uz
Feedback
Tikvah-University

Tikvah-University

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
352 742
Obunachilar
-9324 soatlar
+37 kunlar
+1 19630 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር በዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤታማነት ላይ ጥናት እያካሔደ ነው፡፡ ጥናቱ በሦስት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ይፋ እንደሚደረግ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡ መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል። እስከ 250 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች በዓመት ሁለት ጊዜ የሚሰጠውን ፈተና እየወሰዱ መሆኑን የገለፁት መሪ ስራ አስፈጻሚው፤ ፈተናው ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት መቅሰም የሚጠበቅባቸውን ክህሎት እና እውቀት ለመፈተሽ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል። የመውጫ ፈተናውን ውጤታማነት በመገምገምና በቀጣይ መሰራት ያለበትን ሥራ በመለየት የአፈጻጸም ወጥነትን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ጥናት በቀጣይ ሦስት ወራት ተጠናቆ ይፋ ይደረጋል ብለዋል። #ኢዜአ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👎 130 82👍 29😱 8😢 6🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት የሚመሩበት አዲስ ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቷል፡፡ ረቂቅ ደንቡ በተለይ በውጭ ሀገር ማኅበረሰቦች ለሚቋቋሙ ትምህርት ቤቶች አስገዳጅ መስፈርቶችን አስቀምጧል። በውጭ ሀገር ማኅበረሰብ የተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ከጠቅላላ በጀታቸው ውስጥ 30% የሚሆነው ከሀገራቸው መንግሥት ድጋፍ ማግኘታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ቀሪውን 70% ደግሞ ራሳቸው መሸፈን የሚችሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ ረቂቁ እንደሚያስገድድ የካፒታል ጋዜጣ ዘገባ ያሳያል፡፡ ይህ የፋይናንስ ማረጋገጫ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና አግባብ ባለው የሰነዶች ማረጋገጫ ባለሥልጣን ተረጋግጦ መቅረብ እንዳለበት ረቂቁ ያመለክታል። ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት አስተያየት ክፍት በተደረገው ረቂቅ ደንብ፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት የአገሪቱን የትምህርት ህግ፣ የመምህራን ብቃት፣ የተማሪዎች መብት እና የትምህርት ደረጃን ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ህጎችን ማክበር እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል። ተቋማቱ የራሳቸው የሆነ የገንዘብ ምንጭ (ከተማሪዎች ክፍያ፣ ከስጦታ ወይም ከኢንቨስትመንት ትርፍ) እና ነጻ አስተዳደር ያለው ድርጅታዊ አወቃቀር ሊኖራቸው ይገባል። የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ ከሦስት ወራት በፊት ተጠቃሚዎችን ማወያየት እንደሚኖርባቸው ያስገድዳል። መንግሥታዊ ያልሆኑ የአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት፣ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንደገና መመዝገብ እንዳለባቸው ተመላክቷል። ትምህርት ሚኒስትሩ አዲሱ ደንብ የመንግሥታዊ ያልሆኑ ትምህርት ተቋማትን ምዝገባ፣ ዕውቅና እና ቁጥጥር በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 መሠረት የሚያከናውን መሆኑን ገልጿል። #Capital @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
61👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
ሰቨን ስታር ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ የበርካታ ዓመታት የማስተማር ልምድ ባላቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሐኪሞች የተመሰረተ ኮሌጅ! 🔔 ለ2018 ዓ.ም ምዝገባ ጀምረናል! በዲግሪ የጤና መርሐግብሮች ➫ ነርሲንግ ፐብሊክ ሄልዝ ፋርማሲ ሚድዋይፈሪ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ በዲግሪ የቢዝነስ መርሐግብሮች (በቀን እና በማታ) አካውንቲንግና ፋይናንስ ማርኬቲንግ ማኔጅመንት ቢዝነስ ማኔጅመንት ሰው ሀብት አስተዳደር በጤና በደረጃ-4 መርሐግብሮች ➫ በፋርማሲበላብራቶሪበነርሲንግበሚድዋይፈሪበሜዲካል ራዲዮግራፊ በቢዝነስ በደረጃ-4 መርሐግብሮች ➫ በአካውንቲንግና ፋይናንስበማርኬቲንግና ሴልስ ማኔጅመንት በሪሚዲያል መርሐግብር ፈጥነው ይመዝገቡ! አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን፣ ከባቡር ትኬት መቁረጫው ፊት ለፊት ☎️ 0982373737 / 0965686819
Hammasini ko'rsatish...
13👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
IFRS, IPSAS, IFRS Conversion, Quick Book, Peachtree and Asset Valuation ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 IFRS + Peachtree + Asset Valuation + IFRS Conversion + IPSAS + Quick Book በአንድ ላይ 👉 ሙሉ በሙሉ በተግባር የተደገፈና ፒስትሪ (Peachtree Software) ላይ የሚሰጥ ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Hammasini ko'rsatish...
34😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለመማር የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ በየትምህርት ቤቶቹ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ባላችሁበት ሆናችሁ ከዚህ በፊት ባመለከታችሁበት ሊንክ በመግባት እስከ ህዳር 03/2018 ዓ.ም በኦንላይን ምዝገባ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል። ምዝገባው እስከ አርብ ህዳር 05/2018 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑ ተገልጿል። የመመዝገቢያ ሊንክ 👉 sbs.moe.gov.et @tikvhauniversity
Hammasini ko'rsatish...
86👎 24👍 10😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች #በመምህርነት ለመወዳደር የተመዘገባችሁና ለቃል ፈተና የተመረጣችሁ ተወዳዳሪዎች፤ ቃለመጠይቁ የሚደረገው እሑድ ህዳር 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡ በተጠቀሰው ቀን ጠዋት 2፡30 ሰዓት በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንድትገኙ ተብሏል፡፡ ለቃለመጠይቁ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ሙሉ የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ልዩ የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና እና የአንድ ዓመት ልዩ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርነት ስልጠና ሰርተፍኬት፣ ➫ የሙያ ፍቃድ እና የእድሳት ሰርትፍኬት፣ ➫ በመምህርነት ተገቢነት ያለው የሥራ ልምድ ማስረጃ የሚገልጽ ደብዳቤ፡፡ (ለቃለመጠይቅ የተመረጣችሁ መምህራን ስም ዝርዝር በትምህርት ሚኒስቴር የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ይመልከቱ፡፡) @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
114👎 20👏 5😢 3🙏 3👍 2😱 2
#MoE በረቂቅ መመሪያዎች እና ደንብ ላይ አስተያየት ይስጡ! በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ባዘጋጃቸው ተከታዮቹ ሦስት ሰነዶች ላይ አስተያየት እንትሰጡ ጠይቋል፡፡ 1. የአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት አመራር፣ አደረጃጀት የኅብረተሰብ ተሳትፎና የፋይናንስ ረቂቅ መመሪያ: https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScdrHGMOV3gb_aOhiFZsxGU1JAB178bvAiDRufSIPFTIfrj_g/viewform 2. መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት ረቂቅ ደንብ: https://forms.gle/LpwGdAu7mBYRUNNU6 3. የአጠቃላይ ትምህርት የውስጥ ኢንስፔክሽን እና ሱፐርቪዥን አተገባበር ረቂቅ መመሪያ: https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdoOaNWgbbPX8M2dEpqcBFOlLBefpFtzeKYyu1HOxEiycCjg/viewform?usp=sharing&ouid=111388231034755887607 @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
19
Photo unavailableShow in Telegram
መስራት ማህበር ለኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች ተግባራዊ ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ ነው፡፡ ✅ በንግድ፣ በፋይናንስ፣ በማርኬቲንግ፣ በኢንቨስትመንት፣ በገበያ ማፈላለግ እና በህግ ጉዳዮች ዙርያ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተዘጋጁ ፅሁፎችን ማጋራት ✅ የንግድ ሥራችሁን ለማስተዳደር የምትጠቀሙበት መመሪያዎችና ሃሳቦችን ማጋራት ✅ በናንተ የሥራ ፈጠራ መንገድ ቀድመው ካለፉና ብዙ ልምድ ማካፈል ከሚችሉ ጋር ሃሳብ የምትለዋወጡበት መድረክ ✅ በሥራችሁ ወደፊት ለመራመድ የሚያግዟችሁን የተለያዩ ሃሳቦች ማጋራት እንዲሁም ጠቃሚ ግንኙነቶችን የምትፈጥሩባቸው ኹነቶችን መጠቆም የንግድ ሥራችሁን አሳድጉ 👇 https://mahber.mesirat.org/wp-login.php?loggedout=true&wp_lang=en_US
Hammasini ko'rsatish...
28
Photo unavailableShow in Telegram
#ERMP_2025 የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (Ethiopian Residency Matching Program/ERMP) ምዝገባ ህዳር 22/2018 ዓ.ም እንደሚጀመር ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡ ፕሮግራሙ አመልካቾች በተለያዩ የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ተወዳድረው ስልጠና የሚያገኙበት ነው፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👎 53 51👍 13
Photo unavailableShow in Telegram
በ2018 ዓ.ም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በኅብረተሰብ ጤና ትምህርት የማስተርስ ፕሮግራም (MPH) በመደበኛ እና በእረፍት ቀናት ለመማር የመግቢያ ፈተና የወሰዳችሁ አመልካቾች ውጤት ይፋ ተደርጓል፡፡ ለቃል ፈተና የተመረጡ አመልካቾች ቃለመጠይቅ ህዳር 05 እና 06/2018 ዓ.ም በኮሌጁ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡ ለቃለመጠይቅ የተመረጣችሁ አመልካቾች ዝርዝር ለመመልከት የኮሌጁን ድረ-ገፅ (https://sphmmc.edu.et/) ይጎብኙ፡፡ ወደ ፈተና ማዕከል በምትሔዱበት ወቅት ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡ ቃለመጠይቁ ከመጀመሩ 15 ደቂቃ በፊት መድረስ እንደሚኖርባችሁ ተገልጿል፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
20👎 5🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ #UnityUniversity ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፍላጎትና ብቃት ያላቸው መምህራን እና አሰልጣኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ➤ የሥራ መደብ፦ መምህራን እና አሰልጣኞች ➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 24 ➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ➤ የሥራ ልምድ፦ ከ2-5 ዓመት ➤ የሥራ ቦታ፦ አዲስ አበባ፣ አዳማ እና ደሴ የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ አርብ ህዳር 05/2018 ዓ.ም የምዝገባ ቦታ፦ ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች CV እና የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒውን በመያዝ አዲስ አበባ ገርጂ የዩኒቨርሲቲው የሰው ሃብት አስተዳደር ቢሮ ወይም ቡራዩ የዩኒቲ አካዳሚ በአካል በመቅረብ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
47👎 7
Photo unavailableShow in Telegram
#ያኔት_ኮሌጅ በ6 ኪሎ ካምፖስ እና በሰፈረ ሰላም ካምፓስ የ2018 ዓ.ም ምዝገባ ጀምረናል! BSc Fields of Study: → BSc in Medical Laboratory Science → Bachelor of Pharmacy → BSc in Nursing TVET Programs: → Nursing → Medical Laboratory → Pharmacy → Accounting and Finance የCPD ማዕከል አገልግሎት ☎️ 0929969696/ 0996828282 አድራሻ፦ መሳለሚያ ሰፈረ ሰላም ንጉሴ ቱሩፊ ህንፃ 6 ኪሎ ካምፓስ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አጠገብ Telegram: @Yanet6kiloc
Hammasini ko'rsatish...
27👎 4
Photo unavailableShow in Telegram
የኢንቴሪየር ዲዛይን (Interior Design) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 AutoCAD, Revit, እና 3D Max ሶፍትዌሮችን በአንድ ላይ 👉 ከንድፈ ሀሳብ እና ሶፍትዌር ስልጠና በተጨማሪ በተግባር በወርክሾፕ የሚሰጥ ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Hammasini ko'rsatish...
38
Photo unavailableShow in Telegram
#JinkaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 10 እና 11/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ለምዝገባ ስትሔዱ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው እንዲሁም አንሶላ እና ትራስ ጨርቅ መያዝ ይኖርባችኋል። ትምህርት ህዳር 15/2018 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
114👍 104👎 13🙏 13😱 8👏 2🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዩኒቨርሲቲዎች በለብለብ እያስተማሩ ተማሪዎችን ማስመረቃቸውን እንዲያቆሙ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሳሰቡ፡፡ የዩኒቨርሲቲዎቹ ስኬት መለካት ያለበት ባስመረቁት ተማሪ ብዛት ሳይሆን፣ በተማሪዎቻቸው ብቃት ሊሆን እንደሚገባ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡ 34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ ነው፡፡ ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለመፍጠር ጥራት ያለው ትምህርት መስጠት የግድ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ በኋላ ለተማሪዎቻቸው ዲግሪ ሲሰጡ ያሰለጠኗቸው ተመራቂዎች ከሌላው ዓለም ጋር መወዳደር እንደሚችሉ ማረጋገጥ ሲችሉ ብቻ ሥራቸውን ተወጥተዋል ማለት እንደሚቻል ሚኒስሩ ገልፀዋል፡፡ በቅርቡ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ በተደረገ ምልከታ ትምህርት ማስተማር ያልጀመሩ ዩኒቨርሲቲዎች መኖራቸውን  አረጋግጠናል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ዩኒቨርሲቲዎች ይህን “እንዝህላልነት“ ሊቆጣጠሩ ይገባል፣ “መምህራን ገብተዋል ወይ፣ ማስተማር ጀምረዋል ወይ? ይህን መቆጣጠርና ማስተካከል ይኖርብናል“ ብለዋል፡፡ #ShegerFM @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
345👎 123👏 44🙏 16👍 14😱 9🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት ተመርቋል፡፡ መዝገበ ቃላቱ በመጀመሪያ ዕትሙ ከ30 በላይ ከሚሆኑ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች የተመረጡ 11,600 ሙያዊ ስያሜዎች በአቻ የአማርኛ ስያሜዎች የተፈቱበትና የተበየኑበት ነው ተብሏል። በመዝገበ ቃላቱ ዝግጅት ከ90 በላይ ከከፍተኛ ትምህርት እና ከምርምር ተቋማት የተመረጡ ባለሙያዎች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ትብብር የታተመው የሳይንስና ቴክኖሎጂ (እንግሊዘኛ-አማርኛ) መዝገበ ቃላት፤ የሞባይል መተግበሪያ እየተዘጋጀለት እንደሆነ ታውቋል፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👏 39 32👎 3
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵 በትናንትናው ዕለት የ11ኛው ዙር ዕድለኞች ዕጣ አወጣጥ በቲክቶክ እና በፌስቡክ ገፃችን ላይ በቀጥታ ስናስተላልፍ በነበረው መሰረት የ1,000,000 ብር ዕድለኛ ከቢሾፍቱ ሆነዋል! ማን ያውቃል ቀጣይ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! የበሽ ጥቅል እየገዛን እንንበሽበሽ! 🥳🎉🎉 ሌሎች የ100 ብር አሸናፊዎች #Besh100Winner በመጠቀም ኮሜንት ላይ ወይም Story ላይ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ታግ በማድረግ ያሳውቁን። 📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ 👇🏽 https://onelink.to/ewsb22 የቴሌግራም ቦታችን 👇🏽 https://t.me/official_safaricomet_bot ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ! #SafaricomEthiopia #MPESASafaricom #furtheraheadtogether #besh
Hammasini ko'rsatish...
27
Photo unavailableShow in Telegram
34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ ነው፡፡ ባለፈው በጀት ዓመት በትምህርት ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችን የሚገመግመው ጉባኤው፤ በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡ በጉባዔው ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ እና አጋር አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
47👍 41👏 9👎 4🙏 1
10ኛው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች አውደ ርዕይና ውድድር በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተከፍቷል። ዓመታዊ አውደ ርዕዩ ትምህርት ሚኒስቴር ከተባባሪ ተቋማት ጋር በመሆን የተዘጋጀ ነው፡፡ “ሳይንስ ለሰላም እና ልማት“ በሚል ጭብጥ ላይ የሚካሔደው አውደ ርዕይና ውድድር፤ እስከ ህዳር 05/2018 ዓ.ም ይቆያል፡፡ መድረኩ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች ልዩ ዝንባሌና ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች እና መምህራንን የሚያገናኝ ነው፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
29👏 14👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሰቨን ስታር ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ የበርካታ ዓመታት የማስተማር ልምድ ባላቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሐኪሞች የተመሰረተ ኮሌጅ! 🔔 ለ2018 ዓ.ም ምዝገባ ጀምረናል! በዲግሪ የጤና መርሐግብሮች ➫ ነርሲንግ ፐብሊክ ሄልዝ ፋርማሲ ሚድዋይፈሪ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ በዲግሪ የቢዝነስ መርሐግብሮች (በቀን እና በማታ) አካውንቲንግና ፋይናንስ ማርኬቲንግ ማኔጅመንት ቢዝነስ ማኔጅመንት ሰው ሀብት አስተዳደር በጤና በደረጃ-4 መርሐግብሮች ➫ በፋርማሲበላብራቶሪበነርሲንግበሚድዋይፈሪበሜዲካል ራዲዮግራፊ በቢዝነስ በደረጃ-4 መርሐግብሮች ➫ በአካውንቲንግና ፋይናንስበማርኬቲንግና ሴልስ ማኔጅመንት በሪሚዲያል መርሐግብር ፈጥነው ይመዝገቡ! አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን፣ ከባቡር ትኬት መቁረጫው ፊት ለፊት ☎️ 0982373737 / 0965686819
Hammasini ko'rsatish...
26