uk
Feedback
የስብዕና ልህቀት

የስብዕና ልህቀት

Відкрити в Telegram
2025 рік у цифрахsnowflakes fon
card fon
68 961
Підписники
Немає даних24 години
-137 днів
-96730 день
Архів дописів
መቶ አንደኞቹ ጅሎች ዕፀገነት ከበደ @Human_intelligence
Показати все...
መቶ አንደኞቹ ጅሎች.mp36.61 MB
👏 18👍 7🥰 3 2
የራስህን ቅጥር ገንባ!!! ከሚከተሉት ሶስት ሁኔታዎች ውስጥ የትኛው የበለጠ ቅር ያሰኝሃል? ሀ) የጓደኛህ ደሞዝ መጨመር እና ያንተ ደሞዝ ምንም አለመጨመር ለ) የጓደኞችህ ደሞዝ አለመጨመር፤ ያንተም እንደዚያው መሆን ሐ ) የጓደኞችህ አማካይ ደሞዛቸው መቀነስና ያንተም እንደዚያው መሆን፡፡ «ሀ» ብለህ የምትመልስ ከሆነ እንደ አብዛኛው ሰው  አንተም የቅናት ሰለባ ነህ። አንድ የሩሲያዊያን ወግ አለ፡፡ አንድ ገበሬ አንድ ምትሃተኛ አምፖል ያገኛል፡፡ አንፖሏን ጫን ሲላትም አንድ ፍላጎቱን ብቻ የምታሟላላት ቀጭን የምትሃት ብርሃን ብቅ ትላለች፡፡ ገበሬው በዚች ነገር ላይ ጥቂት አሰብ አደረገና እንዲህ አለ፡- «ጎረቤቴ ላም አለው፤ እኔ ግን የለኝም፡፡ አሁን የእሱም እንደትሞትበት እፈልጋለሁ፡፡› አለ ይባላል። ይህ ምንም ያህል ፀያፍ ቢመስልም አንተም እንደ ገበሬው ( አይነት የምታስብባቸው አጋጣሚዎች አሉ፤ እመን! የስራ ባልደረባህ ከፍተኛ ቦነስ ሲቀበል አንተ ግን የምስክር ወረቀት ብቻ ተሰጠህ እንበል፤ ትቀናለህ፡፡ ይህ የኢ-ምክንያታዊ ባህሪያትን ትስስሮሽ ይፈጥራል። ከዚያ በኋላ ይሄን ባልደረባህን አትረዳውም፤ ምናልባት በቻልከው መጠን እንቅፋት ልትሆንበትም ትችላለህ። እግሩ ሲሰበር በውስጥህ ምስጢራዊ ደስታ ይሰማሃል። ከሁሉም ስሜቶች ይልቅ ቅናት ፀያፍ ነው፡፡ ለምን? ምክንያቱም ይህ በአንፃራዊነት ለመቀያየር ቀላል ነው፡፡ ከንዴት፣ ከፍርሃት እና ከመከፋት አንፃር ማለቴ ነው፡፡ ‹‹ከእሱ የሚገኝ ምንም ጥቅም የለምና ቅናት ከሁሉም ስሜቶች ፀያፉ ስሜት ነው›› ይላል ባልዛክ። ባጭሩ ቅናት ለራስ የመመኘት ጥብቅ ፍላጎት የሚያመጣው ጊዜ ማባከን ነው። ቅናትን ብዙ ነገሮች ሊያመጡት ይችላሉ፤ ባለቤትነት፣ ደረጃ፣ ጤና፣ እድሜ፣ ችሎታ፣ ታዋቂነት፣ ቁንጅና ወዘተ፡፡ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ቀጥተኛ ቅናት የሚያድርብን በብዙ ነገር ከሚመሳሰሉን ሰዎች ላይ ነው፡፡ ከመቶ አመታት በፊት ባሉ ስኬታማዎች አንቀናም፡፡ በእንስሳት ወይም በእፅዋትም አንቀናም፡፡ በከተማችን በሌላኛው ክፍል ባሉ ባለሃብቶች እንጂ በአለማችን በዚህኛው ክፍል ባሉ ባለሃብቶች አንቀናም፡፡ እኔም እንደ ጸሐፊ በሙዚቀኞች፣  በማናጀሮች ወይም በጥርስ ሃኪሞች አልቀናም፡፡ ይቺን ነገር አርስቶትል በሚገባ ጠቅሷታል፡፡ ‹‹ገጣሚ በገጣሚ ይቀናል!›› . . ሌላው በብዛት የምናየው የመወዳደሪያ ሜዳ ማህበራዊ ሚዲያው ነው። ዛሬ ላይ ፌስቡክ ብዙ ተጠቃሚዎቹን ብስጭትና ለዝለት እንደዳረገ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ የሃምቦልድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ይህ ለምን እንደሆነ ለማጥናት ሞክረው ነበር፡፡ ውጤቱን? ገምተህ ይሆናል፡፡ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው ቅናት ነው፡፡ ይህ በቀላሉ የሚገባን ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም ፌስ ቡክ የተሰራው ራሱ ተመሳሳይ ሰዎች ራሳቸውን የሚያወዳድሩበት መድረክ ተደርጎ ነው፡፡  በውስጥ ያሉት እንደ መውደድ (like) እና መጋራት (share) ያሉት ይዘቶቹም በከፍተኛ ሁኔታ ደስታን ለሚፈታተኑ ማወዳደሪያነቶች የተስማሙ ናቸው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ጓደኛህ በፌስ ቡክ ላይ የሚጭነው አንድ ፎቶ ከእውነተኛ ሕይወቱ ጋር ያን ያህል የሚገናኝ አይደለም፡፡ ፎቶ ብዙ ማበጃጀቶች የተጨመሩበትና አንተን ሌሎች የፌስ ቡክ ጓደኞችህ እየበለጡህ እንደሆነ እንድታስብ በሚያደርግ መልኩ የሚመጡ ናቸው፡፡ ይህም እነሱ በእውነተኛው ሕይወታቸው እየሆነ ካሉት በላይ የተቀባባ ነው፡፡ እንደዛሬው ዘመን ሰዎች ራሳቸውን ከሌሎች ጋር ማወዳደር የየእለት ተግባራቸው ያደረጉበት ዘመን የለም፡፡ ኢንተርኔት ቅናትን ወደ ወረርሺኝነት አሸጋግሮታል፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ ውድድርን በአግባቡ ከተቆጣጠርክ በኋላ በመደበኛው ሕይወትህ ውስጥ ራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደርንም መቀነስ አለብህ፡፡ አስተውሉ በሁሉም ነገር አንደኛ መሆን  አይቻልም፡፡ በአለም ትልቁን የገንዘብ መጠን ሊኖራችሁ ይችላል ግን በአለም በጣም ውብ የሆነ ፊት አይኖራችሁም፡፡ አንድ ለማኝ ሊያስቀናችሁ ይችላል፡፡ የለማኙ አካል፣ ፊት፣ አይኖቹ እናንተ ካላችሁ ሊበልጥ ይችላል እናም ያ..ያስቀናችኋል፡፡ አንድ ለማኝ አንድ ንጉስን ሊያስቀና ይችላል፡፡ እና ይህንን ሁልጊዜ  አስታውሱ ሁሉም ነገር ሊኖራችሁ በፍፁም  አይችልም። ወደ መፍትሄ ስንመጣ ቅናትን መቆጣጠር የሚቻለው እንዴት ነው? በመጀመሪያ ደረጃ ራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደር አቁም፡፡ ያን ጊዜ ከቅናት የፀዳ ሕይወትን ትኖራለህ፡፡ ራስህን ከሌሎች ጋር ከማወዳደር ሕይወት ውጣ፡፡ ይህ ወርቃማ ህግ ነው፡፡ ሁለተኛ የራስህን "የችሎታ ክልል "ፈልግና በራስህ ሙላው። የራስህን ቅጥር ገንባ እና ራስህን ከቀድሞ ራስህ ጋር ብቻ አወዳደር። ✍️ሮልፍ ዶብሊ የስብዕና ልህቀት @Human_intelligence
Показати все...
👍 89 10🤔 2
ግራ ዘመን (ተስፋኣብ ተሾመ) ላይ ላዩን ሲታይ የኛ ዘመን ጥሩ ይመስላል። በትክክል ግን ግራ አጋቢ  ዘመን ነው። የማይጨበጥ ዘመን! ዛሬ ላይ አላስፈላጊ መተራመስ ውስጥ ነን፥ እርጋታ የለም፥ የጋራ እሴት የለም።  ግለሰባዊነት ማበቡ ያልበቁ ግለሰቦች እንዳሻቸው እንዲፈነጩ አድርጓል። ያልተማሩቱ መምህራን የሚሆኑበትን እድል አግኝተዋል። ራሱን ለመግዛት ያልታደለ የመንጋው አውራ ለመሆን በሚያደርገው ትግል የተነሳ መንጋው ታምሳል። እውነተኛ ተመሪ ልከኛ መሪ የለም። ልክ ያልሆነ ቦታ መቀያየር ተፈጥሯል በመረጃ ጎርፍ ብንጥለቀለቅም እውቀት አልሆነንም። ጥራዝ ነጠቅ አደረገን እንጂ! በየሴኮንዱ ከሚለቀቀው መረጃ መኻከል እውነት የሆነውን የመለያ ጥበብ አላዳበርንም። ትርምስ ብቻ። ዘመናችን ግራ አጋቢ ነው። በግራ አጋቢ ዘመን በግራ መጋባት እየተራመስን ነው። ትርምስ ብቻ! ዘመን መዋጀት ይኹንልን!
Показати все...
👍 39 8🙏 2
መጀመሪያ በሶሻሊስቶች ላይ መጡ፤ እኔም ድምጼን አላሰማሁም      ሶሻሊስት አልነበርኩምና። ቀጥለው በሠራተኛ ማሕበረተኞች ላይ መጡ እኔም ድምጼን አላሰማሁ- የሠራተኛ ማሕበረተኛ አልነበርኩምና። ከዚያ በአይሁዶች ላይ መጡ፤አሁንም ድምጼን አላሰማሁ አይሁድ አልነበርኩምና። በመጨረሻ በራሴ ላይ መጡ - ነገረ ግን ድምፄን ስለእኔ ለማሰማት የተረፈ ሰው ግን አልነበረም። -- Martin Niemoller @Human_Intelligence
Показати все...
👍 44 5👏 3
ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ችግሮችን ማስወገድ ተማር!! ጥበብ ሕይወትን የምንቀዝፍባቸው ክህሎቶች መለኪያ ነው። ችግሮችን አስቀድሞ መከላከል ከተፈጠሩ በኋላ ከመፍታት የተሻለ ጥበብን  ይጠይቃል፡፡እውነታው ሕይወት ከባድ መሆኗ ነው፡፡ ችግሮች በሁሉም አቅጣጫ በየጊዜው ይተኮሱብሃል፡፡ እጣ ፈንታ መርገጫህ ስር ጉድጓዶችን ልትቆፍርብህ ወይም መሿለኪያዎችህን ልትዘጋብህ  ትችላለች። ይህንን መቀየር አትችልም፡፡ አስቀድሞ አደጋ ያለው የት ጋር እንደሆነ ከተረዳህ ግን ወዳንተ እንዳይመጣ ለማጠር እድል ይኖርሃል፡፡ በዚህ መንገድ መሰናክሎችን ሁሉ ማስወገድ ትችላለህ፡፡ ይህንን ሀሳብ አልበር አንስታይን እንዲህ ያስቀምጠዋል፡፡ “ጎበዝ ሰው ችግሮችን ይፈታል፤ ጥበበኛ ሰው ግን ችግሮችን ያስወግዳል፡፡” ችግሩ ችግሮችን ማስወገድም የሚወደስ ነገር አለመሆኑ ነው፡፡ ሁለት ፊልሞችን አስብ፡፡ 1.በመጀመሪያው ፊልም ውስጥ አንድ መርከብ ከበረዶ ክምር  ጋር መጠነኛ ግጭት ይገጥመዋል፡፡ መርከቡም ይሰምጣል። በዚህ ጊዜ የመርከቧ ካፒቴን ራስ ወዳድነት በሌለበት መልኩ ራሱን አበርትቶ ተሳፋሪዎቹን ሁሉ ከመስመጥ ይታደጋቸዋል፡፡ መርከቧ ለዘለዓለሙ ከመሰወሯ ከደቂቃዎች በፊት ሁሉንም ተጓዦች በማዳን ከጀልባው ላይ ዘሎ ወደ ሕይወት አድኑ ቦቴ ውስጥ በመግባት የመጨረሻው ሰው ነበር። 2.በሁለተኛው ፊልም ውስጥ ደግሞ እንዲህ ሆነ፡፡ መርከበኛው  መርከቧ ከበረዶ ክምሩ ጋር ከመጋጨቷ በፊት አስተውሎ በቂ ርቀት ላይ እንድትቆም አደረጋት፡፡ የትኛውን ፊልም ለማየት የበለጠ ትከፍላለህ?በእርግጠኝነት የመጀመሪያውን ፊልም፡፡ ሌላ ጥያቄ ደግሞ ላንሳልህ፡፡ አንተ በመርከቧ ውስጥ ተጓዥ ብትሆን ኖሮ በየትኛው ፊልም ሁኔታ ውስጥ መሆንን ትመርጣለህ? ያለ ምንም ጥርጥር ሁለተኛው ፊልምን። እነዚህ ምሳሌዎች እውነተኛ ገጠመኞች ናቸው ብለን እናስብ፡፡ ቀጥሎ ምን ይፈጠራል? የመጀመሪያው ፊልም ውስጥ ያለው ካፒቴን የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ ይጋበዛል። ምናልባት መርከበኛነቱን ትቶ አነቃቂ ንግግሮችን እያደረገ ሕይወቱን መምራት ሊጀምር ይችላል። መንገድም በስሙ ሊሰየምለት ይችላል፡፡ ልጆቹም (ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ) በአባታቸው ይኮራሉ፡፡ የሁለተኛው ፊልም ውስጥ የሳልነው ካፒቴንስ? ከስራው በጡረታ እስኪገለል ድረስ ችግሮች እንዳይከሰቱ በቅድመ ጥንቃቄ የመርከበኝነት ስራውን ይሰራል። መርሁም “ከ20 ጫማ እርቀት ላይ ልታልፈው የምትፈራውን ነገር በ500 ጫማ እርቀህ እለፈው” የሚለው የቻርሊ ሙገር የሕይወት መርህ ይሆናል፡፡ እንግዲህ ተመልከት፡- የሁለተኛው ፊልም ካፒቴን ከመጀመሪያው ፊልም ካፒቴን በሚታይ መልኩ የሚሻል ቢሆንም እኛ የምናከብረውና የምናደንቀው ግን የመጀመሪያውን ፊልም ካፒቴን ነው፡፡ ለምን? በቅድመ ጥንቃቄ የሚመጣ ስኬት ለውጪው ዓለም እይታ የሚጋለጥ አይሆንም፡፡ ጋዜጠኞች አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንዳይመጡ ካረጉ በሳል ሰዎች ይልቅ ችገሮችን የቀለበሱ የሥራ መሪዎችን ነው የሚያሞካሹት ።የቅድመ ጥንቃቄ ስኬቶች  ለውጪው ዓለም የማይታዩ ባለመሆናቸው ምክንያት ሳይታዩና ሳይወደሱ ይኖራሉ፡፡ የእንደዚህ አይነት ስኬቶት ባለቤቶችን ጥበብ የሚያውቁት በእሱ ዙሪያ ያሉ የቡድኑ አባላት ብቻ ናቸው። እነሱም ቢሆን በተወሰኑ መልኩ ቢያውቁት ነው፡፡ የአንተስ ሕይወት? አመንክም አላመንክም ከስኬቶችህ ሁሉ 50% የሚሆኑት የቅድመ መከላከል ጥንቃቄህ ውጤቶች ናቸው፡፡ ሁላችንም እንደምናደርገው ሁሉ አንተም አንዳንድ ነገሮችን በንዝህላልነት ልታደርግ ትችላለህ፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖም ግን ስህተቶችን ላለመስራት ሁልጊዜም ትጠነቀቃለህ፡፡ በአርቆ · አሳቢነት ያስወገድካቸውን በስራህ፣ በትዳርህ፣ በትምህርትህ ወይም በሌላ የሕይወትህ ዘርፍ ሊገጥሙህ የነበሩ ችግሮችን አስብ፡፡ ጥንቃቄ (prevention) ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ቅድመ ጥንቃቄ በባህሪው ቀድሞ ማየት (imagination) ይጠይቃል ቀድሞ መረዳትና የሚመጣውን መገመት ደግሞ ብዙውን ጊዜ አዛብተን የምንረዳቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ይህ አዲስ ሀሳብ አያመጣልንም፡፡ በዓይነ ህሊና ማየት (imagination) ማለት የመጨረሻው ፍትሃዊ ነገር ሆኖ እስክናይ ድረስ ሊሆኑ የሚችሉት ነገሮች ውጤቶችና የመፈጠር እድላቸውን ሁሉ እንዲያስብ አዕምሯችንን ማሰራት ማለት ነው፡፡ ስለሆነም አስቀድሞ ማየትና መገመት ከባድ ስራ ነው። በተለይ ጉዳዩ ስለአደገኛ ችግሮች ሲሆን ደግሞ ቀድሞ የመገመት ሥራ የበለጠ ፈታኝ ይሆናል፡፡ ሊመጡ እድል ባላቸው ችግሮች ላይ ሁሉ እየተጠነቀቅክ መኖር ይጠበቅብሃል? ይህስ ሁልጊዜ የተጨናነቀ ሰው ሆነህ እንድትኖር አያደርግህም? ተሞክሮዎች የሚያሳዩት እንደዚያ እንዳልሆነ ነው፡፡ ቻርሊ ሙገር እንዲህ ይላል “በሕይወት ዘመኔ ሁሉ የሚመጠብኝን አደጋዎች ስገምት ኖሬያለሁ፡፡ ሁልጊዜ ይሄንን እያሰብኩ፣ አደጋዎች ከመጡም እንዴት መመከት እንዳለብኝ እያሰላሰልኩ መኖሬ ደስተኛ እንዳልሆን አላደረገኝም፡፡” ሮልፍ ዶልቢ The art of good life ሀገራችን  እንደዚህ ውጥንቁጡ የወጣ ችግር ውስጥ የገባችው አደጋዎችን ቀድሞ መከላከል የሚችሉ በሳል ሰዎች ስለሌሏት ይመሰለኛል።ጎበዝ ጦረኞች ያስፈልጉናል ግን ከዛ የበለጠ ጦርነት እንዳይከሰት ቀድመው በሳል እርምጃ የሚወስዱ መሪዎች ያስፈልጉናል። እርዳታ የሚያሰባስቡ ዲፕሎማቶች ቢያስፈልጉንም ከዛ የበለጠ ኢኮኖሚያችንን በዘላቂነት የሚያሻሽሉ ፖሊሲዎችን የሚቀርፁ ሙሁራን  ያስፈልጉናል። የስብዕና ልህቀት @Human_Intelligence
Показати все...
👍 77 8🔥 1👏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
“ጦርነት ሲጀምር-ፖለቲከኞች ጥይት ያቀብላሉ፡፡ ባለፀጎች ምግብ ያቀርባሉ፡፡ ድሆች ልጆቻቸውን ይለግሳሉ፡፡ ጦርነቱ ሲያበቃ-ፖለቲከኞች ቀሪ ጥይቱን ይሰበስባሉ፡፡ ባለፀጎች ከጦርነቱ በተረፈው ሐብታቸው ማደግ ይጀምራሉ፡፡ ድሆች ግን ልጆቻቸውን በመቃብር ስፍራ ይፈልጋሉ” ሰርቦች
Показати все...
154👍 51😢 37
የጥቁር ሳጥን አስተሳሰብ (Black box Thinking) ጥቁር ሳጥን (Back Box) ማለት በአውሮፕላኖች ላይ የሚገጠም የበረራ መረጃዎችን የሚሰበስብ መሳሪያ ሲሆን  ይህ ሳጥን የአብራሪውን ንግግሮች ጨምሮ ሌሎች በርካታ የበረራ መረጃዎችን በፍጥነት ማከማቸት የሚችል ሪኮርደር ነው፡፡ ስለሆነም የአንድን አውሮፕላን አደጋ መንስዔ ለማወቅ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የአየር መንገዶችን ያህል ስህተቶችን የሚጠቀም ኢንዱስትሪ የለም። ሳለን በርባር የተባለው ካፒቴን በሚገርም ሁኔታ በሆድሰን ወንዝ ላይ አውሮፕላኑን ማሳረፍ ከቻለ በኋላ የሚከተለውን ፅፏል፡፡ “በአቬሽን ውስጥ የምናውቃቸውን እያንዳንዳቸውን ነገሮች፣ በበረራ መመሪያው ውስጥ ያሉትን እያንዳንዳቸውን ህጎች እና የምንጠቀምባቸውን እያንዳንዳቸውን ሥነ ሥርዓቶች በሙሉ ለማወቅ የቻልነው የሆነ ቦታ ላይ፣ የሆነ ሰው ሞቶ ነው፡፡” አደጋ በደረሰ ቁጥር ከዚያ በኋላ ያሉት በረራዎች ደህንነት የበለጠ አስተማማኝ እየሆነ ይሄዳል፡፡ ይህ መርህ (የጥቁር ሳጥን አስተሳሰብ እንበለው) በሌሎች የሕይወት ዘርፎች ላይም መተግበር የሚችል ጥሩ የአዕምሮ መሳሪያ ነው፡፡   የሰው ልጆች የአቬሽን ኢንዱስትሪው ፍፁም ተቃራኒ ናቸው።ምክንያቱም እውነታን ተቀብለው ሪከርዳቸውን የመተንተን ልማድ ያላቸው በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው።ይህ ደግሞ ቢያንስ ሁለት ነገሮችን ይጠይቃል፡፡ 1) የመቀበል አቅም እና 2) የጥቁር ሳጥን አስተሳሰብ። መጀመሪያ እውነታን መቀበል አለብህ፤ ስትቀበልም ሙሉ በሙሉ ይሁን። በተለይ ያልወደድካቸውን የእውነታውን ክፍሎች። በወቅቱ ከባድ ሊሆንብህ ይችላል። ነገር ግን የግድ ማድረግ አለብህ። ዋጋውንም በኋላ ታየዋለህ። ሕይወት ቀላል አይደለችም። ጥሩ ሕይወትን እየኖርክ እንኳን የውድቀትን ፅዋ መጋትህ አይቀርም።  መሳሳት ችግር የለውም። ዋናው ቁልፍ ስህተቱ ለምን እንደተፈጠረ ለይቶ ማስተካከያ ማድረግ ነው፡፡ ምክንያቱም ችግሮች እያደር ይጣፍጡ ዘንድ የወይን መጠጦች አይደሉም። የምናየውን ነገር የምንወደው በሆነ ጊዜ እውነታን መቀበል ቀላል ነው፡፡ ችግሩ የምናየውን ነገር የማንወደው በሆነ ጊዜ ነው፡፡ ሩሴል ምሳሌ ያነሳል። "የፃፈው ተውኔት አንድም ቀን ተዋጥቶለት የማያውቅ ደራሲ “ተዋናዮቹ ብቃት የላቸውም የሚለውን የሚያፅናና መደምደማያ ሲይዝ ማየት የተለመደ ነው።” አንተ ተውኔት ላትፅፍ ትችላለህ፡፡ የራስህን እንደነዚህ አይነት ምሳሌዎች ማምጣት እንደምትችል ግን እርግጠኛ ነኝ፡፡ በየጊዜው ስህተቶች ያጋጥሙሀል ለችግሩ ዋናኛ ተጠያቂ ራስህ ሆነህ ሳለ ራስህን ተጠያቂ ላለማድረግ ራስን መሸወጃ ሰበቦችን ትፈጥራለህ። ድክመትንና ሽንፈትን መቀበል የአስተማማኝ እና የዘላቂ ደስታ ቅድመ ሁኔታ ነው።ከዚህ እውነታውን ከመቀበል ጎን ለጎን ጥቁር ሳጥንም ያስፈልግሀል። ልክ  እንደ አቬዬሽኑ አንተም የራስህን ጥቁር ሳጥን ገንባ። ትላልቅ ውሳኔዎችን በምትወስን ጊዜ ሁሉ በአዕምሮህ ውስጥ የሚንሸራሽረውን ሀሳብ -ፃፍ፡፡ ቅድመ - ግምቶችን፣ አማራጭ ሀሳቦችን፣ መደምደሚያዎችን ወዘተ፡፡ በኋላ ውሳኔህ መጥፎ ውጤት ካመጣ ወደኋላ ተመለስና የበረራ መረጃህን (የግልህን ጥቁር ሳጥን) መርምር፡፡ ለስህተት የዳረገህ ነገር ምን እንደሆነም ከመዘገብከው ነገር ውስጥ ፈልፍለህ አውጣ፡፡ በዚህ ደረጃ ቀላል ነው፡፡ በሰራሃት እያንዳንዷ ስህተት ልክ  ሕይወትህ እየተሻሻለ ይሄዳል፡፡ ስህተትህን ማወቅ ካልቻልክ ግን ወይ አለምን ወይም ደግሞ እራስህን መረዳት አልቻልክም ማለት ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ የት ጋር አረጋገጥህ እንደተሳሳትክ የማታውቅ ከሆነ፣ እንደገና በአፍጢምህ መደፋትህ አይቀርም፡፡ ጉዞህን በመተንተን ውስጥ መፅናት ከዚህ ሁሉ ያወጣሃል፡፡ ይህ የጥቁር ሳጥን አሰራር ለግለሰቦች ብቻ ሳይሆን ለድርጅትም ይሰራል። ለየትኛውም ድርጅት የሚስማማ መለመድ ያለበት አሰራር ነው፡፡ እውነታን መቀበልና የጥቁር ሳጥን አስተሳሰብ በራሳቸው በቂ አይደሉም። ስህተቶችህን ማረም አለብህ። ራስህን እያሻሻልክ መሄድ ይጠበቅብሃል፡፡  ቻርሊ ሙንገር እንዳለው “መፈታት የሚችልን ችግር እርምጃ ሳትወስድበት ምንም መደረግ የማይችልበት ሁኔታ ላይ እስኪደርስ የምትጠብቅ ከሆነ፣ አንተ የደረሰብህ ችግር የሚገባህ ሞኝ ሰው ነህ ማለት ነው፡” ውጤቱ እስኪመጣ አትጠብቅ፡፡ “እውነታን ተቀብለህ ማድረግ ያለብህን ካላደረግክ እውነታ እንደፈለገች ታደርግሃለች”፡፡ (አሌክስ ሃሌ) ✍️ ሮልፍ ዶብሊ The art of clearly thinking የስብዕና ልህቀት @Human_Intelligence
Показати все...
👍 65👏 9 5🤔 4
ውብ ጥቅሶች 1."ጥበብ የትናንት ረቂቅ ሚስጢር ስትሆን፤ ውበት ደግሞ የነገ ቃልኪዳን ናት።" ኦሊቨር ሆልምስ 2."አስተሳሰብህና ምግባርህ ስብዕናህን ውብ ያደርጉታል።" ስኮት ዌስተርፊልድ 3."ህይወትን ለቸረህ ፈጣሪህ ለስጦታው የምትከፍለው ምላሽ በህይወት ዘመንህ የምትሰራው ታላቅ ስራ ነው።" ቢሊ ሚልስ 4."መልካም ሰው ላይ ምድራዊ በሮችን መዝጋት ይቻል ይሆናል ፣ መልካም ስራው በየሰው ልብ ውስጥ የከፈተለትን በር መዝጋት ግን አይቻልም።" ምንዳርያለው ዘውዴ 5."እውነተኛ ፍቅር ልክ እንደ መንፈስ ነው ሁሉም ቢያወራውም የሚያዩት ጥቂቶቹ ናቸው።" ፍራንኮይስ 6."ከምግብ ረሀብ ይልቅ የፍቅርን ርሀብ ማስታገስ ከባድ ነው።" ቴሬዛ 7."ሁሌም ስንገናኝ ፈገግታ አይለየን፣ ፈገግታ ለመዋደድ በር ከፋች ነው።" ማዘር ቴሬዛ 8."ፈገግታዬን ላዘኑ ልቦች ሁሉ እንድለግስ ነብሴ በልቤ መስኮት ፤ ልቤ ደግሞ በዓይኔ ውስጥ ትሳቅ። ዮጋናንዳ 9."አንዳንድ ነገሮች አሉ አስር ጊዜ ተጠይቀው ፤ አስር ጊዜ ተመልሰው ፤አስር ጊዜ የሚጠየቁ።" ሰለሞን ደሬሳ 10."ስለ ራሳችን ብዙ የምናወራው ፤ እውነተኛ ማንነታችንን ለመደበቅ ነው።" ያልታወቀ 11."ልባዊ ፈገግታ የለበስከውን የነተበ ልብስ እንኳ ይደብቅለሀል።" ሊ ሚልደን 12. ."ህይወት የፈለገነውን ያህል ሳይሆን የሚበቃንን ብቻ የምናነሳለት የልደት ኬክ ናት።" ጆርጅ ሀሪሰን @Human_Intelligence @Human_Intelligence
Показати все...
👍 66 16🤔 5🥰 3👏 3
ልማድና ጥንቃቄ “ልማድ በመጀመሪያ እንደ እንግዳ ይመጣል፣ ከዚያም እንደ ጓደኛ ይከርማል፣ በመጨረሻም እንደ ጌታ ይገዛል” – Anonymous የሰውን ዘር የሚያሳስቡትና ብዙ የሚጠነቀቅላቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ የሚያሳስቡን ጉዳዮች ምናልባት ትኩረት ብንሰጣቸውም ሆነ ባንሰጣቸው ብዙም ችግር የማያመጡ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ግን ካልተጠነቀቅንና ካላሰብንባቸው ለአደጋ የሚያጋልጡን ናቸው፡፡ ከእነዚህ እጅጉን ልናስብባቸውና ልንጠነቀቅላቸው ከሚገቡን ሁኔታዎች ቀዳሚው የልማድ ጉዳይ ነው፡፡ እንደውም፣ ልማድ በቀዳሚነት ሊታሰብበት የሚገባና የሁሉ ነገር መሰረት ነው ብንል አንሳሳትም፡፡ ሰው ከልማድ ውጪ መኖር አይችልም፤ ወይ ጤናማ ልማድ ወይም ደግሞ ጤና-ቢስ! ከልማድ ውጪ መኖር ያለመቻልህን ሁኔታ መቀየር ስለማትችል፣ አንደኛህን ጤናማ ልማዶችን የማዳበር ውሳኔ ውስጥ ግባ፡፡ ዛሬ ብዙ አስበህበትና ሞክረህ በፍጹም ልትላቀቅ ያልቻልከውና ክፉ ውጤት ሊያስከትልብህ የሚችል አንድ ልማድ ካለብህ፣ ቆም ብለህ አስብ፡፡ መጀመሪያ ስትሞክረው እንደ እንግዳ ነገር ነው የቆጠርከው፡፡ ከዚያም ስትለምደው ልክ እንደ ጓደኛ ይናፍቅህ ጀመረ፡፡ የኋላ ኋላ መዘዙን እያየኸውና ልማዱ እያስገደደህ ሲመጣ መላቀቅ እስኪያቅትህ ድረስ አለቃህና ጌታህ እንደሆነ ማሰብ አያስቸግርህም፡፡ ለዚህ ነው የየእለት ልማዳችን ጉዳይ እጅግ ወሳኝ እንደሆነና በጣሙን ልንጠነቀቅለት የሚገባን ጉዳይ እንደሆነ ደግሞና ደጋግሞ የሚነገረን፡፡ ዶ/ር እዮብ ማሞ @Human_Intelligence @Human_Intelligence
Показати все...
👍 53 10👏 5
የዓለም ወርቃማ ጥቅሶችና አባባሎች ✓ We must all learn to live together as brothers, or we are all going to perish together as fools. -Martin Luther King Jr. ➢ “ሁላችንም እንደ ወንድማማቾች ተፈቃቅረን መኖር ካልቻልን፤ እንደ ሞኞች ተያይዘን መጥፋታችን አይቀርም::” ✓ Love is fire. But whether it's gonna warm your heart or burn your house down you can never tell. Jason Jordan. “ፍቅር እሳት ሲሆን፤ መቼ ልብህን እንደሚያሞቀው፣ መቼ ቤትህን እንደሚያቃጥለው አታውቅም፡፡” ✓ Success is not the key to happiness. Happiness is the key to success. If you love what you are doing, you will be successful. Albert Schweitzer. ➢ “ደስታ የስኬት ቁልፍ እንጂ፤ ስኬት የደስታ ቁልፍ አይደለችም፡፡ የምትሰራውን የምትወደው ከሆነ ስኬታማ ትሆናለህ::” ✓ The bad news is time flies. The good news is you're the pilot— Michael Althsuler. ➢ “መጥፎው ዜና ጊዜ መብረሩ ሲሆን፤ መልካሙ ዜና ደግሞ አብራሪው አንተ መሆንህ ነው፡፡” ✓ Every king was once a crying baby & every building was once a picture. It's not about where you are today but where u will reach tomorrow. Anonymous. ➢ ሁሉም ንጉስ ባንድ ወቅት የሚያለቅስ ህፃን ነበር፤ እያንዳንዱ ህንፃ ንድፍ ነበር፤ ወሳኙ ነገር የዛሬው አንተነትህ ሳይሆን ለነገ የምትሰራው ማንነትህ ነው፡፡ ✓ Age wrinkles the body. Quitting wrinkles the soul. Anonymous. ➢ “እድሜ ቆዳን ሲሸበሽብ፤ ተስፋ መቁረጥ ነብስን ያነትባል፡፡” ✓ I don't know the key to success, but the key to failure is trying to please everybody. Bill Cosby. “የስኬትን ሚስጥር አላውቀውም፤ የውድቀት ሚስጥር ግን ሁሉንም ለማስደሰት መሞከር ነው፡፡” ✓ God gave us a gift of 86,400 seconds today. Have we used one to say Thank you? William Arthur Ward. ➢ “ፈጣሪ በዛሬዋ ቀን 86,400 ሴኮንዶችን ሲሰጠን፤ አንድዋን ሴኮንድ እንኳ ለምስጋና አውለናታልን?” A successful marriage requires falling in love many times, always with the same person. Mignon McLaughlin. ➢ “ስኬታማ ትዳር ማለት ከአንድ ሰው ጋር በተደጋጋሚ በፍቅር መውደቅ ማለት ነው፡፡” ✓ What is success? It is a toy balloon among children armed with pins Gene Fowler. ➢ “ዝና፣ መርፌ በያዙ ብዙ ህፃናት መካከል ተወጠሮ የሚንከባለል ፊኛ ነው:: ✓ Success is more permanent when you achieve it without destroying your principles. Walter Cronkite. ➢ “የራስህን እምነትና ፍልስፍና ሳታጣ የምታገኘው ስኬት ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡” @Human_Intelligence @Human_Intelligence
Показати все...
👍 80 25
ከዚህ ክልል መጣህ፣ ያኛው የአንተ ክልል ነው፡፡ አንተ ነባር አንተ መጤ ነህ እንደምንለው እስቲ "ይሄ ጤፍ መጤ ነው አልበላውም፣ ይሄ ስኳር የዚህ ክልል ነው አልጠቀምም፣ ይሄ ዘይት ባዕድ ነው ይቅርብኝ እንበል?" የጅማ ቡና እየጠጣን ጅማ ላይ መዶለት፣ የጎጃም ጤፍ እየበላን ጎጃምን ማጥላላት አብሮ አይሄድም፡፡ ወገኔ እኛ እኮ እንደተተበተበ ክር ነን፡፡ የቱ ጋር ተገናኝተን የቱ ጋር እንደምንለያይ የማይታወቅ ሰለሞን ዴሬሳ እንዳለው...."ወንድ አያታችን በማንኛዋ ሴት ደጃፍ እንዳለፈ አናውቅም" አያታችን ቆንጆ ሴት አይቶ ከእኔ ወገን አይደለችም ብሎ አላለፈምና ዘር የምንቆጥርበትና ነጥለን የምናወጣበት ምንም እድል የለንም፡፡ እርፍ በሉ! ይሄ የእኔ፣ እሱ የአንተ የምንባባለውም የለን፡፡ ሁሉም የእኛ ነው። ሰው እንዴት የሚያጠፋ ምኞት ይመኛል? ወገኔ... የፀበኛን ቤት ራት ገላጋይ ይበላዋል ማለት ይሄኔ ነው። ኃይለኛ መሆንህ ዋጋ የለውም፤ ኃይልህ ከተበታተነ፣ ለማንም ኢምንት ነህ፡፡ ግርማና መጎናፀፊያህ አንድነት ነው፡፡ ከተለያየህ ራቁቱን እንደቆመ ሰው ነህ፤ እንኳን ሌላው ሊፈራህ አንተም የራስህን ጥላ ትፈራዋለህ። በነገራችን ላይ ዘረኛ ከሆንክ፣ የፈለገ ወደ ላይ ብትሳብ ወደ ታች ካልወረድኩ ባይ ነህ፡፡ በዘረኝነት ኢትዮጲያን ከአለም በመሪነት ደረጃ ላይ ካላቆናጠጥናት ባዮች፣ ሳናመሰግናችሁ አናልፍም፡፡ ዕፀገነት ከበደ @Human_Intelligence @Human_Intelligence
Показати все...
👍 34 14
Repost from TgId: 1163708603
መሰውር - ኘሌቶ ምንጭ ፦ ፍልስፍና (ከዘርዐ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ) ፀሀፊ ፦ ፍሉይ አለም በመንገድህ ላይ አንዲት አሮጊት አጋጠመችህ፤ እናም ይህቺ ሴት ትንሽ፣ ግን እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነን ስጦታ ሰጠችህ - አስማተኛ ቀለበት! ይህም ቀለበት አንተን ለሌሎች እንዳትታይ አድርጎ ይሰውርሃል፤ ወደፈለግከው ስፍራ መጓዝ ትችላለህ፤ ማንም ሰው አንተን ማየት አይችልም፡፡ ጥያቄውም ይህ ነው በዚህ ቀለበት ምን ታደርጋለህ? ይህን አስማታዊ ኃይል እንዴት ትጠቀመዋለህ? “የጋይጂ ቀለበት” ሪፐብሊክ በተሰኘው የፕሌቶ ዘመን አይሽሬ ስራ ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ መጽሐፉ የፕሌቶ ታላቅ ወንድም ስለሆነውና ግላውኮን ጋይጂ ስለተባለ አንድ ተራ በግ ጠባቂ ታሪክ ይነግረናል። ይህ እረኛ ከክርስቶስ መወለድ ሰባት መቶ አመታት በፊት የሊድያ ግዛት ተብላ በምትጠራው ስፍራ ይኖር ነበር፡፡ (ይህን ግዛት አሁን ላይ በቱርክ ውስጥ እናገኘዋለን።) ፕሌቶ ታሪኩን እንዲህ ይተርከዋል፡- ከእለታት በአንዱ ቀን በእጅጉ ሃይለኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በሊድያ ግዛት ውስጥ ተከሰተ፡፡ በምድር ገጽ ላይም ትልቅ መሰንጠቅ ተፈጠረ፡፡ በስንጥቁ መሃልም እረኛው ጋይጂ አንድ የተደበቀ ዋሻ ተመለከተ፡፡ በዋሻው ውስጥም ጋይጂ ከነሐስ የተሰራ የፈረስ ሐውልት አገኘ፡፡ በዚህ ሐውልት ውስጥ በከፊል የበሰበሰ የአንድ ግዙፍ ሰው ሙት አካል ይገኝበት ነበር፡፡ በአስክሬኑ የቀኝ እጅ አንደኛው ጣት ላይም ወርቃማ ቀለበት ያብረቀርቅ ነበር፡፡ እናም ጋይጂ ይህንን ቀለበት ለራሱ ወሰደው፡፡ እረኛው ይህ ቀለበት ተራ ቀለበት እንዳልነበረ ለመረዳት ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ በቀለበቱ አናት ላይ ያለችውን ጌጥ ሲያሽከረክራት፣ ጋይጂ ሰው እንዳያየው ሆኖ ተሰወረ፡፡ ቀለበቱ ለጋይጂ የመሰወርን ኃይል ሰጠው። አስደናቂ የመሰወር ኃይልን እንዳገኘም፣ ይህ ተራ የበጎች እረኛ ወደ ቤተ መንግስት ቅጥር ዘለቀ፡፡ በዚያን ዕለት ምሽትም ከንግስቲቷ ጋር ተኛ፡፡ ንጉሱንም ገደለው፡፡ ንግስናንም ተቀበለ፡፡ እናም ራሱን የሊድያ ግዛት ገዢ አድርጎ ሾመ። ፕሌቶ በዚህ ታሪክ ውስጥ ለማስተላለፍ የሞከረው ዋነኛ ሃሳብ ቢኖር ይህ ነው ሰዎች መጥፎ ድርጊቶችን የማያደርጉት ብያዝስ በሚል ፍራቻ ነው። ሙሉ ለሙሉ የማንታይበት እና የምንሰወርበት ኃይል ቢኖረን - ከውርደት፣ ከመያዝ አልያም ከመታየት ፍራቻ እንላቀቃለን፡፡ ፕሌቶም - የመሰውርን ኃይል ያገኘ እና የሌላን ሰው ንብረት ላለመዝረፍ ያሰበ አልያም መጥፎ ተግባርን መፈጸም ያልፈለገ ቢኖር፣ እርሱ የአለማችን ሞኝ ሰው ነው' ይለናል፡፡ አንተስ የመሰወር ኃይል ቢኖርህ ምን ታደርጋለህ? በአጠገብህ ያለ ጓደኛህን ጠይቀው፤ ራስህንም ጠይቅ፡፡ የሚያስገርም፣ የሚያስቅ አልያም የሚያሳቅቅ ምላሽን ታገኛለህ ። እናስ የመሰውር ኃይል ቢሰጥህ ባንክ ቤት አትዘርፍም? ልክ እንደ ጋይጂ ወደ ቤተመንግስት ለመግባት አትሞክርም? ከዚህም ሲከፋ ለመናገር የሚከብዱ ወንጀሎችንስ አትፈጽምም? እናም... እኛን ወንጀልን ከመፈጸም የከለከለን ነገር ቢኖር “ሰው ምን ይለኛል' የሚለው ሃሳብ ብቻ ነው። የፕሌቶ 'ሰዎች መልካም የሚሆኑት በምርጫቸው ሳይሆን ተገደው ነው' የሚለው ሃሳብ ለዘመናት ብዙ ፈላስፋዎችን አጨቃጭቋል። ሆኖም ይህ የጋይጂ ቀለበት ከሁለት ሺ አመታት በላይ ያስቆጠረ አፈ-ታሪክ ቢሆንም፣ ከምንግዜም በላይ አሁን ላይ ላለነው ሰዎችም የሚሰራ ምሳሌ ነው። ለምሳሌ፤ ትክክለኛ ማንነታቸውን የማይገልጽ የፌስቡክ አካውንት ያላቸው ግለሰቦች፣ ማን እንደሆኑ አይታወቁምና እጅግ በዘቀጠ ሁናቴ ጸያፍ ስድቦችን ሲወራወሩ አልያም ጠብ አጫሪ እና በህግ ሊያስጠይቋቸው የሚችሉ የጥላቻ ንግግሮችን ሲዘሩ ይውላሉ፡፡ ሌላ ምሳሌ የሚሆነን እና የዘመናዊው ዓለም የመሰውር ቀለበት የሆነው ገንዘብ ነው፡፡ አስተውለህ ከሆነ የናጠጡ ሃብታሞች ምን ያህልም ጥፋት ቢያጠፉ ከህግ አይን የሚሰውራቸው ኃይል አላቸው፡፡ በገንዘባቸው ከምንም አይነት የወንጀል ውንጀላ ነጻ ይሆናሉ፡፡ ይህ ደግሞ በእጅጉ ጨካኝ የሆኑ እና ስለ ሌላው ግድ የሌላቸውን ህሊና አልባ ሰዎችን ፈጥሯል። @Zephilosophy @Zephilosophy
Показати все...
👍 33 6🙏 2
ውድ አልማዞች! ••••••• የግመል ነጋዴው በገበያው ለሽያጭ ከቀረቡት ግመሎች መካከል በአንዱ እጅግ ስለተሳበ ከሻጩ ጋር ድርድር ጀመረ። በገዢና በሻጭ መካከል ብዙ ደቂቃዎችን የፈጀ የቀንስልኝ፣ አልቀንስም ክርክር ከተደረገ በኋላ ገዢው በዋጋ ተስማምቶ ግመሉን ገዝቶ ወደ ቤቱ ሄደ። የግመል ነጋዴው ቤቱ እንደደረሰ አገልጋዩን ጠርቶ የግመሉን ኮርቻ እንዲያወርድ ይነግረዋል። አገልጋዩ የግመሉን ኮርቻ ሲፈታ ከኮርቻው ስር አነስተኛ መጠን ያላት የተቋጠረች ከረጢት ያገኛል። ከረጢቷን ሲፈታ በውድ የአልማዝ ማእድን ተሞልታለች። አገልጋዩም "አለቃ የገዟት ግመል በነጻ ይዛ ያመጣችውን በረከት ይመልከቱ!" ሲል በደስታ ተሞልቶ ጮኸ። ነጋዴውም  በአገልጋዩ መዳፍ ላይ በጸሐይ ብርሀን የሚንቦጎቦጉ የአልማዝ እንክብሎች ሲመለከት እጅግ ተደነቀ። ይሁንና "ግመሏን እንጂ አልማዞቹን አልገዛኋቸውም። አሁኑኑ ለባለቤቱ መመለስ አለብኝ" አለ - ነጋዴው። አገልጋዩም "ምን የማይረባ አለቃ ነው ያለኝ?!" ሲል በሆዱ ካወራ በኋላ "ማንም ሰው የአልማዞቹን ትክክለኛ ባለቤት ሊያውቅ አይችልም! ሲል ተናገረ። ይሁንና ነጋዴው ምክሩን ችላ ብሎ ጊዜ ሳይወስድ ባለቤቱም ፍለጋ ወደ ገበያው ተመለሰ። ብዙም ሳይለፋ የተቀሩ ግመሎችን ለመሸጥ ገዢ ሲጠብቅ የነበረውን የግመል ሻጭ አግኝቶ ትንሿን ከረጢት መለሰለት። የግመል ሻጩም እጅግ ተደስቶ " እጅግ የከበሩ ማእድናቴን በግላሱ ስር መደበቄን ዘንግቼ ነበር። አሁን ሽልማት እንዲሆንህ በከረጢቱ ውስጥ ካሉት አልማዞች ውስጥ ለዐይንህ ደስ ያሰኘህን ውሰድ!' አለ። "ለከፈልኩት ገንዘብ ጥሩ ግመል ሽጠህልኛል። ተጨማሪ ሽልማትም ስጦታም አልቀበልም።" አለ - ነጋዴው። ነጋዴው ስጦታውን አልቀበልም ቢልም ግመል ሻጩ እንዲቀበለው ይወተውተው ጀመር። በመጨረሻም ነጋዴው በፈገግታ ተሞልቶ "ከረጢቱን ልመልስልህ ስወስን ሁለት እጅግ የከበሩ አልማዞችን እራሴ ዘንድ አስቀርቻለሁ! ከእነርሱ የሚልቅ ሽልማት የለም!" አለው። የግመል ሻጩ የነጋዴው የእምነት ቃል ሲሰማ እጅግ ተበሳጭቶ በከረጢቱ ውስጥ ያሉትን ውድ አልማዞች የጨርቅ እራፊ ላይ ደፍቶ ይቆጥራቸው ጀመረ። ይሁንና ቆጠራውን እንደጨረሰ በእፎይታ ተሞልቶ "በከረጢቱ ውስጥ ከነበሩት አልማዞቼ መካከል አንድም አልጎደለም። የትኞቹን ውድ አልማዞች ነው ለራሴ አስቀርቻለሁ ያልከኝ?" ነጋዴውም በኩራት ተሞልቶ "እኔ ዘንድ ያስቀረኋቸው ውድ አልማዞች ታማኝነቴና ለእራሴ ያለኝ ክብር ናቸው!" ሲል መለሰለት። ሻጩ የሰማውን ነገር ባለማመን ዐይኖቹን አፍጥጦ ነጋዴውን ከመመልከት ውጪ መልስ ሊሰጠው አልቻለም።                    ** ሁላችንም ወደ እራሳችን መመልከትና እነዚያ ውድ አልማዞች እንዳሉን እንፈትሽ። ሁለቱ ውድ አልማዞች ያሉት ማኛውም ሰው የዓለማችን ባለጸጋው ሰው ነው።
Показати все...
👍 24 6
ለቡሄ ያበደ ሆ ሲል ይኖራል!! ከዕለታት የሆነው ቀን፣ አንድ ስኮትላንዳዊ እና እንግሊዛዊ ዱር ውሥጥ ሲንሸራሸሩ ሳለ አንበሳ መጣባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ስኮትላንዳዊው ያጠለቀውን ትልቅ ቦቲ ጫማ አውልቆ ሸራ ሲቀይር እንግሊዛዊው በመገረም "አሁን ጫማ መቀየር ምን ያደርጋል? አንበሳውን ሮጠህ ልታመልጠው ነው? ይለዋል፡፡ "አንበሳውንማ እንደማልቀድመው የታወቀ ነው፤ ሸራውን ግን የምቀይረው አንተን ለመቅደም ነው" አለው.... አንተን እስኪበላህ እኔ ጊዜ አገኛለሁ አይነት... ይህችን ጨዋታ ሃገሪቱ ላይ የምትጫወቱ፣ ነገር አቀጣጥላችሁ ሸራ ጫማችሁን አጥልቃችሁ ለመሮጥ የተዘጋጃችሁ ሰዎች ሆይ... አንበሳው እኛን እስኪበላ ጊዜ ታገኙ ይሆናል፤ ነገር ግን... አንደኛ አንበሳ ብቻውን አይመጣም፣ሁለተኛ ቀጣዩ ታዳኝ እናንተ መሆናችሁን በልባችሁ ፃፏት...ለዚህ እኮ ነው የወሎዋ አልቃሽ አሁን ምን ያደርጋል የሴት ወየው ባይ ወሎ የመጣው ሞት ሸዋ የለም ወይ? ያለችው... አገር አለን ለማለት እየከበደን ነው፤ ነፃነቱ እና ልቅነቱማ ተደበላልቆብናል፡፡ ፨፨፨ አንዳንድ ሰው ግን..."መብራት ጠፋብን" እያለ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል ቆይቶ፣ ለእሱ ሲበራ ሌላው ሰፈር ግን ሲጠፋ ፍትሃዊ የሚመስለው ለምንድነው? ሌሊሳ ግርማ እንዳለው የሰው እግር ቆርጦ ከራስ እኩል እንደማድረግ ያለ ‹ፍትህ› አንዳንድ ተምሬያለሁ የሚል ሰውስ የተማረ ሳይሆን በዩኒቨርሲቲ የፊት በር ገብቶ በኋላ በር የወጣ የሚመስለውስ? ሃገሪቱ ላይ ያለው ህዝብ ይህን ይመስላል፡፡ እንዲህ ያለህዝብ ያላትን ሃገር ደግሞ ጤነኛ ትሆናለች ብሎ ማሰብ ራሱ ህመም ነው... ዝም ብሎ እጅና እግሯን ጥፍር አድርጎ ሁለት ሰባት ማስጠመቅ ይሻላል፡፡ አሁን በቀደም የመብራት ኃይል ኃላፊው መብራት በተደጋጋሚ የሚያጠፉበትን ምክንያት ጋዜጠኛው ሲጠይቃቸው "አሁን እንደድሮው አይደለም፤ መብራት መጥፋቱ ባይቀርም ምክንያቱ ግን ተቀይሯል" ካሉ በኋላ... "ዘንድሮ መብራት የሚጠፋው አሁን በተያያዝነው የብልፅግና ጎዳና የደም ግፊታቸው የሚጨምር ሰዎች በንዴት ኮረንቲ መያዛቸው አይቀርም፤ እናም መንግስት የእነዚህን ሰዎች ደህንነት ለመጠበቅ ነው መብራት የሚያጠፋው" ቀጠሉ... 'ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ የኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች ልብስ አጥበው የሚያሰጡበት ቦታ ስለሚያጥራቸው ቀን ቀን የኤሌክትሪክ ገመዶቹን እንደልብስ ማስጫ እንዲጠቀሙ መንግስት መብራት በማጥፋት ይተባበራቸዋል" ጋዜጠኛው ችኮ ነው ጥያቄውን ቀጠለ "እሺ ራሳቸውን በኮረንቲ ማጥፋት የሚፈልጉ ዜጎችን መብት መጨቆን እንዳይሆን... መንግስት ምን ያመቻቸው ነገር አለ? ብሎ ጠየቀው ማለዳን መናፈቅ መምህርት ዕጸገነት ከበደ @Human_Intelligence @Human_Intelligence
Показати все...
👍 13 1
ጊዜ እንዳለኝ እያሰብኩ ነበር — እንደምኖር። በመጻሕፍት መደርደሪያዬ እኔን መጠበቅ ያደከማቸው ያልተነበቡ መጻሕፍት ተገጥግጠዋል። አንድ ቀን እንደማነባቸው ተስፋ ሳደርግ ምጽዓት ደረሰ —ሀገሬ። በሲዖል ውስጥ መጽሐፍ ማንበብ አይቻልም። አንደኛ ሀገሩ የእሳት ነው። በእሳት ሀገር ወረቀት ቀለም ይዞ አይቆይም። ይነዳል፥ አመድ ይሆናል። ብዙ ጩኸት አለ —ሰቆቃ። እና አይመችም። ዙሪያው ገደል ነው። ልብ ዝቅ ያደርጋል። ቀን በቀን መጻሕፍቴን እየተሰናበትኩ ነበር። ምን ትርጉም አለው? ሳልፈልግ አእምሮዬ እንደተረበሸ ከተማ ሐሳብ ይጎሎጉላል።  በሥነ ሥርዓት ላጠነጥን እሞክራለሁ —መሥመር ላስይዝ። ግን አልችልም ይሳከርብኛል። አንጎሌ፥ ሰውነቴ ይሰንፋል።  የምናደርገው ነገር ትርጉም መስጠት ያቆመበት በሚመስልበት ጊዜ ላይ ነን። እዚህ ሀገር ልጅ እንወልዳለን። የምናወርሰው ሀገር ግን ሲዖል ነው። ምሽቶች ባሎቻቸው ድንገት በወጡበት ይቀራሉ። ይታፈናሉ፥ ይታገታሉ። ልጆች ያልጠገቡትን፥ በውል ያለዩትን አባቶቻቸውን ባልጠበቁት ቅጽበት ይሰናበታሉ። ለሀገራቸው ውለታ የዋሉ ዋርካ ሰዎች በልጅ እግሮች ይገደላሉ። ደም ይፈሳል —በየመንገዱ፥ በየጫካው።  አድባራት አንድ ባንድ ይፈርሳሉ። ማንም ምንም ማምጣት የሚችል አይመስልም። ድንገት ኢምንትነት እንዲሰማህ ትሆናለህ። ሞት እየጠራህ ትማራለህ? ሞት እያነፈነፈህ ታከማቻለህ? በደጅህ ሞት እያደባ ታገባለህ? ሀገር እየተቃጠለ ትሰርጋለህ? ቆንጆ ቆንጆ ልጆች የጥይት እራት እንዲሆኑ ትወልዳለህ? መሣሪያ የታጠቀ ወንበዴ ቤትህን እየሠረሠረ ታንቀላፋለህ? ዳሩ ብትነቃስ ምን ታደርጋለህ? የዓለም ምጽዓት አንተ ጋር እስከሚደርስ ብትተኛ አይከፋም፥ ብትማር፥ ብትቆጥብ፥ ብታገባ፥ ብትወልድ። ሀገሩ የባለጌ ነው። ማን ጌታ እንደሆነ አይታወቅም። በመንገድ ስታልፍ ረግጦህ የገላመጥከው ሰው ዘመደ ብዙ ነው። የጦር መሣሪያ አለው። ባታውቀውም የጎበዝ አለቃ ነው። ትንሽ መንግሥት ነው። ሕይወትህን ከአፈር ይደባልቀዋል። ያየህ እስከማይገኝ ድረስ ድራሽህ ይጠፋል። ወዝህ ያስቀናው ሰው ዳር ሊያስይዝህ ይችላል። ሀገርህ ከየት እስከየት እንደሆነ አታውቅም። እግርህ ከቤት ወጣ እንዳለ የጠላት ሀገር ነህ። በካርታ ባይከለልም የተበጀ ድምበር አለ። ድንገት  ትጨመደዳለህ፥ እጅ ትሰጣለህ። ብትማረክም ትገደላለህ። ከቀን ውሎህ ተርፈህ፥ በሰላም ወጥተህ ከገባህ እድለኛ ነህ።  ከሄድክበት ስትመለስ ቤትህን በገነባህበት ስፍራ ላታገኘው ትችላለህ። ማንንም መርዳት አትችልም። ግፍና መከራ ተንከባሎ በሁሉም ቤት ይደርሳል። እስከዚያው ግን ተራው ያንተ ከሆነ ያንተ ነው። ትከሻህን ማስፋት፥ መቻል፥ መቀበል ይጠበቅብሃል። እውነት አይመስልም አይደል? ትላንት በእቅፍህ የነበረ ሰው እንደወጣ ሲቀር? ደብዛው ሲጠፋ?? ግን ይህ የብቻህ እውነት ነው። ይህ የብቻህ ሕመም ነው —ጽና። እ. . . ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን በሌላ አውድ የጻፈው አንድ ግጥም አለ። ያለ ዐውዱ እዚህ ጋር እንድጠቀመው ይፈቀድልኝ፦ “...ተገልለህ ርቀህ እውነት ይተዉኛል ብለህ እንዴት ተስፋ ታደርጋለህ?! . . . . ተስፋ አድርገህስ ምን ልትሆን ፡ ወይስ ተስፋው ምን ሊሆንህ ? እንቅልፍ እንጂ እሚያስወስድህ።” እሱባለው አበራ @Human_Intelligence @Human_Intelligence
Показати все...
👍 11 6
[ተስፋ በመቁረጥ ተስፋ መቀጠል] እንዳለ ገጣሚው መዘክር ግርማ...! -/ ተስፋ በተስፋ ይተካል:: በማይቀየር  እና ከቁጥጥራችን ውጭ በሆነ ነገር ላይ ተስፋ መቁረጥ... ሊቀየር በሚችልና በቁጥጥራችን ውስጥ በሆነ ጉዳይ ተስፋ ለመቀጠል/ለማድረግ ያግዛል:: [ አዲስ ተስፋ ለመቀጠል በአሮጌው ተስፋ መቁረጥ ያስፈልጋል::]... ትውልድ ያለ ዕዳው እየተቀጣ ነው:: አባቶቹ ባለራዕይና ንቁ አልነበሩም:: ለሃያላን ስሁት ህልም የተገበረ የመስዋእት በግ ሆኑዋል:: ይህን ለመቀየር ረፍድዋልና ተስፋ መቁረጥ አለበት... ይህን የሚነግሩት ደፋር ብእርና አንደበት ያላቸው ቀንዲሎችም ያስፈልጉታል:: አዎ! ተስፋ መቁረጥ ከባድ ነው: ዙሪያን ጨለማ: መንገድን ግራ ያስመስላል ያኔ ግን የራስ ህልም ይወለዳል: አዲስ ተስፋ ይቀጠላል:: መጀመሪያ ተስፋ እንቁረጥ! አባቶቻችን አያቶቻችንን አይመስሉም:: ቅዠት እንጂ ህልም አልነበራቸውም:: [ናትናኤል ዳኛው] @Human_Intelligence @Human_Intelligence
Показати все...
👍 7😢 1
ቅደም ተከተልን የማወቅ ጥበብ “የሚያጣድፍ ነገር ሁሉ አስፈላጊ ነገር አይደለም” - Stephen Covey አንድ ቀን አንድ የማኔጅመንት ሳይንስ ሊቅ ለተማሪዎቹ ንግግር በማድረግ ላይ ነበር፡፡ ይህ ሰው ለእነዚህ በጣም ለተነሳሱና ብሩህ አእምሮ ላላቸው ተማሪዎች በመናገር ላይ እያለ አንድን ነገር አደረገ፡፡ አንድ ባሊ አመጣና ጠረጴዛው ላይ ካስቀመጠ በኋላ ድንጋዮችን በማምጣት ባሊውን አፉ ድረስ ጢም አድርጎ በድንጋይ ሞላው፡፡ ይህንን ካደረገ በኋላ፣ “ይህ ባሊ ሙሉ ነው የሚል እጁን ያውጣ” አለ፡፡ በክፍሉ ያሉ ተማሪዎች በሙሉ እጃቸውን አወጡ፡፡ “እርግጠኛ ናችሁ?” አላቸው፡፡ “አዎን” በማለት እርግጠኝነታቸውን አረጋገጡለት፡፡ ከዚያም ከጠረጴዛው ስር አስቀምጦት ወደነበረው ሌላ ባሊ አጁን ዘርግቶ አነሳውና በውስጡ ያለውን ጠጠር ወደዚያ ድንጋይ ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰው፡፡ ጠጠሮቹ ሹልክልክ እያሉ ባገኙት ቀዳዳ ሁሉ ገቡ፡፡ “አሁንስ ባሊው ሙሉ ነው የምትሉ ስንት ናችሁ?” አለ መልሶ፡፡ አሁን አሰልጣኙ ምን ሊል እንደፈለገ በመጠኑ እየገባቸው ስለመጣ በማንገራገር የተደባለቀ ምላሽ ሰጡት፡፡ አንዳንዶቹ፣ “አሁን ሙሉ ነው” ሲሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ፣ “አሁንም አልሞላም” አሉ፡፡ አሁንም በመቀጠል እጁን ወደ ጠረጴዛው ስር ሰደድ በማድረግ ሌላ ባሊ አነሳ፡፡ ይህኛው ባሊ በአሸዋ የተሞላ ነው፡፡ ወዲያውኑ አሸዋውን ወደዚያ ድንጋይና ጠጠር ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰው፡፡ አሸዋዎቹ ሹልክልክ እያሉ ባገኙት ቀዳዳ ሁሉ ገቡ፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ፣ “አሁንስ ባሊው ሙሉ ነው የምትሉ ስንት ናችሁ?” አሁን ተማሪዎቹ በሙሉ በአንድ ቃል፣ “ባሊው አሁንም አልሞላም” ብለው መለሱለት፣ አካሄዱ ገብቷቸው፡፡ አሰልጣኙ እንደገና ሌላ ውኃ የሞላበት ባሊ ከጠረጴዛው ስር በማንሳት ድንጋይ፣ ጠጠርና አሸዋ ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰውና በባሊው ውስጥ ሌላ ምንም ነገር መጨመር እስከማይቻል ድረስ ሞላው፡፡ የመጨረሻው ትምህርታዊ ጥያቄ እንዲህ የሚል ነበር፡፡ “ከዚህ ምሳሌ የምናገኘው ዋና ቁምነገር ምንድን ነው?” አላቸው፡፡ አንዱ ሰልጣኝ አጁን አውጥቶ፣ “ምንም እንኳ ጊዜህ በብዙ ነገር ቢጨናነቅ፣ አሁንም ሌላ ነገርን አጨናንቀህ ማድረግ እንደምትች ነው” አለው፡፡ አሰልጣኙም፣ “ተሳስተሃል! የዚህ ምሳሌ ዋነኛ ትምህርት በመጀመሪያ ትልልቆቹን ድንጋዮች ባሊው ውስጥ ባትጨምር ኖሮ ትንንሾቹን ጠጠሮች፣ አሸዋውንና ውሃውን መጨመር አትችልም ነበር፡፡ ትልልቆቹ ድንጋዮች የሚወክሉት በሕይወትህ ያሉትን ዋና ዋና የሕይወት አላማዎችና ግቦች ነው፡፡ ቤተሰብህ፣ ጤንነትህ፣ የትምህርትህ አቅጣጫ፣ ዋነኛ ሕልሞችህና የመሳሰሉት … ዋና ዋና ከሚባሉት “ድንጋዮች” መካከል ይገኛሉ፡፡ በመጀመሪያ በእነዚህ ነገር ካልተደላደልክና የሕይወትህን አቅጣጫ ካልሞላኸው፣ በጥቃቅን ነገሮች ተጨናንቀህ ሕይወትህን ታባክናለህ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ጊዜን በአግባቡ የመጠቀምን ጥበብ ማዳበር በራሱ እጅግ አድካሚ ስራ ነው  ብለው  ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ሁኔታው የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ ዛሬ የሕይወቴን ዋና ዓላማ በመለየትና ቅድሚያን ለእርሱ በመስጠት መልክ የያዘ ሕይወት ለመኖር ማቀድ ካልቻልኩ ነገ በዚህና በዚያ የባከነውን ጊዜዬን መለስ ብዬ ከማየትና ከመቆጨት ውጪ ምንም ነገር ለማድረግ ያስቸግረኛል፡፡ “የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተቀነጨበ፡፡ @Human_Intelligence @Human_Intelligence
Показати все...
👍 14🤣 2 1
በዋናው ነገር ላይ ማተኮር! (“ትኩረት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) አንድን እጅግ በጥበብ የላቀን ሰው አገኘሁትና ባለችኝ የጋዜጠኝነት ሙያ ተጠቅሜ መጠየቅ የምችለውን ያህል ለመጠየቅ ሞከርኩ፡፡ ጠቢቡ - “ና ጠጋ በል … ጥያቄ ልትጠይቀኝ እንደፈለግህ ታስታውቃለህ” አለኝ፣ የልቤን ፍላጎት ገምቶ፡፡ እኔ - “ጊዜ ካለህ” አልኩት፡፡ ጠቢቡ (ልብን በሚሰርቅ ፈገግታ) - “ለማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ጊዜ አለኝ” ብሎ መለሰልኝ፡፡ ይህ ጥበበኛ እንዴት ለሰው ሁሉ ጊዜ ሊኖረው ቻለ? እያልኩ ሳወጣና ሳወርድ በፈገግታና በትእግስት ይጠብቀኝ ነበር፡፡ እኔ፡- “ስለ ሰው ፍጥረት ከሚያስገርሙህ ነገሮች መካከል ጥቂቱን ንገረኝ” አልኩት፡፡ ጠቢቡ - •  “ልጆች ሳሉ መሰልቸታቸውና ትልቅ ለመሆን መሮጣቸው … ካደጉ በኋላ ደግሞ ልጅ መስሎ ለመታየት መሯሯጣቸው ያስገርመኛል … •  ገንዘብ ለማካበት ጤንነታቸውን ማጣታቸው … ጤናቸውን ለመመለስ ደግሞ እንደገና ያንኑ ገንዘብ ማፍሰሳቸው ያስደንቀኛል … •  ስለ ነገ በመጨነቅ ዛሬን ለመኖር አለመቻላቸውና ከዛሬም ሆነ ከነገ ሳይሆኑ መንከራተታቸው ያስገርመኛል … •  ልክ እንደማይሞት ሰው መኖራቸውና ልክ እንዳልኖረ ሰው ተጽእኖ ቢስ ሆነው መሞታቸው ያስገርመኛል፡፡ ይህን ጠቢብ ዝም ብለው ሌሎች ሃሳቦች እንደሚጨምር እየተሰማኝ በማቋረጥ፣ “ሌላ ጥያቄ ልጠይቅህ?” አልኩት፡፡ ጠቢቡ፡- ደስ በሚያሰኝ ፈገግታ ፈቃደኝነቱን ገለጠልኝ፡፡ እኔ፡- “የሰው ልጅ ሁሉ አባት ብትሆን ለሰው ልጆች እንዲያደርጉ ከምትመክራቸው ነገሮች መካከል ጥቂቶቹን ንገረኝ” አልኩት፡፡  ጠቢቡ (ረዥም ጺሙን ዳበስ ዳበስ በማድረግ ካሰበ በኋላ)፡- •  ማንም ሰው እንዲወዳቸው ማስገደድ እንደማይችሉ፣ ነገር ግን ማድረግ የሚችሉት የሚወደድ ማንነትን ማሳደግ ብቻ እንደሆነ እንዲያወቁ እመክራቸው ነበር፡፡ •  መልካም ማንነትንና የተመሰከረለት ማህበራዊ ሕይወት ለመገንባት አመታት እንደሚፈጅ፣ ለማፍረስ ግን አንድ ደቂቃ እንደሚፈጅ እንዲያውቁ አስተምራቸው ነበር፡፡ •  የሕይወታችቸውን አቅጣጫ የሚወስነው ያላቸው ንብረትና ሃብት ሳይሆን በሕይወታቸው ያስጠጓቸው የወዳጆች አይነት እንደሆነ እንዲገነዘቡ አሳስባቸው ነበር፡፡ •  ታላላቅ ሕልሞችን ለማለምና ከግባቸው ለማድረስ የሚያስፈልገው ታላቅ ሰው መሆን ሳይሆን ከግብ ለመድረስ የቆረጠ ማንነት እንደሆነ እንዲያውቁ የተቻለኝን አደርግ ነበር፡፡ •  ሃብታም ሰው ብዙ ገንዘብና ቁሳቁስ ያለው ሰው ሳይሆን የሚያስፈልገውን ነገር ያወቀ ሰው እንደሆነ እንዲያውቁልኝ እጥር ነበር፡፡ •  ራሳቸውን ከሌላው ጋር ማነጻጸርና ማወዳደር እንደማይገባቸውና ከእነርሱ የሚያንስ ሰው እንዳለ ሁሉ የሚበልጥም ሰው የመኖሩን እውነታ እንዲቀበሉት አስረዳቸው ነበር፡፡ •  አመለካከታቸውን መቆጣጠር እንዳለባቸው አለዚያ አመለካከታቸው እነሱን እንደሚቆጣጠራቸው እንዲማሩ እሞክር ነበር፡፡ •  እጅግ በጣም የሚወዷቸውና የሚያከብሯቸው ነገር ግን ያንን በቅጡ ለመግለጽ የማይሆንላቸው ብዙ ወዳጆች እንዳሏቸው አስረዳቸው ነበር፡፡  •  እውነተኛ ጓደኛ ማግኘት እጅግ ከባድ እንደሆነ፣ ያንን ያገኘ ግን የሕይወቱን አብዛኛውን ችግሩን እንዳቃለለ እንዲያውቁ እመክራቸው ነበር፡፡ •  የቅርብ ወዳጆቻቸውን ለማቁሰል ሰከንድ እንደሚበቃ ለመፈወስ ግን አመታት እንደሚፈጅ እንዲገባቸው እጣጣር ነበር፡፡ •  ሰዎችን ለመቆጣጠር በመሞከር እንደሚያጧቸው፣ ምርጫቸውን በማክበር ነጻነታቸውን በመስጠት ግን ለዘለቄታው ወዳጆች እንደሚያደርጓቸው እንዲገነዘቡ ለማድረግ እሞክር ነበር፡፡ •  የውስጥ ሰላም ለማግኘት ከሰዎች ይቅርታን ማግኘት ብቻ ሳይሆን ራሳቸውንም ይቅር ማለት እንደሚገባቸው እንዲያስታውሱ አሳስባቸው ነበር፡፡ •  ከመናገር በሚቆጠቡበት ነገር ላይ ጌታ፣ በልቅነት ለሚናገሩት ንግግር ደግሞ ባሪያ ሆነው እንደሚኖሩ አሳውቃቸው ነበር፡፡ •  እውነተኛ ደስታ የውሳኔ ጉዳይ እንደሆነ፣ በማንነታቸውና ባላቸው ነገር ደስተኛ መሆን፣ አለዚያ በቅንአትና በፉክክር ወጥመድ ውስጥ እንደሚገቡ አስገነዝባቸው ነበር፡፡ •  በአጭሩ በዋናው የሕይወት ነገር ላይ ያተኮረ ዝንባሌ ቢኖራቸው እመክራቸዋለሁ፡፡ @Human_Intelligence @Human_Intelligence
Показати все...
👍 12👏 2
ሶፋ ወይስ አልጋ? አስፈላጊው ነገር ላይ የማተኮር ምስጢር! “ወሳኙና ትኩረታችንን ልንጥልበት የሚገባው ነገር ሰው የሚያይልንና የሚያደንቅልን ነገር ላይ ሳይሆን ለሕልውናችንና ለእድገታችን አስፈላጊ የሆነው ጉዳይ ላይ ሊሆን ይገባዋል” የትኩረት አስፈላጊነት የገባቸው ሰዎች የሰዎችን አድናቆት ከማግኘት የዘለለ የሕይወት ዘይቤ ያዳበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ሰዎች አይተውላቸው “ደስ ይላል” ብለው የሚያደንቁላቸውን ነገራቸውን የማስዋብን አስፈላጊነት ባይክዱም ከዚያ የበለጠ ትኩረት የሚገባው ነገር ግን ለእድገታቸውና ለሕልውናቸው ወሳኝ የሆነው ነገር እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ ትኩረታቸውም በዚያ ላይ ነው፡፡   አንድ ሰው በሚኖርበት ማሕበረሰብ አካባቢ አንድን ጥናት ማድረግ ፈለገ፡፡ ከጥናቱ ሊያገኝ የፈለገው እውነታ ይህንን ይመስላል፡፡  በአንድ በኩል ትኩረታቸው ከላይ ለሰዎች የሚታየውን ብቻ ቀባ ቀባ ማድረግ የሆነና ለታይታ ብቻ የሚኖሩ ሰዎችን የሕይወት ሁኔታ ማወቅ ፈለገ፡፡ በሌላ ጎኑ ደግሞ ለታይታ ብቻ ሳይሆን በትክክለኛውና በሕይወት ላይ ለውጥ በሚያመጣው ነገር ላይ የሚያተኩሩ ሰዎችን ሁኔታ መገንዘብ ተመኘ፡፡ ይህንን ሁኔታ በቀላሉ ለማወቅ የሚችልበትን ዘይቤ ሲፈልግ አንድ ነገር ብልጭ አለለት፡፡ በየሰፈሩ እየተዘዋወረ ፈቃድን ባገኘበት ቤት ሁሉ እየገባ አንድን ጥያቄ መጠየቅ ጀመረ፡፡ ጥያቄው አጭርና ግልጽ ነበር፡- “በቤትዎት ካለው ሶፋ እና አልጋ በዋጋ የትኛው ይበልጣል? እነዚህንስ እቃዎች ሲገዙ ብዙ ትኩረት የሰጡበት የትኛውን ነው? ብዙ ዋጋ ላወጡበት እቃስ ያንን ያህል ዋጋ እንዲያወጡ ያነሳሳዎት ምንድን ነው?” የሚል ነበር፡፡ እነዚህን ሶስት ጥያቄዎች ከጠየቀ በኋላ የሰዎቹን የአኗኗር ሁኔታ በቀስታ ያጤን ነበር፡፡ በመቶ የሚቆጠሩ ቤቶችን በመጎብኘት ይህንን መጠይቅ ለማቅረብና መረጃ ለመሰብሰብ ወደ አንድ አመት ፈጅቶበታል፡፡ በመጨረሻ ያገኘው መልስ ሲጨመቅ አስገራሚ ስእል አመላከተው፡፡ በዚህ ጥናታዊ መጠይቅ ላይ ከተሳተፉት ሰዎች አብዛኛዎቹ ለገዙት አልጋ ካወጡት ዋጋ ይልቅ በብዙ እጥፍ የከፈሉት ለሶፋቸው ነበር፡፡ ከዚህ በላይ ግዢውን ሲፈጽሙ ብዙ አማራጭ ለማግኘት ጊዜን የወሰዱትና ብዙ ሰው ያማከሩበት እቃ ሶፎውነበር፡፡ አልጋ ለመግዛት ካወጡት ገንዘብና ለምርጫ ካሳለፉት ጊዜ ይልቅ በሶፋ ላይ የበለጠ ገንዘብና ጊዜ የማውጣታቸውን ምክንያት ሲጠየቁ የሰጡት መልስ ሲጨመቅ፣ “ሰዎች ሲገቡ የሚያዩት ሶፋውን ስለሆነ ነው፣ አልጋውንማ ማን ያየዋል?” የሚል ነበር፡፡ ግኝቱ ይህ ነው፡- አንድ ሰው በቀን ውስጥ በአማካኝ ሰባት ወይም ስምንት ሰዓታትን በአልጋው ላይ ያሳልፋል፡፡ በቀን በሶፋው ላይ ተቀምጦ የሚያሳልፈው ጊዜ ግን በአማካኝ ከሶስትና ከአራት ሰዓት በላይ አይሆንም፡፡ ስምንት ሰዓታት ሰውነቱን ጥሎበት የሚያሳልፈው ይህ አልጋ የተሰኘው ነገር በአካላዊ ጤንነቱ ላይ ይህ ነው የማይባል ስፍራ አለው፡፡ በተጨማሪም ከማይመች አልጋ የሚመጣ የእንቅልፍ ማጣት ችግር ለቀን ተግባር ስኬታማነት ወሳኝ መሆኑም እሙን ነው፡፡ አስፈላጊ ከሆኑት  በሕልውናችንና በስኬታማነታችን ላይ ዘላቂ ተጽእኖ ከሚያመጡት የሕይወታችን ጉዳዮች ላይ ትኩረታችንን ማንሳት ብዙ አሉታዊ ተጽእኖዎች አሉት፡፡ እንዲህ አይነቱ አካሄድ ከታይታ ወደማያልፉ ነገሮች እንድንዞርና ብዙ ውድ ነገሮቻችንን እንድናባክን አሳልፎ ይሰጠናል፡፡ ለምሳሌ ጊዜአችንን፣ ገንዘባችንንና ሃሳባችን በተለያዩ ጊዜአዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የመበታተን የሕይወት ዘይቤ ውስጥ እንገባለን፡፡ ትኩረቱን ከጊዜአዊውና ለታይታ ከሆነው ነገር ላይ በማንሳት ወደ አስፈላጊውና ወደ ዘላቂው ነገር ያዞረ ሰው ለጊዜው ሰዎች አይተው የሚያደንቁለት ነገር ባይኖረውም እንኳ ለነገ እንደሚሰራ ያውቀዋል፡፡ የሚታየውንና ጥቅሙ ውስን የሆነውን የኑሮአችንን ሁኔታ ከማይታየውና ጥቅሙ እጅግ የላቀ እንዲሁም ደግሞ ዘላቂ ከሆነው ሁኔታ ለመለየት ልናስታውሳቸው የምንችላቸው እውነታዎች አሉን፡፡ ምናልባት ለረጅም አመታት ከለመድነው የኑሮ ዘይቤ ለመላቀቅ ከባድ ቢሆንም እንኳ የማይቻል አይደለምና ዛሬውኑ ጉዞውን መጀመር እንችላለን፡፡ 1.  ከስውር የዝቅተኝነት ስሜት ተላቀቅ:- ለታይታ ለመኖር የመጣጣር አንዱ ምንጭ የዝቅተኝነት ስሜት ነው፡፡ ከሌሎች በታች የሆንን ሲመስለንና በዚህ ስሜት በስውር ስንጠቃ አውቀነውም ሆነ ሳናውቀው ራሳችንን ከሌላው ለማስተካከል ወይም የበለጥን እንደሆንን ለማሳየት ስንጣጣር እንታያለን፡፡ 2.  የትርጉም ማስተካከያ አድርግ:- ትክክለኛ ኑሮ ማለት እኛ ሲመቸን እንጂ በእኛ ሁኔታ ሌላው ሲገረም ማለት አይደለም፡፡ ዘላቂ ስኬት ማለት እኛ ተመችቶን ለሌላው ስንተርፍ እንጂ ኑሮአችን ወድቆ በውጫዊው “ውበታችን” ሌላው ሲገረም ማለት አይደለም፡፡ 3.  የእቅድ ሰው ሁን:- ከሰው ጋር መወዳደርን አቁምና ለራስህና ለቤተሰብህ መሻሻል ካወጣኸው እቅድ አንጻር መሮጥ ጀምር፡፡ ትክክለኛ ስኬት ማለት የት መድረስ እንደሚፈልጉ ማወቅና በዚያ አቅጣጫ በመገስገስ፣ በሂደቱም መርካት ማለት ነው፡፡ ዶ/ር እዮብ ማሞ
Показати все...
👍 7 2
Repost from TgId: 1163708603
ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው...(1ኛ ዮሐ.3፡15) “ብሔርተኛ የሆነ አምባገነናዊ አገዛዝ ለጊዜው ምክንያታዊነት በጎደለው ስሜታዊና ግልብ በሆነ አስተሳሰብ ዜጋውን ወይም “ብሔር” ብሎ ከፋፍሎ ያደራጃቸውን በመንዳት የተሳካለት ይምሰለው እንጂ፣ አገዛዙን ለማስቀጠል ሲል የሚፈጽማቸውን ግፎች በሂደት ሕዝቡ እየተገነዘበው ስለሚሄድ ምንም ዓይነት ሴራ ቢጠቀም አገዛዙ ያሰበው እቅድ ዘለቄታ ሊኖረው አይችልም፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥ ብዙሃን ይሁን አናሳ ቁጥር ባለው “በብሔር” ማንነት ላይ የተመሠረተ ማንኛውም አገዛዝ የሳይንሳዊ ፖለቲካዊ ስርአት ሳይሆን በአዕምሮ ቅዠት ህመም የተጠቃ፣ ፋሽስታዊ አምባገነን፣ ኢ-ሰብአዊ፣ ስርአተ አልበኛ፣ የወሮበላና የደንቆሮ ገዢ ቡድን ነው፡፡ በአጠቃላይ “የብሔርተኛ ፋሽስታዊ አገዛዝ በፖለቲካ ሳይንስ የተቃኘ ሕዝባዊ አስተዳደር ሳይሆን፣ ከአዕምሮ ቅዠት ህመም የመነጨ የድንቁርና አገዛዝ ነው:: በአሁኑ ዓለም የመልካም አስተዳደር ሳይንሳዊ ፖለቲካ ማለት፣ የአንድ ሀገርን ብዙሃን ሕዝብ አዕምሮ ከፖለቲካዊ ቁጭት፣ ጥላቻና በቀል ነጻ በማድረግ በኑሮ ደረጃዉ እያሳደገ የማስቀጠል ብቃት ነው፡፡ በአንድ ሀገር መንግሥታዊ አገዛዝ ላይ ብዙሃኑ ሕዝብ አዕምሮ ውስጥ ቁጭት፣ ጥላቻና በቀል ከተፈጠረ ሀገሪቱ የብዙሃን ሕዝብ ድጋፍ የተቸረው የአገዛዝ ሥርዓት ባለመሆኑ ሀገሪቱ ያልተረጋጋችና ልማቷም ዘለቄታ የሌለዉ ስለመሆኑ ማሳያ ነው፡፡ ይህም ቁጭት፣ ንዴትና ጥላቻ እያደገ በመሄድ በዋናነት በአፍሪካ ውስጥ ኢትዮጵያን የመሳሰሉትን ሀገራት ሁልጊዜ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እየከተተ ዜጋውን ወደተሻለ ኑሮ እንዳያድግ የሚገድብ ነው፡፡ ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው...(ኛዮሐ.3፡15)፡፡ አንድ ሰው ግድያ ከመፈጸሙ በፊት የሚፈጠረው የጥላቻ አስተሳሰብ ይቀድማል፡፡ የጥላቻውም አስተሳሰብ በሂደት በግድያ ድርጊት ይፈጸማል፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥ ብዙሃኑ ሕዝብ በፊት ስለሚገድለው ሰው በአዕምሮው ውስጥ  ቁጭት፣ ንዴትና ጥላቻን የሚፈጥር መንግሥት ካለ አምባገነን አገዛዝ እንጂ፣ መንግሥታዊ ስርአት አይደለም፡፡ ስርአት ማለት ማንም ሰው እንደፈለገው የማይቀያይረው፣ በሳይንሳዊ እውቀት የተደራጀ፣ ህግንና ደንብን በመከተል የታለመለትን ግብ የያዘ ተቋም  ነው፡፡ “የብሔርተኛ” አምባገነናዊ አገዛዝ ሳይንሳዊ የፖለቲካ ስርአት ሳይሆን፣ በባህሪው በቀሪው ዜጋ አዕምሮ ውስጥ ሁልጊዜ ቁጭት፣ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ ንዴትና ጥላቻን የሚፈጥር የስርአተ አልበኛና የአሸባሪነት አገዛዝ ነው፡፡ የብዙሃኑ ህዘብ አዕምሮ ለቁጨት፣ ለንዴትና ለጥላቻ የሚዳርግ አገዛዝ ይዋል ይደር እንጂ፣ አንድ ቀን በብዙሃኑ ህዝብ አመጽ በውርደት መወገዱ እንደማይቀር የአሁኑ ዓለም ታሪካዊ ሃቅ ነው፡፡ በአሁኑ ዓለም “በብሔር” ማንነት ላይ የተመሠረተ ፋሽስታዊ አገዛዝ በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚዊ እንዲሁም በኃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ እንኳ ሳይቀር የበላይነቱን በማረጋገጥ ሰውን ከሰው የሚለይ፣ የሚያገልና አድልኦን የሚፈጽም ሳይንሳዊ ያልሆነ አገዛዝ ነው፡፡ ስለሆነም በብዙሃኑ ሕዝብ ዘንድ ምንጊዜም ቢሆን ተቀባይነት ስለሌለው ሁልጊዜ ሰላምና መረጋጋትን በማሳጣት ለአብዮት የሚዳርግ ነው፡፡ በ”ብሔር” ማንንነት አዕምሮ በተቃኘ ፋሺስታዊ አገዛዝ ውስጥ ሁሉም ባይቀበለውም ነገር ግን እጅግ አብዛኛው ዜጋ በ”ብሔር” ማንንነት አዕምሮ ቅዠት ህመም ይለከፋል፡፡ የ”ብሔርተኛ” ፋሽስታዊ አገዛዝ የስልጣኑን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሲል የሚያራምዳቸው መሠረታዊ ሴራዎች አሉት፡፡ እነዚህ ሴራዎችም በህዝብ አዕምሮ ውስጥ ቁጭት፣ ንዴትንና ጥላቻን በአገዛዙ ላይ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመሩ ይሄዳሉ፡፡ በመሆኑም ይህ ቁጭት፣ ጥላቻ ይዋል ይደር እንጂ “በብሔር” ማንነት ተከፋፍሎ የነበረውን ሕዝብ ወደ መተባበበር ይገፋፋውና አገዛዙን ለማስወገድ የሞት ሽረት ትግል ውስጥ ሳይወድ በግዱ ይገባል፡፡ ሰብስቤ አለምነህ @Zephilosophy @Zephilosophy
Показати все...
👍 6