uk
Feedback
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

Відкрити в Telegram

Journalist-at-large

Показати більше
2025 рік у цифрахsnowflakes fon
card fon
133 743
Підписники
-4624 години
-1437 днів
-61730 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#Attention| ከሰሞኑ ከሚያባንኑኝ ጉዳዮች አንዱ በቅርብ ቀናት አዋሽ አካባቢ የተከሰተው ርዕደ መሬት እና አያድርስ እና ከፍ ያለ መጠን ያለው መንቀጥቀጥ ቢከሰት በአካባቢው ያሉ ግድቦች ላይ መደርመስ አስከትሎ ዜጎች ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ነው በአካባቢው ያለው ግዙፉ የከሰም ግድብ ላይ ጉዳት ቢደርስ ሊለቀው የሚችለው ግዙፍ የውሀ መጠን በታችኛው ተፋሰስ ላይ ያሉ ዜጎችን ሊውጥ ይችላል። "ቀፈን ቀበና ግድብ በተመሳሳይ በክረምቱ ወቅት ግዙፍ የውሀ መጠን ይዞ ይገኛል፣ አደጋ ቢከሰት ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለማሰብ ይከብዳል" ያሉኝ አንድ ባለሙያ ከአካባቢዎቹ እስካሁን 700 አባወራዎች እንዲነሱ ቢደረግም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም ለአደጋው ተጋልጠው ይገኛሉ ብለዋል። አደጋ ከደረሰ በኋላ ብዬ ነበር ማለት ወይም ከንፈር መምጠጥ ዋጋ የለውም፣ ስለዚህ ሌላው አለም ላይ እንደሚደረገው ቢያንስ ሁኔታው በደንብ እስኪጠና ተጋላጭ ወገኖችን ወደ ሌላ ቦታ ማስፈር ቢቻል እጅግ መልካም ነው። እባካችሁ የሚመለከታችሁ አካላት ትኩረት፣ ትኩረት፣ ትኩረት! @EliasMeseret
Показати все...
👍 794 69😢 36🙏 19🕊 9😁 5😱 4🤔 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መርካቶ ሸማ ተራ ተከስቶ በነበረው አውዳሚ የእሳት አደጋ ወቅት አንዳንድ የእሳት አደጋ አጥፊ ቡድን አባላት ከባለሱቆች ጋር የገንዘብ ድርድር ሲያደርጉ እንደነበር ሰምቻለሁ፣ ከአንድ እና ከሁለት ሳይሆን 8 ሰዎች አረጋግጠውልኛል በስፍራው ከደረሱ በኋላ እሳቱን ከማጥፋት ይልቅ "ማንን ነው ምናናግረው?" በማለት ለረጅም ደቂቃዎች ማጥፋት እንዳልጀመሩ እነዚህ የአይን እማኞች ይናገራሉ። "ማለት የፈለጉት ብር እንዲሰጣቸው ከማን ጋር ነው ምንደራደረው ነው። ይህ ነገር የተለመደ ቢሆንም ይሄ ሁሉ ንብረት እስኪወድም ግን በዚ ደረጃ አይመስለኝም ነበር" ያለኝ አንድ የአደጋው ተጎጂ ቤተሰብ ይህን መረጃ በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች እንደሚያውቁ ነግሮኛል። መሠረት ሚድያ ደግሞ በደረሰው መረጃ በስፍራው ቀድመው በአምቡላንስ የደረሱ የእሳት አደጋ ቡድን አባላት 4 ሚልዮን ብር በመቀበል በድርድር ተስማምተዋል። ብር ከፋዮቹ በጊዜው የነበሩ የሱቅ ባለቤቶች ሲሆኑ የብዙ ሚሊዮን ብር ንብረት ሱቆቹ ውስጥ ላይ ስለነበራቸው የተጠየቁትን ለመክፈል ምርጫ ስላልነበራቸው አላቅማሙም ነበር፣ ጠያቂዎቹ ደግሞ በጊዜው ቀድመው አምቡላንስ ይዘው የደረሱ የእሳት አደጋው ሰራተኞች ናቸው ተብሏል። ይህን ድርጊት የፈፀሙት ሁሉም ሳይሆኑ በእሳት አደጋ ሰራተኞች መሀል የሚገኙ የሰው ንብረት ውድመት ሳይታያቸው እና ሙያቸውን የካዱ ጥቂቶች እንደሆኑ ይሰማኛል። ጉዳዩን "ውሸት" ምናምን ብሎ ለማለፍ ሊሞከር ይችላል፣ የሚያዋጣው ግን አጣሪ ቡድን ወደስፍራው በመላክ እነዚህን አሳፋሪ ጥፋተኞች በህግ መጠየቅ ነው። አሳፋሪ ነው! @EliasMeseret
Показати все...
👍 1 280😢 549🤔 85😱 62 51😁 13🕊 11🙏 1
Показати все...
👍 121😁 109🤔 18 9😱 6
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ከፍተኛትኩረት በደቡባዊ የሀገራችን ክፍል በቅርብ አመታት ታይቶ የማይታወቅ የወባ ወረርሽኝ ተከስቶ ህዝብ እየረገፈ ነው በአካባቢው ያሉ የጤና ባለሙያዎች እንደነገሩኝ በወላይታ፣ በከምባታ፣ በጉራጌ ዞኖች እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ እና ዙርያው ወረርሽኙ ተባብሷል። ፈጣን ትኩረት ያሻዋል፣ መሠረት ሚድያ በምሽት ዜናው ሁኔታውን በስፋት ይዳስሳል። @EliasMeseret
Показати все...
👍 406😢 183 22😱 16🤔 12😁 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከወንድም ጌጡ ተመስገን እና ጓድ ታደለ አሰፋ ጋር በአፍሪካን ኢምፓክት አዋርድ ፕሮግራም Was fun. @EliasMeseret
Показати все...
👍 570 99😁 38🤔 15😢 11🕊 7🙏 5😱 4
#ለግልፅነት ከሚሰራበት ቦታ ተባሮ እና የሚኖርበት ቤት እንደሚፈርስ ሲነገረው ራሱን ስላጠፋው አዲሱ ካሳሁን ትናንት አንድ መረጃ እና የድጋፍ ጥሪ አቅርቤ ነበር እስከ አሁኑ ሰአት ድረስ ብቻ 520,000 ብር (አምስት መቶ ሀያ ሺህ ብር) በባለቤቱ የቀጥታ የባንክ አካውንት ድጋፍ ተደርጎላታል። ድጋፍ ላደረጋችሁ እንዲሁም መረጃውን በአካውንታችሁ እና ገፃችሁ መልሳችሁ ሼር ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ። @EliasMeseret
Показати все...
👍 1 580🙏 403 262😢 40😱 9🤔 5
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ህዝቡ በጣም ገቢው አድጎ ስለበለፀገ አምና በሳንቲሞች ይጨምር የነበረው የትራንስፖርት ዋጋ አሁን እስከ እጥፍ በሚሆን ጭማሪ አሳይቷል... የመዓት ግዜ! @EliasMeseret
Показати все...
😢 1 336👍 164😁 93😱 41🤔 40 27🙏 20🕊 6
‼️ ከሁለት ሰአት በፊት ያጋራሁት የድጋፍ ጥሪ የባንክ አካውንት ቁጥር እንደማይሰራ (inactive እንደነበር) በገለፃችሁት መሰረት አሁን ተስተካክሏል
Показати все...
304👍 141🙏 44😢 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አዲሱ ካሳሁን በአዲስ አበባ ከተማ ከኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ አትላስ ሆቴል በሚወስደው መንገድ አካባቢ በሚገኘው 'በፀጋህ ሆስፒታል' ፊት ለፊት ባለ አንድ ግቢ ነዋሪ ነበር። አዲሱ ነጠላ ከሚሸጥበት ኡራኤል ቤተከርስቲያን አካባቢ ስራ እንዳይሰራ ሶስት ግዜ በደንብ አስከባሪዎች ተባሮ እና ንብረቱም ተወስዶበት እንደነበር ባለቤቱ እንዲሁም ጓደኞቹ ይናገራሉ። ከዚህም በተጨማሪ ከአምስት ቀን በፊት ምሽት ወደ ቤቱ ሲገባ ተከራይቶ የሚኖርበት ቤት በነጋታው ጠዋት እንደሚፈርስ ሲነገረው ተስፋ በመቁረጥ ስሜት እዛው ግቢ ውስጥ ራሱን እንዳጠፋ ባለቤቱ በእንባ እየታጠበች ነግራኛለች። "የዛን እለት ብዙ ሲጨናነቅ ነበር፣ ቤት ሲያጠያይቅ 13 ሺህ እና 15 ሺህ ሲሉት ነበር፣ በዛ ላይ ቤተሰብ ያለው አናከራይም እያሉት። ሊነጋጋ ሲል ራሱን አጥፍቶ አግኝተነዋል፣ አሁን የት እንደምሄድ እና ምን እንደማረግ እንዳለብኝ አላውቅም" በማለት ነግራኛለች። የሁለት የልጅ አባት የሆነው አዲሱ (አንደኛው ገና 5 ወሩ ነው) ባሳለፍነው አርብ እለት ስድስት ሰአት ላይ በኡራኤል ቤተክርስቲያን ቀብሩ ተፈፅሟል። ባለቤቱን እማኑሽ ፈንታን በቻልነው አቅማችን እንደግፍ፣ ለማስጀመርያ እንዲሆን እኔም በግሌ የአቅሜን ድጋፍ አደርጋለሁ። እማኑሽ ፈንታ ስልክ: +251920660393 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000334824652
Показати все...
😢 970👍 326 68🙏 42🤔 13😱 10
የዘንድሮው የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ስነ ስርአት ሜሪላንድ በሚገኘውና ኢትዮጵያዊያን በባለቤትነት በሚያስተዳድሩት ሜትሮ ፖይንትስ ሆቴል ዛሬ፣ እሁድ ኦክቶበር 13/2024 ምሽት በደማቅ ዝግጅት እየተካሄደ ነው፣ እኛም በስፍራው ተገኝተናል በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የተመሰረተውና ለትርፍ ያልተቋቋመው ኖቫ ኮኔክሽን ያዘጋጀው የ2024 አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ የዘንድሮ የክብር የሽልማት ሥነ ስርዓት እየተከናወነ ነው። ይህ አመታዊ የእውቅና ሽልማት ስነ ስርአት በአሜሪካና በአፍሪካ በሙያቸው ታላቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን ለማክበር የተዘጋጀ ነው። በየአመቱ ከስፖርት፣ ከስነ ጥበብና ከስራ ፈጠራ ዘርፎች ለማህበረሰቦቻቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦና ለለውጥ ላደረጉት የላቀ ተሳትፎ ከየዘርፉ ተመርጠው የሚሸለሙበት መድረክ ነው። አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ እስካሁን ለአራት ጊዜያት ተካሂዷል። ዘንድሮም በተለያዩ ዘርፎች ለአምስት ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊያንን የክብር እውቅና እየሰጠ ይገኛል። የዘንድሮ ተሸላሚዎች አርቲስት አስቴር አወቀ፣ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ፣ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ ወ/ሮ ሬቤካ ሀይሌ እና አትሌት ትግስት አሰፋ ናቸው። ለግብዣው ዶ/ር ጋሻው አበዛን አመሰግናለሁ። @EliasMeseret
Показати все...
👍 421 67😁 15🤔 9🕊 5
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#FactCheck ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሂደት ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃ ሆነች በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ሚድያዎች፣ የግብርና ሚኒስቴር እንዲሁም የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተጠቃሚዎች “ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሂደት ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃ ሆነች” የሚል መረጃ አጋርተዋል። ይህን መረጃ ያጋሩት ሚድያዎች እና ግለሰቦች እንደ መረጃ ምንጭነት የተጠቀሙትም ኢን ኦን አፍሪካ (IOA) የተሰኘ ድረ-ገጽ ነው፡ https://www.inonafrica.com/  ይህ በደቡብ አፍሪካ እአአ በ 2007 ዓ/ም የተመሰረተ ተቋም በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ጥናቶችን በማድረግ የሚታወቅ ነው። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ እየተሰራጨ የሚገኘውን መረጃ በተመለከተ የኢን ኦን አፍሪካን ድረ-ገጽን እንዲሁም የማህበራዊ ትስስር ገጾቹን የተመለከተ ሲሆን የተባለው ሪፖርት በድርጅቱ የመረጃ ቋቶች ላይ እንደሌሉ አረጋግጧል። እየተጋራ በሚገኘው ስክሪን ቅጂው የላይኛው ክፍል ላይ የሚገኙ ጽሁፎች እና ምስሎች ከተቋሙ ትክክለኛ ድረ-ገጽ ጋር ተመሳሳይነት ቢኖራቸውም ሪፖርቱ ግን ትክክለኛው የ ‘IOA’ ድረ-ገጽ ላይ እንደሌለ አረጋግጠናል። በተጨማሪም ከመረጃው ጋር እየተጋራ የሚገኘው የስክሪን ቅጂ የፊደል አቀማመጥ/ፎንት ስህተቶች የሚታዩበት መሆኑንም ተመልክተናል። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መረጃውን በፌስቡክ ገጹ ካጋራ ከሰዓታት በኋላ መልሶ ማጥፋቱንም ተመልክተናል። ከሰሞኑ ተመሳስለው የተዘጋጁ ሀሰተኛ ስክሪን ቅጂዎች በስፋት እየተሰራጩ እና በርካቶችን ለስህተት እየዳረጉ ይገኛሉ። በመሆኑም መሰል ስክሪን ቅጂዎችን አምነን መረጃዎችን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ። Via Ethiopia Check
Показати все...
👍 748😁 385 60😢 21🤔 14🙏 12🕊 4😱 3
በዛሬው እለት በአለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ የዋለውን የአእምሮ ጤና ቀን ምክንያት በማድረግ ከክሊኒካል ሳይኮሎጂስት ዶ/ር አወቀ ምህረቱ ጋር በመሠረት ሚድያ ቆይታ አድርጌ ነበር ከራስን ማጥፋት ጀምሮ እስከ የአእምሮ መቃወስ ያሉ ብዙ ስለማይነገርላቸው ነገር ግን ህዝቡን በከፍተኛ ደረጃ እየጎዱ ስላሉ ጉዳዮች አውርተናል https://youtu.be/zh8I3sgXGC0?si=Lzh_EnUavzu7ufPy
Показати все...
👍 165 20🙏 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Показати все...
😁 286👍 140 16🙏 14🕊 6
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አሻም የህዝብ ድምፅ! @EliasMeseret
Показати все...
👍 1 331 125😁 90😢 52😱 20🤔 14🙏 10🕊 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በዚህ አካሄድ አውሮፕላን መግዛት ሳያዋጣ አይቀርም Totally insane! @EliasMeseret
Показати все...
😁 1 061😢 187👍 134 49😱 47🤔 16🙏 9🕊 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
እንኳን ለደማቁ የእሬቻ በአል አደረሳችሁ፣ አደረሰን! Baga Irreecha Baranaa Geenye! መልካም በአል! @EliasMeseret
Показати все...
😁 537 199👍 145😢 35🤔 34🙏 19🕊 18😱 17
የሰሞኑን የብር መዳከምን (የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን) ተከትሎ ገበያ ላይ ያልጨመረ ነገር የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም ይህ አልበቃ ብሎ የመንግስት ተቋማት ህዝብ ላይ እልህ እየተወጡ ይመስል ተራ በተራ እስከ 700 ፐርሰንት ጭማሪ ያረጉ አሉ። ኢሚግሬሽን፣ ንግድ ባንክ፣ ኤሌክትሪክ፣ ውሀ፣ ቴሌ፣ አየር መንገድ፣ የመኪና ቦሎ እና መንጃ ፈቃድ፣ የትራፊክ ቅጣት... ከሰሞኑ ደግሞ የዳኝነት ክፍያ እንኳን ጭማሪ ይደረግበታል። የኔ ጥያቄ: አንደኛ፣ ጭማሪ ሲደረግ ነባራዊ የህዝብን አቅም እና ችግር ማገናዘብ የለበትም ወይ? ሁለተኛ፣ በሌላው አለም እንደምናየው progressive የሆነ የ10%፣ የ20%... ወዘተ እያለ ጭማሪ ይደረጋል እንጂ ሲፈልግ የ150%፣ ሲያሻው የ700% ጭማሪ ማድረግ ማለት ነው? ሶስተኛ ደግሞ አንድ ሰሞን ሲወራ የነበረውን ጥቂት የሆነ የደሞዝ ጭማሪ እንኳን ተግባራዊ ሳያደርጉ ህዝብ ላይ ሸክም መጫን ለምን ተፈልጎ ይሆን? እውነት ይሄ ነገር አንድ ወዳጄ እንዳለኝ "መንግስት ከህዝብ ጋር እልህ ተጋብቶ እየቀጣው ነው" ያለው እውነት ይሆን እንዴ? ዝመት ሲባል ዘምቶ ለሚቆም፣ ደግፍ ሲባል በሚሊዮኖች ወጥቶ ለሚሰለፍ፣ ሀገርህ ተደፈረ ሲባል "ኢትዮጵያን!" ብሎ ለሚዘምት ግን ይህ አይገባውም። @EliasMeseret
Показати все...
👍 2 344😢 418 224🙏 161😁 46🤔 28🕊 7😱 6
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ለግልፅነት በትናንትናው እለት ለእታገኝ አየናቸው ያጋራሁትን የድጋፍ ጥሪ ተከትሎ ከ 375,000 ብር በላይ በቀጥታ በንግድ ባንክ አካውንቷ ተሰብስቧል። አንድ ዶክተርም ለታማሚው ልጅ ህክምና ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነዋል። ድጋፍ በማድረግ ለተካፈላችሁ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋና ይድረሳችሁ።
Показати все...
🙏 1 403 336👍 174🕊 29😁 3