uz
Feedback
TIKVAH-MAGAZINE

TIKVAH-MAGAZINE

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
194 465
Obunachilar
-2724 soatlar
-1037 kunlar
-80330 kunlar
Postlar arxiv
የዓለም ፍጻሜ ተቃርቧል በማለት ሺዎችን ቀስቅሶ፤ ቀኑ ሲደርስ ትንቢቱ ተሯዝሟል ሲል የገለጸው ጋናዊ የዛሬ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል። እራሱን "ነብይ" ብሎ የሚጠራው ጋናዊው ኤቦ ኖኅ ምድር በፈረንጆቹ ከታህሳስ 25 [ዛሬ] ጀምሮ በከባድ ጎርፍ እንደምትጠለቀለቅ እና ፈጣሪ ሰዎችን ከሚያጠፋውና 3 አመት ከሚቆየው ጎርፍ እንዲድኑ መርከብ እንዲሰራ እንዳዘዘው ተናግሮ ነበር። ይህንን ማለቱም ተከትሎ በርካታ ተከታዮቹ ንብረታቸውን በመሸጥ ለእሱ ገንዘብ በመስጠት የመርከብ አገልግሎት ለማግኘት ወደ እሱ አምርተዋል። ኤቦ በመፅሐፍ ቅዱስ ከምናውቀው የኖህ ዘመን ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነገር ይፈጠራል ብሎ የተነበየ ሲሆን የሰራው ግን አስር መርከቦችን ነው። የ30 አመቱ ኤቦ መርከቦቹን ሲሰራም ቪዲዮ እየቀረፀ በማህበራዊ ሚዲያዎች ያጋራ የነበረ ሲሆን ከገና እለት ጀምሮ ለተከታታይ 3 አመታት ዝናብ ያለማቋረጥ ይዘንባል ብሎ ነበር። ዛሬ ታህሳስ 25 ግን ምንም ያልተፈጠረ ሲሆን ኤቦ የመርከብ ፕሮጀክቱን እንዲያስፋፋ ፈጣሪ ተጨማሪ ጊዜ እንደሰጠውና ትንቢቱ እንደተራዘመ ገልጿል። ትንቢቱ ለመቼ እንደተራዘመ ያልገለፀው ኤቦ ተከታዮቹ በሰጡት ገንዘብ የ100 ሺህ ዶላር መርሴዲስ መኪና ገዝቷል ተብሏል። ዘገባው የ WION ነው። 👋   |   @tikvahethmagazine
Hammasini ko'rsatish...
2.42 MB
🤣 470 72😢 15👎 8🤔 5🔥 2🤯 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዩኤኢ ከኤም-ፔሳ ጋር በመተባበር የብሎክቼይን ቴክኖሎጂን በአፍሪካ ለማስፋፋት አቅዳለች በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ወንድም በሚመራውና 240 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ባለው ኩባንያ የሚደገፈው ኤዲአይ ፋውንዴሽን (ADI Foundation) ከኤም-ፔሳ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ እስከ 2030 ድረስ አንድ ቢሊዮን ሰዎችን የብሎክቼይን ተጠቃሚ የማድረግ እቅድ አካል ሲሆን የብሎክቼይን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎችን ቀልጣፋ እና አስተማማኝ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም፥ ከውጭ ሀገር የሚላክን የገንዘብ ልውውጥ (Remittance) ወጪን በእጅጉ የሚቀንስና እንደ ኤም-ፔሳ ያሉ የዲጂታል የክፍያ አማራጮች ዓለም አቀፍ ተደራሽነት እንዲኖራቸው ያስችላልም ነው የተባለው። ኤዲአይ ፋውንዴሽን ዋና መሥሪያ ቤቱን አቡ ዳቢ አድርጎ፣ በአቡ ዳቢ ግሎባል ማርኬት (ADGM) ስር የመጀመሪያውን ይፋዊ የብሎክቼይን ፈቃድ በማግኘት በሕጋዊ መንገድ ስራ የጀመረ ተቋም ነው። ከኬንያ መንግስት ጋር በመተባበር በአፍሪካ የብሎክቼይን ቴክኖሎጂ ማዕከል (Blockchain Hub) ለመገንባት ስምምነት ቀደም ሲል የተፈራረመ ሲሆን ዓላማውም የኬንያን የግብር አሰባሰብ እና የመንግስት አገልግሎቶችን በብሎክቼይን ለማዘመን ነው። አሁን ላይ ኤዲአይ ፋውንዴሽን እና ኤም-ፔሳ የተፈራረሙት ስምምነት በቬነም የሚለማውን የብሎክቼይን የዲጂታል ክፍያ መሠረተ ልማት ከኤም-ፔሳ ሰፊ የደንበኞች መረብ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ነው። ኤም-ፔሳ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ በ7 ሀገራት (ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ታንዛኒያ፣ ሞዛምቢክ ዲአርሲ፣ ሌሴቶ እና ግብጽ ) ውስጥ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ኤዲአይ ፋውንዴሽን እስከ 2030 ድረስ በታዳጊ አገራት የሚገኙ 1 ቢሊዮን ሰዎችን የብሎክቼይን ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዷል። ተቋሙ በጥር 2026 ዋጋው ከዶላር ጋር የተያያዘ ዲጂታል ገንዘብ (Stablecoin) ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ይህ ዘገባ የሴማፎር ነው። 👋   |   @tikvahethmagazine
Hammasini ko'rsatish...
star reaction 2 59👍 14👎 5
#መልዕክት: በአቶ ኤፍሬም ጌታቸው ኃይሉ ስም ያለ የመኪና ሊብሬ ወድቆ ያገኙ ቤተሰቦቻችን ለባለቤቱ ለመመለስ መልዕክት አስቀምጠዋል። ባለቤቱ ከተገኘ መልዕከት የተላከልንን የስልክ አድራሻ ለባለቤቱ የምናሳውቅ ይሆናል። መልዕከት ለመላክ ከስር ያለውን DM (💬) ይጠቀሙ! 👋   |   @tikvahethmagazine
Hammasini ko'rsatish...
👍 32 17
Photo unavailableShow in Telegram
በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ የቀጥታ ምርጫ እየተደረገ ነው። የሞቃዲሾ ከተማ ነዋሪዎች ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ በከተማቸው እየተደረገ ባለ ምርጫ ዛሬ ድምፅ እየሰጡ ነው። ሶማሊያ ለመጨረሻ ጊዜ ህዝብ በቀጥታ የመረጠበትን ምርጫ ያደረገችው በፈረንጆቹ 1969 ሲሆን ከፊል ራስገዟ ፑንትላንድ እና ራስገዟ ሶማሊላንድ ግን ከዛ በኋላም ህዝባዊ ምርጫ ሲያደርጉ ቆይተዋል። በ1969 ምርጫ ከተደረገ ከጥቂት ወራቶች በኋላ ዚያድ ባሬ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን መያዙ ሲታወስ ባሬ በ1991 ከስልጣን መውረዱን ተከትሎ በ2004 ቀጥተኛ ያልሆነ በጎሳ ተወካዮች የሚካሄድ ምርጫን አስተዋውቃለች። ከ2004 ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው የኢ-ቀጥተኛ ምርጫ ስርዓትም የጎሳ ተወካዮች ህግ አውጪዎችን ሲመርጡ፣ ህግ አውጪዎች ደግሞ ፕሬዚዳንቱን ይመርጡ ነበር።ለዋና ከተማዋ ሞቃዲሾም ከንቲባ የሚሾመው በዚሁ መንገድ በተመረጠ ፕሬዚዳንት ነው። 3 ሚሊየን ነዋሪዎች ባሏት ሞቃዲሾ የሚካሄደው ምርጫም በቀጣይ ለሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ሙከራ ይሆናል ተብሏል። በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ምርጫ ለ390 የምክር ቤት ወንበሮች 1605 እጩዎች እንደሚወዳደሩም ተገልጿል። ሶማሊያ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ከ10 ሺህ በላይ የጸጥታ ኃይሎችንም አሰማርታለች። ዘገባው የሮይተርስ ነው። 👋   |   @tikvahethmagazine
Hammasini ko'rsatish...
41👍 10🕊 6🤬 4
Photo unavailableShow in Telegram
 በመሀል ሳር ቤት     ከቴምር ፕሮፐርቲ ➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 5.7ሚሊዮን 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 6.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 143ካሬ = 10.2ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 10.9ሚሊዮን ከሌሎች የካሬ አማራጭ ጋ ➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 143ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.7ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) 🌴 ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። 🌴በተጨማሪም በአዋሬ በተለያዩ የካሬ አማራጭ አፓርትመንቶችን እኛ ጋ ያገኛሉ ለበለጠ መረጃ 0938262649
Hammasini ko'rsatish...
10
በጥቅምት ወር ድንበር አቋርጠው የሚወጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በ38 በመቶ መጨመሩ ተገለጸ ​የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የጥቅምት 2025 ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ በኢትዮጵያ በሚገኙ ስድስት የድንበር ፍሰት መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ የታየው የሰዎች እንቅስቃሴ ካለፈው መስከረም ወር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። በወሩ ውስጥ በአጠቃላይ 45,150 የሰዎች ዝውውር የተመዘገበ ሲሆን፣ ይህም በቀን በአማካይ 1,456 ሰዎች ድንበር እንደሚያቋርጡ ያሳያል ነው የተባለው። ከእነዚህ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አብዛኛው ማለትም 78.3 በመቶው (35,341 ሰዎች) ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚወጡ ሲሆን፣ ቀሪው 21.7 በመቶው (9,809 ሰዎች) ደግሞ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ናቸው። በጥቅምት ወር ድንበር አቋርጠው የሚወጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ካለፈው የመስከረም ጋር ሲነጻጸር የ38 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ሪፖርቱ አመላክቷል። ይህ የፍልሰት መጨመር በተለይ በሱዳን ድንበር በሚገኘው በመተማ በኩል በከፍተኛ ሁኔታ የታየ ሲሆን፣ ለዚህም በስደተኞቹ መነሻ አካባቢዎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ መባባስና ወቅታዊ ሁኔታዎች እንደ ዋና ምክንያት ተጠቃሽ ሆነዋል። ከሀገር ወደ ውጭ የሚወጡት ዜጎች በዋነኝነት የሚጠቀሙባቸው የጅቡቲ ድንበር የሆኑት ገላፊ እና ደወሌ እንዲሁም የሶማሊያ ድንበር የሆነው ቶጎ ውጫሌ ጣቢያዎች ሲሆኑ፣ እነዚህ መስመሮች 53.2 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ፍልሰት የተመዘገበባቸው ናቸው ተብሏል። ስደተኞቹ ለፍልሰት የሚያነሳሷቸውን ምክንያቶች በዋነኛነት ( 59.8 በመቶ የሚሆኑት ) ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ምክንያት ያደአጉ ናቸው። በመዳረሻ ሀገር ሲታይም፣ አብዛኞቹ ማለትም 14,126 (40 በመቶ) የሚሆኑት የሚሰደዱት ወደ ሳውዲ አረቢያ ለማቅናት ዓላማ ሰንቀው ነው። ሌሎች ደግሞ ወደ ሱዳን (21%)፣ ኬንያ (10.8%)፣ ጅቡቲ (5.5%) እና ሶማሊያ (4.5%) ለማምራት በመጓዝ ላይ መሆናቸውን ሪፖርቱ በዝርዝር አመልክቷል። በተለይ ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚደረገው ጉዞ አብዛኛውን ጊዜ በየመን በኩል የሚያልፍ በመሆኑ ከፍተኛ ሥጋት ያለው መስመር መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። 🔗 ምስላዊ መረጃ ከላየ ተያይዟል። 👋   |   @tikvahethmagazine
Hammasini ko'rsatish...
57😢 34🕊 6
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካ በፈቃዳቸው ከሃገሯ ለመውጣት ለሚፈልጉ ሰነድ አልባ ስደተኞች የ3000 ዶላር ክፍያ አዘጋጅታለች። የአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደህንነት ቢሮ በ2026 መጨረሻ ከአሜሪካ በገዛ ፈቃዳቸው ለመውጣት ለሚፈልጉ ስደተኞች "የገና ጉርሻ" ሲል የሰየመውን ክፍያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል። ቢሮው እስከ መጪው ታህሳስ 31 የሚመዘገቡ ስደተኞች ወደ ሃገራቸው የነፃ በረራ የሚሰጣቸው ሲሆን የ3000 ዶላር ክፍያም ይሰጣቸዋል ብሏል። ከባለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ አሜሪካ በፈቃዳቸው መውጣት ለሚፈልጉ ስደተኞች የ1000 ዶላር ክፍያ ስትፈፅም እንደነበር ሲታወስ ስደተኞቹ ለዚሁ ጥቅም እንዲውል ታስቦ በተሰራ መተግበሪያ በኩል ምዝገባቸውን ያከናውኑ ነበር። አሜሪካ በገዛ ፈቃዳቸው ሃገሯን ለቀው የማይወጡ ስደተኞች እስራት፣ በግዳጅ መባረርና ዳግም ወደ አሜሪካ መግባት እንዳይችሉ እገዳ እንደምትጥል መግለጿ ይታወሳል። ዘገባው የDW ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Hammasini ko'rsatish...
🤣 61 46🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካ ሰጥታ የነበረውን ህጋዊ ከለላ ማንሳቷ ትክክል አይደለም ያሉ አራት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በፍርድ ቤት ክስ መሰረቱ። የትራምፕ አስተዳደር ከወር በፊት ከ200 ለሚበልጡ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ሰጥቶት የነበረውን ጊዜያዊ የህግ ከለላ ማቋረጡ ይታወሳል። ይህ የህግ ከለላ መቋረጡ ተገቢ አይደለም ያሉ 4 የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መንግስታዊ ካልሆነው "አፍሪካ ኮሚዩኒቲስ ቱጌዘር" ተቋም ጋር በመሆን በቦስተን ፍርድ ቤት ክስ መስርተዋል። ከሳሾቹ የከለላው መነሳት በደቡብ ሱዳን ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ የዘነጋና ስደተኞችን ማግለል ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል። የአፍሪካን ኮሚዩኒቲስ ቱጌዘር ዳይሬክተር አምሃ ካሳ ውሳኔው "ስደተኞች የሚገጥማቸውን አደጋ ትቶ ቀለምን መሰረት ያደረገ ነው" ብለዋል። 232 የደቡብ ሱዳን ዜጎች የህጋዊ ከለላ ተሰጥቷቸው እንደነበሩ በክሱ ሲገለፅ ይህ ከለላም ከመጨው ጥር 5 ጀምሮ ያበቃል። ዘገባው የሮይተርስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Hammasini ko'rsatish...
47🤣 22🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
የቱርኪዬ የጦር መሳሪያ እና አቪየሽን ሽያጭ በ11 ወራት 7.4 ቢሊየን ዶላር ደርሷል። የቱርኪዬ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ሃገራቸው ወደ ውጪ ከላከችው የጦር መሳሪያ እና አቪየሽን እቃዎች በ11 ወራት 7.445 ቢሊየን ዶላር ማግኘቷን ገልፀዋል። ገቢው ከባለፈው አመት አንፃር በ30% ጭማሪ ስለማሳየቱና ቱርኪዬም በጦር መሳሪያ ሽያጭ ከአለም 11ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ፕሬዚዳንቱ ጨምረው ተናግረዋል። ቱርኪዬ በ2028 ከዘርፉ 11 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ያቀደች ሲሆን አሁን ላይ የራሳቸውን የጦር መርከብ ሰርተው መጠቀም ከሚችሉ አስር ሃገራት መካከል አንዷ መሆኗንም ፕረዚዳንቷ አስታውቀዋል። ዘገባው የአናዶሉ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Hammasini ko'rsatish...
44👎 10💔 10👍 3😢 3🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
✨ከእኛ አንድ ቤት ሲገዙ ከኢትዮዽያ አየርመንገድ ET🇪🇹 Sheba Miles ደረጃዎን በእጥፍ ያሳድጉ ✈️🤝 በተጨማሪም በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ባለቤት ልናረጎ ሲሆን:- እስከ 25% ቅናሽ ያላቸው በነፋሻማዋ ሰሜን ማዘጋጃ ላይ ግንባታቸው እየተካሄደ ያለ በካ.ሜ ከ65,000 ብር ጀምሮ ይዘንላቹ መተናል! 👉በ 25% ቅናሽ (100% ለሚከፍሉ ደምበኞች) ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ)=5,300,000ብር ባለ 2መኝታ(110ካ.ሜ)=7,200,000ብር ባለ3መኝታ(130ካ.ሜ)=8,500,000ብር 👉በ 10% ቅድመ ክፍያ ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፍሉት! ባለ 1 መኝታ(81 ካ.ሜ) = 700,000 ብር ባለ 2 መኝታ(110ካ.ሜ) =957,000 ብር ባለ 3 መኝታ(130ካ.ሜ)=1,131,000ብር ✨በተጨማሪም እንደ ቅድመ ክፍያዎ ቀድመዉ ለሚመጡ 15 ደምበኞች ብቻ ከ3% እስከ 25% ቅናሽ ያለን ሲሆን ይህንን እድል ተጠቃሚ ለመሆን በ0913599755 ወይም 0912915147 ይደውሉ! #Akoyaproperties #EthiopianAirlines #ShebaMiles #Partnership
Hammasini ko'rsatish...
11🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
የሳዑዲ የጸጥታ ዘመቻ እና ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ባለፉት 4 ወራት ህገ-ወጥ ተብለው ከተያዙት ውስጥ ግማሹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ባለፉት 2 ሳምንታት ብቻ በሳዑዲ አረቢያ ከተያዙ 19,500 ግለሰቦች ውስጥ 57 በመቶው ኢትዮጵያውያን ናቸው። በየሳምንቱ በአማካይ 900 አዳዲስ ኢትዮጵያውያን በየመን ድንበር አቋርጠው ወደ ሳዑዲ ሊገቡ ሲሉ ይያዛሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ወራት (ከመስከረም 2025 ጀምሮ) በሳዑዲ አረቢያ መንግስት የወጡ ሳምንታዊ የጸጥታ ሪፖርቶችን በዝርዝር ተመልክቷል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገር ቤት እየተመለሱ ቢሆንም መረጃዎቹ እንደሚያሳዩት ከሆነ ግን አደገኛው የስደት ጉዞ ግን እልባት የተገኘለት አይመስልም። ቁጥሮች ምን ያሳያሉ ? ጠቅላላ በሳዑዲ አረቢያ የጸጥታ ዘመቻ (ከመስከረም ጀምሮ ባሉት 4 ወራት) የተያዙ ሰዎች ቁጥር 323,546 መሆኑ ተገልጿል። እነዚህም ሦስት ዋና ዋና ጥሰቶች የሚያመለከት ነው። በመኖሪያ ፈቃድ (Iqama) ጥሰት 210 ሺ የሚጠጉ ሰዎች የተያዙ ሲሆን፥ የመኖሪያ ፈቃድ (ኢቃማ) የሌላቸው ወይም ያላደሱትን የሚመለከት ነው። ወደ 78,000 የሚጠጉት ደግሞ ድንበር በመጣስ በብዛት በየመን በኩል ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ናቸው። ቀሪዎቹ ወደ 35,000 የሚሆኑት የሥራ ህግ ጥሰት ፈጽመው የተገኙ ሲሆኑ ከአሰሪዎቻቸው ጠፍተው በሌላ ቦታ ሲሰሩ የተገኙ ናቸው። 📝 በድንበር ጥሰት የተያዙ ኢትዮጵያን ስንት ናቸው ? ባለፉት 16 ሳምንታት (ከመስከረም 1 እስከ ታህሳስ 20/2025) በድንበር በኩል በህገወጥ መንገድ (በብዛት በየመን) ሊገቡ ሲሉ ከተያዙ ከ78 ሺ በላይ ሰዎች ኢትዮጵያውያን በአማካይ 57 በመቶ ይሆናሉ። ይህም በዚህ ጊዜ ውስጥ ከ14ሺ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሳውዲ ለመግባት ሲሉ በድንበር ጥሰት መያዛቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። ታዲያ ኢትዮጵያዊያኑ የሳውዲ ድንበር የሚደርሱት ኢትዮጵያዊያን በዓለም አቀፍ ደረጃ የምስራቁ መስመር (The Eastern Route) ተብሎ የሚታወቀውና ከኢትዮጵያ ተነስቶ በጅቡቲ/ሶማሊያ አቋርጦ በየመን በኩል ወደ ሳዑዲ የሚወስደው መንገድን አልፈው ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያቀዱበት ሳይደርሱ የሚቀሩበት መስመር ነው። 📝 በመኖሪያ ፈቃድና የሥራ ህግ ጥሰት የሚያዙትስ ? በሳዑዲ በከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ሰዎችን በቁጥጥር ስር ስታውል ባለፉት 4 ወራት ከ200 ሺ ሰዎች በላይ በቁጥጥር ሥር አውላለች ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ከተያዙት 19,500 ሰዎች መካከል 11,115 (57%) ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ዘገባዎቹ ያመለክታሉ። በተጨማሪም በደላላ ተታልለው ከቤት ሰራተኝነት ወይም ከሌሎች ስራዎች የጠፉ ዜጎች በተመለከተ ምን ያህል ኢትዮጵያዊያን እንደተያዙ በቁጥር ባይጠቀስም በርካቶች ተታለው ለከፋ ችግር እየተጋለጡ መሆኑን በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። 📝 በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምን አለ ? ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ የአገሪቱን የሥራና የመኖሪያ ፈቃድ ሕግጋት ተላልፈው የተገኙ ኢትዮጵያን ቁጥር 11ሺ እንደሚበልጥ ገልጿል። በኮንትራት የመጡ ዜጎች "የተሻለ ክፍያና የሥራ አማራጭ አለ" በሚሉ ደላሎች ተታልለው ከሥራ ገበታቸው (ከአሰሪዎቻቸው) እንዳይጠፉ በማሳሰብ፥ መጥፋታቸው ዜጎችን ከህጋዊ ከለላ ውጭ እንደሚያደርጋቸው አስጠንቅቋል። በተጨማሪም አንድ ሰራተኛ ከኮንትራት ስራው ሲጠፋ (ሁሩብ ሲደረግበት) ለጾታዊ እና አካላዊ ጥቃት፤ ለጉልበት ብዝበዛ እና ደሞዝ ባይከፈላቸው እንኳ መብታቸውን መጠየቅ የማይችሉበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ነው የጠቆመው። ዜጎች ችግር ሲገጥማቸው ከመጥፋት ይልቅ በማናቸውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ቢሆን እንኳን ለኤምባሲው ማመልከት፤ በአካል በመቅረብም አስፈላጊውን የህግ ድጋፍ ማግኘት እና መብታቸውን ማስከበር ይችላሉ ብሏል። በአጠቃላይ ባለፉት 4 ወራት የታዩት መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በየሳምንቱ በአማካይ 900 የሚጠጉ አዳዲስ ኢትዮጵያውያን በድንበር በኩል ሲታሰሩ፣ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ በከተማ ውስጥ ያሉትም በደላላ ተታልለው ከህጋዊ ስራቸው በመጥፋት ለእስር እየተዳረጉ ይገኛሉ። ይህም በሳዑዲ ያለውን የዜጎች ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ አድርጎታል። #TikvahEthiopia 😀   |   @tikvahethmagazine
Hammasini ko'rsatish...
61😢 35🕊 7👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
የሳዑዲ የጸጥታ ዘመቻ እና ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ባለፉት 4 ወራት ከተያዙት ህገ-ወጥ ተብለው ከተያዙት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ግማሹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ባለፉት 2 ሳምንታት ብቻ በሳዑዲ አረቢያ ከተያዙ 19,500 ግለሰቦች ውስጥ 57 በመቶው ኢትዮጵያውያን ናቸው። በየሳምንቱ በአማካይ 900 አዳዲስ ኢትዮጵያውያን በየመን ድንበር አቋርጠው ወደ ሳዑዲ ሊገቡ ሲሉ ይያዛሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ወራት (ከመስከረም 2025 ጀምሮ) በሳዑዲ አረቢያ መንግስት የወጡ ሳምንታዊ የጸጥታ ሪፖርቶችን በዝርዝር ተመልክቷል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገር ቤት እየተመለሱ ቢሆንም መረጃዎቹ እንደሚያሳዩት ከሆነ ግን አደገኛው የስደት ጉዞ ግን እልባት የተገኘለት አይመስልም። ቁጥሮች ምን ያሳያሉ ? ጠቅላላ በሳዑዲ አረቢያ የጸጥታ ዘመቻ (ከመስከረም ጀምሮ ባሉት 4 ወራት) የተያዙ ሰዎች ቁጥር 323,546 መሆኑ ተገልጿል። እነዚህም ሦስት ዋና ዋና ጥሰቶች የሚያመለከት ነው። በመኖሪያ ፈቃድ (Iqama) ጥሰት 210 ሺ የሚጠጉ ሰዎች የተያዙ ሲሆን፥ የመኖሪያ ፈቃድ (ኢቃማ) የሌላቸው ወይም ያላደሱትን የሚመለከት ነው። ወደ 78,000 የሚጠጉት ደግሞ ድንበር በመጣስ በብዛት በየመን በኩል ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ናቸው። ቀሪዎቹ ወደ 35,000 የሚሆኑት የሥራ ህግ ጥሰት ፈጽመው የተገኙ ሲሆኑ ከአሰሪዎቻቸው ጠፍተው በሌላ ቦታ ሲሰሩ የተገኙ ናቸው። 📝 በድንበር ጥሰት የተያዙ ኢትዮጵያን ስንት ናቸው ? ባለፉት 16 ሳምንታት (ከመስከረም 1 እስከ ታህሳስ 20/2025) በድንበር በኩል በህገወጥ መንገድ (በብዛት በየመን) ሊገቡ ሲሉ ከተያዙ ከ25 ሺ በላይ ሰዎች ኢትዮጵያውያን በአማካይ 57 በመቶ ይሆናሉ። ይህም በዚህ ጊዜ ውስጥ ከ14ሺ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሳውዲ ለመግባት ሲሉ በድንበር ጥሰት መያዛቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። ታዲያ ኢትዮጵያዊያኑ የሳውዲ ድንበር የሚደርሱት ኢትዮጵያዊያን በዓለም አቀፍ ደረጃ የምስራቁ መስመር (The Eastern Route) ተብሎ የሚታወቀውና ከኢትዮጵያ ተነስቶ በጅቡቲ/ሶማሊያ አቋርጦ በየመን በኩል ወደ ሳዑዲ የሚወስደው መንገድን አልፈው ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያቀዱበት ሳይደርሱ የሚቀሩበት መስመር ነው። 📝 በመኖሪያ ፈቃድና የሥራ ህግ ጥሰት የሚያዙትስ ? በሳዑዲ በከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ሰዎችን በቁጥጥር ስር ስታውል ባለፉት 4 ወራት ከ200 ሺ ሰዎች በላይ በቁጥጥር ሥር አውላለች ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ከተያዙት 19,500 ሰዎች መካከል 11,115 (57%) ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ዘገባዎቹ ያመለክታሉ። በተጨማሪም በደላላ ተታልለው ከቤት ሰራተኝነት ወይም ከሌሎች ስራዎች የጠፉ ዜጎች በተመለከተ ምን ያህል ኢትዮጵያዊያን እንደተያዙ በቁጥር ባይጠቀስም በርካቶች ተታለው ለከፋ ችግር እየተጋለጡ መሆኑን በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። 📝 በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምን አለ ? ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ የአገሪቱን የሥራና የመኖሪያ ፈቃድ ሕግጋት ተላልፈው የተገኙ ኢትዮጵያን ቁጥር 11ሺ እንደሚበልጥ ገልጿል። በኮንትራት የመጡ ዜጎች "የተሻለ ክፍያና የሥራ አማራጭ አለ" በሚሉ ደላሎች ተታልለው ከሥራ ገበታቸው (ከአሰሪዎቻቸው) እንዳይጠፉ በማሳሰብ፥ መጥፋታቸው ዜጎችን ከህጋዊ ከለላ ውጭ እንደሚያደርጋቸው አስጠንቅቋል። በተጨማሪም አንድ ሰራተኛ ከኮንትራት ስራው ሲጠፋ (ሁሩብ ሲደረግበት) ለጾታዊ እና አካላዊ ጥቃት፤ ለጉልበት ብዝበዛ እና ደሞዝ ባይከፈላቸው እንኳ መብታቸውን መጠየቅ የማይችሉበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ነው የጠቆመው። ዜጎች ችግር ሲገጥማቸው ከመጥፋት ይልቅ በማናቸውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ቢሆን እንኳን ለኤምባሲው ማመልከት፤ በአካል በመቅረብም አስፈላጊውን የህግ ድጋፍ ማግኘት እና መብታቸውን ማስከበር ይችላሉ ብሏል። በአጠቃላይ ባለፉት 4 ወራት የታዩት መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በየሳምንቱ በአማካይ 900 የሚጠጉ አዳዲስ ኢትዮጵያውያን በድንበር በኩል ሲታሰሩ፣ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ በከተማ ውስጥ ያሉትም በደላላ ተታልለው ከህጋዊ ስራቸው በመጥፋት ለእስር እየተዳረጉ ይገኛሉ። ይህም በሳዑዲ ያለውን የዜጎች ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ አድርጎታል። #TikvahEthiopia 😀   |   @tikvahethmagazine
Hammasini ko'rsatish...
1
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ የአውራ አምባ ማይክሮፋይናንስ በ0 አመት እና የሥራ ልምድ በሚጠይቁ ክፍት የስራ ቦታዎች በአዲስ አበባ እና በባህርዳር አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጥር እንደሚፈልግ ገልጾልናል። 🔗 ዝርዝሩ ከላይ ባለው ምስል ተያይዟል።
Hammasini ko'rsatish...
24👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል አድሪስ የሱዳንን ጦርነት ይቋጫል ያሉትን የሰላም እቅድ ለተመድ የጸጥታው ምክር ቤት አቅርበዋል። ባለፈው ግንቦት ወር በጀነራል አልቡርሃን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ካሚል እድሪስ በተመድ፣ የአፍሪካ ህብረትና የአረብ ሊግ የሚመራ የሰላም እቅድ አቅርበዋል። በሰላም እቅዱ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ትጥቅ በመፍታት ከያዛቸው ግዛቶች ለቅቆ ይውጣ የሚለው ይገኝበታል። እድሪስ በተጨማሪ ነፃ ምርጫ እንደሚደረግና የጦር ወንጀል ያልፈፀሙ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ተዋጊዎች ወደ ማህበረሰቡ እንደሚቀላቀሉም ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ እየተሳተፉ የሚገኙት የሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ጠይቀዋል። በተጨማሪ ሚኒስትሩ የመሳሪያ፣ የገንዘብ፣ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ትሰጣለች ብለው የከሰሷትን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ተጠያቂ እንድትሆን ጠይቀዋል። ዘገባው የአልጄዚራ እና አፍሪካ ኒውስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Hammasini ko'rsatish...
32🤣 18🤔 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በትራምፕ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ከሚደረጉት መካከል አይደሉም- ኤምባሲው የትራምፕ አስተዳደር ለበርካታ አመታት በዲፕሎማሲው የቆዩ በተለይ በአፍሪካ የተመደቡ አምባሳደሮችን ከኃላፊነታቸው እንደሚያነሳ ሲገለፅ፣ የወቅቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋም ከሚነሱት መካከል ናቸው የሚሉ ዘገባዎት ተሰራጭተው ነበር። በአዲስ አበባ ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ ኢትዮጵያ በትራምፕ አስተዳደር እንዲነሱ ከተቀመጡት ሃገራት ውስጥ እንደሌለችና አምባሳደሩ በስራቸው እንደሚቀጥሉ ገልጿል። ኤምባሲው አምባሳደሩ አለመጠራታቸውና ዘገባው ሃሰት መሆኑን ገልፆ ትናንት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በተፈረመው የጤና ስምምነትም መገኘታቸውንም አስታውቋል። ትራምፕ በባይደን አስተዳደር የተመደቡ አምባሳደሮችን እንደሚያነሱ ሲነገር፣ ኤርቪን ማሲንጋ በአምባሳደርነት ወደ ኢትዮጵያ በአምባሳደርነት የተሾሙት በቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆ በባይደን አስተዳደር ወቅት በፈረንጆቹ 2023 ነበር። የመረጃው ምንጭ አዲስ ስታንዳርድ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Hammasini ko'rsatish...
37👍 9👎 8🤔 3
Photo unavailableShow in Telegram
የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የአፍሪካ ሃገራት A7 የተሰኘውን የፋይናንስ መድረክ እንዲቀላቀሉ ጠየቁ። ላቭሮቭ የንግድ መረጋጋትና ኢንቨስትመንትን ለመጠበቅ ያስችላል ያሉትን ይህንን የፋይናንስ መተግበሪያ አፍሪካውያን አጋሮች እንዲቀላቀሉ ጠይቀዋል። ከአፍሪካ እስካሁን በሩሲያ የተመሰረተውን የፋይናንስ መድረክ ናይጄሪያ እና ዚምባቡዌ ተቀላቅለውታል። ላቭሮቭ በብሔራዊ የሃገራት መገበያያ ገንዘቦች ንግድ ለማድረግ የሚያስችል መንገድ መፍጠር ይገባል ብለዋል። ላቭሮቭ ሩሲያ በ2024 ይፋ ያደረገችው የA7 መድረክ የሩሲያ ቢዝነሶች በየትኛውም መገበያያ ገንዘብና ሃገር የገንዘብ ዝውውር እንዲያደርግ ያስችላል ያሉ ሲሆን በሩሲያ መገበያያ ገንዘብ ሩብል የሚፈፀሙ የጋራ ንግዶችም 84% መድረሳቸው ተነግሯል። A7 የተሰኘው ድርጅት በሩሲያ የመከላከያ ዘርፍ ላይ ትኩረት በሚያደርገው PSB ባንክ የተመሰረተ ሲሆን የሩሲያን የአለም አቀፍ ንግድ ለማቀላጠፍ በማሰብ የተመሰረተ ነው። ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት የተነሳ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ዝውውር ስርዓት ስዊፍት የታገደች ሲሆን አለም አቀፍ ንግዶችንም በእገዳው ምክንያት ማከናውን ከብዷታል። A7 ለዚህ እገዳ አማራጭ በመሆን ሩሲያ በተለያዩ ሃገራት መገበያያ ገንዘብ የአለም አቀፍ ንግድን እንድታከናውን ሲያስችላት የአውሮፓ ህብረትም ከህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ እገዳ ጥሎበታል። ተቋሙ መተግበሪያው ላይ የሚጣሉ እገዳዎች ምንም ተፅዕኖ እንዳያመጡ ተደርጎ መሰራቱን ገልፆ ተጠቃሚዎቹ ምንም ስጋት እንዳይገባቸው ተናግሮ ነበር። ዘገባው የስፑቲንክ እና ሮይተርስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Hammasini ko'rsatish...
42👍 12👎 1🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
 በመሀል ሳር ቤት     ከቴምር ፕሮፐርቲ ➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 5.7ሚሊዮን 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 6.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 143ካሬ = 10.2ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 10.9ሚሊዮን ከሌሎች የካሬ አማራጭ ጋ ➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 143ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.7ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) 🌴 ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። 🌴በተጨማሪም በአዋሬ በተለያዩ የካሬ አማራጭ አፓርትመንቶችን እኛ ጋ ያገኛሉ ለበለጠ መረጃ 0938262649
Hammasini ko'rsatish...
12