Jafer Books 📚
Відкрити в Telegram
የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !! አድራሻችን ለገሃር ተወልደ ህንጻ አራት ኪሎ ብርሃና ሰላም ፊት ለፊት አብርሆት ቤተመጻሕፍት ግቢ ውስጥ ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ሳሪስ አዲሱ ሰፈር ጀሞ ለቴሌግራም https://t.me/Jafbok ለፌስቡክ https://www.facebook.com/jaferbookshop?mibextid=ZbWKwL ለዌብሳይት www.jaferbooks.com
Показати більше2025 рік у цифрах

30 545
Підписники
-124 години
+607 днів
+21530 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በእስጢፋኖስ ኃይለማርያም የተዘጋጀው " የአፋር ምርኮኞች " መጽሐፍ ለንባብ በቃ ::
❤ 12
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ምናልባት… መንገድ የሕይወት ምሳሌ፣ የ“ትናንት” አስረጂ ማሟሻ እና የ“ዛሬ” ድንበር ጠባቂ እንዲሁም የ“ነገ” ተስፋ ሥሪት ውጤት ይሆን ይሆናል፡፡
ለዚያም ይሆናል… ከ”ትናንት” “ዛሬ” እና ነገ ቅንብብ ያመልጥ በሚሳነው ሕይወታችን… ታመልጥ በማትፈልግ ነፍሳችን… የሥሪቱ አካል ይሆን በወደደ ጠጠር እና አቧሯ አልባ የሀሳብ መንገድ ይገለጥልን የወደድነው ይፈጸም የምንጠብቀው፡፡
ለዚያም ይሆናል… “ዛሬ ቅዳሜ አይደለም” ብዬ ቀን እክድ እወድ የምሆነው… ወይም “ትናንት እመጣለሁ” ስል የዙረት አቅጣጫዬን ከተፈጥሮ የማጣርሰው፡፡
ምናልባት… ተፈጥሮ የእኔ፣ የአንቺ እና የአንተ ስምምነት ይሆን ይሆናልና!
❤ 12
መዲና ዲጂታል መጽሔት
ቅጽ 2 ቁጥር 2 እነሆ
የዚህ ዕትም የቤት ለእንግዳ ዐምዳችን ከጋሽ ኃይለ መለኮት መዋዕል ጋር ያደረግነው ቆይታ ነው። ከዚያ በተጨማሪ ሱራፌል አየለ በወጉ ልንወያይበት ስለሚገባው ጾታን መሠረት ስላደረገ ጥቃት ወደመጨረሻ አካባቢ የሚለን ነገር አለው። ሌሎችም ቤተኛ እና እንግዳ ዐምደኞች አሉ። የተለመዱት የሽርሽር፣ የአጤሬራ እና የእፍታ ዐምዶች እንደተጠበቁ ናቸው። ሀሳብ አስተያየታችሁን ከታች በተጠቀሱት የኢ-ሜይል አድራሻችን ወይም የመዲና ዲጂታል መጽሔት ቦት ላይ ይላኩልን። በተለይ ሱራፌል አየለ ያነሣው ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ላይ ሰፊ ውይይት እንዲኖር ስለምንፈልግ ሀሳባችሁን ብታሳውቁን ደስ ይለናል። ጽሑፋችሁን መላክም ሆነ ማስታወቂያ ማሠራት የምትፈልጉ በተጠቀሱት አድራሻዎቻችን ቢልኩልን ይደርሰናል።
https://t.me/Medinamagazine
medinadigitalmagazine@gmail.com
ወይም @medinamagazinebot
ከዚህ በፊት የወጡትን ቅጾች Medina DM Bot👆 በተሻለ ጥራት ያገኟቸዋል።
በተጨማሪም በፌስቡክ፣ በዋትሳፕ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን!
https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL
https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj
https://chat.whatsapp.com/GTCtybsFRDGKTtzu8c1Sgc?mode=ac_t
ቅጽ2 ቁጥር 2.pdf12.64 MB
❤ 7🕊 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ገጣሚና ደራሲ ታገል ሰይፉ " የእኔ ደማቅ ሰዎች " ሲል የሰየመው መጽሐፉ ለንባብ በቃቷል :: መጽሐፉ በሁሉም መደብሮቻዥን ይገኛል ::
❤ 18
01:03
Відео недоступнеДивитись в Telegram
#ንባብ_ለሕይወት_2017
በኤግዚብሽን ማዕከል አይቀርም !
ልዩ ቅናሽ አለን ::
ብዙ አማራጭ እንይዛለን !!
8.09 MB
👍 16❤ 9
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በሽመልስ አሰፋ የተዘጋጀው " ቅምሻ - የኢትዮጵያ ትንሳኤ እና የሽግግር ጉዞ " መጽሐፍ ለንባብ በቃ :: መጽሐፉ በመደብሮቻችን ይገኛል ::
❤ 10🕊 4
00:40
Відео недоступнеДивитись в Telegram
#ንባብ_ለሕይወት_2017
ዝግጁ ናችሁ ?
ከሐምሌ 24 - ሐምሌ 27 - በኤግዚብሽን ማዕከል ::
5.07 MB
🔥 12👍 4❤ 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
እነዚህ ከታች የምታዩዋቸውና በቅርብ ቀን ለንባብ የበቁ እህትማማች መጻሕፍት---
-- ትውልድ ያንፃሉ፤ ለመልካም ተግባራትና ለተሻለ ኑሮም ያተጋሉ ከሚባሉ የመጻሕፍት ዘርፎች የሚመደቡ ናቸው። አንብበንና አነብንበን ጊዜያዊ መነቃቃት የሚፈጥሩብን ሳይሆኑ፣ በተግባር እንድንሞክራቸው ራሳችንንም እንድንፈትንባቸው የሚያደርጉ ናቸው። በተለይ ሥራ አጥ፣ ሥራ ፈትና ሥራ ጠል ለሚበዛባት አገራችን ከፍቱን መድሃኒቶች መካከል አንዱ፣ "ኒዮሮ ሳይንስ ለሥራ ፈጠራ" እንዴት እንደሚያግዝ መረዳት እና የ"ኒዮሮ አመራር ሳይንስ" ምንነትን በጥልቀት መገንዘብ ነው።
አንብቤ እንደጨረስኳቸው በእነዚህ መጻሕፍት የተነሱ ሃሳቦች ባክነው እንዳይቀሩ ምን መደረግ አለበት ብዬ ራሴን ጠየቅሁ። የመጽሐፉ ባለቤት ያሬድ ኢሳያስ (ዶ/ር)ም ሆነ እሱን መሰል ሙያተኞችና 'አእምሮን ተጠቅሞ ነገን መፍጠር እንደሚቻል' የሚያምኑ አማኞች---በእነዚህ መጻሕፍት መነሻነት በየብዙሃን መገናኛው፣ በየከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱና መሰል ስፍራዎች የአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎችን ቢሰጡ፣ ተለውጠው የሚለውጡ ንቁና ብቁ ልጆችን በአጭር ጊዜያት ማፍራት ይቻላል ብዬ አምናለሁ።
ሥራን መፍጠር የሚችሉ ወጣቶች በዙርያችን ባንዣበቡ ቁጥር ተስፋ የሚቆርጡ፣ በቀላሉ ለሱስ እጅ የሚሰጡና ራሳቸውን ለማጥፋት የሚፈጥኑ እግሮች አደብ እየገዙ ይመጣሉ ብዬ አምናለሁ። ይህ እንዳይሆን ደግሞ እንደ ያሬድ ኢሳያስ እንዲህ በትጋትና በንቃት የተጻፉ መጻሕፍትን ማንበብና ማስነበብ አንደኛው መንገድ ነው። ያኔ የደበዘዘው ሲፈካ፣ የዘመመውም ሲቃና ይታወቀናል።
( ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ስለመጽሐፉ አስተያየት የሰጠው )
❤ 21
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ገበያ ላይ ጠፍቶ የነበረው “የከተማው መናኝ” መጽሐፍ በድጋሚ ለንባብ በቃ፡፡
የተወዳጁን ሙዚቃኛ ኤልያስ መልካ ሕይወትና ሥራዎች የሚተርከው “የከተማው መናኝ” መጽሐፍ በአንባብያን ጥያቄ መሰረት በድጋሚ ለገበያ መብቃቱ ተነገረ፡፡
በደራሲና ጋዜጠኛ ይነገር ጌታቸው (ማዕረግ) የተዘጋጀው መጽሐፉ ለንባብከ በቃበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል፡፡
በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራን ያኖረው ኤልያስ መልካ ሕልፈተ ሕይወቱ የፊታችን መስከረም ስድስት ዓመት ይሞላዋል፡፡
“የከተማው መናኝ” መጽሐፍ የተናፋቂውን ኤልያስ መልካ አነጋጋሪ የግል ፍልስፍና እና የሕይወት ውጣ ውረድ የሚተርክ ሲሆን በወጣበት ዓመትም በኢ-ልብወለድ ዘርፍ ከዓመቱ አምስት ምርጥ መጽሐፍት አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡
ይነገር ጌታቸው (ማዕረግ) በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ላይ ምርምርን በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን በ2015 ዓ.ም ሙዚቃ፣ታሪክና ፖለቲካ ላይ ያተኮረውን “ጠመንጃና ሙዚቃ” የተሰኘ መጽሐፍ ለአንባብያን አድርሷል፡፡
“የከተማው መናኝ” መጽሐፍ ከዛሬ ሰኞ ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የጃፋር መጽሐፍ መድብሮች ገበያ ላይ ይውላል፡፡
❤ 27🥰 5👎 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ትናንት - ከዛሬ በፊት የነበረ፣ ያለፈ፣ የማይመለስ፣ የተሰናበተ ቀን፡፡
ዛሬ - አሁን፣ በእጅ ያለ፣ እየኖርንበት ያለ ቀን፡፡
መዝገበ ቃላቱ ፍቺ ይሆን ዘንድ ይህን ተናግሯል፡፡ እውነት ይሆን ታምኖ ሠፍሯልና እናምን ተገድደናል፡፡
እውነት ከሆነ፤ ጥያቄ አልባ በነበር እምነት እና እሳቤ ተቀብለነው ከነበር ከ “ትናንት” እንላቀቅ፣ ወደኋላ አንጓዝ እያወቅን በቁጭት መብሰልሰላችን፣ በደስታ ሲቃ እናስበው በነበር ኀላፊ ቀን አሁንም ወደ “ትናንት” አሻግረን እንመለከት እንዴት ተቻለን?
እውነት ከሆነ፤ በእጅ እንዳለ ባመንነው፣ እናምን በተገደድነው “ዛሬ” ዛሬን ትተን ነፍሳችን ወደ “ትናንት” እና “ነገ” ስትቅበዘበዝ፣ የ“ዛሬ”ን ዋጋ እና ሁለንተና ንቃ “ነገ” ላይ “ትናንት” እስኪሆን ለሚጠብቅ “ዛሬ” ለምን ራሳችንን አስገዛን?
👍 10❤ 2🥰 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በዶክተር ወዳጄነህ መሐረነ የተዘጋጀው " 101 የጥበብ ጠብታዎች " መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል :: መጽሐፉ በመደብሮቻችን ያገኙታል ::
👍 16❤ 3🔥 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በዲያቆን አቤል ካሳሁን የተዘጋጀው " ቅዱስ ጳውሎስ " የተሰኘው መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል :: መጽሐፉንም በመደብሮቻችን ይገኛል ::
❤ 58🥰 1
