uk
Feedback
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

Відкрити в Telegram

| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና | የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል! የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ "የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው " https://www.youtube.com/user/TheNahusenai Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc

Показати більше
2025 рік у цифрахsnowflakes fon
card fon
10 762
Підписники
-424 години
-527 днів
-15730 день
Архів дописів
✍️ የዚህ ድንቅ መምህር የህይወት ታሪክ በአጭሩ እንዲህ ፅፌዋለሁ፣የምር ግን አንድ 5 ፊልም ይወጣዋል 😲 👉 አባቴ ጥበቃ እየሰራ፣ጫማውን እየሰጠ ነው ያስተማረኝ፣8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ሳልፍ በጣም ደስ ብሎት አልጋ ላይ መተኛት ያለበት እሱ ነው ብሎ ከእናቴ ጋር መሬት እየተኙ እኔ አልጋ ላይ እተኛ ነበር። 👉 ዩንቨርስቲ ስገባ ነበር መበላሸት የጀመርኩት፣የመጀመሪያ አመት ጥሩ ውጤት ነበረኝ፣ሁለተኛ አመት ግን ከትምህርቱ ሱሱ ቀደመና ክላስም መግባት ተውኩኝ፣መማር አቃተኝ ከዛም ከዩንቨርሲቲው ተባረርኩ። 👉አባቴ ይሄን አያውቅም ህንድ ሀገር የጀመርኩት ፕሮሰስ ነበር ለሱ ስሮጥ ለዩንቨርሲቲ ዊዝድሮው ሞልቼ ነው ብየ ዋሸሁት፣በዚህ አላበቃም የህንዱም ፕሮሰስ እንደተበላሸ ዋሸሁት 👉 በጣም ስለሚያምነኝ ያሰብከው አይቀርም ብሎ ያለውን ዕቃ ሸጦ ቻይና ላከኝ 👉ቻይናም ሄጄ ሱሱ አላቆመም፣ ቀጠለ እዛም በሱስ ምክንያት ከአመት በኋላ ተባረርኩ፣ ኢትዮጵያ መጥቼ ለ2ኛ ጊዜ አባቴን ዋሸሁት፣እርሱም ለ2ኛ ጊዜ የቤት እቃውን ሸጦ ድጋሚ ላከኝ🤔 👉 በዚህ ዙር ተለውጬ አባቴን ለመካስ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር የሄድኩ፣ነገር ግን በሱስ ተተብትቤ ስለነበር አሁንም አልተሳካም 1 አመት ሙሉ ክላስ ሳልገባ ሱሱን ሳካሂድ ቆየሁ፣ ለ3ኛ ጊዜ ከዩንቨርሲቲ ተባረርኩ፣ለአባቴ ሳልናገር ተመልሼ መጣሁ፣አዲስ አበባ አልጋ ይዤ የነበረኝ ገንዘብ እስከሚያልቅ ቆየሁ፣ሱሱም ቀጥሎ ነበር 👉የነበረኝ ብር አለቀ፣በስተመጨረሻም ጎዳና ወጥቼ መኖር ጀመርኩ፣አባቴ ግን ቻይና እንዳለሁ ነበር የሚያውቀው 👉እናም ጎዳና ላይ ብዙ ጊዜያቶች አሳለፍኩ የረሀብና የጥማት ጊዜያቶች፣ለመተኛት ከ22 የካአባዶ ጫካ እሄድ ነበር፣ለሊት እቀመጣለሀ፣ቀን ነበር የምተኛው በጣም ከባድ ጊዜ ስለነበር 👉 አንድ ቀን ጎዳና ላይ ቁጭ ብዬ የሚያውቁኝ ልጆች በአጠገቤ ሲያልፉ አየሁ እነሱ በጣም ተጎሳቁየ ስለነበር አለዩኝም ነበር ግን ድንገት የሚያውቀኝ ሰው አይቶኝ ለአባቴ እንዳይናገር ፈርቼ ለምኜ ወደ ደብረዘይት ሄድኩ። 👉 እዛም መነሀሪያ አካባቢ የሚያድሩ ልጆች ጋር ጎዳና መኖር ጀመርኩ፣ከዛም የህይወቴን ከባዱን የመራብና የመጠማት ጊዜ አሳለፍኩ 👉 ከዛም ልሞት ስለመሰለኝ፣ከሞትኩም በቃ የሚያውቀኝ ሰው እንዲያገኘኝ አዲስ አበባ ሄጄ ልሙት ብየ ወደ አዲስ አበባ መንገድ ጀመርኩ 👉 እኔ ደክሞኝ ተስፋ ቆርጬ በጨረስኩ ሰዓት እግዚአብሔር ጀመረ፣ የተሳፈርኩበት ሚኒባስ ውስጥ ታሪኬ እንዲቀየር ምክንያት የሆነችዋን ሴት አገኘሁ....................ይቀጥላል ።©የእውነትመንገድ @psychoet
Показати все...
👍 39 9
👍 1
#3ቱ_የትኩረት_መንገዶች ተግባራቶችን እየቀያየሩ አንዴ እዚህ፣ አንዴ እዛ ከሚል በውጥረት የተሞላ የአእምሮ ሁኔታ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ቀጣዩን ተግባርህን በጥንቃቄ ምረጥ፤ #1_እጅህ_ላይ_ባለው_ስራ_ላይ_አተኩር ሌላውን ነገር ሁሉ ወዲያ በል እና በእጅህ የያዝከው ስራ ላይ ብቻ ትኩረትህን አድርገህ ስራ፡፡ በእጅህ የያዝከውን ስራ በጥድፊያ ጨርሰህ ወደሚጠብቅህ ቀጣይ ስራ መሄድ እንዳለብህ ከሚያሳስብህ ስሜት ውስጥ ወጥተህ በእጅህ ባለው ስራ ላይ ብቻ ተመሰጥ፡፡ ሁልጊዜም ቀጣይ የሚሰራ ስራ ይኖራል፤ ምክንያቱም የስራ ዝርዝሮች ባህሪያቸው እንዲህ ነው፣ ማብቂያ የላቸውም፡፡ #2_በኋላ_የሚሰሩትን_ስራዎች_ለበኋላ_አቆያቸው፡፡ ይህ መላው ዓለምህ እንደሆነ ቆጥረህ መቶ ፐርሰንት ትኩረትህን በእጅህ ላይ ባለው ስራ ላይ በማድረግ እርሱን ስራ፡፡  #3_አሁኑ_ቅጽበት_ላይ_ሁን። ሙሉ በሙሉ አትኩሮትህን አንድ ጊዜ አንድ ተግባርን መፈጸም ላይ አድርግ፡፡ #ቁም_ነገሩ - ዝግ በል፡፡ ተንፍስ፡፡ ተነሳሽነትህንና ግቦችህን ገምግም፡፡ መቅደም ያለበትን ነገር አስቀድም፡፡ አንድ ጊዜ አንድ ተግባርን ብቻ ፈጽም፡፡ አሁን ጀምር፡፡ በየሰዓቱ የ5 ደቂቃ እረፍት አድርግ፡፡ እንደገና ደጋግመው፡፡ (እናም አስታውስ፤ ውጤት ውጤቱን ለማምጣት ከሚወስደውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ነው፡፡) 📗📒📕 © ድሬ አስተማሪ መልእክቶችን፣  ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።
Показати все...
👍 21 2
116. ዝቅ ብሎ የሠራ ከፍ ብሎ ይኖራ 117. የሰነፍ አእምሮ የሰይጣን ቤተ_ሙከራ ነዉ 118. ለስራ ያልታደለ አእምሮ ለተንኮል ማንም አይወዳደረዉም 119. የሴት ልጅ ውበቷ ታማኝኀቷ 120. ከማይረባ ጉልበት ይሸለል ልብ አርጉልኝ ማለት 121. መኖር ደጉ ብር ባያስቆጥረን ቀን ያስቆጥረናል 122. የእናት ሞትና የድንጋይ መቀመጫ እያደር ይቆሮቁራል 123. "ቀስ ብሎ ማደግን ሳይሆን ቁሞመቅረትን ፍራ"አለች ባጃጅ!!! 124. አራዳ እናቱን ሚረዳ 125. ሞላ የሰው ስም ነዉ ተጠጉ 126. አፍ ከመክፈት ሱቅ መክፈት 127. ውፍረትና ውሸት ለባለቤቱ አይታወቅም 128. ለላዳና ለካፌ ብዙብዙ ይከፍላሉ ምነው እኛጋ ሲመጡ ለምን ይጨቃጨቃሉ 129. አንበሳ ሲያረጅ ቢሾፍቱ መጣ 130. ያለ ምክንያት መኖር ክልክል ነዉ 131. ታክሲና መግስተ ሰማያት ሞልቶ አያውቅም 132. ሲሰሩ አትስራና አዞሩብኝ በል ስትዞር ዋልና 133. በጎ አሳቢ ከስድብ ምክር ያወጣል 134. ዝምታዬ ካልገባችሁ ንግግሬ አይገባችሁም 135. ተጠጉ ሲባሉ ቦታ የለም አይበሉ፣ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነዉ 136. ጥይትንና ድህነትን ተኝቶ ነዉ ማለፍ 137. ጠጋ ጠጋ በሉ የቻይና እዳ አለብን 138. መቆጨት የለብክ በማፍቀርክ ሳይሆን ማፍቀር ያለብክን ሠው ባለማወቅክ ነው 139. ጠንካራ ሠው በጨለማ በስተጀርባ ብርሀን ይታየዋል 140. ሣያሥቡ መናገር ሣያልሙ መተኮስ ነው 141. ጓደኞችህ አካውንት ይከፍታሉአንተ አፍህን ትከፍት አለህ 142. ከምታማኝ ምከረኝ 143. በፍየል ዘመን በግ አትሁን 144. ድንች ቢውፍር ሹካ ያነሳዋል 145. ያሳደግናት ውርንጫ መልሳ በእርግጫ 146. አመል ከሌለሽ ወደ ባስሽ። 147. ወረድ ወረድ ይህ ታክሲ እንጂ ፌስቡክ አይደለም 148. እዉነት የሚያዳምጥ እዉነት ከሚናገር አይተናነስም 149. መማሩንስ ተምረሃል ማስተዋልን ዘንግተሃል 150. ያለፈለት ሀብታም ደሀን አይጋብዝም 151. ፍቅር ማለት የምትወዳትን ልጂ ደስታ ማገኘት ማለት ነዉ 152. መኖርህ ማንንም ካልጠቀመ መሞትህ ማንንም አይጎዳም 153. ወረኛ ገንፎ አድሮም ላቃጥል ይላል 154. ማቀድ ካልቻክ ዉድቀትህን እያቀድክነዉ 155. ያህያ ውርንጫ ጠጉሮ ጉፍፍ ያለው 156. የምንወደውን ስንከተል የምወደንን እናጣለን 157. ማስቲካ የሚታደል መስሎቹ አፋቹን አትክፈቱ 158. ይህችም እንጀራ ሆና ምጥምጣ በዝብት 159. ትችትና ሻወር ከራስ ይጀምራል 160. አራዳ እና ጭስ መውጫ አያጣም 161. ፋራ ከሚስመኝ አራዳ ይንከሰኝ 162. የምግብ ቅመሙ ረሀብ ነዉ 163. ፍቅር ካለ ፍሪጅ ይሞቃል 164. ባጎረስኩ ተነከስኩ 165. ወሬ ዳቦ አይሆንም 166. ዘሎ የወረደ ዋጋው ይቀንሳል 167. ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች አትግቡ ጋቢና ሹፈሩ ላደጋ ይጋለጣልና 168. ብድር መጠየቅና እንግሊዝኛ መናገር ድፍረት ይጠይቃል 169. ለኔ ብላ ለኔ ብላ ትገዛለች ሊፋን መኪና 170. የምትወደዉን እስክትሰራ የምትሰራዉን ዉደደዉ 171. ፍቅር ካለ የቁንጫ ቆዳ ለሺ ሠው ይበቃል 172. በሬ ያረደና ቆንጆ ያገባ ብቻውን አይበላም 173. የዉሸት እየኖርን የእዉነት እንሞታለን 174. ከሰው ጋር ስትሆን አፍህን ብቻህን ስትሆን ራስህን ጠብቅ 175.የማታፈቅርህን ማፋቀር ኤርፕርት ሄዶ በቡር መጠበቅ ነዉ 176. መባልን ሳይሆን መሆንን ፍራ 177. የአራዳ ልጅ መልስ አይጠይቅም 178. ነጋልሽ ደግሞ ልትጠበሽኝ 179. ከባጃጅ ላይ ሳይከፍሉ መዉረድ ከህፃን ልጅ ላይ ዳቦ እንደመንጠቅ ይቆጠራል 180. ገንዘብ ከድህነት እንጂ ከሞት አያስጥልም 181. እባክዎን በፀባይ ይዉረዱ እምቢ ካሉ እንደ ጋዳፊ ይወርዳሉ 182. ሦስት ቀን ለመኖር አራት ቀን አትጨነቅ 183. እባክዎን መስኮት በመክፈት ለትራፊክ አያጋልጡን 184. ከሙስና የፀዳ የስራ ዘርፍ የታክሲ ሹፌር ብቻ ነዉ 185. ለሰዉ ቅን እንጂ ቅንቅን አትሁን 186. ከስልጣን እና ከጫት ላይ መነሳት ይከብዳል 187. ምንም ብታምሪ ከሚስትነት አታልፊም 188. ሐብታም ግጦ በጣለዉ አጥንት ደሀዉ ይሰቃያል 189. የእከክ መድሀኒት ጠንክሮ ማከክ ነዉ 190. ፊትሽ ላይ የሌለዉ የካዲስኮ ቀለም ብቻ ነዉ 191· የታክሲ ከሌለህ ወርደህ በባስ ሂድ 192· ፍቅር ካለ ባጃጅ ባስ ይሆናል 193· ሒሳብ ሳይከፍሉ ሀሳብ አይጀምሩ 194· ባለጌና ዋንጫ ከወደአፉ ይሠፋል 195· ኤች.አይ.ቪንና የጫማ ሽታን በጋራ እንከላከል 196· ማንችስተር ያሸንፋል አርሠናል ለዘለዓለም ይኑር 197· ሠው አካውንት ይከፍታል አንዳንዱ አፉን ይከፍታል 198· ሞባይል ለጣለ ሲም እንመልሳለን 199· ሹፌሩን መጥበስ ክልክል ነው በነገር 200· ሠው ብቻ ነው የምንጭነው በስህተት የገባ ይውረድ 201· ታክሲ ለሚጠቀሙ ብቻ 202· ክቡራን ተሳፋሪዎቻችን በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይአስተያየት፣ ቅሬታ፣ ትዝብት ወይም መሻሻል አለበት የምትሉት ነገር ካለ አንቀበልም!! መውረድ ይቻላል:: 203. ለሠው ቅን ሁን እንጂ ቅንቅን አትሁን 204· ማስቲካ የሚታደል መስሎአችሁ አፋችሁን እንዳትከፍቱ 205· መስኮቱን በመክፈት ለትራፊክ ፖሊስ አያጋፍጡን! 206· ጥብቅ ማሳሰቢያ ለክቡራን ሌቦች ሒሳብ ሰብስበን ሳንጨርስ ስራችሁን መጀመር አትችሉም! የማይስማማ ሌባ ካለ መውረድ ይችላል፡፡ 207· ታክሲና መንግስተ ሰማያት ሞልቶ አያውቅም። የተደደጋገሙት ቁጥር ለማብዛት ሳይሆን ከዚህም ከዚያም የተሰበሰበ ስለሆነ ነው። ምንጭ:- ምርጥ መጣጥፎች T.me/psychoet
Показати все...
🚺✅ ከ200 በላይ አስገራሚ ጥቅሶች 🚹✅ 1. እንኑር ብለን ነው እንጂ መሞት አያቅተንም! 2. የያዝናት እድሜ አይደለም ለጠብ ለፍቅር እንኩአን አትበቃም! 3. ብቸኝነት ደስ የሚለው ሽንት ቤት ብቻ ነዉ 4. ማች ከመሞቱ በፊት ፍቅረኛውን ዜብራላይ ይስም ነበር 5. ጭቅጭቁን ትተን ብንፋቀር ምነው ሁሉም ቅርብ ወራጅ ነው ከፈጣሪ በቀር 6. ታክሲ ዉስጥ መጨቃጨቅ ኣሸባሪነት ነው 7. ሰዉ ብቻ ነዉ የምንጭነዉ በስህትት የተሰቀለ ካለ ይዉረድ 8. የሰራ የእጁን የተቀመጠ የቂጡን ያገኛል 9. አንገትክ ብቆረጥም ዋናዉ ጤና ነዉ 10. መብትዎን ታክሲ ላይ ትዝ ኣይበልዎ 11. ጤፍና በርበሬ ሲወደድ ችላቹ ታክሲ ላይ ታማርራላቹ 12. መንግስትና ተሳፋሪ ሊወርዱ ሲሉ ነገር ነገር ይላቸዋል 13. ስልጣን የህዝብ ማስተዳደሪያ እንጂ ማስፈራሪያ አይደለም 14. የምተኛዉ የማይተኛ ጌታ ስላለኝ ነዉ 15. አምላኬ 100000000 ዶላር እና ጤንነቴን ስጠኝ 16. ጡትና መንግስት ጊዜውን ጠብቆ መውደቁ አይቀርም 17. ምከረው ምከረው አንቢ ካለ በሴት አስመክረው 18. ጎንበሥ ቀና ብዬ ባገለግላቸው ከወንዝ የተገኘ ድንጋይ መሠልኳቸው 19. ፍቅረኛዬን አጣው ብለህ አትጨነቅ ታክሲም ማጣት አለና 20. ጠጋ ጠጋ በሉ! ! በኛ ታክሲ ተዋውቀው ብዙ ሰው ተጋብቷል 21. ነገረኛ ተሳፋሪ አደባባይ ላይ " ወራጅ አለ " ይላል 22. ሰውን ስትወድ ከመልካም ስብዕናው ውጪ ምኑንም ሳታይ ይሁን 23. አንድ ማፍቀር ግድ ነው ሁለት ማፍቀር ግን ንግድ ነው ሶስት ማፍቀር ግን ኮንትሮባንድ ነው 24. መዶሻ ጭንቅላት ያለው ሰው ሁሉም ስው ሚስማር ይመስለዋል 25. ከሰራህ ትበላለህ ካልሰራ ሲበሉ ታያለህ 26. እግዝአብሄር ድሃን ማስደሰት ሲፈልግ አህያውን አጥፍቶ እንዲያገኘው ያደርጋል 27. የበታችነት ከተሰማ ዛፍ ላይ ዉጣ 28. ጨበሶ ከመቃጠል በልቶ መመዘን ይሻላል 29. ቅናት ያገረጣዉ ፊት ቅባት አያወዛዉም 30. አስተዉሎ የሚራመድ ጫት ተራ ይደርሳል 31. እንኳን ተሳፋሪ ሙታንም ይሸጋሸጋል 32. ተሳፍሪ ጠጋጠጋ በሉ የአባይ አደራ አለብን 33. ባለጌ ሰው ዜብራ ላይ ወራጅ ይላል 34. ከጫት ሙቀት እንጂ አይገኝም እውቀት 35. ዜብራውን አንስተን አህያ እናስተኛልህ ወይ(ለሹፌሮች) 36. ለወሬኛ እና ለአምስት ሳንቲም መልስ የለንም 37. ፍቅር ፍቅር እያልሽ አትጨማለቂ ልቤ ዉስጥ ለመግባት ጫማሽን አዉልቂ 38. አባይን ያላየ ሄዶ ማየት ይችላል 39. ሴት ልጅ ታርሳ የምትገኝ ቢሆን ኖሮ ወንድ ሁላ ገበሬ ይሆን ነበር 40. ሰዉን አትናቁ ሰው እንዴት ይናቃል ቅማል እንኳን በአቅሙ ሱሪ ያስወልቃል 41. እስቲ ይሁን ብለን የተከለዉ ቃጋ ጎበስ ጎበስ አለ እኛኑ ሊወጋ 42. ባላገር ሲሰለጥን በዜና ይደንሳል 43. መሀይም ሀብታም ደሃን የፈጠረ ይመስለዋል 44. ምን ጊዜው ቢረዝምም ቋንጣ እና ባለ ስልጣን መውረዱ አይቀርም 45. ዝናብ ጥሎ ጥሎ መሬቱ ጭቃ ሲሆን ያን እያነሱ ግርግዳዉ ላይ ልጥፍ 46. በፍየል ዘመን በግ አትሁን 47. ሹፌሩን በፍቅር ማሣቅ እንጅ በነገር ማሣቀቅ ክልክል ነው 48. ትሞህርት በዱላ ቢሆን ኖሮ አህያ ፕሮፌሰር ትሆን ነበር 49. ሴት ልጅ ሒሣብ ሥትማር እንጂ ስትከፍል አይተን አናቅም 50. ደሀ ነዉ ችስታ ነዉ ብለሽ ትይኛለሽ ጭንና ዳሌ እንጂ አንችስ ምን አለሽ 51. መልስ ለረሳ ማትሪክ ላይ እንመልሳለን 52. ሴትና ሎተሪ ለማይፈልጋቸዉ እንጂ ለሚፈልጋቸዉ አይወጡም 53. ሹፌር ለጠበሰ ባለ 100ብር ረዳት ለጠበሰ ባለ 50 ብርካርድ እንሞላለን 54. የቅድብ ፀጉርና ምቀኛ አያድጉም 55. ንፁህ ህሊና ምቹ ትራስ ነዉ 56. ላታመልጪኝ አታሩጪኝ 57. ስራ ያጣ ተሳፋሪ ጋቢና ይቀመጣል 58. የማያልፍለት ደሃ ሀብታምን ይጋብዛል 59. በባጃጅ ስትጋዝ ንፋስ መታኝ አትበል ባጃጅ የመኪናዎች የልጅ ልጅ ናትና 60. ደንበኛ ካልቀበጠ ንጉስ ነዉ 61. ጧት ስትሄድ በእንቅፋት የመታህ ድንጋይ ማታ ከደገመህ ድንጋዩ አንተ እንጂ እሱ አይደለም 62. ጋይስ እንጀራ የለም እንጂ ወጥ ቢኖር ኖሮ በልታቹ ትሄዱ ነበር 63. ድብርትንና ጥይትን ተኝቶ ማሳለፍ ነው 64. ጠጋ ጠጋ በሉ ሁሉም ቅርብ ወራጅ ነው ከፈጣሪ በቀር 65. ከድሃ ቤት ጥቅስ ከሀብታም ቤት ጥብስ አይጠፋም 66. የቤትክን አመል እዛው 67. በፍርፍር ያዘነ በጥብስ ይደሰታል በፍቅር ያዘነ.....? 68. የመኖር ወርቃማ ዘዴ መቻቻል ብቻ ነው 69. ሁለት ክንድ አንድ ሜትር ነው ከዛ ያሳለፈ ውሸታም ነው 70. የሰው ልጅ አረም የበዛበት የመከራ ተክል ነው 71. የሚፈልገውን ያላገኘ ልብ ዘውትረ መንገደኛ ነው 72. የአለም ሙቀት መጨመር መንስኤ ጭቅጭቅ ነው 73. ፈገግታዬ ብዙ ነው ልቤ ግን ለአንድ ሠው ነው 74. ባለጌና ዋንጫ ወደ አፉ ሰፊ ነው 75. መስታወት በቆጣሪ ቢሆን ኖሮ ሴቶች ምን ይዉጣቸዉ ነበር 76. ድሀ በህልሙ ቂቤ ባይጠጣ ኖሮ ምን ይዉጠዉ ነበር ? 77. ማንበብ ከቻልክበት ሁሉም ሰው መፅሀፍ ነው 78. ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ቃል አትናግር 79. ባጃጅን አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት ታፔላ አወጡላት 80. ይሄ አናት ለቴስታ እንጂ ለትምህርት አይሆንም 81. ለኛ ከራሳችን የበለጠ የሚያስብልን የለም 82. ዝቅ ብለህ ስትሰራ ሁሉም ነገር ዝቅ ብሎ ይታይሃል 83. ማንም ሠው የጣለውን ሲያነሱበት አይወድም 84. ከሹፌሩ ጋር የምትጨቃጨቁ በኢቦላ እለቁ 85. ፍቅር ካለ ታክሲ ባሥ ይሆናል 86. የኪስ ሌቦች ቆዩ ሒሳቡን ሳንቀበል ስራ እንዳትጀምሩ 87. ሲጠሉህ ሳይሆን ሲወዱህም ለምን በል 88. ለሰዉ ሳይሆን ለራስህም ታመን 89. አለመዘጋጀት ለውድቀት መዘጋጀት ነው 90. ሂሳብ ሳይከፍሉ ሀሳብ አይጀምሩ 91. ሰርቶ የማይዝናና አህያ ብቻ ነዉ 92. ሹፌሩን በፍቅር እንጂ በነገር መጥበስ ክልክል ነው 93. እንደምን አደራቹ ውሸት መሮኛል ስራ ፈልጉልኝ 94. ኑሮና ታክሲ ካልታገሱት አይሞላም 95. እስክናውቅ እንጂ እስክናብድ አንማርም 96. የትም ፍጪው ምግቡን ብቻ ስጪኝ 97. አንድን ሳትይዝ ሁለትን አታገኝም 98. ያለዉን የሰጠ ባዶዉን ይቀራል 99. ሱሪህን ሳይሆን ራስህን ዝቅ አድርገህ ኑር 100. ህይወት በደረጃ ፈተና በኩረጃ 101. ለመኖር ብላ እንጂ ለመብላት አትኑር 102. ሾርባ ያቃጠለው በርጎ ይናደዳል 103. ያልተነገረ እንጂ ያልተባለ የለም 104. ሠርቶ የማይዝናና አህያ ብቻ ነዉ 105. የጊዜ ጀግና እንጂ የሰው ጀግና የለውም 106. ሰው እና ድፎ በትዛዝ እንደፋለን 107. እንደ ባሪያ ከሰራ እንደ ንጉስ ትኖራለህ 108. አንድ ጎል እና አንድ ሚስት አትመን 109. ወይ ጉድ ሀይሩፍ በዶልፊን ይስቃል አሉ 110. ሰዉን ማመን ቀብሮ ሳይሆን ቀብድ ተቀብሎ ነዉ 111. በፍቅር ለወደቀ የመሬት ስበት ተጠያቂ አይደለም 112. የማያልፍለት ደሀ ሀብታም ይጋብዛል 113. በሰዉ ላይ ከምትስቅ መጀመሪያ ራስህን እወቅ 114. አበሻ አንድ እግሩን ካልቆጹለት የሁለተኛው እግር ጥቅም አይገባውም 115. ከምታማ ወንጌል ሰማ
Показати все...
በ"ሜሎሪና" ሦስቱም መጽሐፍት ላይ ያደረግነውን ውይይት እንድትከታተሉ እጋብዛለሁ https://youtu.be/VxBArnirP1I?si=AyhHYAfgMjNKcmkH
Показати все...
👍 10
ሀሙስ 20 #ውሸት ለምን እንዋሻለን ??? ውሸት ተናጋሪዎችን እንዴት እናውቃለን??? ለምን እንዋሻለን ?? ሀ. ግላዊ ጥቅም ለማግኘት፡–  ለምሳሌ ለስራ ስንወዳደር ቃለ መጠየቅ ላይ የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈለን አሁን የሚከፈለንን የደመወዝ መጠን ከፍ አድርገን እንናገራለን፡፡ ለ.ቅጣትን ለማስቀረት፡– ህፃናት በወላጆቻቸው እንዳይቀጡ ያጠፉትን ነገር አይናገሩም ወይም አልሰራንም ይላሉ፡፡ ሐ. ሌሎች ስለኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ፡- ሰዎች ስለኛ ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ያልሆነውን ሆንን፣ ያላደረግነውን አደረግን ብለን እንናገራለን፡፡ ከላይ የተጠቀሱት የውሸት ዓይነቶች  በእኛ ዙሪያ ያጠነጠኑ እና  እራሳችንን ለመጥቀም የታለሙ  (self oriented) ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ለሌላ ሰው  ተብለው የሚዋሹ ውሸቶችም አሉ ለምሳሌ፡- ሀ. ሌሎች ሰዎችን ለመጥቀም፡– እናት ልጇን ከፍርድ ቤት ቅጣት ለመጠበቅ ስትል ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ልጄ እቤት ነው ብላ ልትመሰክር ትችላለች፡፡ ለ. ሰዎች ለማህበራዊ ግንኙነት ሲባልም ይዋሻሉ፡– ጎረቤት እራት ተጋብዘን እዚህ ግባ የማይባለውን  ምግብ ጣት ያስቆረጥማል ብለን የምንወጣው ቀጣይ የሚኖረንን ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማሰገባት ነው፡፡ ሐ. ሰዎችን ለመጉዳት እንዋሻለን :- ይህ ደግሞ በሌሎች እንዲቀጡ ባልሰሩት ነገር ላይ በሀሰት በመመስከር የሚደረግ ውሸት ነው ፡፡ ሰዎች እንደሁኔታው ዓይነት ውሸቶችን ይዋሻሉ ለምሳሌ #ሮቢንሰን ባጠናው ጥናት ላይ ስራ ለማግኘት ተብሎ ቃለ ምልልስ ላይ የሚዋሽ ውሸትን #83% የሚሆኑ የጥናት ተሳታፊዎች የነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች እንደ ውሸት አይቆጥሩትም፡፡ #ሮዋት ባጠናው ጥናት ደግሞ #40% የሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ወደፊት የፍቅር አጋር ይሆናል ብለው ላሰቡት ሰው በመጀመሪያ ግንኙነት ላይ እንደሚዋሹ አረጋግጠዋል፡፡ ሆኖም ግን ምን ያህል የሚሆነው የተሳካ የፍቅር ግንኙነት ኖሮት እንደቀጠለ ጥናቱ የሚለው ነገር ባይኖርም ከላይ በተቀስነው የውሸት ዓይነት ማለትም ሰዎች ስለ እኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ለማድረግ በሚዋሽ ውሸት ፍፃሜው ያማረ የፍቅር ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፡፡ ሌላው በጥናቱ ላይ የተመለከተው ነጥብ ጾታን በተመለከተ የታየ ልዩነት የለም ይህም ማለት ሁለቱም ወንዶችም ሴቶችም በእኩል መጠን ይዋሻሉ፡፡ በእኛስ ሀገር የትኛው የበለጠ ይዋሻል?? #ወንድ ወይስ #ሴት?? መልሱን ለእናንተ ተውኩት፡፡ ተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው ተጫዋች (ማህበራዊ) (Extraverts) ግላዊ (Introvert) ከሆኑት በበለጠ ውሸት እንደሚያዋሹ አመልክተዋል፡፡ ውሸትን እና ውሸታሞኝችን ለመለየት ሰዎች በጥናት የተደገፉ ከቤተ ሙከራ እስከ ውሸትን የማወቂያ መሳሪያ (polygraph) ድረስ ያሉ የተለያዩ ዓይነት ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ፖሊግራፍን ውሸትን ለማወቅ የሚለካው እንደ ልብ ምትና የመሳሰሉትን አካለዊ ለውጦችን እንደመሆኑ መጠን እንደየ ግለሰቡ ባህሪ ትክክለኝነቱ ሊወሰን ይችላል፡፡ ስሜታቸውን በቀላሉ የሚቆጣጠሩ ሰዎች ውጤቱን ሊያሳስቱ ሲችሉ፤ ድንጉጥ፤ ስሜታዊና ለነገሩ አዲስ የሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በተቃራኒው የቀጣፊነት ባህሪ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ አሁን አሁን ግን ከጎንዮሽ ጉዳቱና ከውጤቱ እርግጠኝነት ጋር በተያያዘ ፖሊግራፍ እየቀረ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ለጊዜው ግን ለእኛ ይሆነን ዘንድ የሰዎችን ባህርይ በማየት እንዴት ውሸታሞችን መለየት እንችላለን የሚለውን እንመለከት፡፡ የተደረጉት ጥናቶች በዋናነት መሰረት ያደረጉት #ስሜታዊነትን (emotional state)፣ #የወሬያቸውን (የመልዕክቱን) ይዘት (content complexity)  እና #ባህርይን ለመቆጣጠር ከሚደረግ ጥረት (attempted behavioral control) በመነሳት ነው፡፡ ስሜታዊነት ላይ ሰዎች ውሸት ሲያወሩ አንደኛ ውሸት እያወሩ ስለሆነ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ሁለተኛ በውሸቱ ምክንያት ወደፊት በሚያገኙት ጥቅም ደስተኛ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ይታወቅብኝ ይሆን በማለት ይፈራሉ፡፡ ከወሬያቸው ይዘት ጋር በተገናኘ ውሸት ተናጋሪዎችን ለመለየት ተናጋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ በመጠየቅ ተመሳሳይ መልስ እንደመለሰልን ማረጋገጥ እና ለምላስ ወለምታዎች ትኩረት መስጠት እንደ ዘዴ ተቀምጠዋል፡፡ የሰዎችን ባህርይ በማየትም ውሸት ተናጋሪዎችን መለየት እንችላለን #ዲፓውሎ_እና_ሮዘንሀል በጥናታቸው እንዳረጋገጡት ከሆነ ውሸት የሚያወሩ ሰዎች በሚያውሩበት ጊዜ እነዚህን ባህሪዎች አሳይተዋል መረጃውን  የሚያስተላልፉለትን ወይም የሚነግሩትን ሰው ዓይን ላለማየት የተለያየ ጥረት ደርጋሉ፣ አላስፈላጊ በሆነ ቦታ ላይ ሊስቁ እና ፈገግ ሊሉ ይችላሉ፣ ተደጋጋሚ የሆነ መንገድ በእጅ ለማስረዳት የእጅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ (ውሸት የማይናገሩ ሰዎች በእጃቸው እንቅስቃሴ ለማስረዳት እንደሚሞክሩ ልብ ይሏል)፣ ፊታቸውን እና  ፀጉራቸውን ያካሉ ወይም ይነካሉ፣ በተለያዩ ፊት ለፊት በተቀመጡ ግዑዝ ነገሮች ይጫወታሉ፣ በፍጥነት ያወራሉ፣ ግንባራቸውን እና እጃቸውን ያልባቸዋል፣ ጥያቄ ሲጠየቁ እስኪመልሱ ድረስ ባንጻራዊነት ሰፊ ጊዜ ይወስዳሉ፣ በመሀል አ……ኧ….እም……ያበዛሉ፣ መንተባተብ (ቃላትን መደጋገም፣ ዐረፍተ-ነገሮችን አለመጨረስ፣ የምላስ ወለምታ)እንዲሁም  ድንገተኛ የሆነ የድምጽ መጨመርና መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡ ሰዎች በተለያየ መንገድ ግንኙነት ፈጥረው ሲያወሩልን ወይም መልዕክት ሲያስተላልፉልን ከላይ ከጠቀስናቸው ምክንያቶች መካከል አንዳንድ ነገሮችን ካየን ውሸታም ብለን ከመፈረጃችን በፊት በእራሳችን መንገድ እና ለምን እንደዋሹን ደግሞ ማጣራት ይኖርብናል፡፡ በዚህች ባጭር ጽሁፍ መሸፈን አልችልም እንጂ ስለ Pathological liars (ህይወታቸው በሙሉ በውሸት ስለተሞላና ውሸት መናገርና ማቆም ስለማይችሉ ውሸት በሽታ ስለሆነባቸው ሰዎች) ጥቂት ባወራ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደፊት ይዤላችሁ እንደምቀርብ ቃል በመግባት የዛሬውን በዚህ ልቋጨው፡፡ ሰላማችሁ ይብዛ……….. ©Zepsychologist @psychoet
Показати все...
11👍 10😁 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሜሎሪና ቁጥር 3 (ሜሎሪና ሕይወቴ) እየተነበበ ነው። ፎቶና የወደዳችሁትን ሀሳብ እያካፈላችሁን ስላለ አመሠግናለሁ። ሜሎሪና መጽሐፍ በጃዕፈር መጸሐፍ መደብር (ለገሀር፣ 4ኪሎና ሳሪስ አደይ አበባ) ፣ በእነሆ መደብር 4 ኪሎ፣ በየኔነህ መደብር ቃሊቲ መናሀሪያ፣ በሱመያ መደብር መርካቶ፣ በባህርዳር ጎንደርና ላሊበላ አካባቢ አዳነ መደብር እና በሌሎችም መደብሮች ይገኛል። በሌሎችም መደብሮች እየተሰራጨ ስለኾነ የቀረውን የክረምት ቀናት ዳጎስ ያሉ (የሥነልቦናና የመሪነት) ሀሳቦችን ከልብወለድ ታሪክ ጋር በማንበብ እንድታሳልፉ እንጋብዛለሁ።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሬድዮ ላይ ስለ ምን ጉዳዮች መስማት ያስደስታችኋል?
Показати все...
#ሞትን_መሸሽ_ወይስ_አምኖ_መቀበል_...? https://youtu.be/v3HVFJUuxjk?si=Q9MwDNcV_uKiZqK4
Показати все...
👍 6👏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከቻናሉ ቤተሰቦች ምን ያህሎቻችሁ "ሜሎሪና-ሕይወቴ" ን እያነበባችሁ ነው? የመጀመሪያው ዕትም ጥቂት ስለቀረ በሚቀርባችሁ መደብር በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት ትችላላችሁ። @psychoet
Показати все...
👍 7
"ይቺ ዓለም የምትፈልግህ ጠቃሚ ነገር አንተ ጋር እንዳለ ስታምን ብቻ ነው፡፡ ባጠቃላይ ዓለም ራስ ወዳድ ናት - ነዋሪዎቿም እንደዛው። ይሳካልህ ብለው መርቀውህ ሲሳካልህ የማይወዱ፣ ሰላም ሁን ብለው ሸኝተውኽ ጥልን የሚመኙልህ፣ ይከናወንልህ ብለው ውድቀትን የሚያስቡልኽ፣ ራሳቸውን ለመጥቀም አንተን የሚጎዱ ሰዎች ብዙዎች ናቸው።" ✍መስፍን እንዳለው ሜሎሪና - ሕይወቴ
Показати все...
👍 43 6
Фото недоступнеДивитись в Telegram
‹‹..ምቀኝነት በመጀመሪያ የሚገለጸው በቀልድ ውስጥ ነው። ስለዚህ ሰዎች በቀልድ የሚሉህን ኹሉ ከመረዳትና ራስህን ከአደጋ ለመጠበቅ ቸል እንዳትል። … ሰው በውስጡ የሌለን ወይም ያልመሰለውን ነገር በአፉ አይተነፍስም።›› ሜሎሪና - ሕይወቴ
Показати все...
30👍 12
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሜሎሪናን እያነበባችሁና አስተያየቶቻችሁኝ እየሰጣችሁን ስላለ እናመሠግናለን። 🙏
Показати все...
7👏 2
ትላንት ምሳ ሰአት ነው…ሶስት ናቸው… ትልቅ ሮቶ ይዘዋል …ላዳ አስቆሙና ሮቶውን ጫኑና ገቡ… ከዛ ሩቅ መንገድ ይዘውት ሄዱ…ብዙ ጉራንጉር አስገቡትና የሆነ ቤት ጋር ላይ ሲደርሱ እዚህ ጋር ነን ብለው አስቆሙት እቃቸውንም ተሸክሞ አወረደና …ሂሳብ ሲል ... የለንም አሉት… ወርዶ ቢለምን ምን ቢል ዝምብለህ ንካው አሉት… ጭራሽ እንድንከፍልህ ከፈለክ ዝፈንልን አሉት… ዘፈን አልችልም አለ… በቃ እሺ #እልል በልና እንሰጥሃለን አሉት …ሰርቼ እኮ ነው ለምን ታንገላቱኛላቹ ይህን የሚያክል ሮቶ ጭኜ መኪናዬን ኮሮኮንች ውስጥ ጎድቼ ምንም አትከፍሉኝም ?ቢልም ጮክ ብለህ #እልልል ካላልክ አንሰጥህም አሉት… ተናደደና ተውት በቃ ከላይ አገኘዋለው ብሎ እየተሳሳቁበት ሳይቀበላቸው ጥሏቸው ሄደ… ትንሽ እንደሄደ ከኋላው ስልክ ጠራ… ዞር ሲል Sumsung Not 8+ የተባለ ስልክ አንሱኝ አንሱኝ እያለ እየጮኅ ነው… መኪናውን ዳር አስያዘና ስልኩን አንስቶት ሃሎ አለ… ይቅርታ ወንድሜ አንተ ታክሲ ውስጥ ስልክ ጥለን ነበር የሚል ድምፅ ተከተለ… ማን ልበል? አላቸው … አሁን ያወረድከን ሮቶውን የጫነው ልጆች ነን… እባክህን ስልክ ጥለን ነው ይሄኔ ይሄ ላዳ ሹፌር ምን ቢል ጥሩ ነው… … , , , , , , , አሁን ነዋ #እልልልልል ማለት ብሎ ጮክ ብሎ ስልክ ጆሮአቸው ላይ እልልልልልልልል, ልልልልልልልልልል, እልልልልልልልልልል, እልልልልልልል 😂😂 መልካም የስራ ቀን መመለስ ነበረበት የሚል #ሼር እርሶ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ ?! ©Fb
Показати все...
😁 20👍 14
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ጠንካራ ሰዋች...
Показати все...
23👍 5
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መልካም አዲስ ዓመት ይኹንላችሁ #2017 ሜሎሪና መጽሐፍ 🌼🌼🌼🌼🌼
Показати все...
👍 12 8
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሜሎሪና ቁጥር 3 (ሜሎሪና - ሕይወቴ) ለአንባቢያን ቀርቧል “ሜሎሪና” ታሪካዊ የሥነልቡና ልብወለድ የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበብ ሚና የሚተርክና ስለ ኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚያወራ ልብወለድ መጽሐፍ ነው ፡፡ በአቀራረቡም #የሥነልቡና_ምክሮችንና ሀሳቦችን #የሥነ_አመራር ጥበቦችን #ከታሪካዊ_ክስተቶች ጋር አጣምሮ ይዟል ፡፡ ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ የተወሰዱ የሕይወት ምክሮችና እውነታዎች 📕 ‹‹ትልቁ ብቸኝነት ሰውን ማጣት ሳይኾን ራስን ማጣት ነው። በምድር ላይ ራሱን እንዳጣ ሰው ብቸኛ የለም።  ራስን ማጣት፥ በኛ ውስጥ ያሉ ችሎታዎቻችንን አቅማችንንና ስሜቶቻችንን ማጣት ነው፡፡  እራሱን ያጣ ሰው በዙሪያው እልፍ ሰዎች ቢሰበስብ እሱ ግን ዘወትር ብቸኛ ነው።›› 📕‹‹...ትዝታ ለብዙ ሰው የዕድሜ ዘመን እስር ቤት ነው። ብዙ ሠዎችም ወደፊት መራመድ እየፈለጉ አስሮ የሚይዛቸው በገዛ አዕምሮአቸው ውስጥ ያስቀመጡት የትናንት ታዝታቸው ነው።›› 📕‹‹አፍሪካ ውስጥ  ‹ሕዝቡ› እንደሚለው ቃል በመሪዎች የተነገደበት ቃል የለም። አንዳንዱ መሪ ሕዝቡ የሚለው የገዛ ራሱን እሳቤ ነው። ሌላው ደግሞ ቤተሰቦቹንና ዘመዶቹ ብቻ ነው ሕዝቡ ብሎ የሚቆጥረው።›› 📕‹‹ሰው የሚሞተው ሥጋው ነፍሱን መሸከም ሲያቅተው ነው፡፡ ሥጋችን ደግሞ የሚያረጅም የሚበላሽም ነው፡፡ ነፍስ ልትሞት ካልቻለችና የሚሞተው ሥጋችን ከኾነ፣ለምን ለነፍሳችን የማያረጅና የማይሞት ሥጋ አንሠራላትም›› 📕‹‹በህይወት ስትኖር መቼም ቢሆን ኹሉንም ሰው ማስደሰት አትችልም፤ ማወቅና መጠንቀቅ ያለብህ ዋናው ቁም ነገር ማስከፋት የሌለብህን ሰው ለይተህ ማወቁ ላይ ነው።››    ሜሎሪና ሕይወቴ @psychoet
Показати все...
14👍 7
Фото недоступнеДивитись в Telegram
...እነዚህ ሰዎች ሲቸግራቸው፣ ሲከፋቸው እና መውጫ ቀዳዳ ሲጠፋቸው ይስታውሱሃል እንጂ በደስታቸውና በስኬታቸው ጊዜ አትታያቸውም፤ የተቸገሩ ጊዜ ከአንተ እርዳታ ለመጠየቅ ፣ የጨነቃቸው ሰሞን ባንተ ለመጽናናት ፣ ዝቅ ያሉ ሲመስላቸው ባንተ ተጠቅመው ወደ ከፍታ ስፍራቸው ለመውጣት ዘወትር ከደጅህ ናቸው። ያገኙ ቀን፣ ያማረባቸው ዕለት፣ በሰዎች በተከበቡ ጊዜ ግን አንተን አያውቁኽም፣ ካጠገባቸው ኾነኽ አያዩህም ፣ እያወራሃቸው አይሰሙኽም፣ እየጠየቅሃቸው አይመልሱልኽም።... ሜሎሪና ሕይወቴ❤ እያነበባችሁ ነው?
Показати все...
👍 21 5
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በሕይወታችን ለማግኘትና ለማሳካት የምንፈልጋቸውን ‹ትልልቅ› የሚባሉ ነገሮች ለማሳካት መክፈል ያለብን ብዙ መሥዋዕትነቶች አሉ፡፡ አንዳንዴ፣ መድረስ ወደ ምንፈልግበት ቦታ ለመድረስ ራሳችንን አዋርደን፣ ዝቅ ብለን፣ ማንነታችንን ደብቀን ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የምንፈልገው ቦታ ለመድረስ መሸጥ ያለብን ማንነት እና መጣል ያለብን ክብር ይኖራል። ሜሎሪና ሕይወቴ
Показати все...
👍 22 1