ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
Відкрити в Telegram
The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man
Показати більше2025 рік у цифрах

44 133
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
-21530 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አፍሪካ ያላትን ሀብት በቀላል ከአሁን በኃላ ማውጣት አይቻልም ሲሉ ማክሮን ተናገሩ
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የሁሉንም አካላይ ፍላጎት በማክበር ለአህጉሪቱ “አሸናፊ አጋርነቶችን” እንደሚደግፉ በመግለጽ ሀገራቸው በአፍሪካ ላይ ያላትን አቅጣጫ ለመቀየር ቆርጣ መነሳቷን እለት በድጋሚ ገልፀዋል። ማክሮን በአፍሪካ ጉብኝታቸው ሶስተኛ ዙር ከጋቦኑ አቻቸው ብሪስ ኦሊጊ ንጉዌማ ጋር በዋና ከተማዋ ሊብሬቪል ከተገናኙ በኋላ ይህንኑ አስተያየት ሰጥተዋል።
እ.ኤ.አ. በ 2017 መገባደጃ ላይ በቡርኪናፋሶ የመጀመርያው የስልጣን ዘመናቸው ከተናገሩት ጀምሮ አሁንም ለአፍሪካ እንደገና የተሻሻለ አጋርነት እንዳለ አምናለው ብለዋል። “በአክብሮት ባለው ግንኙነት ፣ አንዳችን ለሌላው አርአያ መሆን ያለብን እና ሁኔታዎች ወደ አሸናፊ አጋርነት ሊመሩ ይገባል” ብለዋል ። ማክሮን “አፍሪካ ከአሁን በኋላ በቀላሉ ሀብቷ የሚወጣባት አህጉር መሆን አትችልም” በማለት እንደ ኢነርጂ እና የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ባሉ ሰፊ ዘርፎች አዳዲስ የትብብር ሞዴሎችን መገንባት ይፈልጋል ሲሉ ተደምጠዋል።
በጋቦን ያለውን የሽግግር ሂደት ያደነቁት ማክሮን ወደ ሀገሪተ ተመልሰው በመምጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፤ በ2023 የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የጋቦን መሪ ንጉዌማን በጋቦን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ለውጥ እንዳመጡ ተናግረዋል። "ሁለቱ ሀገራት በጥልቅ በመታደስ፣በማካተት እና በብዝሃ ሃሳብ ላይ የተመሰረተ አዲስ ዘመንን ከፍተዋል ብለዋል። በዚህም የተነሳ ነው ፈረንሳይ ገና ከጅምሩ ሽግግሩን የደገፈችው ሲሉ አክለዋል። ደህንነት በፈረንሳይ-ጋቦን ትብብር ውስጥ ታሪካዊ ምሰሶ እንደሆነም ገልፀዋል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
😁 27❤ 16💯 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከቦሌ ኤርፖርት ወደ ጎሮ የሚወስደው መንገድ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀን ያህል በከፊል ዝግ ነው ተባለ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከቦሌ ኤርፖርት ወደ ጎሮ የሚወስደው መንገድ የመጨረሻ ደረጃ ተደራራቢ አስፋልት የማልበስ ስራ እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በዚህም ምክንያት ከህዳር 15 ጀምሮ ለሦስት ቀናት ያህል ከቦሌ አቅጣጫ ወደ ጎሮ ሚወስደው የመንገዱ ክፍል በከፊል ለትራፊክ ዝግ ይሆናል ሲሉ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የጥገና ስራው ሙሉ በሙሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ መንገዱ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ በመሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አሳስቧል።
የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 4 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 60 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ነው፡፡
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 14👍 2
ለህዝብ ማረፊያ በተሰሩ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም ላይ እርምጃ ተወሰደባቸዉ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም በኮሪደር ልማት ለህዝብ ማረፊያ በተሰሩ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም እርምጃ መውሰዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።
ድርጊቱ የከተማው ገፅታ የሚያበላሽ በመሆኑ ጥፋቱን ፈፅመው የተገኙ የኮርደሩ ልማቱ መዝናኛ ካፌ እና ሰራተኞቹን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ተጠያቂ በማድረግ ጉዳዩ እስኪወሰን ካፌው መታሸጉ ተገልጿል።
ህብረተሰቡ በከተማዋ ውስጥ በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ የኮሪደር ልማቶችና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶችን እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ መገልገልና መጠቀም እንደሚገባም ገልፀዋል።
ባለስልጣኑ ደንብ የተላለፈው የመንግስት ይሁን የግል ድርጅቶች እና ግለሰቦች ያለ ልዩነት በህጉ መሠረት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል። ባለስልጣኑ ጥቆማውን የሰጠው የህብረተሰብ ክፍል በማመስገን ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።
በሰመሀር አለባቸው
#ዳጉ_ጆርናል
😁 49❤ 15👏 5💔 3👎 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አፍሪካ ያላትን ሀብት በቀላል ከአሁን በኃላ ማውጣት አይቻልም ሲሉ ማክሮን ተናገሩ
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የሁሉንም አካላይ ፍላጎት በማክበር ለአህጉሪቱ “አሸናፊ አጋርነቶችን” እንደሚደግፉ በመግለጽ ሀገራቸው በአፍሪካ ላይ ያላትን አቅጣጫ ለመቀየር ቆርጣ መነሳቷን እለት በድጋሚ ገልፀዋል። ማክሮን በአፍሪካ ጉብኝታቸው ሶስተኛ ዙር ከጋቦኑ አቻቸው ብሪስ ኦሊጊ ንጉዌማ ጋር በዋና ከተማዋ ሊብሬቪል ከተገናኙ በኋላ ይህንኑ አስተያየት ሰጥተዋል።
እ.ኤ.አ. በ 2017 መገባደጃ ላይ በቡርኪናፋሶ የመጀመርያው የስልጣን ዘመናቸው ከተናገሩት ጀምሮ አሁንም ለአፍሪካ እንደገና የተሻሻለ አጋርነት እንዳለ አምናለው ብለዋል። “በአክብሮት ባለው ግንኙነት ፣ አንዳችን ለሌላው አርአያ መሆን ያለብን እና ሁኔታዎች ወደ አሸናፊ አጋርነት ሊመሩ ይገባል” ብለዋል ። ማክሮን “አፍሪካ ከአሁን በኋላ በቀላሉ ሀብቷ የሚወጣባት አህጉር መሆን አትችልም” በማለት እንደ ኢነርጂ እና የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ባሉ ሰፊ ዘርፎች አዳዲስ የትብብር ሞዴሎችን መገንባት ይፈልጋል ሲሉ ተደምጠዋል።
በጋቦን ያለውን የሽግግር ሂደት ያደነቁት ማክሮን ወደ ሀገሪተ ተመልሰው በመምጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፤ በ2023 የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የጋቦን መሪ ንጉዌማን በጋቦን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ለውጥ እንዳመጡ ተናግረዋል። "ሁለቱ ሀገራት በጥልቅ በመታደስ፣በማካተት እና በብዝሃ ሃሳብ ላይ የተመሰረተ አዲስ ዘመንን ከፍተዋል ብለዋል። በዚህም የተነሳ ነው ፈረንሳይ ገና ከጅምሩ ሽግግሩን የደገፈችው ሲሉ አክለዋል። ደህንነት በፈረንሳይ-ጋቦን ትብብር ውስጥ ታሪካዊ ምሰሶ እንደሆነም ገልፀዋል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
የወለደችውን ልጅ መፀዳጃ ጉድጓድ ውስጥ በመጣል ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገች ተከሳሽ በእስራት ተቀጣች
በኢሊባቡር ዞን ቡሬ ወረዳ ሲቦ 01ቀበሌ ውስጥ ከጋብቻ ውጭ የወለደችውን ልጅ መፀዳጃ ጉድጓድ ውስጥ የጣለች እናት በእስራት ተቀጥታለች። ከኢሊባቡር ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮምንኬሽን ፅህፈት ቤት ብስራት ያገኘው መረጃ እንዳመለከተው ተከሣሽ ዘር ትሑን አዲሱ የተባለች ወጣት የወንጀል ድርጊቱን መስከረም 11 ቀን 2018 ከምሽቱ ሶስት ሠዓት ላይ ፈፅማለች።
በዚሁ እለት የወለደችውን ልጅ ማንም ሣያያት መፀዳጃ ጉድጓድ ውስጥ በመጣል የተሸሸገች መሆኑ ተመላክቷል። መፀዳጃ ጉድጓድ ውስጥ የተጣለው ልጅ አስክሬን መጥፎ ጠረን በማምጣቱ በተደረገ ፍተሻ ከአራት ቀን በኃላ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ በፖሊስና በሕብረተሠቡ ትብብር ከመፀዳጃ ቤት የወጣ እንደሆነ ተገልፅዋል።
ፖሊስ ከመፀዳጃ ውስጥ የወጣውን አስክሬን ወደ ሆስፒታል ለምርመራ በመላክ ተከሳሿን ከተሸሸገችበት በቁጥጥር ስር አውሏል። ተከሳሿ በሰጠችው ቃል ከጋብቻ ውጭ ፀንሣ በመውለዴ ባደረባት ጭንቀት ድርጊቱን መፈፀሟን ተናግራለች። ፖሊስም የምርመራ መዝገቡን በማስረጃ በማጠናከር ለአቃቤ ሕግ ልኳል።
በአቃቤ ሕግ የተመሠረተውን ክስ የተመለከተው የኢሊባቡር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሕዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሣሽ ዘርትሁን አዲሱ ጥፋተኛ በማለት በአስራ አንድ አመት ከአራት ወር እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል።
በሰመሀር አለባቸው
#ዳጉ_ጆርናል
😱 15❤ 7🙏 4🤔 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሃማስ ከግብፅ የስለላ ሃላፊ ጋር ባደረገው ቆይታ እስራኤል በጋዛ የተኩስ አቁምን አደጋ ላይ ጥላለች አለ
የሐማስ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን የግብፅን የስለላ ሀላፊ በካይሮ አግኝቶ በእስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት መጣስ ላይ መወያየቱን ቡድኑ ገልጿል።በጋዛ ውስጥ ፍልስጤማውያን ላይ በቅርብ ጊዜ በእስራኤል ጥቃቶች ለተገደሉ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች የቀብር ስነስርአት ተፈፅሟል።
ቡድኑ የተኩስ አቁም ስምምነቱን የመጀመሪያ ምዕራፍ ከግብፅ የስለላ ኃላፊ ሃሰን ራሻድ ጋር ባደረገው ስብሰባ ተግባራዊ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጧል። ነገር ግን እስራኤልን "ስምምነቱን ለማፍረስ" የምትወስደው እርምጃ ያሰጋል ያለው ሃማስ "የቀጠለውን ጥሰት" በማንሳት እስራኤልን ወንጅሏል።
በልኡካን ቡድኑ ውስጥ በስደት የሚገኘው የጋዛ መሪ ካሊል አል-ሀያን ያካተተው ሃማስ፣ ማንኛውንም የስምምነት ጥሰት ለመመዝገብ እና ለማስቆም በአስታራቂዎች ቁጥጥር ስር “ግልጽ ዘዴ” እንዲተገበር ጠይቋል። ግብፅ፣ኳታር እና አሜሪካ ባለፈው ወር ተግባራዊ የሆነው የተኩስ አቁም ስምምነት በሃማስ እና በእስራኤል መካከል እንዲደረስ የሽምግልና ሚና መወጣታቸው ይታወሳል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
😢 19❤ 2🔥 2
ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከበረ
👉ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል ተዋናይ ቸርነት ፍቃዱን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ
ሆስፒታሉ "25 ዓመታት ከልብ በመነጨ እንክብካቤ ወደ ላቀ ምዕራፍ" በሚል መሪ ቃል 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አክብሯል።
ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል ከክሊኒክ ተነስቶ ዛሬ ላይ ዓለም የደረሰበትን የህክምናው የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች፣ ስፔሻሊስቶች እና ሰብስፔሻሊስቶችን በመያዝ እየሰራን እንገኛለን ሲሉ የሆስፒታሉ ም/ል ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ቤዛ ሀይሉ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ሆስፒታሉ በስሩ ከ550 በላይ ሰራተኞች የሚያስተዳድር ሲሆን 85 በመቶ የሚሆኑት ሴት ሰራተኞች መሆናቸውን የሆስፒታሉ ም/ል ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ቤዛ ሀይሉ አክለው ተናግረዋል።
በተጨማሪም ሆስፒታሉ የድንገተኛ ህመም ህክምና ለ24 ሰዓታት አገልግሎት ይሰጣል ያሉት የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር መክሊት አያሌው፤ ዘመናዊ መሳሪያዎችን በመጠቀም የቀዶ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን ብለዋል። የቅድመ ወሊድ፣ የድህረ ወሊድ፣ የህፃናት እና የማህፀን ካንሰር ህክምና በመስጠት ላይ እንገኛለን ሲሉ አክለው ተናግረዋል።
የሆስፒታሉ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ የተሾመው ተዋናይ ቸርነት ፍቃዱ፤ የተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል ስራዎች እና አገልግሎቶች ለቀጣዮቹ 6 ወራት ለማስተዋወቅ እና አብሬአቸው ለመስራት ቃል እገባለሁ ብሏል።
ሆስፒታሉ አዲስ ኮምፕሬሄንሲቭ ሆስፒታል ለመገንባት ያቀደ ሲሆን፣ ሆስፒታሉ ሲጠናቀቅ ከ200 በላይ አልጋዎች ይኖሩታል መባሉን ብስራት ሰምቷል። ሆስፒታሉ የ25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ለ 6 ወራት ያክል ለማክበር ያቀደ ሲሆን ይህም ከህዳር 14 እስከ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም የሚዘልቅ ነው።
ሆስፒታሉ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች፣ የነፃ ህክምና፣ በሆስፒታሉ በተመረጡ ቀናት ለሚወልዱ እናቶች ልዩ ሽልማት እንዲሁም ልዩ የህክምና ክፍያ ቅናሽ በማድረግ ለቀጣዮቹ 6 ወራት ለማክበር መዘጋጀቱን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።
ሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 37🔥 5🤝 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ወንድማማቾች በአንድ ቀን በተለያዩ የመኪና አደጋዎች ህይወታቸው አለፈ
የሁለት ወንድማማቾች ዕለታዊ ድርብ ሐዘን
1. ታላቁ ወንድም - ይስሐቅ አብርሃም
በአርባ ምንጭ ሃይላንድ ሙሉ ወንጌል አባልና አገልጋይ የነበረ። ከአዲስ አበባ ወደ አርባ ምንጭ በሚያደርገው ጉዞ ላይ እያለ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወቱ አልፏል።
2. ታናሹ ወንድም - አቤኔዘር አብርሃም
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪ የነበረ። የታላቅ ወንድሙን (ይስሐቅን) መርዶ እንደሰማ፣ ቀብር ለመድረስ ከሆሳዕና ወደ ወላይታ ሶዶ ሲጓዝ ነበር። በትላንትናው ዕለት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በከምባታ ዞን በደረሰ ሌላ የመኪና አደጋ ሕይወቱ አልፏል።
#ዳጉ_ጆርናል
😢 181💔 77❤ 15😭 11🙏 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የፊልም ግብዣ ከዳጉ
👉 THE BEAST IN ME
የልጅህን ሀዘን በቅጡ ሳትወጣ ራስ ምታት የሆነ ፣ ትከሻ ለመለካካት የሚከብድ አዲስ ጎረቤት ቢመጣብህስ 🤔የደራሲዋ አጊ እና በቀድሞ ሚስቱ ህልፈት እጁ እንዳለበት የሚጠረጠረው ባለሀብቱ ጃርቪስ : ከጅምሩ የተዋደዱ አይመስልም ። ዳጉ ይህንን ልብ አንጠልጣይ mini series ትመለከቱ ዘንድ ጋበዛችሁ
❤ 23👍 7🔥 3
ከቦሌ ብራስ - በኤድናሞል ወደ አትላስ ሆቴል የሚወስደው መንገድ ለሁለት ቀናት እንደሚዘጋ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።
በሥፍራው የሚካሄደውን የኮሪደር ልማት በፍጥነት ለማጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች በከፍተኛ ትጋት እየሰራ መሆኑን እየገለፀ፣ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት በአትላስ መብራትና አካባቢው በሚከናወነው የግንባታ ሥራ ምክንያት፤ ቅዳሜ ህዳር 13 እና እሁድ ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቦሌ ሩዋንዳ አቅጣጫ ወደ ውሃ ልማትና ተቃራኒ አቅጣጫ የሚወስደው መንገድ ለትራፊክ ዝግ የሚደረግ መሆኑን ያስታውቃል፡፡
በመሆኑም አሽከርካሪዎች በተጠቀሱት ቀናት አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ለግንባታው መፋጠን እንዲተባበሩ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በአክብሮት ያሳስባል፡፡
የተሻለ መንገድ፣ ለተሻለች አዲስ አበባ፤
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
❤ 11👎 9👍 2
ንሰር ማይክሮፋይናንስ አጠቃላይ ተቀማጩ 80 በመቶ እድገት ማሳየቱን አስታወቀ
ንስር ማይክሮ ፋይናንስ በሒሳብ ዓመቱ መጨረሻ ላይ ከብር 1.6 ቢሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘቡን ከ 3.7 ቢሊዮን በላይ አድርሷል። ካለፈው አመት አንፃር የ8ዐ በመቶ እድገት ማስመዝገቡ ተገልፆ በቀጣዩ ሒሳብ ዓመትም የተቀማጭ ገንዘቡን ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ለማድረስ መታቀዱን አስታውቋል።
የብድር እድገቱ በዓመቱ መጨረሻ ተቋሙ ያለው የብድር መጠን 3.8 ቢሊዮን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን ካለፈው አመት አንጻር የ74 በመቶ እድገት አስመዝግቧል። በቀጣዩ ሒሳብ ዓመትም የ7ዐ በመቶ እድገት በማስመዝገብ አጠቃላይ የብድር መጠኑን 6.1 ቢሊዮን ብር በላይ ለማድረስ በእቅድ መያዙ ተገልጿል። ጠቅላላ የዓመቱ የተቋሙ ገቢ ከታክስ በፊት ከ ብር 120 ሚሊዮን በላይ ካለፈው አመት ጭማሪ በማሳየት 165 ሚልዮን ብር በላይ ደርሷል። ጠቅላላ የዓመቱ ወጪ ደግሞ 800 ሚሊዮን ብር ሲደርስ ካለፈው አመት አንጻር 45 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
ተቋሙ በአጠቃላይ ከግብር በፊት ብር 165 ሚሊዮን ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን ይህም ከተጠናቀቀው ሒሳብ አመት ጋር ሲተያይ የ268 በመቶ ጭማሪ የተመዘገበበት ወጤታማ ዓመት መሆኑን አክለዋል። በሂሳብ አመቱ የተቋሙ ጠቅላላ ሀብት 5.53 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ2 ቢሊዮን ብር ወይም የ 58 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተገልጿል። በቀጣዩ ሒሳብ አመትም ጠቅላላ ሃብቱን ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ለማድረስ ታቅዷል።
ቅርንጫፍ ከማስፋፋት ጋር በተያያዘ የነበሩትን 13 ቅርንጫፎች ወደ 20 ቅርንጫፍ አሳድጎ አድማሱን ለማስፋት ከአዲስ አበባ ከተማ በተጨማሪ በኦሮሚያ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ተደራሽነታችንን ያስፋፋበት ዓመት ሆኖ ማለፉ ተገልጿል። በተጨማሪም የንሰር ማይክሮፋይናንስ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ በ 2017 ሒሳብ ዓመት 3.73 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የብር 1.66 ቢሊዮን ወይም የ80 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ይህ ከፍተኛ የተቀማጭ ገንዘብ እድገት ሴክተሩ ላይ ከሚታየው ከፍተኛ ፋክክር ጋር ሲታይ መልካም መሆኑን ተመላክቷል።
በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 16👎 12👍 1🔥 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አሐዱ ባንክ ከታክስ በፊት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ
አሐዱ ባንክ በዛሬዉ ዕለት ባካሄደዉ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ በተመሠረተ ጥቂት ዓመታት ዉስጥ በ2024/25 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን ለብስራት ሬዲዮ አስታውቋል ።
የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ በበጀት ዓመቱ 7.88 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ይህም ካለፈዉ ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ41 በመቶ እድገት አሳይቷል ። በዉጭ ምንዛሬ ግኝት ከ88.2 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካ ዶላር መሰብሰቡ የተገለፀ ሲሆን ይህም ካለፈዉ ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ10.3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል ።
የባንኩ ጠቅላላ ገቢ ከ2.16 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን ያስታወቀዉ ባንኩ ይህም ከአምናዉ ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ87 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጿል ። ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት 502.1ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማስመዝገብ ካለፈዉ ዓመት የ351 በመቶ ብልጫ በማስመዝገብ ከፍተኛ ብልጫ አሳይቷል ።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባንኩ ተጨማሪ 390ሺህ ደንበኞችን በመመልመል የደንበኞቹን ብዛት 1.1 ሚሊዮን ማድረሱን አስታዉቋል ።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
👎 16🔥 12❤ 9👍 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከቦሌ ብራስ - በኤድናሞል ወደ አትላስ ሆቴል የሚወስደው ኮሪደር በግንባታ ምክንያት ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።
በሥፍራው የሚካሄደውን የኮሪደር ልማት በፍጥነት ለማጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች በከፍተኛ ትጋት እየሰራ መሆኑን እየገለፀ፣ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት በአትላስ መብራትና አካባቢው በሚከናወነው የግንባታ ሥራ ምክንያት፤ ቅዳሜ ህዳር 13 እና እሁድ ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቦሌ ሩዋንዳ አቅጣጫ ወደ ውሃ ልማትና ተቃራኒ አቅጣጫ የሚወስደው መንገድ ለትራፊክ ዝግ የሚደረግ መሆኑን ያስታውቃል፡፡
በመሆኑም አሽከርካሪዎች በተጠቀሱት ቀናት አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ለግንባታው መፋጠን እና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 16
ያንጎ ኢትዮጵያ፣ የመንገድ ደህንነት ስልጠና እና የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና መስጠት ጀመረ
የዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ ያንጎ ግሩፕ አካል የሆነውና በጂቱጂ አይቲ ሶሊውሽን አ.ማ. እና በኤለጋንስ ኢምፖርት ኤንድ ኤክስፖርት ፒኤልሲ ስር የሚተዳደረው ያንጎ ኢትዮጵያ፣ ለደኅንነት፣ ለአገልግሎት ልህቀት እና ቅልጥፍና እንዲሁም ለማህበረሰብ ተሳትፎ ያለውን ቁርጠኝነት በማጠናከር የመንገድ ደህንነት ፕሮግራም እና የመጀመሪያ እርዳታ እና የአገልግሎት ልህቀት ስልጠና መርሐግብር ለአጋር አሽከርካሪዎች መስጠት ጀምሯል፡፡
“ያንጎ ኬርስ” በተሰኘው የማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎት ስር የተጀመረው ይህ ተነሳሽነት፣ የኩባንያው ትኩረት ይበልጥ ደህንነታቸው በተጠበቁ መንገዶች፣ በጠንካራ ማህበረሰቦች እና ለተሳፋሪዎች ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ያሳያል፡፡ የስልጠናው ክፍለ ጊዜ፣ አጋር አሽከርካሪዎች የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ እና ተግባራዊ የመጀመሪያ ህክምና ክህሎቶችን እንዲታጠቁ በማድረግና የተሳፋሪዎችን ልምድ በማጎልበት- በመላ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰፊው ሕዝባዊ ደህንነት አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።
በተመሳሳይ ጊዜም፣ ያንጎ ከፍተኛ አፈጻጸም፣ ቁርጠኝነት፣ አስተማማኝነት ላላቸው እና ደንበኛን ያማከለ አገልግሎት ለሚሰጡ አጋር አሽከርካሪዎች ዕውቅና መስጠቱን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል። ኩባንያው ለእነዚህ ግለሰቦችእውቅና በመስጠት፣ አሽከርካሪዎች በዘርፉ ለሚጫወቱት ወሳኝ ሚና አፅንዖት በመስጠት ለስራቸው ያለውን አድናቆት ያሳያል።
በፕሮግራሙ ላይ፣ በኢትዮጵያ የያንጎ ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ይቅናአለም አበበ፣ የያንጎን አገልግሎት የሚጠቀሙና የሚሰጡ አሽከርካሪዎች የልብ ትርታዎቻችን ናቸው፡፡ በመሆኑም ደህንነታቸው እና ዕድገታቸው ቀዳሚ ጉዳዮቻችን ናቸው። በተለይ በዚህ ራስን የማደስ ጊዜ፣ በስልጠና፣ ዕውቅና በመስጠት እና የማህበረሰብ ተነሳሽነት ላይ ኢንቨስት በማድረግ ለሾፌሮቻችን ብቻ ሳይሆን ለምናገለግላቸው ማህበረሰቦች ደህንነት ተቆርቋሪነታችንን በማሳየት የኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ ላይ የድርሻችንን እንደምናበረክት እናምናለን ሲሉ አክለው ተናግረዋል፡፡
ያንጎ፣ በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ባለው የግል ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ዘርፍ ውስጥ የመሪነት ቦታውን እያጠናከረ ነው። ያንጎ፣ ተጨማሪ አሽከርካሪዎች በማደግ ላይ ያለው የያንጎ ትራንስፖርት አገልግሎት ስርዓት አካል እንዲሆኑ ጥሪውን የሚያቀርብ ሲሆን፣ ይህም የስልጠና ዕድሎች ማግኘትን፣ የዕውቅና ፕሮግራሞችን እና የአሽከርካሪዎችን አስተዋጽዖ ዋጋ የሚሰጥ ደጋፊ የግንኙነት መረብን ጨምሮ በርካታ ጥቅማ ጥቅሞችን ያካተተ ነው።
ሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 15👎 6
ውሐ ከወንዝ ቅጅ በማለት 16 ዓመቷን ታዳጊ እንድትጠለፍ ያመቻቸች ግለሠብ ና ጠላፊው በእስራት ተቀጡ
የወንጀል ድርጊቱ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳዋ ወረዳ ሴደሬ ሐርቡ ቀበሌ ውስጥ ተፈጽሟል። የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ እንደገለፀው አንደኛ ተከሣሽ ሙሉነሕ በይዶ እና ሁለተኛ ተከሣሽ አለሚቱ ተሾመ በመሆን ታዳጊዋ ላይ ጠለፋ እንዲፈፀም ና የመደፈር ጥቃት እንዲፈፀም በማድረግ ና በማመቻቸት ተከሠው በእስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።
ሁለተኛ ተከሣሽ አለሚቱ ተሾመ የተባለችው ግለሳብ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓም ከቀኑ አስራ አንድ ሠዓት ላይ በሥዋ ስር የምትተዳደረውን ታዳጊ አንደኛ ተከሣሽ እንዲጠልፋት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት አቅዳ ውሃ ከምንጭ እንድትቀዳ እንደ አዘዘቻት ና የታዘዘችውም ልጅም ውሃ ከምንጭ ለመቅዳት ሄዳለች፡፡
አንደኛ ተከሳሽ በሁለተኛ ተከሣሽ አመቻችነት ውሃ ለመቅዳት ወደ ምንጭ የሔደችውን ታዳጊ ልጅ ጠብቆ በጉልበት ጠልፎ ወደ አዘጋጀው ስፍራ ወስዷል፡፡ተከሣሹ በጠለፋት ታዳጊ ላይ በጉልበት የመድፈር ጥቃት የፈፀመባት ሲሆን ተጎጂዋ ከቀናት በኃላ አመቺ ግዜ ስታገኝ ካለችበት ስፍራ አምልጣ የደረሰባትን ለምታቃቸው ሰዎች በመናገሯና ጉዳዩን ለፖሊስ በመጠቆሙ ወደ ጤና ተቋም እንድታመራ በማድረግ ሁለቱን ተከሣሾች በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡
ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ሙሉ በሙሉ በማስረጃዎች አጠናክሮ ለአቃቢ ሕግ የላከ ሲሆን አቃቢ ሕግም ክስ መስርቷል፡፡የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሣሽ ሙሉነሕ ቦይዶ በጠለፋና በመድፈር ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑ በመረጋገጡ በአስራ አምስት አመት እስራት እንዲቀጣ ሲወሠን ሁለተኛ ተከሣሽ አለሚቱ ተሾመ ለዚሕ የወንጀል ድርጊት ሑኔታዎችን በማመቻቸት ጥፋተኛ ተብላ በሁለት ዓመት እስራት እንድትቀጣ ወስኗል፡፡
በቤዛዊት አራጌ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 26👎 12🤩 2💔 2👍 1
