uz
Feedback
Tikvah-University

Tikvah-University

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
352 777
Obunachilar
-4824 soatlar
+967 kunlar
+1 45930 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት አመራሮች የአሠልጣኞች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል። መምህራን ከማስተማር ሥራ ጎን ለጎን አቅማቸውን የሚያጎለብቱበት የሥራ ላይ ተግባራዊ ስልጠና ተዘጋጅቶ በመላ ሀገሪቱ እንደሚሰጥ በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች ልማት ዴስክ ኃላፊ አሰገድ መሬሳ ተናግረዋል፡፡ በተያዘው ዓመት መጨረሻ ድረስ የሚሠጠው ይህ ስልጠና 70% መምህራኑና የትምህርት አመራሩ በሥራ ገበታቸው ላይ ሆነው የሥራ ላይ የተግባር ስልጠና የሚወስዱ ሲሆን፤ 20% ከሌሎች ልምድና ተሞክሮ የሚቀስሙበት እንዲሁም 10% የገጽ-ለገጽ ስልጠና እንደሚወስዱ ገልፀዋል። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
❤ 44👎 9👍 4🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ያኔት_ኮሌጅ በ6 ኪሎ ካምፖስ እና በሰፈረ ሰላም ካምፓስ የ2018 ዓ.ም ምዝገባ ጀምረናል! BSc Fields of Study: → BSc in Medical Laboratory Science → Bachelor of Pharmacy → BSc in Nursing TVET Programs: → Nursing → Medical Laboratory → Pharmacy → Accounting and Finance የCPD ማዕከል አገልግሎት ☎️ 0929969696/ 0996828282 አድራሻ፦ መሳለሚያ ሰፈረ ሰላም ንጉሴ ቱሩፊ ህንፃ 6 ኪሎ ካምፓስ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አጠገብ Telegram: @Yanet6kiloc
Hammasini ko'rsatish...
❤ 34🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ETA የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ከረዕቡ ህዳር 10/2018 ዓ.ም ጀምሮ በክልል የሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲሁም ለክልል መንግስታት እና ቢሮዎች ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የዳግም ምዝገባ የመስክ ግምገማ ያደርጋል፡፡ ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳዳር የሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዳግም ምዝገባ ውጤትን ባለፈው መስከረም ይፋ ባደረገበት ወቅት፣ ዳግም ምዝገባው በክልሎችም እንደሚጀመር መግለፁ ይታወሳል፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
❤ 63👎 24😢 6👍 3🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
በሀገሪቱ እየተፈጠረ ያለውን የመምህራን እጥረት ለመቅረፍ በጥናት ከተለዩ የአጭር ጊዜ መፍትሔዎች መካከል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲጨርሱና 4ኛ ዓመት ከመጀመራቸው በፊት በየትምህርት ዘርፋቸው ለአንድ ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ የሚለው አንዱ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ሰሞኑነን መግለፃቸው ይታወቃል፡፡ በጉዳዩ ላይ ውይይት መጀመሩ የተገለፀ ሲሆን፤ ውይይቱ በዚህ ዓመት ተጠናቆ ደንብ እንደሚወጣለትና በሚቀጥለው ዓመት ወደ ሥራ ሊገባ እንደሚችል ተነስቷል፡፡ ይህን ተከትሎ፣ በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ከትናንት ሰኞ ህዳር 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ፡፡ “በጉዳዩ ላይ እኛ ተማሪዎች በመጀመሪያ አስተያየት ልንጠየቅ ይገባል“፣ “ብዙ ጊዜያት ባክነውብናል፣ ተጨማሪ አንድ ዓመት ተቀባይነት የለውም“፣ "የመምህርነት ሙያ ስልጠና ያልወሰዱ ተማሪዎችን የማስተማር አገልግሎት ስጡ ማለት ተቀባይነት የለውም"፣ የመሳሰሉትን አስተያየቶቹ ተማሪዎቹ ይዘው ወጥተዋል፡፡ በተማሪዎቹ ተቃውሞ ላይ ትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡ ይሁን እንጂ ውሳኔው ያልተጠናቀቀና በውይይት ላይ ያለ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ በምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ ላይ ገልፀዋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ የሚሰጠውን ማንኛውም ውሳኔ ተከታትለን የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
❤ 403👍 122👎 42🙏 21🥰 12😢 10😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
የዓለም አቀፍ ግብይት (Import and Export Business) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ! 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አሰራሮች የሚተነተንበት 👉 በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች የሚሰጥ 👉 ስልጠናው በቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር ይሰጣል። ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Hammasini ko'rsatish...
❤ 44👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#MekdelaAmbaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። የምዝገባ ቦታ፦ ➫ የተፈጥሮ ሳይንስ የሪሚዲያል ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ (ጊምባ) ➫ የማኅበራዊ ሳይንስ የሪሚዲያል ተማሪዎች በመካነ-ሰላም ካምፓስ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ስምንት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣ ➫ የሌሊት አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
❤ 147👍 31👎 20👏 6🙏 5
Photo unavailableShow in Telegram
#MattuUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መቱ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ታህሳስ 01 እና 02/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ትምህርት ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ በበዴሌ እና በመቱ ካምፓሶች ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አራት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda) ➫ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
❤ 120👍 22🙏 13👎 9
Photo unavailableShow in Telegram
#ArbaMinchUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ትምህርት ሰኞ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች https://smis.amu.edu.et/pages/check_campus_placement ሊንክን በመጫንና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መለያ ቁጥር በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ማወቅ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል። የምዝገባ ቦታ፦ ➫ አባያ እና ጫሞ ካምፓሶች የተመደባችሁ ተማሪዎች አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙት አባያ እና ጫሞ ካምፓሶች ➫ ሳውላ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ አራት ፓስፖርት መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
❤ 83👍 64👎 20😱 5😢 5👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠና ይውሰዱ! ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ባሉበት ሆነው ይውሰዱ። የስልጠና ዘርፎች፦ 🌐 ዌብ ፕሮግራሚንግ 🤖 አንድሮይድ ማበልፀግ 📊 ዳታ ሳይንስ 🧠 አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ይመዝገቡ 👇 https://www.ethiocoders.et/ በ8 ሳምንታት ውስጥ ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ፥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይሰጥዎታል። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👎 98❤ 97👍 12🙏 11😢 9
Photo unavailableShow in Telegram
#JimmaUniversity ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ የውጭ ሀገራት ተማሪዎች አቀባበል አድርጓል፡፡ ተማሪዎቹ ከጎረቤት ሀገራት ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ የመጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በተማሪዎች አገልግሎት፣ በዩኒቨርሲቲው ደንብና መመሪያዎች እንዲሁም በአጠቃላይ የትምህርት እና የካምፓስ ደህንነት ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡ መንግሥት የትምህርት ዲፕሎማሲን በማጠናከር፣ ለጎረቤት ሀገራት ነጻ የትምህርት ዕድል በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በመስጠት ላይ ይገኛል። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👎 249❤ 101👍 26😱 8🙏 3😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE በክፍያ እና በጥቅማ ጥቅም ማነስ ምክንያት ወደ መምህርነት ሙያ የሚገባ የሰው ኃይል እየቀነሰ በመሆኑ፣ የመምህራን እጥረት ያጋጥማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለህ/ተ/ም/ቤት የሰው ሃብት ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡ የክፍያ ጉዳይ ለመምህራን ብቻ ሳይሆን የመንግሥት ሰራተኛውንና ሌላውንም የሚመለከት በመሆኑ፣ የደመወዝ ማስተካከያ መደረጉን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ ይህም በቂ ባለመሆኑ ክፍያው መጨመር እንዳለበት አስረድተዋል፡፡ አሁን ባለው የኑሮ ሁኔታ ምክንያት ወደ መምህርነት ሙያ የሚገባው የሰው ኃይል ቀንሷል ያሉት ሚኒስትሩ፤ የመምህራን እጥረት የሚጠበቅ በመሆኑ ችግሩ በጥናት ተለይቶ የአጭር ጊዜ መፍትሔ ለማግኘት ሙከራ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ የመጀመሪያው መፍትሔ ከመምህርነት ውጪ በሌላ የትምህርት መስክ ዲግሪ ያላቸውና ሥራ የሚፈልጉ ዜጎችን የአንድ ዓመት የፔዳጎጂ ስልጠና በመስጠት ወደ መምህርነት ገብተው እንዲያስተምሩ ለማድረግ ካሪኩለም ተዘጋጅቶ የገንዘብ ሚኒስቴር ፋይናንስ ተጠይቆ እየተጠበቀ ነው ብለዋል፡፡ ሁለተኛው መፍትሔ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አገልግሎት መጀመር ሲሆን፤ የ3ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ ዓመት ከመጀመራቸው በፊት በየትምህርት ዘርፋቸው ለአንድ ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፤ በዚህም ውይይት መጀመሩንና በርካታ መምህራን ለማፍራት ይቻላል ተብሎ እንደሚጠበቅ አብራርተዋል፡፡ ውይይቱ በዚህ ዓመት ተጠናቆ ደንብ ከወጣ በኋላ፣ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ሥራ እንደሚገባ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ #ሪፖርተር @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👎 443❤ 119😢 14👍 13🙏 4😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
37ኛ፣ 38ኛ እና 39ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና ነገ ማክሰኞ ህዳር 09/2018 ዓ.ም እና ሐሙስ ህዳር 11/2018 ዓ.ም በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ይጀመራል። 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 መሠረታዊ የአካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ 👉 ስልጠናው ከፒስቺሪ በተጨማሪ በExcel፣ Word እና ተግባራዊ ዶክመንቶች ታግዞ የሚሰጥ ነው። የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 ☎️   0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Hammasini ko'rsatish...
❤ 63👎 3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የግል ትምህርት ቤቶችን ፈቃድ የመስጠት፣ እውቅና የማግኘት እና የመመዝገብ ሙሉ ሥልጣን ለክልል ትምህርት ቢሮዎች ተላለፈ። ውሳኔው ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው አዲስ መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት ረቂቅ ደንብ መሠረት መሆኑ ተገልጿል። ውሳኔው በመላ አገሪቱ የሚገኙ የግል ትምህርት ተቋማትን አሠራር ለማካለል እና የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል። አዲሱ ረቂቅ ደንብ በጠቅላላ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 ላይ የተመሰረተ ሲሆን፤ የክልል ትምህርት ቢሮዎች የግል ትምህርት ቤቶች፣ በሲቪል ማኅበራት የሚተዳደሩ ተቋማት እና የኃይማኖት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የሁሉም መንግሥታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች ፈቃድና ምዝገባ ጉዳዮችን እንዲያከናውኑ ስልጣን ሰጥቷቸዋል። ምንም እንኳን በረቂቅ ደንብ አብዛኛው ሥልጣን ለክልሎች የተላለፈ ቢሆንም፣ የትምህርት ሚኒስቴር በዋናነት በአለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች (International Schools) እና በማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች (Community Schools) ላይ ያለውን ብቸኛ የፈቃድና የቁጥጥር ስልጣን እንደያዘ ይቆያል። ከሥልጣን ክፍፍሉ በተጨማሪ ረቂቅ ደንቡ ሁሉንም የግል ትምህርት ቤቶች ዳግም ምዝገባ እንዲያደርጉ ያስገድዳል እንዲሁም የመመዝገቢያ፣ የገንዘብ አስተዳደር እና የተቋማዊ አመራር ጥብቅ ደረጃዎችን አስቀምጧል። በረቂቁ መሠረት ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ኮሚቴ እንዲያቋቁሙና በገንዘብ አስተዳደራቸው ሙሉ በሙሉ ገለልተኛና ግልፅ እንዲሆኑ ይጠበቅባቸዋል። #Capital @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
❤ 222👎 81👍 14🙏 10😢 9🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ ኦሞ ዞን የምርምር ማዕከል ሊያቋቋም ነው። ዩኒቨርሲቲው በደቡብ ኦሞ ዞን ዲመካ ከተማ ላይ የምርምር ማዕከል ለማቋቋም የያዘውን እቅድ መተግበር መጀመሩን ገልጿል። ዩኒቨርሲቲው በ2018 በጀት ዓመት ለማከናወን ካቀዳቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል፣ በደቡብ ኦሞ ዞን ዲመካ ከተማ የምርምር ማዕከል መክፈት አንዱ እንደሆነ ተገልጿል። ዩኒቨርሲቲው ለተቋሙ ግንባታ የተረከበውን 3 ሄክታር መሬት ወደተግባር ለማስገባት የጠረጋ እና ሳይቱን የማስተካከል ሥራ በዛሬው ዕለት ጀምሯል። የምርምር ማዕከሉ በብዝሃ-ባህልና ሀገር በቀል ዕውቀት፣ በቱሪዝም እንዲሁም በእንስሳት ሃብት ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሠራል ተብሏል። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
❤ 97👏 11🥰 5👎 4🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል። ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥራት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል። የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል። ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል። #Fortune @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👎 2 736❤ 363😢 205👍 62😱 62🥰 15👏 15🙏 7
Photo unavailableShow in Telegram
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሦስት ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው የ100 ሺህ ብር ሽልማት ሰጥቷል። ቢሮው በክልሉ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪ ራይስ ባሳ (ከዳውሮ ዞን)፣ ተማሪ በፍቃዱ አስናቀ (ከዳውሮ ዞን) እና ተማሪ ኤፍሬም ተገኝ (ከቤንች ሸኮ ዞን) የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል። ቢሮው ከ500 በላይ ነጥብ ላመጡ 13 የክልሉ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው የ20 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል። በተጨማሪ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቷል። ቢሮው ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የእውቅናና የምስጋና ሰርተፍኬት ሰጥቷል። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
❤ 120👏 13🙏 13😱 6👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
#ያኔት_ኮሌጅ በ6 ኪሎ ካምፖስ እና በሰፈረ ሰላም ካምፓስ የ2018 ዓ.ም ምዝገባ ጀምረናል! BSc Fields of Study: → BSc in Medical Laboratory Science → Bachelor of Pharmacy → BSc in Nursing TVET Programs: → Nursing → Medical Laboratory → Pharmacy → Accounting and Finance የCPD ማዕከል አገልግሎት ☎️ 0929969696/ 0996828282 አድራሻ፦ መሳለሚያ ሰፈረ ሰላም ንጉሴ ቱሩፊ ህንፃ 6 ኪሎ ካምፓስ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አጠገብ Telegram: @Yanet6kiloc
Hammasini ko'rsatish...
❤ 21
Photo unavailableShow in Telegram
የኮምፒውተር ጥገና እና ኔትዎርኪንግ (Computer Maintenance and Networking) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን! 👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና 👉 የሶፍትዌር ላይ ጥገናን አካቶ የሚሰጥ ☎️   0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Hammasini ko'rsatish...
❤ 34
Photo unavailableShow in Telegram
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት 124 የህክምና ባለሙያዎችን አስመረቀ። ዩኒቨርሲቲው በህክምና ዶክተር በመጀመርያ ዲግሪ (62) እና በሁለተኛ ዲግሪ (62) በአጠቃላይ 124 የህክምና ባለሙያዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
❤ 212👍 43👏 20😢 20😱 14👎 13🙏 4
#MoE የክብር ዶክትሬት የተሠጣቸውን ግለሰቦች “ዶክተር ወይም የክብር ዶክተር“ በማለት በመጠሪያነት መጠቀም አይቻልም፡፡ - የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የተቋማቸውን የ1ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ትናንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡ በከፍተኛ ትምህር ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ ችግር የነበረበት መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ወጥ አሰራር ለመከተል በማስፈለጉ የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ ሀገራዊ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል። ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸው ያሉት ብርሃኑ (ፕ/ር)፤ የክብር ዶክትሬት ማዕረግ የሚያገኙ ሰዎችን 'ዶክተር' ወይም 'የክብር ዶክተር' በሚል መጠሪያ መጠቀም እንደማይቻል አሳስበዋል። የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው በመመሪያው ተገልጿል፡፡ በሙያው የተለየ ሥራ ያበረከተ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ በመመሪያው የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ማግኘት እንደሚችል ጠቅሰዋል። ትምህርት ሚኒስቴር የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን የተመለከተ መመሪያ (Guideline for the Bestowal of Honorary Doctorate Degrees in Ethiopian Higher Education Institutions) አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት ሐምሌ 2017 ዓ.ም መላኩ ይታወቃል። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
❤ 169👍 39👎 14👏 13😢 5