uz
Feedback
TIKVAH-ETHIOPIA

TIKVAH-ETHIOPIA

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
1 572 371
Obunachilar
-46024 soatlar
-1 9487 kunlar
-3 00530 kunlar
Postlar arxiv
#NewsAlert🚨 #Gambella የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ ! የጋምቤላ ከተማን ጨምሮ የፀጥታ ችግር በሚስተዋልባቸው የክልሉ አካባቢዎች ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ። የጋምቤላ ክልል መንግስት ከዛሬ ጀምሮ ከምሽት 2 :00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 :00 ሰዓት ከተፈቀደላቸው አካላት ውጪ ማንኛውም ሰው ሆነ ተሽከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥሏል። ሰሞኑን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት የሰዓት እላፊ ገደቡ መጣሉን የገለጸው ክልሉ ይህም ላልተወሰነ ጊዜ ተግባራዊ ሆኖ የሚቀጥል ነው ብሏል። ከዛሬ ጀምሮ ከተመደቡ የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ተሽከርካሪ ሆነ ሰው መንቀሳቀስ ተከልክሏል። ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጪ የትኛውም ቦታ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ተገልጿል። ሁሉም ይህንን ትዕዛዝ እንዲፈጽም ማሳሰቢያ ተላልፏል። #TilvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
629🕊 63👏 61🙏 36😭 36🥰 15😡 15🤔 13
የአውሮፓ የፀረ ደን ምንጣሮ ደንብ (EUDR) መራዘሙ ለኢትዮጵያ ቡና ዘርፍ ምን ትርጉም አለው ? የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ ከሁለት ዓመት በፊት ያፀደቀውን የፀረ ደን ምንጣሮ ደንብ (EUDR) ትግበራ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ማራዘሙን አስታውቋል። ደንቡ ከቀጣዩ ታኅሣሥ 21/2018 ዓ.ም ጀምሮ ይተገበራል ተብሎ ቢጠበቅም፣ አሁን በተወሰነው መሠረት ለአነስተኛና ጥቃቅን አምራቾች የ1 ዓመት ከ6 ወር፣ ለከፍተኛ ኩባንያዎች ደግሞ የ1 ዓመት የዝግጅት ጊዜ ተሰጥቷል። የአውሮፓ ኅብረት ፀረ ደን ምንጣሮ ደንብ (EUDR) ምንድን ነው? ከኢትዮጵያ ጋር ምን አገናኘው? EUDR ወደ አውሮፓ የሚገቡ ምርቶች ለደን ጭፍጨፋ እና ለደን መመናመን አስተዋፆ አለማድረጋቸውን ለማረጋገጥ የወጣ ደንብ ነው። ይህ ደንብ የኢትዮጵያን ዋነኛ የውጪ ንግድ ምርት የሆነውን ቡናን ጨምሮ ሰባት ምርቶች (ከብት፣ ካካዋ፣ የፓልም ዘይት፣ አኩሪ አተር፣ እንጨትና ራበር) ላይ ያነጣጠረ ነው። በደንቡ መሠረት ከታኅሣሥ 22/2013 ዓ.ም ወዲህ በደን ምንጣሮ የተገኙ ምርቶች ወደ አውሮፓ መግባት አይችሉም፤ ጥሳቱ ከተገኘም ኩባንያዎቹ ከባድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ኢትዮጵያ ከጠቅላላ የቡና ምርቷ 40 በመቶ የሚሆነውን ወደ አውሮፓ የምትልክ በመሆኗ ደንቡ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አለው። የኢትዮጵያ ቡና ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግዛት ወርቁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ፥ "ደንቡ በቀኑ ተፈፃሚ ቢሆን ኖሮ እነሱም ቡናውን ሊያጡት ይችላሉ፣ እኛም መስፈርቱን አሟልቶ ማቅረብ ይከብደን ነበር" ብለዋል። የማረጋገጫ ሂደቱ እና የቴክኖሎጂው ፈተና የቡና ምርቱ ከደን ምንጣሮ ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ Geolocation የተሰኘ በጂፒኤስ (GPS) እና በሳተላይት የታገዘ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ መዋል ይኖርበታል። ይህ ሂደት ግን ለኢትዮጵያ ከባድ እንደሆነ ባለሙያዎች ይስማማሉ። የአቶ ግዛት ወርቁ"6 ሚሊዮን አርሶ አደር ማሳ ላይ ቆመህ ጂኦሎኬት ማድረግ ብቻ እንኳ ከፍተኛ ወጪና ጊዜ የሚጠይቅ ሥራ ነው" በማለት የሥራውን ስፋት ያስረዳሉ። ሌላው የዘርፉ ባለሙያ አቶ ዳንኤል ዘረዓ ያዕቆብ በበኩላቸው "እንደ ብራዚልና ቬትናም በትልልቅ እርሻ ሳይሆን በየቦታው በተበጣጠሰ ማሳ ላይ ለሚመረት የኢትዮጵያ ቡና፣ እያንዳንዱን ማሳ ኦዲት አድርጎ ዳታ ቤዝ ውስጥ ማስገባት ከፍተኛ የቴክኒክ ሥራ፣ የሰው ኃይል እና የገንዘብ አቅም ይጠይቃል" ብለዋል። እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች እና የመራዘሙ ጥቅሞች ምንም እንኳ ፈተናው ከባድ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን መረጃ የሚተላለፍበት ሞባይል መተግበሪያ (App) ማዘጋጀቱንና ትልልቅ ማኅበራት (ዩኒየኖች) ጂኦሎኬት የማድረግ ሥራ መጀመራቸውን አቶ ግዛት ጠቅሰዋል። “መስፈርቱን ለማሟላት የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች በ2025 (በፈረንጆች አቆጣጠር) ሲለፉ ነው የቆዩት። ጂኦሎኬት ማድረግን ጨምሮ የቻሉትን ያህል ሄደዋል። ትላልቆቹ ኮሜርሻል ፋርሞችም እየሰሩ ነው።. . . ጂኦሎኬት ተደርጎ ለአውሮፓ ህብረት ገበያ ዝግጁ የሆኑ አሉ። የኦሮሚያ፣ የሲዳማና የይርጋጨፌ ዩኒየኖች የራሳቸወን ጥረት ሲያደርጉ ነው የቆዩት” ብለዋል። የደንቡ መራዘም የሚሰጠው ጥቅም ይኖር ይሆን ? አቶ ግዛት፥ "አሁን ቢጀመር ኖሮ ለአውሮፓ ቡና ለመሸጥ እንቸገር ነበር፤ መራዘሙ በትክክል ጠቅሞናል" ሲሉ ጥቅሙን አስረድተዋል። 40 በመቶ ትንሽ አይደለም አይደለም የሚሉት አቶ ግዛት  የአውሮፓን መስፈርት ለማሟላት ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን ሰሜን አፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ ያሉ አማራጭ ገበያዎችን ለማየት ጊዜ ይሰጣል ብለዋል። አቶ ዳንኤል በበኩላቸው፥ ልክ እንደ አረንጓዴ አሻራ ሁሉ መንግሥት በሀገር ደረጃ የቡና ማሳዎችን ዳታ ቤዝ በማደራጀት ረገድ ከፍተኛ እገዛ ሊያደርግ ይገባል የሚል ሀሳብ አንስተዋል። የአውሮፓ ኅብረት የወሰደው የመራዘም ውሳኔ ለኢትዮጵያ ቡና ኤክስፖርት ትልቅ "የትንፋሽ ጊዜ" የሰጠ ሲሆን፣ በቀጣዩ አንድ ዓመት ውስጥ ግን የተቀመጡትን የቴክኖሎጂ መስፈርቶች አሟልቶ መገኘት ለዘርፉ ህልውና ወሳኝ ሆኖ ቀጥሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TilvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
498👏 27🤔 8😡 7😢 3🥰 2😭 2🕊 1
#Gambella🚨 በጋምቤላ ክልል ፤ ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ፑልኮት / ተርፋም አካባቢ (ወደ ደቡብ ሱዳን ድንበር) ዛሬ ኃይለኛ ግጭት ሲካሄድ እንደዋለ፤ በዚህም የሰዎች ህይወት መጥፋቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጋምቤላ ቤተሰቦቹ ሰምቷል። ዛሬ በአካባቢው ያለው ሁኔታ እንደሚያስፈራ የገለጹልን ነዋሪዎች የፌዴራል መንግሥት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈልግ አሳስበዋል። በአንድ ቀበሌ ብቻ የበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋቱን አመልክተዋል። ቤቶችም ሲቃጠሉ እንደዋሉ ጠቁመዋል። ለስራ ጉዳይ ከጋምቤላ ከተማ 120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኚኛንግ እንዳለ የገለጸልን አንድ የቤተሰባችን አባልም የግጭቱን አሳሳቢነት ገልጾልናል። መሄጃም ይሁን መምጫ መንገድ መዘጋቱን በመጠቆም ስጋት ላይ መውደቃቸውን አስረድቷል። ግጭቱ እንዲበርድ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግ እንዲሁም ወደ ጋምቤላ ከተማ የሚወጡበት መንገድ እንዲመቻችላቸው ጠይቋል። በጋምቤላ ከተማ እና ዙሪያው በሌሎችም ቦታዎች ሰሞነኛው ግጭት በአገር መከላከያ እና ፌዴራል ፖሊስ እንዲረጋጋ ቢደረግም በኢታንግ ልዩ ወረዳ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል። #TilvahEthiopiaFamily @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
😭 239 237🕊 33🙏 12😡 10😢 6🥰 3😱 2💔 2
#HopeOncology በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የካንሰር ህክምና ብቻ የሚሰጥ ማዕከል የሆነው Hope Oncology 2ተኛ አመት የአገልግሎት ዘመኑን እያከበረ ይገኛል። ይህም በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ ያለውን የህፃናት እና የአዋቂ የካንሰር ህመም የተለየ ትኩረት አጊኝቶ የተሻለ ህክምና እና እንክብካቤ ታካሚዎች እንዲያገኙ ያስቻለ ሲሆን ከሚሰጣቸውም አገልግሎቶች ውስጥ የኬምቴራፒን እና አስተኝቶ ማከምን ጨምሮ 7ቱንም ቀን 24 ሰአት የካንሰር ህክምና ላይ ልምድ ባላቸው ስመጥር ሀኪሞች አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል። በቅርቡ አለም አቀፍ የቀዶ ጥገና ሀኪሞችን በማካተት የካንሰር ቀዶ ጥገና ህክምናን በሀገር ውስጥ ለማስጀመር እየተዘጋጀ ሲሆን ይህም ታካሚዎች ወደ ውጪ ሀገር መጓዝ ሳያስፈልጋቸው የላቀ የካንሰር ቀዶ ህክምና አገልግሎት በሀገር ውስጥ ማግኘት እንዲችሉ ያደርጋል። አድራሻ:-  ጦር ሀይሎች ከሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን 200 ሜትር ዝቅ ብሎ ኢብራሂም ህንፃ ፊት ለፊት ☎️ ስልክ:- 0916363738 / 0973555566
Hammasini ko'rsatish...
371👏 73🙏 23😭 11🕊 5😡 4😢 2
የአውሮፓ የፀረ ደን ምንጣሮ ደንብ (EUDR) መራዘሙ ለኢትዮጵያ ቡና ዘርፍ ምን ትርጉም አለው ? የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ ከሁለት ዓመት በፊት ያፀደቀውን የፀረ ደን ምንጣሮ ደንብ (EUDR) ትግበራ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ማራዘሙን አስታውቋል። ደንቡ ከቀጣዩ ታኅሣሥ 21/2018 ዓ.ም ጀምሮ ይተገበራል ተብሎ ቢጠበቅም፣ አሁን በተወሰነው መሠረት ለአነስተኛና ጥቃቅን አምራቾች የ1 ዓመት ከ6 ወር፣ ለከፍተኛ ኩባንያዎች ደግሞ የ1 ዓመት የዝግጅት ጊዜ ተሰጥቷል። የአውሮፓ ኅብረት ፀረ ደን ምንጣሮ ደንብ (EUDR) ምንድን ነው? ከኢትዮጵያ ጋር ምን አገናኘው? EUDR ወደ አውሮፓ የሚገቡ ምርቶች ለደን ጭፍጨፋ እና ለደን መመናመን አስተዋፆ አለማድረጋቸውን ለማረጋገጥ የወጣ ደንብ ነው። ይህ ደንብ የኢትዮጵያን ዋነኛ የውጪ ንግድ ምርት የሆነውን ቡናን ጨምሮ ሰባት ምርቶች (ከብት፣ ካካዋ፣ የፓልም ዘይት፣ አኩሪ አተር፣ እንጨትና ራበር) ላይ ያነጣጠረ ነው። በደንቡ መሠረት ከታኅሣሥ 22/2013 ዓ.ም ወዲህ በደን ምንጣሮ የተገኙ ምርቶች ወደ አውሮፓ መግባት አይችሉም፤ ጥሳቱ ከተገኘም ኩባንያዎቹ ከባድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ኢትዮጵያ ከጠቅላላ የቡና ምርቷ 40 በመቶ የሚሆነውን ወደ አውሮፓ የምትልክ በመሆኗ ደንቡ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አለው። የኢትዮጵያ ቡና ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግዛት ወርቁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ፥ "ደንቡ በቀኑ ተፈፃሚ ቢሆን ኖሮ እነሱም ቡናውን ሊያጡት ይችላሉ፣ እኛም መስፈርቱን አሟልቶ ማቅረብ ይከብደን ነበር" ብለዋል። የማረጋገጫ ሂደቱ እና የቴክኖሎጂው ፈተና የቡና ምርቱ ከደን ምንጣሮ ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ Geolocation የተሰኘ በጂፒኤስ (GPS) እና በሳተላይት የታገዘ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ መዋል ይኖርበታል። ይህ ሂደት ግን ለኢትዮጵያ ከባድ እንደሆነ ባለሙያዎች ይስማማሉ። የአቶ ግዛት ወርቁ"6 ሚሊዮን አርሶ አደር ማሳ ላይ ቆመህ ጂኦሎኬት ማድረግ ብቻ እንኳ ከፍተኛ ወጪና ጊዜ የሚጠይቅ ሥራ ነው" በማለት የሥራውን ስፋት ያስረዳሉ። ሌላው የዘርፉ ባለሙያ አቶ ዳንኤል ዘረዓ ያዕቆብ በበኩላቸው "እንደ ብራዚልና ቬትናም በትልልቅ እርሻ ሳይሆን በየቦታው በተበጣጠሰ ማሳ ላይ ለሚመረት የኢትዮጵያ ቡና፣ እያንዳንዱን ማሳ ኦዲት አድርጎ ዳታ ቤዝ ውስጥ ማስገባት ከፍተኛ የቴክኒክ ሥራ፣ የሰው ኃይል እና የገንዘብ አቅም ይጠይቃል" ብለዋል። እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች እና የመራዘሙ ጥቅሞች ምንም እንኳ ፈተናው ከባድ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን መረጃ የሚተላለፍበት ሞባይል መተግበሪያ (App) ማዘጋጀቱንና ትልልቅ ማኅበራት (ዩኒየኖች) ጂኦሎኬት የማድረግ ሥራ መጀመራቸውን አቶ ግዛት ጠቅሰዋል። “መስፈርቱን ለማሟላት የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች በ2025 (በፈረንጆች አቆጣጠር) ሲለፉ ነው የቆዩት። ጂኦሎኬት ማድረግን ጨምሮ የቻሉትን ያህል ሄደዋል። ትላልቆቹ ኮሜርሻል ፋርሞችም እየሰሩ ነው።. . . ጂኦሎኬት ተደርጎ ለአውሮፓ ህብረት ገበያ ዝግጁ የሆኑ አሉ። የኦሮሚያ፣ የሲዳማና የይርጋጨፌ ዩኒየኖች የራሳቸወን ጥረት ሲያደርጉ ነው የቆዩት” ብለዋል። የደንቡ መራዘም የሚሰጠው ጥቅም ይኖር ይሆን ? አቶ ግዛት፥ "አሁን ቢጀመር ኖሮ ለአውሮፓ ቡና ለመሸጥ እንቸገር ነበር፤ መራዘሙ በትክክል ጠቅሞናል" ሲሉ ጥቅሙን አስረድተዋል። 40 በመቶ ትንሽ አይደለም አይደለም የሚሉት አቶ ግዛት  የአውሮፓን መስፈርት ለማሟላት ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን ሰሜን አፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ ያሉ አማራጭ ገበያዎችን ለማየት ጊዜ ይሰጣል ብለዋል። አቶ ዳንኤል በበኩላቸው፥ ልክ እንደ አረንጓዴ አሻራ ሁሉ መንግሥት በሀገር ደረጃ የቡና ማሳዎችን ዳታ ቤዝ በማደራጀት ረገድ ከፍተኛ እገዛ ሊያደርግ ይገባል የሚል ሀሳብ አንስተዋል። የአውሮፓ ኅብረት የወሰደው የመራዘም ውሳኔ ለኢትዮጵያ ቡና ኤክስፖርት ትልቅ "የትንፋሽ ጊዜ" የሰጠ ሲሆን፣ በቀጣዩ አንድ ዓመት ውስጥ ግን የተቀመጡትን የቴክኖሎጂ መስፈርቶች አሟልቶ መገኘት ለዘርፉ ህልውና ወሳኝ ሆኖ ቀጥሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TilvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
1
#Gambella🚨 በጋምቤላ ክልል ፤ ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ፑልኮት / ተርፋም አካባቢ (ወደ ደቡብ ሱዳን ድንበር) ዛሬ ኃይለኛ ግጭት ሲካሄድ እንደዋለ፤ በዚህም የሰዎች ህይወት መጥፋቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጋምቤላ ቤተሰቦቹ ሰምቷል። ዛሬ በአካባቢው ያለው ሁኔታ እንደሚያስፈራ የገለጹልን ነዋሪዎች የፌዴራል መንግሥት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈልግ አሳስበዋል። በአንድ ቀበሌ ብቻ የበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋቱን አመልክተዋል። ቤቶችም ሲቃጠሉ እንደዋሉ ጠቁመዋል። ለስራ ጉዳይ ከጋምቤላ ከተማ 120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኚኛንግ እንዳለ የገለጸልን አንድ የቤተሰባችን አባልም የግጭቱን አሳሳቢነት ገልጾልናል። መሄጃም ይሁን መምጫ መንገድ መዘጋቱን በመጠቆም ስጋት ላይ መውደቃቸውን አስረድቷል። ግጭቱ እንዲበርድ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግ እንዲሁም ወደ ጋምቤላ ከተማ የሚወጡበት መንገድ እንዲመቻችላቸው ጠይቋል። በጋምቤላ ከተማ እና ዙሪያው በሌሎችም ቦታዎች ሰሞነኛው ግጭት በአገር መከላከያ እና ፌዴራል ፖሊስ እንዲረጋጋ ቢደረግም በኢታንግ ልዩ ወረዳ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል። #TilvahEthiopiaFamily @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
1
🎄ልዩ የበአል ቅናሽ🎄
ከ ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር ዘመናዊ እና ቅንጡ የቤት እቃዎችን ለ አጭር ጊዜ በሚቆይ ልዪ የ በአል ቅናሽ ይጠብቆታል። 🫵 ዛሬም ከጊዜው ጋር አብሮ መጓዝ የሁሉም ሃላፊነት ነው። በዚህ እድል መጠቀም ደሞ የእርሶ ድርሻ ነው። 📌 ከ 10 — 25% ልዩ ቅናሽ የውበት፤ ጥራት እና የምቾት ዳር ድንበር ! 📍አድራሻችን 1. ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ) 2. ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት 3. ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ አያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ) ☎️ ይደውሉልን +251957868686 +251995272727 +251993828282 Telegram | Facebook | Instagram | TikTok #ታልቅቅናሽ
Hammasini ko'rsatish...
124🥰 4🙏 4👏 3😱 1
#ሕፃፅ " በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የተለያዩ የሰብአዊ ድጋፍ ችግሮች መኖራቸውን እና ተጨማሪ የፌዴራል ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ቢጠየቅ ኖሮ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁነት አለን " - የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ➡ " በመጠለያ ጣብያዎች ያለው ሰብአዊ ቀውስ ጦርነት መልሶ መቀስቀስ እንደሚችል ማሳያዎች አሉት " - ታደሰ ወረደ (ሌ/ጄ) የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን፣ አስገደ ወረዳ፣ ሕፃፅ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦትን በተመለከተ መግለጫ ሰጠ። ምን አለ ? " መንግሥት በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎቻችንን የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት በማድረግ የምግብ ሰብአዊ ድጋፍ እያቀረበ ይገኛል። ሆኖም በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በሕፃፅ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎቻችን የሰብአዊ ድጋፍ እንዳልደረሳቸው የሚገልጽ የተሳሳተ እና የመጠለያ ጣቢያውን አጠቃላይ ሁኔታ የማይገልጽ ዘገባ እየተሰራጨ ነው። የሰብአዊ ድጋፍን በሚመለከት በመደበኛነት ዓመቱን በሙሉ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የምግብ ስርጭት ሳይቆራረጥ እየተከናወነ ነው። በሕፃፅ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያም የሚገኙ ዜጎቻችን ዓመቱን ሙሉ ተመሳሳይ ድጋፍ ሲደረግላቸው ነበር። ከመስከረም ወር 2018 ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ ወር 2018 ድረስ የተሟላ እና ያልተቆራረጠ የምግብ ሰብአዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን መረጃዎቻችን ያሳያሉ። በአሰገደ ወረዳ ሕፃፅ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ባለፉት አራት ወራት የተደረገውን ድጋፍ በቁጥር ለመግለጽ 14 ሺህ 413 ዜጎች ድጋፍ ሲደረግ ቆይቷል። በተጨማሪም ከአጎራባች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎችን ጨምሮ ፦ ➡ በመስከረም ወር 16 ሺህ 775፤ ➡ በጥቅምት ወር 18 ሺህ 290፤ ➡ በኅዳር ወር 17 ሺህ 813፤ ➡ በታኅሣሥ ወር ለ14 ሺህ 413 ዜጎች የሚያስፈልግ ምግብ ተሰራጭቷል። በዚህም በድምሩ 11 ሺህ 406 ኩንታል ምግብ (ስንዴ፣ ማሽላ፣ ጥራጥሬ እና የምግብ ዘይት) ባለፉት አራት ወራት እንዲዳርሳቸው ተደርጓል። ይህ ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን ከ257 ሚሊዮን (ከሁለት መቶ አምሳ ሰባት ሚሊየን) ብር በላይ ይሆናል። በሌላ በኩል በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የተለያዩ የሰብአዊ ድጋፍ ችግሮች መኖራቸውን እና ተጨማሪ የፌዴራል ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ቢጠየቅ ኖሮ በኮሚሽናችን በኩል አስፈላጊውን ድጋፍ ለመፈጸም የሚያስችል ዝግጁነት ያለን መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። ከላይ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ለተፈናቃይ ማኅበረሰብ የሚላከው ድጋፍ #ለታለመለት_ዓላማ ብቻ መዋሉን የማረጋገጥ እና ክፍተቶች ቢኖሩም እንዲሟላ የማድረግ ኃላፊነት የክልሉና የአካባቢው ጊዜያዊ አስተዳደር መሆኑን እናሳስባለን። " ⚫ በሌላ በኩል ፤ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ)  ትላንት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚሁ መግለጫቸው ፥ " በመጠለያ ጣብያዎች ያለው ሰብአዊ ቀውስ ጦርነት መልሶ መቀስቀስ እንደሚችል ማሳያዎች አሉት " ብለዋል። " ያለውን ሰብአዊ ቀውስ ወደ ደህንነት ቀውስ ተሸጋግሮ ጦርነት መልሶ ካገረሸ ከአገር አልፎ ለቀጠናችንም የሚረበሽ ነው " ሲሉ ገልጸዋል። ሌላስ ምን አሉ ? - " 99.8 በመቶ ወደ ቀዬ መልሱኝ የሚል ህዝብ በማስገደድ በተቀደደ ፕላስቲክ እንዲኖር ማድረግ ዘላቂ ሰላም የሚያፈጥር አይደለም። " - " ተፈናቃዮች ሳይመለሱ የሚረጋገጥ የተሟላ ሰላም የለም። " - " ጊዚያዊ አስተዳደሩ ተፈናቃዮቹ ለስድስተኛ ክረምት ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ እንዳይከርሙ አተኩሮ እየሰራ ነው ፤ በዚ ዓመት የግድ መመለስ አለባቸው። " - " ተፈናቃዮቹ ባሉበት ሆነው እንዴት እየተረዱ ይቆዩ ሳይሆን በዛላቂነት እንዴት ወደ ቄያቸው እንመልሳቸው ነው ዋናው ነገር። " - " የፌደራል መንግስትና ዓለም አቀፍ ለጋሾች ከነብስ አድን ስራ እኩል ተፈናቃዮቹ ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ መስራት አለባቸው። "  - " የፌደራል መንግስት ተፈናቃዮች በመመለስ በኩል የአንበሳ ድርሻ አለው። እኛም እንዲሁ የዓለም ማህረሰብ ድጋፍም እንሻለን። " - " የማህበረሰብ አንቂዎች በሕፃፅ የተከሰተው ረሀብ ወለድ በሽታና ሞት ለዓለም ማህበረሰብ ለማስተጋባት ያደረቁት ጥረት እናደንቃለን። " ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ መቐ @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
870😡 245🤔 33😭 28🙏 25🕊 19😢 13😱 12👏 11🥰 3
02:33
Video unavailableShow in Telegram
#AddisAbaba " የውስጥ ለውስጥ አጥሮችን ራሳችሁ አንሱ ብዬ ባስጠነቅቅም ስላልተነሱ እራሴ በግብረኃይል ወደማንሳት ገብቻለሁ " ያለው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ፤ " ዛሬ ከረፋድ አንስቶ በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን የማስከፈት ሥራ አጠናክሬ ቀጥያለሁ " ብሏል። ባለስልጣን መ/ቤቱ ዛሬ ትኩረቱን ፦ - በየካ - በቦሌ - በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች በማድረግ በተለያዩ ሥፍራዎች በብረት አጥር የተዘጉ መንገዶችን እየከፈተ መሆኑን አሳውቋል። @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
5.16 MB
👏 829 328😡 141😭 39🥰 16🤔 15😢 13🕊 4💔 1
#AddisAbaba " የውስጥ ለውስጥ አጥሮችን አንሱ ብዬ ባስጠነቅቅም ስላልተነሱ እራሴ በግብረኃይል ወደማንሳት ገብቻለሁ " ያለው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ፤ " ዛሬ ከረፋድ አንስቶ በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን የማስከፈት ሥራ አጠናክሬ ቀጥያለሁ " ብሏል። ባለስልጣን መ/ቤቱ ዛሬ ትኩረቱን በየካ፣ በቦሌና በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች በማድረግ በተለያዩ ሥፍራዎች በብረት አጥር የተዘጉ መንገዶችን እየከፈተ መሆኑን አሳውቋል። @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
" ችግሩ የተከሰተው በወር ለተረጂዎች ይሰጥ የነበረው 15 ኪሎ ማሽላ መቀነሱ እና እህሉም ለምግብነት አመቺ ባለመሆኑ ነው " - ጤና ጽ/ቤቱ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ ከእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ አቅራቢያ የምትገኘው #ሕፃፅ የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው መዘገባችን ይታወቃል። ተፈናቃዮቹ በትክክል የሚገኙበትን ሁኔታ ምልከታ ለማድረግ እና መረጃ ለመሰብሰብ ከትላንት በስቲያ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ወደ አካባቢው የላከው ቡድን በስፍራው መረጃዎችን እየሰበሰበ ይገኛል። ቡድኑ የደረሰበትን መረጃ ለመጠየቅ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጤና ቢሮውን ያነጋገረ ሲሆን ቡድኑ የሰበሰበውን መረጃ የማጠናቀር (Finalize) የማድረግ ስራ እየሰራ በመሆኑ የመጨረሻ ደረጃ ውጤቱ እንደደረሰ እናሳውቃለን የሚል ምላሽ አግኝቷል። የመጠለያ ጣቢያው የሚገኝበት አስገደ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በጣቢያው ባደረገው ምልከታ ታይተው የነበሩ ውጤቶችን በተመለከተ ቲክቫህ ያነጋገራቸው የወረዳው ምንጭ 1ሺ 700 በመጠለያ ጣቢያው የሚገኙ ሰዎች የጤና ችግር ያለባቸው ናቸው ብለዋል። ወረዳው አከናውኖ በነበረው ዳሰሳ የተመለከተው ምንድነው ? • በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ በአጠቃላይ 14 ሺ 174 ሰው ተጠልሎ ይገኛል። • በጣቢያው ከሚገኙ ሰዎች ውስጥ 4 ሺ 342 የሚሆኑት እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች ናቸው። • 2 ሺ 506 እድሜያቸው ከ 60 አመት በላይ ናቸው። • 1700 የሚሆኑት ምንም አይነት ተንከባካቢ (Care Giver) የላቸውም። • 497 አካል ጉዳተኞች በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይገኛሉ። • ምንም አይነት የምግብ አቅርቦት የሌላቸው 360 ሰዎች አሉ። • 1700 በላይ የሚሆኑት የጤና ችግር አለባቸው። በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ተረጂዎች ለረሃብ የተጋለጡት ለምንድነው ? - በወር ለተረጂዎች(ለአንድ አባውራ/Household) ይሰጥ የነበረው 15 ኪሎ ማሽላ መቀነሱ ነው እና እህሉም ለምግብነት አመቺ አለመሆኑ። - በአለም የምግብ ፕሮግራም በኩል ይቀርብ የነበረው የተለያዩ ስራዎች በመቆማቸው። - በአካባቢው የጤና ህክምና አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ተንቀሳቃሽ ተቋማት አገልግሎት ማቋረጣቸው(በቀን እስከ 150 ታካሚዎችን ይመለከቱ ነበር)። - ነዳጅም ባለመኖሩ የአምቡላንስ አገልግሎት በመቋረጡ ለምግብ እና ለጤና ችግሮች መጋለጣቸውን ጠቅሰዋል። ወረዳው በምልከታው በችግሩ ሳቢያ ምን ያህል ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ በቁጥር ባይጠቅስም ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡት የመረጃ ምንጭ ህይወታቸው ያለፉ ተረጂዎች መኖራቸውን ታሳቢ መደረግ አለበት ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ወደ መጠለያ ካምፑ ከተንቀሳቀሰው ቡድን የመጨረሻ ደረጃ ውጤት እንደደረሰው የሚያቀርብ ይሆናል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
520😭 323😡 35💔 27😢 19🕊 14🙏 11😱 6🤔 4
የዜጎች የመደራጀት እና የፖለቲካ ፖርቲ የመመሥረት ሕገ-መንግሥታዊ መብት ጥሠትን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዛሬ አንድ መግለጫ አውጥቷል። በዚህም መግለጫ ይህን ሰርፎ ተመልክተናል ፦ 1. " ' የኮንቶማ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ' መሥራቾች ፓርቲ ለመመሥረት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ሕጋዊ ሠነዶች አሟልተው የመሥራች ጠቅላላ ጉባዔያቸውን ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡታጅራ ከተማ እንደሚያደርጉ ለቦርዱ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ቦርዱ፦ - ለክልሉ መንግሥት አስተዳደር፣ - ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ - ለምሥራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ - ለቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፣ - ለማረቆ ልዩ ወረዳ ከማንድ ፖስት እና ለቡታጅራ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ለመሥራቾቹ የፀጥታ ድጋፍ ትብብር እንዲደረግላቸው በደብዳቤ አሳውቋል። የቦርዱ ባለሙያዎችም በሕጉ መሠረት በቦታው በመገኘት ታዝበው ሪፖርት እንዲያቀርቡ ተመድበው ነበር፡፡ ሆኖም ግን የክልሉ የፀጥታ አካላት፤ ጉባዔ መደረግ የማይችልበትን ሁኔታ በጽሑፍ ለቦርዱ ሳያሳውቁ #መሣሪያ_የታጠቁ የቡታጅራ ከተማ የፀጥታ አካላት በጉባዔው ዕለት ' ከተማው በኮማንድ ፖስት ሥር ስለሆነች መሰብሰብ አይቻልም ' በሚል ለስብሰባ የመጡ የፓርቲው መሥራች አባላቶችን ከአዳራሽ በማስወጣት በቁጥጥር ሥር እንዳዋሏቸው ቦርዱ በታዛቢነት ከላካቸው ባለሞያዎቹ ሪፖርት መረዳት ተችሏል። " 2. " ' የደንጣ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ' መሥራቾች ፓርቲ ለመመሥረት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ሕጋዊ ሠነዶች አሟልተው የመሥራች ጠቅላላ ጉባዔ ታኅሣሥ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀድያ ዞን ቢጠና ታዳጊ ከተማ እንደሚያደርጉ ለቦርዱ ማሳወቃቸውን ተከትሎ፤ ቦርዱ ለክልሉ መንግሥት አስተዳደር፣ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እና ለሀድያ ዞን አስተዳደር ለመሥራቾቹ የፀጥታ ድጋፍ እንዲደረግላቸው በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ የቦርዱ ባለሙያዎችም በቦታው ተገኝተው በመታዘብ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ተመድበው ነበር። ሆኖም ግን መሥራቾቹ ተሟልተው ጉባዔው ሊጀመር ሲል የከተማዋ የፀጥታ አካላት ' ስብሰባውን ማድረግ አይቻልም፣ የፀጥታ ድጋፍ አናደርግላችሁም፣ አደጋ ቢደርስባችሁም ኃላፊነቱን አንወስድም እንዲሁም ስብሰባውን ለመረበሽ የተዘጋጁ አካላት አሉ ቦታውን ለቃችሁ ውጡ ' በማለት የቦርዱን ታዛቢዎች ከከተማዋ ለቀው እንዲወጡ አድርገዋቸዋል፡፡ " ቦርዱ ምን አለ ? በየደረጀው የሚገኙ የክልሉ የመንግሥት አካላት በሕገ መንግሥቱ እንዲሁም በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት ለዜጎች የተረጋገጠውን የመደራጀት እና የፖለቲካ ፓርቲ የመመሥረት መብት ማስተጓጎላቸው የፖለቲካ ምኅዳር የሚያጠብ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ተግባር ነው ብሏል። በየደራጃው የሚገኙ የክልሉ የመንግሥት አካላት የዜጎች የመደራጀት እና የፖለቲካ ፖርቲ የመመሥረት ዲሞክራሲያዊ መብት ላይ የሚፈጸሙ የማስተጓጎል ተግባራት ላይ ተገቢው የዕርምት ዕርምጃ እንዲወስዱ በጥብቅ አሳስቧል። #NBE @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
396👏 35😡 25🤔 13🙏 6😢 5😭 3