uz
Feedback
Addis Ababa Education Bureau

Addis Ababa Education Bureau

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
150 232
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+677 kunlar
+34630 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
ማስታወቂያ! (23/12/2017 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ተሰጥኦና ብቃት ያላቸው ተማሪዎች መልምሎ ልዩ ትምህርትና ስልጠና እንዲያገኙ በፌደራል ደረጃ በተቋቋሙ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት እነዚህን ትምህርት ቤቶች የሚመሩ ዳይሬክተሮችን ከመላ ሀገሪቱ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ እና በልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዳይሬክተር መሆን ለምትፈልጉ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች http://sbs.moe.gov.et/directors/apply ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ገልጻል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
104👍 15👎 4😁 4🤮 3
Photo unavailableShow in Telegram
ነፃ የትምህርት እድል ማስታወቂያ መመዝገቢያ ሊንክ:- https://forms.gle/9Cp99fyiQpvzSVMe7 (23/12/2017 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
54👏 9👎 4😁 3👍 2
በ2018 ትምህርት ዘመን ትራንስፎርም የሚያደርጉ 129 ትምህርት ቤቶች ላይ ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡ (ነሀሴ 23/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክቶሬት በ2018 ትምህርት ዘመን ትራንስፎርም የሚያደርጉ 129 ትምህርት ቤቶች ላይ ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ የቢሮ ባለሙያዎችና የክፍለከተማ ቡድን መሪዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡ የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በኦረንቴሽኑ ላይ እንዳሉት የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን በየበጀት አመቱ ትራንስፎርም ለማድረግ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ የቆዩ መሆኑን አስታውሰው በቀሪ129 ትምህርት ቤቶች ላ ያሉ የግብአትና መሰረተ ልማቶችን በዚህ ዘመን ለማሟላት እንዲቻል ትምህርት ቤቶቹ ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም የሚስችል ቼክሊስት መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ ምከትል ቢሮ ሃላፊው እንዳሉት በድጋፍና ክትትል በሚገኘው ውጤት መሰረት ምቹ የመማሪያ አካባቢን ለመፍጠርና ትምህርት ቤቶቹን በግብአት ለማሟላት ቢሮው ቅድመ ዝግጅት እንደሚያደርግ አብራርተዋል፡፡ የአክለውም ድጋፍና ክትትሉን የሚያደርጉ ባለሙያዎች በቼክሊስቱ መሰረት ያለውን ክፍተት ለመለየት የሚያስችል ተአማኒ መረጃ በመሰብሰብ በቀጣይ ለትምህርት ቤቶቹ ለሚደረግ ድጋፍ ግብአት የሚሆን መረጃ እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡ የዘርፈብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ በላይነሽ የሻው የድጋፍና ክትትል ቼክሊስቱ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል አያይዘውም የሚገኘው ውጤት የተሻለ የትምህርት ስርዓትን ለማስፈን ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በድጋፍና ክትትል ስራው የቢሮ ባለሙያዎችና የክፍለከተማ ቡድን መሪዎች እንደሚሳተፉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
86👍 13
ቢሮው ያቋቋመው የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ (የተገልጋይ ካውንስል) ለመማር ማስተማር ስራው ውጤታማነት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ። (ነሀሴ 23/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ ተግባር እና ኃላፊነት ዙሪያ ከጉባኤው አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራቱ በመማር ማስተማር ሂደቱ ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤው ቢሮው የሚሰጠው አገልግሎት ተሻሽሎ በትምህርት ተቋማት ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር በጉባኤው የማቋቋሚያ ማኑዋል በተቀመጠው መሰረት ኃላፊነት እና ተግባራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በበኩላቸው ቢሮው የሚያከናውናቸው ተግባራት የተገልጋዩን እርካታ እንዲያሻሽሉ እና ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤው መቋቋሙን ጠቁመው ቢሮው በቀጣይ ከጉባኤው አባላት ጋር የቅርብ ግንኙነት እየፈጠረ የተከናወኑ ተግባራትን እንደሚገመግም አስገንዝበዋል። የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ(የተገልጋይ ካውንስል) ከተገልጋይ ግለሰቦች የሚወከሉ አባላትን ጨምሮ ከሲቪክ ማህበራት፣ ከባለድርሻ ተቋማት እንዲሁም ከትምህርት ቢሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎችን አካቶ መቋቋሙን የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ አመላክተዋል።
Hammasini ko'rsatish...
67👎 16
Hammasini ko'rsatish...
56
አዲስ አበባ አሸናፊ ሆናለች! (22/12/2017 ዓ.ም) https://www.bloomberg.org/press/the-bloomberg-philanthropies-initiative-for-global-road-safety-announces-winners-of-inaugural-speed-challenge/ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
60👍 48👎 11👏 4😨 4
Photo unavailableShow in Telegram
32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ YAA’II BARNOOTAA 32FFAA SADARKAA MAGAALAA (22/12/2017 ዓ.ም) በዕውቀትና በክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን! DHALOOTA BEEKUMSAAFI DANDEETTIIN GAHOOME HORACHUUDHAAN ITIYOOPHIYAA BIYYA FAKKEENYAA NITAASIFNA! መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
47👍 10🥰 5👏 4
Barnoota Herregaa Kutaa 5ffaa https://youtu.be/wu40ax4x6DM
Hammasini ko'rsatish...
26👍 6
የትምህርት ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 ዓ.ም በኮሙኒኬሽን ስራ አፈጻጸም1ኛ ደረጃ በመያዝ እውቅና ተሰጠው፡፡ (21/12/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ በተካሄድ የኮሙኒኬሽን ስራዎች አፈጻጸም ምዘና በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ሴክተር ተቋማት መካከል1ኛ ደረጃ በመያዝ እውቅና ተበርክቶለታል፡፡ እውቅናው በቀጣይ ለሚከናውኑ የኮሙኒኬሽን ስራዎች አቅም በመሆን ለተሻለ አፈጻጸም የሚያነሳሳ ሲሆን ለዚህ ውጤት መመዝገብ የድርሻችሁን ለተወጣቸው አካላት በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
103👍 35👎 12🥰 6🖕 5
Hammasini ko'rsatish...
33👎 6👏 4
Photo unavailableShow in Telegram
32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ YAA’II BARNOOTAA 32FFAA SADARKAA MAGAALAA (20/12/2017 ዓ.ም) በዕውቀትና በክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን! DHALOOTA BEEKUMSAAFI DANDEETTIIN GAHOOME HORACHUUDHAAN ITIYOOPHIYAA BIYYA FAKKEENYAA NITAASIFNA! መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
81👍 33 1
Hammasini ko'rsatish...
6
Call for Registration: EGATE Short Training Programs for Gifted Ethiopian Youth The Ethiopian Gifted and Talented Education School (EGATE) announces a call for registration for one-month training programs tailored for gifted and talented Ethiopian youth. These programs focus on Astronomy & Space Science, Biotechnology, Digital & Emerging Technology, and Robotics & Electronic Technology, designed to inspire and equip young innovators with cutting-edge skills through an immersive learning methodology. Program Details * Duration: 1 month per program, intensive and hands-on. * Target Group: Gifted students aged 15–21 with a passion for science, technology, and innovation. * Location: EGATE campus, Burayu town, with select sessions at science laboratories in Addis Ababa University (AAU), the Biotechnology Institute, Addis Ababa Science and Technology University (AASTU), and other partner facilities. * Cost: Free for gifted and talented participants, supported by EGATE and partners. Program Highlights: please visit https://egate.et Curriculum Features * Self-Paced Learning: Flexible modules allow students to progress at their own speed. * Differentiated Instruction: Tailored content to match individual skill levels and interests. * Enrichment Program: Advanced challenges, projects, and real-world applications to deepen understanding. * Immersive Learning Methodology: Hands-on experiments, collaborative projects, and mentorship by renowned professors and doctors in their respective domains. How to Register 1. Apply Online: Visit https://egate.et to complete the application form. 2. Submit Documents: Provide academic records and a short statement of interest (200 words max). 3. Recommendation: Include one teacher or mentor recommendation. 4. Video Submission: Submit a 3-minute video showcasing your talents, passion for science/technology/innovation, and any relevant project profiles or accomplishments. The video should highlight your creativity, skills, and motivation for joining the program. 5. Selection Process: Applicants will be shortlisted based on the criteria outlined on https://egate.et Interviews may be required. 6. Deadline: Applications close on Sept 7, 2025. Limited spots available. Why Join? * Expert Mentorship: Learn from renowned professors and doctors specializing in astronomy, biotechnology, digital technology, and robotics. * Advanced Facilities: Access state-of-the-art laboratories at AAU, AASTU, and the Biotechnology Institute for hands-on learning. * Practical Skills: Gain real-world experience through immersive, project-based training. * Networking: Connect with like-minded peers and industry leaders. * Future Opportunities: Top performers may be invited to advanced EGATE programs or internships. For inquiries visit https://egate.et . Apply now, including your 3-minute video, to unlock your potential and shape Ethiopia’s future in science and technology! መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
155👍 6😁 2🔥 1🥰 1👏 1
ለወጣት ፈጠራ ባለሞያዎች የቀረበ የስልጠና ጥሪ! (19/12/2017 ዓ.ም) በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ባለ ተሰጥኦና ተውህቦ ማበልጸግ ትምህርት ቤት የአጭር ጊዜ የሥልጠና መርሃ ግብሮች በተለያዩ ዘርፎች አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል። 👉 የስልጠና ዘርፎቹ 🌐 ዲጂታል እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ 🤖 ሮቦቲክስ እና ኤሌክትሮኒክስ 🛰 አስትሮኖሚ እና የጠፈር ቴክኖሎጂ 🧬 ባዮቴክኖሎጂ 🔬 ስቴም 👉 ስልጠናውን ለመውሰድ ማን ማመልከት ይችላል? ✔️ እድሜ 15-21 ✔️ በሳይንስ ወይም በፈጠራ ሀሳቦች የተሻለ አፈጻጸም ያለው ✔️ ሃሳባቸውን ለመግለጽ የ3 ደቂቃ ቪዲዮ ማስገባት የሚችል 👉 ምዝገባው የሚጠናቀቀው፡ ጷግሜ 2/2017/ ሴፕቴምበር 7፣ 2025 👉 የምዝገባው ሊንክ 👉 https://egate.et ነው። 👉 በስልጠናው ዙርያ ለጥያቄዎች ካሏችው፡- 📞 +251 925 518 888 📧 mesay.hallemariam@mint.gov.et ተሰጥኦና ተውህቦን ማበልጸግ የነገውን ትውልድ በመቅረጽ ውስጥ የማይተካ ድርሻ አለው!
Hammasini ko'rsatish...
51
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያስተላለፉት መልእክት የኢትዮጵያ ማንሠራራት ጅማሮ፤ የደም ጠብታ የላብ ጠብታ የዕንባ ጠብታ የውኃ ጠብታ ድምር ውጤት መሆኑን፣ ይህ ግድብ ህያው ምልክት ሆኖ ለትውልድ ሲመሰክር ይኖራል።
Hammasini ko'rsatish...
85👍 22🤔 2
የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡ (19/12/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በፕብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የአውት ሶርስ ልማት ድጋፍና ቁጥጥር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኢሳያስ ግርማ በጥልቀት ማሰብ/Critical thinking/ ላይ መሰረት ያደረገ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በጥልቀት ማሰብ/Critical thinking/ ለመማር ለማወቅና ለመመራመር ለምን ብሎ መጠየቅን ባህል እንድናደርግ የቀረበው ሰነድ የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰው በጥልቀት ማሰብን ለማዳበር ጥረት በማድረግ ሂደት ውስጥ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን ማለትም የአስተዳደግ ፣ የባህል ፣ የሀይማኖት ፣ የቤተሰብ ፣ የልምድና የስሜታዊነትን ጉዳዮች ማጤን ይገባል ብለዋል፡፡ ሀላፊ አክለዉም ተማሪዎች በክፈል ውስጥ ከመምህራን ጋር በሚኖራቸው የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ እንዲጠይቁ እንዲመራመሩ በማድረግ በጥልቀት ማሰብ እንዲችሉ በመለማመድ አቅማቸዉን እንዲያዳብሩ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
107👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ YAA’II BARNOOTAA 32FFAA SADARKAA MAGAALAA (18/12/2017 ዓ.ም) በዕውቀትና በክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን! DHALOOTA BEEKUMSAAFI DANDEETTIIN GAHOOME HORACHUUDHAAN ITIYOOPHIYAA BIYYA FAKKEENYAA NITAASIFNA! መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
131👍 29🤮 9🔥 5👏 3
Hammasini ko'rsatish...
13
ማስታወቂያ! Beeksisa! (17/12/2017 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
123👍 54👎 15🤨 10👀 6👏 3🔥 2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው እለት አካሂደናል:: (16/12/2017 ዓ.ም) ካቢኔው በዛሬው ውሎው በቀረቡ ሁለት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚህ መሰረት፡- 1ኛ :-በኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ውስጥ የመንግስትና የግል አጋርነት ጽ /ቤት የተፈረመውን ስምምነት ለሚለሙ 30 ፕሮጀክቶች ከ733 ቢሊዬን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ እና 27 አልሚዎችን የሚያካትት በመሆኑ ፤ ልማቱን ዉጤታማ ለማድረግ ካቢኔዉ መርምሮ እንዲያፀድቅ የቀረበለት አጀንዳ በመወያየት ፣ካላቸው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ፣ የሚፈጥሩት ሰፊ የስራ እድል እና ከተማን ትብብር የማልማት ትልቅ ፋይዳ እና አዲስ አሰራር በመሆኑ ከቢኔው በቀረበ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አፆድቋል፡፡ 2ኛ :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችን የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ አፈፃፀም ደንብ በተመለከተ በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ጥራት ያለው ሥልጠና ለመስጠት፣ ኮሌጆቿን ውጤታማ ከማድረግ እና በተደራጀ አግባብ ለመምራት በሚያስችል መልኩ የደንቡ መውጣት እገዛው የጎላ በመሆኑ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
Hammasini ko'rsatish...
159👍 29👎 8🥰 4😁 4😇 1