Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
Kanalga Telegram’da o‘tish
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Ko'proq ko'rsatish2025 yil raqamlarda

228 615
Obunachilar
-14224 soatlar
-1 0407 kunlar
-4 59630 kunlar
Postlar arxiv
"…የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።ዮሐ 16:2
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
Photo unavailableShow in Telegram
“…እኛስ ዘወትር በሚያስፈራ ኑሮ የምንኖር ስለ ምንድር ነው?” 1ኛ ቆሮ 15፥30
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
06:49
Video unavailableShow in Telegram
• አለን…!
• ሁላችንም ዝግጁ ነን።
7.72 MB
Photo unavailableShow in Telegram
"…አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይግባው። አሜን…🙏
~ የዛሬውስ ነጭ ነጯን እንዴት ነበር ጎበዝ…?
Photo unavailableShow in Telegram
• ጀምረናል ገባ ገባ በሉ…!
• አላችሁ አይደል…?
👍 405❤ 117🙏 26💔 15🔥 13🕊 8🏆 6🤔 3
Photo unavailableShow in Telegram
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 2:00 ሲሆን በዘመድ ቴቪ መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።
~ በአሩሲ ስለታረዱት የተዋሕዶ ልጆች የሻማ ማብራት መርሀ ግብርም ይኖረናል እና ሻማ ለማብራት ተዘጋጁ። 🙏
• ቲክቶክ 👉 http://tiktok.com/@zemedkun.b
• ZemedTv 👉 zemedtv.com/live.html
• በትዊተር (×) 👉 x.com/i/broadcasts/1mrGmBNVyYNJy
• በራምብል 👉 rumble.com/v714jug--zemede-november-02-2025.html?e9s=src_v1_cbl%2Csrc_v1_upp_a
• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Yahsat 52.5° East
11977 H 27500
• ላይ ይከታተሉን።
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!
❤ 336👍 120🙏 39🏆 8🕊 6⚡ 4🔥 3🤯 3😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
"…ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ።" መዝ 63፥2
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
🙏 956❤ 284👍 128🕊 19✍ 6🔥 5🏆 4😡 2
መልካም…!
"…በተባበሩት ኤምሬትስ ድሮን፣ ቦንብ እና ጥይት ልንጨፈጨፍ፣ በቱርክ እና በሳዑዲ ዓረቢያም ሰይፍ ልንሰየፍ እንችላለን። በጊዜ መላ ካላበጀንለት ጉዳቱ ከባድ ነው። ነገር ግን ዘግይቶም ቢሆን እምቢኝ ብሎ ተነሥቶ የኃይል ሚዛኑን እንዳስጠበው እንደ ዐማራ ፋኖ እምቢኝ፣ አሻፈረኝ፣ በበላሽ አልታረድም ብለን መንፈራገጥ ካልጀመርን በየጊዜው የእርድ ዜና መስማት እንደ ነጠላ ዜማ ይለመዳል። እናም አገዛዙ እንደ መንግሥት እንደ ዜጋም ቆጥሮ ካልጠበቀህ ራስህን አደራጅተህ ጠብቅ። ይኸው ነው።
"…የአቢይ አገዛዝ ትግራይን እያስተዳደረ አይደለም። አይሄድም። አይጎበኝም። ዐማራንም እንደዚያው። በኦሮሚያም ከጅማና ናዝሬት በቀር ድርሽ አይልም። ያው እንደ ልቡ የሚሆነው ደቡብ ብቻ ነው። ደቡብም በፓስተሮቹ ስብከት ብርታት የተነሣ ነው።
"…ሳይወድ በግዱ ይሆን ዘንድ ይጠበቅ የነበረው የዐማራ አንድነት በወሎ ቤተ ዐምሓራ በብአዴኖች በቁም እስር ላይ የሚገኘው ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሓባው ብቻውን ከጎጃሙ ማስረሻ ሰጤና ደህንነቱ መስፍን ጋር ሲቀር ክፍለጦሮቹ በሙሉ አፋብኃ ምሥራቅ ዐማራ ምንሊክ ዕዝን ተቀላቅለው ዐማራን አስደስተዋል። የጎንደሮችም ሰሞኑን ምንአልባትም በዚህ ሁለት ቀን የምሥራች ሊያሰሙን ይችላሉ። የሸዋው አስጊ አይደለም። ጎጃምም ሠራዊቱ በእነ ማርሸት እና አስረስ ላይ ስለባነነ የሆነ የሚጠበቅ ነገር ይኖራል። ብቻ ተወደደም ተጠላም የዐማራ አንድነት የህልውና ትግሉን የድል ቀን ያፋጥነዋል። የዐማራም የመከራ ዘመን ያጥራል።
"…ሚሊሻ አባት ነው። ፋኖ ልጅ። ሚኒሻ የፋኖ አጎት ነው። ዘመዱም ነው። ፋኖ ልጅ። በድኑ ብአዴን የዐማራ ሚኒሻን በዐማራ ፋኖ፣ አባትና ልጅን እያተኳኮሰ ማስገደሉም እየተነቃ ስለመጣ ብአዴን ኪሳራ ላይ መውደቅ ጀምሯል። ብአዴን ከጎጃም በቀር በሌላው የዐማራ ግዛት በሰቀቀን ነው የሚኖረው።
"…ዐማራ ባይኖር አስባችሁታል? ትግሬ ለመገንጠል፣ ኦሮሞ ለመገንጠል፣ ታሪክ፣ ሰንደቅ ዓላማን ለማጥፋት፣ ለማውደም፣ ሀገር ለመበታተን፣ ዐማራና ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ከነፋስ በፈጠነ ፍጥነት በጊዜ ይቋጩት ነበር። የዐማራ መኖር ሁሉንም አደብ አስገዛቸው። ከፊንፊኔ ኬኛ፣ ጎጃም ኬኛ፣ ጎንደር ኬኛ፣ ወሎ ኬኛ አሰብ የኢትዮጵያ፣ ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ አሰኛቸው። 😂 አይ ዐማራ። ኑርልኝ አንበሳዬ። ይኸው ዛሬ በናዝሬቱ የብልፅግና የሥልጠና ስብሰባ ስልክ መያዝ ተከልክለው አሰብ፣ ወደብ ሲሉ ዋሉ።
"…ሥርዓቱ ይወድቃል። ነገር ግን ደግሞ አሜሪካ ያሉ ጩሉሌዎች ትግሉን እንዳይነጥቁት እና ሌላ ጨፍጫፊ አቢይ አሕመድ እንዳይተክሉብን ከወዲሁ ኮስተር ብሎ መላ ማበጀት ያስፈልጋል። አፈ ጮሌ ሁላ ሲንጣጣ እያየሁት ነው። ፋኖ ያሸንፋል። አያያዙም ያስታውቃል።
• እስቲ ደግሞ እናንተ ተንፍሱ። ከሊቃውንተ ኢትዮጵያ ጋር የነበረንን ውይይት ወደ ርእሰ አንቀጽነት የቀየርኩትን እንዴት አገኛችሁት…? እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ እስቲ እንወያይ። ጻፉ። ✍✍✍
2.80 MB
12.27 MB
6.39 MB
👆⑤✍✍✍ …"…ዱባይ ዓረብ መሩ የኦሮሞ ብልጽግናው የአቢይ አገዛዝም መውደቁ እንደሁ አይቀርም። የጊዜ ጉዳይ ነው። ኔፓል የተጀመረው የወጣቶች ዐመጽ እና ተቃውሞ ማዳጋስካር ገብቶ፣ አገዛዙን ወደ ዱባይ አስፈርጥጦ፣ ካሜሮን ተሻግሮ ቀውጢ እየፈጠረ፣ አሁን ላይ ጎረቤት ሀገር ታንዛኒያ ደርሷል። በታንዛኒያና በኢትዮጵያ መሃል ያለው ኬንያ ነው። የታንዛኒያ መንግሥት እንደለመደው ጥቁቶችን ገድዬ ተቃውሞውን አስቆመዋለሁ ብሎ ፎክሮ በጥቂቱ 700 ታንዛኒያውያን ቢገድልም እንዲያውም ሕዝቡ ብሶበት አደባባይ ግልብጥ ብሎ በመውጣት በኑሮ የደቀቀው ሕዝብ፣ እኛንም ግደሉንና ገላግሉን በማለት አገዛዙን አስጨንቆ፣ ወታደሩን ከጎን አሰልፎ ሥርዓቱን በአናቱ ተክሎ ነፃ ሊወጣ ከጫፍ ደርሶ ነው ያለው። ከማዳጋስካር የተነሳው የለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ዐመጽ ታንዛኒያ ደርሷል። በታንዛኒያና በኢትዮጵያ መካከል የምትገኘው ኬንያ ብቻ ናት። የኢትዮጵያው ከማዳጋስካሩም፣ ከታንዛኒያውም፣ ከኔፓሉም የሚለየው ዐመፁ በድንጋይ አለመሆኑ ነው። ዐመጹ በጥይት ነው። ኦሮሙማውም ከወዲሁ ሸኔ የሚባለውን ኃይል አዲስ አበባ ዙሪያ አስፍሯል። መውረዳችን ካልቀረ በማለት በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ቅርስ ለማውደም፣ ንፁሐንን በጅምላ ለመጨፍጨፍ በዝግጅት ላይ ናቸው። በሸገር ሲቲ በሚባለው በቀን በጠራራ ፀሐይ ሲሯሯጡ የሚታዩት ኦነግ ሸኔዎች ለዚሁ ጭፍጨፋ ተብለው የተዘጋጁ ናቸው። በባሌ፣ በኤርትራ፣ በሱማሊያ የሰለጠነው አራጅ የወሀቢያ ቡድን ደግሞ በአሩሲ የጀመረውን የዘር ማጽዳት በሀረርጌ፣ በባሌና በጅማ፣ በወለጋም ለማጣጧፍ እያሟሟቀ ነው።
"…አዎ ከባድ ግዜ ከፊታችን መጥቷል። ደቡብ ሱዳን የሰለጠነ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአክራሪ የወሀቢይ እስላም ቡድን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ካማሽ ዞን በኩል ወደ ወለጋ በብዛት እየገባ መሆኑ ተነግሯል። በሱዳን የጅምላ ጭፍጨፋ እንደሚፈጽመው እንደ አረመኔው የዱባይ ቅጥረኛው ሀሚቲው ቡድን ያለ ጨካኝ ነው። የሚገድሉት ብሔር ሳይለዩ ኦርቶዶክሱን ብቻ ነው። የሚያወሩት አረብኛ ሲሆን ትንሽ ትንሽ ኦሮሚኛ እንደሚያወሩ ነው የሚነገረው። አሁን ላይ ከፍተኛ ውጊያ በዚያ አካባቢ እየተካሄደ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሞ ብልፅግና ብአዴንን በማዘዝ ወደ አሰብ እንዳንሄድ፣ ሻአቢያን እንዳንበቀል እንቅፋት የሆነን ፋኖ ነው ብላችሁ ሚሊሻ፣ ፖሊሱን ከፋኖ ጋር አጋጥሙልኝ በማለት ያዘዘ ሲሆን፣ ብአዴንም የታዘዘውን ቢፈጽምም ልባሙ ዐማራ ግን መሳሪያውን እንደያዘ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው። በኦሮሚያ ደግሞ ሕዝቡን ሰብስበው ዐማራ መጣልህ፣ በዘመናት ተጋድሎ ከእጃችን የገባውን ሥልጣን ነጥቆ ሊወስድብህ ነው። ተነሥተህ የማትዋጋ ከሆነ፣ በብዙ ነገር የተከፋ፣ ቂም የቋጠረ ኃይል ስለሆነ እየመጣ ያለው እንደ ሩዋንዳ የዘር ፍጅት ነው የሚፈጸምብህ፣ ተነሥ፣ ታጠቅ፣ ዐማራ ሥልጣን እንዳይዝ ዝመት፣ ተዋጋ እያሉት እንደሆነም ተሰምቷል። የሆነው ሆኖ ይሄ ሥርዓት ያበቃለት ሥርዓት ነው። አወዳደቁም ከሁሉ የከፋ ነው። ይደፈርሳል። ግን ደግሞ ይጠራል።
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ ከራየን ወንዝ ማዶ።
👆④✍✍✍ …ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አለመቻል። ዘመድ ጥየቃ፣ ለልቅሶም ቢሆን ገጠር መሄድ አለመቻል የመጣው በዘመነ ኦሮሞ ነው። በዘመነ ዐማራ 1ዶላር 1 ብር ነበር። አሁን 1 ዶላር 200 መቶ። ነዳጅ ላይ አምስት ሳንቲም ጨመረ ብሎ ዘውዳዊውን ሥርዓት የገረሰሰው የሻአቢያ፣ የትግሬና የኦሮሞ አቢዮት አሁን ላይ ነዳጅን በሊትር 120 ብር እየሸጠ አጨሰው ሕዝቡን። በዘመነ ዐማራ በ600 ብር ደሞዝ ውኃ፣ መብራት፣ ስልክ፣ የቤት ኪራይ፣ የቤት ቀለብ አስቤዛ ችለህ እንደ ዲታ ትኖር ነበር። በዘመነ ኦሮሙማ እግርህን ትበላታለህ። የመቶ ሚልዮን ብር በአናትህ ላይ የሚነዳው ቄሮ ብቻ ነው። አለቀ።
"…አሁን አገዛዙ የዳጎን ሐውልት ነው። የዳጎን ሐውልት ለኤሎፍላውያን አምላክ ነው። ታቦተ ጽዮን ስትመጣ ግን አመድ ነው የሆነው። አቢይ በላይ ሲያዩት ንጉሥ ነው፤ በፋኖ ዘንድ ግን ገለባ ነው። አወዳዳቁም የከፋ ነው። እስካሁን የሄደበት አካሄድ ስሕተት መሆኑን አምኖ ሌላ መፍትሔ በማምጣት ፈንታ አሁንም የበለጠውን የስሕተት ገደል መርጧል። በጀት፣ በድሮን፣ በመድፍ ያልቀለበሰውን በኦሮሚያ ልዩ ኃይል እቀለብሰው ይሆናል ብሎ በአርባ ዙር ያሰለጠነውን ሠራዊት ወደ ዐማራ ቀጠናዎች አስገብቷል። ይህ እብደት ነው። ያለ ሓሳብ በተዘረፈ ብር ጥሬ ሥጋ በመብላት ጥይት በባዶ ሜዳ እንደመተኮስ ቀላል አይደለም። በእኔ ግምት ይህ የእግዚአብሔር እጅ ያለበት ይመስለኛል፤ በኦሮሚያ የዐማራ እናቶችን ያረደው የሽመልስ አብዲሳን ቅልብ ጦር ፈጣሪ ዐማራ መንደር ድረስ ሰተት አድርጎ አስገብቶለት አራጁ በእጅን ራሱ ዐማራው ተበቅሎት ፍርድ ሰጥቶት በዚያው እንዲቀበር በተዘዋዋሪ የፈረደለት ነው የሚመስለኝ።
"…አቢይን እስካሁን የተዋጋው የፋኖ ማዕበል ነው። በፐርሰንት ቢለካ 2% እንኳ የማይሞላ የፋኖ ኃይል። ያውም በውስጡ ከዚህቹ ለመከፋፈል የሚጋጋጡ በበዙበት፣ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎ የተሰገሰጉ፣ በሸዋ የተሰነቀሩ ባንዳዎች ሞልተውበትም ቢሆን በጥቂት ኃይል ነው መክቶ እያደባየ የሚገኘው። ባንዳው ብቻውን እየቀረ ነው። በወሎ ብአዴኖች በቁም ያሠሩት ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሐባው ከማስረሻ ሰጤ ጋር ሲቀር፣ ጎንደር እነ ደረጄ ሰሞኑን የሚያበስሩን ብሥራት የሚጠበቅ ሆኖ ወደ አንድነት እየመጣ ነው። የሸዋውም እስክንድር አንቆ የያዘው የላይኛው የእነ መከታው ቡድን ሲቀር በአብዛኛው ታች ያለው ፋኖ ያለወረቀት ተዋሕዶ በአንድነት መዋደቅ የጀመረ ነው። የጎጃሙ ነው አደገኛው። መሰሪው፣ ሾተላዩ። እሱም ቢሆን የጊዜ ጉዳይ ነው ብቻውን ይቀራል። የጎጃም የበላይ ዘለቀ ልጆችም ወደፊት ይመጣሉ። እናም አቢይ አሁን በያዘው አቋም ግን የፋኖ ሳይሆን የሕዝብ ማዕበል ያጥለቀልቀዋል። በጥላቻ የሰከረው የሽመልስ አብዲሳ ልዩ ኃይል ሕዝቡን ከፋኖ አይለይም። ከእስካሁኑ ጭፍጨፋ በበለጠ ሕዝብ ይጨፈጨፋል። በመድፍ፣ በጀት፣ በድሮን የዐማራ ከተሞችን ያወድማል። ለዚህም ይልማ መርዳሳ ዝግጅቱን ጨርሷል። ፋኖ ቅንጣት ታህል ጉዳት አያገኘውም። አገዛዙ ግን ይህን እያወቀ ዐማራን እንደ ጋዛ ሊያደርጋት ተዘጋጅቷል። አቢይ መገንዘብ ያልቻለው፣ እስራኤል በጋዛ ያን ያህል ውድመት አድርሳ ሐማስን ያላሸነፈች፤ የታገቱትንም በሠራዊቷ ያላስለቀቀች መሆኑን ነው። አቢይም ፋኖን ማሸነፍ ቀርቶ ካለበት ኢንች ፈቀቅ ማድረግ አይችልም። የሕዝብ ማዕበል ይነሳል፤ የአቢይን አራጅ ሠራዊት በዱላ፣ በመጥረቢያ፣ በማጭድ፣ እጁ ላይ ባገኘው መሣሪያ ይውጠዋል። ፋኖ የሚታጠቀውን መሣሪያ ሕዝቡ ይታጠቀዋል። ውድቀቱም ይፋጠናል። አወዳደቁም የከፋ ነው የሚሆነው። ብቻውን ሳይሆን በስሙ ብዙ ወንጀል የሠራበትን የኦሮሞን ሕዝብም ይዞ ነው የሚወድቀው። አቢይ ሆይ የአንተን ስሕተት የኦሮም ሕዝብም ያወራርደዋል። እናም ምክሬ ሳይመሽ የኦሮሞ ሕዝብ ከዐማራ ወንድምህ ጎን የምትቆምበት አጋርነትህን የምታሳይበት የመጨረሻው ወቅት አሁን ነው። ለወደፊት ህልውናህ ስትል ዕወቅበት። አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ እንዳይሆን ፍጠን። የአቢይ ውድቀት ይዞህ እንዳይጠፋ ተጠንቀቅ። መራር ነው ግን እውነት ነው ዋጠው።
"…ዐማራን ወደብ ላመጣ ነው፣ ቀይ ባህርን ልመልስልህ ነውና አትውጋኝ አትበለው። ኤርትራንም በወልቃይት በኩል ስትፈልግ በዛላንበሳ በሽሬ ሞክራት፣ ውረራት፣ በአፋር በኩልም ቅርብ ነው። ስታርደው፣ ስትገፍፈው፣ ስታሸማቅቀው፣ አዲስ አበባ እንዳትገባ ስትለው፣ ወራሪ፣ ሰፋሪ ስትለው፣ በድሮን፣ በቦንብ ስትጨፈጭፈው ውለህ የምታድረውን ዐማራ አሁን ላይ ደርሰህ አንድ ጊዜ መዋጋቱን እናቁምና አሰብን፣ ወደቡን እናምጣው ናና ተከተለኝ አትበለው። ፊንፊኔን ኬኛ፣ ጎጃም ኬኛ፣ ጎንደር ኬኛ፣ አክሱም ኬኛ፣ ወሎን ኬኛ ስትል ቆይተህ አሁን ድንገት ደርሰህ አሰብ የኢትዮጵያ ነው ብለህ አትጃጃል ጋሽ ኬኛ። አዎ አይደለም አሰብ ኤርትራም የኢትዮጵያ አካል ናት። ይሄን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከጠላት፣ ከባንዳ በቀር ያምናል። በዘመነ ኦሮሞ፣ በሁሉም ኬኛ ዘመን አሰብ የኢትዮጵያ ነው ብትል የሚሰማህ የለም። ይልቅ ደሞዝ፣ የቤት ኪራይ፣ አበል እከፍልሃለሁ እና ለፊንፊኔ ፖሊስነት ለ30 ዙር ኑና ሰልጥኑ ብለህ በማስታወቂያ የምትጠራቸውን የሊሙ ሰቃ የአባ ገዳ ልጆች ይዘህ ንካው። ለጊዜው የዐማራ ወደቡ አራት ኪሎ ብቻ ነው። መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ ብሎሃል ዐማራ። ሀሚቲንና አቢይን የምትረዳው ኤምሬትስ በሱዳንና በአሩሲ አላህ ወአክበር እያለ እናትን ከእነ ልጆቿ ጨፍጭፎ የሚበላ አራጅ ቡልጉ ጭራቅ ተከትሎ ኤርትራ የሚዘምት የለም። እነ የትነበርክ ተድላም አድቡ፣ ተኝታችሁ ከርማችሁ ዐማራ ላይ አታናፉ። ዐማራ የቤት ሥራ አለበት። የምትፈርስ ሀገር ላዩ ላይ ወድቃ ቢያንስ በፍርስራሹ እንዳይቀበር የመከላከል አቅሙን ማጎልበት፣ ከዚያም አለፍ ሲል ከዚህ ፀረሰው የሰው ቡልጉ ሥርዓት ኢትዮጵያን አይደለም ቀጠናውን መታደግ አለበት። እናም እረፉ። የአቢይ አገዛዝ ይወድቃል። ማዳጋስካር፣ ካሜሮን፣ አሁን ታንዛኒያ የደረሰው ሕዝባዊ ዐመጽ ብልጽግና የተባለን ሁሉ ከፋኖ በፊት ቆረጣጥሞ ይበላዋል። መራራ ጉዲና ያለውም ቃል ይፈጸማል። የራበው ሕዝብ መንግሥቱን ይበላዋል። አከተመ። …👇④✍✍✍
👆③✍✍✍ …ለዐማራ ፋኖ እጅ እየሰጠ አብሮ ለመታገል ቃል እየገባ ነው።
"…ለማንኛውም የሰሜን ኢትዮጵያው ሕዝብ በጥንካሬ፣ በሥነ ልቡና፣ በወኔ፣ በውጣ ውረድ ችግርን በመጋፈጥ ለዘመናት የቆየ ከፍተኛ የሆነ ልምድ ያከበተና የአመራርና የመዋጋት አቅሙም ላለፉት ሺህ ዘመናት የዳበረና የበለጸገም ነው። በሽምቅ ውጊያ፣ በቆረጣ፣ በፊት ለፊት ውጊያ፣ ስቦ በመምታትም እጅግ የተካነ ነው። ጦርነትን በስሜት ሳይሆን በስሌት የሚመራ፣ ወደ ጦርነት ከመግባቱ በፊት አሸንፎ የሚገጥም አደገኛ ሕዝብ ነው። ዐማራው መንግሥት እንኳ ባይኖር ራሱን በጎበዝ አለቃ አደራጅቶ ራስን የመከላከል የዳበረ ልምድም ያለው ድንቅ ሕዝብም። በሰብአዊ ርኅራሄው፣ በምርኮ አያያዝ፣ ለሰው ልጆች ባለው እኩልነትና ነጻነት፣ በሚሰጠው ፍቅር ጠላት እሱን ከመፍራት ይልቅ ጠላቱን እንደ ዱር እንስሳ አላምዶ ወዳጅ ማድረግን የሚችልበት ሕዝብ ነው። ለዚህ ነው የአቢይ አሕመድ ሠራዊት ወደ ዐማራ ግዛት ገብቶ እንደ እንቧይ ካብ እየተናደ ወደ ዐማራ ፋኖ እየተመመ፣ እየጎረፈም ያለው። ይህ የዳበረ የዐማራ ጠባይና ስብዕና ነው አሁን ላይ ዐማራን ጠላቱን እየቀነሰለት ወዳጅም እያበዛለት ለዐማራ የፋኖም የጀርባ አጥንት እየሆነለት የመጣው።
"…የፋኖ አደረጃጀት በካምፕ፣ በቦታ፣ በድንበር የተወሰነ ሳይሆን በጎጥ፣ በቀበሌ፣ በወረዳ፣ በአውራጃ፣ በክፍለ ሀገር፣ በመላው ዐማራ የመላ በመሆኑ አገዛዙ በቀላሉ ለመቆጣጠር አያስችለውም። ሌላኛው የፋኖ ጥንካሬ የመልክዐ ምድር ጠቀሜታ ነው። በየሰፈሩ የተበተነው ሠራዊት በቀላሉ ይጠቃል። በየሰፈሩ የሚረወረው የድሮን ቦንብ፣ የሚተኮሰው መድፍና ሞርታር በቀላሉ ይባክናል። ወጪው ደግሞ የማይቀመስ ነው። መቼም ከሱዳንና ከኢትዮጵያ ተዝቆ በሚሄድላት ወርቅ፣ እንዲሁም ዓረቦችን አረብ መስላ በማዳከም አዲሷ የዓረብ ቅኝ ገዢ የሆነችው ኤምሬትስና ቱርክ ለጥቅማቸው ሲሉ በገፍ የሚያቀርቡለት ቦንብና ድሮን ከነ ቴክኒሽያኖቹ በገፍ ስላሉት ነው እንጂ ወጪው በኢትዮጵያ አቅም የማይቀመስ ነበር የሚሆነው። እንዲያም ሆኖ በ10 ሚልዮን አንድ የድሮን ቦንብ 2 አህያ፣ አንድ በሬ፣ ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ፣ እናትና ልጅ መግደሉ አልቀረም። በእስከአሁኑ ድካማቸው የፋኖን ኃይል ሊያጠቁ አልቻሉም። ወታደር ይመረቃል፣ ይመረቃል፣ በገፍ ወደ ክልሉ ይገባል። ነገር ግን የገባው ቤርሙዳ እንደገቡ መርከቦች ሰምጠው ከመቅረት በቀር ሌላ አማራጭ የሌላቸው ሆነዋል። ወታደሩ በቲክቶክ ይፎክራሉ፣ በአካል ይኮመተራሉ። አሁን ላይ በዐማራ ግዛት የተበተነው ሠራዊት በማያውቀው ሸለቆ፣ ተራራ፣ ሰፈር፣ ቀበሌ ገብቶ እንደ ሰም ቀልጦ እየቀረ ነው። የዐማራ ፋኖ መውጫ መግቢያውን ስለሚያውቅ፣ የቦረቀበት ሸለቆ፣ ጋራና ሸንተረር በመሆኑ መቶውን የአቢይ አሕመድ ሠራዊት ሁለት የዐማራ ፋኖ እንደ ከፍት ይነዳዋል፣ ይደመስሰዋልም። ፋኖ በልምድ ያካበተውን የተኩስ ችሎታ በሥልጠና አዳብሮ አንዲት ጥይት መሬት አትወድቅም፤ ቅንድብ ነው የምትላጨው።
"…ይህን በየሰፈሩ የተዋቀረን ዘመናዊ የፋኖ አደረጃጀት እንኳን ማሸነፍ ለመደራደርም ቢሆን አሁን ላይ አዳጋች ነው። በሳምንት ውስጥ ሱሪውን፣ ቀበቶውንም እናስፈታዋለን የተባለው ዐማራ የመከላከያውን ሱሪም፣ ቀበቶም እያስፈታ ታየ። ሦስት ጠምንጃ ይዞ መንግሥት መገልበጥ አይቻልም የተባለለት ዐማራ ዛሬ ላይ በአርፒጂ ያደባየው ጀመር። ሺ ዓመት ብትዋጉንም አታሸንፉንም የተባለ ዐማራ በሁለት ዓመት ፍርክርኩን አወጣው። 10 ቢልዮን ዶላር መድቤ እዋጋቸዋለሁ ያለውን አቢይ አሕመድን 10 ቢልዮን ዶላር ለማግኘት አይኤምኤፍ እግር ስር ተደፍቶ ውሎ እንዲያድርም አደረገው። 1ዶላር በብላክ ለ200 ብር ፈሪ የሚዘረዘር ሆኖ ተገኘ። አንድ ሊትር ነዳጅ 120 ብር መቅዳት ግድ ሆነ። ኑሮ ሰማይ፣ ጣራ ነካ። ይሄ ሁሉ የዐማራ ፋኖ በአገዛዙ ላይ ባሳረፈው ጡጫ ምክንያት የመጣ ኪሳራ ነው። አንድ የዐማራ ልጅ በአስተዳደጉ እንደ መደበኛ ትምህርት ከእናት አባቱ፣ ከማኅበረሰቡ የሚወስደው ሥልጠና አለ። ከስም አወጣጡ ጀምሮ ብንመለከት አሸናፊ፣ መክት፣ ንጉሡ፣ መኳንንት፣ ከበደ እየተባለ ነው የሚጠራው። ተሸንፎ ከቤት የመጣ ልጅ ምግብ አይሰጠውም። ሥነ ልቦናው በጥንካሬ ነው የሚገነባው። በራሱ የሚኮራ ትግራይ ላይ የካሌብን፣ የአብርሃን፣ የአጽብሃን፣ የምኒልክን፣ የሳባን፣ የዐጼ ዮሐንስን ታሪክ ተግቶ ነው የሚያድገው። ወሎ ላይ የላሊበላን፣ የነራስ ካሳን ታሪክ ይጠጣል። ጎንደር የፋሲልን፣ የቴዎድሮስን ወኔ የተላበሰ ነው። ጎጃም የበላይ ዘለቀን፣ የንጉሥ ተክለ ሃይማኖትን ታሪክ ይጎናጸፋል። ሸዋ ላይ የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብን፣ የዐፄ ዳዊትን፣ የዳግማዊ ምኒልክን ታሪክ ይዋኝበታል። በዚህ የሕሊና ውቅር የተመሠረተን የዐማራ ፋኖ በቀላሉ ማሸነፍ ሕልም ነው የሚሆነው።
"…የአገዛዙ ሠራዊት በተቃራኒው በጥላቻ ያበደ፣ ከኢትዮጵያ ታሪክ የተነጠለ፣ ማንነት ፍለጋ የሚንከራተት፣ ሥነ ልቦናው የተጎዳ፣ ያየው ሁሉ የሚያምረው፣ ማውደም እንጂ መገንባት የማይችል፣ የትላንት ማንነትህ ተነጥቋል ተብሎ ያደገ፤ መንጠቅ መቀማትን እንደ ባህል የሚቆጥር፣ በቀላሉ የያዘውን መሣሪያ የሚያስነጥቅ፣ መማረክን እንደ ባህል የሚቆጥር፣ ርእዮተ ዓለም የሌለው፣ ጭፍን፣ ወሬ ብቻ፣ እንደ ሕፃን በአሻንጉሊት፣ በብልጭልጭ ነገር የሚታለል፣ የሚፈዝ፣ እንደ ሴተኛ አዳሪ ጨለማን እንደ ቡናቤት በመብራት፣ በዲምላይት ማንቦግቦግን ይሄንኑ እንደ እድገት ቁጠሩልኝ፣ ቢርባችሁ፣ ቢጠማችሁም በመናፈሻና በፓርኮቹ ውስጥ እየተንሸራሸራችሁ አየር ብሉና ኑሩ የሚል ቀሽም፣ በተንኮል ከኢትዮጵያ ተነጥሎ ያደገ በመሆኑ አገዛዙን ክስረት አድርሶበታል።
"…ሌላው የአገዛዙ ስሕተት የዐማራን ሥነ ልቦና ጠንቅቆ አለማወቁ ነው። ዐማራ ነጻ የሆነ፣ የማንንም ነጻነት የማይቀማ፣ የራሱን የማይሰጥ፣ የሰውን የማይወስድ፣ በእኩልነት፣ በፍትሐዊነት የሚያምን፣ ጭቆናን ፈጽሞ የማይቀበል ብቻ ሳይሆን አምርሮ የሚጸየፍ ጭምር። ለጠብም የማይመች ሕዝብ ነው። መሸነፍንማ ፈጽሞ የማይወድ ብቻ ሳይሆን የሚያስቀጣው ጭምር ነው። ሞቶ ካልሆነ በቀር በሕይወት እያለ የማይማረክም ነው ዐማራ። ዐማራ ሲበዛ በቀለኛ ነው፤ ደም ሳይመልስ እንቅልፍ አይወስደውም። አባቱን ሰው የገደለበት ልጅ ደም መላሽ ተብሎ ነው የሚጠራው። በምድር ላይ ካሉ ጦረኛ ሕዝቦች የሰሜኑ ሕዝብ አንደኛ ነው። ሁለተኛ እስራኤላውያን ናቸው። እንዲያው ውኃ ቀጠነ ብሎ ዘው ብሎ ጦርነት ውስጥ የሚገባ ሕዝብም አይደለም ዐማራ። ኢትዮጵያን ለብዙ ዓመታት የገዛ፣ በክብርም ያቆያት ነው ዐማራ። በሃይማኖት፣ በባህል የዳበረን ሕዝብ በፍፁም በቀላሉ ማንበርከክ አይቻልም። በሕዝቡ ብዛት፣ በሚኖርበት የምድሩ ቆዳ ስፋት ሲታይ ዐማራ በመላው ኢትዮጵያ ይገኛል። ከዐማራ የተነጠለችን ኢትዮጵያ እያየናት ነው። በዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በእድገት አሁን በዘመነ ኦሮሙማ የት ነው ያለቸው? ጅቡቲ የምትንቃት፣ ሱማሌ የምታሾፍባት፣ ትናንት በራሷ በኢትዮጵያ ድጋፍ የተፈጠሩት ደቡብ ሱዳንና ኤርትራ ግዛቶቿን ወርረው የሚይዙባት። ኬንያ የምትፀየፋት። የዓለም መንግሥታት የማይጎበኟት። ምኖቹ ላይ ጣለሽ ብለው ወዳጆቿ ሁሉ የሚያለቅሱላት ሀገር ነው የሆነችው። ማርያምን ኢትዮጵያንማ ዐማራ ይምራት። ትግሬም መርቷት ያተረፍነውን አይተናል። ስደት፣ ዝሙት፣ ግሉምትና፣ ሌብነት፣ በዘር መከፋፈል ነው ያተረፍነው። ኦሮሞም ይኸው እየመራት አይተናል፣ የዘር ጭፍጨፋ፣ ግድያ፣ ሰው አግቶ ሚልዮኖች መጠየቅ፣ የጉቦ ሕጋዊ መሆን፣ የነውር ጌጥ መሆን፣…👇③✍✍✍
👆②✍✍✍ …ገፊ ምክንያቶች ዐማራው ፋኖ የሚል ኃይል እንዲፈጥር ትልቅ እድል ከፈተለት። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…ዐማራው በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በማእከላዊ መንግሥት ላይ አመጸ። አቢይ በተሳሳተ ስሌት፣ በዕውቀት ማነስ በምዕራባውያን ጫና፣ የፕሪቶርያውን ስምምነት ፈርሞ ሕወሓትን በለመደው የቁማር ፖለቲካ ከጎኑ አሰልፎ ሕወሓት እግረ መንገዷን በቅሏን ትበቀል ዘንድ በመወትወት፣ በመደለል ትግሬን በሌሎች እንዳደቀቀው ዐማራንም በትግሬና በኤርትራ ለማድቀቅ አሰበ። ትጥቅ ፍቱ በማለት ዐማራ ላይ ጦርነት ዐወጀ። ሕወሓትን ያሸነፋት አቢይ ሳይሆን ዐማራው እንደሆነ ሕወሓት በደንብ ስለገባት ድምጿን አጥፍታ አቅሟንም ዐውቃ ከቤቷ ሳትወጣ፣ ከሰፈሯም ሳትንቀሳቀስ ፀባይ ገዝታ ተቀመጠች። የኤርትራው ሻአቢያም የኦሮሞዎቹ አካሄድ ስለደበረው አይመለከተኝም፣ ከዐማራ ጋር አልነካካም ብሎ ኢግኖር ገጨው። ፖለቲካ ቁማር ነው። በቁማር ዓለም ደግሞ ማን ምርጥ ቁማር ተጫወተ ሳይሆን ቁማሩን ማን በላው፣ ጠቀለለው የሚለው ነው። እናም እኔ ዓባይ ማዶ ተሻግሬ ዐማራን ቁማር በልቼዋለሁ በማለት በአደባባይ በወንፊቱ ሽመልስ አብዲሳ በኩል ተነግሮ በእኔ በዘመድኩን በቀለ በኩል ለሕዝብ ይፋ የሆነበትን የኦሮሙማውን ቁማር ሴራ የሰማችው ህወሓት ብር ቢሰጣት፣ ሚሊንየም አዳራሽ አሸንዳን ጨፍሪበት ተብላ በአዳነች አበቤ እንክብካቤ ቢደረግላት። የጥፋት መሃንዲሱን አቦይ ስብሃት ነጋንና በጦርነቱ የተማረኩትን ወያኔዎች በሙሉ ፈትቼላችኋላሁ ብሎ እጅመንሻ ቢያቀርብ ወያኔ ሞኝህን ፈልግ ብላ እሷም እንደ ሻአቢያ ኦሮሙማውን ኢግኖር ገጭታው ብቻህን ተወጣው በማለት እንዲያውም ለምን ዐማራና አቢይ ሲፋለሙ ከሩቅ ሆኜ አልመለከትም በማለት ከዳር ቆማ ማጤን ጀመረች። ተባብረው የወጓት በጦር ሲቀራደዱ እሷ በደስታ እየሰከረች ተመለከተች። በአቢይ ጅልነትና ማይምነት ምክንያት ዋና አጋሩ የሆነውን ዐማራን ያጣውን አቢይን እያመሰገነች ራሷን እያሻሻጠች አገገመች። አቢይ በወቅቱ አብረውት የነበሩትን ሁሉ ሲያጣ፣ ከዳያስጶራው ጋር ሲቆራረጥ፣ ከዚያም አልፎ ከዋናው አጋሩ ከሻአቢያ ጋር እሳትና ጭድ ሲሆኑ እያየች አፈር ልሳ ተነሣች። በጁንታው ጦርነት ወቅት ከአቢይ አገዛዝ ጋር ኢትዮጵያን ብለው የተሰለፉ ክልሎች፣ ቤርቤረሰቦች ለአቢይ ጀርባቸውን ሰጡት። የደቡብ የጴንጤ ፓስተሮች፣ የኦሮሞ የጴንጤና የወሀቢያ እስላም ሓላፊዎች ብቻ አቢይ ከወደቀ እኛም ያበቃልናል በሚል ሰበብ በአደባባይ እየቀሰቀሱ የደቡብና የኦሮሞ ወጣቶች ብቻ በግዳጅ፣ በአፈሳ ጭምር ወደ ዐማራ ክልል ከማዝመታቸው በቀር ሁሉም በዐማራ ጉዳይ ጀርባውን ነው የሰጠው። ሰልፍ የሚወጣ የለም፣ ስንቅ ለሠራዊቱ የሚያቀብል የለም። ሠራዊቱ ደጀን ሕዝብ የለውም። አቢይን ጨምሮ በወያኔ ላይ ከስድብ አንስቶ እስከማዋረድ የሚደርስ መግለጫ ይሰጡ የነበሩት እነባጫ ደበሌ፣ እነአዳነች አበቤ፣ የድሬደዋው ከንቲባ፣ የደቡብ፣ የጋንቤላ፣ የቤኒሻንጉል አስተዳዳሪዎች ዐማራን ወጥተው እንደ ትግሬዋ ሂዊ ለመሳደብ አልሞከሩም። በቃ ዐማራ ይችላል። ቢሮክራሲውም ጠንካራ ነው። ያስፈራል። ይሄን ሁሉ ሳያገናዝብ ነው በጎንደር ስኳድ፣ በጎጃም አገው ሸንጎ፣ በፀረ ዐማራ የኦሮሞ ፖለቲከኞችና በእነ ዳንኤል ክብረት ምክርና አይዞህ ባይነት አቢይ ዐማራን በቀላሉ ትጥቅ አስፈታለሁ ብሎ ዘው ብሎ ዐማራ ግዛት ገብቶ ከፋኖ ጉያ ተወሽቆ በዚያው ሟሙቶ የቀረው። ፋኖም አንድ ጥይት ሲተኮስ ሽምጥ የሚጋልበው መከላከያን በጁንታው ጦርነት ጊዜ አጠገቡ ሆኖ በደንብ የሚያውቀው ተቋም በመሆኑ ምንም ጭንቀት አልገባውም፣ አላሳሰበውም፣ አላስፈራውምም። ውጤቱም ይኸው ባለፉት ሁለት ዓመታት ወደ ዐማራ ቀጠናዎች የሚገባ ሠራዊት እንጂ የሚወጣ ባለመኖሩ ታይቷል።
"…ፋኖ ቀለቡን ከእናት እና ከአባቱ፣ ትጥቁን ደግሞ ከጠላቱ በመበጀት፣ አገዛዙ ላይ በኢኮኖሚ፣ በሰው ኃይል፣ በፕሮፓጋንዳ፣ በወጪ ኪሳራ በማድረስ ራሱን በውጊያ፣ በትጥቅ፣ ከታች ወደ ላይ በመደራጀት፣ በመሰብሰብ፣ የውስጥ ባንዳን በማጥራት፣ ስሕተቱን ከስር ከስር በማረም የመንግሥትነትን ቁመና በመላበስ፣ ነጻ ቀጠና በማስፋት፣ የዐማራ ብልፅግና ተብዬውን የብአዴንን አመራር የማይላወስ፣ ወገቡን የተመታ ጩኸት ብቻ የሚሰማ ውሻ በማድረግ ለመደራደርም ለማሸነፍም የማይመች የእሳት አሎሎ፣ የብረት ቆሎ ሆኖ አሁን ካለበት ቁመና ደረሰ። የፋኖ ጥንካሬ የራሱ ብቻ ሳይሆን የአገዛዙም ስሕተት ነው። በመጀመሪያ የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል እንዲሉ አገዛዙ ወጣቶችን መረሸን፣ ሴቶችን መድፈር፣ አዛውንቶችን ማሰር፣ ቀሳውስትን መግደል ጀመረ። በዚህ ስሕተቱ ወጣቱ ተገፍቶ የፋኖን ትግል በገፍ ተቀላቀለ። ሕዝቡም መከላከያን እንደ ኢትዮጵያ ሠራዊት ሳይሆን እንደ ግራዚያኒ፣ እንደ ደርቡሽ፣ እንደ ግራኝ አህመድ አድርጎ ተመለከተው። ከፋኖ ጎን እንዲሰለፍ አስገደደው። በወለጋና በመተከል ያየውን ጭካኔ በየደጁ እስኪበቃው ተመለከተ። ማዳበሪያ ይሰጠንና አምርተን ሀገር እንቀልብ ብለው በጨዋ ደንብ በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁ የዐማራ ገበሬዎችን "የጅራፍ ቦለጢቀኞች" በማለት አላገጠባቸው። ከሚታረዱት በተጨማሪ አዲስ አበባ ለመግባት የሚታገቱት፣ ታግተውም በኦሮሚያ ባንክ በሰው ሚልዮን ብር የሚጠየቁት ዐማሮች ይህንና ይህን የመሰለውን የኦሮሙማውን አፓርታይድ ሥርዓት ሲመለከቱ "የሕዝብ ልብ" ሸፈተ። ሕፃናቱ፣ አዛውንቱ ፋኖ ፋኖ አለ። አገዛዙ በራሱ ፈቃድ የሕዝብን ወገንተኝነት አጣ። ሠራዊቱ ደጀን የሌለው፣ በሕዝብ ዘንድ የተጠላ፣ ዐይንህን ለአፈር የሚባል ሆነ። አሁን ላይ ሠራዊቱ ሕዝብን አያምንም፤ ሕዝብም ሠራዊቱን አያምንም። ይህ የአቢይ ስሕተት ነው ለዐማራ ፋኖ ዋና የ ጥንካሬ ምንጭ የሆነው።
"…ሌላው፣ መከላከያው ሀገራዊ ስሜት የሌለው ግማሹ የታፈሰ፣ ግማሹ በጥላቻ የሰከረ፣ ዓላማ ቢስ፣ የመዋጋት ብቃት ሞራል የሌለው፣ በፍርኃት የተዋጠ፣ በማያውቀው ነገር እና ሠፈር ለሠፈር የሚንከራተት፣ በቀላሉ የሚጠቃ፣ የሚማረክ፣ የሚኮበልል፣ መሣሪያውን ለፋኖ የሚያስረክብ፣ የአገዛዙን የጦር መጋዘን የሚያራቁት፣ የፋኖን የትጥቅ ፍላጎት በቀላሉ የሚያሟላ ስለሆነ ፋኖን ከሽምቅ ውጊያ ወደ ፊት ለፊት መደበኛ ውጊያ አሳደገው። በሌላ በኩል፣ የአቢይ ጀነራሎች ችሎታ ማነስ፣ በሙስና መዘፈቅ፣ በመሣሪያ ንግድና በሰዎች ሕገ ወጥ ዝውውር መሰማራት፣ የአንድ ብሔር የበላይነት ጎልቶ መታየት፣ እርስ በርስ አለመተማመን፣ በሚካሄደው ጦርነት አለማመን፣ ጊዜን ጠብቆ መክዳት፣ የግል ጥቅምን ማሳደድ፣ መረጃን በቀላሉ ለፋኖ ማሾለክ፣ ውጊያን ማበላሸት፣ በሁለት ቢላ መብላት፣ አንድ እግራቸውን ከአቢይ አንድ እግራቸውን ከፋኖ በማድረግ የአገዛዙ ሠራዊት በደፈጣና በውጊያ፣ በምርኮና በኩብለላ እንዲያልቅ በማድረግ የዐማራ ፋኖ በአጭር ጊዜ ውስጥ ራሱን ግዙፍ ጠንካራ ወሳኝ ኃይል ሆኖ እንዲገለፅ ረድቶታል። አቢይ ዐማራ እና ልምድ ያላቸው ሆነው ብአዴኖች እንኳ ቢሆኑ ብሎ የሚጠረጥራቸውን እንኳ የማይምር መሆኑ፣ ሕዝብ ይወዳቸዋል፣ ያዳምጣቸዋል፣ የሕዝብ ተቆርቋሪዎች ይሆናሉ ያላቸውን በሙሉ በመግደል፣ በማሰር፣ በማባረር፣ ጡረታ በሚል በማሰናበት አስወገደ። በምትካቸው የተሾሙትም በሆዳቸው እንጂ በራሳቸው የማያስቡትንና ሞግዚት የሚያስፈልጋቸውን ሾሞ ሲያለቅስ የሚያለቅሱ፣ ሲስቅ የሚስቁ አቅመ ቢሶች፣ የፖለቲካ ዐይነ ስውራን፣ ጀነራሎች ቁጭ ብድግ የሚያሰኟቸው ድኩማን በመሆናቸው ፋኖ እንዲጠነክር አድርጎታል። ፋኖን ይመክታል የተባለው ሚሊሻና አድማ በታኝ አሁን ልብ ወደ መግዛት እየተመለሰ ነው። በገፍም…👇②✍✍✍
"ርእሰ አንቀጽ"
• የአቢይ አወዳደቅ
"…አቢይ ዋና ችሎታው ማስመሰል ሲሆን የወረሰውም ከአባቱ ከሕወሓት ነው። ነገር ግን የሕወሓት ትወና ብልኃት፣ ጮሌነትና ጥንቃቄ የተሞላበት፣ ትወናው በስውር የሚከናወን ነው። በተቃራኒው የአቢይ ትወና በሸፍጥ፣ በገሐድ፣ በጅልነት፣ በማይምነት የሚፈጸም ድንጋይ ዳቦ ነው የሚል ቂልነት የተጠናወተው፣ የተቀደደ ስልቻ ይመስል በሽመልስ አብዲሳ በኩል የሚያንዘረዝር ወንፊት፣ መቆጣጠሪያ የሌለው አቁማዳ፣ ካልተነፈሰ የሚፈነዳ የሚመስለው፣ ከዚህ በፊት የመምራትም ሆነ የማስተዳደር ልምድ የሌለው ጥራዝ ነጠቅ፣ በአጋጣሚ ሥልጣን ከእጁ የገባ፣ የታሪክና የዕውቀት ደሀ፣ የሥልጣን ጥመኛ፣ የማንነት ቀውስ የተጠናወተው፣ ካየው ሰፋሪ፣ ሁሉ ኬኛ ባይ፣ ያልሰከነ ዛር፣ ቀምቶ፣ ወንብዶ፣ ሸፍቶ፣ ዋሽቶ ሲበላ ሲቀማ የኖረ ወፈፌ በመሆኑ ሀገርን በቅጡ አይረዳም። ሥልጣን እንዴት ማቆየትና ማሻገር እንዳለበት አያውቅም፤ ችሎታም የለውም። ከጎኑ ያሰለፋቸው ሰዎችም የተለያየ ዓላማ ያነገቡ ናቸው፤ በዕውቀትም ከእሱ ያነሱ ናቸው። ኢትዮጵያን የምታህል ታላቅ፣ በዓለም የተከበረች፣ የተፈራች፣ ልዩ ስፍራ የሚሰጣትን ሀገር ይቅርና የአንዲት አነስተኛ መንደር ዕድር እንኳ መምራት የማይችሉ ደካሞች ናቸው። አማካሪዎቹ የራስ ማንነት የተጫናቸው፣ ግላዊ ሰብእና የሚያስጨንቃቸው ተዋናዮች፣ ዘፋኞች፣ ሞዴላ ሞዴሎች ናቸው። እንደ ዳንኤል ክብረት ያሉ በዲፕሎማ የእነዋሪ ተለማማጅ መምህር፣ የሰውን ታሪክና ሥራ በመቀማት የሚኩራሩም ቀማኞች ሁሉ ናቸው አጠገቡ የኮለኮሏቸው።
"…ብታምኑም ባታምኑም ከፈለጋችሁ ይህን ርእሰ አንቀጽ ለታሪክ አስቀምጡት። የአቢይ ፍጻሜ እጅግ በጣም የከፋ ነው የሚሆነው። የእሱ ውድቀት ከሁሉ እጅግ ከባድ ነው። የእሱ ውድቀት እንደ ግርማዊ ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ አይደለም። የእሱ ውድቀት እንደ ደርጉ መንግሥቱ ኃይለማርያም አደይለም። የእሱ ውድቀት እንደ ወያኔ ሕወሓት እንደ መለስ ዜናዊ እንደ ስብሃት ነጋ የዓድዋው ስርወ መንግሥት ያለ አወዳደቅም አይሆንም። የእሱ ከሁሉ የከፋ ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት እንዳለው "…ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም። ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ፤ ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል፤ ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።) መዝ፥ 14፥ 3-6 …እንዳለ ነቢዩ ሁሉም አንድ ሆኖ የደነቆረበትና የወነጀለበት ጊዜ ነውና አወዳደቁም ሲታሰብ ያስፈራል። ጊዜው ታጣቂዎች እንደ አሸን የፈሉበት፣ የሕግ የበላይነት የተናደበት፣ ዝቅም ያለበት፣ ወሮ በላ ዘራፊ ቀማኛ ዱርዬ የሰፈር ሽፍታ የበዛበት፣ ዘመነ መሳፍንትን የሚያስንቅ ጊዜ ነው። በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ውድቀት እሳቸውና ሥርዓቱ ብቻ ነበር ተለይተው የወደቁት። የዘውዳዊው ሥርዓት በዚያ መልክ መውደቅ ደስ ባያሰኝም ሀገሪቱ ግን ቀጥላለች፤ በደርግም ጊዜ አመራሮቹን ወያኔ ገሚሱን እንዲሰደዱ አድርጋ፣ ገሚሱን ገድላ ቀሪዎቹን በወኅኒ ቤት ዘብጥያ አቆይታ፣ የሞተው ሞቶ በሕይወት ከቆዩት መካከልም በምህረት ነፃ ወጥተው እስከአሁን በነፃነት የሚንቀሳቀሱ ሁሉ አሉ። ደርግ ወደቀ መንግሥትና ሀገር ግን ቀጠለ። በሕወሓትም እንደዚያው ነው። የወያኔ አመራሮች እህል ውኃቸው ሲያልቅ ገሚሱ ተሰደደ፣ ገሚሱ ጫካ ገባ፣ ገሚሱ ወደ ትግራይ ተሰደደ፣ ጥቂቶች ከዚያም ከዚህም እየተጫወቱ መሃል ላይ ቀሩ። ጥቂት የማይባሉትም በኤርትራና በኦሮሞ ብልጽግና ተገደሉ። አሁን ግን ሀገራችን እንደ ሦስቱም መንግሥታት አይደለም የምትሆን የሚመስለው። መለኮታዊ ጣልቃገብነት ከሌለ በቀር ሀገሪቱ ከአቢይ ጋር አብራ የመንኮታኮት አደጋ ነው ከፊቷ የተጋረጠባት።
"…አቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን እንደመጣ በቀላሉ የመምራት ዕድል ያለ መስሎት በመርገጥ፣ በመደፍጠጥ፣ በመጨፍጨፍ፣ ሰጥ ለጥ አድርጎ የኦሮሙማን ፍላጎት ለማሳካት በበላይነትም ለማስጓዝ አቅዶ የሄደበት ርቀት አሁን ላይ የሌለ እና ከማይወጣበት ቅርቃር ውስጥ ከቶታል። አሁን ያለውን ሁኔታ አስቀድሞ ተረድቶ ቢሆን ኖሮ በእርግጠኝነት አቢይ አሕመድ ፈጽሞ አይሞክረውም ነበር። የሰሜኑ ጦርነት ለአቢይም፣ ለፋኖም፣ ለሕወሓትም ያልተገመተ ክስተት አሳይቷቸዋል። ሕወሓት በተነሳበት ተቃውሞ በአሜሪካ ግፊት በቀላሉ ከአራት ኪሎ ወደ መቀሌ ሲዛወር የሕዝብን ቁጣ አብርዶ፣ አስተማማኝ ኃይል ገንብቶ፣ እፎይታ ወስዶ፣ ብሔር ብሔረሰቦች የሚለውን አሰልፎ፣ አቢይን ፈንቅሎ መልሶ አራት ኪሎ እንዲደላደል ነበር። ግን የሆነው ግልባጩ ነው። አቢይ ወያኔ ራሷ ጠፍጥፋ በአምሳሏ የፈጠረቻቸውን ብሔር ብሔረሰቦችን ከራሷ ቀምቶ፣ እነሱኑ ጠመንጃ አስይዞ አሰልፎ ከጎረቤት በወያኔ ላይ የ20 ዓመት ቂም ይዛ ምቹ ቀን ትጠብቅ የነበረችዋን ኤርትራን ጨምሮ የሕወሓትን ወንጀል በእጥፍ አባዝቶ በከፍተኛ ቅስቀሳ የሕወሓትን ሕልም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አመከነ። ሕወሓት አሁን የሚጮኸው ስለ አራት ኪሎ አይደለም ስለ ሕልውናው እንጂ። አከተመ።
"…የሰሜኑ ጦርነት ለአቢይ አሕመድ የፈጠረለት ስሜት ቢኖር እንዴት በቀላሉ ጦርነት ማሸነፍ እንደሚችል ነው። ሰማይ የደረሰው ፈርኦን ናቡከደነፆሩ ሕወሓት በዚህ ደረጃ መውደቁን ሲመለከት ጦርነትን ዋና የስልጣኑ ማቆያ ቁልፍ ጉዳይ አድርጎ መቁጠር ነው የጀመረው። ሕወሓት በኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸመችው ግፍ በሕወሓት ላይ ቂም የነበረው ሁላ ያን ቂሙን ይወጣ ዘንድ በብሔራዊ ቴሌቭዥን እና ራዲዮ፣ በጋዜጣ፣ በፓርላማ፣ በዘፈንና በድራማ፣ በሰልፍ ጭምር እየተቀሰቀሰ ሙሉ ኢትዮጵያ ተሰልፎ ሕወሓት የወጋበትን ምስጢር አለማወቁም ነው ዳግመኛ ከዐማራም ጋር ብዋጋ ልክ እንደ ሕወሓት ጀማውን አንቀሳቅሼ ልክ አገባዋለሁ ብሎ በተሳሳተ ስሌትና ቀመር እንዲንቀሳቀስ አደረገው። ትግሬን አግዝፎ፣ ዐማራን ንቆ አቅልሎ ገባበት። መግባት ግን እንደ መውጣት ቀላል አልሆነለትም። የዐማራው ምድር ረግረግ ሆኖ ዋጠው። ሰለቀጠው። ኢትዮጵያንም በሁሉ ነገር ሽባ አደረጋት። እነ ብርሃኑ ጁላ፣ እነ ባጫ ደበሌ፣ እነ ሽመልስ አብዲሳ፣ እነ አዳነች አበቤ፣ አማካሪዎቹ እነ ዳንኤል ክብረት በተረት፣ በፉከራ፣ በማዋረድ፣ በማቅለል ያላግጡበት የነበረ ዐማራ ዛሬ ሁላቸውንም ሳይለንት ሙድ ላይ ቆልፎ አስቀመጣቸው። አሞሌ ጨው የለ፣ ጃዊሳ፣ ኩይሳ፣ ፈይሳ፣ ጃርት የለ፣ ሽፍታ፣ ፅንፈኛ… ዝም። ጭጭ።
"…የሰሜኑ ጦርነት ለዐማራው ኃይል ደግሞ የፈጠረው ስሜት ከሕወሓትም ከአቢይም የተለየ ነው። አይደለም ጠብመንጃ በትር እንኳ በእጁ እንዳይዝ የተከለከለው ዐማራ የሕወሓት ወሎን አልፋ ደብረ ሲና መድረስ ያስጨነቀው ኦሮሙማ በብአዴን በኩል ተዋጋልኝና በምትኩ ከህወሓት የምትማርከውን መሳሪያ ማርከህ እስከ አፍንጫህ ድረስ ታጠቅ ተባለ። እግዚአብሔርም የተገፋውን ዐማራ በጥበብ አገዘው። ከዘመነ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ጀምሮ እስከ ዘመነ አቢይ አሕመድ ድረስ የላሸቀው ዐማራም ወኔው ተቀሰቀሰ። አቢይ በዐማራው ላይ ሊያደርግ ያሰበውን ጭፍጨፋ ዐማራው በሰሜኑ ጦርነት በቅርበት ከመከላከያ ጎን በመሆን ተረዳ። ለወደፊት ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበትም ወሰነ። በወለጋ፣ በመተከል የተደረገው የዐማራ ጭፍጨፋ፣ ከማእከላዊ መንግሥቱ የዐማራው በገፍ መገለል፣ የነሽመልስ አብዲሳ የኦሮሞ ቦለጢቀኞች በሙሉ የሰበርናቸውና ዓባይን ተሻግረን ቁማር በላናቸው ቀረርቶ፣ በሌሎችም…👇①✍✍✍
መልካም…
"…ለትናንት አርብ ተዘጋጅቶ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወደ ዛሬ የተሸጋገረው ርእሰ አንቀጻችን አሁን ይቀርብና እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ስንወያይበት እናመሻለን። ይህን ከሊቃውንተ ኢትዮጵያ ጋር በነበረኝ ጉባኤ ወቅት የያዝኩትን ማስታወሻ በርእሰ አንቀጽ መልክ አዘጋጅቼ ለእናነተ ለወዳጅ ጓደኞቼ ሳቀርብ ታላቅ ኩራትና ደስታ ነው የሚሰማኝ።
"…ከኔፓል የተነሳው የለውጥ ፈላጊ ወጣቶች እምቢተኝነት ማዳጋስካር ገብቶ፣ አምባገኑን በአፍጢሙ ደፍቶ፣ በፈረንሳይ ጀት፣ ወደ ኤምሬትስ አስፈርጥጦ በታላቅ ድል ተጠናቅቋል። አፍሪካ የገባው የለውጥ ፈላጊዎች ዐመጽ በካሜሮን እየጋመ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ በምሥራቅ አፍሪካ ታንዛኒያም ሰተት ብሎ ገብቷል። የታንዛኒያው ደግሞ የተለየ ነው።
"…በታንዛኒያ ፕሬዘዳንቷ ወሮ ሳሚያ ሱሉሁ በምርጫ 98% ከመቶ አሸንፌአለሁ ብላ በብርቱካን ሚደቅሳ መሳይ ምርጫ ቦርዷ በኩል ዐወጀች። ሕዝቡም እንደ ኢትዮጵያ ሕዝብ " አቤት ውሸት፣ ምንአይነቷ አጭበርባሪ ናት? ትልቅ ሰው ይዋሻል እንዴ? በስመአብ፣ ቢስሚላሂ፣ ጌታ ሆይ ድረስ። ፈጣሪ የአንቺን መጨረሻ ያሳየኝ ብሎ ወደ ቤቱ ገብቶ መተኛትን አልመረጠም። ይልቁንም ግልብጥ ብሎ ነቅሎ አደባባይ ወጣ። ውረጂ፣ አልመረጥንሽም በማለት ሰቅዞ ያዛት። ፕሬዘዳንቷም እንደ ወያኔ፣ እንደ ኦሮሙማው እስቲ ጥቂቶችን ገድዬ ብዙሃኑን በማስደንገጥ አስደንብሬ አመፁን በእንጭጩ ልቅጨው አለችና ሰልፈኛው ላይ ተኩስ ከፈተች። 700 ሰውም ገደለች። ሕዝቡ ግን ጭራሽ ባሰበት። በመላው ሃገሪቱ አደባባይ ወጣ። ፎቶዋን ገንጥሎ እሳት ውስጥ ዶለው። አቃጠለውም። በመጨረሻም ወታደሩ ክፍል መሪዎቹ ኦሮሞ ብቻ ስላልሆኑ የለም፣ የለም ይሄነገር ያበቃለት ነው፣ ከአንዲት ሴት ጎን ቆመን ሀገር ያህል ከምናጣ ከሕዝብ ጎን እንቁም። ግድያም እናቁም በማለት ዜጎቻቸውን መግደል እንዳቆሙ። ከሕዝቡም ጎን ተሰልፈው እንደ ሕዝቡ ሆነው መጨረሻውን እያዩ እንደሆነ ነው እየተነገረ ያለው።
"…ልብ በሉ የታንዛንያዋ ፕሬዜዳንት እንደ አቢይ አህመድ አንድ ሚልዮን ትግሬ አልጨፈጨፈችም። ቁጥሩ እስከአሁን ያልተገለጠ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር ዐማራ እንደጨፈጨው ዓይነት ጭፍጨፋ አልፈጸመቺም። ያደረገችው ነገር ቢኖር ልክ እንደወያኔ፣ እንደ ብልፅግናውን ጠልፋ 98% አሸንፌአለሁ ስላለች ብቻ ነው የታንዛኒያ ሕዝብ ከቤቱ ወጥቶ አደባባዩን ሞልቶ ሰማይ ምድሩን እያንቀጠቀጠው የሚገኘው። እንጂ ቤቱ፣ ትዳሩ፣ ንብረቱን፣ ሀገሩን እንደተነጠቀው፣ በሃላል እንደተጨፈጨፈው፣ እንደታረደው እና 120 ሚልዮን ኢትዮጵያዊ ጄኖሳይድ ተፈጽሞበት አይደለም። ልዩነቱ ግን ታንዛኒያውያን ይሄ "በኃጢአታችን ምክንያት እግዚአብሔር ያመጣብን ቁጣ ነው" ብለው እጃቸውን አጣጥፈው፣ አፋቸውን ለጉመው፣ ወደ ቤተ ክርስቲያንና ወደ መስጊድ በመሄድ ጌታ ሆይ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤልን ሰይፍ አስይዘህ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስን ጦር አስይዘህ ይሄን አረመኔ ገላግልልን አለማለታቸው ብቻ ነው። ወዳጄ ይልቅ እንደ ፋኖ የቅዱሳን መላእክቱን ሰይፍ፣ የሰማእቱን ጦር ይዞ ዓድዋ ድረስ ሄዶ ዘምቶ ድል እንደማድረግ አቡነ ሳዊሮስ እግር ላይ ተደፍቶ የሥርዓት ለውጥ መጠበቅ ኃጢአት ነው። ለማንኛውም ሥርዓቱ ይወድቃል። ሲወድቅ ላያችን ላይ እንዳይወድቅ ምን እናድርግ በሚለው ዙሪያ በጊዜ መወያየት መጀመር መልካም ነው።
"…መልካም… አሁን አመስጋኙ አንድ ሺ ሰው ሞልቷል። ለትናንት ተዘጋጅቶ የነበረው ርእሰ አንቀጹን ለዛሬ ልለጥፍላችሁ ነኝ። እስከዚያው የታንዛኒያውን አጫጭር ቪዲዮ እያያችሁ ርእሰ አንቀጹን ለማንበብ፣ አንብቦም በጨዋ ደንብ ሓሳብ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ…?
• እስኪ አንድ 100 ያህል ሰው "ዘመዴ ዝግጁ ነነ" ይበል። ✍✍✍
1.76 MB
3.73 MB
7.85 MB
6.39 MB
Photo unavailableShow in Telegram
"…እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው፤ ክፋትን አያደርግም፤ ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም፤ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም። ሶፎ 3፥5
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
መልካም…
"…ዛሬ በዕለተ አርብ በሳምንቱ መጨረሻ በእኔ በዘመዴ ፔጅ ይቀርብ የነበረው ተጠባቂው ርእሰ አንቀጻችን ከሊቃውንተ ኢትዮጵያ ጋር በነበረን ውይይት ላይ ከተያዘ ማስታወሻ ተውጣጥቶ በግሩም ሁኔታ ተዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም እንደ ድንገት ባየሁት የሱዳን የንጹሐን ጭፍጨፋ ምክንያት በትክክል ማሰብ፣ ጣቶቼንም በትክክል ለማዘዝ በመቸገሬ ምክንያት ሳላቀርብላችሁ ቀርቷል።
"…ነገ በጠዋት በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ከጠዋቱ የሥራ መጀመሪያ የምስጋና መርሀ ግብራችን በኋላ ግን ተዘጋጅቶ የተቀመጠ ስለሆነ በቶሎ እለጥፍላችኋለሁ።
"…የተባበሩት አረብ ኤምሬት በሱዳን የግመል ነጋዴውን ሀሜቲ የመሀመድ ደጋሎን ፈጥኖ ደራሽ ጨፍጫፊ አሸባሪ ቡድን፣ በኢትዮጵያም የኦሮሞ ብልጽግና ወንጌል ፕሬዘዳንቱን አቢይ አሕመድን ይዛ ንፁሐንን በመጨፍጨፍ፣ በማስጨፍጨፍ፣ ለሀሜቲና ለአቢይ ድሮን ከእነ ኦፕሬተሩ፣ ከነ ቦንቡ፣ ጠመንጃ ከነ ጥይቱ፣ ዶላር በኮንቴነር እየሰጠች እሷ በምትኩ የሱዳንና የኢትዮጵያን ወርቅና መዓድነት ያለከልካይ ትዝቀዋለች፣ ታግዘዋለችም።
"…በሱዳን መልካቸው ጠቆር ያሉት ሱዳናውያን እናንተ አረቦች አይደላችሁም ተብለው ለዘር ሳያስቀሩ ጨፍጭፈዋቸዋል። ክርስቲያን ሱዳኒዎችም ከጭፍጨፋው አልተረፉም። አላመለጡም። አላህ ወአክበር እያሉ ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ ነው የፈጇቸው። በተለይ እናቶችና ሕጻናቱ እንዴት አንጀት እንደሚበሉ አትጠይቁኝ። አላሃቸው ግን ምን አይነት ነው በማርያም? አንዲት ሴት እጇን አስረው አንጠልጥለው የሚፈጽሙባትም ግፍ ይዘገንናል። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕም የሱዳኑን ጭፍጨፋ ሳይጠቅሱ በዓለም ላይ ክርስቲያኖች እና ክርስትና ጥቃት እየደረሰበት ነው በማለት የናይጄሪያው ቢኮ ሃራም ላይ እንደዛቱ ፎክስ ነውስ ለጥፎም አይቻለሁ።
"…በኢትዮጵያችን በኦሮሚያ አሩሲ እንደዚሁ እንደ ሱዳኑ ያለ አረመኔያዊ ግፍ ነው የተፈጸመው። ሕፃን ሽማግሌ አልቀራቸውም። ጭፍጭፍ ነው የደረጓቸው። የሱዳኑ በስልክ እየቀረጹ ቀጥታ በቲክቶክና በፌስቡክ ነው የለቀቁት። የበተኑት። የእኛዎቹ እሱን ተከልክለው ሕዝቡ ነው አስከሬንና ዋይታውን ቀርጾ ዓለም ይመልከተን ያለው። የብልጽግና አገዛዝ እስከአሁን ትንፍሽ አላለም። የሱዳኑ ዓለም አቀፍ ጫጫታ ሲበዛበት ዋናውን ጨፍጫፊ በክብር አስረው ወደ ማረፊያ ወስደውታል። የኢትዮጵያዎቹ ማን አባቱ ነው የሚጠይቀን በማለት ጭራሽ ለቢቢሲ "ውሸት ነው" ሐሰት ነው የተጨፈጨፈ የለም በማለት ለሚዲያው ቃላቸውን ሰጥተዋል።
"…ሲኖዶሱ ከስንትና ስንት ውትወታ በኋላ "እንደማንም ተራ ነገር በጉዳዩ አዝነናል" የሚል አናዳጅ፣ አብሻቂ መግለጫ ሰጥቷል። የኦሮሞ ብልጽግናን የገጽታ ግንባታ ለመከላከል ሲባልም ገዳዮቹን " ያልታወቁ ኃይሎች" በማለት ዘግበዋል፣ መግለጫም አውጥተዋል። ይሄን ባለቤቱ ያቀለለውን ዐሞሌ የጰንጤ፣ የእስልምናና የኦሮሞ የሃይማኖት ጉባኤ ተብየዎችም "ቤተ ክርስቲያኒቱ የሰጠችውን መግለጫ ዋቢ አድርገው እሷ እንዳለችው "ባልታወቁ ኃይሎች በተወሰደው ግድያ አዝነነናል" የሚል የለበጣ መግለጫ አውጥተዋል። እነ ኢቲቪ፣ ዋልታ፣ አሚኮ፣ ፋና፣ ኦቢኤምም ዝም ጭጭ ብለዋል። ኦኤምኤንም ትንፍሽ አላለም።
"…የአሩሲው ሊቀጳጳስ አቡነ ያሬድ ሀገረ ስብከቱ ሄደው አያውቁም። አሁንም አሜሪካ ከርመው አርፈው ነው የመጡት። አሜሪካ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳኑ ቀሲስ በላቸው የሚመሩት የቅዱስ ዮሐንስ ምእመናን ተራ ገብተው ሲቀልቧቸው ከርመው፣ በመጨረሻም ዶላር ተሸክመው ሀገር ቤት ከገቡ ገና ሳምንት ቢሞላቸው ነው አሉ። በጌታቸው አሰፋ ምክትል በያሬድ አማካኝነት በዘር ኮታ የተሾሙት አቡነ ያሬድ በሥልጣን ዘመናቸው ኦሮሙማው ከወይብላ ማርያም ጀምሮ የሚፈጽመውን ጭፍጨፋ እኔን አትንኩኝ እንጂ ምን አገባኝ በሚል ስሜት በደንታ ቢስነት መንጋውን ማስጨፍጨፋቸውን ቀጥለውበታል። የሚገርመው ነገር አሁን እንኳ ከሞት ተርፈው ሀኪም ቤት ያሉትን ሕጻናት እነ አቡነ ሳዊሮስ፣ ያሬድ መጎብኘት፣ ማጽናናት ሳይፈልጉ በመቅረታቸው ምክንያት የወላይታው ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ቦታው ድረስ ሄደው ሊያጽናኑ እንደሆነ ነው የሰማሁት። በረከታቸው ይደርብን።
"…እኔን ትንፋሼን አሳጥሮ መጻፍ እስኪያቅተኝ ከፈጣሪዬ ጋር ሲያሟግተኝ የዋለውን ቪድዮ እያያችሁ ነግ በእኔ እያላችሁ እደሩልኝ። በነገራችን ላይ ኤምሬት ለሱዳኑ ሀሚቲ ከደቡብ አሜሪካ ከኮሎምቢያ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮችን ዶላር እየከፈለች ሶማሊያ ላይ በተከራየችው ወደቧ በኩል በገፍ እንደምታስገባም ዘገባዎችን እያየሁ ነበር። በዐማራ ክልልም የሚፈነዳውን ቦንብ ድሮን ኦፕሬት የሚያደርጉት ኤምሬት ቀጥራ ያመጣቻቸው ሲሆኑ አስተኳሾቹ ግን ኦፒዎቹ እዚያው ጎጃም፣ ጎንደር፣ ሸዋና ወሎ ያሉ ዐማሮች ናቸው ይባላል።
"…ዘመናዊ ቀኝ ገዢ ለመሆን አፍሪካውያንን እየፈጀች ማዕድኑንም ዝቃ አፍሳ እየወሰደች ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች እየገነባች፣ ለመዝናናት ደግሞ እኔው ጋር ኑ እያለች በንፁሐን ደም እየተገነባች የምተገኘውም ባቢሎን ኤምሬት ዱባይም እንደሰዶምና ገሞራ መጥፋቷ አይቀርም። ይሄ የጊዜ ጉዳይ ነው። ሱዳኖችም በአቢይ አሕመድ ምክንያት ኢትዮጵያም አብራ ነው የጨፈጨፈችን የሚል ክስ ማቅረብ ጀምረዋል። ይሄ የጠንቋይ የመተት የአስማት ባለዛር የኦሮሞ ብልፅግና መሪ ከሁሉ አጣልቶን ምን ዓይነት መዓት እየጠራብን እንደሆነ ፈጣሪ ይወቅ።
• ደኅና እደሩልኝ የነገ ሰው ይበለን። 🙏🙏🙏
2.40 MB
2.77 MB
4.49 MB
14.07 MB
3.17 MB
❤ 829🙏 241💔 143👍 98🤔 12✍ 11🏆 9🕊 8👌 7🔥 3😱 2
ከደጋው መብረቅ ኮር የተሰጠ የአንድነት ብሥራት መግለጫ
የአማራ ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ሞት ከጥላው የቀረበ መሆኑንና የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የአገዛዙ ኃይልና አማራ ጠል ኃይሎች በአማራው አንገት ላይ ያለማቋረጥ ሠይፍ እያሳረፉ ያሉበት ጊዜ መሆኑን ለአፍታም እንኳን የማንዘነጋው ጉዳይ ነው። አማራን በሌሎች ወገን ሕዝቦች ለማስጠላት የተኬደበት ርቀትም ረጅም ነው፤ በቢሮክራቲክ ተቋማት፣ በፖለቲካዊ ሹመት፣ በዲፕሎማሲው ረገድ ሳይቀር አማራው ከፍተኛ በደል እየደረሰበት ይገኛል፡፡ የአማራ ፋኖን ትግል በድል ለመቋጨት የአማራ የህልውና ታጋዮች አንድነት ወሳኝ ነው፡፡
እኛ የአማራ ፋኖዎች ወደ በረሃ የወረድነው፣ ቤታችንን ዘግተን ዱር ቤቴ ያልነው፣ የአማራ ሕዝብ ላለፉት ዘመናት በጎበጠ የፖለቲካ ትርክት ምክንያት ተገዳይና ተሳዳጅ መሆኑ እንዲያበቃ፣ ነጻነቱን እንዲያገኝ ነው። እኛን ከክፋት ሠሪዎች ጋር ፊት ለፊት በጠመንጃ አፈሙዝ እንድንጋፈጥ ያደረገን ወገናችንን በሀገሩ ላይ ከእኩልነት ደረጃ አውርደው በሕልውና ጥያቄ ቅርቃር ውስጥ ስላስገቡት ነው። የአማራ ሕዝብ የህልውናና የፍትሕ ትግል በሞራል፣ በሰብአዊነት፣ በሃይማኖት፣ በማኅበራዊና ዓለም አቀፋዊ የሕግ ሚዛኖች ሁሉ ፍትሓዊ ብቻ ሳይሆን ሰው ሆኖ መፈጠር የሚያስከትለውን ራስን በክብር የመጠበቅ ተፈጥሮአዊ እዳን የመክፈል የማይቀር ትግል ነው።
ታላቁ ሰማዕት ፕ/ር አሥራት ወልደየስ “አማራ የለም” ለሚሉ ጠላቶች ምላሽ ሲሰጡ “አማራ የለም ትላላችሁ፤ ለመግደል ስትፈልጉት ግን ታገኙታላችሁ” እንዳሉት ጠላቶቻችን በጅምላ ሊጨፈጭፉን የሚፈልጉን ሕዝቦች ነን፡፡ ይኸውም ከወለጋ እስከ ባሌ፣ ከሞያሌ እስከ ማይካድራ ድረስ የተደረገ የትላንት ታሪክና እስከ ዛሬ የቀጠለ በአለም ፊት በገሃድ እየተፈጸመ ያለ ሐቅ ነው፡፡
ጠላቶቻችን መርጠው የማይገድሉን፣ በጋራ የዘመቱብን፣ በአማራነታችን ብቻ በጅምላ የሚፈጁን ከሆነ እኛ በአንድነት በመሠለፍ ትግላችንን ከድል ምዕራፍ ለማድረስ የሚያግደን ምናለ? ሥልጣን ነውን? ገዳይ በበዛበት፣ ሕዝባችን ዕለት ዕለት እየሞተ ባለበት ሁኔታ የትኛው ሥልጣን አጓጉቶን ነው? ዝና እና ሕዝበኝነት ነውን? ሕዝባችን በሞትና በስደት መከራ በሚያይበት ሀገር ላይ ሆነን እኛ ታጋዮች ስለ ምን ዝና መናገር እንችላለን? ፍትሕ በተጓደለበት ሕዝባችን ፊት ስለምን ዝና ልናወራ እንችላለን? ኃብትና ገንዘብ ነውን? ለመሞት ወስነን ዱር ቤቴ ያልን መቼና እንዴት በምን ሁኔታ ልንሞት እንደምንችል እያወቅን ኃብትና ገንዘብ ምናችን ነው? ለአንድነታችን እንቅፋት የሚሆንብን ምክንያት ሁሉ ከሕዝባችን ክብርና ሕልውና በታች ነው፡፡ ሆኖም ግን ሰበብ በማብዛት አንድ ላይ ለመቆም የሚቆዝም ቢኖር ከጠላቶቻችን ጋር የተሰለፈ አልያም ለግል ፍላጎቱ ያደረ ነውና ባንዳ መሆኑን በዚህ እናውቀዋለን።
ስለሆነም እኛ ቀደም ሲል የአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አመራሮች ከአፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ አመራሮች ጋር በአማራ ሕዝብ የትግል መስመር፣ መዳረሻ ዓላማና ግብ፣ መዋቅራዊ የግንኙነት መስመር፣ የትብብርና የአጋርነት ማዕቀፍ ላይ ባደረግነው ተከታታይ ጥብቅ ውይይት በዝርዝር ከተወያየን በኋላ ከዚህ ቀደም የነበሩ ቅሬታዎችን በወንድማዊ ይቅርታ በመዝጋት ፍጹም መግባባት ላይ ደርሰናል፡፡ በመሆኑም ይህ መግለጫ ከተሰጠበት ከዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የደጋው መብረቅ ኮር በሚል አምስት ክፍለ ጦሮችን የያዘ አደረጃጀት ያለው ግዙፍ ኃይል አደራጅተን በአፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጋር በመዋሐድ በአንድ መዋቅር ለመታገል መስማማታችንን አንድነታችንን ለምትናፍቁ ወገኖቻችን ስናበሥር በታላቅ ደስታ ነው።
በደጋው መብረቅ ኮር የተካተቱ ክፍለጦሮች:-
1. ፅናት ክፍለጦር
2. ደጀን ክፍለጦር (የቀድሞው የደጋው መብረቅ ክ/ጦር)
3. አንሻ ሰይድ ክፍለጦር
4. ሰንጥቅ ክፍለጦር
5. ቀኝ-አዝማች ተበጀ ክፍለጦር እንዲሁም በሻለቃ አደረጃጀት ያሉ ሀይሎችን ያካተተ ኮር መሆኑን ለመላው የትግሉ ደጋፊ እና ታጋዩ መግለፅ እንፈልጋለን።
የደጋው መብረቅ ኮር አመራሮች እና ኃላፊነታቸው ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ሰብሳቢ ……………………… አርበኛ ኃብቴ አባቡ
ወታደራዊ አዛዥ ……………. አርበኛ ተመስገን አለባቸው
ምክትል ወታደራዊ አዛዥ …... አርበኛ ማረጉ አስፋው
ፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ………… አርበኛ መ/ር ብርሃን አረጋ
ዘመቻ ኃላፊ …………………. አርበኛ አስፌ አበጋዝ
ም/ል ዘመቻ………………………. አርበኛ ጨለፍ ተስፋው
ሎጂስቲክስ …………….…….. አርበኛ መሳፍንት ደሴ
ቃል አቀባይ ………………….. አርበኛ መ/ር መኩሪያ አጋዥ
ፋይናንስ ……………………… አርበኛ 10 አለቃ ሙላቱ ሰጠ
ም/ል ፋይናንስ...................አርበኛ ፍቅር አራጌ
የሰው ኃብት አስተዳደር …….. አርበኛ መካሽ የኋላው
መረጃና ደህንነት ……………. ***
ስልጠና መምሪያ ……………. አርበኛ 100 አለቃ ሲሳይ
ም/ል ስልጠና መምሪያ.......አርበኛ ጋሻው ቢያርጎ
ሕግ ክፍል ..............አርበኛ 100አለቃ ፈለቀ ጌትነት
ህክምና መምሪያ……………………… አርበኛ ዶ/ር መላኩ የሻነው
ወታደራዊ አስተዳደር …………………… አርበኛ ናቲ ውዱ
ም/ል ወታደራዊ አስተዳደር...............አርበኛ ውበት ደምሴ
ሚዲያ ክፍል………………………. አርበኛ እሸቱ አባተ
ኦርዲናንስ ................................አርበኛ ሙሉጌታ አሻግር
ሴቶች ጉዳይ ………………… ፋኒት መቅደስ ብርሃን
የሕዝብ አስተዳደር …………… አርበኛ መኩሪያ ፈንቴ
ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጂ … አርበኛ አወቀ ብዙአየሁ
የኮር ልዩ ዘመቻ ……………………. አርበኛ አበበ ቢራራ
የኮር ም/ል ልዩ ዘመቻ..................አርበኛ ኪዳን ወዳጄ
ኦዲትና ኢንስፔክሽን ………….. አርበኛ አንደበት ወረታ
የኮር አማካሪ ………………….. አርበኛ አለሙ ገላው
የኮር ም/ል አማካሪ.............አርበኛ እንዳለማው ፈጠነ
ግዥ …………………………… አርበኛ አለበል ተካልኝ
ወታደራዊ አደረጃጀት ………….. አርበኛ ሻለቃ ወንድሙ፡
ም/ል ወታደራዊ አደረጃጀት ...........አርበኛ ሻምበል ደመቀ እንየው
በዚህ አጋጣሚ በተለያዩ የአማራ ቀጠናዎች የምንገኝ ፋኖዎች ለድል የምንበቃውና የወገናችንን ግፍ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በፍጥነት እንዲያከትም የምናደርገው በአንድነትና በመተባበር መታገል ስንችል ብቻ ነው፡፡ ዛሬ የታወጀው አንድነት በወሎ ቀጠና ይሁን እንጂ አገዛዙ የሀገር በጀት ይዞ ያለ እረፍት በገፍ እያሰለጠነ የሚልከውን የጠላት ኃይል የክተት ጦርነት መክቶ ድል ለማድረግ በሌሎችም የአማራ ቀጠናዎች በልዩነት የምትገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች ወደ አንድነት እንድትመጡ ያስፈልጋልና ወንድማዊ ጥሪያችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን፡፡
በመጨረሻም፣ በተፈጠረው አንድነት የተሰማንን ከፍተኛ ደስታ እየገለጽን በቀጣይ የሚጠብቀን ትግል ውጣ ውረድ ያለበትና ከፍተኛ መሥዋዕትነትን የሚጠይቅ በመሆኑ መላው የአማራ ልጆች ሁለንተናዊ ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
በአፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የደጋው መብረቅ ኮር
ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም.
"…እግዚአብሔር ፈጽሞ ያረጋጋቸው ዘንድ ስለ አዘኑና ስለ ተከዙ ሰዎች እንማልዳለን።
"…ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወገን ስለ ሞቱ_ሰዎች እግዚአብሔር የዕረፍት ቦታ ይሰጣቸው ዘንድ እንማልዳለን። በእንተ ቅድሳት።
• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?
• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
3.93 MB
Photo unavailableShow in Telegram
"…እንዲህ በየቦታው፣ በየተራራ ሸንተረሩ የሚያልቀው የደሀ ኢትዮጵያውያን ልጆች ናቸው። አገዛዙ እንደሆነ ምንም ደንታ የለውም። ቢያንስ እንኳ ለሟች ወታደሮች ቤተሰብ እርማቸውን እንዲያወጡ መርዶ እንኳን አይነግርም። ከትግራዩ ጦርነት ጀምሮ አሁን ከዐማራ ፋኖ ጋር እየተካሄደ እስካለው ጦርነት እንደ ቅጠል የሚረግፉት ወታደሮች መጨረሻቸው ምን ይሆን…?
"…ዐማራስ ምን ያድርግ? ወታደሮቹ ወንድሞቹ እንደሆኑ ያውቃል። ቢተዋቸው አይለቁት። ከቤቱ ከመንደሩ መጥተው ነው እየገደሉት ያሉት። ዳር ድንበር መጠበቅ፣ ማስከበር የነበረበት አገዛዝ ወታደሩን ሁሉ በገዛ ሀገሩ ሕዝብ ላይ አዘመተው። ይኸው እንደ ሱዳን ደርቡሽ፣ እንደ ሱማሌ አልሸባብ፣ እንደ ኤርትራው ሻአቢያ ጠላት ያልሆነ የሀገር ልጅ በአንድ ፀረ ሰላም፣ ፀረ ሀገር ግለሰብ ምክንያት እንደ ቅጠል በየቦታው ይረግፋል። ብርሃኑ ነጋ ተማሪ ይጥላል። ብርሃኑ ጁላ የወደቁትን ተማሪዎች ይቀበላል። በ3 ወር የለብለብ ሥልጠና ወታደር ነህ ተብሎ ይላካል። በመጨረሻም እንዲህ የአሞራ ቀለብ ይሆናል? ግን እስከመቼ…?
አንድ እግር በርበሬ መንቀል አቅቷችሁ
ለብልቦ፣ ለብልቦ አቃጥሎ ፈጃችሁ።
