uk
Feedback
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

Відкрити в Telegram

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Показати більше
2025 рік у цифрахsnowflakes fon
card fon
44 133
Підписники
Немає даних24 години
-747 днів
-34830 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በስምንት ዓመቷ ታዳጊ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ ተከሳሽ ጌቱ ተረፈ የተባለ ግለሰብ በምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወረዳ ሰንዳፋ ቦነያ ቀበሌ ውስጥ የታዳጊዋ ቤተሰቦች ቤት አለመኖራቸውን ተከታትሎ በማረጋገጥ በ8 አመት ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል መፈፀሙ በማስረጃ መረጋገጡ ተገልጿል ። በወቅቱ ታዳጊዋ ውጪ እየተጫወተች ባለችበት ወቅት አታሎ ይህንኑ ድርጊት መፈፀሙ የተገለፀ ሲሆን  በደረሰባት ጉዳት ዉሃ ሽንት መሽናት አቅቷት ስትቸገር የተመለከቱ ቤተሰቦች በምን ምክንያት እንዲህ ልትሆን እንደቻለች በጠየቋት ጊዜ የደረሰባትንና ድርጊቱን የፈፀመዉን ግለሰብ በመናገሯ ጉዳዩን ወዲያውኑ ለፖሊስ በማሳወቅ እና በጤና ተቋም በማስመርመር ተከሳሹ በቁጥጥር ስር ሊዉል ችሏል ። ፖሊስ ከህክምና ተቋም ያገኘዉ መረጃ የመደፈር ጥቃት መፈፀሙን የሚያረጋግጥ በመሆኑ መረጃዉን ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር በማጠናከር ለአቃቤ ህግ ልኳል ። አቃቤ ህግ ከፖሊስ የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ህግ ቁጥር 627 በህፃናት ላይ የሚፈፀም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ክስ መስርቷል ። ክሱን የተከታተለው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ እድሜዋ 13 ዓመት ያልሞላት ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል መፈፀሙ በማስረጃ ሙሉ በሙሉ በማረጋገጡ በ16 ዓመት እስራት እንዲቀጣ የወሠነበት መሆኑን ብስራት ሬዲዮ ከምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ የኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት መግለጫ ተመልክቷል ። በመባ ወርቅነህ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👎 23 18🤬 4
ከኮሎምቢያ ጋር ለተቀሰቀሰዉ ግጭት ለዲፕሎማሲ ምንም ቦታ የለም ሲሉ የታይላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ የታይላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፑአንግኬው እንደተናገሩት ካምቦዲያ ለሰላም ድርድር "ዝግጁ አይደለችም" እና አሁን ያለው ግጭት ለዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ቦታ እንደማይሰጥ ለአልጀዚራ ተናግረዋል።የታይላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር "ሁኔታው ለዲፕሎማሲው ቦታ ሲሰጥ ዲፕሎማሲ ይሠራል" ብለዋል፤ "አሁን ያ ቦታ የለንም ይቅርታ አድርጉልኝ።" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ታይላንድ በሰላም ለመደራደር ከካምቦዲያ "ቁርጠኝነት" ማየት ትፈልጋለች፤ ይህ ቁርጠኝነት በትክክል በምን እንደሚመጣ ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡"በእርግጥ በአሁኑ ጊዜ ዝግጁ አይደሉም። በአንድ በኩል ዝግጁ ነን ይላሉ፣ ነገር ግን መሬት ላይ የሚያደርጉት ተግባራቸው ሙሉ በሙሉ በተቃራኒ አቅጣጫ ነው።" ብለዋል፡፡ ምንም እንኳን ቀጣይነት ያለው ጠላትነት እና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በሁለቱም ወገኖች ላይ ኪሳራ እያመጣ ቢሆንም ፑአንግኬው አክለው ሲገለጹ "የካምቦዲያን ኃይሎቨች የሚያደርጉትን ነገር ለማስቆም ዝግጁ መሆናቸውን እንዲያሳዩ እንፈልጋለን፤  ያ ከሆነ በእርግጥም የዲፕሎማሲ እና የድርድር ተስፋን ግምት ውስጥ ማስገባት እንችላለን" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ካምቦዲያ የታይላንድ ጦር ማክሰኞ ማለዳ ላይ በድንበር አካባቢዎች ጥቃቱን እንደቀጠለ እና ቢያንስ ሰባት ሰዎችን ገድሏል ሲል አስታዉቋል። በጥቃቱ ቢያንስ ሶስት ወታደሮች መሞታቸውን ታይላንድ ተናግራለች። ታይላንድ በ2024 5.73 ቢሊዮን ዶላር የመከላከያ በጀት እና ከ360,000 በላይ የታጠቁ ሃይል አባላት ያለው ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ ያለው ወታደር አላት።የታይላንድ ጎረቤት ካምቦዲያ እ.ኤ.አ በ2024 1.3 ቢሊዮን ዶላር የመከላከያ በጀት የመደበች ሲሆን 124,300 ንቁ ወታደራዊ ኃይል አላት፡፡ በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
😁 11 6🤔 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በኢትዮጵያ  የፖሊዮ ክትባት ያልጀመሩ እና ጀምረው ያቆረጡ  ህጻናት በርካታ ናቸው ተባለ    👉 ለ25 ሚሊዮን ህጻናት  የፖሊዮ ክትባት በዘመቻ መልኩ መሰጠት ይጀመራል የፖሊዮ ክትባትን በሀገር አቀፍ ደረጃ 25 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ህጻናት የዘመቻ ክትባት እንደሚሰጥ ተገልጿል ።ክትባቱ በመላው ኢትዮጵያ ቤት ለቤት የሚሰጥ ሲሆን ከክትባት ውጪ የግንዛቤ እና ሌሎች የጤና ችግሮችን የመለየት ስራ እንደሚሰራ ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ  ክትባት ያልጀመሩ እና ጀምረው ያቋረጡ ህጻናት ቁጥር በርካታ ሲሆን  ህጻናቶችን  የመለየት ስራ እንደሚሰራ በጤና ሚኒስቴር የክትባት ፕሮግራም የኮሙኒኬሽን አማካሪ ወይዘሮ ፀጋነሽ ገድሉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ  ክትባት ሲጀመር ስድስት የክትባት ዓይነቶች ብቻ ሲሆኑ በአሁን ሰዓት 15 መድረሱ ተጠቁሟል። ባለፉት 50 ዓመታት 154 ሚሊዮን ለሚሆኑ ህጻናት ክትባት በመስጠት ከሞት መታደግ መቻሉ ተነግሯል ። በተጨማሪም የማህጸን በር ካንሰር ክትባት በዘመቻ መልክ መሰጠቱ ቀርቶ በመደበኛ አገልግሎት ብቻ የሚሰጥ መሆኑ ተነግሯል። ማንኛውም ህጻን የእጅ እና የእግር መልፈስፈስ ሲያጋጥመው የፖሊዮ የላብራቶሪ ምርመራ ሊያደርግ ይገባል ተብሏል።ኢትዮጵያ  በ2017 የዋይልድ ፖሊዮ ነጻ መሆኗን የሚያመላክት ሰርተፍኬት እንደተጣት ተጠቁሟል። ይሁን እና ከ2019 ጀምሮ የክትባት እጥረት  ሲያጋጥም መቆየቱ ተገልጿል ። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
12😱 2👎 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በአፍጋኒስታን ፓኪስታን ግጭት ዉጥነት በነገሰበት ወቅት ቢያንስ ስድስት የፓኪስታን ወታደሮች በታጣቂዎች ተገደሉ በሰሜን ምዕራብ ፓኪስታን የጸጥታ ኬላ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ስድስት ወታደሮች መገደላቸውን ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።ባለፉት ሁለት ቀናት የታጠቁ ኃይሎች በኪበር ፓክቱንክዋ ግዛት በኩራም የጎሳ አውራጃ የሚገኘውን የፍተሻ ኬላ በመውረር ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የፖሊስ እና የደህንነት ምንጮች ገልጸዋል። ጥቃቱ በፓኪስታን እና በአፍጋኒስታን ድንበር ላይ ውጥረት በነገሰበት ወቅት የተፈጸመ ሲሆን ባለፉት ሳምንታት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደለው ተከታታይ ፍጥጫ ሊያራዝም ይችላል የሚል ስጋትን አንግሷል፡፡የፓኪስታን ታሊባን ወይም ቲቲፒ ለጥቃቱ ሃላፊነቱን ወስዷል ሲል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል። "6 የጸጥታ አባላት ሰማዕትነት ሲቀበሉ አራቱ ቆስለዋል፣ ሁለት ታጣቂዎችም በጦርነቱ ተገድለዋል" ሲሉ አንድ ስማቸው ያልተገለጸ የመንግስት ባለስልጣን ተናግረዋል።ከኢስላማባድ ጋር ለሁለት አስርት አመታት ሲዋጋ የነበረው ቲቲፒ ከቅርብ አመታት ወዲህ በፓኪስታን ድንበር ክልሎች ላይ ጥቃቶችን ከፍቷል። ኢስላማባድ እ.ኤ.አ. በ 2021 በአፍጋኒስታን ስልጣን የያዙ የታሊባን ባለስልጣናት ቡድኑን እየጠለሉ ነው ሲል ከሰዋል።ከኢስላማባድ ጋር ለሁለት አስርት አመታት ሲዋጋ የነበረው ቲቲፒ ከቅርብ አመታት ወዲህ በፓኪስታን ድንበር ክልሎች ላይ ጥቃቶችን ከፍቷል። የኢስላማባድ መንግስት እ.ኤ.አ በ 2021 በአፍጋኒስታን ስልጣን የያዙት የታሊባን ኃይሎች ቡድኑን እየደገፉ ነዉ ሲል ከሷል።የካቡል መንግስት በበኩሉ ክሱን ውድቅ በማድረግ የፓኪስታን ደህንነት ችግር የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ተናግሯል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
16😁 1🕊 1
በጎረቤቷ ላይ አሲድ በመድፋት የመግደል ሙከራ ወንጀል የፈጸመች ግለሰብ በ9 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት ተቀጣች። ተከሳሽ አበበች ቡናሻ የተባለች ግለሰብ ወንጀሉን የፈጸመችው መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 7 ሰዓት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ነው። ተከሳሿ የግል ተበዳይ በር ላይ ቆሻሻ ደፍታ ስትመለስ የግል ተበዳይም ለምን እንደዚህ ታደርጊያለሽ ብላ በምትጠይቅበት ሰዓት በተፈጠረ አለመግባባት ተከሳሽ ፊት ላይ አሲድ በመድፋት በግራ አካሏ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሷን በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮተቤ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገልጿል። ፖሊስ የግል ተበዳይ መጎዳት ሪፖርት ከደረሰው ጀምሮ ወዲያው በቦታው ደርሶ ተጎጂን ወደ ህክምና በመውሰድ እንድትረዳ ማድረጉ ተጠቁሟል። ከህክምው ጎን ለጎን ተከሳሿን በቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢውን መረጃና ማስረጃ የማሰባሰብ ሂደት እና የምርመራ ስራ ማጠናቀቁን ፖሊስ ጣቢያው አመላክቶ በተጠርጣሪዋ ላይ በህክምና እና በሰው ማስረጃ የተጠናከረውን የምርመራ ውጤት ለአቃቤ ህግ ልኳል። ጉዳዩ በአቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተ በኋላ ሂደቱን ሲከታተል የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በ9 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል። በተለያዩ ምክንያቶች የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በስሜታዊነት ወደ ግጭት በመውሰድ በሰው ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ግለሰቦች ከስሜት በጸዳ መንገድ ችግሮችን በውይይት መፍታት ይኖርባቸዋል ሲል ያሳሰበው ፖሊስ ችግሩ ከአቅም በላይ ከሆነም ወደ ህግ አካል በመቅረብ እንደሚገባ አሳስቧል። ምንጭ:- አአ ፖሊስ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
21💔 10👍 4🤬 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#Breaking_news ቀጣዩ ምርጫ እለተ ሰኞ ግንቦት 24 2018 እንዲሆን ጸደቀ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ሰኞ ግንቦት 24፤ 2018 ሆኖ መጽደቁን አስታወቀ። ቦርዱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ ባደረገው የጸደቀ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ፤ የምርጫ ውጤት በቦርዱ ደረጃ ይፋ የሚደረገው ሰኔ 4 ቀን እንደሆነ ገልጿል። Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
🤣 44👍 15👎 3 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በጋምቤላ ክልል የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱ ተነገረ። በጋምቤላ ክልል የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት ቀደም ካሉት ጊዜያት አንፃር አሁን ላይ መቀነሱን የክልሉ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት አስታውቋል።በጽህፈት ቤቱ የዘርፈ ብዙ ምላሽ የኤች አይ ቪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አቡላ ድንጉር ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም በክልሉ የነበረው የቫይረሱ ስርጭት ምጣኔ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኝ ነበር። ከፍተኛ የቫይረስ ስርጭትን በማስመዝገብ ክልሉ ቀዳሚ እንደነበር ገልፀው ከሁለት አመታት ወዲህ  ግን ከአዲስ አበባ በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ እንደቻለ አስረድተዋል። ስርጭቱ እ.አ.አ በ2023 ላይ ከነበረበት   3 ነጥብ 14 በመቶ ባለፈዉ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ባደረገው የዳሰሳ ጥናት መሰረት ወደ 3ነጥብ 09 በመቶ መቀነሱ ተረጋግጧል። የክልሉ መንግስት ለጉዳዩ ልዮ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱ፣ የቫይረሱን ስርጭት በመግታት በኩል የአጋር አካላት  ድጋፍ መኖር እንዲሁም ለማህበረሰቡ የግንዛቤ መፍጠር ስራዎች መሰራታቸው ለዚህ ውጤት አስተዋፅኦ አበርክቷል።አሁን ላይ በክልሉ ያለው የበሽታው ስርጭት የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳይም በሚፈለገው ልክ መሻሻሎች አላሳየም። በክልሉ የኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት አምራች ኃይል በሆኑት ወጣቶች ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት አሁንም ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑ ተጠቁሟል። በቅድስት ደጀኔ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
10👏 8😁 2
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሀገራችን ባህልና ሥነ-ምግባር ያፈነገጠ አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ ‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥነ-ምግባር ባፈነገጠ አኳሃን ሰውነታቸውን የገላለጠ አለባበስ ለብሰው በአደባባይና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎችን ከነግብረ-አበሮቻቸው በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል። ‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን በሀገራችን አዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው 3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩ፣ ዝግጅቱን በስፖንሰርነት የደገፋ እና ፕሮግራሙን ያቀነባበሩ ተጠርጣሪዎች:- ‎1ኛ. ወንጌላዊት ገብረ እንድርያስ በርሄ፣ ‎2ኛ. በርከት ፀጋዬ ጅፋር፣ ‎3ኛ. መቅድም ደረጄ መንግስቱ፣ ‎4ኛ. ግሩም ገዛሀኝ ቀጭኔ እና ‎5ኛ. ዮሃንስ መኮንን ሀ/ማርየም ‎የተባሉ ግለሰቦች መሆናቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከህብረተሰቡ ባህልና እሴት ያፈነገጡ አለባበሶችና መጤ ባህሎች ተስፋፍተው በትዉልዱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያስከትሉ ተጠርጣሪዎቹ ላይ የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል። #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👍 112👏 34 15😁 13🤔 3👌 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የቦልሶናሮ ልጅ ለብራዚል ፕሬዝዳንት እንደማይወዳዱ አስታወቀ የቀድሞው ፕሬዝዳንት የጃየር ቦልሶናሮ የበኩር ልጅ ሴናተር ፍላቪዮ ቦልሶናሮ በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ለፕሬዚዳንትነት እንደማይወዳደር ተናግሯል፡፡ወጣቱ ቦልሶናሮ በአባቱ በኩል የሊበራል ፓርቲ ወክሎ እንዲወዳደር መመረጡን የሚያሳይ ዘገባ አርብ ዕለት ከተገለጸው የተገላቢጦሽ መግለጫ ሰጥቷል። ሰኞ እለት ሴናተሩ በሃይማኖታዊ አገልግሎት ከተሳተፈበኋላ ይህንኑ ተናግሯል ።"ሁሉንም መንገድ የማልሄድበት እድል አለ" በማለት ይህ ዓይነቱ ጉዞ "በዋጋ" እንደሚመጣ ገልጿል።በጃንዋሪ 2023 የህዝብ ሕንፃዎችን በመውረር እና በማውደም የተከሰሱትን በምርጫ ውጤቱን በመቃወም በእስር ላይ የሚገኙትን አባታቸዉን በተመኮንግረስ ይቅርታ የሚጠይቅ ህግ ይሰጥ እንደሆነ ሴናተሩ ለመናገር ፈቃደኛ አልሆኑም። "በብራዚል አደጋ ስላለው እና ከእጩነቴ መነሳቴ ለእኔ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው እንድታስቡ ብቻ ነው የምፈልገው።" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡የ27 አመት እስር የተፈረደባቸዉ የቀድሞው የቀኝ ክንፍ ፕሬዝዳንት ጃየር ቦልሶናሮ በ2022 ምርጫ በግራ ክንፍ ሉዊስ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ከተሸነፉ በኋላ መፈንቅለ መንግስት በማሴር መከሰሳቸዉ ይታወሳል፡፡ በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
11
የቦልሶናሮ ልጅ ለብራዚል ፕሬዝዳንት እንደማይወዳዱ አስታወቀ የቀድሞው ፕሬዝዳንት የጃየር ቦልሶናሮ የበኩር ልጅ ሴናተር ፍላቪዮ ቦልሶናሮ በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ለፕሬዚዳንትነት እንደማይወዳደር ተናግሯል፡፡ወጣቱ ቦልሶናሮ በአባቱ በኩል የሊበራል ፓርቲ ወክሎ እንዲወዳደር መመረጡን የሚያሳይ ዘገባ አርብ ዕለት ከተገለጸው የተገላቢጦሽ መግለጫ ሰጥቷል። ሰኞ እለት ሴናተሩ በሃይማኖታዊ አገልግሎት ከተሳተፈበኋላ ይህንኑ ተናግሯል ።"ሁሉንም መንገድ የማልሄድበት እድል አለ" በማለት ይህ ዓይነቱ ጉዞ "በዋጋ" እንደሚመጣ ገልጿል።በጃንዋሪ 2023 የህዝብ ሕንፃዎችን በመውረር እና በማውደም የተከሰሱትን በምርጫ ውጤቱን በመቃወም በእስር ላይ የሚገኙትን አባታቸዉን በተመኮንግረስ ይቅርታ የሚጠይቅ ህግ ይሰጥ እንደሆነ ሴናተሩ ለመናገር ፈቃደኛ አልሆኑም። "በብራዚል አደጋ ስላለው እና ከእጩነቴ መነሳቴ ለእኔ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው እንድታስቡ ብቻ ነው የምፈልገው።" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡የ27 አመት እስር የተፈረደባቸዉ የቀድሞው የቀኝ ክንፍ ፕሬዝዳንት ጃየር ቦልሶናሮ በ2022 ምርጫ በግራ ክንፍ ሉዊስ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ከተሸነፉ በኋላ መፈንቅለ መንግስት በማሴር መከሰሳቸዉ ይታወሳል፡፡ በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
😁 9👎 5 2
ኮንትራት ይዘው በመሄድ አሽከርካሪውን ገድለውን ንብረት ዘርፈው የተሰወሩት ግለሰቦች ከዓመታት በኋላ በእስራት ተቀጡ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ጨለለቃ ክፍለ ከተማ  አናታ የረር  ወረዳ ዳንኤል መለሰ የተባለ የባጃጅ አሽከርካሪ  በድንገት መሰወሩን ከቤተሰብ ጥቆማ ደርሷል።ፖሊስ የባጃጅ አሽከርካሪዎች መነሻ አካባቢ ባደረገው ማጣራት ኮንትራት ተብሎ ሁለት ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ኤረር  ዋልያ ፋብሪካ ወደተባለ አካባቢ መጓዙን ከባጃጅ ተራ አስከባሪዎች መረጃ ይደርሰዋል። በዚህም ከተወሰኑ ወራት በኋላ በአንድ ማሳ ውስጥ ለእርሻ የተሰማሩ አርሶ አደሮች አንድ ተገድሎ የተቀበረ  አስክሬን አጥንት ያገኙና ለፖሊስ ሪፖርት ማድረጋቸውን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና መምሪያ ኮማንደር ግርማ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።ፖሊስ  ወዲያው በአካባቢው ተገኝቶ የተቀበረውን የሰው አስክሬን በማንሳት  አጥንቱን  በመለቃቀም በቀጥታ ለጳውሎስ ሆስፒታል ይልካል። የጳውሎስ ሆስፒታል የተላከውን  ቅሪት አካል መርምሮ  የሰው ቅሪት አካል መሆኑን ያረጋግጣል ። ከወራት በፊት የጠፋው የባጃጅ አሽከርካሪ ቅሪት አካል ይሆናል ተብሎ በመጠርጠሩ ከቤተሰብ መካከል የሁለት ሰው ደም በፌደራል ፖሊስ የፎረሲክ ምርመራ እንዲጣራ ተደርጎ 99.8  የተገኘው የቅሪት አካል የተሰወረው የባጃጅ አሽከርካሪ የዳንኤል መለሰ መሆኑ ይረጋገጣል ።ፖሊስም ኮንትራት ብለው የባጃጅ አሽከርካሪውን ይዘው የሄዱትን ሁለት ወጣቶች ላይ ክትትል ሲደረግ  2016 ዓ.ም ላይ ኩማ አሰፋ እና ደረጀ ግርማ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በአንድ መጠጥ ቤት ቁጭ ብለው ከዓመታት በፊት የፈፀሙትን የግድያ ወንጀል በማንሳት እንዳልተደረሰባቸው  እና ለሌላ የዘረፋ ወንጀል ቁጭ ብለው ሲወያዩ ለፖሊስ ጥቆማ ይደርሰዋል። በዚህም ፖሊስ ሁለቱንም በቁጥጥር ስር ያውላቸዋል። ተከሳሾቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1A-06505 ኦ.ሮ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪን የሚያሽከረክረውን ዳንኤል መሰለን ሰዋራ ጫካ ስፍራ ሲደርሱ በማስቆም የተለያዩ ንብረቶችን ዘርፈዋል። በተጨማሪም ባለ ሶስት እግር ባጃጁን ደግሞ ሚሊዮን ግርማ በተባለ ሶስተኛ ግለሰብ አሽከርካሪነት መቂ ከተማ  በመውሰድ ታርጋ፣ ሊብሬ እና የሻሲ ቁጥር በሀሰት በማዘጋጀት ደቡብ ክልል ዱራሜ ከተማ ወስደው በመሸጥ የተመለሱ እንደሆነ ለፖሊስ በሰጡት የእምነት ቃል ተረጋግጧል። ፖሊስ ባለ ሶስት እግር አሽከርካሪውን ሚሊዮን ግርማን በቁጥጥር ስር በማዋል ተሽከርካሪውን ደቡብ ክልል ዱራሜ ከተማ ገጠራማ መንገድ የትራንስፖርት አገልግሎት ስትሰጥ በቁጥጥር ስር አውሎ በማስረጃነት ወደ ቢሾፍቱ ማምጣቱን ኮማንደር ግርማ ማሞ ገልጸዋል።ፖሊስም በሶስቱ ግለሰቦች ሰፊ ክትትል እና ምርመራ በማድረግ የምርመራ መዝገቡን በአስክሬን ምርመራ እና በሌሎች ማስረጃዎች በማጠናከር ለአቃቢ ህግ ይልካል፡፡አቃቤ ህግ በወንጀል ህግ ቁጥር 539 በከባድ ሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቷል። የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 26 ቀን 2018 በዋለው ችሎት ተከሳሽ ኩማ አሰፋና ደረጀ ግርማ እያንዳዳቸው በ23 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ሲወስን ሶስተኛው ተከሳሽ በወንጀል ድርጊት የተገኘውን ባጃጅ በማሻሻጡ በ20 ዓመት  ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል።ባለ ሶስት እግር ባጃጁ ለተጎጂው ቤተሰብ እንድትመለስ መወሰኑን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር አቃቢ ህግ ፅ/ቤት የተለያዪ ወንጀሎች ምርመራ ክፍል ሃላፊ አቃቢ ህግ ሰኚ ነሞምሳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
😢 43 35👍 3🤔 3👎 2😁 2💔 1
1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
♦️🌴ቴምር ሪልስቴት ሱቅ ሽያጭ የተንጣለለ ዘመናዊ G+4 ሞል በቃሊቲ(ገላን)
💢8 ሳይቶችን ሰርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ቃሊቲ(ገላን) ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ
🛑ቃሊቲ( ገላን ) ሱቅ ሽያጭ  🎯አራተኛ Floor ላይ       👉ጠቅላላ ክፍያ = 2.5 ሚሊዮን ብር       👉የካሬ መጠን = 23.5ካሬ       👉ቅድመ ክፍያ = 500,000 ብር 🎯ሶስተኛ Floor ላይ       👉ጠቅላላ ክፍያ = 2.6ሚሊዮን ብር       👉የካሬ መጠን = 26.8ካሬ       👉ቅድመ ክፍያ = 600,000 ብር 🎯ሁለተኛ Floor ላይ       👉ጠቅላላ ክፍያ = 2.8 ሚሊዮን ብር       👉የካሬ መጠን = 26.8ካሬ       👉ቅድመ ክፍያ = 800,000 ብር 🎯አንደኛ Floor ላይ       👉ሙሉ ክፍያ = 3.2 ሚሊዮን ብር       👉የካሬ መጠን = 26.4ካሬ       👉ቅድመ ክፍያ = 1.2 ሚሊዮን ብር 🎯Ground ላይ ባለ 16 ካሬ       👉ጠቅላላ ክፍያ = 4.3 ሚሊዮን ብር       👉ቅድመ ክፍያ = 1.8 ሚሊዮን ብር 🎯Ground ላይ ባለ 26 ካሬ       👉ጠቅላላ ክፍያ = 4.5 ሚሊዮን ብር       👉ቅድመ ክፍያ = 2 ሚሊዮን ብር 🎯Ground ላይ ባለ 24 ካሬ       👉ጠቅላላ ክፍያ = 6.9 ሚሊዮን ብር       👉ቅድመ ክፍያ = 3 ሚሊዮን ብር ☎️ለበለጠ መረጃ ይደውሉ 👇👇👇👇👇👇 +251937341286 +251714558361 📲👇በ WhatsApp ማግኘት ከፈለጉ https://wa.me/251937341286 📲Channel: https://t.me/TemerRealEstateSalesAdvisor 📲Telegram : t.me/AbrhamTemerSales
Показати все...
10
ትራምፕ  የቅርብ ጊዜውን የሰላም እቅድ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ባለማንበባቸዉ መበሳጨታቸዉን ተናገሩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ጦርነት እንዴት ማስቆም እንደሚቻል የሚያትተዉን የቅርብ ጊዜውን እቅድ የዩክሬን አቻቸዉ ቮልዲሚር ዜለንስኪ አላነበቡትም ሲሉ ተናግረዋል ።በኬኔዲ ማእከል ዋሽንግተን ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ትራምፕ እንደተናገሩት የዜለንስኪ ሰዎች በፍሎሪዳ ከዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ጋር ሲነጋገሩ የቆዩት እቅዱን ወደዉት ነበረ ሲሉ አጥብቀው ተናግረዋል ። ትራምፕ “ሩሲያ ጥሩ ናት” ብለዋል ። "ሩሲያ ዩክሬንን በሙሉ ብትይዝ እንደምትመርጥ እገምታለሁ። ነገር ግን፣ ጥሩ ነች፣ ዘሌንስኪ ጥሩ ስለመሆኑ ግን እርግጠኛ አይደለሁም።" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ዘሌንስኪ ቀደም ሲል ዩክሬን ግዛትን ለሩሲያ አሳልፋ እንድትሰጥ እና የመከላከያ አቅሟን እንድትገድብ የቀረበውን ሀሳብ ተቃውመዋል።ሰኞ ማለዳ ለዩክሬን ህዝብ ባደረጉት ሳምንታዊ ንግግር ዘሌንስኪ ከትራምፕ ልዑካን ጋር "ጠቃሚ ውይይት" መደረጉን ተናግረዋል።አክለውም "የአሜሪካ ልዑካን የዩክሬንን ዋና አቋም ያውቃሉ እና ውይይቱ ቀላል ባይሆንም ገንቢ ነበር፤ ስራችንን እንቀጥላለን አንዳንድ ጉዳዮችን በአካል ብቻ መወያየት ይኖርብናል" ብለዋል፡፡ በቀጠለዉ ዉጊያ በሱሚ ክልል ሰሜን ምስራቅ በምትገኘው ኦክቲርካ ከተማ ሩሲያ በፈጸመችዉ ጥቃት ቢያንስ ሰባት ሰዎች በአንድ ሌሊት ቆስለዋል ሲሉ የክልሉ አስተዳዳሪ ኦሌግ ግሪጎሮቭ ተናግረዋል።ይህ የሆነው ሰው አልባ አውሮፕላኖች አፓርተማዎችን ከመተ በኋላ ነው። በተጨማሪም በቼርኒሂቭ እና ዲኒፕሮፔትሮቭስክ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል፡፡እሁድ እለት በሩሲያ ጥቃቶች አራት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸዉ ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት ብቻ በ1,600 የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና 70 የሚጠጉ ሚሳኤሎች ጥቃት ዩክሬን ደርሶባታል ሲሉ ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ ተናግረዋል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
9😁 7🔥 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
1
ህገወ-ወጥ ጫት ማስቃሚያ ቤቶችን ጨምሮ በተለያዩ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ በተደረገው ፍተሻ ከ17 ሺህ በላይ የሺሻ ዕቃዎችና 605 ኪሎ ግራም ሀሺሽ በመገኘቱ ተሰብስቦ በህግ አግባብ መወገዱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። የቦሌ ክፍለ ከተማ ለወንጀል መንስኤዎችን የሆኑ ድርጊቶችን ለመቆጣጣር ከተለያዩ ከባለድርሻ አካላት በቅንጅት እየሰራ ይገኛል። ዛሬ ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ/ም የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ በተለያዩ ጊዜያት ባደረገው ፍተሻ በኤግዚቢትነት የያዛቸውን የሺሻ ዕቃዎችንና አዕምሮን የሚያደነዝዙ እፆችን ባለድርሻ አካላት፣ የኃይማኖት አባቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በህግ አግባብ አስወግዷል፡፡ ከሐምሌ 2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ህዳር 2018 ዓ/ም በምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ በፔንሲዮኖች፣ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶችና ጫት ማስቃሚያ ቤቶች ላይ በህግ አግባብ በተደረገ ፍተሻ 17ሺ 95 የሺሻ ዕቃዎች፣ 605 ኪሎ ግራም ሀሺሽ እና 100 ኪሎ ግራም ጫት በቁጥጥር ስር በማዋል በህግ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት እንዲወገድ ተደርጓል፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አድማሱ ኢፋ እንደተናገሩት የዜጎችን ሠላም የሚያውኩ እና ለወንጀል መስፋፋት መንስኤ የሆኑ አዋኪ ድርጊቶችን አስቀድሞ ለመከላከል መምሪያቸው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆንኑ ገልፀው አስቀድሞ በተደረጉ ጥናቶች ተገቢውን መረጃና ማስረጃዎችን በማሰባሰብና ወደ ተግባር በመቀየር የወንጀል መንስኤ በሆኑ ደርጊቶች ላይ ተከታታይነት ያለው እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ አስታውሰው ችግሩ ሙሉ በሙሉ እስኪቀረፍ እርምጃችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ሠላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሪድ አስፋው በበኩላቸው ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ እና በተደረጉ ጥናቶች በርካታ የሺሻ ዕቃዎች መያዛቸውን ገልፀው በተለይ ህጋዊ የንግድ ሽፋንን በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባር በሚፈፅሙ ህገ-ወጦች ላይ የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡ በስፍራው ተገኝተን ያነጋገርናቸው ግለሰቦች በሰጡት አስተያየት ፖሊስ ለወንጀል መንስኤ በሆኑ ተግባራት ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ የሚያበረታታ መሆኑን ተናግረው በህገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው በተገኙ ግለሰቦችና የንግድ ድርጅቶች ላይ አስተማሪ ቅጣት ሊወሰድ እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
5🤔 5