uz
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

Kanalga Telegram’da o‘tish

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
65 757
Obunachilar
-2524 soatlar
-567 kunlar
-31830 kunlar
Postlar arxiv
ፍቅር በዝምታ ደስ የሚለው ህመም ሰውን የ መውደድ አዎ ያማል እኮ ለማይገባው ሰው ጨርቅ ጥሎ ማበድ ባንተ ደስታ መሳቅ የራስን ሀዘን ረስቶ ደሞ ማዘን መጨነቅ ሀዘንክን አይቶ ሁሉም ስላንተ ብቻ አንዳች ሳልል ለኔ ያንተን ህይወት ኖራለው ባክኖ ስለ የኔ እራሴን ገደልኩት የኔ ምለው አጣው የኔን ደስታ የኔን ስሜት ከቶ ምን ዋጠው ? እንዴት ነው የቻልኩት ሁሌ አንተን ማሰቡን በሁሉም ቦታ ላይ ምስልክን መሳሉን ለማን ይግባኝ ላቅርብ ላሰማ ስሞታ ላንተ ብቻ ልቤ ሁሌም እየመታ ማን ይገባው ይሆን ባወራ የሆዴን ያልተፈቀደልኝን በጥልቅ መውደዴን እኔማ መረጥኩኝ ችሎ መቆየቱን ደና መስሎ መሳቅ መሰንበቱን ልክ እንደ አምላኬ ልክ እንደ አንዱ ጌታ ልቤ በ ሰው ፍቅር እየተንገላታ ለካስ ፍቅር ማለት እግዚአብሔር ማለት ነው እራሱ ክርስቶስ የተሰቀለው ነው ታድያ እኔ ማነኝ ወደድኩኝ የምለው በፍቅር ምክንያት እንዲ የማነባው ፍቅር ማለት ህመም መሆኑን ባወኩኝ አንተን በ ማጣቴ እንዲህ ባላዘንኩኝ መጥቼ እንዳልነግርክ ቤትኛው ድፍረቴ በህይወቴ ሞልቶ የ ገዛ ጭንቀቴ እንኳን ግድ ሳይሰጥክ ለኔ ምንም ሳትወደኝ አድርጎት ፈጣሪ ድንገት እንኳን አንተ እኔን ብትወደኝ የለኝም አቅሙ ልነግርክ የልቤን ትርታ ስወድክ ኖራለው ሁሌም በ ዝምታ ነሀሴ 12 By mhret @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
40🔥 4👍 2
ተስፋ? . . እንደ እምዬ እቅፍ የምንናፍቀዉ፤ ዘወትር ሳንታክት የምንጠብቀዉ፤ ብርሃን እንዲሆን በምናብ የሳልነዉ በልባችን ያለ ተስፋ ግን ምንድነው? ...................................... በዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
37
" አይ ወጣትነቴ"              ( ግዮናይ ነኝ)!፧ በባህል ታጥሬ  በ'ምነቴ እየኮራሁ: ወጣትነቴ አልቆ  እንዳላረጅ ፈራሁ። በመጠጥ ሰክሬ  ፖሊስ ሳላስቸግር: ከመንገዱ ቆሜ  ሴቶችን ሳልፎግር። ለነገ 'ሚበጀኝ  እውቀቱን ሳልቀስም: ወይ እንደኩዮቼ  ሸጋ ከንፈር ሳልስም። አወይ ወጣትነት... በቅኔ ሳልዘምር  ሳልዘፍን ባ'ራራይ: ወይ አንዷን አቅፌ  አልጋ ሳልከራይ። ብላክ ሌብል ውስኪን ሳላንቆረቁረው: የ'ግር አጣጣሌን  ምንም ሳልቀይረው። ከሜዳ ሳልቦርቅ  ፈረስ እየገራሁ፣ ወጣትነቴ አልቆ  እንዳላረጅ ፈራሁ። @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
53😢 13👎 5👍 3🤩 1
ኪሴ፣ እኔ ፣ እግዜር (ሳሙኤል አለሙ) ዝር---ዝር አምስት ብር ዝር---ዝር አስር ብር ከኪሴ ቁና ፥ ሞልቶ ሲሰፈር አላውቀውምና ፥ የነገን ነገር ከንፈሬን እመጣለው። ስምህን አዋጣለው። (እግዜር ይስጥልኝ!) እያለኝ፥ አለ-ማፈሬ እያለኝ፥ የታጠፈው ብሬ ባለ-መቀደዱ... እያለኝ፥ የኪሴ ጨርቁ ባለ-መተልተሉ... ግን እንዴት ፥ ያጣ ስንመስል፤ እኔና ኪሴ ፥ አንዲት አንቆስል። ስለማርያም ሲሉኝ... ኖሮኝ እጄን እንዳልሰበስበው፤ ስለወላዲቷ ሲሉኝ... እንዳጣ ሰው ኪሴን እንዳልደባብሰው፤ ወይ በፀሐዩ ወይ በዝናቡ ወይ በንፋሱ ብቻ ምልክት ስጠኝ ፥ የሚያስታውሱ @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
👍 17 10🤩 1
እኔ ጭምቱ ሰው ፍቅር ተለክፌ ከእድገት ሀገሬ ለሷ ስል ከንፌ ሮቤ አለች ሲሉኝ ሮቤ በርሬ ሳስስ ስፈልጋት ስጠይቅ አድሬ ሸገር ሄደች ሲሉኝ ባቀና አዲሳባ እንኳንስ አካሏ ዳናዋም አልገባ ባክኜ ባክኜ ከደከምኩ በኋላ ምፈልጋት ፍቅሬ ታየች ከ አሰላ ገላንን ዱከምን ቢሾፍቱን አልፌ ከሞጆና ናዝሬት ወንጂ ተገኝቼ በሶደሬ በኩል ልሂድ ወደ ዴራ ኢትያን አልፌ እንድገኝ አሰላ። መነ ጂረኛ ኮ አቲ ቤክተ ላታ ዮካን ፉዴን ጎንደር ኮ ሊጣ (ዋ ነን ጀዲ አኒስ አብዲን ሙራ አፉራ ኬ ዴቤን በርባቸ ኬን ጆራ) ዮኒ     ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
20👍 8🔥 8🤩 3
የአብስራ ሳሙኤል አባ "ደፋር'ሁን" ብለህ እንዳ'ስተማርከኝ፣ እደፍር ብዬ ጦሬን አነሳሁ፤ ግን ሰው ነኝና ለነፍሴ ሳሳሁ። እናም አባ፣ ያንተንም ምክር ከንቱ ሳላስቀር፣ ጀግና ነኝ ብዬ እንዲው ባክኜ ከሜዳ እንዳልቀር።      * * * ከምክርህ ጦሬን፣ ከፍርሀቴ ጋሻን አበጀው፤ እንዲያ ሲሆን ነው ውረድ! እንውረድ! ሲሉ የሚበጀው። ዝናቡ እስኪ'ጠል ሸሸት ማለት፣ ጠለል ማለት መፍራት አይከፋም፣ ውድቀት ነው ብለን ከሳቅንበት ስር፣ መማሪያ የሚሆን ጥበብ አይጠፋም! by Yabisra Samuel @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
39👍 3🔥 2
እንዴት ነሽ  ስላት ሳቅ ታበዛለች ትጫወታለች ፤ < አለሁ ! >  ትላለች - እንደሞላላት ቁስሏን የማላውቅ እዬመሰላት ፤ የዐይኗ መደፍረስ የገጿ ሽክረት የአንጀቷ ማረር የልቧ ቁስለት ጥልቅ ስቃይዋን እዬነገረኝ ፤ እርሷ ግን ሁሌም አንድ የምትለኝ ፤ - - - - - - - - -  አለሁ ደህና ነኝ ! ልዩ ፍጥረት ናት አይደረሱባትም ፤ ስሟ ሕይወት ነው ካልተሸከሟት አይረዷትም ፤ በሕመሟ መሳቅ በቁስሏ ማጌጥ ታውቅበታለች ፤ ልክ እንደ መሬት ውኃ'ን ከእሳት ጋር ታቻችላለች ፤ ከራስ ቅራኔ ከራስ ጋር ሙግት ቢኖርባትም ፤ ከመሳቅ በቀር በሰው ፊት ማልቀስ አይኾንላትም  ፤ ደህና ነኝ ከሚል ከአንድ ቃል በቀር ——   ሌላ አይወጣትም ፤ እወድዳታለሁ ፤ ደህና ነኝ ስትል ደህና እንዳልሆነች አውቅባታለሁ። By Tewodros kassa @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
72😢 11🔥 7👍 2🤩 1
#ከተጣሉ_ገፆች_መሃል የፊቱን እያየ የኋላውን ትቶ ማንነቱ ጠፍቶት እልህ ጋ ተጋብቶ           ጎጆውን ቀልሶ ማን እንደነበረ ረስቶት ጨርሶ የገዛ እልሁ ደፋው ከፊት ደርሶ። ብላችሁ ንገሩ ላገር ለመንደሩ በምን ጠፋ ቢሉ! ንሸጣ: ጋሽ ደበበ ሰይፉ (በምን ሞተ ቢሉ) ዮኒ      ኣታን   @yonatoz @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
👍 14 8
ዝብርቅርቅ ባለዉ በህይወት አዙሪት፤ ፍቺዉም ሳይገባኝ እንደዉ ስንከራተት፤ ሠርክ በጥበቃ በይሆናል ተስፋ፤ ይሞላልኝ መስሎኝ ስዳክር ስለፋ፤ በሰለለ ቅኝት ኑሮዬን ስገፋ፤ የቁሙ ቅዠቴ እጅግ አደከመኝ፤ በህልም መደሰት መኖር አታከተኝ፤ ትርጉም ያጣሁበት ብኩኑ ህይወቴ፤ መኖሬ ከጎዳኝ ይጥቀመኝ መሞቴ፤ ለመሞትም ለካ መመኘት አይበቃም፤ ቀኑ ካልደረሰ ትንፋሽ አይገታም። ነጠላ አዘቅዝቄ ዘወትር እዬዬ፤ ራሴን ፈርቼ ስሸሽ ከጥላዬ፤ እንደዉ ምን ተሻለኝ? ምንስ ነው የሚበጀኝ? ................................................. በዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
23👍 4🔥 2
ጊዜው ተቀይሮ ፍቅር ጥምቡን ጥሎ ብናኝ ትቢያ አክሎ ሁሉ እንኳን ቢሆን ፥ የማይታመን አንተ ግን እመን አንተ ግን ታመን አሁንም በግ ሁን ፥ በፍየል ዘመን ። ግዴታ አይደለም ወከባን መልመድ ወቅትን መዛመድ ከጊዜው እኩል ፥ አብሮ መራመድ ስለዚህ ውረድ ! እምቢ በል ገግም ቀስ ብለህ አዝግም ። አጉል መሰልጠን አያስፈልግም ። ክፋት የለውም በወግ በወጉ ለገዢ ሀሳብ ቦታ ቢለቁ ያረጀን ነገር በአዲስ ቢተኩ ግን ደሞ አሉ - የማይነኩ ። በጊዜ ፍጥነት የማይለኩ ። እስካሁን ከመጣው ገናም ከሚያመጣው ከቁስ ከማሽኑ ዘመን የማይሽርህ ፥ አንተ ነህ ፋሽኑ ። By Hab Hd @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
37🔥 6😱 3🎉 1
• [የውሃ ውርደቱ — የዥረት ቅሌቱ...... «መመለሱ ላይቀር ጎብጦ መደፋቱ ፤ "ፋውንቴን ነህ" ተብሎ ወደ ላይ መውጣቱ ።» ] • እኔ ገራም የምንጭ ውሃ ..... ኩልል ያልኩኝ ድምጽ አልባ “ማይ” ፤ ተራራ ላይ የቆምሽውን ክንፋም ውበት በሩቅ የማይ ። ክብርስ ለእኔ መውረድ ነው መፍሰስ ቁልቁል በመሬት ፣ አንቺ ደግሞ ከከፍታው በክንፍሽ አቅም መቆዬት ። እንዳይሆን አርጎታል መቼም ተፈጥሮ ነው እንቆቅልሽ ፤ እንዳንቺ ወደ ደመና ከፍ ማለት ምን አውቅልሽ?! ዥረት ነኝ እንዳኗኗሬ "ውረጅ እንውረድ" ነው ምልሽ ። • መቼም ኗሪ ዝም አያውቅም .... ይበልሽ ያሻውን ይፍረድ ፣ ዝቅ በይ “ውረጅ እንውረድ” ። • እንደዚህ ነግሬሽ እንጂ መሪር ሀቁን አሳውቄ ፤ ውሃ ብሆን (እንዳመሌ) አልወስድሽም አሳስቄ ። • ውብዬ ... (ወደድኩም ብዬ.....) ወዳንቺ ሽቅብ ለመውጣት ብሞክር እንኳን አልደርስም ፤ ተፈጥሮ ሕጉን አልጥስም ። አንቺ ግን የመጣሽ እንደሁ..... «ቤቷ ነበር ያ ደመና .... ቤቷ ነበር ያ ተራራ ፣ እዩዋት ክንፍ እንደሌላት በዥረት ጀርባ ተሳፍራ ፣ ወረደች! አይ ተዋረደች አጃዒብ ፍቅር! » ይባላል ማ`ናችን ብንቀል ይቀላል? • By @Bekalushumye @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
24👍 3
የአብስራ ሳሙኤል እንዲያው እንደ'ድንገት፣ እንዲሁ እንደ'ሁኑ፣ ደርሰን ስንገናኝ አይንሽን ብፈራ፣ "እረስቶኝ ነው" ብለሽ እንዳት'ጨነቂ፣ "ይጠላኛል" ብለሽ እንዳትጠብቂ። * * * አይን የማያይው፣ ጆሮ የማይሰማው፤ የልቤን ትርታ አፍኜ በልቤ፣ ወንድነት ቢያንሰኝ ነው፦ አይኔን መሰብሰቤ፣ ፊቴን መሸበቤ... * * * እንዲያው እንደ'ድንገት፣ እንዲያው እንደ'ነገው፣ ብዙ አመታት አልፎ፣ ቀን እና ቀን ተጠላልፎ፣ አዲስ ታሪክ ጽፎ፣ አዲስ ህይወት ነድፎ፣ መልክሽ እንደ አደይ፣ እንደ ጤዛ እረግፎ፣ የልጅነት ጊዜ ጭዋታና ፍቅሩን ስናፍቂ... "ይጠላኛል" ብለሽ፣ "ይረሳኛል" ብለሽ እንዳትጠብቂ! * * * የዕድሜ መሰላሉን ብወጣ፣ ብሄድም፣ ህይወትን ብጓዘው፣ አለም ካጣበቡ እልፍ ሴቶች መሀል፦ ያንቺ ሳቅ ብቻ ነው፣ ቀልቤን የሚይዘው። @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
27🔥 4
ጨዋታዉ ፈረሰ . . ልጅነቴ ልጅነትህን፤        ለጋነትህ ጮርቃነቴን፤ በትዝታ እየቃኘሁ፤         ሳቃችንን እየሰማሁ፤ በትዉስታ ምልሰት፤        በጥሞና ስመለከት። በድንጋይ ከታትፈን፤            ማባያ ጨምረን፤ መረቁን ከልሰን፤           የሰራነዉ ጎመን። ለሚመጣዉ ዘመን፤           የእቃቃ ሰርጋችን፤ ሚዜ ስናዘጋጅ ፤          መኖርን ስንዋጅ፤ ወረቀት ቀዳደን፤             ቦጭቀን፤  ቦጫጭቀን፤            እየጎዘጎዝን፤ ሰፈር ስናበላሽ፤        መንደር ስናቆሽሽ፤ ቡና አፍልተን፤         ቁርሱን በልተን፤ ደግሞ ስንጣላ፤         ይጠፋናል መላ፤ ኩርኩም ስንቃመስ፤           ጮኸን ስንዋቀስ፤ መተቃቀፍ በማግስቱ፤          መንከባለል በክረምቱ፤ ስንቱ አለፈ በጊዜያቱ።               የእቃቃ ቤታችን፤ ያለምነዉ ኑሯችን፤           ጨዋታዉ ፈረሰ፤ ዳቦዉ ተቆረሰ። በዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
48🔥 4👍 3
የአብስራ ሳሙኤል ቀኑስ ከዳኝ እንዳላቅፍሽ  እንግዲህ ህልሜን ልለመነው  ወይ ወድጄሽ ላይሞላልኝ  ያገናኘን ለምንድነው  —  ኪዳን አለኝ ከለሊትሽ  ምስኪን ልቤን ሊያስተሳስር  በሰመመን ያደርሰኛል  ከመዳፍሽ ከእግሮችሽ ስር  —  ወብ ፈገግታሽ ተስረቅርቆ  እንደ ንፋስ ሊዳብሰኝ  ከጽናትሽ ተስፋን ሰርቆ  ለንጋት ጀንበር ሊያውሰኝ  —  ከልካ ይ የለው አጋጅ የለው  ወይ አይመሩት ወይ አይገሩት  ተኝቶም ቢሆን ይሄዳል....  ልብ እንደው ወዳ 'አፈቀሩት  —  አይዞሽ እዛ ትግል የለም  አረፍ በይ ከታዛው ስር  ህቡእ ፍቅሬን ታገኛለሽ  ህልሙን ከአንቺ ሲያስተሳስር  የእንቅልፉን በር ሲሰረስር። —  አይዞሽ እዛ መራዝ የለም  የተራበ ሁሉ ይጠግባል  በህይወት የጠወለገው  አንቺን አይቶ ልቤ ያብባል  ተስፋ ምኞት ይቀለባል። —  **ኪዳን አለኝ ከለሊትሽ  ምስኪን ልቤን ሊያስተሳስር  በሰመመን ያደርሰኛል  ከመዳፍሽ ከእግሮችሽ ስር  —  ቀኑስ ከዳኝ እንዳላቅፍሽ እንግዲ'፣ ህልሜን ልለመነው ወይ ወድጄሽ ላይሞላልኝ ያገናኘን ለምንድነው....... .    .    .    .    .    .    .    .    .    .    .     .   . @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
26🔥 4👍 1
በምድር ፍትህ የለም       ......................... ለእውነት የሚቆም ራሱን የካደ ከራሱ አስበልጦ አምሳሉን የወደደ የአዳም ዘር ሆኖ በምድር ስለሌለ ፍትህ በቃል ብቻ ተመዝግቦ ዋለ::✍               ፠፠፠፠ ባለንባት አለም የኔም ያንተም ጠባይ ለምድር ይቅርና ያስፈራል ለሰማይ:: እናም!... .        ፍትህ ለእገሊት! ፍትህ ለእገሌ!      ፍትህ.......ፍትህ......! ፍትህ........! እያሉ መጮህ አንዳችም አይሰራም እንኳንስ ለሰው ልጅ ምንኖርባት ምድር ለንጉስ አትራራም፡፡ By @Abuugida @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
41😢 13🔥 4👍 3
የአብስራ ሳሙኤል እስቲ ትንሽ እንፋለስ እስቲ እግዜ'ርን እንሞግተው። ህሊና ያለው ፍጡር መቼም መልስ ቢያጣም ጥያቄ አይተው። ስለምን ሰው እንደ ቅጠል በየመስኩ እረገፈ? ባለቤት አልባ ይመስል በ"እኔ ነኝ" ባይ ተቀጠፈ? — ይቆረቁራል ጎዳናው ደምና አጥንት መሰለኝ... እንዴት አድርጌ ዝም ልበል? ውስጤ "ጩኽ! ጩኽ!" እያለኝ! — ስለምን ጡት ያልጠባ ህጻን ከእናቱ እቅፍ ተነጠቀ? ለነፍሱ አጽናኝ ሳይኖረው "በረብ! በቁር!" ማቀቀ... ወደቀ...ወደቀ...ወደቀ... — ስለምን ምስኪን እናቱን በኑሮ አካልበህ ደፋሀት? የልጇን ጠረን ሳጠግበው ከመቀመቅ ገፋሀት? — ህመም ሲቃ ጩኸት ነው ንፋስ የሚንሾካሹከው... እንደምን ይመጣል ብዬ ምእመንህን ልስበከው? — "ያልፈል" ብሎ ቢጽናና ቀን �ይዞት እያለፈ፤ ስለምን አማኝ ከእምነቱ መፈተንን አተረፈ? — ዝምታው ተሰማኝ አሁን ነገዬን ማሰብ ከበደኝ። በየመስኩ በጎዳናው የቁስል ጠረን እያወደኝ... — ከታሪክ አመሳክረናል ወንጌል ላይ ነው ተአምርህ? በዘመን ገጽ ስንቱን እንዳለፈ እየነበርክ ምኑን ልንገርህ? — ስለምን ቸልታህ በዛ? የስምህ ትርጉም ቀለለ? በረሀብ ይሞታል ህዝብህ  ስለ እግዘብሔር እያለ!  —  ይቆረቁራል ጎዳናው  ደምና አጥንት መሰለኝ...  እንዴት አድርጌ ዝም ልበል?  ነፍሴ "ጩኽ! ጩኽ!" እያለኝ . . . . . . . . . . . . . @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
29🔥 5👍 2😢 1
የሚጠቅመኝን ፥ አልወደድኩትም አልጠቀመኝም ፥ የወደድኩትም ። ከማን ጋር ልሁን ? ከምወደው ? ወይስ ... ከሚጠቅመኝ ጋር ? ተንገዳገድኩኝ ፥ በጭንቀት ስካር ! የቱን ላስቀድም ? የቱ ይበልጣል ? የቱ ያከስራል ? የቱ ያወጣል ? እንዴት የሰው ልጅ ምርጫ ተሰጥቶት ፥ ነጻነት ያጣል ? ፈጣሪ ራሱ ከዚህም ከዚያም እያማረጠኝ መሐል መንገድ ላይ ከሚያፋጥጠኝ ምናል ከሁሉም ፥ ሁሉን ቢሰጠኝ ?! By Hab HD @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
61👍 12😁 4🔥 3🤩 2😱 1
ድክም ብል በሂወት መንገድ እግሬ ቢዝል ብሰናከል ቆፈን ብለብስ ለገላዬ  ቁራሽ ዳቦ ብከለከል ቀን ቢገፋኝ ካለሁበት ከከፍታ ብወረወር "አትመጥንም" ብባል በአፍ ከአመት አመት በቀን በወር አይኔ ደምን ሰርክ ቢያነባ እቅድ ግቤ ቢፋለስም ዳና ትግሌን አደብዝዘው ያለ ስሜ ቢሰጡኝ ስም አትጨናነቂ ዝምብለሽ ሳቂ! አታውቂምና ነው! ቀን የገፋውን ሰው ቀን እንደሚያነሳው ፈጣሪ ላልከዳው እሱ እንደማይረሳው አታውቂምና ነው! ዝቅ ያለ ሰው ሁሉ ከፍታ እንደሚያገኝ ማርያም ማርያም ላለ ፈጣሪ እንደሚገኝ አታውቂምና ነው! ሞን ያስለቅስሻል ለምን ትጨነቂ ሁሉ በርሱ ይሆናል ዝም ብለሽ ሳቂ ቀን ሳይገፋ አያልፍም ቀን አልፈጠረብሽም ምንድነው ሰቀቀን ለኔ ብለሽ አትድከሚ አይብረድሽ ፍርሃት ቁር ጊዜ አይፈጅም ለመልስማ ካምላክ ሄጄ ብቆረቁር አትጨናነቂ ዝም ብለሽ ሳቂ! ተስፋ መቁረጥ አይነበብ ካካል ገፅሽ ከመልክሽ ላይ ሀይል ብርታቴ ይጨምራል የፊትሽን ፈገግታ ሳይ። አንዲት ቅንጣት እንባ እንዳላይ ተደርድሮ ከጉንጭሽ ስር ቀን እንደሆን አመሏ ነው ልታነሳ ምትሰረስር። አትጨናነቂ ዝም ብለሽ ሳቂ! ዮኒ      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
31👍 4🔥 1🎉 1
" አሜን"           ( ግዮናይ ነኝ)!፧ አንቺ ጋር ለመኖር... ሺ ቁልቁል ወርጄ  ብዙ ዳገት ወጣሁ፣ ዳኛ ሳይፈርድብኝ... እንደ ወንጀለኛ    በኑሮ ተቀጣሁ፣ ያ'ርባ ቀን ዕድሌን  እጣ ፈንቴን አጣሁ።   *                  *                  * ህይወትን ተራብኩኝ... እንጃ ስለ ፍቅር   ጥላቻን ተጠማሁ፣ ይኸው ደሞ ዛሬ... እንለያይ የሚል   ካ'ንደበትሽ ሰማሁ። አሜን ያደርግልኝ... እዛ ማዶ ልጓዝ   ፍቅርሽን አልፌ፣ (አልጋዬ የት ነበር?)... እስኪ ጋደም ልበል  ናፍቆኛል እንቅልፌ።    *                  *                  * ሰውነቴ ሁሉ... እንደ ብሉይ ኃጢያት  ለምጻም ሰው መሰለ፣ ፈጣሪ ያውቀኛል... ህይወቴ ላ'ንቺነት   ብዙ እንደ ቆሰለ። ልሽሽ ካለሽበት... ምድር እስከምታልቅ  በሌትና ቀትር፣ ባህር እንኳን ባገኝ... ሙሴ ይሰጠኛል   የመክፈያ በትር። @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
32👍 2🔥 2🤩 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጥራታቸውን የጠበቁ የአውሮፓ ቦንዳ አልባሳት እና ጫማዎች መሸጫ 👌👏 አድራሻ 24 ሲድራ ሆቴል ጀርባ ወደ 40/60 መግቢያ 20 ሜትር 🤳 0913803516
Hammasini ko'rsatish...
7🔥 3👍 1