uk
Feedback
Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

Відкрити в Telegram

ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን! Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf! Freedom to our People – Prosperity to our Nation!

Показати більше
2025 рік у цифрахsnowflakes fon
card fon
163 172
Підписники
+324 години
+1157 днів
+40130 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ላዺሶ ጌ. ዴሌቦ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ማለፋቸውን በታላቅ ኀዘን ሰማሁ። ነፍሳቸውን በዐጸደ ገነት እንዲያኖርልን እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንዲሰጥልን እመኛለሁ።
Показати все...
02:51
Відео недоступнеДивитись в Telegram
በባህር ዳር ከተማ በነበረን ጉብኝት የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን እንዲሁም ከተማዋን ለቱሪዝም ዘርፍ ምቹ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ተመልክተናል። የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ባስቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ደረጃውን የማሻሻል ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ነው። ስታዲየሙ 52 ሺህ ተመልካቾችን መያዝ የሚችል ሲሆን የወንበር መግጠምና የሳር ንጣፍ ስራዎች ተጠናቀዋል። የመብራት ዝርጋታን ጨምሮ ሌሎች የስታዲየም ውስጥ መሰረተ ልማቶችም በፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን መሠረት በማድረግ በባህር ዳር ጣና ሀይቅ ዳርቻ እየተገነባ ያለው ፈለገ ጊዮን ሪዞርትን የተመለከትን ሲሆን ሪዞርቱ ወደ ስራ ሲገባ የከተማዋን ተሪዝም ከማነቃቃት ባሻገር ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር ይሆናል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በባህር ዳር እያስገነባ ያለው የኢትዮ-ፌሪስ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት በጣና ሃይቅ ዳርቻ እየተከናወኑ ካሉ ሌሎች የልማት ስራዎች ጋር ተደምሮ ባህር ዳርን ወደ አዲስ የከተሜነት ምዕራፍ ለመሸጋገር ትልቅ ሚና ያበረክታል።
Показати все...
11.72 MB
02:39
Відео недоступнеДивитись в Telegram
በጎርጎራ ጣናነሽ የተሰኘችዉን ጀልባ ሥራ አስጀምረናል። በጣና ውሃ ላይ እየቀዘፈች ባሕር ዳር ከተማን ከጎርጎራ ኤኮ ሎጅ ማገናኘት ጀምራለች። ከ180 ተጓዦች በላይ የማጓጓዝ አቅም ያላት ጣናነሽ ለጉብኝት፣ ለመዝናናት እና አስደማሚውን የጣና ሀይቅ የተፈጥሮ ከባቢ ለመጎብኘት ወደ ጎርጎራ ኤኮ ሎጅ የሚደረገውን ጉዞ የበለጠ ምቹ አድርጋዋለች። In Gorgora, we’ve launched the long-awaited voyage of the Tananesh Ferry, now gracefully cruising the waters of Lake Tana, connecting Bahir Dar City with the newly established Dine for Generations project — Gorgora Eco Lodge. With a capacity of over 180 passengers, Tananesh makes the remarkable Gorgora Eco Lodge more accessible than ever before; a truly worthy destination to visit, relax, and admire the breathtaking natural beauty of Lake Tana.
Показати все...
7.08 MB
12:18
Відео недоступнеДивитись в Telegram
ጉልበት ይሸሻል፣ ጊዜ ይሸሻል፣ ስልጣን ይሸሻል፣ ሁሉ አላፊ ነው ፣ የማያልፈው እንደዚህ ያለው ታላቅ ስራ ነው።
Показати все...
25.26 MB
02:07
Відео недоступнеДивитись в Telegram
በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል። ፕሮጀክቱ 870 ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን 17000 ሄክታር መሬት በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል። የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ መልኩ ተጠናቋል። የቀሩት ሥራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ ይገኛሉ። የመገጭ ግድብም በሚጠናቀቅበት ወቅት የአካባቢውን የግብርና ምርታማነት የሚያሳድግ ይሆናል። Daawwannaa Goondaritti taasifneen haala hojii Misooma Jallisii Magac gamaaggamneerra. Piroojektichi hektaara 870 irra kan buufate yoo ta'u, lafa hektaara 17,000 dhiyeessii jallisiitiin misoomsa jedhamee eegama. Hojii ijoo piroojektichaa kan ta'e laga jallisuun haala milkaa'een xumurameera. Hojiiwwan hafanis yeroo qabameef keessatti hojjetamaa jiru. Jallisiin Magac wayita xumuramu homishtummaa qonnaa naannichaa kan guddisu ta'a.
Показати все...
45.01 MB
08:10
Відео недоступнеДивитись в Telegram
የገጠር ሽግግርን ለማረጋገጥ አንዱ መንገድ የእርሻ ማሽነሪዎችን ማበራከት ነው ።
Показати все...
28.53 MB
ዛሬ በምስራቅ ሸዋ ዞን የነበረን ጉብኝት በክረምት የስንዴ ምርት ሥራዎች የተገኘውን ውጤት የምርት አሰባሰቡን በመመልከት ለመገምገም እና የበጋ ስንዴ ሥራ ማስጀመር ላይ ያተኮረ ነበር። በዚያው አካባቢ የሙዝ፣ ፓፓያ እና አሳ ክለስተር ሥራዎችንም ተመልክተናል። ነባሩ ባሕላዊ የግብርና ዘዴ አሁንም ያለ ቢሆንም በሰፊው ለማረስ የሚያስችለው ሜካናይዜሽን እያደገ በመሄዱ የአካባቢውን የግብርና ብቁነት እና ምርታማነት እያሳደገ ይገኛል። ወደኋላ መለስ ብለን የነበረውን አሰራር ስንገመግም እነዚህን መሰል ዘመናዊ ዘዴዎችን ከብዙ አመታት በፊት እንደ ሀገር ጀምረን ቢሆን ኖሮ የግብርና ምርታችን በከፍተኛ ደረጃ የተለየ ይሆን እንደነበር እንረዳለን። ዛሬ ከአመት ወደ አመት እየጨመረ የሚሄድ ምርታማነት እየተመለከትን እንገኛለን። ለማደግ ምንም አይነት የውጭ ድጋፍ አይመጣም። እውነተኛውን የሀገራችን ለውጥ የሚመራው የራሳችን ጽናት፣ ፈጠራ እና የሥራ ትጋት ነው።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram