አዲስ ነገር መረጃ
Kanalga Telegram’da o‘tish
#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot
Ko'proq ko'rsatish2025 yil raqamlarda

103 350
Obunachilar
-5124 soatlar
-3077 kunlar
+12730 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
የሱዳኑ ጦርነቱ ወደ ኢትዮጵያ እየተስፋፋ ነው!
አስከፊው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ወደ ኢትዮጵያ እየተስፋፋ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዛሬው እለት አስጠንቅቋል።
አልጀዚራ ከሁለት ሳምንት በፊት ባወጣው ዘገባ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ክልል ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የጦር ቤዜ ሰጥታለች ሲል ዘግቦ ነበር።
ይህን ተከትሎም የአልቡርሃን ጦር በቤንሻንጉል አቅጣጫ ጥቃት ለመክፈት እየተዘጋጀ መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል።
ተመድ በበኩሉ ጦርነቱ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር የመስፋፋት አዝማሚያ እያሳየ መሆኑን ዛሬ አሳውቋል።
በሱዳን ጦርነት የሕወሓት ወታደሮች እና ኤርትራ ከአልቡርሃን ጎን እንደተሰለፉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 33🙏 4🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ ድቤይቤህ የሊቢያ ጦር አዛዥ መሐመድ አሊ አህመድ አል-ሃዳድ እና ሌሎች አራት ሰዎች በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ አቅራቢያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ መሞታቸውን አረጋግጠዋል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢 11❤ 9
00:05
Video unavailableShow in Telegram
በአጥር ተዘግተው የነበሩ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን የማስከፈት ሥራ ተጀመረ
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች መንገድ ዘግተው የሚገኙ አጥሮችን በማንሳት የውስጥ ለውስጥ መተላለፊያ መንገዶችን የማስከፈት ዘመቻ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።
በዚህም መሠረት በቃሊቲ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ በአጥር ተዘግተው የነበሩ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በግብረ ኃይል የማንሳት ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል ተብሏል። ይህ እርምጃ በከተማዋ ያለውን የትራፊክ ፍሰት ለማሳለጥና የህዝብን የመንቀሳቀስ መብት ለማስከበር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ የመንገድ ማስከፈት ተግባር በቃሊቲ ገብርኤል ብቻ የሚገታ ሳይሆን፣ በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች በተመሳሳይ ሁኔታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተመልክቷል። ህብረተሰቡም ለመንገድ መከፈት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
AQNyQ8G83e5HhDticSS4UTJkjYWNodabrUik_wOch7fi68EyOn2Gyj0gl6pxDXn.mp42.16 KB
❤ 38👍 17🤪 2🤔 1😨 1
Photo unavailableShow in Telegram
መስማት ለተሳናቸው ዜጎች የመንጃ ፍቃድ ስልጠና መስጠት ተጀመረ
የአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ባለሥልጣን መስማት ለተሳናቸው ዜጎች የማሽከርከር ሥልጠና መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።
ሰልጣኞቹ የማሽከርከር ፈቃድ እንዲሰጣቸው ረጅም ዓመታት ሲጠይቁ ቢቆዩም ትኩረት ሳይሰጣቸው እንደቆየ አንስተው እንዲሠለጥኑ በመደረጉ የተሰማቸውን ደሥታ ገልፁዋል ፡፡
መስማት የተሳናቸው ዜጎች የክህሎትና የሥነ ባህሪ ሥልጠናውን በተቀመጠው ሥታንዳርድ መሰረት በመውሰድ ብቁና ምስጉን አሽከርካሪ ለመሆን በትኩረት እንደሚሰሩ አንስተዋል።
የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢ/ር ደሳለኝ ተረፈ የረጅም ጊዜ የአገልግሎት የፍትሀዊነት ጥያቄዎች ለመመለሥ በመልካም አስተዳደር ዕቅድ ተይዞ ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው ለተግባራዊነቱ የሰሩትን አመስግነዋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 30🤔 11😢 6
Photo unavailableShow in Telegram
🇪🇹🔥 ቤታቹሁ ቁጭ ብላቹ በወር ከ10,000 እስከ 20,000 ብር የምታገኙበት ስራ መስራት ይፈልጋሉ⁉️
💸የኦንላይን ስራዎች የሚሰሩበት እና እንዲሁም የስራ ማስታወቂያዎችን የሚያገኙበት አሪፍ አፕልኬሽን እናስተዋውቅዎ ባሉበት ቦታ ሆነው በስልኮ በቀላሉ የሚሰሩበት እና በየወሩ ተከፋይ የሚሆኑበት አፕ በቀላሉ ከታች ባለው ሊንክ ዳውንሎድ በማድረግ መጠቀም ትችላላችሁ።
✅Download ለማድረግ
👇👇👇👇👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.habeshanjobs.habeshanjobs
❤ 2😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
የርህራሄው ጥግ!
24 ሰዓት ባልሞላ ስአት ውስጥ 11,000,000 (አስራ አንድ ሚሊዮን) ብር ተሰበሰበ።
ይህ ከምንም በላይ የሆነ ተአምር ነው!
የዓመቱ ምርጥ TikToker አዶናይ (Adonay) በሕፃፅ ለሚገኙ ወገኖቻችን የጀመረው 100 ብር Challenge የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት ለዓለም በተግባር አሳይቷል።
አንድ ቀን ሳይሞላ 11 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል!
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፣ ክበር! የሰጣችሁት 100 ብር ተደምሮ ዛሬ ለሺዎች የህይወት ተስፋ ሆኗል።
በሕፃፅ የሚገኙ እናቶችና ህፃናት ዛሬ በእናንተ ምክንያት ፈገግ ይላሉ።
አንድነት ሲኖር ተራራው ይነዳል፤ ርህራሄ ሲኖር ህይወት ይለመልማል።
ይህንን የኩራት ዜና ለሁሉም እንዲደርስ Share በማድረግ አጋሩት።
ጉርሻ ፔጅ
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 149👏 29🥱 3🤪 3
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ብር በአለም ሶስተኛዉ ደካማዉ ገንዘብ ተባለ
👉🏼 በአንድ አመት ዉስጥ ብቻም ብር ዋጋው በ15 በመቶ መዳከሙ ተዘግቧል
የኢትዮጵያ ብር ዋጋ በተያዘው የአውሮፓዊያን ዓመት ብቻ ከአሜሪካ ዶላር አንጻር ዋጋው በ15 በመቶ ማሽቆልቆሉን ብሉምበርግ ዘገበ።
ብር ባሁኑ ወቅት ከአርጀንቲናው ፔሶ እና ከቱርኩ ሊሬ ቀጥሎ በዓለም ደካማው መገበያያ ገንዘብ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
የብር ዋጋ ወደፊትም ኢትዮጵያ የውጭ እዳዋን ማሸጋሸግ ከመቻሏ ጋር የተሳሰረ ሆኖ እንደሚቀጥል ዘገባው አመልክቷል።
መንግሥት የአገሪቱን 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር መልሶ ለማዋቀር ከወራት በፊት ከአበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ላይ መድርሱ ይታወሳል። ኾኖም የአገሪቱ የወጪ ገቢ ማደግ፣ የመንግሥት የበጀት ክፍተት መቀነስ እንዲሁም መንግሥት ከ1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮቦንድ ያዥ ዓለማቀፍ ኢንቨስተሮች ጋር በቦንዱ አከፋፈል ላይ ስምምነት ሊደርስ ይችላል የሚለው ተስፋ፣ በብር ላይ ያለውን ጫና ሊያቃልለው እንደሚችል ባለሙያዎች እምነታቸውን ገልጸዋል ተብሏል።
ባኹኑ ወቅት መደበኛው የ1 ዶላር መግዣ ዋጋ 151 ብር ሲሆን፣ በትይዩ ገበያ ደሞ ወደ 180 ብር አሻቅቧል።
Via ዋዜማ
@Yenetube @Fikerassefa
😢 44❤ 17🤣 4💔 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጋዜጠኛ ፋኑኤል "ማንነታቸው ካልታወቁ ሰዎች" ለማምለጥ ሲሞክር ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ገለፀ
የፈንታሌ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ፋኑኤል ክንፉ “ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች” በአዲስ_አበባ “ሊፈፀምብኝ ነበር” ካለው ጥቃት ለማምለጥ ሲሞክር ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል።
ጋዜጠኛ ፋኑኤል በደረሰበት ጉዳት ሳቢያም ለመራመድ ከሶስት እስከ ስድስት ወር ሊፈጅበት እንደሚችል በህክምና ባለሞያተኞች እንደተገለጸለት ተናግሯል።
ጋዜጠኛው ስለደረሰበት ጉዳት ሲያብራራ፣ ከወር በፊት ማለትም ህዳር 10/2018 ዓ.ም ስምንት ሰዓት አከባቢ “ሲቪል የለበሱ ሰዎች እንደሚፈልጉኝ” ከቤተሰብ ሰማሁ ሲል ይጀምራል።
በወቅቱ “የቅርብ ጓደኛው ገስት ሀውስ ብታርፍ ይሻላል ብሎኝ ወደዚያው በማቅናትት እዛው ክፍል አግኝቼ ገባው” ሲል ጋዜጠኛው ገልጿል።
ሆኖም የቅርብ ጓደኛው ከሄደ ከ50 ደቂቃ በኋላ ያረፈበት ክፍል በሩ በጣም ይደበደብ እንደጀመረ ጠቅሶ፤ በወቅቱ “ክፈት የሚል እና ሀይለቃል የተሞላበት ቃል እሰማ ነበር” ብሏል።
“በሩን በጣም እየገፉት ሲመጡ፤ ደብድበው ሞቶ ተገኘ ልባል እችላለሁ የሚል ስጋት አደረብኝ በዚህም አራት ሜትር አከባቢ ከሚረዝም ሁለተኛ ፎቅ ላይ ዘለልኩ” ሲል ተናግሯል።
“ዘልዬ ከወደኩኝ በኋላ ልነሳ ስል ራሴን ሳትኩ ጭልም አለብኝ” በማለት፣ “ቀና ስል አጥንቴ ተሰብሯል” ብሏል።
በአከባቢዬ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ነበሩ፤ "ይሄን እድል ደግመህ አታገኝም" ብለውኝ ሄዱ ከዛም ሰዎች ወደ ሆስፒታል ወሰዱኝ ብሏል።
“ከዛ በኋላ ለ20 ምናምን ቀናት ለማንም ጉዳዩን አልተናገርኩም ነበር” ያለው ጋዜጠኛ ፋኑኤል፣ ነገር ግን ጉዳዩ “ከሚዲያ ስራው ጋር የተገናኘ ነው” ብሎ እንደሚያምን ተናግሯል።
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 22😢 17
Photo unavailableShow in Telegram
ከ1ሺህ ዶላር ወደ 3000‼️
🇺🇸 የአሜሪካ መንግስት በገዛ ፈቃዳቸው ለሚወጡ ስደተኞች የ3,000 ዶላር ክፍያ ማበረቻ አቀረበ‼️
የአሜሪካ መንግስት ባልተሟላ ሰነድ (Undocumented) ሀገሪቱ ውስጥ ለሚገኙ እና በገዛ ፈቃዳቸው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ለሚመርጡ ስደተኞች አዲስ የማበረታቻ ፕሮግራም ይፋ አድርጓል።
የፕሮግራሙ ዝርዝር መረጃዎች፦
🔹 የገንዘብ ድጋፉ መጠን፦
ቀደም ሲል ከነበረበት $1,000 ወደ $3,000 ከፍ ብሏል።
🔹 የጉዞ ወጪ፦
ወደ ትውልድ ሀገር የሚቆረጥ የአንድ መንገድ የአውሮፕላን ትኬት ሙሉ በሙሉ በመንግስት ይሸፈናል።
🔹 የጊዜ ገደብ፦
ፕሮግራሙ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ የሚቆይ ሲሆን እስከ ታህሳስ 31፣ 2025 (December 31, 2025) ድረስ ይቆያል።
🔹 እንዴት መመዝገብ ይቻላል? ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች "CBP Home" በተሰኘው ይፋዊ የመንግስት መተግበሪያ (App) በኩል መመዝገብ አለባቸው።
ይህ ክፍያ እንዲሁ በነጻ የሚሰጥ ገንዘብ አይደለም። ክፍያው የሚፈጸመው ግለሰቡ በገዛ ፈቃዱ ከአሜሪካ መውጣቱ ሲረጋገጥ እና ሁሉንም መስፈርቶች ሲያሟላ ብቻ ነው።
ይህ ፕሮግራም በ2025 መጀመሪያ ላይ በ$1,000 ክፍያ ተጀምሮ የነበረ ሲሆን፣ አሁን እንደ አመት ማጠቃለያ ስልት ክፍያው ወደ $3,000 አድጓል።
ባጭሩ:-
1 እስከ $3,000 የጥሬ ገንዘብ ክፍያ
2. ነጻ የአውሮፕላን ትኬት
3. እስከ 2025 መጨረሻ የሚቆይ
4. በራስ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ነው"ብሏል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 28🤣 13🫡 2😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR)፤ በጋምቤላ ክልል የተጠለሉ ስደተኞች ላይ በማነጣጠር በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ “የተሳሳቱ መረጃዎች” “በእጅጉ እንዳሳሰቡት” ገለጸ።
ለሁኔታው በአፋጣኝ መፍትሔ ካልተበጀለት በአካባቢው ውጥረትን ሊያባብስ እንደሚችል ድርጅቱ አስጠንቅቋል።
የተመድ የስደተኞች መርጃ ተቋሙ ማስጠንቀቂያውን የሰጠው፤ ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 14፤ 2018 ባወጣው መግለጫ ነው።
ድርጅቱ በዚሁ መግለጫው፤ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በሀገራቸው ከሚደርስባቸው ጥቃት “ደህንነትን እና ጥበቃን ለማግኘት” እንደሆነ አስታውሷል።
የጥገኝነት ሲቪል እና ሰብአዊ ባህሪያት “ለድርድር የማይቀርብ መርህ” መሆኑን በመግለጫው አጽንኦት የሰጠው ድርጅቱ፤ “በትጥቅ እንቅስቃሴ” ውስጥ ሲሳተፍ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ በሀገሩ ሕግ መሰረት ተጠያቂ እንደሚሆን አመልክቷል።
ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩ መረጃዎች፤ ከደቡብ ሱዳን ተፈናቅለው በጋምቤላ ክልል ተጠልለው የሚገኙ ስደተኞች በክልሉ ሰሞኑን በተቀሰቀሰው ግጭት ውስጥ ተሳትፎ እንዳላቸው ወንጅለው ነበር።
UNHCR በዛሬው መግለጫው ስደተኞች ላይ ያነጣጠሩ “የተሳሰቱ መረጃዎች” መሰራጨታቸውን ቢገልጽም፤ ስለ መረጃዎቹ ምንነት በግልጽ ያለው ነገር የለም።
በጋምቤላ ክልል ባሉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ላይ የቀረበውን ውንጀላ፤ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ኃላፊዎችም ሆነ ከገለልተኛ አካላት ማጣራት አልቻለችም።
🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16862/
@EthiopiaInsiderNews
❤ 10👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
ሩሲያ በዋትስአፕ ላይ የገደብ እርምጃዎችን ቀስ በቀስ እየወሰደች መሆኑን አስታወቀች
ሩሲያ ቀስ በቀስ በዋትስአፕ ላይ የገደብ እርምጃዎችን እያስተዋወቀች መሆኑን የሀገሪቱ የኮሙኒኬሽን ተቆጣጣሪ ሮስኮሜንዳዞር አስታውቋል። የሮስኮሜንዳዞር የፕሬስ አገልግሎት መግለጫን በመጥቀስ አርቢኬ የዜና ማሰራጫ እንዳስታወቀው ዋትስአፕ “የሩሲያን ህግ መጣሱን ቀጥሏል” ሲል ዘግቧል።
ከዚህ አንፃር ቀስ በቀስ በዋትስአፕ ላይ ገዳቢ እርምጃዎችን እየተተገበሩ ይገኛል። ይህንኑ ተከትሎ የዋትስ አፕ ጥሪዎች ቀስ በቀስ ማሽቆልቆል የጀመረው በነሐሴ ወር ላይ ነው። በመገናኛ ብዙኃን እንደዘገበው ተጠቃሚዎች ወደ ሌሎች የመልእክት መላላኪያ መተግበሪያዎች እንዲቀይሩ ለማስቻል ቀስ በቀስ እገዳው እየተጀመረ ኑው።
ቀደም ሲል ሰኞ እለት በዋትስአፕ ላይ ወደ 1,600 የሚጠጉ ቅሬታዎች በ24 ሰአታት ውስጥ ቀርበዋል። ተጠቃሚዎች በመተግበሪያው ላይ መቆራረጦችን፣ መልዕክቶችን የመላክ ችግሮች እና የመተግበሪያው እና የድር ጣቢያው ያልተረጋጋ አሠራር ሪፖርት አድርገዋል። ከዚህ ቀደም የዋትስአፕ እና የቴሌግራም ጥሪዎች በሩሲያ ውስጥ “ለደህንነት እና ማጭበርበር ለመከላከል” ተገድበው ነበር። በኖቬምበር መገባደጃ ላይ ሮስኮሜንዳዞር ዋትስአፕ የሩስያ ህግን የማያከብር ከሆነ ሙሉ በሙሉ እንደሚታገድ አስጠንቅቋል።
በስምዖን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
❤ 20
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ27 ቢሊየን ብር በላይ የብድር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዳሉት፤ አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ቦታ ያለው እንዲሆን በማድረግ ረገድ የድርጅቱ ሰራተኞች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
አየር መንገዱ ከዚህ በፊት ለሰራተኞቹ 1 ሺህ 200 ቤቶችን ገንብቶ ማስረከቡን አስታውሰው፤ አሁን ላይ 5 ሺህ ቤቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል ብለዋል።
ይህ የቤት ግንባታ እንዲሳካ ለማድረግ በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ27 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የብድር ስምምነት መፈረሙን ነው የገለጹት።
የብድር ስምምነቱ ለረዥም ዓመታት የዘለቀውን የሁለቱን ተቋማት ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያደርሰው እንደሆነም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ተወካይና የኮርፖሬት አገልግሎቶች ኤክስኪዩቲቭ ምክትል ፕሬዚዳንት ኤፍሬም መኩሪያ በበኩላቸው፤ ባንኩ የብድር አገልግሎትን በበቂ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
በተለይም ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ምቹ ምህዳር ፈጥሯል ነው ያሉት፡፡
በዛሬው ዕለት ከአየር መንገዱ ጋር የተፈረመው ስምምነት ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንደሚያስገኝ ጠቁመው፤ ተቋማቱ በሀገራዊ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራታቸውን እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 23👍 3🤔 3🤪 2
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ እንዳመለከተው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶን ተቀብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክትም፥ በዛሬው ዕለት ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶን ተቀብለው የሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።
ይህም በሰላምና መረጋጋት ለአፍሪካ መር መፍትሔዎችና ለንግግር ያለንን የወል ጽኑ አቋም ያሳያል ነው ያሉት፡፡
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 20🤣 10
Photo unavailableShow in Telegram
🫠ያስደነግጣል
በአፋር ክልል አንዲት ላም ሁለት ራስ ያለውና ፊቱ የሰውን የሚመስል ጥጃ መዉለዷ እየተዘገበ ነው አጀብ ነው የሰው እጅ አለበት ያስብላልኮ።
@seledadotio
@seledadotio
😨 74🤔 13😢 9❤ 8🤣 8🥱 5
Photo unavailableShow in Telegram
የአፈና ዜና‼️
በአማራ ክልል እና በትግራይ ክልል መካከል የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ከሚነሳባቸው ቦታዎች አንዱ በሆነው በራያ አላማጣ ወረዳ ጥሙጋ ቀበሌ እና በአላማጣ ከተማ 04 ቀበሌ ሀርኪሳ ጎጥ ዛሬ ከሌሊቱ 9:30 አጠቃላይ 19 ሰዎች በታጣቂዎች ወደአልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል። ከእነዚህ ታጋቾች ውስጥ ቄስ ካህሳይ ቢወጣ የራያ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ሀላፊ እንደሚገኙበት ምንጮች ገልፀዋል።
@Addis_News
@Addis_News
💔 25❤ 9
40 ቀንና አርባ ሌሊት በሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ጋር የተነጋገረ ድንቅ አባት🙏
እግዚአብሔር ለትልቅ ስራ ያጨው እስራኤልን ከ215 ዓመታት ባርነትና ከ430 ዘመን ስደት በኋላ መርቶ ሀገራቸው ያስገባ ታላቁ ነቢይ ነው፡፡ 40 ቀንና አርባ ሌሊት በሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ጋር የተነጋገረ ድንቅ አባትም ነው፡፡ የአምስት ዓመት ሕጻን ሳለ በሁሉም ዘንድ እጅግ የሚፈራውን ፈርኦንን በጥፊ መታው፡፡ ለንጉሳቸው ትልቅ ቦታ በሚሰጡት ግብጻውያን ዘንድ ድርጊቱ ሕጻን ቢሆንም የሚያስገድል ነበር፡፡ ይሁንና ከውሃ አጊኝታ ልጇ አድርጋ የምታሳድገው የፈርኦን ልጅ ቴርሙት ሕጻን ስለ ሆነ ክፉና ደጉን አይለይም፣ እሳት እንኳ በፊቱ ቢቀመጥ አንስቶ ይበላል ብላ ተከራከረች፡፡ እንደተባለውም የጋለ ፍም ከፊቱ ሲቀመጥ አንስቶ በመጉረሱ ምላሱ ኮልታፋ ቢሆንም ነፍሱ ግን ከሞት ተርፋለች፡፡ ከ12 የያእቆብ ልጆች የእስራኤል ነገዶች አንዱ ከሆነው ከሌዊ ወገን የሚወለደው ሊቀ ነቢያት ሙሴ የስሙ ትርጓሜ “ከውሃ የተገኘ” ማለት ነው፡፡
ቅዱስ ዻውሎስ ለዕብራውያን ክርስቲያኖች በጻፈው መልዕክቱ በምዕራፍ 11÷24 እንዳለው “በአሕዛብ ቤት ካለ ምቾት ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን ሊቀበል ወዷልና” አንድ ግብጻዊ እስራኤላዊ ወገኑን ሲመታ ቢያየው ገድሎ አሸዋ ውስጥ ቀበረው፡፡ በፈርኦን ቤተ መንግስት ቢያድግም ወገኖቹ እስራኤልን አልረሳም፡፡ እናቱ ዮካብድ ሞግዚት ሆና ስላሳደገችው የወገኖቹን ታሪክና ማንነቱን ትነግረው ነበርና 40 ዓመት በሆነው ጊዜ የፈርኦንን ቤት ምቾትና የንጉሥ ልጅ መባልን ናቀ፡፡ በግብጻዊው ላይ ያደረገው ነገር እንደተሰማ ሲያውቅም ወደ ምድያም ሸሸ:: በምድያምም ለ40 ዓመታት የካህኑን ዮቶርን በጐች እየጠበቀ፣ ኢትዮዽያዊቱን ሲፓራን አግብቶ ልጆች አፈራ:: በ80 ዓመቱ እግዚአብሔር በደብረ ሲና ተናገረው፡፡ ሕዝቡንም ከባርነት ቀንበር እንዲታደግ ላከው፡፡
አንደበቱ ኮልታፋ ቢሆንም ወንድሙ አሮን በንግግር እያገዘው ግብጻውያንን በዘጠኝ መቅሰፍትና በአስረኛ “ሞተ በኩር” መትቶ እስራኤላውያንን ነጻ አውጥቷል፡፡ ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት በሚያደርጉት ጉዞ ውስጥም ትልቁን የመሪነት ሚና የተወጣ ሲሆን፣ ባሕር ከፍሎ በደረቅ ያሻገራቸው፣ ለህዝቡ መና ከደመና ያወረደ፣ አለት ከፍሎ ውሃ ያፈለቀ፣ ሌቱን በብርሃን ምሰሶ ቀኑን በሰባት ደመናት ጋርዶ የመራቸው፣ ጠላቶቻቸውን የደመሰሰላቸው እግዚአብሔር መሳሪያው እንዲሆን የመረጠው ታላቅ አባት ነው፡፡ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል እየተራዳው እስራኤላውያን ነጻ ስላወጣቸው አላከበሩትም፤ ይልቁንም ደግመው ደጋግመው አስከፍተውታል፡፡ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሮ “አሰርቱ ትዕዛዛትን” ይዞ ከተራራው ሲወርድ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አሳዝነው ጠበቁት፡፡
ወንድሙ አሮንን አስገድደው ጣኦት አሰርተው ሲያመልኩ፣ ሲበሉ፣ ሲጠጡ፣ በደስታም ሲጨፍሩ ነው ያገኛቸው፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር “እነርሱን ላጥፋቸውና በሌላ ታላቅ ሕዝብ ዘንድ ልሹምህ” ሲለውም፣ “እነርሱን ከምታጠፋቸው እኔን ከጻፍከኝ ከሕይወት መጽሐፍህ ደምስሰኝ ያለ ታላቅ አባት ነው፡፡ በጽላቱ ጣኦቱን መትቶት ሲሰበርም በድጋሚ ጽላቱን በእጁ ሰርቶ አምጥቶ በእግዚአብሔር ጣቶች 10ቱ ትዕዛዛት ተጽፈዋል፡፡ በረከቱ ትደርብንና በየትኛውም ምቾት ውስጥ ብንሆን፣ ክብራችን ከፍ ቢልም ወገንንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አለመርሳት ከአባታችን ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ እንማራለን፡፡
እግዚአብሔር በረከትን እዲያበዛልን፣ ሕይወታችን እንዲባረክ፣ መውጣት መግባታችን የደስታ እንዲሆን በልባችን እንዳሰብን ገዳማውያንን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
❤ 46👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሳዑዲ አረቢያ ከመጪው ጥር 1፣ 2026 ጀምሮ የቤት ሰራተኞች ክፍያ መንግስት በዘረጋው ስርዓት እንዲከፈል ወስናለች።
በሳዑዲ አረቢያ የሚሰሩ የቤት ሰራተኞች ከመጪው ጥር 1፣ 2026 ጀምሮ ክፍያቸውን በተዘረጋው የኤሌክትሮኒክስ ስርዓት እንደሚከፈላቸው ይህም የደመወዝ ጥበቃ እንደሚሰጣቸው እና ግልፀኝነትን እና ጊዜውን የጠበቀ ክፍያ እንዲሰጣቸው እንደሚያደርግ የሃገሪቱ የሰው ሃብት ሚኒስትር አስታውቋል።
ሰራተኞቹ ወቅቱን ጠብቆ ደሞዛቸው በጥሬ ገንዘብ ሳይሆን "ሙሳነድ" በተባለው ሥርዓት የሚከፈላቸው ሲሆን ያገኙትን ገንዘብም በተፈቀዱ መንገዶች ውጪ ላሉ ቤተሰቦቻቸው ማስተላለፍ ይችላሉ።
ሳዑዲ ይህንን ስርዓት ከ2024 ጀምሮ ወደ ስራ ለገቡ አዳዲስ ሰራተኞች መጠቀም የጀመረች ሲሆን የተለያዩ ሂደቶችን ካለፈ በኋላ ከ2026 ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ ይገባል ተብሏል።
በአዲሱ ሥርዓትም ሰራተኞቹ የሂጂራ ወር መጨረሻ ላይ በኮንትራታቸው መሰረት ክፍያቸውን ያገኛሉ ተብሏል።
አዲሱ ሥርዓትም የቤት ሰራተኞች ጊዜውን የጠበቀ ክፍያ እንዲያገኙ በማስቻል ከሚጠብቃቸው መንገላታትና የክፍያ ማጣት ይጠብቃቸዋል።
ዘገባው የዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ ነው።
@Addis_News
@Addis_News
❤ 40👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
♨️የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ Jobs ✅
---—----------------------------
✅ በ0 አመት እና በልምድ
✅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ብቁ ሠራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፣ ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ ከዚህ በታች ያለዉን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ብዛት: ከ20,000 በላይ
ደሞዝ ማራኪ
How To Apply
👇👇👇
🟥 ፈጥነው ታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ
⁉️ ማሳሰቢያ:- VPN ወይም Psiphon መጠቀም ይኖርባችሗል
👇👇👇👇👇Apply Now👇👇👇👇👇👇
👇👇👇👇
https://reportervacancy.com/the-ethiopian-shipping-and-logistics-job-vacancy-2025/
--------Follow Our Website--------
👇👇👇👇👇👇
https://reportervacancy.com
--------Join Our Telegram---------
👇👇👇👇👇
https://t.me/reporter_vacancy
❤ 9
