uk
Feedback
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

Відкрити в Telegram

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Показати більше
2025 рік у цифрахsnowflakes fon
card fon
50 494
Підписники
-624 години
+27 днів
+10030 день
Архів дописів
=>ይህቺ እናት አስቀድማ የኦርዮ ሚስት: ቀጥሎ ደግሞ የልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ሚስትና የሰሎሞን እናት ለመሆን በቅታለች:: ቁጥሯ ከደጋግ እናቶቻችን ሲሆን የድንግል ማርያም ቅድመ አያትም ናት:: አንዳንድ ሊቃውንት ደግሞ ስሟን "ቤትስባ (ቤተ ሳባ)" : ትውልዷንም ከኢትዮዽያ ያደርጉታል::=>አምላከ ኤልያስ በምልጃው ለሃገራችንና ለሕዝቧ ርሕራሔውን ይላክልን:: ከቅዱሳኑም በረከትን ይክፈለን:: =>ታሕሳስ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ኤልያስ ርዕሰ ነቢያት 2.ቅዱስ ዼጥሮስ ዘጋዛ 3.ቅድስት ቤርሳቤህ (ቤትስባ) 4.ናቡቴ ኢይዝራኤላዊ 5.አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት =>ወርኀዊ በዓላት 1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር 5.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት =>+"+ ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝኩትን: የባሪያየን የሙሴን ሕግ አስቡ:: እነሆ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላቹሃለሁ:: መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች: የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል:: +"+ (ሚል. 4:4) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
Показати все...
✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ታኅሣሥ ፩ (1) ❖ ✞✞✞✝ እንኩዋን ለታላቁ ነቢይ "ቅዱስ ኤልያስ" : "ቅዱስ ዼጥሮስ ዘጋዛ" እና "ቅድስት ቤርሳቤህ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +*" ታላቁ ቅዱስ ኤልያስ "*+ =>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ቀጥላ ቅዱስ ኤልያስን ታከብራለች:: "ርዕሰ ነቢያት - የነቢያት ራስም" ትለዋለች:: እርሱ ሰማይን የለጐመ: እሳትን ያዘነመ: ፍጥረትንም በቃሉ ያዘዘ አባት ነውና:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- +ቅዱሱ ትውልዱ (ነገዱ) ኢዮርብዓም ነጥሎ ከወሰዳቸው እሥራኤል (10ሩ ነገድ) ሲሆን አባቱ "ኢያስኑዩ" : እናቱ ደግሞ "ቶና (ቶናህ)" ይባላሉ:: በጐ አምልኮ ነበራቸውና እግዚአብሔር ማሕጸነ ቶናህን ቀድሶ ይህንን ቅዱስ ፍሬ ፈጠረ:: +ቅዱስ ኤልያስ በተወለደ ቀን በቤታቸው ብርሃን ተሞልቶ ታይቷል:: ብርሃን የለበሱ 4 ሰዎች (መላእክት) መጥተውም በእሳት ሰፋድል (መጐናጸፊያ) ሲጠቀልሉት ወላጆቹ በማየታቸው ደንግጠው ለነቢያትና ለካህናት ነገሯቸው:: +ካህናቱ ግን ነገሩ ቢረቅባቸው "ምን ዓይነት ፍጥረት ይሆን? በእሥራኤል ይነግሥ ይሆን! ወይስ ነቢይ ይሆን?" ብለውም አድንቀዋል:: ቅዱስ ኤልያስ ከልጅነቱ ጀምሮ ኮስታራ: ቁም ነገረኛ: ንጽሕናንም የሚወድ እሥራኤላዊ ነው:: +ወቅቱ (ከክርስቶስ ልደት 900 ዓመት በፊት) ሕዝቡና ነገሥታቱ የከፉበት: እግዚአብሔር ተክዶ ጣዖት የሚመለክበት ነበር:: ድሮ በኢሎፍላውያን እጅ የነበሩት ጣዖታት (ዳጐንና ቤል) በዚያ ዘመን ወደ እሥራኤል ገብተው ነበር:: +ቅዱስ ኤልያስ ግን በዚህ ክፉ ትውልድ መካከል ሆኖም ሥርዓተ ኦሪትን የጠነቀቀ: የንጽሕናና የአምልኮ ሰው ነበር:: +በዚያ ወራትም እግዚአብሔር ለነቢይነት ጠራው:: እርሱም "እሺ" ብሎ ታዞ የእግዚአብሔርን የጸጋ ጥሪ ተቀበለ:: ቅዱሱ ብዙ ጊዜ ለጉዳይ ካልሆነ ከሰው ጋር መዋል: ማደርን አይወድምና መኖሪያውን በተራሮችና በዱር አደረገ:: +በተለይ ደብረ ቀርሜሎስ ለእርሱ ቤቱ ነበር:: በዚህ ሕይወቱም ከመልከ ጼዴቅ ቀጥሎ:- 1.ለድንግልና (ድንግል ነበርና) 2.ለብሕትውና (ብቸኛ ነበርና) 3.ለምንኩስና (ተሐራሚ ነበርና) በብሉይ ኪዳን መሠረትን የጣለ ነቢይ ይባላል:: +መቼም በብሉይ ኪዳን የቅዱስ ኤልያስን: በዘመነ ክርስቶስ የመጥምቁ ዮሐንስን: በዘመነ ሊቃውንት ደግሞ የአፈ ወርቅ ዮሐንስን ያህል ደፋርና መገሥጽ አስተማሪ አልነበረም:: በጊዜው ደግሞ አክአብና ኤልዛቤል የሚባሉ ክፉ ባልና ሚስት በእሥራኤል ላይ ነግሠው ሕዝቡን ጣዖት አስመለኩት:: +ይባስ ብለው ደግሞ በወይኑ እርሻ አማካኝነት ኢይዝራኤላዊው ናቡቴን በሃሰት ምስክር ደሙን አፈሰሱት:: ናቡቴም "የአባቶቼን ርስት አልሸጥም: አልለውጥም::" በማለቱ እንደ ሰማዕት ይቆጠራል:: +ኤልያስ ግን ይህንን ሲሰማ ወደ አክአብና ኤልዛቤል ቀርቦ "የናቡቴ ደም በእናንተ ላይ አይቀርም:: የአንቺንም ደም ውሻ ይልሰዋል" አላቸው:: በዚህ ምክንያትም ኤልዛቤል ልትገድለው ብትፈልገውም እርሱ የእግዚአብሔር ነውና አላገኘችውም:: +በዚህ ብስጭትም ይመስላል አንድ ሺህ ነቢያትን ሰብስባ "ፍጇቸው" አለች:: 900ው ሲታረዱ አንድ መቶውን ግን ቅዱስ አብድዩ በዋሻ ውስጥ ደብቆ እየመገበ አተረፋቸው:: በእሥራኤል ውስጥ ግን ዓመጻና ኃጢአት እየተስፋፋ ሔደ:: የእግዚአብሔርን ስጦታ እየተመገበ ሕዝቡ ለቤል (ለበአል) ሰገደ:: +ይህን ጊዜ ግን ቅዱስ ኤልያስ እንዲህ አለ:- "ሕያው እግዚአብሔር አምላከ ኃይል: ዘቆምኩ ቅድሜሁ: ከመ ኢይረድ ጠል በእላ መዋዕል ዘእንበለ በቃለ አፉየ::" ብሎ ዝናም ከሰማይ እንዳይወርድ ከለከለ:: ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል ለመከር ከመስጠት ተከለከለ:: +ሕዝቡ በኃጢአቱ ምክንያት ተጐዳ:: እርሱን ቁራ ይመግበው: ምንጭ ፈልቆለት ይጠጣ ነበር:: ይሔው ቢቀርበት ጸለየ:: እግዚአብሔርም ከፈለገ ኮራት ወደ ሰራፕታ እንዲወርድ አዘዘው:: በዚያም የነቢዩ ዮናስ እናት እንጐቻ ጋግራ ብታበላው ቤቷ በበረከት ተሞላ:: +ልጇ ሕጻኑ ዮናስ ቢሞትም በጸሎቱ አስነሳላት:: ቀጥሎም 7 ጊዜ በትጋት ጸልዮ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት የዘጋውን ሰማይ ከፍቶታል:: ሕዝቡም ዕለቱኑ ከበረከቱ ቀምሰዋል:: +ከዚያ አስቀድሞ ግን ከኤልዛቤል 850 ነቢያተ ሐሰትና ካህናተ ጣዖት ጋር ተወዳድሮ አሸንፏቸዋል:: መስዋዕት ሰውተው የእርሱን ብቻ እሳት ከሰማይ ወርዳ በልታለታለችና ሕዝቡ 850ውን ሐሰተኛ ነቢያት በወንዝ ዳር በሰይፍ መትተዋቸዋል:: +ይሕንን የሰማች ኤልዛቤልም ትገድለው ዘንድ አሳደደችው:: "አቤቱ ከአባቶቼ አልበልጥምና ውሰደኝ! ብቻየን ቀርቻለሁና" ብሎ ቢጸልይ እግዚአብሔር ለጣዖት ያልሰገዱ ሰባት ሺህ ሰዎችን እንዳተረፈ: እርሱንም ወደ ብሔረ ሕያዋን እንደሚወስደው ብሥራትን ነገረው:: +ደክሞት ተኝቶ ሳለም ቅዱስ መልአክ (ሚካኤል) ቀስቅሶ ታየው:: እንጐቻ ባገልግል: ውሃ በመንቀል አቅርቦ "ብላ! ጠጣ!" አለው:: በላ: ጠጣ: ተኛ:: እንደ ገና ቀስቅሶ አበላው:: በ3ኛው ግን "ብላዕ እስከ ትጸግብ እስመ ርሑቅ ፍኖትከ - ጐዳናህ ሩቅ ነውና እስክትጠግብ ብላ" አለው:: +ኤልያስም ለ40 ቀናት ያለ ምግብ ተጉዟል:: ከዚያ በሁዋላም ምድራዊ ሕብስትን አልተመገበም:: እግዚአብሔር አክአብና ኤልዛቤልን ከተበቀላቸው በሁዋላም ቅዱስ ኤልያስ በክፋተኞች ላይ 2 ጊዜ እሳትን አዝንሟል:: +የሚያርግበት ጊዜ ሲደርስም ደቀ መዝሙሩን ኤልሳዕን "የምትሻውን ለምነኝ" ቢለው "እጥፍ መንፈስህን" አለው:: 3 ጊዜ ሊያስመልሰው ሞከረ:: ቅዱስ ኤልሳዕ ግን በብርታት ተከተለው:: ዮርዳኖስን ከፍለው ከተሻገሩ በሁዋላ ግን ቅዱስ ኤልያስን ሠረገላ እሳት ወርዶ ነጠቀው:: ለኤልሳዕም እኩሉን ግምጃውን ጣለለት:: +ዛሬ ቅዱስ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን ያለ ሲሆን በዘመነ ሐሳዌ መሲሕ መጥቶ በሰማዕትነት ከቅዱስ ሔኖክ ጋር ያርፋል:: (ራዕይ) ¤ለተጨማሪ ንባብ ( ከ1ነገ. 17-2ነገ. 2, እና ዕርገተ ኤልያስን ያንብቡ::) <<ነቢዩ ኤልያስ በእውነት ታላቅ ነው!>> +"+ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘጋዛ +"+ =>ይህ ቅዱስ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በታናሽ እስያ አካባቢ የተወለደ ሲሆን የክቡራኑ የመሣፍንት ልጅ ነው:: በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድጐ የቁስጥንጥንያ ንጉሥ ትንሹ ቴዎዶስዮስ ወደ ቤተ መንግስቱ ወሰደው:: +በዚያም "አገረ ገዥ ላድርግህ" ብሎ ቢጠይቀው "ትንሽ ቆየኝማ" ብሎት ጠፍቶ በርሃ ገብቶ መነኮሰ:: ቅዱስ ዼጥሮስ በምንኩስና ሲጋደል: ካለበት በርሃ መጥተው በግድ ወስደው: የጋዛ (አሁን የፍልስጤምና እሥራኤል ደንበር) ዻዻስ አደረጉት:: +ከደግነቱ የተነሳም በቅዳሴ ጊዜ ሥጋ ወደሙ ሲለወጥ ያየው ነበር:: መላእክትም ያጫውቱት ነበር:: ሕዝቡ ሲያጠፉ በየዋሕነት ዝም ቢላቸውም ቅዱስ መልአክ ገሥጾታል:: +የፋርስ ነገሥታት አጽመ ሰማዕታትን ሲያቃጥሉም እርሱ የቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድን አጽም ይዞ ተሰዷል:: ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑሮም በዚህች ቀን ዐርፏል:: +"+ ቅድስት ቤርሳቤህ +"+
Показати все...
✝እንኳን አደረሰነ! ✞ ✝በዓለ ቅዱሳን፦ ✿አካክዮስ ሊቀ ጳጳሳት ✿አናንዮስ ዘዓምድ ✿መርቆሬዎስ ሰማዕት ✿ጴጥሮስ መነኮስ ✿ገብረ መስቀል ንጉሥ ✿ቆዝሞስ ወድምያኖስ ✿ቴዎዳዳ ወውሉዳ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ በረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡ https://t.me/zikirekdusn
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አንበሶቹን ቀስቅሷቸው !!! ነጣቂ ተኩላ ሲፈልግ ለምድ ለብሶ . . . ሲያሻውም በተገላጭ በጎችን ወሰደብን !! አንበሶቹ (ሊቃውንት) ምነው ዝም አላችሁ ?? አይታያችሁም በእናንተ ቦታ ሌላ ተተክቶ መንጋው ሲቅበዘበዝ !! ምነው የመንጋው በጎችስ እውነተኛ እረኞችን ማወቅ ተሳነን ?? (ዮሐ. 10, 21:15) ድምጽ ማጉያና ብዕር ለጨበጠ ሁሉስ እስከ መቼ እናረግዳለን ?? ከእውነተኞቹ እረኞች ድምጽስ እስከ መቼ እንርቃለን ?? ኧረ ለእረኛው አቤት እንበል !! ምናለ የተኙ : ዝምታን የመረጡትን : በየቤተ ጉባኤው የተወሰኑትን : ሰሚ ጀሮ ያጡትን : ተገፍተው በየመቃብር ቤቱ የወደቁትን አናብስት ብናስነሳቸው !! { ሲመስለኝ ለተኩላዎቹ መድኃኒቶቹ አንበሶቹ ናቸውና ወደ አናብስቱ እንጠጋ! } ኅዳር ፴ - ፳፻፰/2008 ዓ/ም https://t.me/zikirekdusn
Показати все...
✞✞✞”The king shall joy in thy strength, O Lord; and in thy salvation how greatly shall he rejoice! Thou hast given him his heart's desire, and hast not withholden the request of his lips. Selah. For thou preventest him with the blessings of goodness: thou settest a crown of pure gold on his head. He asked life of thee, and thou gavest it him, even length of days for ever and ever. His glory is great in thy salvation”✞✞✞ Ps. 20(21):1-5 ✞✞✞ Salutations to God ✞✞✞ (Translated by Mhr. Esuendale Shemeles with the permission of Dn. Yordanos Abebe)
Показати все...
And when both awakened from their contemplation/trance in the hymn, the King was shocked and asked, “How should I recompense you?” and the Saint answered, “Let me go to the desert.” ✞Thence, Emperor Gebre Meskel in grief gave him permission. And St. Yared on the other hand, raised a cubits length and suspended in the air, praised with the “Anqetse Brihan – Gate of Light” in a pleasant melody as a farewell singing, “Veneration and homage to the Mother of the Lord, holy and blessed . . .” And the Emperor who heard this wept. ✞He then accompanied him on the road with the people and his soldiers. Thereafter, when St. Yared reached Tselemt he sang loudly, “Peace be with you”. And when Emperor Gebre Meskel and the people replied, “And with your spirit” and looked up, the Saint disappeared from their eyes. The Emperor in his day labored for the expansion of the Heavenly Chant [of St. Yared].  ✞✞✞The Emperor and the Nine Saints✞✞✞ ✞Emperor Gebre Meskel had also labored much so that the Nine Saints could preach in our country, translate books, and expand monasticism. ✞Particularly, he had close relations with Abba Pentelewon and Abba Liqanos of Debre Qonatsle. And he daily used to take their blessings. And it is said that he used to visit Abune Aregawi time and time again. ✞✞✞The Emperor and the Ark✞✞✞ ✞Like the Holy Cross, it is said that this was the Emperor who had the Ark of God be glorified with a procession that went around the church. And it started because of the construction of Debre Damo. One day, when the Emperor asked Abune Aregawi for his wish, the Saint answered, “Build for me the Church of our Lady Saint Mary”.   ✞Thence, in jubilation, he built the church. And on the day of the consecration, the Emperor, the Saint, and the Scholar (that is Gebre Meskel, Aregawi and Yared respectively) were present with other saints. And at the time, while the Ark (Altar-Board) was glorified as St. Yared sang and the fathers chanted, the Ark went around the church in a procession and there took place a great elation.   ✞And during that time, Debre Damo had a ladder. And when the Emperor and St. Yared returned [to Axum], by the request of Abune Aregawi, it was demolished. ✞And because the Saint said, “Dahmemo (Demolish it)” the plateau has since been called Dahemo (Damo). The Righteous Emperor Gebre Meskel after building many churches departed on this day and was entombed. ✞✞✞Saint Acacius the Patriarch of Constantinople✞✞✞ =>This Saint was one of the holy scholars that rose in the 5th century. He was born and raised in Constantinople, where he was educated in the teachings of the faith as well. And in 451 A.D, during the Council of Chalcedon (The Council of the Indolent), he was also called to attend. ✞However, because he knew the scheme that was weaved by the Emperor, Marcian, and the Bishop, Leo, he did not go. And when he heard that when the Council concluded St. Dioscorus was killed and the Faith was renounced [by those that gathered], he was grieved. ✞And after cursing the Emperor, he said, “O Lord! I praise You Who have not involved me in such an accursed Council.” And a few years later, the faithful discerning that he was a good shepherd of an upright faith appointed him as the Patriarch of the Great City of Constantinople. ✞And he wrote many works. However, an order from the leaders came to him to renounce his Miaphysite Faith. And because he rejected the notion, he was sentenced to exile and there in exile he departed. ✞✞✞May the God of the Righteous Emperors grant us kind leaders in all the places. And may He not separate us from the blessings of His beloved. ✞✞✞ Annual feasts celebrated on the 30th of Hedar 1. Emperor Gebre Meskel the Righteous (Emperor of Ethiopia) 2. Saint Acacius the Scholar (Patriarch of Constantinople) 3. Saints Cosmas and Damian 4. Saint Anianus of the Stylite 5. Abba Mercurius the Martyr✞✞✞ Monthly Feasts 1. St. Mark the Apostle 2. Abba Salusi the Honorable 3. St. Gregory the Theologian 4. St. Sophia the Martyr 5. St. John the Baptist
Показати все...
#Feasts of #Hedar_30 ✞✞✞On this day we commemorate the Departure of Emperor Gebre Meskel and Saint Acacius the Patriarch of Constantinople✞✞✞ ✞✞✞In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, one God. Amen!✞✞✞ ✞✞✞The Righteous Emperor Gebre Meskel✞✞✞ ✞✞✞The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is gifted in many aspects. And of these gifts, unlike anywhere else, She is endowed with more than a dozen Holy Emperors. It is very important for one country to have leaders that are good Christians.  ✞And when we see the spiritual weariness and moral degradation of the past 40 years, we notice that one of the problems is due to our leaders. However, when we see the history of our country, we find many Emperors that submitted to God in the midst of fire and war. ✞✞✞And as examples we find 1. Queen Saba/Sheba 2. Menelik I 3. Abreha and Atsbeha 4. Kaleb 5. Gebre Meskel 6. Harbe 7. Lalibela 8. Yemreha 9. Neakuto Leab 10. Dawit 11. Tewodros I 12. Zara Yaqob 13. Bede Maryam 14. Naod 15. Lebne Dengel 16. Gelawdios 17. Yohannes 18. Iyasu I 19. And Tekle Haymanot the abdicator of the throne. ✞And from these monarchs while some left their throne and entered the desert as ascetics, others were good doers while on their throne. And some admitted their wrong doings and were repentant.  ✞Amongst the righteous rulers, today is the commemoration date of Emperor Gebre Meskel. The Saintly Emperor was the son of Emperor Kaleb (Saint Elesbaan) and he reigned starting from 515 E.C. He was young when he was crowned. And the reason for it was because he was the son that was seated on the throne after his father Kaleb had abdicated the throne and became an ascetic after the battle of Najran. ✞What we admire about this Saint is first his name. It shows that 1,500 years ago there were leaders to whom the Cross was pride and who venerated It (submitted to It) indicating the status of Christianity during that era as Gebre Meskel means “Servant of the Cross”. ✞It seems that the identity of his righteous father helped Emperor Gebre Meskel to be a good King. He was like his powerful and strong father who was feared by the world because he saw firstly his father captivated by the love for Christ and the love for His Virgin Mother and secondly, because he saw him leave his throne like a piece of cloth without any preconditions. ✞And as he had seen from his father, in the years he reigned the Empire of Axum, he tried to live in prayer and fasting, judging in fairness and with legitimacy, and without chastising the poor. ✞✞✞ Atse Mesqel (Teqesel Tsege)✞✞✞ ✞✞✞One of the tenets that this Righteous Emperor left for us and that takes precedence is celebrating the Feast of the Cross in a public arena. The Feast is celebrated around [the month of] Meskerem/end of September/  and is called “Atse Mesqel”. ✞[And on the feast day] the people, the priests and the nobles with bouquets of “Adey Abeba” (a yellowish flower of the season native to Ethiopia) go to the Emperor’s Square. There, by the hymnal notes of St. Yared celebrate a great feast for the Holy Cross. And this Feast is now registered by UNESCO. ✞✞✞The Emperor and Saint Yared✞✞✞ ✞Our country also received the great heavenly hymn during the reign of this Emperor, Gebre Meskel. And St. Yared who received this heavenly chant, when he sang: “Halelujah! Before Zion He created heaven then He showed Moses the workings of the Tabernacle” in Araray from the three tones at Axum Zion for the first time; the Emperor taken by the melody run to and reached [the Church of] Zion. ✞And all [the inhabitants] were astounded by the tang of the melody of the chant. And the Emperor from that day onwards was unable to separate himself from St. Yared. And he partook, for many days, from the Praise of God by St. Yared who organized it with a delightful melody.✞In fact at one time, while St. Yared chanted for the Righteous Emperor, Gebre Meskel, the monarch pierced the leg of the Scholar with his royal staff.
Показати все...
=>አምላከ ነገሥት ጻድቃን ቅኑን መሪ በሁሉም ሥፍራ ያድለን::ከወዳጆቹ በረከትም አይለየን::=>ኅዳር 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አፄ ገብረ መስቀል ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ) 2.ቅዱስ አካክዮስ ሊቅ 3.ቅዱሳን ቆዝሞስ ወድምያኖስ 4.ቅዱስ አናንዮስ ዘዓምድ 5.አባ መርቆሬዎስ ሰማዕት ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ) 2.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት 3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 4.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ++"+ አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል:: በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል::የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው::የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም::በበጐ በረከት ደርሰህለታልና::ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ::ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም::ለረጅም ዘመን ለዘለዓለሙ::በማዳንህ ክብሩ ታላቅነው:: +"+ (መዝ. 20:1-5) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Показати все...
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ✞✞✞ እንኩዋን ለጻድቅ ንጉሥ "አፄ ገብረ መስቀል" እና "ቅዱስ አካክዮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችህ ✞✞✞ " ኅዳር 30 " +"+ ጻድቅ አፄ ገብረ መስቀል +"+ =>የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በብዙ ነገሮቿ የታደለች ናት:: ከእነዚህም መካከል በዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መንገድ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ነገሥቶቿ (መሪዎቿ) ቅዱሳን (ጻደቃን) ናቸው:: ለአንዲት ሃገር የመሪዎቿ ጥሩ ክርስቲያን መሆን እጅግ ወሳኝ ነው:: +ባለፉት 40 ዓመታት እንኩዋ የደረሰብንን የመንፈስ ዝለትና የሞራል ዝቅጠት ስንመለከት አንድም ችግሩ ከመሪዎቻችን እንደ ሆነ እናስተውላለን:: የሃገራችንን ታሪክ ስንመለከት ግን በእሳትና በጦርነት መካከል ሆነው ለፈጣሪ የተገዙ ብዙ ነገሥታትን እናገኛለን:: +እንደ ምሳሌም:- 1.ንግሥተ ሳባ 2.ቀዳማዊ ምኒልክ 3.አብርሐ ወአጽብሐ 4.ካሌብ 5.ገብረ መስቀል 6.ሐርቤ 7.ላሊበላ 8.ይምርሐ 9.ነአኩቶ ለአብ 10.ዳዊት 11.ቴዎድሮስ ቀዳማዊ 12.ዘርዓ ያዕቆብ 13.በእደ ማርያም 14.ናዖድ 15.ልብነ ድንግል 16.ገላውዴዎስ 17.ዮሐንስ 18.ኢያሱ ቀዳማዊና 19.ተክለ ሃይማኖት መናኔ መንግሥትን እናገኛለን:: +ከእነዚህ መሪዎቻችን መካከል እኩሉ መንግስታቸውን ትተው በርሃ የገቡ ሲሆኑ እኩሉ ደግሞ በዙፋናቸው ላይ ሳሉ በጐ ሠርተው የተገኙ ናቸው:: አንዳንዶቹ ደግሞ በጥፋታቸው ተጸጽተው ንስሃ የገቡ ናቸው:: +ከነገሥት ጻድቃን መካከልም ይህች ዕለት የአፄ ገብረ መስቀል መታሰቢያ ናት:: ጻድቁ ንጉሥ የአፄ ቅዱስ ካሌብ ልጅ ሲሆን በኢትዮዽያ የነገሠው በ515 ዓ/ም ነው:: ሲነግሥም እጅግ ወጣት ነበረ:: ምክንያቱም አባቱ ካሌብ ከናግራን ጦርነት መልስ በመመነኑ በዙፋኑ የተቀመጠ ልጁ እርሱ ነበርና:: +ከዚህ ቅዱስ የመጀመሪያ የምናደንቀው ስሙን ነው:: የዛሬ 1,500 ዓመት እንኩዋ በመስቀል የሚመኩ: ለመስቀል የሚገዙ መሪዎች መኖራቸው በዘመኑ የነበረውን የክርስትና ደረጃ ያሳያል:: "ገብረ መስቀል" ማለት "የመስቀል አገልጋይ (ባሪያ)" ማለት ነውና:: +አፄ ገብረ መስቀል በጐ ንጉሥ እንዲሆን የቅዱስ አባቱ ማንነት የረዳው ይመስላል:: ያ ኃያል: ብርቱና ዓለም የፈራው አባቱ ሲጀመር በፍቅረ ክርስቶስና በድንግል እናቱ ፍቅር የተያዘ ደግ ሰው መሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መንግስቱን እንደ ጨርቅ ትቶ ሲሔድ መመልከቱ እርሱንም ያው አድርጐታል:: +እርሱም ከአባቱ እንዳየው በአክሱም ላይ በነገሠባቸው ዓመታት በጾምና በጸሎት: ፍትሕ ርትዕ ሳደያጉዋድል: ድሃም ሳይበድል ይኖር ዘንድ ጥረት አድርጉዋል:: +"+ አፄ መስቀል +"+ =>ይህ ጻድቅ ንጉሥ ለእኛ ከተወልን ትሩፋቶቹ አንዱ በዓለ መስቀልን በአደባባይ ማስከበሩ ቅድሚያውን ይይዛል:: በዓሉ መስከረም አካባቢ የሚደረግ ሲሆን "አፄ መስቀል" ይባላል:: +ሕዝቡ: ካህናቱና መሳሣፍንቱ አድዬ አበባ እየዘነጠፉ ወደ ንጉሡ አደባባይ ይተማሉ:: በዚያም በያሬድ ዝማሬ ለቅዱስ መስቀሉ ታላቅ በዓል ይከበራል:: ይህ በዓል ይኼው ዛሬ በUNESCO ተመዝግቧል:: +"+ ንጉሡና ቅዱስ ያሬድ +"+ =>ሃገራችን ታላቁን ሰማያዊ ዜማ ያገኘችው በአፄ ገብረ መስቀል ዘመን ነው:: ቅዱስ ያሬድ ከሰማይ ያገኘውን ማኅሌት ለመጀመሪያ ጊዜ በአክሱም ጽዮን:- "ሃሌ ሉያ . . .! ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ:: ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ::" ብሎ ከ3ቱ ጸዋትወ ዜማ በአንዱ በአራራይ ሲያዜም ንጉሡ በዜማው ተመስጦ እየሮጠ ወደ ጽዮን ደርሷል:: +ከዜማው ጥፍጥና (ጣዕም) የተነሳ ሁሉም ተደመሙ:: ንጉሡም ከዚያች ቀን ጀምሮ ከቅዱስ ያሬድ የማይለይ ሆነ:: ስብሐተ እግዚአብሔርንም ለብዙ ጊዜ ከቅዱሱ ሊቅ በጥዑም ዜማ ተቀምሞለት ተመገበ:: +እንዲያውም አንዴ ሊቁ ሲያዜምለት ጻድቁ አፄ ገብረ መስቀል የቅዱስ ያሬድ እግር ላይ በትረ መንግስቱን ተክሎበታል:: ሁለቱም ከተመስጧቸው ሲነቁ ግን ንጉሡ ደንግጦ "ምን ልካስህ?" ቢለው "ወደ በርሃ አሰናብተኝ" አለው:: +አፄ ገብረ መርስቀልም እያዘነ ፈቅዶለታል:: ቅዱስ ያሬድም ከመሬት ክንድ ከፍ ብሎ ተንሳፎ: የመሰናበቻ ምስጋናን:- "ውዳሴ ወግናይ: ለእመ አዶናይ: ቅድስት ወብጽዕት . . ." ብሎ አንቀጸ ብርሃንን: በሚጣፍጥ ዜማ ሰተት አድርጐ አደረሰ:: ይህንን ሲሰማ ንጉሡ ፈጽሞ አለቀሰ:: +እስከ መንገድ ድረስ ከሕዝቡና ሠራዊቱ ጋር ከሸኘው በሁዋላም ቅዱስ ያሬድ ጸለምት ላይ ሲደርስ በዜማ አሰምቶ "ሰላም ለኩልክሙ" አለ:: አፄ ገብረ መስቀልና ሕዝቡም "ምስለ መንፈስከ" ብለውት ቀና ሲሉ ከዓይናቸው ተሰወረ:: ንጉሡም በዘመኑ ማኅሌተ ሰማይ እንዲስፋፋ ብዙ ጥሯል:: +"+ ንጉሡና 9ኙ ቅዱሳን +"+ =>ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ወንጌልን እንዲሰብኩ: መጻሕፍትን እንዲተረጉሙና ገዳማዊ ሕይወትን እንዲያስፋፉ አፄ ገብረ መስቀል ትልቅ ጥረት አድርጉዋል:: +በተለይ ከአባ ዸንጠሌዎንና አባ ሊቃኖስ ዘደብረ ቆናጽል ጋር ልዩ ቅርበት ነበረው:: ዘወትርም ከእነርሱ ይባረክ ነበር:: አቡነ አረጋዊንም በየጊዜው ይጐበኛቸው እንደ ነበር ይነገራል:: +"+ ንጉሡና ታቦት +"+ =>ልክ እንደ ቅዱስ መስቀሉ ሁሉ ታቦተ እግዚአብሔር በዑደት እንዲከበር ያደረገ ይህ ንጉሥ ነው ይባላል:: መነሻው ደግሞ የደብረ ዳሕሞ መታነጽ ነው:: አንድ ቀን አቡነ አረጋዊን ምን እንደሚሹ ቢጠይቃቸው "የድንግል እመቤታችን ማርያምን መቅደስ አንጽልኝ" አሉት:: +በደስታ አንቆጥቁጦ አነጻት:: የምርቃቱ ዕለትም ንጉሡ: ጻድቁና ሊቁ (ማለትም ገብረ መስቀል: አረጋዊና ያሬድ) ከሌሎች ቅዱሳን ጋር ተገኙ:: በጊዜውም ታቦቱ ሲነግሥ ቅዱስ ያሬድ ባቀረበው ማኅሌታዊ ዜማና አበው ባደረጉት ዝማሬ: ታቦቱ እየዞረ ታላቅ መንፈሳዊ ሐሴት ሆነ:: +ደብረ ዳሞ ያኔ መወጣጫ ደረጃ ነበረው:: ንጉሡና ቅዱስ ያሬድ ከበዓል ሲመለሱ በአቡነ አረጋዊ ጥያቄ መወጣጫው ተደርምሷል:: +ጻድቁ "ዳሕምሞ (ደርምሰው)" ስላሉት ቦታው ዳሕሞ (ዳሞ) ተብሎ ቀርቷል:: ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጾ በዚህች ቀን ዐርፎ ተቀብሯል:: +"+ ቅዱስ አካክዮስ +"+ =>ይህ ቅዱስ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ከተነሱ ቅዱሳን ሊቃውንት አንዱ ነው:: ተወልዶ ያደገው በቁስጥንጥንያ ሲሆን ትምሕርተ ሃይማኖትንም እዚያው ተምሯል:: በ451 ዓ/ም ጉባኤ ኬልቄዶን (ጉባኤ አብዳን) ሲጠራ እሱም ጥሪ ደርሶት ነበር:: +ነገር ግን ከመጀመሪያው ንጉሡ መርቅያንና ዻዻሱ ልዮን የተበተቡትን ሴራ ያውቅ ነበርና ሳይሔድ ቀረ:: ጉባኤው ተጠናቆ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ መገደሉንና ሃይማኖት መካዱን (በተሰብሳቢዎቹ) ሲሰማ አዘነ:: +ንጉሡን ረግሞ "ጌታ ሆይ! ከዚህ ከረከሰ ጉባኤ ያልደመርከኝ ተመስገን" አለ:: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላም ምዕመናን ሃይማኖቱ የቀና መልካም እረኛ መሆኑን ሲረዱ የታላቂቱ ቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: +ብዙ ድርሳናትንም ደረሰ:: ወዲያው ግን ከመሪዎች ተዋሕዶን እንዲተው ትዕዛዝ መጣለት:: እንቢ በማለቱም ስደት ተፈርዶበት በስደት ላይ ሳለ ዐርፏል::
Показати все...