uz
Feedback
TIKVAH-ETHIOPIA

TIKVAH-ETHIOPIA

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
1 573 115
Obunachilar
-46124 soatlar
-1 6017 kunlar
-2 64930 kunlar
Postlar arxiv
"ድሬዳዋን እንደ ቦርደር ነው የሚሸጋገሩበት። በሚያሳዝን ሁኔታ በልመና ሁሉ የተሰማሩ ከአማራና ትግራይ ክልሎች የመጡ ሰዎች አሉ። በጣም የሚበዙት ከአማራ ክልል ናቸው’’ - የድሬዳዋ ሴቶች ፌዴሬሽን በጦርነት እና ጸጥታ አለመረጋጋት ሳቢያ ከአማራ እና ትግራይ ክልሎች ተነስተው ለመሰደድ ድሬዳዋን እንደመውጫ ለመጠቀም የሚሞክሩ ዜጎች በከተማዋ በልመና ተሰማርተው እንደሚገኙ በጥናት መረጋገጡን የድሬዳዋ ከተማ ሴቶች ፌዴሬሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። የድሬዳዋ ከተማ ሴቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ኢፍቱ አባስ፣ ‘’ድሬዳዋን እንደ ቦርደር ነው የሚሸጋገሩበት። በሚያሳዝን ሁኔታ በልመና ሁሉ የተሰማሩ በተለይ ከአማራና ትግራይ ክልል የመጡ አሉ። በጣም የሚበዙት ከአማራ ክልል ናቸው” ብለዋል። “ሲመጡ ወደሌላ ሀገር ለመሸጋገር ነው የእነሱ ፍላጎት’’ የሚሉት ኢፍቱ፣ በቅርቡ ስለጉዳዩ ጥናት እንደተደረገ፣ ጥናቱን ለማድረግ ያነሳሳቸው አንዲት እናት አስፋልት ስትሻገር ሁለት ልጆቿ በመኪና ተገጭተው ሲሞቱባት ወደትውልድ ስፍራዋ ወስዳ እንድትቀብር በመጠየቅዋ በከተማዋ ተፈናቃዮች እንዳሉ በመገመቱ መሆኑን አስረድተዋል። ‘’ያ አደጋ እንደ እናት ያማልና ይህን ነገር ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? እስኪ ጥናት ይሰራ ምን ያክል ሰዎችስ ያሉት? ከተማው ውስጥ መኖር የሚፈልጉ ካሉ ዜጎች ናቸውና እንዲኖሩ ምን መሰረታዊ ነገር ልናሟላላቸው ይገባል? በሚል ከሲነርጅ፣ ከሴቶች ፌዴሬሽን ጋር ሆነን ተቀናጀተን ጥናቱ ባለፈው ክረምት ተሰርቷል” ብለዋል። “ከህጻናት ጋር በትንሹ ወደ 200 ሰዎች ተገኙ” ሲሉም ከአማራና ትግራይ ክልሎች በጸጥታ ችግር ተፈናቅለው ወደ ድሬዳዋ ከተማ የሸሹ ዜጎች መኖራቸው በጥናቱ እንደተረጋገጠ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል። “ቤቶችን ለሦስት፣ ለአራት እየተከራዩ የሚኖሩ አሉ፣ ባልተመቼ ሁኔታ ነው እየኖሩ ያሉት የሚባል ነገር መጣ፣ ከዚያም እነርሱን (ሸሽተው የሄዱትን) ለማግኘት ተሞከረ፣ ኢንተርቪው ተደረጉ። አብዛኛዎቹ እዛው (ከነበሩበት ከትውልድ ቦታቸው) ያለው የሰላም ሁኔታ ስላልተረጋጋ ባንመለስ ነው የሚሻለው ብለው ውስጣቸው ጥሩ ነገር አልተሰማቸውም” ነው ያሉት። “አንዳንዶቹ ደግሞ 'የትራንስፖርት ከቻላችሁን ወደዛው ብንመለስ ነው የሚሻለን' የሚሉም ተመለከትን” ያሉት ፕሬዚዳንቷ፣ መመለስ የሚፈልጉት የመመለስ ስራ እንደተሰራ፣ በአንፃሩ አሁንም በድሬዳዋ እየኖሩ ያሉ እንዳሉ፣ ህጻናቱም ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል። “ደብተር እንዲገዛላቸው፣ በሚቀርባቸው ቦታ በመንግስት እንዲመዘገቡ አደረግን። ግን አሁንም ማድረግ አለብን ብዬ የማስበው ስራ ብንፈጥርላቸው፣ በዘላቂ መንገድ በራሳቸው ዳቦ የሚያገኙበትን መንገድ ብናመቻችላቸው ጥሩ ነው። ግን አይርባቸውም፣ ሆኖም አለመራባቸውን አይደለም ማየት ያለብን፣ ሁሌም መለመን ስነልቦናን እየጎዳ ነው የሚመጣው” ነው ያሉት። “አብዛኛዎቹ በልመና ነው ያሉት፣ ስራም የሚሰሩ አሉ፣ በርበሬም እየቀነጠሱ ለሌሎች እያዘጋጁ እየሰሩ ቢያንስ አልራባቸውም። ወንዶችም ማስቲካ ይዘው እየዞሩ የሚሰሩ አሉ። ግን ዘለቄታ አለው ብዬ አላስብም። በዚህ ሁኔታስ እስከመቼ ነው የሚቀጠለው የሚለው ጥያቄ ውስጥ ይከታል” ያሉት ወ/ሮ ኢፍቱ፣ ለዚህም መንግሳታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እያነጋገሩ መሆኑን ተናግረዋል። በሌላ በኩል በወባና መሰል ገዳይ በሽታዎች እንዳይጠቁ በማንኛውም ጤና ጣቢያ ሂደው በነጻ እንዲታከሙ መደረጉንም ፕሬዚዳንቷ ገልጸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
1
ሱፐር ኤስ ጂ ኤስ ፈርኒቸር ! 🎄የገና በዓል ልዩ የቅናሽ ከስጦታ ጋር ከሱፐር ኤስ ጂ ኤስ! በዚህ ገና እንግዶችዎን የሚያስደምሙበት፣ የቤትዎን ውበት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድጉ ጥራት ያላቸው የፈርኒቸር ውጤቶችን ይዘንላችሁ ቀርበናል። ያልነውን ካላገኙ ወረታውን እንከፍላለን! ✅ እስከ 40% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ (ለኪስዎ አዋጭ!) ✅ ለገዢዎች የሚሰጡ ነጻ ስጦታዎች🎅✨ ✨ ለምን እኛን ይመርጣሉ? •  ጥራት፡ ፈጽሞ በማንደራደርበት ጥራት ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉ ምርቶች። •  ዘመናዊነት፡ የቤትዎን ድምቀት የሚጨምሩ ከተራው ወጣ ያሉ ማራኪ ዲዛይኖች። •  ሰፊ አማራጭ፡ ከቱርክ በቀጥታ የገቡ (Imported) እና በሀገር ውስጥ በከፍተኛ ጥራት የተመረቱ ሶፋዎች፣ አልጋዎችና የቢሮ እቃዎች። •  ነጻ ትራንስፖርት፡ የገዙትን እቃ ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ እስከ ቤትዎ እናደርሳለን! 🚚 📍አድራሻችን፡- ከሜክሲኮ ወረድ ብሎ፣ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት፣ የድሮ ብስራት ኤፍ ኤም (Bisrat FM) ህንጻ። 📞 አሁኑኑ ይደውሉልን፡ 📱 0947555555 📱 0920753333 ሱፐር ኤስ ጂ ኤስ ፈርኒቸር - ለተመቻቸ ኑሮ! 🛋✨ 🎄 መልካም የገና በዓል! 🎄
Hammasini ko'rsatish...
24
" ከተሞቻችን ገበሬዎችን እያፈናቀሉ ድሃና ለማኝ እያደረጉ ነው " - ባጫ ከበደ (ዶ/ር) 🔴 " እንደሀገር ወጥ የሆነ የመሬት አስተዳደር ፖሊሲ የለንም "- አቶ ቱሉ በሻ " ላንድ ፎር ላይፍ ኢትዮጵያ " የተሰኘው ሀገር በቀል ተቋም " የመሬት አስተዳደርን ማጠናከርና የመሬት መብቶችን ማረጋገጥ " በሚል መሪ ቃል 3ኛው የኢትዮጵያ የመሬት ቀን የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል። በዚህ መድረክ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የኢትዮጵያ የሕዝብ አስተዳደር ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት፣ በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ባጫ ከበደ (ዶ/ር) እና በGIZ አፍሪካ ህብረት የመሬት አስተዳደር አማካሪ አቶ ቱሉ በሻ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በዚሁ ወቅት ባጫ (ዶ/ር) ፥ በሀገሪቱ የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ላይ የሚታዩ ስር የሰደዱ ችግሮችን በሚመለከት ጠንከር ያሉ ኃሳቦች አካፍለውናል። ባጫ ከበደ (ዶ/ር) በዝርዝር ምን አሉ ? " ከተሞቻችን ገበሬዎችን እያፈናቀሉ ድሃና ለማኝ እያደረጉ፣ በሀገሩ እንዳይኖር አድርገዋል። ይህ እኔንም ይሰማኛል፤ አዲስ አበባንም መመልከት ይቻላል፤ ሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ችግር አለባቸው። ይህን ችግር ለመቅረፍ ደግሞ መስዋዕትነት ያስፈልጋል። መሬት ለኢንቨስተሮች ስንሰጥ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ያቀፈ መሆን አለበት። አንድን ሰው ከመሬቱ ላይ አፈናቅሎ ሌላ ሰው ማምጣት ልክ አይደለም። ሰው ሀብት አያግኝ አይደለም፤ ነገር ግን የአካባቢው ማኅበረሰብ በልማት ውስጥ መቀናጀት አለበት፤ ይህ ከሆነ የመሬት ባለቤትነት በቀላሉ ይመጣል። ​ከመሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ጋር በተገናኘ ከሥርዓት ወደ ሥርዓት እየተወራረሱ የመጡ፣ አሁን ላይ ተደራራቢ የሆኑ ችግሮች አሉ። አክለውም በቴክኖሎጂ ሽግግር ምክንያት የመጡ ተግዳሮቶች አሉ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜም የመሬት አስተዳደር እና የተቋማዊ አሰራር ውስብስብነት እየጨመረ መጥቷል። ይሁንና ይህንን ችግር ለመቅረፍ በባለሙያው ዘንድ የአቅም ግንባታ ሥራዎች እየተሠሩ አይደለም፤ በትምህርት ደረጃ፣ በካሪኩለምና በምናስተምራቸው ትምህርቶች ላይ ክፍተቶች አሉ። ትምህርቶቹ ሀገራዊ ወይም ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘቡ አይደሉም። ​ሀገራችን የምትከተላቸው ሪፎርሞች ከቬትናም፣ ከቻይና፣ ከአሜሪካ እና ከእንግሊዝ የመጡ ወይም በቀጥታ የተቀዱ ናቸው። እነዚህ ነገሮች ቢስተካከሉ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን መቅረፍ ይቻላል። አሁን ላይ መንግሥት በፖሊሲ የፈቀደውን አሠራር ለሕዝቡ እስከ መከልከል ተደርሷል። መንግሥት ፈቅዶ አድርጉልኝ፣ መረጃ ስጡልኝ ብሎ 'አንሰጥም' የሚሉም አሉ። ይህን ለመከላከል መንግሥት ያለውን የመሬት ክምችት ማወቅ አለበት " ብለዋል። የመሬት አስተዳደር አማካሪው አቶ ቱሉ በሻ ምን አሉ ? "እንደሀገር ወጥ የሆነ የመሬት አስተዳደር ፖሊሲ የለንም። አሁን ላይ የመሬት ጉዳዮችን የሚነኩ የሴክተር ፖሊሲዎች ናቸው። የከተማ እና የገጠር መሬት አስተዳደር ተብሎ በመከፈሉ አንድ ወጥ የሆነ የመሬት አስተዳደር እንዳይኖር አድርጓል። ከጊዜ ወደ ጊዜ የገጠሩ ማህበረሰብ ቁጥር እየጨመረ ነው፣ ከተሞች እየተስፋፉ ነው፣ ወጣቱ መሬት የለውም፣ ስራ አጡ እየበዛ ነው፣ ስለዚህ መሬትን በዘላቂነት መጠቀም የሚያስችል ተቋማዊ አደረጃጀት እና አንድ ወጥ የሆነ የመሬት አስተዳደር ፖሊሲ ሊኖረን ይገባል " ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahethiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
884😭 66🙏 40👏 28🕊 22😡 16🥰 13😢 11💔 9🤔 8😱 5
#Update #Gambella " ከተርፋም የተላኩ ተጎጂዎች ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው። 50 ተጎጂዎች ልከውልናል ትናንት። ሁለቱ መንገድ ላይ ህይወታቸው አልፏል። 48ቱ ሆስፒታል ደርሰዋል " - ጋምቤላ ሆስፒታል ⚫️ " በአሁኑ ወቅት ትልቁ የተቸገርንበት የደም እጥረት ነው። አብዛኛዎቹ ተጎጂዎች ብዙ ደም እየፈሰሳቻው ነው! " በጋምቤላ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ወቅት ተጎድተው ህክምና ላይ ለሚገኙ ታካሚዎች የመድኃኒትና የደም እጥረት እንዳጋጠመው የጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ዛሬ ከሰዓት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። በአሁኑ ወቅት በሆስፒታሉ ብቻ ከ65 በላይ ታካሚዎች እንዳሉ አመልክቷል። በኃላፊነት ላይ የሚገኙ አንድ ሆስፒታሉ አካል በሰጡን ቃል፣ " እንደ ሆስፒታል በከተማው ውስጥም እንቅስቃሴ ስለሌለ መድኃኒት ለማግኘት ተቸግረናል " ሲሉ ገልጸዋል። " የመድኃኒት እጥረት አለ ፤ ከተለያዩ ቢሮዎች እና አጋር ድርጅቶች ጋር በመነጋጋር እርዳታ እንዲያደርግልን ጠይቀን እየጠበቅን ነው " ሲሉ ተናግረዋል። የምን አይነት መድኃኒት እጥረት አጋጠማችሁ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ " አንድ ተጎጂ ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስበት በተለይ በጥይት የተመታ ሲሆን የሚያስፈልጉ የስቃይ፣ የኢንፌክሽን መከላከያ (አንቲባየቲክስ) የሚባሉ መድኃኒቶች፣ የሚፈሰውን ደም ለማስቆም የሚረዱ መድኃኒቶች እጥረት በዋናነት አጋጠሞናል " ብለዋል፡፡ " በአሁኑ ወቅት ትልቁ የተቸገርንበት የደም እጥረት ነው። አብዛኛዎቹ ተጎጅዎች ብዙ ደም እየፈሰሳቻው ነው። በክልሉ ደም ባንክ አቅርቦት አልነበረም። ስለዚህ ከብሄራዊ ደም ባንክ የተወሰነ ደም እንዲልኩልን ጠይቀናል" ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡ ታዲያ የጠየቃችሁት የደም ድጋፍ ተልኮላችኋል ? የሚያስፈልጋችሁስ ምን ያክል ነው ? ለሚለውን ጥያቄም፣ " እስካሁን አልተላከልንም እስከ ነገ እንልካለን እያሉ ነው። ቢያንስ ከ100 ዩኒት በላይ ደም ቢሰጡን የተሻለ ነው፣ ቢያንስ እስከ 100 ዩኒት ያስፈልገናል። ምክንያቱም አንድ ተጎጅ ብቻ ብዙ ደም ስለሚፈሰው እስከ አምስት ዩኒት ሊጠቀም ይችላል " ሲሉ መልሰዋል። ከመድኃኒት እጥረት ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ሲያስረዱም፣ " አሁንም ሆስፒታሉ እየተሯሯጠ ነው ያለው " ያሉ ሲሆን፣  በተለይ ከደም መፍሰስ ጋር በተያያዘ የሚያስፈልገው " የፍሉድ መድኃኒት " ችግር በመኖሩ የክልሉ ጤና ቢሮ እንዲልክላቸው መጠየቃቸውን ገልጸዋል። በሌላ በኩል በክልሉ በሚገኘው ኝንኛንግ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰሩ ሀኪም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ሀኪሙ ከትላንት ወዲያ በኢታንግ ልዩ ወረዳ በነበረው ተኩስ የተጎዱ ከ50 በላይ ሰዎች ወደ ጋምቤላ የመጀመሪያ ሆስፒታል ሪፈር እንደተደረጉ ገልጸዋል። መንገድ ዝግ በመሆኑ ወደ እነርሱ ተቋም የሄዱት ሁለት ተጎጅዎች እንደሆኑ አስረድተዋል። ከተርፋም በፊት በነበረው ጥቃት ጭምር 10 ሰዎች በሆስፒታሉ መታከማቸውን፣ ባለፈው ሳምንት ወደ ጅማ ሪፈር ተጽፎላቸው የነበሩ ሦስት ተጎጅዎችም ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ተብለው ገና በህክምና ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ከትናንት ወዲያ በኢታንግ ልዩ ወረዳ (ተርፋም ቀበሌ) በነበረው ተኩስ የተጎዱ ስንት ታካሚዎች ወደ ሆስፒታሉ መጥተዋል ? ሲንል የጠየቃቸው የጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አካል በበኩላቸው፣ " ከተርፋም የተላኩ ተጎጅዎች ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው። ወደ 50 ተጎጅዎች ልከውልናል ትናንት " ብለዋል። " ከእነዚህ መካከል ሁለቱ መንገድ ላይ እያሉ ሕይወታቸው አልፏል። 48ቱ ናቸው ሆስፒታል የደረሱት፡፡ አሁን ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ። 48ቱ ሁሉም ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው " ሲሉ አክለዋል። ከተርፋም ተኩስ በፊትም በተለያዩ ወረዳዎች ተኩስ እንደነበር ይታወቃል፣ በዚያ ወቅት በአጠቃላይ ምን ያክል ተጎጅዎች ናቸው ወደ ሆስፒታሉ መጥተው ህክምና ያገኙት ? ለሚለው ጥያቄ፣ " በየጊዜው መንገድ ላይ ባስ፣ የሆስፒታል አውምቡላንስ ላይ ጭምር ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ነበሩ " ብለዋል፡፡ " በሌላ ተቋም ሪፖርት የሚደረጉ አሉ " የሚሉት የሆስፒታሉ አመራር፣ የጋምቤላ የመጀመሪያ ሆስፒታል ቀጥታ ሪፖርት ማድረግ በሚችለው ብቻ ከተርፋሙ ግጭት በፊት ወደ ሆስፒታሉ 22 ቁስለኞች እንደሄዱ፣ 10 በመንገድ ላይ እንደሞቱ፣ በሌሎች ተቋማት ሪፖርት ከሚደረጉት ጋር ሲሆን ወደህክምና ያቀኑ ቁስለኞች ቁጥር ከዚህ ከፍ እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡ በተርፍም ጥቃት ወደ ሆስፒታሉ ለህክምና ከሄዱት 48 ተጎጅዎች በተጨማሪ በፊተኛው ጥቃት ለህምክና ወደ ጋምቤላ ሆስፒታል የሄዱ 18 ተጎጅዎች አሁንም በሆስፒታሉ እንዳሉም አመራረሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። በመድኃኒት እጥረት ወይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አጋጥሟቸው እንደሆነ ስንጠይቃቸውም፣ " አንድ ተጎጁ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ ህይወታቸው አልፏል " ብለዋል። በተኩሱ የቆሰሉት ሴቶችና ህፃናት ጭምር መሆናቸውን፣ በሆስፒታሉ ሦስት ሴቶችና አንድ ህፃን፣ በሌሎች ተቋማትም በርካቶች እንዳሉ ገልጸዋል። "የተዘጋው መንገድ መከፈት አለበት። እኛ የመጡትን ተጎጂዎች አብዛኞቻቸው ዘግይተው ነው የደረሱት። አንድ በሽተው ቁስል ካለበት ኢንፌክሽን ሳይፈጥርበት ነው መታከም ያለበት። ነገር ግን መንገድ በመዘጋቱ ቁስለኞች አብኞቻቸው ኢንፌክሽን ከፈጠረባቸው በኋላ ነው የተላኩት" ሲሉም ገልጸዋል። በጋምቤላ ሆስፒታል ያጋጠመውን የመድኃኒት እና የደም እጥረት ለመፍታት ምን እንደተደረገ እንሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚመለከታቸው ተቋማትን የሚጠይቅ ይሆናል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahethiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
293😭 109🕊 21😢 7😡 4🙏 1
እስራኤል ለሶማሊላንድ የሃገርነት እውቅና ሰጥታለች። በዚህም ለሶማሊላንድ የሃገርነት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሃገር ሆናለች። ላለፉት 30 አመታት የሃገርነት እውቅና ለማግኘት ጥረት ላይ የነበረችው የነበረችው ሶማሊላንድ በመጨረሻም ሙከራዋ ተሳክቶ ከእስራኤል የሃገርነት እውቅና አግኝታለች። የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር እስራኤል እና ሶማሊላንድ የሙሉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን ለመጀመር፣ አምባሳደሮችን ለመመደብና ኤምባሲዎችን ለመክፈት መስማማታቸውን አስታውቀዋል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኔያሁ ከሶማሊላንዱ ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን እውቅናው ታሪካዊ ነው ብለውታል። ኔታኔያሁ ዛሬ ሶማሊላንድን እንደ ነፃ እና ሉዓላዊ ሃገር እውቅና መስጠታቸውን አውጀዋል። እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና የሰጠችው አመት ከፈጀ ንግግር በኋላ መሆኑንም አስታውቃለች። እስራኤል እውቅናውን የሰጠችው በፕሬዚዳንት ትራምፕ አነሳሽነት በተረቀቀው የአብርሃም ስምምነት አማካኝነት መሆኑ ተገልጿል። እነማን ተቃወሙ ? ሶማሊያ ፦ የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ሶማሊላንድ አንዷ የሶማሊያ አካል መሆኗን በመግለፅ የእስራኤልን ውሳኔ ተቃውማለች። የሀገሪቱ ግዛታዊ አንድነት እንዲከበር አሳስባለች። ግብፅ ፦ ግብፅ ከሌሎች ጋር በመሆን እስራኤል የሰጠችውን እውቅና ተቃውማለች። የሶማሊያ አንድነት እና ሉዓላዊነት እንዲከበር አስገንዝባለች። ቱርክ ፦ ቱርክ የእስራኤልን ውሳኔ ተቃውማለች። ጅቡቲ ፦ ጅቡቲም የእስራኤልን ውሳኔ በመቃወም ከግብፅ ፣ ቱርክ እና ሶማሊያ ጋር በመሆን መግለጫ አውጥታለች። @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
star reaction 3👏 822 509😡 74🤔 56🕊 18🙏 16😭 15🥰 11😢 3
"በአንዳንድ ቦታዎች መንገድ አጥረው ሲያበቁ ሰዎች ለማለፍ ሲሄዱ በዚህ በኩል እንዴት ትመጣለህ ተብሎ የሚደበደብባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ከህብረተሰቡ ይሰማል" - አቶ ኢያሱ ሰለሞን "መንገድ የሚያጥሩ አካላት ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምንም መንገዱ ለተገነባለት ዓላማ ጥቅም እንዳይውል ማደረግ ህገወጥ ድርጊት ነው"! የከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ያጠሩ ሰዎች ምክንያታቸው ምንም ቢሆን ማጠራቸው ተቀባይነት እንደሌለው፣ መጠኑ የተለያዩ ቢሆንም በሁሉም አካባቢዎች መንገዶች እንደታጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ። የባለልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኢያሱ ሰለሞን፣ "የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥሮ መዝጋት በስፋት እየተከናወነ ያለ ህገወጥ ድርጊት" መሆኑን፣ አጥሩ እንዲነሳ መልዕክት ሲያስተላልፍ ቢቆይም፣ "ከመሻሻል ይልቅ የመስፋፋት አይነት አስማሚያዎች" መታየታቸውን ገልጸው፣ ባለስጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን አጥሮቹን የማፍረስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ሰዎች የውስጥ ለውስጥ መንገድ ያጠሩበት ምክንያት ምን እንደሆነ ጠይቃችሁ ነበር? ምክንያታቸው አሳማኝ ከሆነ መፍትሄ አስቀምጣችኋል? ከዚህ በፊት የታጠሩ መንገዶችን አጥር የማንሳት ሥራ ተጀምሮ ነበር፤ ለምን ተቋርጦ ቆዬ? ሲል ለአቶ ኢያሱ ጥያቄ አቅርቧል። ኃላፊው ምን መለሱ? "ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምንም መንገዶች በከተማዋ መዋቅራዊ ፕላን መሰረት ሲገነቡ ደረጃቸው ይለያይ እንጂ ትራፊክ ለማሳለጥ ተብለው ነው። የእግረኛውንም የተሽከርካሪውንም እንቅስቃሴ በተገቢው ሁኔታ ለማስተናገድ ነው መንገዶች የሚከፈቱት ከዚህ ውጭ ሌላ ዓላማ የላቸውም። ስለዚህ መንገድ የሚያጥሩ አካላት ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምንም መንገዱ ለተገነባለት ዓላማ ጥቅም እንዳይውል ማድረግ ህገወጥ ድርጊት ነው። ምክንያት የሚለው ነገር ምንም አሳማኝነት ሊኖረው አይችልም። ሰው መንገድ ላጠረበትን ምክንያት የተለያዩ ጉዳይ ሊያነሳ ይችላል፤ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምንም ግን በከተማዋ መዋቅር ለመንገድ የተተወ ቦታ የመንገድ አገልግሎት እንዲሰጥበት ነው። ያ ማለት ደግሞ በአንድ አካባቢ ለሚኖሩ ብቻ የተፈቀደ ሳይሆን የሁሉም ህብረተሰብ የጋራ መጠቀሚያ ነው። አንዳንድ ቦታዎች ላይ መንገድ አጥረው ሲያበቁ ሰዎች ለማለፍ በአካባቢው ሲሄዱ በዚህ በኩል እንዴት ትመጣለህ ተብሎ የሚደበደብባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ከህብረተሰቡ ይሰማል። የመንገድ አካል ስለሆነ ለግንባታ ፈቃድ ስለማይሰጥበት የግል ይዞታ አድርጎ ለማካተት ስለማይሞከር እንጅ፣ የመጋዘን በር የሚመስል፣ ሰው እንኳን ወደ ውስጥ ማለፍ አይደለም ማየት የተከለከለበት እስኪመስል ድረስ አጥር የሚታጠርባቸውም ሁኔታዎች አይተናል። ድርጊቱ ያልተገባ ነው መስተካከል አለበት" ብለዋል። አጥር ማንሳቱ ተቋርጦ መቆየቱን በተመለከተ በሰጡን ምላሽ ደግሞ፣ "በተለያዩ ጊዜያት ሥራዎቹን ለመቀጠል ተሞክሯል። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ ነበር። ምክንያቶቹን ለመጥቀስ እቸገራለሁ። ተቋርጦ ቢቆይም አሁን መጀመሩ ትክክል ነው" ብለዋል። የውስጥ ለውስጥ መንገዶች መታጠር ስላስከተለው ጉዳት አቶ ኢያሱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ? "ሁሉም ማህበረሰብ በእኩልነት የመጠቀም መብትን ስለሚጋፋ በሰው፣ በትራፊክ እንቅስቃሴው አሉታዊ ተፅዕኖ አምጥቷል። መንገዶች ሲዘጉ በሌሎች መንገዶች ተሽከርካሪዎች ተጨናንቀው ይጓዛሉ፣ ይህም ለትራፊክ አደጋ ተጽዕኖ አሳድሯል። በአደጋ ጊዜ የአደጋ እርዳታ ለማድረስ የእሳት አደጋ፣ የአምቡላንስ እንቅስቃሴ ገድቧል። የከተዋማ ገጽታም ላይ የፈጠረው ችግር አለ" ብለዋል። ይህን ከግምት በማስገባት በመጀመሪያ መንገዶችን የዘጉ አካላት እንዲያነሱ የጊዜ ገደብ ሰጥቶ መልዕክት መተላለፉን የገለጹት አቶ እያሱ፣ "በተሰጠው የ7 ቀናት የጊዜ ገደብ ውስጥ የተወሰኑ ፈቃደኛ ሰዎች በራሳቸው ፈቃድ ያነሱ አሉ፣ ግን አብዛኛው ቦታ ላይ ብዙ ለውጥ አላየንበትም" ሲሉም ተናግረዋል። ስለዚህ ከትላንት ጀምሮ የማንሳት ሥራውን እያከናወኑ እንደሆነ በማስረዳት፣ "ችግሩ አንድ ቦታ ላይ የሚገልጽ አይደለም፤ ስፋትና ጥልቀቱ ቢለያይም በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች ተመሳሳይ ችግሮች አሉ" ብለው፣ "ይህን ለማተካከል ባለፉት ሳምንታት ባለድርሻ አካላት ጠርተን በጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ የጋራ ውይይት ተደርጎበታል" ነው ያሉት። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
1 055👏 253🥰 20🙏 20🕊 17😡 13💔 10😭 10🤔 8😱 2😢 1
🎄 የገና በዓል ልዩ የቅናሽ ከስጦታ ጋር ከሱፐር ኤስ ጂ ኤስ! 🎁 በዚህ ገና እንግዶችዎን የሚያስደምሙበት፣ የቤትዎን ውበት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድጉ ጥራት ያላቸው የፈርኒቸር ውጤቶችን ይዘንላችሁ ቀርበናል። ያልነውን ካላገኙ ወረታውን እንከፍላለን! ✅ እስከ 40% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ (ለኪስዎ አዋጭ!) ✅ ለገዢዎች የሚሰጡ ነጻ ስጦታዎች 🎅✨ ✨ ለምን እኛን ይመርጣሉ? •  ጥራት፡ ፈጽሞ በማንደራደርበት ጥራት ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉ ምርቶች። •  ዘመናዊነት፡ የቤትዎን ድምቀት የሚጨምሩ ከተራው ወጣ ያሉ ማራኪ ዲዛይኖች። •  ሰፊ አማራጭ፡ ከቱርክ በቀጥታ የገቡ (Imported) እና በሀገር ውስጥ በከፍተኛ ጥራት የተመረቱ ሶፋዎች፣ አልጋዎችና የቢሮ እቃዎች። •  ነጻ ትራንስፖርት፡ የገዙትን እቃ ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ እስከ ቤትዎ እናደርሳለን! 🚚💨 📍 አድራሻችን፡- ከሜክሲኮ ወረድ ብሎ፣ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት፣ የድሮ ብስራት ኤፍ ኤም (Bisrat FM) ህንጻ። 📞 አሁኑኑ ይደውሉልን፡ 📱 0947 55 55 55 📱 0920 75 33 33 ሱፐር ኤስ ጂ ኤስ ፈርኒቸር - ለተመቻቸ ኑሮ! 🛋✨ 🎄 መልካም የገና በዓል! 🎄
Hammasini ko'rsatish...
93🙏 2🕊 2😭 1
Photo unavailableShow in Telegram
✨🎁 አየር ሰአትና ጥቅል ከውጭ አገራት ይቀበሉ፤ 50% ተጨማሪ የበዓል ስጦታ ያግኙ!! ከውጭ ሀገራት በአጋሮቻችን ✅ Ethio remit        ✅ EZECALL ✅ Prepaynation    ✅ ding ✅ reloady              ✅ Omnivas ✅ Boss በኩል ከ150 ብር ጀምሮ የተላከልዎን የሞባይል አየርሰዓት ወይም ጥቅል ሲቀበሉ:- 💁‍♂️ ለ15 ቀናት የሚያገለግል የ50% ተጨማሪ ስጦታ እናበረክትልዎታለን፡፡ ደንብና ሁኔታዎች 👉 https://bit.ly/4j7iOcI #Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
Hammasini ko'rsatish...
114🕊 4😭 2💔 1
" የቀን ወጫችን 3 ሚሊዮን ብር ሆኗል" - የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ ➡️ " በጤና ዙሪያ የጤና ባለሙያዎችን እገዛ እንፈልጋለን። መቄዶንያ ውስጥ ከ2500 በላይ የአዕምሮ ህሙማን ከ3000 በላይ የአልጋ ቁራኛ የሆኑ አሉ ! " መቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና አረጋዊያን መርጃ ማዕከል በየቀኑ 3 ሚሊዮን ብር ለማውጣት በመገደዱ፣ ያስጀመረው ሆስፒታል ባለመጠናቀቁ፣ በየክልል ከተሞች አዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈቱ ለጋሽ እጆች የተለመደ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉለት ጠይቋል። ዛሬ ባካሄደው የውይይትና የምስጋና ፕግራም፣ ባለፈው አመት በርካቶች እንደተረባረቡበት አይነት በቀጥታ ስርጭት ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ የፊታችን የካቲት 1 2018 ዓ/ም እንደሚካሄድ ገልጿል። እስከዚያው ሁሉም መረጃውን በማዳረስ፣ መረጃውን የሚሰሙ ከወዲሁ ተዘጋጅተው የአቅማቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ማዕከሉ ጥሪ አቅርቧል። የካቲት 1/2018 ዓ/ም ገቢ የማሰባሰብ ሥራ ከባለፈው አመት የሚለየው በአሁኑ በመቄዶንያና በማንኛውም የግለሰቦች ዩቱብ በቀጥታ ስለሚተላለፍ መሆኑን የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ ገልጸዋል። በዛሬ መርሃግብር የተገኘው ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ በበኩሉ፣ ባለፈው ዓመት የተሰባሰበ ገቢ ነበር፣ በግንባታ ላይ ያለው የሆስፒታል ህንፃ ከምን ደረሰ? አሁን የሚጎድላችሁ ነገር ምንድን ነው ? ሲል ጠይቋል። የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን መለሱ ? " ባለፈው ትልቅ የገቢ ማሰባሰቢያ አድርገን ወደ 900 ሚሊዮን ብር ሰብስበናል። 100 ቤቶች (ድጋፍ ተደርጓል)። እየተሰራ ያለው ህንፃው ግዙፍ ህንፃ ነው፤ ሆስፒታል ነው። ወጩ ብዙ ነው። አሁን ጤና ጥበቃ የሰጠን ፊገር አለ ወደ 6 ቢሊዮን ነው የሚፈጀመው ከእነኢኩፕመንት አሟልቶ ወደ ስራ ለማስገባት። አሁን ፎቁን ለመጨረስ በጣም ትንሽ ነው የቀረን። ብር እንዲሰባሰብ የፈለግነው ሆስፒታሉን ለመጨመረስ፤ በየክልሎች ለጨመርናቸው 12 ቅርንጫፎች ብዙ ኮንስትራክሽን ስላሉ ለመስራት ነው። አስጨርሶ ሰው ለማስገባት ነው፤ ፎቁን ብቻ መጨረስ ሳይሆን ፈርኒቸርም አሟልተን ለሰዎች ዝግጁ ማድረግ ነው የቀረን። አዲስ የተከፈቱት ቅርጫፎች ፦ - ቀብሪድሃር፣ - ሞያሌ፣ - ኮንሶ፣ - ዓዲግራት፣ - ዓድዋ፣ - አምቦ፣ - ጅማ፣ - ሞያሌ...በመሳሰሉት ቦታዎች የሚገኙ ነው። የተጀመሩ ህንፃዎችን እየሰራን ነው ቀብሪድሃር፣ አርባምንጭ፣ ላሊበላ እነርሱን መጨረስ አለብን። ወጫችን ብዙ ነው፤ 56 ቦታ ሰዎችን ማኖር ማለት ነው። ቋሚ ገቢ የውጭ ፈንድ የሌለው፣ በቀን 3 ሚሊዮን ብር ወጭ ያለበት ማዕከል ነውና በጣም ከባድ ነው " ብለዋል። ከህክምና አኳያ ችግር ካለ ስንጠይቃቸውም፣ የአዕምሮ ህሙማኑና አረጋዊያኑ ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸው፣ " የጤና ባለሙያ፣ የፊዚትራፒ፣ ነርሶች፣ ዶክተሮች እንፈልጋለን። በግል ሆስፒታሎች ያሉት በሳምንት አንዴ ቢረዱን በጣም ትልቅ እገዛ ነው። ትልቁ ነገር ህክምና ነው። የአልጋ ቁራኛ የሆነ ሰው የሚያስፈልገው ህክምና ነው " ብለዋል። " በጤና ዙሪያ የጤና ባለሙያዎችን እገዛ እንፈልጋለን። መቄዶንያ ውስጥ ከ2500 በላይ የአዕምሮ ህሙማን ከ3000 በላይ የአልጋ ቁራኛ የሆኑ አሉ። ሌላው አረጋዊ፣ አካል ጉዳተኛ ነው" ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። የመቄዶንያ ወጭ በቀን 2 ሚሊዮን መሆኑን ማዕከሉ ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል፤ አሁን ወጩ በምን ምክንያት እንደጨመረ ቲክቫህ የጠየቃቸው ቢንያም (የክብር ዶ/ር)፣ በአመት ውስጥ ብቻ አዳዲስ ቅርንጫፎች በመከፈታቸው መሆኑን በመጥቀስ አስረድተዋል። የማዕከሉ የቀን ወጭ 3 ወደ ሚሊዮን ብር ከፍ ማለቱን፣ በተለይ በአዳዲሶቹ ብራንቾች ብዙ ስራዎች እንዳሉባቸው ገልጸው፣ ሰዎች በማዕከሉ ስልክ ቁጥር 09432020 እየደወሉ እንዲጎበኟቸው፣ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
3 354🙏 379💔 88🤔 45😭 38😡 35🕊 30🥰 16😢 11😱 7👏 2