uk
Feedback
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

Відкрити в Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

Показати більше
2025 рік у цифрахsnowflakes fon
card fon
166 278
Підписники
-1724 години
-227 днів
-430 день
Архів дописів
ሕዳር 28/፳፰/
በዚች ቀን የሀገረ ኒቅዮስ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ሰረባሞን በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ በተወለደ ጊዜ በአባቱ ስም ስምዖን ብለው ጠሩት አባቱም ሲሞት ክርስቲያን ይሆን ዘንድ ወደደ። መልአክም ተገለጸለትና ወደ ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስ እንዲሔድ አዘዘው እንዳዘዘውም ሔደ። እርሱም የጌታችንን ሰው የመሆኑን ምሥጢር ገለጠለት ግን ዘመዶቹ የሆኑ አይሁድን ስለፈራ በኢየሩሳሌም አገር የክርስትና ጥምቀትን ሊአጠምቀው አልደፈረም። ኤጲስቆጶሱም ስለርሱ ምን እንደሚያደርግ ሲያስብ እመቤታችን ተገልጣለት ወደ እስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎናስ እንዲልከው አዘዘችው። ሰረባሞንም እየተጓዘ ሳለ እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ ቀደም ብሎ በሰው አምሳል ወደ ቴዎናስ ቀርቦ ስለ ቅዱስ ሰረባሞን አስረዳው ሰረባሞንም በደረሰ ጊዜ የእግዚአብሔርን ሕግ አስተምሮ የከበረች የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው። ከዚህም በኋላ ኒቅዮስ ለሚባል አገር ኤጲስቆጶስነት ሾመው። እግዚአብሔርም ከሀገረ ስብከቱ ጣዖታትን ደመሰሰ ዳግመኛም አብን ወልድን መንፈስ ቅዱስን አንድ አካል የሚያደርግ የሰባልዮስን ስድብ አስወገደ። ዲዮቅልጥያኖስም ስለ ቅዱስ ሰረባሞን በሰማ ጊዜ በብዙ ዓይነት ሥቃይ አሠቃየው። ሕዝቡ ሁሉ በእርሱ ምክንያት በጌታችን እንዳያምኑ ንጉሡ ፈርቶ ወደ ላይኛው ግብጽ ሰደደው በዚያ  ቅዱስ ሰረባሞንንም  ለሀገሩ ደቡብ ወደ ሆነ ቦታ ወስደው ራሱን በሰይፍ ቆረጡት ምእመናንም መጥተው ሥጋውን ወስደው በክብር ገነዙትና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት ከሥጋውም ድንቆች ተአምራት ሆኑ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Показати все...
star reaction 10 000 123🕊 10
Показати все...
63
Repost from TgId: 2131344856
Фото недоступнеДивитись в Telegram
« አሁን ያለሁበት ሁኔታ በጥቂቱ 😁 » እያወራን ያለንው ስለምናደርገው እውነታ ነው • Laptop • Internet • በቂ ጊዜ አላችሁ ? ይሄው አሁን ተመዝገቡ ባለሙያ ሁኑ @Greenbirdtechnology √ በ300 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ √ ጠቅላላ ክፍያ ደግሞ 4500 √ ቤታቹ ሆናቹ ብቻ ብቁ ግራፊክስ ዲዛይነር ሁኑ ደግሞም Video Editing Course ተሸለሙ 1ኛ አሸናፊ 100% በነጻ 2ኛ አሸናፊ 50% በነጻ 3ኛ አሸናፊ 25% በነጻ የኮርስ ቀናት ቅዳሜ ምሽት 1:00 - 3:00 እሑድ ምሽት 1:00 - 3:00 3ኛ ቀን በብዙሃኑ ምርጫ ሆኖ ምሽት 2:00 - 4:00 @greenbirdtechs @greenbirdtechs የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥
Показати все...
39🔥 4
መረቤን በአሳ የመላ መረቤን በአሳ የመላ /2/ ማን አለ ከአምላኬ ሌላ /2/ ነገር ሁሉ ውብ የሚሆነው ባንተ ነው ጌታ ባንተ ነው /2/
አዝ
በስምህ ስንጀምር ፍፃሜያችን ያምራል እጅህ ከኛ ጋራ በጥበብ ይሰራል ከቶ ያላንተ ፈቃድ ማን ከዚህ ደረሰ ደስ ብሎት ያደረ ተድላን የቀመሰ
አዝ
ከብዙ ድንቢጦች እበልጥብሀለሁ የማትዘነጋኝ ነህ ይህንን አውቃለው የግራው መንገዴን በቀኝ የምትመራ እስተካከላለው ስሆን ካንተ ጋራ
አዝ
አቤኔዘር አለ ሳሙኤል በቋንቋው በጨለማው ዘመን ስለረዳኸው አንተን የታመነ ሲሳዩ ይበዛል ባዶውን የመጣ አፍሶ ይመለሳል
አዝ
መኝታው ይሞቃል እንጀራው ያጠግባል እግዚአብሔር ካለበት ኑሮ ይደላደላል ብዙ ብንበለፅግ እልፍ ቢኖረን ፀጋው ከሌለበት አይደምቅም ድንኳን ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Показати все...
6082726593_1 (19).mp36.14 MB
140🥰 5🕊 1
1.60 MB
44🔥 3
2.13 MB
star reaction 1 41🔥 11
star reaction 1 42🔥 3
5
18
1.40 MB
17😍 8
1.10 MB
27🥰 4
1.56 MB
star reaction 1 36
2.60 MB
38🔥 3
✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::✝️ እንደምን አመሻችሁ የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳውያን እህቶቼ ና ወንድሞቼ? አሁን ከትንሽ ደቂቃ በኃላ ስለ ዘፈን ክፍል ሁለትን በአዲስ መልኩ እንልካለን:: በእዚህ ድምጽ ውስጥ የሚዳሰሱት ነጥብ 🌹ኢሉምናቲ ማህበር ምንድነው? ማን ነው ያለበት 🌹የኢሉምናቲ ማህበር አሁን ላይ እየተቆጣጠረው ያለው ማነው? 🌹 ስለ ምዕራባዊያን ዘፋኞች የዘፈን ክሊፕ ዳሰሳ እናደርጋለን(keny weste, Jay-Z, beyonce, rihana, justin biber ...) ሌሎችም ስለዚህ ጠብቁን
Показати все...
star reaction 1 61🥰 1
‎ሕዳር ፳፯ /27/
‎ ‎በዚችም ቀን በንሑር ከሚባል አገር ቅዱስ ጢሞቴዎስ በሰማዕትነት አረፈ ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሁልጊዜ በጾም በጸሎት ተጠምዶ የሚኖር ነው ስሟ ሞራ የሚባል ሚስት አለችው እርሷም የአጎቱ ልጅ ናት በሥራዋ ሁሉ ደስ የምታሰኘው መልካም ሴት ናት ። ‎ ‎እንደዚህም በፍቅርና በስምምነት ሲኖር ከከሀዲ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ዘንድ የጣዖታት ቤቶች ይከፈቱ ዘንድ አብያተ ክርስቲያናት እንዲዘጉ ትእዛዝ ወጣ ። ቅዱስ ጢሞቴዎስም ይህን ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ። እርሱ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ደሙን ያፈስ ዘንድ ይህን ዘመን ይጠብቀው ነበርና ለሚስቱም ሊሠራው ያሰበውን ነገራት እርሷም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን አለች ። ‎ ‎ከዚህም በኋላ መንገዱን ያቀናለት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ጌታችንም በዚያች ሌሊት በሕልሙ ተገልጾለት ወዳጄ ጢሞቴዎስ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን እነሆ ከጻድቃኖቼ ቁጥር ውስጥ ቆጥሬሃለሁ አሁንም ተነሣ ሚስትህንም ይዘህ ወደ ብህንሳ ከተማ ሒዳችሁ ጣዖታትን በሚያመልኩ ሁሉ ሕዝብ ፊት በስሜ ታመኑ አለው ። በነቃ ጊዜም ለሚስቱ ነገራት እርሷም ይህንኑ የሚመስል ሕልሟን ነገረችው ። ‎ ‎ከዚህም በኋላ ተነሥተው በአንድነት ሔዱ ወደ መኰንኑ ወደ ቊልቊልያኖስም ደረሱ መሰንቆና እንዚራ እያስመታ ለጣዖታቱ በዓልን ሲያከብር አገኙት ያንጊዜ ወታደሮቹ ይዘው በመኰንኑ ፊት አቆሙት ሚስቱም ተከተለችው መኰንኑም ለጣዖት መስገድን እያግባባ በርኅራኄ ቃል ተናገረው ቅዱሱ ግን እርሱንና የረከሰች ሃይማኖቱን ሰደበ ስለዚህም መኰንኑ ተቆጥቶ ከሚስቱ ጋር ወደ ወህኒ ቤት እንዲአስገቡት አዘዘ ። ‎ ‎ከጥቂት ቀኖች በኋላም ከሚስቱ ጋር አውጥተው ደማቸው እንደ ውኃ እስቲፈስ በአለንጋዎች እንዲገረፉአቸው አዘዘ ያለ ርኅራኄም ገረፏቸው ሚስቱም በዚህ ሥቃይ ምስክርነቷን ፈጸመች ። ‎ ‎ዳግመኛም ለጣዖታት መስገድን እሺ ይለው ዘንድ ቅዱስ ጢሞቴዎስን ማባበል ጀመረ እምቢ ባለውም ጊዜ የነዳጅ ድፍድፍ ሥጋውን ቀብተው ከእሳት ማንደጃ ውስጥ እንዲጨምሩት አዘዘ በጨመሩትም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ከዚህ ቃጠሎ አዳነው ። ‎ ‎ከዚህም በኋላ ሁለተኛ ወደ ወህኒ ቤት መለሱት ተአምራትንም የሚያደርግ ሆነ በአንዲት ዕለትም በዚያ ሲጸልይ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደርሱ መጥቶ ቃል ኪዳንን ገባለት ሰላምታንም ሰጠው። ‎ ‎በማግሥቱም ከእሥር ቤት አውጥተው ወደ በንሑር ከተማ ወስደው ቅድስት ራሱን ቆረጡ ያን ጊዜ ንውጽውጽታ ሆነ አየርም መላእክትን ተመላች አማንያን ሰዎችም መጥተው ሥጋውን ወስደው በመልካም አገናነዝ ገንዘው ቀበሩት ። የመከራውም ዘመን በአለፈ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ሠሩለት ሰኔ ሃያ ሰባት ቀንም አከበርዋት ሥጋውንም በውስጥዋ አኖሩ። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️ ‎
Показати все...
156🕊 7🥰 6
ሰረገላዎችህ ሰረገላዎችህ የእሳት ናቸው የሌጌዎን ጭፍሮች ማይችሏቸው የገሀነም ደጆች ማይችሏቸው አንተ ብቻ ንጉሥ ሀያል ጌታ ሳመልክህ እኖራለሁ ጠዋት ማታ/2/
አዝ
በእሳት ሰረገላ ታጥሮአል መንደራችን ጊያዝ ሆይ አትፍራ አለ ፈጣሪያችን የጠላትን ምሽግ በቃሉ ይቆርጣል ከእኛ ጋራ ያለው ከነሱ ይበልጣል
አዝ
ከቴማን ተራራ ከፋራን ሲወርድ ጠላት ይጨነቃል በድምጹ ሞገድ ጦረኛ አያበዛም ሞአብን ሲመታ በአህያ መንጋጋ ሺውን ጥሏል ጌታ
አዝ
የጥልቁን መሰረት በንፋስ አስሮታል ከሰማያት በላይ ዙፋኑን ዘርግቷል ዘንባባ ይዛችሁ ግቡ ከመቅደሱ በምስጋናው ስርአት እንድትቀደሱ
አዝ
ወደረኞቻችን ከቁጥር ቢበዙም እንደ ቃየል ልጆች ሾተል አንመዝም እንጀራን መግበን እንሰዳቸዋለን በቀል እና ፍርድን ለአምላካችን ትተን ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Показати все...
ሰረገላዎችህ_የእሳት_ናቸው_ዘማሪት_ምርትነሽ_ጥላሁን_Official_AudioM4A_128K_1.m4a6.20 MB
170🕊 7🥰 6
ኅዳር ፳፮ /26/
‎ ‎በዚች ዕለት ቅዱስ ቢላርያኖስ ሚስቱ ኪልቅያና እኅቱ ታቱስብያ በሰማዕትነት አረፉ ። ‎ ‎ይህም ቅዱስ የሮም አገር ሰው ነው ወላጆቹም አረማውያን ናቸው ከሮሜ አገርከታላላቆች ሰዎች ልጆች ውስጥ ሚስትን አጋቡት እርሷም ስሟ ኪልቅያ የሚባል ክርስቲያን ናት እጅግም ወደዳት እንደወደዳትም በአወቀች ጊዜ የቀናች የክርስቲያን ሃይማኖትን በግልጽ ታስተምረው ጀመረች እርሱም አምኖ ተጠመቀ ልቡም ብሩህ የሆነ መለኮታዊት ጸጋም አደረችበት እርሱም ታቱስብያ የተባለች እኅቱን አስተማራት እርሷም አምና ተጠመቀች ። ‎ ‎ይህም ቅዱስ ቢላርያኖስ መላእክት ሁልጊዜ ወደርሱ መጥተው የሚሻውን ምሥጢራትን እስከሚገልጡለትና እስከሚያስተምሩት ድረስ ታላቅ ተጋድሎን መጋደል ጀመረ ። ‎ ‎ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስም በነገሠ ጊዜ ክርስቲያኖችን አሠቃያቸው ብዙዎችንም አሠቃይቶ በሰማዕትነት አረፉ ። ይህ ቅዱስ ቢላርያኖስም ከእኅቱ ታቱስብያ ጋርእየዞሩ የሰማዕታትን በድናቸውን እያነሡ የሚቀብሩዋቸው ሆኑ አንድ ክፉ የሆነ ሰውም በአወቀባቸው ጊዜ የንጉሥ ወዳጁ ለሆነ ለአግማስዮስ ሒዶ ነገረው እርሱም ወደርሱ እንዲአቀርቧቸው አዘዘ በፊቱም በቆሙ ጊዜ ስለ ሃይማኖታቸው ጠየቃቸው እነርሱም ክርስቲያኖች እንደሆኑ አመኑ ። ‎ ‎ይህም መኰንን ሸነገላቸው ለአማልክት ይሠዉ ዘንድ ብዙ ቃል ኪዳንንም ገባላቸው እነርሱ ግን አልሰሙትም እንዲህም ብሎ አሰፈራራቸው ካልሰማችሁኝና ለአማልክት ካልሠዋችሁ እኔ በጽኑ ሥቃይ አሠቃያችኋለሁ አላቸው እነርሱም ሥቃዩን ከቶ አልፈሩም ። ‎ ‎ጽናታቸውንና ትዕግሥታቸውን አይቶ አንገታቸውን ለሚቆርጥ አሳልፎ ሰጣቸው ራሶቻቸውንም በቆረጧቸው ጊዜ ከዚያ ያሉ ሁሉ ነፍሶቻቸውን በደስታ ሲቀበሉ ብርሃናውያን መላእክትን አዩአቸው መኰንኑም ይህን አይቶ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ። ንጉሡም ሦስት ቀን አሠረው በአራተኛውም ከእሥር ቤት አውጥቶ ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው ከቅዱስ ቢላርያኖስና ከሚስቱ ኪልቅያ ከእኅቱ ታቱስብያ ጋር የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ ። ‎ ‎ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️ ‎
Показати все...
star reaction 7 961 164🕊 8
አንተ ነህ ተስፋዬ አንተ ነህ/2/ተስፋዬ አንተ ነህ አምላኬ ተስፋዬ/2/ ወረት የማታውቅ ቅዱስ ጌታዬ መጣል የማታውቅ  ቅዱስ ጌታዬ አንተ ነህ/2/ተስፋዬ
አዝ
ያደፈ ነውና መጎናጸፊያዬ እንዴት አስገባኸኝ ከቤትህ ጌታዬ ያለምክንያት መውደድ ትችልበታለህ ምንአይነት አባት ነህ በሰማያት ያለህ ምንአይነት አምላክ ነህ በሰማያት ያለህ
አዝ
ድንጋዮች በውሀ ቢሆን መኖሪያቸው ነገር ግን በነሱ ህይወት የለባቸው አንተን እየፈሩ በቤትህ ከኖሩት ከሚድኑት አርገኝ ከሚለመልሙት/2/
አዝ
አለቱን ሠንጥቀህ ውሀ ታፈሳለህ ደረቁንም በትር ታለመልማለህ በተዘጋው ገብተህ ሰላም ትሰጣለህ በል ልቤን ስበረው ትችልበታለህ/2/
አዝ
ያደፈ ነውና መጎናጸፊያዬ እንዴት አስገባኸኝ ከቤትህ ጌታዬ ያለምክንያት መውደድ ትችልበታለህ ምንአይነት አባት ነህ በሰማያት ያለህ ምንአይነት አምላክ ነህ በሰማያት ያለህ ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Показати все...
ለጾማችን_የሚሆን_መዝሙር_አንተ_ነህ_ተስፋዬ_Kesis_Ashenafi_ethiopia_orthodox.m4a7.71 MB
110🥰 7🕊 7
ግሩማን መላእክት ግሩማን መላእክት የምተጉ ለምሕረት ለሰው ድኅነት ከልዑል ዘንድ ለምኑልን ቸርነቱን እንዲያደርግልን
አዝ
እስራኤልን በጉዟቸው/2/ የመራሃቸው ሚካኤል ነህ ጠባቂያቸው ማዕበሉን ያሻገርካቸው
አዝ
ያበሠርካት ለድንግል /2/የሕይወት ቃል መልእክተኛው ለልዑል መልአከ ኃይል ገብርኤል
አዝ
እናቶችን በጭንቃቸው /2/የምትረዳቸው ሩፋኤል ነህ ጠባቂያቸው በምጥ ጊዜ አዋላጃቸው
አዝ
ሱራፌል ወኪሩቤል አፍኒን ወራጉኤል ወሳቁኤል በልዑል ፊት የምትቆሙ ምልጃችሁን ስለ እኛ አሰሙ ቀሲስ ሊቀ መዘምራን ግርማ አዳነ  💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Показати все...
6082726593_1 (17).mp35.73 MB
130😍 11🥰 9
ሕዳር ፳፭ /25/ በዚች ዕለት ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ አረፈ። በ፪ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ግዛቶች በአንዱ [አስሌጥ] ከአባቱና ከሚስቱ ጋር የሚኖር "አሮስ" የሚሉት ሰው ይኖር ነበር:: ሚስቱ ደምግባት የሠመረላት እርሱም ደግነት ያለው ሰው ቢሆኑም የሚያመልኩት ግን ጣዖትን ነበር:: አንድ ቀን አሮስ ሚስቱን ከቤት ትቶ ለአደን ከአባቱ ጋር ወጣ:: እንደ ልማዳቸው ወጥመዱን አስተካክለው ተደበቁ:: የወጥመዱ ደወል ሲያቃጭል: "እንስሳ ተያዘልን" ብለው ሲሯሯጡ ዐይናቸው ያየው ነገር በድንጋጤ እንዲፈዙ አደረጋቸው:: ፪ ገጻተ ከለባት በወጥመዱ ውስጥ ተይዘው ነበር:: እነዚህ ፍጡራን ሰዎች ናቸው:: ግን ባልታወቀ የተፈጥሮ አጋጣሚ እንደዚህ እንደ ሆኑ ይታመናል:: ግን እጅግ ግዙፍ: ከአንገታቸው በላይ እንደ ውሻ: ወገባቸው እንደ ሰው: ጉልበታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ታችኛው እግራቸው የጋለ የናስ ብረት ነው የሚመስል:: እነዚህን ፍጡራን ሰማያዊ ካልሆነ ምድራዊ ፍጡር አይችላቸውም:: አንበሳና ነብርን እንኩዋ እንደ ጨርቅ በጣጥሰው ይጥሏቸው እንደ ነበር ይነገራል:: ዐይናቸው እንደ እሳት ይነድ ስለ ነበር ማንም ትክ ብሎ ሊያያቸው አይችልም:: ምሥጢራቸውን ግን የሚያውቀው የፈጠራቸው አምላክ ነው:: ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና :- አሮስና አባቱ ባዩአቸው ጊዜ ደንግጠው ወደቁ:: ገጻተ ከለባቱ የብረት ወጥመዱን እንደ ክር በጣጥሰው የአሮስን አባት በቅጽበት በሉት:: አሮስን ሊበሉት ሲሉ ግን ድንገት ቅዱስ መልአክ ወርዶ በእሳት ሰይፍ አጠራቸው:: "ከእርሱ የሚወጣ ቅዱስ ፍሬ አለና እንዳትነኩት" አላቸው:: ወዲያውም መልአኩ ያንን ኃይለኝነታቸውን አጠፋው:: በዚህ ጊዜ ፪ቱም ወደ አሮስ ሒደው ሰገዱለት:: አሮስም ወደ ቤቱ ወስዶም ደበቃቸውና የሆነውን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት:: ጥቂት ቆይታም ጸንሳ ወለደች:: ልጃቸውን ፒሉፓዴር [ፒሉፓተር] ሲሉ ስም አወጡለት:: ትርጉሙም "መፍቀሬ አብ - የአብ ወዳጅ" ማለት ነው:: ከዚያም አሮስ ሚስቱን : ልጁንና ፪ቱን ገጻተ ከለባት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ ተጠመቀ:: አበው ካህናት እሱን "ኖኅ" : ሚስቱን "ታቦት" : ልጁን ደግሞ "መርቆሬዎስ" ሲሉ ሰየሟቸው:: መርቆሬዎስ ማለትም "ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ - የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" እንደ ማለት ነው:: ከዚያም ደስ እያላቸው: ክርስቶስን እያመለኩ: ነዳያንን እያሰቡ: ልጃቸውን መርቆሬዎስን አሳደጉ:: ነገር ግን የገጻተ ከለባት ወሬ በመሰማቱ ንጉሡ "ካላመጣሃቸው" አለው:: ኖኅ ጸልዮ ወደ ኃይለኝነታቸው መልሷቸው ስለነበር ፊታቸው ገና ሲገለጥ ብዙ አሕዛብ በድንጋጤ ሞቱ:: ንጉሡም ስለ ፈራ ኖኅን የጦር መኮንን አደረገው:: በጦርነት ጊዜም ገጻተ ከለባቱ ኃይላቸው ስለሚመለስ ተሸንፎ አያውቅም ነበር:: አንድ ጊዜ ግን ፪ቱን ገጻተ ከለባት ንጉሡ አታሎ ወሰዳቸው:: ሃይማኖታቸውን ሊያስክዳቸው ሲል "እንቢ" በማለታቸው አንዱ ሲገደል ሌላኛው አምልጦ ጠፋ:: በዚያ ወራትም ኖኅ ለጦርነት ወጥቶ ተማረከ:: ንጉሡ ደግሞ ታቦትን "ላግባሽ" ስላላት የ፭ ዓመት ልጇን ቅዱስ መርቆሬዎስን ይዛ ተሰደደች:: በስደት ጥቂት እንደ ቆየች ግን ባሏን ኖኅን አየችው:: እርሷ ብታውቀውም እርሱ ዘንግቷት ነበር:: በሁዋላ ግን በሕጻኑ መርቆሬዎስ አማካኝነት ማስታወስ በመቻሉ ደስ አላቸው:: በዚያው በሮም ዙሪያ ሳሉም አንዱ ገጸ ከልብ መጥቶ አገኛቸው:: በዚህም ምክንያት በስደት ሃገርም መኮንን ሆኖ ተሾመ:: በዚያም ቤተ ክርስቲያንን አንጾ: ቤቱን ቤተ ነዳያን አድርጐ ኖኅ ለዓመታት ኖረ:: ቅዱስ መርቆሬዎስ ወጣት ሲሆንም ወላጆቹ ታቦትና ኖኅ ዐረፉ:: እርሱ ከባልንጀራው ገጸ ከልብ ጋር ሆኖ በጾምና ጸሎት ሲኖር ስለ አባቱ ፈንታ የጦር መሪ አደረጉት:: በጦርነትም እጅግ ኃያል: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ: የጾምና የጸሎት ሰው ሆነ:: ያን ጊዜ ግን ዳክዮስ ንጉሡ ክርስቶስን በመካዱ ምዕመናን ላይ ሞት ታወጀ:: በጊዜው ደግሞ የበርበር ሰዎች በሮም መንግስት ላይ ጦርነትን በማንሳታቸው ዳኬዎስና ቅዱስ መርቆሬዎስ ለጦርነት ወጡ:: ነገር ግን በርበሮች እንደ አሸዋ ፈሰው ብዛታቸውን ሲያይ ንጉሡ ደነገጠ:: ለማግስቱ ቀጠሮ ተይዞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሰይፍ ሰጠው:: በማግስቱም "ምን ይሻላል?" ሲባል ቅዱስ መርቆሬዎስ "እኔ የክርስቶስ ባሪያ ነኝና ብቻየን እቁዋቁዋማቸዋለሁ" ቢል ሳቁበት:: እርሱ ግን በጥቁር ፈረሱ [አብሮት ያደገ ነው] ተጭኖ በርበሮችን "ጠብ ይቅርባችሁ: በሰላም ሒዱ" ቢላቸው ተሳለቁበት:: ያን ጊዜም ጸሎት አድርሶ የመልአኩን ሰይፍ ሲመዘው ብዙዎቹ ወደቁ:: ከበርበሮችም ለወሬ ነጋሪነት እንኩዋ የተረፈ አልነበረም:: ነገሩ በሮም ሲሰማ ታላቅ ሐሴት ሆነ:: ዳሩ ግን ከሃዲው ዳኬዎስ "ድሉ የጣዖቶቼ የነ አዽሎን ነው" በማለቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲያዝን አደረ:: በ፫ኛው ቀንም "ለጣዖት ሠዋ" የሚል ትዕዛዝ ከንጉሡ ዘንድ መጣ:: ቅዱሱ ግን ወደ አደባባይ ሔደ:: የክብር ልብሱንና መታጠቂያውን አውልቆ በንጉሡ ፊት ወረወረው:: "ሃብትከ ወክብርከ ይኩንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: [ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ]" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው:: ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው:: ለዚያ ነው ሊቃውንት :- "አመ አንደዱ ላእሌከ ውሉደ መርገም:: እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም:: አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍህም::" ያሉት:: ከዚያም ወስደው ወኅኒ ቤት ውስጥ ጣሉት:: ክርስቶስን ያስክደው ዘንድ በረሃብ: በግርፋት: በእሳት: በስለትም አሰቃየው:: በመጨረሻ ግን አሰቃይተው እንዲገድሉት ወደ እስያ ሰደደው:: በስፍራውም ብዙ አሰቃይተው ኅዳር ፳፭ ቀን አንገቱን ሰይፈውታል:: እርሱ ካረፈ በሁዋላም የተባረከ ፈረሱ ለዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: አረማውያንንም ከአፉ በወጣ እሳት አጥፍቷል:: ተአምረኛውና ኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በ፪ መቶ ዓ/ም እንደ ተወለደ: በ፪ መቶ ፳ ዓ/ም መከራ መቀበል እንደ ጀመረና በ፪፻፳፭ ዓ/ም ሰማዕት እንደሆነ ይታመናል:: ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Показати все...
220🥰 10🔥 3🕊 2