መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿
Відкрити в Telegram
☑ ከጥንት አባቶቻች በተቸረን ሰሎሞናዊ ጥበብ ተፈጥሮ ያበቃላቸው የእፅዋት መድሀኒቶችን በመጠቀም ክፉ ዓይነ ጥላ ፣ በቤተሰብ ወይም በዘር የሚተላለፉ መናፍስት መፍትሔዎቻቸው ይተነተናሉ። ☑ አድራሻ ቁጥር 1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ቁጥር 2 አ/አ አየር ጤና እንዲሁም በተለያዩ የክልል ከተሞች እንልካለን 📞#0918834904 📞#0915310455 መልዕክት ካለዎት @merigetaamedeberhan
Показати більше2025 рік у цифрах

118 402
Підписники
-16024 години
-1 0107 днів
-4 57830 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
❤️ፍታሕ፡ሊተ፡እግዚኦ፡እስመ፡አንሰ፡በየዉሀትየ፡አሐውር❤️
ፍረድልኝ፡ አቤቱ፡ እኔ፡ በገርነቴ፡ እሔዳለሁና።
በእግዚአብሔር፡ አመንሁ፡ እንዳልደክም፡ፍተነኝ።
አቤቱ፣ መርምረኝም ፣ልቤን ፣ኩላሊቴንም፣ፍተን።
ምሕረትህ፡ባይኔ፡ፊት፡እንደ፡ሆነ፡በማዳንህ፡ደስ፡አለኝ።
በምናምን፡ሸንጎ፡አልተቀመጥሁም፡ከወንጌለኞች፡ጋራ፡ አልገባሁም
👍 1❤ 1
♥የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው♥
♦ስለጥበብ እና ስለ እጽዋት ጥቅም በተማማርን ጊዜ ስለፈጣሪ ረቂቅ ጥበብ ሳይረዱ እና ሳይመረምሩ እንዲህ ብለው ሲሳለቁ ይስተዋላሉ።
¡በኢየሱስ ስም ይህ መንፈስ ይወጋ!
¡ዘመናዊ ጠንቋይ!
¡በኢየሱስ ስም ይፍረስ!
¡አጋንንት እንዳያጋቡባችሁ!
¡ደብተራ!ወዘተ በማለት እውነተኛው የቀደምቶቹ የአበው ጥንታዊ የእጽዋት ሕክምናን ወደኃላ አንድ እርምጃ ለመጎተት በእውቀትም ያለእውቀትም ለተነሱ ወዳጆቼ ይሁን።
♥በስመአብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ ፡ቅዱስ፡ ፩ አምላክ፡ እጀምራለሁ፡ምድር፡ታበቅል ሣሩን ሁሉንም እንደ ዘመዱ ብሎ ለኛ የሠጠንን ሁሉ ምግብ በምድር ላይ እንደሚገባ። ለአካላታችን እጥፋለሁ በጤናም በእመምም እንደሚሆን እንዲሁም!
♥ምስጋና ለእግዚአብሔር ቀድሞ ለነበረ ኋላም በዚህ ዓለም ልጁን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለኛ ቤዛ አድርጎ ለሰደደ ለመንፈስ ቅዱስም ለሚያጸናን አሜን።
#የደዌ መጀመርያው ራብ ነው፡፡
በራበህ ጊዜ እንጀራ ብላ ትፈወሳለህ ይላል ቃል በቃል የአባቶች መልእክት።
#ዳግመኛም ጥም ነው።
⏩ውኃ በጠማህ ጊዜ ውኃ ጠጣ፡፡ትፈወሳለህ።
ይህንን ሁሉ ስጦታ አይተህ ሁልጊዜ ለእግዚአብሔር ምስጋና ስጥ የእግዚአብሔርን ባለጠግነት ያንተን ድኅነት በዚህ እወቀው አንተ ከናትህ ሆድ በወጣህ ጊዜ እራቁትህን ወጣህ እግዚአብሔር ግን ከዚህ መጣ ከዚህ ወጣ መጀመርያው ከዚህ ነው መጨረሻው ከዚህ ነው የሚል የለም።
♥ባለጠግነቱም እንደ ሰው አያከማችም። አይከትም። ጎታም የለው። ሣጽንም የለው።እንዲያው ይሠጣል እንጅ።ጥበብንም ሰጠን።
⏩እስቲ አስተውል አንተ ሰው ይህን ሰማይና ምድር ከወዴት አምጥቶ ሠራው ይህነንስ ሁሉ ፍጥረት ቀድሞ ይህ ሁሉ አልነበረም።
⏩እየው እግዚአብሔር የሚያመጣበት አይታወቅም። ባለጠግነቱ ስለዚህ ይታወቃል።አሁንም ክብር እና ምስጋና ይሁን።ለእግዚአብሔር አብ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን።
♥ደግሞም አንተ ሰው ብልሐተኛ ብትሆን የነፍስና የሥጋ መድኃኒት ብትፈልግ ሳትደክም ታገኛልህ።በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ብታምን አንተም ለዘላለም ትድናለህ ሰውም ታድናለህ።እርሱም ጌታ ብሏል የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል እምነት ቢኖራችሁ ኮረብታውን ታፈልሱታላችሁ።
♥ስለዚህ የእጽዋት ድንቅ ጥበብ እና ስራም ከእግዚአብሔር ዘንድ መሆኑን ተረድተህ መፍትሔውን ብትሻ ፈውስ ታገኛለህ።
❤️ፍጥረታት ሁሉ ሲፈጠሩ አንዱን አንዱን ይረዳ ዘንድ ነውና እጽዋቶችም የታመሙ የሰው ልጆችን ፈውስ ይሆኑ ዘንድ!
❤️ለሰው ልጆች፣ ለምድር አራዊቶች፣እንዲሁም ለሰማይ አእዋፋቶች ፣ለባህር እንስሳቶች፣ ይረዱ ዘንድ የተፈጠሩ ድንቅ ፍጥረታር ናቸው።
✅እናማ ውድ ቤተሰቦቼ ብንችል ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ትመለስ ዘንድ ስለ ጥበብ እንዘምር።
✅ባንችል ደግሞ ባልመረመርነው ነገር፣ በአፈታሪክ ብቻ ፀያፍ እና ያልተገቡ ቃላት በመጠቀም ጥበብን አንድ እርምጃ ወደ ኃላ በመጎተት የሀገራችን ተስፋ አናበላሽ !!!
👍 5❤ 2
☘መርጌታ አምደ ብርሃን የሀገረ ሰብእ ህክምና☘☘
🌿ለግርማ ሞገስ🌿
🌿ለገበያ ወለመንድግ🌿
❤️ሰላም
❤️ፍቅር
❤️ጤና ለእምየ ኢትዮጵያ እና ለሃገሬ ልጆች ይሁን።
🌿ዛሬ ስለ ግርማ ሞገስ እና ስለ መፍትሔ ሃብት በመጠኑ ገለጻ አድርጌ ወደ መፍትሔው የምገባ ይሆናል።
🌿ግርማ ሞገስ ማለት ሞገስን መጎናጸፍ፡ ግርማን መላበስ፡ መወደድ ፡መፈራት:በሰዎች ዘንድ ተፈላጊ መሆንን ያካትታል።
🌿ግርማ ሞገስ መጠቀም ያለበት ሰው ማን ነው?
🌿የሰው ልጅ በተፈጥሮው መልከ መልካም እና ባለ ግርማ ሞገስ ነው።
የኃላ ኃላ ግን ጸላኢ ሰናይ ወይንም አጋንንት በሰው ልጅ ተግባር በመቅናት እንዲሁም በመተት፣ በዛር አምልኮ፣በዓይነጥላ፣ ወዘተ... አማካኝነት ከ ፈጣሪ ዘንድ የተሰጠነው ፀጋ ፣ግርማ ሞገስ፣ የሰው መውደድ፣ ስንነጠቅ የምንጠቀመው መፍትሔ ነው።
🌿ለምሳሌ ህጻናቶች እጅግ ተወዳጆች ናቸው የህጻን ማስጠያ እስከዚህም ነው የለም ማለት ይቻላል።
ምክንያቱም ከፈጣሪ ዘንዳ የተሰጠው ጸጋ ስላልተነጠቀ የደስደሱ፣ የፍቅር ጸጋው፣ ስለተላበሰ እንወደዋለን እንሳሳለታለን።
🌿ህፃኑ ከፍ እያለ በሄደ ቁጥር ዕድሜው ሲገፋ መናፍስቶቹ ግርማውን በመሻማት የመሰለብ መንፈስ፣ የመጠላት መንፈስ ሲረጩበት ግርማ ቢስ ፣ነጠላ፣የምታስጠላ ይባላል።
🌿ይህንን ችግር ለማስተካከል መጸለይ፣ ስጋሁ እና ደሙ ፣መቀበል፣ መስገድ፣ መጸበል፣ የጥበብ አባቶችን፣ ማማከር ግድ ይለናል።
🌿መፍትሔ ሃብትም እንዲሁ እኛ ዘንድ ያለው ዕድል ሲሰለብ በረከት እናጣለን፣ ስራ እናጣለን ፣ትዳር እናጣለን፣ገበያ እናጣለን፣የልጅነት ዕድላችን ስንነጠቅ የምንጠቀመው የቀደምት አባቶቻችን መፍትሔ እነዚህ መናፍስት የማራቅ ሃይል የድሮ ጸጋችን የማስመለስ ስራ መፍትሔ ሃብት ይባላል።
ሃብትን የሚፈታ ድህነትም የሚቀርፍ ለማለት ነው።
ይህ ደግሞ ካልሰራን መቼም ሊሆን አይችልም አንድ አንድ ሰዎች ሳልሰራ ብር ማግኘት እፈልጋለው ብለው የሚጠይቁ ሰዎችም ስላሉ ነው።
🌿ወደ መፍትሔው ስንሄድ🌿
ጸሎት ፡በእንተ ፡ግርማ ፡ሞገስ፡ ወውሂበ፡ ንዋይ፡ ወመንድግ፡ወአደባባይ፡ፎንርፎን :ራፎን ፡አኽያ፡ሸራኽያ ፡ዳማኤል፡ብርናኤል: አቅናኤል:ሱባኤል:ፍናኤል፡ኤልናኤል:ብርላኤል፡ ከማሁ፡ ይስግዱ፡ መኳንንት፡ እለ፡ ሀለዉ፡ በአደባባይ ፡ከማሁ ፡የሀቡኒ፡ ንዋዮሙ፡ ነጋድያን፡ወሐረስት፡በገበያ፡ ወቤት፡ሀቡ ፡ሀቡ፡ ሀቡ፡ ይበሉክሙ፡ አብ ፡ወወልድ፡ ወመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ሊተ ለገብርከ ዕገሌ: (የዓለም ስም አስገቡ)
🌿ገቢር ፦የጠምበለል (ጠንበለል)Jasminum spp.ተቀጽላ ማክሰኞ ቀን ቆርጠው አድርቀው አድቀው ውኃ ባልነካው ቅቤ ወይም (በቅብዓ ቅዱስ) በንጹህ እቃ ለውሰው ለሰባት ቀን ሰባት ሰባት ጊዜ እየጸለዩ በየቀኑ እየተቀቡ ወደስራ አልያም ወደ ገበያዎት ይውጡ።
ዘተፈትነ!!!
🌿የተለወሰው መፍትሔ የተረፈ እንደሆነ ንጹህ በሆንንበት ሰዓት እየተቀባነው ብንውጣ ግርማሞገስም መፍትሔም ነው።
🌿በብር ቀለበትም ለሰባት ቀን በቅብዓ ቅዱስ ዘፍዝፈን ሰባት ሰባት ጊዜ እየጸለይን በሰባተኛው ቀን ጸልየን ብናስረውም ግርማሞገስም መፍትሔ ሃብትም ነው።
🌿የጠምበለል ተቀጽላ ከዚ ውጭ ሊቃውንቶች ለመፍዝ ፣ለጠላት መከላከያ፣ለብትር ለዱላ ለጥይት ወዘተም ሲጠቀሙበት ይታያል።
ይህ ጥበብ ውጤቱ አርኪ የማያደክም የተቸገሩትን የሚያነሳ መፍትሔ ነውና እንጠቀምበት ዘንድ!
🌿ስራ ላጡ፣ ገበያ ለጠፋባቸው፣ በሰዎች ዘንድ ያለምክንያት ለሚጠሉ፣ግርማ ሞገስ ለሌላቸው የሚሆን የአበው ቀደምት መፍትሔ ነውና ሼር በማድረግ ተጠቅመን ሰው እንጥቀም።
👉አድራሻችን
አዲስ አበባ አየር ጤና ወደ ዓለም ባንክ መሄጃ በ ቤተል መገንጣያ በኩል ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ትራንስፖርት ማሰልጠኛው አጠገብ እንገኛለን
👉 ዋና መገኛ ቦታዬ ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከመናኸሪያው ወደ ሽዲ መሄጃ መስመር ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ 100 ሜትር ገባ ብሎ አገኛለሁ።
☎️#0918834904
☎️#0915310455
✔️ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@merigetaamedeberhan
✔️ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@merigeta_amedebrhan
✅ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/profile.php?id=100076378898155
✅የቴሌ ግራም ቻናላችን
https://t.me/mergeta_amdebrhan
✅የቴሌ ግራም ቻናላችን
t.me/mergeta_amdebrhane
✳️የቲክቶክ ቻናላችን
http://tiktok.com/@mergetaamdebrhan
🌿የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
👍 1👏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
❤️ገቢሩ፦
❇️ይህ ጸሎት ፡ጧት ጧት ሰርክ ብንጸልየው መልካም ነው።
የፍርሃት፣የድንጋጤ፣የዓይነጥላ መፍትሔ ነው።
❇️ከመተት፡ከጥላወጊ፡ከዛር መንፈስ ከቁራኛም ይከላከላል።
❤️ከተቻለ ማታ ማታ በከርቤ ዕጣን እየጸለያችሁ ማታ ማታ ይታጡኑ።
✔️ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@merigeta_amedebrhan
Фото недоступнеДивитись в Telegram
❤️መፍትሔ ዘዓይነጥላ❤️
❇️አብርሃም፡በካራን፡ሀገሩ፡ተከለ፡፫ ዕፀወ፡፩ ነግሠ፡ወ፩ የብሰ፡ወ፩፡መገጸ....❇️
የተውጣጡ የዓይነጥላ እና የአጋንንት መራቅያ ጸሎቶች!
በእንተ ዓይነጥላ.doc0.35 KB
👍 2
✝ሳዶር✝አላዶር✝ዳናት✝አዴራ✝ሮዳስ✝
📖ለጸሎት እንነሳ📖
✔️የዓይነ-ጥላ መናፍስቶችን ድል እንንሳ♥
♣ዓይነ -ጥላ በሳይንሳዊ አባባል የስነልቦና ችግር ይሉታል።
#ዓይነ -ጥላ ከልጅነት ጀምሮ እስከ እውቀት ስነ ልቦናዊ፣ማሕበራዊ፣እንዲሁም አካላዊ ችግሮችን መፍጠር የሚችል በአብዛኛው ሰው የሚገኝ በሽታ ነው።
# ዓይነ-ጥላ የሚባለው ችግር በተለያዩ ሰዎች ቁራኛ ሁነው ለማሰቃየት የተዘጋጁ ፣ህይወትን የሚያጨልሙ፣ በክፉ መናፍስቶች የሚከሰት በሽታ ነው።
#ዓይነ-ጥላ የአጋንንት ሴራ እንዲሁም የክፉ መናፍስት ተንኮል ከሰው ዘንዳ ያላቸው ቅናት እና ተንኮል የሚያንጸባርቁበት እንዲሁም የምያሸማቁቅበት ክስተት ነው።
#የዓይነ ጥላ ምልክቶች፦ብዙ ጊዜ አጋንንት በቅናት መንፈስ ሰዎችን በመተናኮል በየትኛውም መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎቻችን የዘወትር ፈተናዎች የሆኑት ጥንተ ጠላቶቻችን ውግያቸው እጅግ በረቀቀ ስልታቸው ከሰዎች ዘንዳ በመላመድ የየእለት ተግባራችንን በመላመድ እንዳናስተውላቸው ወጥመዳቸውን በማጥመድ ለብዙ ፈተናዎች ይዳርጉናል።
♣ከዚህም የተነሳ የዓይነ ጥላ መናፍስቶች የሚፈጥሯቸው ችግሮች ከስር በትንሹ አስቀምጫቸዋለሁ።
#ትዳር መገርገር/ትዳር መበተን
#የበታችነት ስሜት /ጭንቀት
#ተስፋ መቁረጥ/ራስን ማጥፋት
#ብሶተኛ መሆን/መነጫነጭ
#ግለ ወሲብ/ሕልመ ለሊት መከሰት
#ብቸኝነት/ዝሙት/ሴሰኝነት
#እድል መዘጋጋት/ንብረት መውደም
#የወር አበባ ሕመም/ሾተላይ/ጽንስ ማስወረድ
#ሆድ መንፋት/ጋዝ መብዛት
#ከቤተሰብ አለመስማማት
#ማይግሬን/ራስምታት
#ፍርሐት/ድንጋጤ/መርበትበት
#የስራ ስኬት ማጣት/ብር ማባከን
#ቅዠት/ጥርስ ሟፋጨት
ጥያቄ?
በዓይነ ጥላ የተያዘ ሰው በሳሳይኮሎጂስት፣እና በሳይካትሪስት ባለሙያዎች ይድናል ወይስ አይድንም?
♣ምናልባት በዚህ ችግር ተጠቅታችሁ የተለያዩ መፍትሔዎች የሞከራችሁ እስኪ ተሞክሯችሁን በኮሜንት መስጫ ሳጥን አካፍሉን።
📖ለጸሎት እንነሳ📖
♥በስመ፡ አብ፡ ወወልድ፡ ቅዱስ፡ ፩ ፡አምላክ፡ ጸሎት፡ በእንተ፡ ዓይነ- ጥላ ፡ወዓይነ- ወርቅ ፡ሰላም፡ ለዓእይንቲከ፡ ለድንግል፡ በኩራ፡ ሳዳር፡ እለ: ርዕያ፡ በትዕግሥት፡ መሥተራትዓተ፡ ሐራ፡ አላዶር፡ ወሞዓቶሙ፡ ለቤተ፡ አይሁድ፡ ማህበራ፡ ዳናት፡ ወትርዕድ፡ እምግርማከ፡ ሶበ፡ ትኔጽር፡ አዴራ፡ አዕይንቲከ፡ ፍሡሐት፡ ሕማማተ፡ መስቀል፡ ፆራ፡ ሮዳስ፡ ክርስቶስ፡ ጻድቅ፡ ወብርሃን፡ ዘበምራቅከ፡ ከሠትከ፡ አዕይንተ፡ ዕውራን፡ ወበቃልከ፡ ይትፌወሱ፡ ዱያን፡ ዛቲ፡ ነፍስ፡ ሕምምት፡ ወጥውቅት፡ ይእቲ፡ ትርከብ፡ ፈውሰ፡ እምገቦከ ፡በከመ፡ ፈትሐ፡ ኤርምያስ፡ እንተ፡ ኮክኅ፡ ክድንት፡ ይእቲ፡ በደመና፡ሰማይ፡ ከማሃ ፡አሕልፋ፡ ወአሰስላ፡ ለሕማመ፡ ዓይነ፡ ጥላ ፡ወዓይነ ፡ወርቅ፡ ወገርጋሪ ፡ዓይነ፡ ቡዳ፡ ወቁመኛ፡ ወተያዥ፡ ሊተ፡ ለእከሌ፡(የራስ ሙሉ ስም)
እስመ ፡አልቦ፡ ነገር፡ ዘይሰአኖ፡ ለእግዚአብሔር፡ ወአልቦ ፡ዘይሰአነከ፡ ወኩሉ፡ ይትከሃለከ፡ ትሰፍሕ፡ የማነከ፡ወታጸግብ፡ ለኩሉ፡ እምበረከትከ፡ ኦ እግዚእየ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ በዝ፡ ቃለ ፡መለኮትከ፡ ዕቀበኒ ፡ወአድኅነኒ ፡እመከራ ፡ሥጋ፡ ወነፍስ፡ ሊተ፡ ለገብርከ፡ እከሌ፡
(የራስ መጠርያ ሙሉ ስም ይግባ)
✔️ወቅቱ የፆም ጊዜም እንደመሆኑ እንደ ፀበል ከምግብ በፊት ሰባት ሰባት ጊዜ በንፁህ ውኃ እየጸለዩ ይጠጡ።
ከቻሉ ማታ ማታም እየጸለዩ ይተኙ መልካም ራእይ ያያሉ።
✔️ትልቅ ጸሎት ነው አበው ይመስክሩ በምትፈልጉት አባት አስመርምሩ ፈውስ ታገኙበታልችሁ ልዩ የፈጣሪ ቅንዋተ መስቀልን እያስተዛዘለ የሚሄድ ጸሎት ነው።
#መርጌታ አምደ ብርሃን
👉አድራሻችን
አዲስ አበባ አየር ጤና ወደ ዓለም ባንክ መሄጃ በ ቤተል መገንጣያ በኩል ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ትራንስፖርት ማሰልጠኛው አጠገብ እንገኛለን
👉 ዋና መገኛ ቦታዬ ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከመናኸሪያው ወደ ሽዲ መሄጃ መስመር ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ 100 ሜትር ገባ ብሎ አገኛለሁ።
☎️#0918834904
☎️#0915310455
✔️ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@merigetaamedeberhan
✔️ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@merigeta_amedebrhan
✅ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/profile.php?id=100076378898155
✅የቴሌ ግራም ቻናላችን
https://t.me/mergeta_amdebrhan
✅የቴሌ ግራም ቻናላችን
t.me/mergeta_amdebrhane
✳️የቲክቶክ ቻናላችን
http://tiktok.com/@mergetaamdebrhan
✝️ የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
👍 4
