uz
Feedback
Addis Ababa Education Bureau

Addis Ababa Education Bureau

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
150 232
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+677 kunlar
+34630 kunlar
Postlar arxiv
Hammasini ko'rsatish...
27👍 8👎 3👏 1
ፕሬዘዳንቱ አያይዘውም የማህበሩ አባላት የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ በተደረገ ጥረት መምህራን በማህበር ተደራጅተው የቤት ባለቤት ለመሆን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸውን፣ ለመምህራን ነጻ ህክምና የሚሰጥ G+6 ሆስፒታል እና G+9 ሁለገብ ህንጻ ግንባታ መጀመሩ፣ መምህራን ከአንበሳ አውቶብስ ባሻገር የሸገር ባስ ትራንስፖርት በነጻ እንዲጠቀሙ መደረጉ እንዲሁም የመምህራን የደረጃ እድገት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ከትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ መሰራቱ እንዲሁም አባላቱ ሙያቸውን ማሳደግ የሚችሉበት ተከታታይ ስልጠና እንዲያገኙ ማህበሩ ያደረገው ጥረት ውጤታማ መሆኑን ገልጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ለሙያ ማህበሩ እያደረጉ ለሚገኘው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ማህበሩ በቀጣይ የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ እና የአባላቱ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ በትኩረት መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል። በጉባኤው የመጀመሪያ ቀን የማህበሩ የአራት አመት አፈጻጸም እንዲሁም የማህበሩ የውስጥ እና የውጭ ኦዲት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ጉባኤው በነገ ውሎው ማህበሩን ለቀጣይ አራት አመታት የሚመሩ ስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ እንደሚያካሂድ የወጣው መርሀግብር ያሳያል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
39👎 10🥰 2🔥 1👏 1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር 23ኛውን መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ። (መስከረም 8/2018 ዓ.ም) በሁለንተናዊው የተጠናከረ ማህበር ለሁለንተናዊ የመምህራን እና ከተማችን እድገት በሚል መሪ ቃል ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በመካሄድ ላይ በሚገኘው ጉባኤ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አመራሮችን ጨምሮ የከተማው ፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች እና ከየትምህርት ቤቱ የመጡ የመሰረታዊ መምህራን ማህበር አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ አሊ ከማል በጉባኤው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ እየተመዘገበ ለሚገኘው የተማሪ ውጤት መሻሻል የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር አመራሮችም ሆኑ አባላት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ቢሮው በቀጣይ የሙያ ማህበሩ የአባላቱን መብት እና ጥቅማጥቅም ለማስከበር እያደረገ የሚገኘው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን ከማህበሩ ጋር በጋራ መስራቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸው የሙያ ማህበሩ የመምህራንን መብትና ጥቅም ከማስከበር ባሻገር በየደረጃው የሚገኙ መዋቅሮቹን በማስተባበር የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ የተለያዩ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን አስታውቀዋል።
Hammasini ko'rsatish...
33😁 3👍 2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ሴት አመራሮች ኮከስ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ፡፡ (መስከረም 8/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ሴት አመራሮች (ኮከስ) 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ : በጉባኤው ተገኝተው ሴቶች ሲመሩ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ያሳዩ ከፍተኛ አመራሮች በከተማችን ያየንበት ወቅት በመሆኑ የሴት መምህራን ማህበሩ ይህን አርአያነት ያለው ሥራ በማስቀጠል ሴቶች ከወንዶች እኩል ካላቸው እውቀት በተጨማሪ ተፈጥሮ የሰጠቻቸውን ጥበብ ተጠቅመው ሀገርን አልፈው አለምን የሚለውጡ እንዲሆኑ በርትቶ መስራት ከማህበሩ ይጠበቃል ብለዋል:: የሴት መምህራን ማህበሩ ከመደራጀት ባለፈ የሚታይ ሥራ እየሰራ መሄድ አለበት ያሉት ፕሬዝዳንቱ ጉባኤው በምክክሩ የተሻሉ ለውጦች እንዲመጡ የሚያደርጉ ውሳኔዎች እንደሚያሳልፍ እንጠብቃለን ብለዋል::
Hammasini ko'rsatish...
46👎 2
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ስርዓተ ፆታ ዘርፍ ተጠሪ ወ/ሮ ደስታዬ ታደሰ በጉባኤው ላይ ተገኝተው እንዳሉት መምህራን ማህበሩ አሁን ያለበት ደረጃ ለማድረስ ሰፊ ሥራ መሰራቱን ጠቁመው አሁን ባለን እውቀት ክህሎትና ተግባቦት ስራቸውን በመመዘን ትችላላችሁ የምንላቸውን ሴቶች ወደፊት የምናመጣበት እንዲሁም ለሴቶች ልዩ ዕድል የሚፈጥርና ቅብብሎሹ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል የሚያደርጉ ትልልቅ ሀሳቦች የሚነሱበት ጉባኤ እንዲሆን ይጠበቃል ብለዋል:: አያይዘውም በውይይቱ በሚደረግ የስራ አፈፃፀም ግምገማ መሰረት የታዩ ጉድለቶችን በማረምና ወደፊት የሚያራምድ የተሻለ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ማህበሩ የተቋቋመበት አላማ ግብ እንዲመታ ልትሰሩ ይገባል ብለዋል:: በጉባኤው ማህበሩ በ4 አመታት ያከናወናቸዉ ዋና ዋና ሥራዎች የያዘ ሪፖርት የማህበሩ ሰብሳቢ በሆኑት ወ/ሮ መስከረም አበራ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል:: በተያያዘም በጉባኤው በተካሄደ ምርጫ መሰረት ኮከሱን በአመራርነት ሲያገለግሉ የቆዩ የአገልግሎት ዘመናቸውን ያጠናቀቁ አመራሮች በአዳዲስ አመራሮች ተተክተዋል : ለቀድሞ የማህበሩ አመራሮችና አጋር አካላትም እውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷል:: በጉባኤው የመምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አቤል ኤፍሬም ፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ስርዓተ ፆታ ዘርፍ ተጠሪ ወ/ሮ ደስታዬ ታደሰ እንዲሁም የኮከሱ ሴት አመራሮች እና የሁሉም ክፍለ ከተሞች መምህራን ማህበር ሴት አመራሮች ተሳትፈዋል:: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
38
ማስታወቂያ! (መስከረም 08/2018 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
104👎 29😁 16👍 5🥰 1👏 1
ቤት የተረከቡ ዜጎች በበኩላቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ህይወታቸውን ሲገፉ መቆየታቸውን ገልጸው አሁን ለተደረገላቸው የበጎነት ተግባር አመስግነዋል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
🤣 14 10🖕 4👍 2
በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎችን ከተጎሳቆለ ህይወት ለማውጣት የተደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው፦ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ (መስከረም 08/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 በበጎ ፈቃድ ያስገነባቸውን 15 መኖሪያ ቤቶች ያስረከበ ሲሆን በርክክቡ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ፣ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ፣ የትምህርትና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ይዘዲን ሙስባህ ፣ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ እንዲሁም ሌሎች አመራሮችና እንግዶች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል፡፡ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎችን ከተጎሳቆለ ህይወት ለማውጣት የተደረገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ዛሬ በአዲስ ከተማ የተደረገው የበጎነት ተግባር በሌሎች ክ/ከተሞችም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል፡፡ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው የሃገራችን መገለጫ የሆነውን የእርስ በእርስ መረዳዳት እሴታችንን በማጎልበት ቤት ገንብታችሁ ያስረከባችሁ የዘርፉ አመራሮች፣ ሰራተኞችና በጎ ፈቃደኞች በሙሉ ክብር ይገባችኋል ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ይዘዲን ሙስባህ 15 የአቅመ ደካማ ቤቶችን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ተገንብቶ ለነዋሪዎች መተላለፉን ጠቅሰው ከዚህም ጎን ለጎን ለ15 አባወራዎች ሰፎና ፓኬጁን በጠበቀ መልኩ ማዕድ ተጋርተዋል ሲሉ ገልፀዋል::
Hammasini ko'rsatish...
26👍 4🥰 1
የቢሮው አጠቃላይ ካውንስል አባላት በየ15 ቀኑ የሚያካሂዱትን የስራ ክፍሎች እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ዛሬም ቀጥለው አካሂደዋል። (መስከረም 8/2018 ዓ.ም) በዛሬው መርሀግብር የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት በቁልፍ አመላካች ተግባራት እና በሪፎርም ስራዎች ያከናወናቸው ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጥላዬ ዘውዴ ስራ ክፍሉ ከቢሮ ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ 128 የሱፐርቪዥን ክላስተር ማዕከላትን በማስተባበር ትምህርት ተቋማት ለ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት ያከናወኑት የቅድመ ዝግጅት ተግባር ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና በየትምህርት ቤቱ በመገኘት የትምህርት አጀማመር ሂደቱን በተመለከት የሱፐርቪዥን ስራ ተሰርቶ ለሚመለከተው አካል ግብረመልስ መላኩን ገልጸው ስራ ክፍሉ በቀጣይ ከሱፐርቪዥን ስራዎች ባሻገር የጥናትና ምርምር ስራዎችን በመስራት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አመላክተዋል። የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ ዕቅና ከተሰጣቸው የስራ ክፍሎች መካከል አንዱ መሆኑን የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ጠቁመው ወቅቱ የ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት የተጀመረበት እንደመሆኑ ስራ ክፍሉ በክላስተር ማዕከላት የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮችን በማስተባበር በየትምህርት ቤቱ በመገኘት የሚያካሂደውን የክፍል ውስጥም ሆነ አስተዳደራዊ ሱፐርቪዥን አጠናክሮ በመቀጠል ግብረ መልሱን ለሚመለተው አካል ተደራሽ ማድረግ የሚጠበቅበት መሆኑን አስገንዝበዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
50👍 8
የአብዲ ጃርሶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የህዳሴውን ግድብ መመረቅን አስመልክቶ ደስታቸውን ገለፁ። (መስከረም 7/2018 ዓ.ም) ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የሚገኘው የአብዲ ጃርሶ ት/ቤት ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ሌሎች የትምህርት ባለድርሻ አባላት የታላቁን ህዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ የድጋፍና የተሰማቸውን ደስታም ገልጸዋል። በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሌማንቾ የህዳሴው ግድብ የትምህርት ማህበረሰቡን ጨምሮ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ርብርብ አድርጎ ተገንብቶ የተመረቀ ኢትዮጵያም ሆነ ሌሎች የጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ነው ብለው በቀጣይም በህዳሴው ግድብ የታየው ሀገራዊ አንድነት፣ የጋራ መግባባትና ቁርጠኝነት በሌሎች ፕሮጀክቶች ላይ በመድገም የብልፅግና ጉዞአችንን ለማፋጠን የጋራ መነሳሳት የፈጠረ እንደሚገባ ገልፀዋል ። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
59
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በጋራ በመተባበር የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና መመረቅን ምክንያት በማድረግ በገላን ቁጥር ሁለት 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደማቅ የድጋፍ መርሃ-ግብር አካሂደዋል። (መስከረም 7/2018 ዓ.ም) በድጋፍ መርሃ-ግብሩ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች በገላን ቁጥር ሁለት 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት የተሰማቸውን ታላቅ ደስታ መፈክሮችን በመያዝና የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን በማቅረብ ገልፀዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ድሪባ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያዊያንን አንድ ያደረገ የትውልዱ አሻራ መሆኑንና ግድቡ በርካታ መስዋዕትነትን የተከፈለበት የውስጥና የውጭ የጥፋት ሀይሎችን ተቋቁሞ ለዚህ የደረሰ መሆኑን ገልፀው መጪው ትውልድ በጋራ በመተባበር ሀገሪቱን ወደ ከፍታ ማማ ማድረስ እንደሚገባ ተናግረዋል። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ መቻልዋን ያሳየችበት ዳግማዊ አድዋ መመሆኑን የገለፁት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሂሩት ዓለሜ በቀጣይ የሚሰሩ በርካታ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ጠቅሰው በህዳሴው የመጣውን ስኬት በትምህርት በመድገም የሀገሪቱን ዕድገት ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል።
Hammasini ko'rsatish...
39👍 4🤮 1
የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር ባለማው sip.moe.gov.et ፖርታል ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ። (መስከረም 7/2018 ዓ.ም) የአሰልጣኞች ስልጠናው ለክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪዎች እና ዘርፉን ለሚያስተባብሩ የስራ መሪዎች እንዲሁም ለአይ ሲቲ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውም ከኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር በመጡ የዘርፉ ባለሙያ ነው የተሰጠው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ፖርታሉ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የተከናወኑ ተግባራትን ጨምሮ በትምህርት ተቋማቱ የሚገኙ እና የጎደሉ ግብአቶች መረጃ የሚሞላበት እንደመሆኑ ህብረተሰቡ ለትምህርት ቤቶቹ ድጋፍ ማድረግ እንዲችል የተቋማቱን መረጃ ወደ ፖርታሉ ማስገባት እንደሚገባ ገልጸው የአሰልጣኞች ስልጠናውን የወሰዱ አካላትም በየትምህርት ቤቱ ተመሳሳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት መረጃዎቹ ወደ ፖርታሉ እንዲገቡ ማድረግ የሚጠበቅባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀጸላ ፍቅረማርያም በበኩላቸው ፖርታሉ የትምህርት ተቋማት ያለባቸውን የግብአት እጥረት በመቅረፍ ደረጃቸውን ማሻሻል እንዲቻል መረጃዎች የሚሞሉበት መሆኑን ጠቁመው የስልጠናው ተሳታፊዎች ህብረተሰቡ በቀላሉ ፖርታሉን ተጠቅሞ የተቋማቱን መረጃ ማየት እንዲችል በየትምህርት ቤቱ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ግንዛቤ መፍጠር የሚገባቸው መሆኑን አመላክተዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
45👍 2👏 1
ኢትዮጵያ ችላለች! (መስከረም 6/2018 ዓ.ም) በምክትል ከንቲባ እና የኢዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ በአቶ ጃንጥራር አባይ የተመራ ልዑክ ቡድን ታላቁ የህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል:: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
62👍 10👌 2🕊 2🔥 1
የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት በጫወታ የማስተማር ስነ ዘዴ ዙሪያ በተግባር የተደገፈ የማጠናከሪያ (refreshment) ስልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን አስታወቀ። (መስከረም 6/2018 ዓ.ም) ስልጠናው በሁሉም ክፍለከተሞች ከሚገኙ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 2,790 መምህራን ለተከታታይ አራት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በዛሬው እለት በሰባት ክፍለ ከተሞች ስልጠናው መጀመሩን እና በቀጣይ ቀናት በቀሩት ክፍለ ከተሞች ስልጠናው የሚሰጥ መሆኑን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው ወቅቱ የ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት የተጀመረበት እንደመሆኑ የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራኑ በተነቃቃ ሁኔታ በጫወታ የማስተማር ስነዘዴን ተግባራዊ ማድረግ እንዲችሉ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸው ቢሮው በ2017 ዓ.ም ከቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን ባሻገር ለሞግዚቶች፣ለአስተባባሪዎች እና ለርዕሳነ መምህራን ተመሳሳይ ስልጠና መስጠቱን አስታውቀዋል። ዳይሬክተሩዋ አያይዘውም ስልጠናው ቀደም ሲል የአሰልጣኞች ስልጠና በወሰዱ መምህራን እየተሰጠ እንደሚገኝ ጠቁመው በቀጣይ ለግል ትምህርት ቤት መምህራን ተመሳሳይ የማጠናከሪያ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን አመላክተዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
32🏆 1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን አስመልክቶ "በህብረት ችለናል!"በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት አካሄደ። (መስከረም 6/2018 ዓ.ም) የቢሮው ስትራቴጂክ ካውንስል አባላትን ጨምሮ ጠቅላላ የተቋሙ ሰራተኞች በተገኙበት በተካሄደው ውይይት የግድቡን መጠናቀቅ አስመልክቶ የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ በምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ወንድሙ ኡመር ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ካለው ላይ ቀንሶ አሻራውን ያሳረፈበት ፕሮጀክት መሆኑን ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ወንድሙ ኡመር ሰነዱን ባቀረቡበት ወቅት ገልጸው ግድቡ ሀገሪቱ የጀመረችው የማንሰራራት ጉዞ ውጤታማ እንዲሆን የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር የመልማት ፍላጎታችንን ከፍ የሚያደርግ ፕሮጀክት መሆኑን አስረድተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በበኩላቸው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ጫናዎችን ተቋቁማ በራሷ አቅም ገንብታ ያጠናቀቀችው ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሰራተኞችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ማህበረሰቦች ለግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ ከደሞዛቸው በማዋጣት ያደረጉት ድጋፍ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አመላክተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን እንደምንችል ያሳየንበት ከመሆኑ ባሻገር ለትውልድ የሚተላለፍ ፕሮጀክት መሆኑን የውይይቱ ተሳታፊዎች ጠቅሰው ግድቡ ሀገራዊ መግባባትንም ሆነ ቀጠናዊ ትስስራችንን የሚያጠናክር ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑን አስገንዝበዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
66👍 10🥰 5👎 1
የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡ (መስከረም 6/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በ2018 የትምህርት ዘመን አጀማመር ምክንያት ሳይካሄድ የቆየ ቢሆንም በዛሬው እለት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሬዲዮ ክፍል ቡድን መሪ አቶ ሴኔሳ ነጋሹ በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ መሰረት ያደረገ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ማህበራዊ ሚዲያውን በአግባቡ በመጠቀም ለበጎ አላማ ማዋል ይገባል ያሉ ሲሆን የቢሮውን ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ሰራተኞች በአግባቡ በመከታተል መረጃዎችን የማጋራት ስራን በማከናወን እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ያሉ አካላት እንዲሳተፉ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
34
በጨዋታ የማስተማር ዘዴ ላይ ስልጠና ለሚሰጡ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ:: (መስከረም 5/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክቶሬት በ11 ዱም ክፍለ ከተሞች በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች በጨዋታ የማስተማር ዘዴ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ለሚሰጡ አሰልጣኞች ኦረንቴሽን ሰጥቷል :: ስልጠናው ለ4 ቀናት በጨዋታ የማስተማር ስነ ዘዴ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰጥ መሆኑን የገለፁት የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክተር ወ /ሮ በላይነሽ የሻው ስልጠናው ቀደም ባለው ዓመት የአሰልጣኞች ስልጠና በተሰጣቸው ባለሙያዎች ለቀዳማይ ልጅነት መምህራን መሰጠቱን አስታውሰው በድጋፍና ክትትል የታዩ የአፈፃፀም ክፍተቶችን በማረም ብቁ የሆኑ በጨዋታ የማስተማር ስነዘዴን ተግባራዊ ማድረግ የሚችሉ መምህራን እንዲኖሩ አቅም ይፈጥራል ሲሉ አብራርተዋል :: አሰልጣኞችም ስልጠናው የታለመለትን ግብ መምታት እንዲችል የቀረቡ የስልጠና ዘዴና ቁሳቁሶችን በመጠቀም ለሰልጣኞች በቂ እውቀት እንዲያስጨብጡ አሳስበዋል :: የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ትግበራ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ይልማ ተሾመ የስልጠናውን አካሄድ አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተው ለአሰልጣኞች የስልጠና ጣቢያ አሳውቀዋል :: በኦረንቴሽኑ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የቀዳማይ ልጅነት አስተባባሪዎች እና መምህራን ተሳትፈዋል :: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
49👍 1🥰 1🥴 1
Hammasini ko'rsatish...
23🔥 3👏 3
በ2017 ዓ.ም በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች (መስከረም 5/2018 ዓ.ም) Haimanot Yohanes wubishet 579 natural science Besrat Gebriel school Simbo Dereje Ayana 548 social science St. John Baptist de La Salle Catholic School መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
👏 153 139👍 48🥰 13🏆 12👎 8🖕 8🔥 7
በመረሃ ግብሩ ላይ በመድረኩ የተገኙ የክቡር እንግዶች ለተማሪዎች የትምህርት ግብአቶች የመስጠት ፕሮግራም እና ችቦ የማብራት እና ቅብብሎሽ ፕሮግራም የተከናወነ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት የትምህርት ዘመን መደበኛ ትምህርት በይፋ የማስጀመርያ መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ፣የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ፣ የየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሳ ወዳጆን ጨምሮ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በዛሬው ዕለት በክፍለ ከተማው ባሉ ሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በይፋ ተጀምሯል።‎ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
29👎 3😁 1