2025 yil raqamlarda

68 961
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-137 kunlar
-96730 kunlar
Postlar arxiv
Repost from TgId: 1163708603
ክቡር ሰው - ካንት
ምንጭ ፦ ፍልስፍና ከዘርዓያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ፀሀፊ ፦ ፍሉይ አለም
ከጓደኞችህ ጋር እራት እየበላህ፣ አንዱ ተስተናጋጅ ከመጠን በላይ እያጨበጨበ አስተናባሪውን ይጣራል “እዚህ ጋር አንድ ምግብ፡፡” አንዳንድ ሰውም በሰላም ላደረሰው ሾፌር “እንዴት ነህ፣ ቻው ወይም አመሰግናለሁ” ሳይል ከታክሲ ወርዶ ወደ ጉዳዩ ያቀናል፡፡ ወንጀለኞች ህጻናትን ሰርቀው እንደ እቃ ይሸጣሉ፡፡ መንግስትም አገሩን ከዳ ብሎ ያስበውን ግለሰብ ያስገድላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች በጋራ የያዙት ነገር ምን አለ?
ኢማኑኤል ካንት አስተናጋጁን የሚያመናጭቀው ጓደኛህም፣ ለሾፌሩ ግድ የሌለው ተሳፋሪም፣ ልጆች የሚጠልፉ ወንጀለኞችም፣ አስገዳዩ መንግስትም... ሁሉም የሰውን ልጅ አግባብ ባልሆነ ሁኔታ አስተናግደዋል ይለናል።
ካንት በምክንያታዊነት ላይ ባለው የጸና አቋም በእጅጉ ይታወቃል። ለእርሱ ምክንያታዊነት ከሁሉ የላቀ ንብረታችን እንደሆነ ነው የሚነግረን። ከዚህም በላይ ምክንያታዊነት ምን ልክ ምን ስህተት ምን ኃጢአት ምን ጽድቅ እንደሆነ ይለይልናል፡፡
ካንት የሞራል ህግጋት አይለወጤ እና የጸኑ ናቸው ብሎ ያስባል። የሚደረስባቸውም በምክንያት እና ምክንያታዊነት ብቻ ነው። ይህንንም ምክንያታዊ ግብረገብነትንም ለማስረዳት ካንት ባለ ብዙ ገፅ መጽሐፎችን አሳትሟል።
ካንት ሁሉም ሰው ሊነካ የማይገባው
ክብር አለው ይለናል። እናም የሁላችንም ድርጊቶች ይህን ክብር የጠበቁ ሊሆኑ ይገባል። በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ብንሆንም የሰውን ክብር መንካት የለብንም፡፡ ሰዎች የምንገለገልባቸው ቁሳዊ መሳሪያዎች አይደሉም፡፡ ሁሉም የራሳቸው ዋጋ አላቸው። ለሁሉም ሰው ግድ ሊኖረን ይገባል።
ሁላችንም እንደ ግለሰብ ዋጋ እንዳለን እናስባለን፡፡ ዓለም የግለሰቦች ጥርቅም ናትና ለራሳችን የምንሰጠውን ዋጋ ለሁሉም ሰው መስጠት የተገባ ነው፡፡ እኛ ምንም አይነት ጥያቄ እና ምክንያት ሳንደረድር፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለራሳችን ከፍ ያለ ዋጋን ከሰጠን፣ እንደ ማህበርም ለሌሎች ሰዎች ዋጋ ሊኖረን ይገባል።
አዎ በማህበረሰብ ውስጥ አንደኛው ተገልጋይ፣ ሌላኛው አገልጋይ ሊሆን የተገባ ነው፤ ሆኖም በዚህ ሂደት ውስጥ ሰዎችን እንደ ሰውነታቸው ልናከብራቸው የተገባ ነው፡፡ አስተናጋጁም፣ የታክሲ ሹፌሩም ሆነ ሀገር ከዳተኛው ሰው ናቸው። ሁሉም ለራሳቸው ዋጋን ይሰጣሉ፡፡ ካንት ከእርሱ በኑሮ ደረጃ ዝቅ ያሉትን አገልጋዮቹን በታላቅ ክብር ይመለከታቸው ነበር፡፡
በቀጣይም ሰውን እንዴት ማዋራት እንዳለብህ ስታስብ ይህን “እንደ ሰው እያከበርኳቸው ነው ወይንስ እንደ መሳሪያ እየተጠቀምኩባቸው?” ይህም ቀላል እና ሊተገበር የሚገባው ግብረገባዊ ህግ ነው፡፡
@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍 50❤ 11😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
ዳኛው የክስተቱን ዝርዝር ሁኔታ ከሰማ በኋላ ልጁን እንዲህ ሲል ጠየቀው።
"በእርግጥ የሆነ ነገር ሰረቅክ? ዳቦና አይብ ሰርቀህ መደርደሪያ ሰባበርክ?"
ልጁም አንገቱን ደፍቶ በአፍረት መለሰ፡-
አዎ.
ዳኛ፡ "ለምን ሰረቅክ?"
ታዲጊው ልጅ: በጣም ፈልጌው ነው
ዳኛ፡ ከመስረቅ ይልቅ መግዛት አልቻልክም ነበር?
ልጅ፡ ምንም ገንዘብ አልነበረኝም።
ዳኛ፡ ወላጆችህን ገንዘብ ልትጠይቅ ትችላለህ።
ልጅ፡ እኔ ያለኝ፣ አልጋ ላይ የተኛች እና ስራ የሌላት የታመመች እናቴን ብቻ ነው... ለሷ ስል ዳቦና አይብ ሰርቄያለሁ።
ዳኛ፡ እና አንተ... ምን እየሰራህ ነው? ሥራ የለህም?
ልጅ፡- የመኪና ማጠቢያ ሆኜ እሰራ ነበር። እናቴን ለመርዳት አንድ ቀን ዕረፍት ወሰድኩ፣ ለዚህም ነው ያባረሩኝ።
ከልጁ ጋር የነበረው ውይይት ካለቀ በኋላ ዳኛው ፍርዱን አስታወቁ፡-
“ሌብነት በተለይም ዳቦ መስረቅ በጣም አሳፋሪ ወንጀል ነው።
ለዚህ የስርቆት ወንጀል ሁላችንም ተጠያቂ ነን። ለዚህ የስርቆት ወንጀል ዛሬ እኔ ራሴን ጨምሮ እዚህ ክፍል ውስጥ የተገኘ ሁሉ ተጠያቂ ነው” አለ።
በመቀጠልም ሁሉም ተሰብሳቢዎች አሥር ዶላር ይቀጣሉ እና ማንም ሰው 10 ዶላር ሳይከፍል ከአዳራሹ አይወጣም.
ዳኛው ከኪሱ የ10 ዶላር ቢል አንሥቶ እስክሪብቶ አወጣና እንዲህ ብሎ መጻፍ ጀመረ።
"በተጨማሪም የተራበውን ልጅ ለፖሊስ ያደረሰው ሱቅ ባለቤት 1,000 ዶላር እንዲቀጣ አዝዣለሁ እና ቅጣቱ በአንድ ሰዓት ውስጥ ካልተከፈለ ሱቁ ተዘግቶ ይቆያል."
በአዳራሹ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ለልጁ ይቅርታ ጠይቀው ሙሉ ገንዘቡን ሰጡት። ዳኛው እንባውን ለመደበቅ እየሞከረ ከችሎቱ ወጣ።
ተሰብሳቢዎቹ የዳኛውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ ዓይናቸው በእንባ ተሞላ።
ዳኛው አክለውም “አንድ ሰው ዳቦ ሲሰርቅ ከተያዘ መላው የዚች ሀገር ህዝብና ህብረተሰብ ሊያፍር ይገባል” ሲሉም አክለዋል።
👍 152❤ 38🙏 3🤔 2
ሰውየው እስራኤላዊ ነው:: የታሪክ ተመራማሪ ነው:: ፕሮፌሰር ነው:: እዛው እስራኤል አገር University of Jerusalem ውስጥ የታሪክ መምህርም ነው:: One of the Brightest Mind on Planet Earth ይሉታል ምዕራባዊያኖች:: ሦስት ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚባሉ ሳይንሳዊ መፅሐፎችን ፅፏል::
ፕሮፌሰር Yuval Noah Harari
የዚህ ፕሮፌሰር የመጀመርያው Non-Fiction መፅሐፍ 'Sapiens: A Brief History of Humankind' ይባላል:: ፕሮፌሰሩ በዚህ መፅሐፉ የሰውን ልጅ [ዘረ-ሰብ] በታሪክ ውስጥ ያለፈበትን ረዥም ጉዞ ያስቃኘናል:: የሰው ልጅ ካልሰለጠነበት ዘመን የእንጨት ጦር ከመወርወር እስከ ተመዘግዛጊ ኒውክለር ሚሳኤሎች እስከማስወንጨፍ የሄደበትን ጉዞ ያትታል:: የሰው ልጅ ከጥንታዊ አደንና ቃርሚያ ህይወት እስከ ዘመናችን የካፒታል ስርዓት ያደረገውን ጉዞ ይዳስሳል::
ሁለተኛው Non-Fiction መፅሐፉ "Homo Deus: A Brief History of Tomorrow" ይባላል:: ፕሮፌሰሩ በዚህኛው መፅሐፉ ደግሞ የሚነግረን ስለ ሰው ልጅ የወደፊት ታሪክ ነው:: ዘመናዊው እና ዲጂታሉ ዓለም ሰብአዊነትን እንዴት እንደሚለውጥ ይተነብያል:: አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የሰውን ልጅ የበላይነት ቀምቶ አለምን በቁጥጥሩ ስር እንደሚያውል ፣ እንደ ባዮ-ቴክኖሎጂ እና ጄኔቲክ ኤንጂነሪንግ ያሉ የቴክኖሎጂ ዕድገቶች ሊያስከትሉ ስለሚችሉት ውጤቶችም ይጠነቁላል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም በ2050ዓ.ም ሰዎች ሞትን ያሸንፋሉ:: ገንዘብ ያለው ማንኛውም ሰው ወደ ሆስፒታል እየሄደ ዕድሜውን ቻርጅ እያስደረገ እስኪሰለቸው ዘላለማዊ ሆኖ መኖር ይችላል:: ኢ-መዋዕቲ ነፍስ ይኖራቸዋል ይላል:: [ Humans are Essentially Algorithm, and the focus shifts from individual experiences and subjective values to objective data and accumulation of knowledge ]
ሦስተኛው መፅለፉ ደግሞ "21 Lessons For the 21st Century" የሚል ነው:: በዚህ መፅሐፉ ደግሞ ፕሮፌሰሩ የሚነግረን የአሁኑ ዘመን ሰው ስለተደቀነበት ተግዳሮቶች እና መከራ ነው:: በዲጂታል ቴክኖሎጂ ፕላትፎርሞች Facebook, Twitter, Instagram, Tik Tok, Youtube ወዘተ የውሸት ዜናዎችና የተሳሳቱ መረጃዎች ይስፋፋሉ ሃገሮች እርስ በእርስ የሳይበር ጥቃት ይከፋፈታሉ:: [ በነገራችን ላይ ከዚህ በኋላ በጦር መሳርያ የሚካሄድ ጦርነት እንዳትጠብቁ ሁሉም ጦርነቶች ሁሉ የሚደረጉት በዲጂታል ነው):: ሌላው የተራቀቁ ማሽኖችና ሶፍትዌሮች እና የኮምፒውተር አልጎሪዝሞቾ በቅርቡ የሰዎን ልጅ አብዛኛውን ዘርፍ ይቆጣጠራሉ:: የቨርችዋል አለም ግዙፋን ካምፓኒዎች - የአንተን ማንነት ለሚፈልጉ ካምፓኒዎች መረጃህን ይሸጡታል:: በአጭሩ እኛ የሰው ልጆች በቀደመው 20ኛው ክፍለ ዘመን የፈጠርነውን የአኗኗር ፣ የአሰራር እና የመንግስት አስተዳደር ስርዓት ይዘን የገባንበትን 21ኛው ክፍለ ዘመንን መሻገር እንደማንችል አስረግጦ ይነግረናል::
ታዲያ ይሄ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር እና የአለማችን ባለብሩህ አዕምሮ የተባለው ሰው ከሰሞኑን The Late Show with Stephen Colbert እና Jimmy Kimmel Live ሾዎችን ጨምሮ በተለያዩ የሚዲያ መድረኮች ላይ እየቀረበ እንደ መጥመቁ ዮሐንስ ብቻውን ከፊታችን ስለሚመጣው ክስተት እየጮኸ እየለፈፈ ነው::
ለምን? ምንስ ብሎ?
We are very near the end of our species because AI is a weapon of mass destruction to Humanity...የሰው ልጅ በታሪክ ሂደት ውስጥ ብዙ አጋዥ ቁሶችን ፣ መገልገያ ማሽኖችን በእጁ ሰርቷል ነገር ግን እነዚህ በሰው ልጅ የተሰሩ ነገሮችን ከድንጋይ ቢላ እስከ አቶሚክ ቦንብ ድረስ ብንመለከት በእኛ ቁጥጥር ስር ያሉ ናቸው እንዴት እና በምን አይነት ሁኔታ መጠቀም እንዳለብን የምንወስነው እኛ ሰዎች ብቻ ነን:: እንጂ እነዚህ ነገሮች በፍፁም በራሳቸው ውሳኔ ማሳለፍ አይችሉም ፣ አዲስ ሐሳብም መፍጠር አይችሉም::
ለምሳሌ የሰው ልጅ አቶሚክ ቦምብን ሰራ ነገር ግን ቦምቡ በራሱ ልፈንዳ ብሎ አይወስንም እኛ የት? እና መቼ? የሚለውን ነገር ካልወሰንን በስተቀር:: በተጨማሪም የሰው ልጅ ፕሪንተር ሜሽን ሰርቷል ነገር ግን ይሄ ፕሪንተር ሜሽን ፕሪንት የሚያደርገው እኛ የሰጠነውን ፅሁፍ ነው:: የእኛን ሃሳብ ነው እንጂ በራሱ አንድ ነጠላ ፊደል እንኳ ፅፎ ማተም አይችልም እኛ ካላዘዝነው::
በአጠቃላይ የሰው ልጅ ከዚህ በፊት የሰራቸው ቁሶች እና ሜሽኖች በእኛ ውሳኔ የሚመሩ እና የእኛን ሃሳብ የሚያስተጋቡ ነበሩ:: አሁን ግን ይሄ ሁሉ ነገር በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ በአደገኛ ሁኔታ ተለውጧል:: ምክንያቱም በራሳቸው ውሳኔ ማሳለፍ የሚችሉ ፣ አዲስ ሃሳብ የሚፈጥሩ እና ከሁኔታዎች ጋር ራሳቸውን በፍጥነት የሚያላምዱ እንደ ሰው ማሰብ የሚችሉ ንቃተ-ህሊና ያላቸው Artificial General Intelligence (AGI) ስለተፈጠረ:: ብሏል:: ይሄም ከፍተኛ እንደሰው የማሰብ ፣ የመረዳት አቅም ያለው ሰው ሰራሽ አስተውሎት በጣም እጅግ በጣም በቅርብ ጊዜ ውስጥ Exist ማድረጉ አይቀርም:: በጣም አስጊ ነው:: ብሎም አክሏል::
Of Course
ዋና መቀመጫውን San Francisco, California, USA ያደረገውና December 2015 የተቋቋመው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር ተቋም ወይም 'OpenAI' በበኩሉ የመጨረሻ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር ግብ የሆነውን ከፍተኛ ሰው ሰራሽ የማሰብ አቅም ያለውን ሮቦት ወይም AGI Achieved አድርጊያለው ብሏል:: የዚህ ተቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ Sam Altman ስዊዘርላንድ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ባዘጋጀው ወይይት ላይ ተገኝቶ
"ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ ያለው ሮቦት ወይም AGI በጣም ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ በአስደናቂ ሁኔታ አለምን ይቀይረዋል" ብሏል:: እነዚህ AGI በተቆጡ ጊዜ የሰው ልጅ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያደርሱና የሰው ልጅም በቀላሉ ታግሎ እንዲጥላቸው ከቀላል ማቴሪያል የተሰሩ ናቸውም:: ብለዋል የግብር አጋራቸው እነ ኤለን መስክ በበኩላቸው::
እውነት ግን እንደ ፕሮፌሰር ዮቫል ኖህ ሃራሪ ስጋት የሰው ልጅ በተፈጥሮ እና በሌሎች ፍጥረት ላይ የተሰጠውን የመሰልጠን እና የበላይነት ስልጣን በእነዚህ ሰው ሰራሽ አስተውህሎቶች ይነጠቅ ይሆን??
እኔ እንጃ እስኪ አብረን የምናየው ይሆናል በመጨረሻም በ1999 ለዕይታ በበቃው ሳይንሳዊ ልቦለድ ዘውግ ባለው 'The Matrix' ከተሰኘው ፊልም ላይ በተዘገነ ቃለ-ተውኔት (Dialogue) ልሰናበት::
"We marveled at our own magnificence as we gave birth to AI.....Singular consciousness that spawned an entire machine"
ከእንግዲህ 'I'm Not A Robot' ብለን የምንሞላው የCaptcha ቦክስም አይኖርም ማለት ነው:: Let's Strive For Peace on Earth 🙏
© YOAKIN BEKELE
👍 61❤ 15🔥 10😢 9🤔 2🙏 1
ልጆቻችሁን ሸጣችሁ ምን ገዛችሁ?
(አሌክስ አብርሃም)
ብዙ ወላጆችን እያየሁ እና እየሰማሁ ልቤ ያዝናል! በተለይ ልጆች ላላችሁ ሰዎች ከልቤ ይህን እላለሁ! በዚች ምድር ላይ ለልጆቻችሁ ከእናተ ውጭ ከልቡ ፍቅር የሚሰጣቸው፣ የሚያወሩት ጠቀመም አልጠቀመም የሚያዳምጣቸው፣ ከልቡ የሚያቅፉቸው፣ የሚስማቸው ፣ ሲያዝኑ መንፈሳቸውን ከፍ የሚያደርግላቸው ፣የሚያጫውታቸው ፣ከዳዴ እስከአዋቂነት ፣ ከዓለማዊ እስከመንፈሳዊው ጉዞ መንገድ የሚመራቸው ፣ የሚያስተምራቸው፣ ከዚህ ክፉ ዓለም በፍቅር እና እንክብካቤ የሚጋርዳቸው ከወላጅ ውጭ ሌላ ሰው የለም! ወላጅ ከሆንክ ከሆንሽ እናንተ ብቻ ናችሁ ለልጆቻችሁ ያላችኋቸው! ወላ ዘመድ ወላ አስተማሪ ከእናንተ ቀጥሎ ነው! መቸም ደግሞ የእናተን ሚና አይተኩም!
በተለይ አባቶች!...(በእናንተ ስለሚብስ) በሜካፕና በ"ላይት" ተብረቅርቀው ራሳቸውን ለገበያ የቀረቡ ሴቶችን የማይረባ ወሬና የወሲብ ስሜት የሚያነሳሳ ዳንስ ፣ ራቁትነት፣ ብልግና ፣ ቆሻሻ ጆክና ሀሜት ፣ ጥቅም የሌለው ጫጫታ ወይም ይሄን የሻገተ ፖለቲካ ለማየት ቲክቶክ፣ ዮቲዮብ፣ ፌስቡክ ወዘተ ላይ ቀን ከሌት አፍጥጠህ ስትገለፍጥና ስትቋምጥ ውለህ የምታድር አባት ...የምትከፍለው ተራ ካርድ ወይም የኢንተርኔት ሂሳብ ብቻ እንዳይመስልህ! የልጆችህን ጊዜ ከፍለህ ቆሻሻ ትገዛለህ! ዱቄት በአመድ ትለውጣለህ!
እነዚህ ሚሊየን ተመልካች ያላቸው ከንቱዎች ለመመልከት ከአንተ ሌላ ተመልካች የሌላቸው ልጆችህን ፊት ትነሳለህ! ፍቅር ትነሳለህ (እንደዛፍ ውሃ እያጠጣህ ስለተውካቸው ልጆች አደጉ አይባልም) ለልጆችህ እያንዳንዷ ሰዓት እያንዳንዷ ደይቃ የነገ እጣፈንታቸው ናት! በየደይቃው በየቅፅበቱ ነው ልጆች በአካልም በመንፈስም የሚሰሩት! የረሳሀቸው ልጆችህ መረሳት የሚያመጣው የበታችነት ህመም ተጠቂ ይሆናሉ! ጊዚያቸውን ስትነጥቃቸው ከወላጅ ሊያገኙ የሚገባውን መብትና ፍቅር ትነጥቃቸዋለህ! ዛሬ የራካቸው ልጆች ነገ ይርቁሃል! ነገ በጣም ቅርብ ነው! ከስልክህ ቀና ስትል አድገው ታገኛቸዋለህ! ውድ ጊዜህን እንቅልፍህን ሰላምህን ሰጥተህ ስልክህ ላይ ለምታያቸው ከነመኖርህ እንኳን ለማያውቁህ የሶሻል ሚዲያ ርካሽ ነጋዴዎች ስትል ከአንተ ሌላ ማንም የሌላቸውን ልጆችህን ቤተሰብህን ትሸጣለህ! "ሊትራሊ" ልጆችህን ሽጠህ ነው የሆነች ቦዘኔ መቀመጫዋን ስታወዛውዝ ለማየት በጊዜህ የምትገዛው፤በሆነ ሰው ቀልድ የምትገለፍጠው! በየቤታችሁ ያስገባችሁት ኢንተርኔት አጠቃቀሙ በወግ ካልተቃኘ ልጆቻችሁን ደርድራችሁ በርካሽ የምትሸጡበት ጉሊት ነው የሚሆነው!
እስኪ ወላጆች ራሳችሁን ታዘቡ! ለቲክቶክ የምትሰጡትን ጊዜ ለልጆቻችሁ እየሰጣችሁ ነው? ወይስ ወደዛ ዝም እንዲሉ ቲቪ ወይ የሆነ ነገር ሰጥታችሁ ስልካችሁ ላይ ናችሁ? ለትዳር አጋሮቻችሁስ? ለወላጆቻችሁስ? ከቲክቶክ ፌስቡክ ምናምን ፋታ ብትውስዱ እንኳ አዕምሯችሁ የተሞላው በትርኪ ምርኪ ነውና ለልጆቻችሁ የምትሰጡት ደህና ሃሳብ እንኳን የላችሁም! ስምህ የልጅህን ስም እየተከተለ እንደውሻ ስለጮኸ አባትነትህ ሙሉ ሆነ ማለት አይደለም! ያለህን ጊዜ ሁሉ ለቤተሰብህ ስጥ ፤የተረፉህን ልቅቃሚ ደይቃዎች ወደሶሻል ሚዲያው ወርውር! በቂ ነው! ልጅህን ቤተሰብህን ሸጠህ ቆሻሻ አትግዛ! በፈጠረህ ለሌሎች የላይክና ቪው ቁጥር ከመሆን ለቤተሰብህ አለኝታ ሁን! ባልታደለች አገር ተፈጥረው ያጡት ስፍር ቁጥር የሌለው ነገር ሳያንስ አንተም ተጨምረህ ልጆችህን የቲም አታድርጋቸው! ቆም ብለህ አስብ ከቤተሰቤ የነጠኩትን ጊዜ ምን ገዛሁበት በል? ምን ገዛህበት? አንችም እናት የሆንሽ እንደዛው!
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
👍 87❤ 31😢 6
ታላላቅ ጥቅሶችና ምክሮች
1.ትልቅ ሰውነት በዘር ወይም በትውልድ ሳይሆን በተግባራዊ ስራና በህይወት ፈተና ውስጥ ነጥሮ የሚወጣ ነው።
2.ከይስሙላ አንድነት ፣በእምነት ካልተዋቀረ ህብረት፣ በግርግር ከተሞላ መንጋነት ይልቅ ጥርት ያለ ልዩነት ለመፍትሄ ያበቃል።
3.በእውቀት ተመራምሮ አዲስ ነገር ማግኘት ለሰው ልጅ የስልጣኔ መጥረጊያ መንገድ ከፋች ሲሆን የሀሰት ወሬ መፍጠር ግን የዝቅጠት መንገድ ነው።
4.ከሚጎትቱንና ከሚያደናቅፉን አሮጌ ችግሮች መውጣት ያሻናል፣አሮጌ ባላንጣዎቻችን በትላንት አባዚያችን ውስጥ እንድነቅዝ እንደሚሹ ማስተዋል አለብን።
5.ዋና ቀጣፊ ሰው ራሱን የሚያታልል ነው።
6.ገደልን የዘለለ ፈረስና ቂምን የተወ ሰው አዋቂ ነው።
7.የሚፈልገውን ያላገኘ ልብ ዘውትር መንገደኛ ነው።
8.ያለውን የማያውቅ የጎደለውን አያውቅም።
9.ጭንቀትህን በስራ ተካውና ተአምር ሲፈጠር ተመልከት።
10.ክፋት የአእምሮ በሽታ ሲሆን ቅንነት ግን የህሊና እረፍት ነው።
11.ሌሎችን ለመምሰል እንደሚመኝ ሰው ጭንቀት የበዛበት ሰው የለም።
12.ፍቅር የከንፈር ወይም የገንዘብ መገጣጠም ሳይሆን የልብ መገጣጠም ነው።
13.ቆንጮ ሴት ባየህ ጊዜ ተፈጥሮን አድንቅ እንጂ የዝሙት መንፈስ አይሰማህ። ዝሙት ከደካማ መንፈስ የሚመነጭ ነው።
14.ብዙ የሚናገሩ ሰዎች የማሰቢያ ጊዜ የላቸውም።
15.የማያውቀውን ነገር ያልተናገረ ጥበበኛ ነው።
16.ፍቅር በድንገት መጥቶ እንደሚያልፍ ጎርፍ ሳይሆን ጠልፎ የማያሰጥም የውቅያኖስ ማዕበል ነው።
17."ቅናት" ፍቅር እና ትዳርን ገዝግዞ የሚጥል ስለት ነው።
18.ሴቶች ጆሮዋቸውን ወንዶች አይናቸውን ያምናሉ።
19.ፍቅር የተፈጥሮ ሁለተኛ ፀሀይ ነው።
20.በፍቅር የተሞላች ቃል የወደቀን ሰው ታነሳለች።
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
👍 72❤ 20😢 1
ስናዳሪ ማለት
"ስናዳሪ ማለት ሳይወለድ የሞተ፣ በስህተት ቢወለድ እንኩዋን የህዝብን ነጻነት ሸጦ፣ የሀገርን ውድመትና የህዝብን እልቂት በባልሰማ ሸምጥጦ፣ እና በእምነቱ ላይ አላግጦ የራሱን ተዝካር በመንግስት እያስደገሰ የሚበላ ሰባዊ አሳማ ነው፡፡"
ለሆዱ ያደረ ሰው ስጋው በህሊናው ላይ ትነግሳለች። ለስጋው ንግስና ስኬት ነባር አላማውን በውራጅ፣ ነፍሱን በሀራጅ ይሸጣል።"
ስናዳሪ ምን ቢማር ምን ቢመራመር ከእውነት ተርታ እና ከፍትህ ከፍታ ስትፈልገው ብትውል ልታገኘው አትችልም። ለምን ? ቢባል አድራሻው ከሆዱ ስር ነውና።"
👍 48❤ 6🙏 3
አንዳንዴ . . . ያለ ነው!
አንዳንድ ጊዜ ማመንታት ያለ ነው - በፍጹም ግን ወደ ኋላ አንመለስም!
አንዳንድ ጊዜ መፍራት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንንበረከክም!
አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ያለ ነው - በፍጹም ግን አናቆምም!
አንዳንድ ጊዜ መሸነፍ ያለ ነው - በፍጹም ግን ሕይወት ከሚያቀብለን የየእለት ጦርነት አንሸሽም!
አንዳንድ ጊዜ መድከም ያለ ነው - በፍጹም ግን ዝለን አንወድቅም!
አንዳንድ ጊዜ ግራ መጋባት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንቅበዘበዘም!
አንዳንድ ጊዜ በሰው መገፋት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከዚያ ሰው ውጪ መኖር አየቅተንም!
አንዳንድ ጊዜ ድብርት ያለ ነው - በፍጹም ግን ደንዝዘን አንቀርም!
አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄ መልስ ያለማግኘት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከመጠየቅ አናርፍም!
አንዳንድ ጊዜ ክፋት ያሸነፈ መምሰሉ ያለ ነው - በፍጹም ግን መልካምነትን አንጥልም!
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
❤ 28👍 18👏 4🔥 3
Repost from TgId: 1163708603
“ጅል አይሙት እንዲያጫውት!”
ከአሌክስ አብርሀም
መፅሀፍ-አልተዘዋወረችም
በአገራችን ባህል የዝምታ ትርጉም ግራ የገባው ነው፡፡ እውነት በአደባባይ ሲደፈጠጥ እያዩ አፍን መሸበብ፤ ግን ደግሞ በስሚ ስሚ ለመጣ አሉባልታ ነፍስን ጭምር መስጠት። ጮኾ የማያወራ፣ ሐሳቡን የማይገልጽ ሕዝብ የሐሜት ጫካ ነው። በየጋራና ሸንተረሩ ጥይት ከማስጮኸ የበለጠ፣ ጮኽ ብሎ ያመኑበትን መናገር የሚከብደው ሕዝብ ጀግንነቱ ከባድ ጥያቄ ውስጥ ነው፡፡ በዝም አይነቅዝም ብሒል የነቀዘ ሕይወት እንመራ ዘንድ የፈቀድን ሕዝቦች መሆናችን ሳያንስ ይኽንንም ባህል አድርገን ልንኮራበት ይዳዳናል፡፡
ይኼ ተወልጄ ያደግሁበት ሕዝብ በሹክሹክታ ያወራል፣ ጓዳ ለጓዳ ያወራል፣ እውነት ይሁን ውሸት አግበስብሶ ያወራል፣ እንደ ወረርሽኝ ወሬ በብርሃን ፍጥነት ያዛምታል፣ በአደባባይ ግን ዝምተኛን ያደንቃል- ያበረታታል፡፡ በተረቱ “ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም” እያለ ዝንብ ፈርቶ ዝም (እንዴት _ ለዝንብ ዝም ይባላል? ለምን ሰፈራችሁን አጽድታችሁ እንደልባችሁ አታወሩም? የሚል የማሪያም ጠላት ነው!) መንግሥትን ፈርቶ ዝም (እንዴት ዝም በሉ ለሚል መንግሥት ዝም ይባላል አፋኝ መንግሥት እጁን ከአፋችን ላይ እንዲያነሳ መንገር የለብንም ወይ? የሚል የአገር ጠላት ነው) ይሉኝታን ፈርቶ ዝም (እንዴት በይሉኝታ እንለቅ? ብንል የባህል ጠላት መባል ይመጣል፡፡)
ሁሉም ስሕተትና ፍርኃታችን እንደ ትልቅ ሐብት በእሳት ሰይፍ ተከቦ የሚጠበቅ ቅርስ ነው፤ እውነት ብቻ ነው ራቁት፡፡ ለዚያም ሳይሆን አይቀርም እውነት የእብዶችና ሰካራሞች ልፈፋ ተደርጋ በየመድረኩ የምትሳለው፡፡ እብዶች እውነቱን እንዲናገሩለት “ጤነኛው' ከፍሎ ይታደማል፡፡ ይኼ ባህላችን ሲሆን ከያኒ የነፍሱን ጥሪ ጥሎ የጅሎች አፈቀላጤ ይሆናል፡፡ ታዲያ የዚህ ሁሉ ምክንያት ፍርኃታችን ቢሆንም፣ ይኼንንም በሰበብ ስንጀቡነው (መቼም ሰበብ አናጣ) “ዝምታችን ትዕግስት የወለደው፤ ትዕግስታችንም አምላካችንን የምንፈራ ሕዝቦች ስለሆንን የተጎናጸፍነው ጸጋ ነው” እንላለን፡፡ እውነታው ግን አምላክን መፍራታችን ሳይሆን ፍርኃትን ማምለካችን ነው።
በዚህ ሁሉ ዝምታ ውስጥ የታቀፈ ጅልነት ድርጊት ሆኖ ሲፈለፈል ከግለሰብ እስከ አገር ስንት የጨነገፈ ኑሮ ፈጠረ!? ታዲያ የራሳችን ዝምታ ተጠራቅሞ ሲከብደንና አላራምድ ሲለን፤ በየዘመኑ ጊዜና ሁኔታ እየጠበቅን በጋራ እንጮኻለን። የጨረባ ተዝካር! ይኼን ዓይነቱን ጩኸት አብዮት እንለዋለን (የታዘዙትን ሁሉ እሺ! እያሉ አብዮት አለ ወይ?!) ነገሩ ልክ ውሃ ውስጥ የተነከረ ውሻ፣ ውሃውን ከላዩ ላይ ለማራገፍ በደመነፍስ እንደሚርገፈገፈው ዓይነት ነው፤ ውሃው ቢራገፍም ውሻው ያው ውሻ ነው፡፡ አጯጯኻችን በአንድ ላይ በየአፋችን ስለሆነ ማንም ማንንም አይሰማም፤ ማንም የማይሰማው ጩኸት ደግሞ ከዝምታ እኩል ነው፡፡
ይኼ ዝምታ፣ የጅል ባንዲራ እንጂ ጨዋነት አይደለም። ባንዲራችን ከፍ ብሎ የሚውለበለበው ለዘመናት በተከመረና በደደረ ጅልነታችን ላይ ይመስለኛል፡፡ የባንዲራችንን ቀለም እየጠቀስን የማንሰጠው ትርጉም የለም። ሁሉንም ቀለም እንደ ዳማከሴ ጨቅጭቀን ብንጨምቀው ከጀግንነታችንም በፊት፣ ከኩሩነታችንም በፊት፣ከአገር ፍቅራችንም በፊት የሚንጠባጠበው ጅልነታችን ሳይሆን ይቀራል?!
እሱን እየተቀባን ስንት ጊዜ ከዘመን በሽታ ተፈወስን ብለናል?! ፈውሳችን ሐሰት ነበርና ምስክርነታችን የታተመበት ቀለም ሳይደርቅ፣ ብዙዎች በነጠላም በጅምላም የጅል በትር ሰለባ ሆነው ወደ መቃብር ወርደዋል፡፡
የተረፍነው እንዴት ተረፍን? እያልኩ ሳስብ፣ አንዳንዶች “ምሕረቱ በዝቶልን'' ቢሉም እኔ ግን ፈጣሪም ከዚህች ከኛ ምድር በተዋሰው ተረት “ጅል አይሙት እንዲያጫውት!” ብሎ ለአጫዋችነት ትቶን ይሆናል እላለሁ፡፡ አገሬ ጨዋታና ተጨዋች ይበዛታል፡፡ እንደ አገር ልጅነታችንን አልጨረስንም ይሆን? እስከምል ድረስ የአገሬ ጨዋታ ወዳድነት ያስደምመኛል፡፡
ጅልነቴ ከሕዝብ ባሕር የተቀዳ ነው ስል፣ ለጥፋቴ ሌላ የሕዝብ ክንብንብ ውስጥ መደበቄ አይደለም፤ ምንስ ቢሆን ሕዝብ የሚባለው አጀብ ለሚሊዮኖች ቢሰነጣጠር አንዱ ስንጣሪ መሆኔ አይቀር፡፡ ሕዝባዊ ጀግንነት፤ ሕዝባዊ ታሪክ እንዳለ ሁሉ ከየቤታችን አዋጥተን አገራዊ ያደረግነው ሕዝባዊ ጅልነት አለመኖሩን ማን አጥንቶ ነገረን?! ጅልነት ቀለም ነው፤ ታሪካችን እኛም በግልና በጅምላ አማርን ብለን የተቀባነው የተኳኳልነዉ ጠይም ቀለም፡፡ በዚህ ጠይምነት በኩል ስለተገለጠ ግለሰባዊ ጅልነቴ በጸጸት አወራለሁ... በጓዳዬ ለአገር ያዋጣሁት የጅልነት ድርሻ... ይኽም ከንስሓ ይቆጠር እንደሆን እንጃ፡፡
@zephilosophy
@zephilosophy
👍 53❤ 5👏 2😢 2
ጣፋጩ ገዳይ መርዝ!
በሰሜን አንታርቲካ ላይ የሚኖሩ እስኪሞ የተባሉ ጎሳዎች ተኩላ ለመግደል ሲፈልጉ የሚዘይዱት ዘዴ አለ፡፡ በበረዶ ውስጥ ጫፉ በጥቂቱ የወጣ ቢላ ይደብቃሉ፤ በላዩ ላይ ጥቂት የበግ ደምን ያደርጉበታል:: ተኩላው ደሙን አሽትቶ ይመጣል፡፡ በረዶው ላይ ያለውን ደም መላስ ይጀምራል።
ደሙ ይጣፍጠዋልና ፍጥነቱን እየጨመረ መላስ ይጀምራል፡፡ በዚህ ፍጥነት ውስጥም እያለ ሳያስበው ደም የተቀባው ቢላዋ ምላሱን ይቆርጠዋል፡፡ ነገር ግን ደም መላሱን አያቆምም፡፡ አሁን ላይ ይህ ተኩላ ባለማወቅ ከራሱ ምላስ የሚፈሰውን ደም እየላሰ ነው፣ ሆኖም ጣፍጦታል እና በፍጥነት መላሱን ይቀጥላል። ከመጠን በላይ ደምም ይፈሰዋልና በነጋታው ተኩላው ሞቶ ይገኛል። የራሱን ደም እየጠጣ እንደነበረም አልታወቀውም።
ይህ ተኩላ ከእኛ ታሪክ ጋር ይቆራኛል፡፡ ብዙዎቻችን ጊዜያችንን የምናሳልፈው በስልካችን ላይ አልያም በቴሌቪዥን ላይ ነው... ጊዜያችንን ሳንጠቀምበት እንዲሁ ያልቃል... ይጣፍጣልና፤ ጥቂት ብቻ አይበቃንም፤ በፍጥነት እና በኃይልም ህይወታችንን፣ ጊዜያችንን ልሰን እየጨረስነው ነው:: በተቻለህ መጠንም ከስራህ እና ከማሰብ ከሚያስተጓጉሉህ ነገሮች ሁሉ ለማራቅ ሞክር።
ድብቁ አእምሮ ድብቁ ኃይል
@Human_Intelligence
👍 86🔥 30❤ 7
Photo unavailableShow in Telegram
በአንድ ወቅት በአንድ ክፍል ውስጥ በሚማሩ ተማሪዎች መሃል አንዱን ጓደኛቸውን prank ሊያደርጉት ፈለጉና ከጀርባው ላይ 'I'm stupid' እኔ ደደብ ነኝ የሚል ወረቀት ለጠፉበት።
ከዚያም ጓደኞቹ በሙሉ በእሱ ላይ መሳቅ ይጀምራሉ ። ከቆይታ በኋላ ግን የሂሳብ መምህራቸው ገባ። መምህሩም እንደገባ አንድ ከባድ ጥያቄ ጥቁር ሰሌዳው ላይ በመጻፍ እንዲመልሱ ጠየቃቸው። ከዚያ ጀርባው ላይ ከተለጠፈበት በስተቀር ሌሎቹ ከብዷቸው ዝም አሉ።
በመጨረሻም ያው ልጂ ወጣና ጥያቄውን በትክክል ሰርቶ አሳያቸው። መምህሩም ከጀረባህ የተለጠፈውን ያወቅክ አትመስለኝም በማለት በእጁ እያነሳለት ወደ ክፍል ተማሪወቹ እየተመለከተ እናንተን ከመቅጣቴ በፊት ሁለት ነገር እነግርሃለሁ፥
በመጀመሪያ በሂይዎትህ ውስጥ ሰዎች አናንተን ከጉዞህ ለማስተጓጎል ብዙ ስያሜወችና ያልተገቡ ነገሮችን ይጭኑብሃል።
የክፍል ጓደኞችህ ያደረጉብህን ነገር ብታውቅ ኑሮ ከመቀመጫህ አትነሳም ነበር። በሂይዎትህ ውስጥም ማድረግ ያለብህ ነገር ሰዎች የሚሰጡህን መለያዎች ችላ ማለትና ለመማር፣ ለማደግና ለመሻሻል ጥረት ማድረግ ነው።
ሁለተኛ ስለስቲከሩ ከጀርባህ ስለተለጠፈው ነገር የሚነግርህ ታማኝ ጓደኛ እንደሌለህ ያሳያል።ነገርግን ብዙ ጓደኛ መኖሩ አይደለም ቁም ነገሩ ዋናው ለጓደኞችህ የምታጋራው ታማኝነት ነው።
ከጀርባህ የሚከላከሉልህ፣ የሚጠብቁህና ሰለ አንተ የሚጨነቁልህ ጎደኞች ከሌሉህ አንተ ብቻህን ትሻላለህ።
@Human_Intelligence
👍 104❤ 21🙏 5🔥 4👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ለፍልስፍና አፍቃሪዎች ድንቅ ቻናል
👇👇👇
@Zephilosophy
ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ
https://t.me/joinchat/RVzIu0-BTYG_XaN8
👆👆👆
በዚህ ቻናል ከተለያዪ የአለም ዳርቻዎች የተነሱ የታላላቅ ፈላስፋዎች አስተሳሰቦች እና ፍልስፍናዎች ይቀርባሉ።ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ፤ ከሰሜን እሰከ ደቡብ የአለምን የአስተሳሰብ ኮምፓስ የቀየሩ ፈላስፋዎች እና ሃሳቦቻቸው ከየመፅሀፉ እየተጨለፉ ለናንተ ይቀርባሉ። ከሶቅራጥስ እስከ ኒቼ ፤ ከቡድሃ እስከ ኦሾ ፤ ከማርክስ እስከ ሌኒን አለም ላይ የማይፋቅ አሻራዎቻቸውን ያሳረፋ ሰዎች ፤ ከክርስትና እስከ ቡዲሂዝም ፣ከእስልምና እስከ ሂንዲይዝም ፣ከሶሻሊስት እስከ ካፒታሊስት በዘመናት ውስጥ የተፈጠሩ ሀይማኖቶች ፣ስርዓቶች ርዕዮተ ዓለሞች ሁሉ ይዳሰሳሉ። ለዓለም ያስገኙት ሞራላዊና መንፈሳዊ ትሩፋቶች ይወዳሳሉ። ታሪካዊ ህፀፆቻው ደግሞ ያለምህረት ይተቻሉ ፣ይወቀሳሉ።
ፍልስፍናን ከተደበቀችበት ጓዳ አውጥተን በአደባባይ እናሰጣታለን። ማህበረሰቡ የሚሳሳላቸው ባህሎቹ እና እምነቶቹ በነፃነት ይጠየቃሉ ፣ይመረመራሉ ይፈተናሉ። እንደ ጣት ቁስል የተፈሩ እውነቶች መሀረባቸው ይገለጣል። እንደ ማህበረሰብ በጉያችን የጋረድናቸው እባጮች የግንባር ስጋ ይሆናሉ።ከግለሰብ እስከ ቡድን ፤ከሀይማኖት እስከ ርዕዮተ -ዓለም
፤ ከኋለቀር ባህሎች እስከ ዘመናዊ ስልጣኔዎች ያለምንም ፍርሃት በግላጭ ይሞገታሉ፣ ይመረመራሉ፣ይጠየቃሉ ውስጣቸው የተደበቀው እውነት እስኪገለጥ ድረስ በአውድማው ላይ መንሽ እየተፈለገ ፍሬው ከገለባ ይለያል።
መንሻችን የሰላ አምክንዮዊ አእምሮ፣ የሰከነ የሞራል ልዕልና እና ንፁህ ሰዋዊ ህሊና ናቸው።
Join
👇👇👇👇
@Zephilosophy
@Zephilosophy
👍 25❤ 2🔥 1
ለትናንት ማንነትህ ደብዳቤ ፃፍለት!
(Note to self)
(እ.ብ.ይ.)
በዓለማችን በተለያየ የሙያ ዘርፍ ላይ አንቱ የተባሉና የስኬት ጫፍ ላይ የደረሱ አብዛኞቹ ሰዎች ለራሳቸው የማስታወሻ ደብዳቤ የመፃፍ ልማድ አላቸው፡፡ ደብዳቤው አንደኛ ራሳቸውን አይዞኝ ለማለትና ለማነቃቃት ጠቅሟቸዋል፤ እንደገናም ትናንትናቸውን በጥራት እንዲያዩት አጉሊ መነፅር ሆኗቸዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ልማድ ከነበራቸው ታዋቂ ሰዎች መካከል የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር፣ ታላቋ ተዋናይትና የቲቪ ሾው አቅራቢዋ ኦፕራ ዊንፍሬይ እና ሌሎችም ተጠቃሾች ናቸው፡፡
የታዋቂ ሰዎችን የግል ማስታወሻ ደብዳቤ በመሰብሰብ በመፅሐፍ መልክ ያሳተመችው ደግሞ የሲቢኤስ ዜና (CBS News) ጋዜጠኛ የሆነችው ጋይል ኪንግ (Gayle King) ነች፡፡ መፅሐፉንም ‹‹Note to self›› በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ 2018 ዓ.ም. ወርሃ ግንቦት ላይ ለአንባብያን አቅርባለች፡፡ በዚህ መፅሐፍ ከተጠቀሱት የማስታወሻ ደብዳቤዎቹ ውስጥ ቀልቤን የሳበው የምርጧ የቴሌቪዥን ሾው አዘጋጅና የፊልም ተዋናይት የነበረችው የአሜሪካዊቷ የኦፕራ ዊንፍሬይ ደብዳቤ ነው፡ ኦፕራ ከዛሬ አስር ዓመት በፊት የወጣትነት ጊዜዋን ፎቶ እየተመለከተች ለራሷ ደብዳቤ ፅፋ ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ሆና ትናንቷን ስታስታውስ ራሷን በራሷ እንዲህ ብላታለች፡-
‹‹ውዷ ባለቡናማ ቆዳዋ ቆንጅዬዋ ሴት ሆይ...››
‹‹ቆንጆ የሚለውን ቃል ለራስሽ ተጠቅመሽ እንዳማታውቂ አውቃለው፡፡ በዓይኖችሽ ውስጥ የሕይወቴን ብርሃንና ተስፋ አይቻለሁ፡፡ የመጀመሪያውን የዜና ዘጋቢነት ስራ ስታገኚ ደስተኛ ነበርሽ፡፡ ነገር ግን ምን ያህል ትጨነቂ እንደነበርም አስታውሳለሁ፡፡ በዛን ጊዜ ላንቺ የምልሽ የነበረው ‹‹አይዞሽ! በርቺ... ሁሉም ነገር በጎ ይሆናል (Relax, It’s going to be OK)›› የሚል ነበር፡፡ ይሄን ስራ በማግኘትሽ ሞራልሽና በራስ መተማመንሽ ጨምሮ ነበር፡፡ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ርግጠኛ አልነበርሽም፡፡ ገና የ10ኛ ክፍል የሃይስኩል ተማሪ በመሆንሽ ትምህርቱንና አዲሱን ቋሚ ስራሽን እንዴት አቀናጅተሸ እንደምትመሪው ግራ ተጋብተሸ ነበር፡፡››
‹‹ከፊል የህይወት ዘመንሽን ያሳለፍሽው ሌሎች የሚፈልጉትን ለመሆንና እነሱን ለማስደሰት ነበር፡፡ ያ ነገር ለምን እንደሆነ ዛሬ እረዳሻለሁ፡፡ ገና በአፍላው እድሜሽ በዘጠኝ ዓመትሽ ተደፍረሽ፣ እስከ አስራአራት ዓመት እድሜሽ ድረስ እንወድሻለን ይሉሽ በነበሩ ዘመዶችሽና ወገኖችሽ እየተሰደብሽና እየተገፋሽ እንደኖርሽ አውቃለሁ፡፡ በስድባቸውና በንቀታቸው እንኳ የምትናደጂበትና የተቃውሞ ሃሳብ የምታሰሚበት አቅም አልነበረሽም፡፡ ጥሩ ያልሆነውን ስሜትሽን እንኳን ለመግለፅ የፈቀደልሽ የለም፡፡ ሁሉም ረጋሚሽና አውጋዥሽ ነበር፡፡ ይሄ ሁሉ ለራስሽ የሚኖርሽን ክብርና አመለካከት እንደሚንድ አውቃለሁ፡፡ አሁን ላይ ግን ብዙ ነገር ገብቶሻል፡፡ መከራውን ተሻግረሽ እዚህ ደርሰሻል፡፡ በራስሽ ልብ ራስሽን ወድደሻል፤ በገዛ ዓይኖችሽ ራስሽን አይተሻል፡፡ ሁሉን ነገር በአምላክሽ ደጋፊነት ችለሽ እዚህ ደርሰሻል፡፡ አሁን ላይ ሆኜ የህይወት ጉዞሽን ሳየው የምትፀፀቺባቸው ነገሮች ኢምንት ናቸው፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ ህይወትን ጥሩ አድርገሽ ኖረሻታል ማለት ነው፡፡ ስኬት ሂደት መሆኑንና ከታላቅ ድል በተቃራኒ መቆም አለመሆኑን ተረድተሻል፡፡ ውዴ ሆይ.. በአንቺ እንድኮራ አድርገሽኛል ....... ››
በማለት ያለፈችበትን የሕይወት ውጣውረድ መንገድ በዓይነህሊናዋ ተመልክታ በራሷ ኮርታለች፡፡
አዎ ትናንትናቸውን የተገነዘቡ አዋቂዎች፣ ዛሬአቸውን የተረዱ ብልሆች፣ ልብ ያላቸው አስተዋዮች፣ ወደውስጥ ማሰብ የሚችሉ ጥልቅ አሳቢዎች፣ ከራሳቸው ጋር መከራከርና መወቃቀስ የሚወዱ ምክንያታዊ ሰዎች ራሳቸውን በራሳቸው ለማየት ለራሳቸው ደብዳቤ ይፅፋሉ፡፡ ማስታወሻው አንድም ከትናንቱ ሕይወታቸው የሚጠቅመውን ልምምድ ለማስቀጠል፤ አንድም ካለፈው ውጣውረድ ትምህርት ለመቅሰም፤ አንድም ኋላቀር አስተሳሰባቸውን አስወግደው ወደፊት የሚያሻግራቸውን አመለካከት ለመፍጠር፤ አንድም የሚደነቀውን ማንነታቸውን ለማድነቅ ነው፡፡
ወዳጄ ሆይ.. ለትናንትናው ማንነትህ፣ ለልጅነት ሕይወትህ፣ ለትኩሱና ለወጣቱ አንተነትህ የምትጽፍለት ማስታወሻ ምንድነው? የምትናፍቀው ማንነት የለህም? የምትፀፀትበት አንተነትህ የየትኛው ዕድሜ ማንነትህ ነበር? ሕይወትን በራስህ መንገድ ኖረሃል? ራስህን ለማስደሰት ነው ወይስ ለሌሎች ደስታ ነው አቅምህን የጨረስከው? በሰው ሃሳብ ነው እድሜህን የገፋኸው? የትናንት አንተነትህን ታስታውሰዋለህ? ዛሬ ላይ ሆነህ ለትናንቱ ራስህ የምትለው ነገር የለም? እንዴት ነበር ንዴትህን የምትገልጸው? ከሀዘንህ በምን ጉልበት ነበር የምትፅናናው? ማግኘትና ማጣትን እንዴት አስተናገድካቸው? ሀዘንህን እንዴት አለፍከው? ድንገቴ ውድቀትህን በምን ተቋቋምከው? ጉርምስናህን በምን አመክንዮ ነው ያስተዳደርከው? ይዘህ የኖርከውን ሃሳብና ማንነት በማስታወሻህ አልገመገምከውም? የመጣህበት መንገድ ጎርበጥባጣ ነበር? በወፍ በረር ቅኝት ራስህን፣ ህይወትህን፣ ትናንትህን፣ ትዝታህን፣ ልጅነትህን፣ ጉርምስናህን፣ ጉልምስናህን፣ እሳቱ ጊዜህን መለስ ብለህ አይተኸዋል? እስቲ ለራስህ የማስታወሻ ደብዳቤ (Self note) ፃፍለትማ.......!
ቸር የሕሊና ማስታወሻ!
ኢትዮጵያና ኢትጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ!
_____
እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)
@Human_Intelligence
👍 58❤ 23🙏 1
የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!
ሕይወታችንን ማስመለስ ማለት በአጭሩ ሲተረጎም በአንድ ሰው፣ ሁኔታ ወይም ልምምድ ምክንያት ከደረሰብን ቀውስ የተነሳ በትክክል ማሰብ፣ መስራት፣ መተኛትም ሆነ መኖር እስከማንችል ድረስ የደረሰውን ሁኔታችንን እንደገና ወደቀድሞው ጤናማ ሁኔታ ማስመለስ ማለት ነው፡፡
• የጎዳችሁና እስክትበቀሉት ድረስ ውስጣችሁን የሚያናድደው ሰው የወሰደባችሁን ሕይወታችሁን አስመልሱ!
• ሰዎችን አምናችሁ በተወሰደባችሁ ቁሳቁስ ወይም ገንዘብ ምክንያት ዘወትር ከመቆጨታችና ከመቆዘማችሁ የተነሳ የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!
• አፍቅራችሁ ትንሽ ከተጓዛችሁ በኋላ ያ ሰው ለእናንተ ምንም ፍላጎት እንደሌለው ብትደርሱበትም ካላችሁ የስሜት ትስስር የተነሳ ልትረሱት ባልቻላችሁት ሰው የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!
• ማንኛውንም ሰውም ሆነ ሁኔታ ከመፍራታችሁ የተነሳ ወደፊት መራመድ እስከማትችሉ ድረስ በመሆናችሁ ምክንያት የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!
ወደራሳችሁ ተመለሱ! ወደቀደመው ሰላማችሁ ተመለሱ! ወደእውነተኛው ማንነታችሁ ተመለሱ! ከምንም ሁኔታና ከማንም ሰው ጫና ውጪ ወደነበራችሁበት ሚዛናዊ ሕይወት ተመለሱ!
ንቁ! ወስኑ! ምክርና እገዛን ፈልጉ! የድሮውን ጤናማ ማንነታችሁን እንደገና የራሳች አድርጉ እንጂ የሰውና የሁኔታዎች ሰለባና መጫወቻ አትሁኑ!
መልካም ቀን!
Dr eyob
👍 79❤ 30👏 2
#የተፈጥሮ_ዑደት
በተፈጥሮ ዑደት ውስጥ ድል ማድረግም ሆነ ድል መሆን የሚባሉ ነገሮች የሉም። ያለው እንቅስቃሴ ብቻ ነው:: ክረምት ከሁሉም የበላይ ሆኖ እስከመጨረሻው ለመዝለቅ ይጣጣራል:: ሆኖም ጊዜውን ጠብቆ የፀደይን ተተኪነት ከመቀበል በቀር አማራጭ አይኖረውም፡፡ ፀደይም አበቦችን እና ፍካትን እንዲሁም ደስታን ይዞ ከተፍ ይላል። በጋውም ቢሆን ሞቃታማ ቀናቱን ለዘለዓለም ለማዝለቅ መውደዱ አይቀርም:: ነገር ግን የበልግን መምጣት ተቀብሎ ስፍራውን አስረክቦ ዘወር ይላል:: በልግም ምድሪቱ ታርፍ ዘንድ እድል ይሰጣታል::
አጋዘን ሳርን ብትበላም እርሷ ራሷ የአንበሳ ምግብ ናት:: ይህ የጥንካሬ ጉዳይ አይደለም:: ማን ይበልጥ ይበረታል ስለማለትም አይደለም:: ይልቁን አምላክ የሞትንና የትንሳኤን ዑደት ለእኛ የሚያሳይበት መንገድ ነው:: በዚህ ዑደት ውስጥም አሸናፊም ተሸናፊም የለም:: መታለፍ ያለባቸው ደረጃዎች ብቻ እንጂ። የሰው ልጅ ልብ ይህንን እውነታ ሲረዳ ነፃ ይሆናል፤ አስቸጋሪ ወቅቶችን ለማለፍ አያዳግተውም፤ በድል አድራጊነት የሞቅታ ስሜትም አይታለልም:: ሁለቱም አላፊ መሆናቸውን አይዘነጋም:: አንዳቸው በሌላቸው ይተካሉ::
ዑደቱም ይቀጥላል::
ስለዚህ የፍልሚያ ቀለበት ውስጥ ያለ ቡጢኛ (የራሱ ምርጫ አሊያም ሊመረመር የማይችል እጣ ፈንታ እዚያ ያስገኘው) ከፊት ለፊቱ በሚጠብቀው ፍልሚያ ተስፋ በደስታ ስሜት ውስጥ ሊዘፈቅ ይችላል፡፡ ክብሩንና ግርማውን መጠበቅ ከቻለ ፍልሚያውን ቢሸነፍም እንኳ ተሸናፊ ሊባል አይችልም:: ምክንያቱም መንፈሱ ምንም አልተሸራረፈምና።
ስለደረሰበት ነገር ሁሉ ሌሎችን መውቀስን ሙጥኝ አይልም፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍቅሮ፤ የፍቅር ጥያቄው ውድቅ ከተደረገበት
ጊዜ አንስቶ ይህ ውድቀት በእርሱ የማፍቀር ችሎታ ላይ ያመጣው አሉታዊ ለውጥ እንደሌለ ያውቃል::
በፍቅር ውስጥ እውነት የሆነው ሁሉ በጦርነት ውስጥም ይሰራል።
ፓውሎ ኮሆልዮ
@Human_Intelligence
👍 68❤ 17👏 4
