uk
Feedback
ETHIO-MEREJA®

ETHIO-MEREJA®

Відкрити в Telegram

News & Media Company® USA : Washington Addisababa, Ethiopia🇪🇹 . Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot

Показати більше
2025 рік у цифрахsnowflakes fon
card fon
110 193
Підписники
-4824 години
-3207 днів
-1 32830 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሳውዲ አረቢያ ኢራን "በኳታር ላይ" የፈጸመችውን ጥቃት አወገዘች **** የሳውዲ አረቢያ መንግሥት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በኩል ባወጣው መግለጫ ኢራን ማምሻውን "በኳታር ላይ" የፈጸመችውን ጥቃት በጽኑ አውግዟል። የሳውዲ መንግሥት በመግለጫው ኢራን "በኳታር ላይ" ያደረሰችውን የሚሳኤል ጥቃት በጽኑ አውግዞ፤ ድርጊቱ የኳታርን ሉዓላዊነት፣ ዓለም አቀፍ ሕግና ቻርተርን እንዲሁም የመልካም ጉርብትና መርሆን የጣሰ ነው ብሏል። አያይዞም፥ ድርጊቱን ከማውገዝ ባሻገር ኳታር ሉዓላዊነቷን ለማስከበር የምትወስዳቸውን እርምጃዎች ሳውዲ አረቢያ ትደግፋለች፤ ከጎኗ በመሆን ለማገዝም ዝግጁ ናት ብሏል።
Показати все...
38👎 14👍 4😁 1
ኢራን በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ የሚሳኤል ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ኳታር በኢራን ለተቃጣባት ጥቃት ተመጣጣኝ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቃለች❗️። ማምሻውን በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን ማጥቃት የጀመረችው ኢራን በምዕራባዊ ኢራቅ የሚገኘውን አል-አሳድ የጦር ሰፈር በሚሳኤል መደብደቧን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። ከሰዓታት በፊት የኢራን መንግሥት በኒውክሊየር መሰረተ ልማቶቹ ላይ በአሜሪካ ለተፈጸመበት ጥቃት ምላሽ እንደሚሰጥ ዝቶ ነበር። በተያያዘ ኳታር በኢራን ለተቃጣባት ጥቃት ተመጣጣኝ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቃለች። የኳታር መከላከያ ሚኒስትር፥ ኢራን ኳታር በሚገኘው አል-ኡዴይድ የጦር ሰፈር ላይ ሚሳኤል ተኩሳለች፤ በዚህም ኢራን የኳታርን ሉዓላዊነት ተዳፍራለች ብለዋል። ኳታር ከኢራን ለተቃጣበት ጥቃት ተመጣጣኝ ምላሽ የመስጠት መብቷ በዓለም አቀፍ ሕግ የተጠበቀ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። አክለውም፥ የኳታር የአየር መከላከያ ሥርዓት የከኢራን የተተኮሱ ሚሳኤሎችን በማክሸፍ ጥቃቱን መመከቱንም ተናግረዋል።
Показати все...
53😁 20👏 3🤔 1😭 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ቴምር ሪልስቴት ‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ ‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ  👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ 👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ 👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ 👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ 👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል 👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ ለበለጠ መረጃ ይደውሉ        👇👇👇👇👇👇      +251939770177      +251996856273 https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant WhatsApp. https://wa.me/251939770177 Telegram :@KalTemerRealEstate
Показати все...
14
Фото недоступнеДивитись в Telegram
💸💲 ይመልሱ 10,000 ብር ያሸንፉ💲💸 በእግር ኳስ ታሪክ ብዙ የፊፋ ያለም ዋንጫ ያሸነፈ ሀገር ማን ነው❓ ትክክለኛውን ውጤት በአፍሮ ስፖርት የቴሌግራም  ወይም ፌስቡክ ቻናላችን ላይ ገብተው በመመለስ 10 ሺ ብር ይሸለሙ! https://t.me/afrosportsbet/663 https://www.facebook.com/share/p/1GfvEbhS7B/
Показати все...
14
አሜሪካ “የእኩለ ሌሊት መዶሻ” ባለችው የኢራኑ ጥቃት የትኞቹን የጦር መሳሪያዎች ተጠቀመች? የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች ኢራን ውስጥ የሚገኙ ሦስት የኒውክሌር ተቋማትን በቦምብ መደብደባቸውን ማሳወቃቸው ይታወሳል። አሜሪካ “የእኩለ ሌሊት መዶሻ” የሚል ስያሜ በሰጠችው ኦፕሬሽን ጂቢዩ 57 ወይም ማሲቭ ኦርዲናንስ ፔኔትሬተር (ኤምኦፒ) ቦምብ ተጠቅማለች፡፡ ይህ ‘ምሽግ ደርማሽ’ ቦምብ 13 ሺህ 600 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን ከመፈንዳቱ አስቀድሞ እስከ 60 ሜትር ድረስ ወደ መሬት ሰርጎ የመግባት አቅም ያለው ነው፡፡ ቦምቡ 'ቢቱ ስቲልዝ' በተባለው አውሮፕላን አማካኝነት ከዒላማው ከ12 ሺህ እስከ 15 ሺህ ሜትር ከፍታ ላይ የተጣለ ሲሆን ያለው ክብደት እና የመሬት ስበት በሚያርፈበት ቦታ ላይ ውድመት እንዲያስከትል ያደርጉታል፡፡ የተቀመጠለትን ዒላማ እንደማይስት የሚነገርለት 'ምሽግ ደርማሹ' ቦምብ በውስጡ በተገጠመለት ጂፒኤስ በመጠቀም ነው ጥቃቱን የሚያደርሰው፡፡ በዚህም ከተጣለ በኋላ ምንም ዓይነት የዒላማ ለውጥ ወይም ቁጥጥር ማድረግ አይቻልም፡፡ የአንዱ ዋጋ ከ3.5 እስከ 4 ሚሊዩን ዶላር እንደሚደርስም ተመላክቷል፡፡ ይህንን ግዙፍ ቦምብ መሸከም የሚችለው የ'ቢቱ ስቲልዝ' አውሮፕላን ባለው ቅርፅ በተለይም በፀረ-አውሮፕላን አነፍናፊ መሳሪያ ላይ ወፍ ወይም በራሪ መስሎ መታየት መቻሉ በዒላማ ማክሸፊያ እንዳይመታ ያስችለዋል፡፡ በተጨማሪም ትክክለኛ ያልሆነ የራዳር መረጃ የሚያቀብል የኤሌክትሮኒክ ቴክኒክ ያለው ነው፡፡ ሌላው አሜሪካ የተጠቀመችው ከ1 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መወንጨፍ የሚችሉት የ'ቶማሃውክ ክሩዝ' ሚሳኤሎች ናቸው፡፡ ከሰርጓጅ መርከብ ላይ የተነሱት ሚሳኤሎቹ ከምድር በታች ያልሆነ ማለትም በምድር ላይ ያለ ዒላማን ለማጥቃት የሚውሉ ናቸው፡፡ በአሜሪካ የ“ሌሊት መዶሻ ኦፕሬሽን” 30 የሚሆኑ የ'ቶማሃውክ ክሩዝ' ሚሳኤሎች ከ640 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መወንጨፋቸው ተገልጿል፡፡ በራዳር ዕይታ ውስጥ እንዳይገባ በዝቅተኛ ከፍታ ላይ መንሳፈፍ የሚችለው ሚሳኤሉ ከተወነጨፈ በኋላ የዒላማ ብሎም የአቅጣጫ ቅየራ እንዲያደርግ ማዘዝ ይቻላል፡፡ እያንዳንዱ 'ቶማሃውክ ክሩዝ' ከ1.5 እስከ 2 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ዋጋ ያለው ነው፡፡
Показати все...
76👏 9👍 3👎 3
11
የኢራን ፓርላማ ወሳኙን የሆርሙዝ የባህር ሰርጥን ለመዝጋት የቀረበውን ሀሳብ አፀደቀ ****** የኢራን ፓርላማ የአለማችን 20 በመቶ የሚሆነው ድፍድፍ ነዳጅ የሚተላለፍበት የባህር ሰርጥን ለመዝጋት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል፡፡ ፓርላማው ውሳኔውን ያስተላለፈው አሜሪካ እስራኤልን በማገዝ በኢራን ሶስት የኒውክሌር ማብለያ ተቋማት ወታደራዊ እርምጃ መውሰዷን ተከትሎ ነው። የፓርላማው ውሳኔ ተፈጻሚ የሚሆነው የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ በሚያሳልፉት የመጨረሻ ትእዛዝ መሆኑ ተነግሯል። 40 ኪሎ ሜትር ብቻ ስፋት ያለው የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ የመዘጋት አደጋ ካጋጠመው በአለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ትልቅ ተፅእኖ ሊፈጥር እንደሚችልም ተገልጿል፡፡ የኢራን ፓርላማ ያቀረበው ይህ ውሳኔ የኢራኑን መሪ የአያቶላህ አሊ ኻሚኒን የመጨረሻ ውሳኔ እየጠበቀ ነው ሲል ኒውስ ዊክ የኢራን ቴሌቪዥንን ጠቅሶ ዘግቧል። የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ፈሳሽ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ የጫኑ መርከቦች ዋነኛ መተላለፊ ሲሆን፤ እኤአ 2024 በየቀኑ ብቻ 20.3 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅና ፔትሮሊየም ተላልፎበታል ተብሏል። አሜሪካ ፎርዶውን ጨምሮ ኢራን ውስጥ በሚገኙ 3 የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ኢራን በቀጣይ ምን አይነት እርምጃ ትወስዳለች የሚለው የሚጠበቅ ሆኗል።
Показати все...
66👍 22😁 7🤯 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ቴምርሪልስቴት መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት ሽያጭ ‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት AU አፓርትመንት ሽያጭ 👉1መኝታ 75ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ 802,500ብር ሙሉ ክፍያ 8,025,000ብር 👉2መኝታ 94ካሬ 10% ቅድመ ክፍያ 1,005,800ብር ሙሉ ክፍያ 10,058,000ብር 👉2መኝታ 103ካሬ 10%ቅድ ክፍያ 1,102,100ብር ሙሉ ክፍያ 11,021,000ብር 👉3መኝታ 132ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ 1,412,400ብር ሙሉ ክፍያ 14,124,000ብር 👉3መኝታ 146ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ 1,562,200ብር ሙሉ ክፍያ 15,622,000ብር ‼️ቀሪውን 90% በ 18ዙሪ ያለምንም ጭማሪ በብር የሚከፍሉት ነው ለበለጠ መረጃ ይደውሉ        👇👇👇👇👇👇      +251939770177      +251996856273 https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Показати все...
10🥰 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🥳 ጓደኛዎችዎን ወደ አፍሮቤት ይጋብዙ እና አስደሳች ቦነስ ያግኙ! 👇 የእርስዎ ልዩ መለያዎን ለጓደኛዎ ወይም ለቅርብ ወዳጅዎ ያጋሩ ሽልማቶችን ያግኙ። 💸💰ለእያንዳንዱ አዲስ ስኬታማ ምዝገባዎች 15% ቦነስ ያገኛሉ። 🔗 አሁኑኑ ማጋራት ይጀምሩ እና ገቢዎትን ያሳድጉ! ከ https://bit.ly/3XbY3o7 ጋር ያሸንፉ።
Показати все...
5👎 1😱 1
አሜሪካ በፈፀመችው ጥቃት የኒውክሌር ብክለት አልተከሰተም - ኢራን ****** አሜሪካ ኢስፋሃን፣ ፎርዶ እና ናታንዝ በተባሉ የኢራን የኒውክሌር ማብላያ ጣቢያዎች ላይ የፈፀመችው ጥቃት የኒውክሌር ብክለት አለመከሰቱን ኢራን ገለጸች። የኢራን ብሔራዊ ሚዲያ የሀገሪቱን ብሔራዊ የኒውክሌር ደኅንነት ሥርዓት ማዕከልን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የጨረራ ቁጥጥር መሣሪዎች ጥቃቱ በደረሰባቸው አካባቢዎች ምንም ዓይነት የራዲዮአክቲቭ ልቀትን አልመዘገቡም። በጣቢያዎቹ የሚገኙ የዩራንየም ንጥረ ነገሮች ከጥቃቱ ቀደም ብሎ ወደ ሌላ ቦታ በመወሰዳቸው በአካባቢው ምንም የሚፈጠር የራዲዮአክቲቭ ልቀት እንደማይኖር እየተነገረ ይገኛል። በመሆኑም ጥቃቱ እንደተፈፀመባቸው በተጠቀሱት አካባቢዎች በሚኖሩ ሰዎች ላይ የሚደርስ አደጋ እንደማይኖር ማዕከሉ ባወጣው መግለጫ መግለጹን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል። ቀደም ብሎም እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ማብላያ ጣብያዎች ላይ ያደረሰችው የአየር ድብደባ በተመሳሳይ መልኩ በተቋማቱ ዙሪያ ምንም ዓይነት ራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገር እንዲለቀቅ አለማድረጉን ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ አስታውቆ ነበር።
Показати все...
91😁 16👏 3😱 3👍 2🤔 1🤯 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አሜሪካ በ3 የኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት ሰነዘረች አሜሪካ ፎርዶውን ጨምሮ ኢራን ውስጥ በሚገኙ 3 የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት ማድረሷን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይሎች በፎርዶ፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃን በሚገኙ የኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ “በጣም የተሳኩ” ጥቃቶችን ማድረጋቸውን እና አሁን ሁሉም የአሜሪካ አውሮፕላኖች ከኢራን የአየር ክልል ውጭ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። በጥቃቱ የዩኤስ ቢ-2 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ተሳትፈዋል ተብሏል፡፡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ የማህበራዊ ትስሰር ገፃቸው ባስተለለፉት መልዕከት “የቴህራን የኒውክሌር መርሃግብር ዘውድ” የሆነው ፎርዶው ጠፍቷል ሲሉ ገልፀዋል። ሮይተርስ እንደዘገበው ኢራን በፎርዶው የኒውክሌር ጣቢያ ጥቃት መድረሱን አረጋግጣለች። ኢራን በእስራኤል ጥቃት ከተከፈተባት ወዲህ 400 ሰዎች መገደላቸውን እንዲሁም በትንሹ 3ሺ 56 ዜጎቿ ደግሞ መቁሰላቸውን ገልፃለች፡፡ በኢራን ጥቃት የሞቱት እስራኤላውያን 24 ናቸው፡፡
Показати все...
42👍 24👎 15😁 6
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አዲስ አበባ📍 100 ሺህ ብር ተቀጣች በብስክሌት መንገድ ላይ በመኪና የነዳች ግለሰብ የ100,000 ብር ቅጣት ተጣለባት አዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚኩራ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 8፣ ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በልማት ኮሪደር ውስጥ በተዘጋጀው የብስክሌት መንገድ ላይ መኪና ስታሽከረክር የተገኘች ግለሰብ ላይ የገንዘብ ቅጣት እንደጣለ አስታወቀ። ግለሰቧ በሰላምና ጸጥታ አካላት እና በአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ትብብር በቁጥጥር ስር ውሎ የተሽከርካሪዋ ባለቤት 100,000 ብር እንዲከፍል ተደርጓል። ባለስልጣኑ ግለሰቧ በቸልተኝነት የፈፀመችውን የትራፊክ ደንብ ጥሰት የባለስልጣኑ ኦፊሰሮች ባደረጉት ክትትልና ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት እርምጃ መወሰዱን ገልጿል። Via የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባ/ኮ ዳይሬክቶሬት
Показати все...
59👎 56👏 16👍 12😁 11🤯 4😱 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ቴምርሪልስቴት መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት ሽያጭ ‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት AU አፓርትመንት ሽያጭ 👉1መኝታ 75ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ 802,500ብር ሙሉ ክፍያ 8,025,000ብር 👉2መኝታ 94ካሬ 10% ቅድመ ክፍያ 1,005,800ብር ሙሉ ክፍያ 10,058,000ብር 👉2መኝታ 103ካሬ 10%ቅድ ክፍያ 1,102,100ብር ሙሉ ክፍያ 11,021,000ብር 👉3መኝታ 132ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ 1,412,400ብር ሙሉ ክፍያ 14,124,000ብር 👉3መኝታ 146ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ 1,562,200ብር ሙሉ ክፍያ 15,622,000ብር ‼️ቀሪውን 90% በ 18ዙሪ ያለምንም ጭማሪ በብር የሚከፍሉት ነው ለበለጠ መረጃ ይደውሉ        👇👇👇👇👇👇      +251939770177      +251996856273 https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Показати все...
10
00:18
Відео недоступнеДивитись в Telegram
🏆🎰በአፍሮ ራፍል እድልዎን ወደ ገንዘብ ለመለወጥ ይፈልጋሉ?🏆🎰 እንግዲያስ ምን ይጠብቃሉ በአፍሮ ቤት ላይ የተለያዩ ጨዋታዎችን በመጫወትና ነጥብ በመሰብሰብ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ! እንዴት? 1️⃣ በሚወዱት ስፖርት ወይም ጨዋታ አፍሮ ቤት ላይ ውርርድዎን ያስቀምጡ 2️⃣ የተለያዩ ጨዋታዎችን በመጫወት ብዙ ነጥብ ይሰብስቡ 3️⃣ ብዙ ነጥብ ይዘው ተዘጋጅተው ይጠብቁ አሸናፊዎች በቅርቡ ይለያሉ! ሽልማቶቹ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል፣ ፕለይ ስቴሽን እንዲሁም ሰባ ሁለት ኢንች ስማርት ቲቪን ያካትታሉ! 💰🎁 እንዳያመልጥዎት! የበለጠ ሲጫወቱ የማሸነፍ እድልዎ ይሰፋል!🎉💪 አሁኑኑ https://afrobetting.net ይቀላቀሉ እና እየተዝናኑ ይጫወቱ ያሸነፉ!🎯🎊
Показати все...
6.91 MB
20
የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማስጠንቀቂያ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የመከላከያ ስለላ ማዕከል ጉብኝት **** እስራኤል በኢራን ላይ የጀመረችውን ጥቃት ካላቆመች ሀገራቸው ለፀፀት የሚዳርግ ኃይለኛ ምላሽ እንደምትሰጥ የኢራኑ ፕሬዚዳንት መስኡድ ፔዜሽኪያን አስጠንቅቀዋል። በእስራኤልና በኢራን መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለማስወገድ ያለው ብቸኛ መንገድ እስራኤል በኢራን ላይ የምታካሂደውን የአየር ድብደባ ማቆም ነው ሲሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ኢራን ሁሌም የምትከተለው የሰላምና የመረጋጋትን መንገድ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ሆኖም አሁን ባለው ሁኔታ ዘላቂ ሰላም ሊፈጠር የሚችለው እስራኤል የጦረኝነት የሽብር ቅስቀሳዋን ለማቆም ዋስትና ስትሰጥ ብቻ ነው ብለዋል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ እስራኤል አሁን በያዘችው መንገድ ኢራንን ማጥቃት ከቀጠለች ግን እስራኤል እንድትፀፀት የሚያደርግ ኃይለኛ ምላሽ ኢራን እንደምትሰጥ መናገራቸውን አናዶሉ የኢራንን ሚዲያ ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። በሌላ በኩል የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከሀገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊና ደህንነት ሃላፊዎች ጋር በመሆን የእስራኤል መከላከያ ኃይል የስለላ ማዕከልን ጎብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት፥ "እስራኤል በጦርነቱ አሸንፋ እንድትወጣ የሚያስችላትን ጠቃሚ የስለላ መረጃ እየሰጠን ያለው የመከላከያችን የስለላ ማዕከል" በማለት በክፍሉ እያገለገሉ ላሉ ወታደሮች አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ብጥቅሉ የእስራኤል መከላከያ ኃይል አባላት እስካሁን ላበረከቱት እና ወደፊትም ሀገሪቱ ድል እስክትቀዳጅ ለሚያበረክቱት አስዋጽኦ አመስግነዋል።
Показати все...
79🤯 3🤔 2👍 1😁 1😱 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢትዮጵያውን ገንዘብ የተገነባውን የሕዳሴውን ግድብ "በአሜሪካ በሞኝነት የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ግዙፉ የኢትዮጵያ ግድብ" ሲሉ ገለጹት። ፕሬዚዳንቱ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው ማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ አሁን በለቀቁት ጽሁፍ "አሜሪካ በሞኝነት የረዳችው የኢትዮጵያ ግድብ፣ ወደ አባይ ወንዝ የሚፈሰውን ውሃ በእጅጉ ይቀንሳል ሲሉ ጽፈዋል። "ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በመሆን በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በሩዋንዳ ሪፐብሊክ መካከል ባለው ጦርነት ላይ አስደናቂ የሆነ ስምምነት ማዘጋጀቴን ሪፖርት በማድረጌ በጣም ደስተኛ ነኝ። ይህ ጦርነት ከብዙዎቹ ጦርነቶች በበለጠ በከፋ የደም መፋሰስ እና ሞት የሚታወቅ ሲሆን ለአስርት ዓመታት የቆየ ነው።" ካሉ በኋላ "የሩዋንዳ እና የኮንጎ ተወካዮች ሰነዶችን ለመፈረም ሰኞ ዕለት ዋሽንግተን ውስጥ እንደሚገቡ ገልጸዋል። "ይህ ለአፍሪካ ታላቅ ቀን ሲሆን፣ በእውነት ለመናገር ለመላው ዓለምም ታላቅ ቀን ነው!" ሲሉ አክለዋል። "ለዚህ የኖቤል የሰላም ሽልማት አላገኝም፣ በህንድ እና በፓኪስታን መካከል ያለውን ጦርነት በማስቆሜ የኖቤል የሰላም ሽልማት አላገኝም፣ በሰርቢያ እና በኮሶቮ መካከል ያለውን ጦርነት በማስቆሜ የኖቤል የሰላም ሽልማት አላገኝም፣ በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል ሰላምን በማስፈኔ የኖቤል የሰላም ሽልማት አላገኝም" ያሉት ትራምፕ በቅንፍ ውስጥ "(በአሜሪካ በሞኝነት የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ግዙፉ የኢትዮጵያ ግድብ፣ ወደ አባይ ወንዝ የሚፈሰውን ውሃ በእጅጉ ይቀንሳል)፣" ሲሉ ጽሁፋቸውን ቀጥለዋል።
Показати все...
😁 110 40👎 14👍 5🤔 3👏 2🤯 2😱 2🥰 1
በዳይመንድ ሊግ ዮሚፍ ቀጄልቻ እና ለሜቻ ግርማ አሸነፉ በፓሪስ በተደረገው የ5 ሺህ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በበላይነት አጠናቅቋል። 12 ደቂቃ 47.84 ሰከንድ ደግሞ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደበት ሰዓት ነው። በውድድሩ ሳሙኤል ተፈራ 5ኛ ሲወጣ መዝገቡ ስሜ እና ገመቹ ዲዳ 11ኛ እና 13ኛ በመሆን ውድድርራቸውን አጠናቅቀዋል። በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የዳይመንድ ሊግ አካል በመሆነው ውድድር አትሌት ለሜቻ ግርማ በአንደኝት አጠናቋልቅ። የርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነው ለሜቻ ግርማ 8 ደቂቃ 07.01 ሰከንድ የገባበት ሰዓት ሆኖም ተመዝግቧል። አተሌት ጌትነት ዋለ ደግሞ 3ኛ ደረጃ ወጥቷል። 8 ደቂቃ 12.58 ጌትነት የገባበት ሰዓት ሆኗል። በርቀቱ አብርሀም ስሜ 8ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል። በተመሳሳይ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ሲምቦ ዓለማየው 9 ደቂቃ 01.22 በመግባ 3ኛ ወጥታለች። አትሌት ሎሚ ሙለታ ደግሞ 9ኛ በመሆን ውድድሩን ፈጽማለች።
Показати все...
👍 13 10
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ቴምርሪልስቴት መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት ሽያጭ ‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት AU አፓርትመንት ሽያጭ 👉1መኝታ 75ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ 802,500ብር ሙሉ ክፍያ 8,025,000ብር 👉2መኝታ 94ካሬ 10% ቅድመ ክፍያ 1,005,800ብር ሙሉ ክፍያ 10,058,000ብር 👉2መኝታ 103ካሬ 10%ቅድ ክፍያ 1,102,100ብር ሙሉ ክፍያ 11,021,000ብር 👉3መኝታ 132ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ 1,412,400ብር ሙሉ ክፍያ 14,124,000ብር 👉3መኝታ 146ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ 1,562,200ብር ሙሉ ክፍያ 15,622,000ብር ‼️ቀሪውን 90% በ 18ዙሪ ያለምንም ጭማሪ በብር የሚከፍሉት ነው ለበለጠ መረጃ ይደውሉ        👇👇👇👇👇👇      +251939770177      +251996856273 https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Показати все...
22😱 1
ትራምፕ የቲክ ቶክ እገዳ ቀነ ገደብን ለሶስተኛ ጊዜ አራዘሙ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቲክ ቶክ እንዲታገድ ያስቀመጡትን የእገዳ ቀነ ገደብ ለሶስተኛ ጊዜ አራዝመዋል። በትሩዝ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ “የቲክ ቶክን ቀነ-ገደብ በ90 ቀናት እንዲራዘም የአስፈጻሚ ትዕዛዝ ፈርሜያለሁ" ብለዋል፡፡ የቀነ ገደቡ መራዘም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን የሚጠቀሙበትን የግንኙነት መረብ በድንገት ላለመዝጋት እና ተገቢውን አካሄድ በሚጠብቅ መንገድ ውሳኔ ለመስጠት ያለመ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡ ቲክ ቶክ በለጠፈው መግለጫ ፕሬዝዳንት ትራምፕ መተግበሪያው ለ170 ሚሊዮን የአሜሪካ ተጠቃሚዎች እና 7.5 ሚሊዮን ለሚሆኑ ምርቶቻቸውን በቲክቶክ ላይ ለሚያስተዋውቁ አሜሪካ ነጋዴዎች እንዲደርስ እና አንዳይቋረጥ ስለረዱት አመስግነኗል ማለቱን  ቢቢሲ ዘግቧል።ሁለተኛው ዙር የቲክቶክ እገዳ ቀነ ገደብ ዛሬ የሚያበቃ ሲሆን ትራምፕ ለቲክቶክ ሶስተኛ አድል መስጠታቸውን ተከትሎ አዲሱ የእገዳ ቀን እስከ ፈረንጆቹ መስከረም 17፣ 2025 ድረስ የሚቆይ ይሆናል።
Показати все...
29👎 4😱 1