምርት ካለቀ በኋላ ግን ነጋዴው እንደሚከስር እያወቀ እቃ ለማስመጣትም ሆነ ለማከፋፈል ፍላጎት እንደማይኖረው ግልጽ ነው። ይህ ደግሞ የእቃ እጥረትና ተጨማሪ የዋጋ ንረት/ግሽበት ፣ እቃ መሰወር፣ ጥራት የጎደለው ምርት ማቅረብና ለኮንትሮባንድ ንግድ መጋለጥን ሊያስከትል ይችላል።
ጊዜያዊ በሆኑ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና በሙስና በተጨማለቁ ደንብ አስከባሪዎች ማዋከብ ነጋዴው ማህበረሰብ ስጋት እንዳያድርበት፣ እንዳይበረግግና ከገበያው እንዳይወጣ፣ በዚህ ምክንያትም ገበያው ይበልጥ እንዳይታወክ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
ከአቅራቢ፣ ከአከፋፋዩና ከቸርቻሪው ጋር በየደረጃው በመወያየት ነባራዊ ሁኔታውን በማስጨበጥ ስግብግብነት ካለም በእንጭጩ በመግታት የነጋዴውንም ችግር በዛው ልክ በመረዳት ነጋዴውን የችግሩ መንስኤ ሳይሆን የመፍትሔው አካል ማድረግ ዘላቂ ጥቅም አለው። "
#MusheSemu
👍 59❤ 4🤣 2🔥 1
ፓሊሲው ተግባራዊ ከሆነ ሳምንት ተቆጥሯል። ስጋቶች ከየአካባቢው እየተነሱ ነው። አንዱ የስጋት ምንጭ የሆነው በገቢ እቃዎች ላይ የታየው የዋጋ ንረት ነው። የችግሩ ምንጭና መፍትሔውን በጋራ እንመልከተው።
ነጋዴው ድሮም እቃ የሚያስመጣው በጥቁር ገበያ ተመን ነበር። እንዲያውም አሁን ላይ ከጥቁር ገበያ ባነሰ የዶላር ተመን የማስመጣት እድል እየተፈጠረለት ነው። የምንዛሪ ዋጋ ለውጥ ከሌለ የእቃ ዋጋ ለምን ይጨምራል የሚል መከራከርያ በስፋት እየተሰማ ነው። ይህ አቀራረብ ሁለገብ ምልከታ የጎደለው ስለሆነ ወደ ተረጋጋ መፍትሔ የሚወስድ አይመስለኝም።
በመጀመርያ ነጋዴው የሚያስመጣው ቁሳቁስም ሆነ ሸቀጥ 100% ከጥቁር ገበያ በሚገኝ የውጭ ምንዛሪ የሚገዛ አይደለም። ሁለተኛ ነጋዴው የሚያስመጣው እቃ ዋጋ የሚወሰነው ጉምሩክ ባዘጋጀው የእቃዎች የዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ተመስርቶ ሲሆን ቀረጥ የሚከፍለው ደግሞ የብሔራዊ ባንክ የእለቱን የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት በማድረግ ነው።
ይህ ማለት ነጋዴው ከሳምንት በፊት በ100 ዶላር ለጫነው እቃ ቀረጥ የሚከፍለው በወቅቱ በነበረው የብሔራዊ ባንክ የአንድ ዶላር ተመን ብር 57.5 ተሰልቶ ሲሆን ዛሬ ላይ ቢጭን ደግሞ በባንኮች በሚያወጡት የውጭ ምንዛሪ አማካይ ተመን ላይ ተመስርቶ በሚሰላ ዋጋ 100 ብር ገደማ ነው።
ይህ ማለት የቀረጥ መጣያ ዋጋው በእጥፍ ጨምሯል ማለት ነው። ዋጋ ቀንስ ብቻ ሳይሆን ነጋዴው በተመን ለወጥ ምክንያት የተፈጠረበትን የቀረጥ ጭማሪ እንዴት ይሸፍን የሚለው ጥያቄ መመለስ ይስፈልጋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊታሰብበት የሚገባው የአውሮፕላን ትኬት፣ ኢንሹራንስ፣ የጭነት ዋጋ፣ የኮንቴይነር ኪራይ በእቃዎች ዋጋ ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም። ቀስ በቀስ በደሞዝና በድጎማ መልክ ወደ ኢኮኖሚው የሚፈሰው ገንዘብም አቅርቦትና ፍላጎትን በማዛባት ግሽበትና የዋጋ ንረት ማስከተሉ የሚጠበቅ ነው።
ሌላው የውጭ ምንዛሪ ግብይት በነጻ የገበያ ውድድር የሚመራ ከሆነ የእቃ ዋጋም ያለማንም ጣልቃ ገብነት ገበያው ውስጥ በሚኖረው አቅርቦት፣ ፍላጎትና የመተኪያ ዋጋን መሰረት አድርጎ መመራት አለበት። ይህ የተሻለው የዋጋ ማረጋጊያ መንገድ ነው። በተቃራኒው በመመርያና በአስተዳደራዊ እርምጃ የሚተመን ዋጋ የግብይትና የአቅርቦት ስርዓትን በማፋለስ፣ የጥራት ጉድለትና የዋጋ ንረት በአጠቃላይ የገበያ ውጥቅጥን ማባባሱ የሚጠበቅ ነው።
በአስተዳደራዊ ውሳኔ አከፋፋዩም ሆነ ቸርቻሪው ዛሬ እጁ ላይ ያለውን ምርት በውሳኔው ዋጋ አጣርቶ ሊሸጥ ይችላል። እጁ ላይ ያለው ምርት ካለቀ በኋላ ግን ነጋዴው እንደሚከስር እያወቀ እቃ ለማስመጣትም ሆነ ለማከፋፈል ፍላጎት እንደማይኖረው ግልጽ ነው። ይህ ደግሞ የእቃ እጥረትና ተጨማሪ የዋጋ ንረት/ግሽበት ፣ እቃ መሰወር፣ ጥራት የጎደለው ምርት ማቅረብና ለኮንትሮባንድ ንግድ መጋለጥን ሊያስከትል ይችላል።
ጊዜያዊ በሆኑ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና በሙስና በተጨማለቁ ደንብ አስከባሪዎች ማዋከብ ነጋዴው ማህበረሰብ ስጋት እንዳያድርበት፣ እንዳይበረግግና ከገበያው እንዳይወጣ፣ በዚህ ምክንያትም ገበያው ይበልጥ እንዳይታወክ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
ከአቅራቢ፣ ከአከፋፋዩና ከቸርቻሪው ጋር በየደረጃው በመወያየት ነባራዊ ሁኔታውን በማስጨበጥ ስግብግብነት ካለም በእንጭጩ በመግታት የነጋዴውንም ችግር በዛው ልክ በመረዳት ነጋዴውን የችግሩ መንስኤ ሳይሆን የመፍትሔው አካል ማድረግ ዘላቂ ጥቅም አለው።
© ሙሼ ሰሙ
Repost from TgId: 1163708603
የሊነጋ ሲል ይጨልማል ስህተት
(The " It will get worse before it gets better" fallacy")
🌗ከጥቂት አመታት በፊት ለሽርሽር በሄድኩበት ከተማ እያለሁ ታመምኩ። የበሽታው ምልክቶች ለእኔ አዲስ ሆኑብኝ፤ ህመሙም በየቀኑ እየጨመረብኝ ሄደ፡፡ በመሆኑም በአካባቢው ካለ የጤና ክሊኒክ እርዳታ ለመጠየቅ ወሰንኩና ሄድኩ፡፡ እንደደረስኩ ያገኘሁት ወጣት ሀኪም ይመረምረኝ ጀመረ። ሆዴን እያሻሸ፣ ጉልበቴን እና ትከሻዬን እየሳበና የጀርባ አጥንቶቼን እየደባባሰ ምርመራውን ቀጠለ፡፡ በሽታዬ ምን እንደሆነ መገመት እንኳን እንዳልቻለ ጠረጠርኩ፡፡ እርግጠኛ ግን አልነበርኩምና ይህን አዲስ ምርመራ ተቋቁሜ ዝም አልኩ፡፡ መጨረሻውን ለማብሰር በሚመስል ሁኔታ ማስታወሻውን አወጣና ‹‹አንቲ ባዮቲክስ በቀን ሶስት ጊዜ አንዳንድ ፍሬ ውሰድ። ሊሻልህ ሲል ሊብስብህ ይችላል፡፡›› አለኝ፡፡ አሁን ታክሜያለሁ በሚል ደስታ ከመድኃኒቶቼ ጋር ወደያዝኩት ሆቴል ተመለስኩ፡፡
🌘ህመሙ ግን እየጨመረ በሚሄዱ ሁኔታ እየባሰብኝ ሄደ - ልክ ዶክተሩ እንደገመተው። እውነትም ዶክተሩ ችግሬ ምን እንደሆነ በሚገባ ተረድቶት ይሆናል። በሶስት ቀን ውስጥ አልቀንስልህ ሲለኝ ግን ደወልኩለት፡፡ በቀን የምትውጠውን ክኒን ወደ አምስት ከፍ አድርገው።ያው ለተወሰነ ጊዜ ትንሽ ያምሃል›› አለኝ፡፡ ከተጨማሪ ሁለት የስቃይ ቀናት በኋላ አንቡላንስ ጠራሁ። የስዊዙ ዶክተር በጥድፊያ መርምሮች ትርፍ አንጀት እንደሆነ አውቆ ቀዶ ጥገናውን ካደረገልኝ በኋላ፡
‹‹ይሄን ያህል ለምን ዘገየህ?› አለኝ፡፡
«እየሆነ የነበረው በሙሉ ልክ ዶክተሩ እንደነገረኝ ስለነበረ አምኜው ነበር» አልኩት፡፡
እሱም ቀጠል አደረገና ««ኦህ የሊነጋ ሲል ይጨልማል ስህተት ሰለባ ሆነሃላ፡፡ ያ የክሮሲካ ዶክተር ምንም የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ በእርግጠኝነት ባንተ ላይ የሆነው ነገር በሌሎች በብዙ ቱሪስቶችም ላይ ሆኗል› አለኝ፡፡
🌗ሌላ ምሳሌም እንመልከት። አንድ የድርጅት ስራ አስኪያጅ የሆነ ሰው በድርጅቱ ስራ መቀነስ ምክንያት አብዝቶ ይጨነቃል፡፡ የሽያጭ ሰራተኞቹ ስራ ተነሳሽነትም ይወድቃል። የሽያጭ ማነቃቂያ ዘመቻ ቢያስደርግም ምንም ውጤት ሳያመጣ ይቀራል። ለዚህ ችግር መፍትሄ ለመፈለግ በማሰብ በቀን 5,000 ብር የሚከፍለው አማካሪ ለመቅጠርና ችግሩን ለመፍታት ወሰነ፡፡ አማካሪውም መጠነኛ ምርመራ ካደረገ በኋላ
ሽያጭ ክፍሉ ምንም ራዕይ የለውም፡፡ ብራንድህም በግልፅ አልተሰረዘም፡፡ ትንሽ የተወሳሰበ ነገር ነው። ላስተካክለው እችላለሁ፤ ነገር ግን ባንድ ምሽት የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ለማስተካከል የሚወሰዱት ነገሮች ጠንከር ያሉም ስለሚሆኑ ችግሩ ከመቀረፉ በፊት የሽያጭ መዳከሙ የተወሰነ ሊብስበት ይችላል›› የሚል ሪፖርት ለስራ አስኪያጁ አመጣለት፡፡
🌒ስራ አስኪያጁም ሪፖርቱን ከተመለከተ በኋላ አማካሪውን ቀጠረው። ከዚያ በኋላ ባለው ሂደት የተቀጠረው አማካሪ ድርጅቱ እንደገመተው እየሄደ እንደሆነ እየደጋገመ ተናገረ። የሽያጭ ድቀቱ ግን ለቀጣዮቹ ሶስት አመት ሊስተካከል አልቻለም፡፡ ስራ አስኪያጁም አማካሪውን አባረረው፡፡
🔱ይህ የሊነጋ ሲል ይጨልማል ስህተት የማረጋገጥ መድልዖ አንድ ዝርያ ነው፡፡ ችግሩ እየባሰበት ከሄደ የተገመተው ነገር ተረጋገጠ ማለት ነው፡፡ ችግሩ ባንድም በሌላ ምክንያት ከተስተካከለ ደግሞ ደንበኛው ደስተኛ ስለሚሆን ክብርና አድናቆትን ያተርፉበታል። ባለሞያው በሁለቱም መንገድ ያሸንፋል ማለት ነው፡፡
🌓ለምሳሌ አንተ የሃገርህ ጠቅላይ ሚኒስተር ነህ እንበል። ሃገሪቱን እንዴት መምራት እንዳለብህ ምንም እውቀት እንደሌለህም እናስብ። ምንድን ነው የምታደርገው? ‹‹ከፊታችን ‹ከባድ አመታት ይጠብቁናል» ብለህ ዜጎች ቀበቷቸውን እንዲያጠብቁ ትጠይቃለህ፡፡ ከዚያም ከዚህ ሁሉ ችግርና ውጥንቅጥ በኋላ ወደ ጥሩ ሁኔታ እንደምትመልሳቸው ቃል ትገባለህ፡፡ በዚህ መንገድ የችግሩን መቆያ ጊዜ እና የችግሩን የግዝፈት መጠን ክፍት አድርገህ ትተዋለህ፡፡ ከዛም የከፉ ችግሮች ሲከሰቱ... ያለስቃይ የሚሆን ነገር የለም መጪው ጊዜ ብርሃናማ ይሆናል እያልክ የስልጣን ጊዜህን ታራዝማለህ ማለት ነው።
🔥" ሊነጋ ሲል ይጨልማል " ወይም "ሊሻሻል ሲል ይብስበታል " የሚሉ ሀሳቦች ሲነገሩ አስተውል!! ነገሮች መጀመሪያ ወድቀው ከዚያ የሚሻሻሉባቸው ሁኔታዎች ቢኖሩም ተጨባጭ ምክንያቶች ሊኖራቸው ይገባል።አንዳንድ ፖለቲከኞች ሊያሰተካክሉት የማይችሉት ከፍተኛ የፖለቲካ ወይም የኢኮኖሚክ ቀውስ ሲከሰት ይህ ችግር ሀገሪቷን ያጠነክራታል ጨለማው የበረታው ሊንጋ ስለሆነ ነው ሲሉ ይስተዋላል ወዳጄ መሰራት ያለበት ስራ እስካልተሰራ ድረስ ጨልሞም ሊቀር ይችላልና አሰተውል ይህ የሊነጋ ሲል ይጨልማል ስህተት
(The " It will get worse before it gets better" fallacy") ነው።
ሮልፍ ዶብሊ
The art of thinking clearly
@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍 54👏 11❤ 4
"ህይወት የልቧን የሚዘምርላት ስታጣ የአዕምሮዋን (የሀሳቧን) አውጥቶ የሚናገር ፈላስፋ ትፈጥራለች።"
ካህሊል ጂብራን
“ለውጥን አስተናግዱ፡፡ ነገር ግን ቀስ በቀስ አድርጉት፣ ምክንያቱም አቅጣጫ ከፍጥነት የበለጠ አስፈላጊ ነውና”
ፓውሎ ኮውሎ
“ስህተት ከአንድ ጊዜ በላይ ሲደጋገም ወደ ምርጫ ቀጠና ይገባል”
ፓውሎ ኮውሎ
" የእሾህ አክሊል የሚሰሩ እጆች ሳይቀሩ ስራ ከፈቱ እጆች ይሻላሉ ። "
ካህሊል ጂብራን
❤ 44👍 32😢 1
ናይጄሪያ ልክ እንደ ኢትዮጵያ መንግሥት የ IMFን ምክረሀሳብ ተቀብላ የዶላር ዋጋን በገበያው እንዲተመን (Floating exchange) ውሳኔ ያሳለፈችው በቅርቡ ነበር፣በዚህም የናይጄሪያ መገበያያ የሆነው ኒያራ የመግዛት አቅሙ ተንኮታኩቶ ዛሬ አንድ ዶላር 1,595 ኒያራ ይመነዘራል። በዚህ የተነሳ ህዝቡ ኑሮ አስቸጋሪ ሆነ፣ሩዝ ከ50% እስከ 100% ጨመረ፣የሀገሪቱ መንግሥት ይህን ለማረጋጋት ደመወዝ ጨመረ፣ነዳጅን በድጎማ አቀረበ ግን መፍትሔ አላመጣም።
የናይጄሪያ መገበያያ ገንዘብ በእጅጉ በመዳከሙ ኑሮ ሰማይ ወጣ፣ርሀብ ተስፋፋ፣ይባስ ብሎ የነዳጅ ድጎማውን መንግስት አነሳ ቀውሱ ተባባሰ፣ህዝቡ አሁን በአደባባይ ተቃውሞ ወጥቷል(አዩዘሀበሻ)።
==≠===============≠===
👍 75😢 16🔥 3🤔 3❤ 2
Repost from ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
ቁጥሮች ይናገራሉ!
- ከሰሞኑ ከአለም አቀፍ የአበዳሪ ተቋማት በብድርና ጥቂቱ ደግሞ በድጋፍ ሊሰጠን ታስቦ ያለው የገንዘብ መጠን 10.7 ቢልዮን ዶላር ነው።
- በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ያጋጠመው የውድመት መጠን ሲገመት 28 ቢልዮን ዶላር ነው
- በመጪዎቹ አምስት አመታት ብቻ ለመልሶ ግንባታ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን 20 ቢልዮን ዶላር ነው
ይህ እንግዲህ በገንዘብ የማይተመነውን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የሞቱ፣ የአካል ጉዳተኛ የሆኑ እና ለተለያዩ ፆታዊ፣ ስነ ልቦናዊ ወዘተ የተዳረጉ ዜጎችን ጉዳት ሳይጨምር ነው።
እንደገና ይህ ቁጥር አሁን ድረስ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የቀጠለው ጦርነት እያስከተለ ያለውን ውድመት ሳያካትት ነው።
ወደ ውጭ ሀገራት ምርት ልከው ዶላር ያስገኙ የነበሩ በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ አምራች ኢንደስትሪዎች፣ እንደ AGOA ካሉ እድሎች ያመለጡን የውጭ ንግድ እድሎች፣ በበርካታ #NoMore ጫጫታዎች ተሸፍነው ማምረቻቸውን ዘግተው የወጡ የውጭ ፋብሪካዎች... ወዘተ ሲታሰብ እና አሁን በአበዳሪዎች እጅ የወደቅንበት ሁኔታ ያስቆጫል።
አሁንም ሰላምን አስፍኖ የቤትን ገበና መሸፈን ካልተቻለ ውጤቱ በሌሎች እጅ በበለጠ ሁኔታ መውደቅ ነው። ነገሩ "ባለቤቱ ያላከበረውን አሞሌ..." አይነት ሆኗል።
@EliasMeseret
👍 67❤ 10
ዲሲፕሊን!
“በምታልሙት ሕልም እና በእጃችሁ ሊገባ በሚገባው እውነታ መካከል ያለው ርቀት መጠሪያ ስሙ ዲሲፕሊን ይባላል” (Paulo Coelho)
ዲሲፕሊን የሌለው ሕልም፣ በምንም ያህል ተነሳሽነት (motivation) ቢጀመርም ከቅዠት ቀጠና አልፎ የመሄድ አቅም የለውም፡፡
ዶ/ር እዮብ ማሞ
👍 79👏 7😢 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Sun Tsu The Art of War summary
@human_intellegence
❤ 9👍 4👏 2
"የዘመን ሩጫ"
* * *
ቅጠል እንደ እንጀራ ፥ እየተጋገረ
ቆርኪ እንደ ሲኒ ፥ እየተቆጠረ
ጨቅላ እንዳ'ዋቂ ፥ እየተሞሸረ
በክላሽ አምሳያ፥ ኮባ ተበጃጅቶ
ከወረቀት ቁራጭ ፥ መርከብ ተዘጋጅቶ
በሽቦ ጥልፍልፍ ፥ መኪና ተሰርቶ
የእቃቃ ጨዋታ
የልጅ ታላቅ ፌሽታ
ደምቆ የነበረ
ቅድም አልነበረ?
በጨዋታ መኻል፣
አይናችንን ከድነን ፥ ደግሞ ስንገልጠው
አሁን የነበረ ፥ አልፎ አገኘነው
አሁን አልነበረ፥ ኳስ የጠለዝነው
አሁን አልነበረ ፥ ገመድ የዘለልነው
አሁን አልነበረ ፥ እቃቃ ደርድረን፥ የተጨዋወትነው
አሁን አልነበረ ፥ ህፃን የነበርነው?
የህፃንነት ወራት ፥ በፍጥነት አለፈ
አበባነታችን ፥ ፈጥኖ ተቀጠፈ
ልጅነት ነጠፈ።
"የልጅነት ዘመን እንደምን ሮጠ
የህፃንነት ጊዜ እንዴት ፈረጠጠ"
ብለን ስንገረም
በእድሜ መሰደድ፥ ብዙ ስንደመም
ጉርምስና አልፎ፥ ወጣትነት መጣ
መገረም ተቀጣ!
ጠዋት ህፃን ሳለን
በጨዋታ መኻል ፥ አይናችንን ከድነን
የልጅነት ወራት ፥ ሮጦ አመለጠን
ረፋዱን ጎርመሰን
በከንፈራችን ላይ፥ ጣታችን አኑረን
ፈጥኖ ባመለጠ፥ በልጅነታችን
በቅልብልብ እድሜ ፥ ስንደመም ሳለ
ጎረምሳነታችን፥ ትቶን ኮበለለ
"የጎረምሳ አመፅ፥ የጎረምሳ ፍቅር ፥ እንደምን ያለ ነው?
የጉርምስናን መልክ ፥ ገላጩ ምንድነው?"
ብለን ልንጠይቅ ፥ስነሰነዳዳ
መጎልመስ በተራው፥ ገባ ወደ ጓዳ
እድሜ ቅልብልቡ ፥ምንድነው 'ሚያሮጠው
ማነው 'ሚያጣድፈው
የቱ አምባገነን ፥ መርጋትን ነጠቀው?
ህፃን የነበርነው ፥ ጠዋት አልበረ
የልጅነት ወራት ፥ እንደምን በረረ?
አሁን ቅርብ ሰኣት ፥ ጎረምሶች አልነበርን
የአመፃው ዘመን ፥ ከምኔው አለፈን?
ተስፋብዓብ ተሾመ
❤ 61👍 36👏 9🤔 1

