️ ንስር አማራ🦅
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ። 💚💛❤️ እኛን በውስጥ ለማናገር @NISIREamhra2 @NISIREamhraa_bot 👈 ይችን አድራሻ ይጠቀሙ🦅 ንስር ዐማራ🦅 #የግፉአን_ድምፅ t.me/NISIREamhra
Ko'proq ko'rsatish2025 yil raqamlarda

63 114
Obunachilar
-2124 soatlar
-2237 kunlar
-78730 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
🔥#አይ_አተኳኮስ_እናቴዋ💪
#ፋኖ_ይችላል💪
ዛሬ ቀን ላይ ሰሜን ጎጃም፣ ሰሜን አቸፈር ወረዳ ሊበን ከተማ ውስጥ በተሰራው ፈጣንና ቀልጣፋ ኦፕሬሽን ጠቋሚ ጣታቸውን ( መተኮሻዋን ) ጭምር እያንጠባጠቡ ያመለጡም አሉ።
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
15/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
👍 66❤ 33❤🔥 20🫡 5🏆 4🙏 3
Photo unavailableShow in Telegram
ከአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር የተሰጠ ማስጠንቀቂያ!
የመካነሰላም ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ካድሬዎች መሬት እየቆረሱ ለባለሀብቶች በጫረታ መልኩ አቅርበው ገንዘቡን የፋሽስቱ አብይ አህመድን ስርዓት እድሜ ማራዘሚያ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን የውስጥ ምንጮች ካደረሱን ጥቆማ ለመረዳት ችለናል::
ካድሬዎች በፕሮፓጋንዳ ብዛት አደናግረው እና በሆድ እየገዙ ከጎናቸው ያሰለፏቸው የፀጥታ ኃይል አባላት ፍላጎት በየጊዜው እያደገ በመምጣቱ የተነሳ እነሱን በሆዳቸው እየገዙ ለማቆየት አስበው የወጣቶች መዝናኛ ስፍራን እና የቀበሌ መኖሪያ ሰፈርን ለባለሀብት በጫረታ ለመሸጥ ካቢኔው አቋም መያዙ ተደርሶበታል::
ከተማይቱ ክልል ውስጥ 03 ቀበሌ የሚገኘው የወጣቶች መዝናኛ ማለትም የስፓርት ቦታ የሆነውን እና የክፍለ ከተማይቱ ውበት ተደርጎ የሚቆጠረውን ሜዳ ለጫረታ አቅርበውታል:: ይህን ብቻ ሳይሆን 02 ቀበሌ በተለምዶ ቲቲአይ ሰፈር ንጋት ፋርማሲ ፊት ለፊት የሚገኘውን ቦታ እና ቀበሌ 01 ጤና ጣቢያ አቅራቢያ ደግሞ የቀበሌ መኖሪያ ቤቶችን ነው ለጫረታ ያሰቧቸው:: በዚህ ምክንያት የቀበሌ ቤት ይኖሩ የነበሩ የድሀ ድሀዎች ልቀቁ ተብለው ከተማይቱ ዳር ወደሚገኘው ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሄደው በቅጥር ግቢው ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ነው ለማረጋገጥ የቻልነው::
የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር እንዲህ አይነት የመሬት ችርቻሮን በጥብቅ የሚያወግዝ ሲሆን በተጫራቾች ላይ ጭምር እርምጃ ከመውሰድ እንደማይቆጠብ ከወዲሁ ያሳስባል::
ስለዚህ በጫረታው ላይ ለመሳተፍ ያሰባችሁ ባለሀብቶች ከወዲሁ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እያሳሰብን ይህን ማስጠንቀቂያ ችላ ብላችሁ በጫረታው ብትሳተፉ ለሚሊሻ ቀለብ እንደሰፈራችሁ ቆጥረነው በእናንተ ላይ ጭምር የማያዳግም እርምጃ እንደምንወስድ እንድታውቁት ይሁን::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም
❤ 70👍 10
🔥206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ እና የጅበላ ሙተራ ሻለቃ ባደረጉት ታላቅ ተጋድሎ ጀብድ ተሰርቷል‼️
ህዳር 15/ 2018 ዓ.ም
የአረመኔው ሰራዊት ከደብረ ኤሊያስ፣ደብረ ማርቆስ እና አማኑኤል ከተሞች በመነሳት ወደ ተርቸከል ሊባኖስ በሶስት አቅጣጫ 8 ዲሽቃ በያዘ ኃይል በመድፍ የታገዘ ጥቃት ለመሰንዘር ቢንቀሳቀስም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በተደረገበት የደፈጣ ጥቃትና መደበኛ ውጊያ በርካታ የሰራዊት አባላት ተደምስሰዋል።
የማዕከላዊ ዕዝ 602ኛ ኮር 32ኛ ክ/ጦርን በተወርዋሪነት የተጠቀመው የአረመኔው ሰራዊት ተጨማሪ ድጋፍ ሰጭ ይዞ ቢንቀሳቀስም በሁለት ግንባር በተከፈተበት ውጊያ ትስስሩ ተቋርጦ ወደኋላ አፈግፍጓል።
ጨለማን ከለላ በማድረግ ስምሪቱን ያደረገው ጠላት በቴዎድሮስ ዕዝ በ206 ኮር የ14ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ ቸርተከል ላይ ባደረገችው የደፈጣ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ ሲሆን በሊባኖስ ግምባር ደምባ ላይ ከፍተኛ ትንቅንቅ የፈፀመችው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ አስደናቂ ጀብድ ፈፅማለች።
በቸርተከሉ ውጊያ ጠላት ተቀጥቅጦ ወደ ኋላ ሲመለስ አስክሬኑን ቀብሮ በአንድ አምቡላንስ እና ፓትሮል ቁስለኛውን ተሸክሞ ፈርጥጧል። የወገን ኃይል ታላቅ ጀብድ የፈፀመበት ደምባ እስከ ምሽት 12:00 አውደ ውጊያው ቀጥሎ የጠላት ሁለት የጦር አመራሮች ተደምስሰዋል ።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
©የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
15/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 85👍 35😡 4🙏 3🏆 3
🔥#የልዩ_ኮማንዶዎች_የምረቃ_ቪዲዬ‼️
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለጦር ለስድስት ወራቶት ያሰለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ‼️
የምረቃውን ወታደራዊ ትርዒት በዩቱዩብ አድራሻችን ይመልከቱ👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/pxFt4LxwuS0?si=ILjg1o1plBaxXG_0
👍 48❤ 35
🔥Statement Issued By Amhara Fano National Force (AFNF)‼️
❤ 47👍 22😢 1
🔥ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የተሰጠ መግለጫ‼️
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
15/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 54👍 11🙏 6😍 4
🔥ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የተሰጠ መግለጫ‼️
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
15/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 1
🔥መብረቅ ክፍለጦር ለስድስት ወራቶት ያሰለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ‼️
ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለጦር ለስድስት ወራቶች ያሰለጠናቸውን በርካታ ቁጥር ያላቸው ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች ህዳር 14/2018 ዓ.ም በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል::
ምኒልክ ዕዝ አደረጃጀቱን በማዘመን የህልውና ትግሉን አጠናክሮ እየታገለ ያለ ሲሆን ሰራዊቱን በመደበኛ እና በልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች ደረጃ በሰው ሃይል እና በጦር መሳሪያ ማጠናከሩን በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራበት ይገኛል::
መብረቅ ክፍለጦር ባለፉት ጊዜያት ተደጋጋሚ ስልጠናዎችን በመስጠት ሰራዊት እያስመረቀ ራሱን በሰው ሃይል አጠናክሮ የመጣ ሲሆን ዛሬም በርካታ ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎችን በማስመረቅ የቀደመ ተግባሩን እያስቀጠለ ይገኛል::
"እየሰለጠንን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!"
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ስልጠና መምሪያ ክፍል
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
15/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 76👍 19😢 1
🔥የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት በቡግና ወረዳ ህዝብ ላይ አሰቃቂና ዘግናኝ ድርጊት ፈፀመ‼️
በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር እና ከብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት፣አድማ ብተና፣ፖሊስና ሚሊሻ መካከል ከባድ ትንቅንቅ ላይ መቆየታችን ይታወቃል።
ስለሆነም ይህ አማራ ጠል የማፊያ ስብስብ 61ኛና 65ኛ ክፍለ ጦር፣ፖሊስ፣አድማ ብተናና ሚሊሻ ሦስት ዙ-23፣አንድ መድፍ፣አራት ባለ 82 ሞርተር፣አንድ ባለ 120 ሞርተር በመያዝ በምድር ሲገረፍ አልበቃው ብሎ በሰማይ ድሮን ቱርክ ሰራሽ ባይራክታር ቲቪ-2 በማሰለፍ አንድም ፋኖ ሳይጎዳ በዘመቻ አደም አሊ (አባ ናደው) ግዳን ወረዳ ሙጃ ማርያም ከተማ ላይ በፋኖ ተማርከው ህክምና ሲያገኙ የነበሩትን እነ ኮሎኔል ዘሪሁን ማሙየን ጨምሮ ሌሎች ሰባት ንፁሃንን መጨፍጨፉን ከዚህ በፊት መረጃ ማድረሳችን ይታወቃል።
ይህ የመዋጋት አቅምና ሞራል የሌለው የትሮይ ፈረስ ሠራዊት የከባድ መሳሪያ ቅምቡላዎችን በዘፈቀደ በመወርወር ማህበረሰቡ ላይ፣እንስሳቶቹ ላይ፣ሰብሉ ላይ እያረፈ እንስሳትን፣ንፁሃን ዜጎችን እየገደለ የገበሬውን ክምር እያቃጠለ የማህበረሰባችን አንገት እያስደፋ በመሆኑ ገበሬው ለፍቶ እንዳለፋ እንዳይሆን ባደረግነው ለተወሰኑ ቀናቶች ገዥ መሬቶችን ወይም ገዥ ቦታዎችን የያዝን ሲሆን ነገር ግን የአማራን ህዝብ እንደ ግሪሳ እያደቀቀ የሚገኘው የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ከሰሞኑ በቡግና ወረዳ ህዝብ ላይ አሰቃቂና ዘግናኝ ድርጊት እየፈፀመ ይገኛል።
መነሻውን ከቡግና ወረዳ አይና ከተማ በማድረግ 08 ቀበሌ ቅዱስ ሐርቤ በመሄድ አማራ ጠሉ የብልፅግና ሰራዊት "የፋኖ እህል ነው" በማለት በባንክ ብድር የሚሰራውን የአንድ ምስኪን ነጋዴ 30 ኩንታል ቦሎቄና 35 ኩንታል ባቄላ ወደ ከተማ ጭኖ ወስዶ ለመሸጥ ባጠራቀመበት መጋዘን ጭነው ወስደውበታል። የተዘጉ ሱቆችንም በመክፈት ዶሮ ብታልም ጥሬዋንእንዲሉ፤ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው በሚል እንደ ህፃን ልጅ ከረሜላ፣ጆሊጁስ፣ጭማቂ፣ብስኩትና የተለያዩ የሱቅ ዕቃዎችን ሱቆችን እየሰባበሩ በልተው የተረፈውን ውጭ ላይ አውጥተው መድፋታቸው፣ እዛው ቅዱስ ሐርቤ ቀበሌ ላይ የአባት አርበኛ ቤት ነው እያሉ ወደ ማህበረሰቡ ውስጥ በመግባት ሁለት ልጃገረዶችንና አንድ የአባውራ ሚስትን ደፍረው ሂደዋል።
በዚህም የዘራፊነትና ሴሰኝነት ጥሙ አልረካ ያለው ጋለምታ የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት 010 ቀበሌ ቋሮ በመሄድ አማራን እንኳን ትጥቁን ቀበቶውን እናስፈታዋለን ብሎ ወደ አማራ ክልል ዘው ብሎ የገባው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት የ78 እና የ84 ዓመት አዛውንቶችን በካራማራ ጦርነት የተሳተፉ አርበኞችን ማስታወሻ ጓንዴና ውጅግራ መሳሪያ የአሁኑ አባት አርበኞች መሳሪያ ነው በማለት ሲወስዱባቸው የግለሰብ ቤት እየጎረጎሩ ቋጠሮ እህል ሳይቀር ከእጅ ወደ አፍ በልቶ የማያድር ማህበረሰብን ረሃብ ላይ ያለ በዕርዳታ ያገኘውን እህል ሳይቀር በመኪና ደርድሮ ጭኖ መውሰዱና ሊጋገር የተዘጋጀ የተቦካ ሊጥ ሳይቀር ቋሮ ቀበሌ ላይ አውጥተው ደፍተዋል።
የግፍ ፅዋ ሞልቶ እንዲሉ እዚያው 010 ቀበሌ ቋሮ ላይ የፋኖ ቤተሰቦች ናቸው በማለት የትግላችን ችቦ ለኳሽ የአሳምነው ፅጌ የበኩር ልጅ አብሪ ኮኮባችን የሆነውን የአርበኛ ኮማንዶ ሃምሳ አለቃ ፍቅሩ ሙሉዬ እናት ቤት በመሔድ እርሳቸውን ሲያጧቸው አጥሩንና ቤታቸውን በማቃጠልና ንብረታቸውን በማውደም የሌሎቹንም አርበኞች ቤተሰቦች ቤትና ንብረት በእሳት እንዲጋይና እንዲወድም አድርገዋል፤ በተያያዘም አንድ የአባውራ ሚስት ለሁለት ደፍረው የእነ ፍቅሩ ሀገር ነው እያሉ የእህቶቻችንን አንገት አስደፍተው ሂደዋል።
ፋኖን መግጠም ሲያቅታቸው ሲቪል ማህበረሰቡ ላይ ግፍ መፈፀማቸውን የቀጠሉበት ሲሆን አይና እየሱስ ከተማ ላይ አንዲትን ሴት ለሦስት የደፈሯት ሲሆን መሠረት የሚባልን የአዕምሮ ህመምተኛን ወጣት የፋኖ መረጃ ነህ በሚል ተልካሻ ምክኒያት በማንበርከክ በስምንት ጥይት ደረቱና ጭንቅላቱ ላይ አከታትለው በመተኮስ ረሽነውታል።
የአይና እየሱስ ቤተ-ክርስቲያን መጠበቂያ የነበረ ከአፄ ያለው ዘመነ መንግስት ጀምሮ የነበረን ጓንዴ መሳሪያ አሁን ላይ ቤተ-ክርስቲያኗ በቅርስነት ያስቀመጠችውን የቤተ-ክርስቲያኗን ክብርና ስርዓት በሚያንቋሽሽ መልኩ በከስክስ ጫማ ለምዕመኗ እንኳን የማይፈቀደውን ቤተ-መቅደሷ ድረስ በመግባት የወሰዱት መሆኑና የቤተ-ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ውስጥም መካነ ቀብር ሳይቀር ሁሉ እየቆፈሩና እያስቆፈሩ ፋኖ የደበቀውን እናገኛለን እያሉ ትኩስ መካነ መቃብር እየፈነቀሉ ከአማራ ማህበረሰብ ዕሴት ባፈነገጠ መልኩ የሙታንን ነፍስ ዕረፍት እየነሱ ይገኛሉ።
በመጨረሻም ከ500 ዓመት በኋላ ዘርህ፣ማንነትህ፣ዕሴትህ፣ባህልህና ወግህ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ የተፈረደብህ የአማራ ህዝብ ሆይ የግፍ ፅዋው ሞልቶ እየፈሰሰ መሆኑን የተረዳኸው ሲሆን እኛ ልጆችህ የጄኔራል አሳምነው ፅጌ እስትንፋሶች፣የአፄ ምኒልክ፣የአፄ ቴዎድሮስና የአርበኛ በላይ ዘለቀ ወራሽ የልጅ ልጆች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የብልፅግናንና ጄሌዎቹን እስትንፋስ ለመቁረጥና የህዝባችንን ዕምባ የምናብስበት ቀን ቅርብ መሆኑንን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን ሲሉ በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የግዙፉ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ምክትል አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ሃምሳ አለቃ ፍቅሩ ሙሉዬ አሳስበዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
15/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 63👍 20💔 11😢 4🎉 2
⛔️በቀን14/03/2018 በሰው በላው የአብይ አህመድ ወራሪ ሀይል የተጨፈጨፉ ንጹሀን ስም ዝርዝር‼️
===========
1.አቶ ደሴ ካሳ፤ እድሜ 60፤ የትውልድ ቦታ ሰከላ ወረዳ አቻይታ ቀበሌ ድማማ ንዑስ ቀበሌ ስራ አርሶ አደር
2.አቶ ወርቄ ገረም፤ ዕድሜ 45፤ የትውልድ ቦታ ሰከላ ወረዳ አቻይታ ቀበሌ ድማማ ንዑስ ቀበሌ ስራ አርሶ አደር
3.ተመስገን በላይነህ፤ ዕድሜ 30፤የትውልድ ቦታ ሰከላ ወረዳ አቻይታ ቀበሌ እንድባ ንዑስ ቀበሌ ስራ አርሶ አደር
4.ዋሴ መኩሪያ፤ ዕድሜ 26፤ የትውልድ ቦታ ሰከላ ወረዳ አቻይታ ቀበሌ እንድባ ንዑስ ቀበሌ ስራ አርሶ አደር
5. አለኸኝ ክንዴ፤ ዕድሜ 27፤ የትውልድ ቦታ ሰከላ ወረዳ አቻይታ ቀበሌ እንድባ ንዑስ ቀበሌ ስራ አርሶ አደር
6. አማኑኤል አዲስ፤ ዕድሜ 20፤ የትውልድ ቦታ ሰከላ ወረዳ አቻይታ ቀበሌ እንድባ ንዑስ ቀበሌ ስራ አርሶ አደር
7. ቻሌ ፈንታሁን፤ ዕድሜ 24፤ የትውልድ ቦታ ቲሊሊ ወረዳ አሽፋ ማርያም ቀበሌ ስራ ባጃጅ ሹፌር
©የቻለ አድማሱ
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
15/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 70💔 40😢 21🙏 7👍 2
🔥#የአቋም_መግለጫ🔥
==========+
ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ለመላው የአማራ ህዝብ ፣ ለመላው የትግሉ ደጋፊ እና ለመላው የአማራ ፋኖ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል( አፋብኃ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ 4ኛ ደጅ አዝማች ኮር በአምስት ክፍለ ጦሮች ከተመሠረተ ጊዜ አንስቶ በታላቅ ተጋድሎ ጎዳና ይገኛል። ፋሺስት ፣ ወራሪው የብልፅግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ሁሉን ዓቀፍ መዋቅራዊ ግፍ እና በሌሎችም ብሔርብሔረሰቦች ላይ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ኪሳራ እያደረሰ ይገኛል።
በአማራ ህዝብ ላይ ዘርን መሠረት ያደረገውን ጭፍጨፋ የአማራ ህዝብ እንደህዝብ በሠላማዊ መንገድ ጭፍጨፋዊ እንዲቆም ቢጠይቅም አገዛዙ ጭፍጨፋውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ጠያቂውን ደግሞ በአፈሙዝ ምላሽ ሰጥቶታል። ሁሉም የሰላማዊ መንገድ አማራጮች በአገዛዙ መዘጋታቸውን ያየው ፋኖ ዱር ቤቴ በማለት ጨፍጫፊዎችን በመጡበት አግባብ እያስተናገደ ይገኛል።
የአፋብኃ እና የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ለኮርና ለክፍለ ጦር አመራሮች ከጥቅምት 20/02/2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 13/03/2018 ዓ /ም ለተከታታይ 23 ቀን ሲሰጥ የቆየው አጫጭር ተቋማዊ ስልጠናዎች ማለትም ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስልጠናዎችን የወሰድን ሲሆን እንዲሁም ከዚህ በፊት በነበረ የትግል ጉዟችን የነበሩትን ጠንካራ እና ተግዳሮቶቻችንን በመገምገም ከዚህ በተጨማሪም ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ፣ ከአፋሪካ እና ከዓለም ዓቀፍ ሀገራት ጋር የሠራውን ዲፖሎማሲ በመገምገም እና በቀጣይ ለምናደርጋቸው ጉዟችንን አቅጣጫ በመስጠት ባለ 9 ነጥብ የአቋም በመግለጫ በማውጣት መድረኩ ተጠናቋል።
1ኛ. እኛ የኮርና የክፍለ ጦር አመራሮች በአፋብኃ እና በዕዝ ከፍተኛ አመራሮች የተሠጡንን ተቋማዊ ግዴታዎች፣ ተልዕኮዎች ለመፈፀም እና ድርጅታችንን አፋብኃን ለመጠበቅ በሙሉ ዝግጅት ላይ እንገኛለን። አጠናክረንም እንቀጥላለን።
2ኛ. ከፍተኞ አመራሮቹ በተከታታይ ሲሰጡት የሰነበቱትን ስልጠናዎች እስከ ብርጌድ አመራሮች ፣ ሻለቃ አመራሮች እና አባላት በማድረስ አንድ አይነት አመለካከት ፣ ግንዛቤ እና እውቀት እንዲኖረን እናደርጋለን።
3ኛ. ፋሺስቱ፣ ወራሪው ፣ ዘራፊው የብልፅግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን መዋቅራዊ የዘር ማፅዳት ዘመቻ ከህዝባችን ጋር በመሆን እኛ ፋኖዎች እንመክታለን።
4ኛ. ደመኛ ጠላቶቻችን ፋኖ ገዳይ ነው፣ ፋኖ ዘራፊ ነው፣ ሌሎች ብሔርብሔረሰቦችን ገፊ ነው ፣ የድሮ ስርዓት ናፋቂ ነው እያለ የሚሠራውን ትርክት የሀሰት ትርክት ሲሆን በአማራ ህዝብ ላይ የጀመረው ሁሉን ዓቀፍ ወረራ በመግደልና በማፈናቀል ሌሎችም ብሔርብሔረሰቦች በእቅድ የሚያስቀጥልና ራሱ ገዳይ መሆኑ የጊዜ ጉዳይ እንጅ በራሱ ጊዜ ይገለጣል። ስለዚህ ይሄን ስርዓት ከስረ መሠረቱ ነቅሎ ለመጣል ከፋኖ ጎን እንድትቆሙ ጥሪ እያስተላለፍን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩል ዓይን የሚያይ ስርዓተ መንግስት እናቆማለን።
5ኛ. በፋሺስቱ፣ በወራሪው፣ በዘራፊው የብልፅግና አገዛዝ መዋቅር ውስጥ እያገለገላችሁ የምትገኙ ከተራ አባል እስከ ላይኛው ወታደራዊ እርከን ያላችሁ ከህዝባችሁ ይልቅ ለጊዜአዊ ጥቅም ብላችሁ ባንዳነትን የመረጣችሁ ከዚህ በፊት ባደረግንላችሁ ጥሪ መሠረት በርካቶች ፋኖን ተቀላቅላችሁ እየተገላችሁ ያላችሁ ሲሆን አሁንም በጠላት መዋቅር ውስጥ ያላችሁ የበደላችሁትን ህዝብ ለመካስ ፋኖን ተቀላቅላችሁ እንድትታገሉ ጥሪ እናስተላልፋለን።
6ኛ. በውጭና በሀገር ውስጥ ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን የትግላችን ደጋፊዎች በሙሉ የፋኖ ትግል በአጭር ጊዜ ይቋጭ ዘንድ በፋይናንስ፣ በዲፕሎማሲ እና በእውቀት ሽግግር እንድታግዙ ጥሪ እናስተላልፋለን።
7ኛ. ለሚዲያ ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ሙሁራኖች፣ አንቂዎች ፣ለሚዲያ ተጠቃሚዎች በሙሉ በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን መዋቅራዊ ሰብአዊ ፣ ቁሳዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በአንድነት ሁናችሁ እንድታሳውቁ ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን።
8ኛ. ከወራሪው፣ ከጨፍጫፊው፣ ከዘራፊው የብልፅግና አገዛዝ የፀጥታ መዋቅርና የፖለቲካ ክንፍ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እና ተልዕኮ በመቀበል በየአውራ መንገዶች ህዝባችንን የምትዘርፉ፣ የምታግቱ፣ የምታንገላቱ በውስጣችን ያላችሁ እንዲሁም "አፈንጋጭ" የሚል የዳቦ ስም ያላችሁ የመዋቅራችን የመረጃ ክፍል ባከሄደው ጥናት አረጋግጧል። በትልልቅ ከተሞች ማለትም በባህርዳር በጎንደር ከተማ ሳይቀር ከአገዛዙ ጋር ተናባችሁ የእገታ፣ የዘረፋ፣ የግድያ ወንጀል እንደሚፈፅሙ ተደርሶባቸዋል። ይህን የምታደርጉ አካሎች ከፋሺስቱ አገዛዝ በላይ ጠላት መሆናችሁን በማመን ከድርጊታችሁ በማትታቀቡት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን።
9ኛ. በአጠቃላይ የአማራ ፋኖ አንድ ጎጆ እንዲሠራ እንጅ ሁለት አማራ ስለሌለ እንድ ቤት እንድንገነባ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናበረክታለን።
ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለአማራ ለፋኖ
©አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
4ኛ ደጃዝማች ኮር
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
15/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 135👍 33🙏 7🫡 7💔 5🎉 2🏆 2
⚫️#እጅግ_አሳዛኝ_ጭፍጨፋ⚫️
በሰከላ ወረዳ አጉት ቀበሌ ስድስት ንፁኋን በአገዛዙ ወታደሮች ተገደሉ!
የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን መከላከያ ሰራዊት ሰከላ ወረዳ አጉት ቀበሌ ስድስት ንፁኃንን አፍኖ በመውሰ በቀበሌው ድጥልም ትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ፣ ብልታቸውንና ምላሳቸውን ከቆረጠ በኋላ ገድሏቸዋል።
#ለታሪክ_ይቀመጥ‼️
በግፍ ለተጨፈጨፉት ወገኖቻችን ነፍስ ይማር😭
💔 143😢 79❤ 71👍 19🙏 9
🔥አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር በጥላት ላይ ታላቅ ድልን ተቀናጅቷል‼️
የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር ከፋሽስቱ ሰራዊት ጋር በተደረገ የሶስት ሰዓት ቆይታ የሸፈነ አውደ ውጊያ ቁጥሩ በውል ያልታዎቀ የፋሽስቱ ሰራዊት የተደመሰሰ ሲሆን በርካታ ቁስለኛም ወደ ወገልጤና ከተማ ፋሽስቱ አጓጉዟል።
ሞትና ጥፋት ተፈጥሯዊ ፀጋው የሆነው የብልፅግና
የዱርየዎች ስብስብ ህዳር 14/2018 ዓ/ም በደላንታ ወረዳ ፀሀይ መውጫ በስቃ አቦ ላይ ተቀጥቅጧል።ከጠዋቱ 12:00 እስከ ረፋድ 3:00 ሰዓት በዘለቀው አውደ ውጊያ በርካታ ቅጥረኛ ሰራዊቶቹ የተመቱበት የፋሽስቱ ቡድን እግሬ አውጭኝ በማለት ወደ ወገልጤና ከተማ ፈርጥጧል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ መምሪያ
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
14/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 77👍 16🏆 6
⚫️ዘር አጥፊው አረመኔው የመከላከያ ሃይል ስድስት ንፁሃንን ምላስና ብልት ቆርጦ ረሽነ‼
በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር በተደረገ ተጋድሎ ብዛት ያላቸዉ ጥቁር ክላሾችና ተተኳሽ ሲማረኩ፣ከሀያ በላይ የአሸባሪው ቡድን አባላት ተወግደዋል ።
ዛሬ ህዳር 14/2018 ዓ.ም ከሰከላና ከቡሬ በሁለት አቅጣጫ በለሊቱ በመንቀሳቀስ ለማፈን የሞከረዉ አረመኔ ቡድን በመልሶ ከበባ ተቀጥቅጧል።
ከአጉት እስከ አሽፋ በዘለቀዉ አዉደ ዉጊያ ጨፍጫፊና ዘራፊው መንግስታዊ ቡድን ሙትና ቁስለኛው እያዝረከረከ፣ በየ ጥሻው እየቀበራቸዉ፣ ያሰበዉን ሳያሳካ የጀግናው ፋኖን ምት መቋቋም ባለመቻሉ የጣለዉን እየጣለ ዉንብሪ ማሪያም ተብላ ምትጠራዉ ቅድስት ቤተክርስቲያን ዉስጥ በመመሸግ እንዳይወጣ ሁኖ ተከቦ ይገኛል።
በአጽኖት አስበው፣ ትርፍና ኪሳራ አገናዝበው የሚንቀሳቀሱት የግዙፉ 44ኛ ክፍለ ጦር ጀግኖች ጥበብ አማካኝነት ተስቦ የገባዉ ዘራፊ ቡድን በከበባ ተቀጥቅጦ በደርዘን የሚቆጠር ክላሽ አስረክቦ 21 ሬሳና ብዛት ያላቸዉ ቁስለኞቹን ተሸክሞ በቅድስቷ ቤተክርስቲያን መሽጎ ይገኛል።
የጀግኖቹን ምት መቋቋም ያልቻለዉ ወንበዴ ቡድን በየአካባቢው ያገኛቸዉን ንፁሐን አርሶ አደር እና የከተማ ወጣቶችን አፍኖ በመዉሰድ ስድስቶችን አይናቸዉን በማጥፋት፣ ምላሳቸዉንና ብልታቸዉን በመቁረጥ አሰቃቄ በሆነ ሁኔታ ረሽኗቸዋል።
"በተመታን ቁጥር አማራን የሆነዉን ሁሉ ህፃን አዛውን ሳንለይ እንመታለን" እያለ ሲያውጅ የከረመዉ አረመኔ ቡድን፤ ፎክሮ ወደ ፋኖ ቀጠና ፋኖን ለማጥቃት ቢመጣም ውጤቱ አባሉን እያንጠባጠበ ፣ ንብረቱን እያስረከበ ንፁሃን ላይ ጉልበቱን በማሳየት የለመደዉን የዘር ማጥፋት እርምጃዉን አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
#ትግላችን_እስከ_ቀራኒዮ_ድላችን_4ኪሎ_ይዘልቃል‼
©የ44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኘነት
ፋኖ አለበል አወቀ።
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
14/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 105💔 15🙏 13🏆 8👍 7
🔥#ከበባው_ተሰባብሯል💪
የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ዋሲል ክፍለ ጦር 3ተኛ መብረቅ ሻለቃ ኃይልን ለማፈን የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር ሰራዊት በምዕራብ ወሎ ግንባር ጃማ ወረዳ ቀይ አፈር ታዳጊ ከተማ ውስጥ ሌሊቱን ከበባ የፈፀመ ቢሆንም እነ ሞት አይፈሬ ጥይት አዝንበውበት ከባድ ሰብአዊ ኪሳራ በጠላት ላይ አድርሰው በጀግንነት በመውጣት ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
የ3ኛ መብረቅ ሻለቃ የተወሰነ ኃይል ከተማይቱ ውስጥ መኖሩን በመረጃ ሰዎቹ አማካኝነት ያረጋገጠው ጠላት ስፍር ቁጥር የሌለው መከላከያ ሰራዊት፣ አድማ ብተና፣ ፓሊስ እና ሰላም አስከባሪዎችን አሰልፎ በሌሊት ከበባ ቢፈፅምም እነ ሞት አይፈሬ በተወሰነ ኃይል ብቻ በርካታ ጠላት በመምታት ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈጽመዋል::
የጃማ ወረዳ መቀመጫ ከሆነችው ደጎሎ ከተማ 2 አምቡላንሶች ወደ ቀይ አፈር ተጉዘው የጠላትን አስከሬን እና ቁስለኛውን ጭነው መመለሳቸውም ታውቋል:: አሁን አመሻሽ ላይ ጭምር አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል አስከሬን ስንዴ ማሳ ውስጥ መገኘቱን ምንጮች ጠቁመዋል:: በዛሬው ውጊያ በድምሩ ከ10 ያላነሰ የጠላት ኃይል መመታቱ ተረጋግጧል::
የ3ተኛ ሻለቃ ብሬን ተኳሹ አርበኛ ሙሀመድ ጀማል በጀግንነት ተፋልሞ ሙሉ ኃይሉን ይዞ መውጣት የቻለ ሲሆን በዚሁ ውጊያ አርበኛ ሼህ አሊ ሀሰን ገነቴ የተባለ ጀግናም እጅ ስጥ ያሉትን የጠላት ኃይል አባላት እረፍርፎ ጥሶ መውጣት ችላል:: "እኔ የአሳምነው ልጅ ነኝ እጅ አልሰጥም" በማለት በጣጥሷቸው የወጣው አርበኛ ሼህ አሊ ሀሰን ከዚህ ቀደም የአማራ ልዩ ኃይል መክት ክፍለ ጦር አባል የነበረና በፋኖ ትግል ሂደትም በሸዋ እና በወሎ ቤተ አምሓራ ግንባሮች የጦር ሜዳ ጀብዱ ሲፈፅም የከረመ መሆኑን ነው ለማረጋገጥ የቻልነው::
የጠላት ኃይል የ3ተኛ መብረቅ ሻለቃ ብሬን ተካሽ የሆነውን አርበኛ ሙሀመድ ጀማልንም ለማፈን ጥረት ያደረገና እጅ ስጥ ያለ ቢሆንም አርበኛውም "አላስለመድንም" በማለት ብሬኑን አንስቶ ግራ ቀኝ እሳት በማዝነብ ከበባ ሊሰብር ችሏል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
14/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 123👍 35👏 5🫡 4💔 1
🔥እራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት በአግባቡ ተወቃ‼️
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ክ/ጦር በኢንጅነር ልጆች ሲወቃ አረፈደ። ባለፈው በ12.03.2018 ዓ.ም በደምበጫ ወረዳ ዋድ እና አካባቢውን ለመውረር በሶስት አቅጢጫ ቢንቀሳቀስም በደምበጫ ፋኖዎች መመከት መቻሉን መዘገባችን ይታወቃል።
የፋኖን በትር መቋቋም ያልቻለ ራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሰየመ የእናት ጡት ነካሽ አራዊት ሰራዊት በቀን 12.03.2018 ዓ.ም ባጣው ሰራዊት ላይ በመተካት እና መጠነ ሰፊ የሰው ሀይል እና ዙ23 በመያዝ በጭፍን ፖለቲካ ሰክሮ በአደንዛዠ እፅ ደንዝዞ ከዋድ ወደ የዘለቃ እንቅስቃሴ እያደረገ ሁለት ሞተሮቹን አቃጥለ።
በሞተሮች መቃጠል የፋኖን እንቅስቃሴ የገታሁ የመሰለው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት #አስቴቦጅ እና #አኳትማ በሚባል ቦታ ፈንጠዝያ ላይ እያለ #በሻለቃ_ይርሳው_ደምስ እየተመራ የገባው 99ኛ ክ/ጦር #የኢንጅነር_ክበር_ተመስገን ልጆች እሬሳና ቁስለኛ ብቻ አድርገውታል ።''ስጭኝ ያለሁሽ በርበሬ የሰጠሽኝ ቃርያ '' እንዳሉት አባቶች ፋኖ ሌላ ንፁኃን ማንገላታት ሌላ ።
ድል ለፋኖ ድል ለአማራ ሕዝብ ድል ለተገፉ ኢትዮጵያውያን!!!
©አፋብኃ 109ኛ ኮር 99ከ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ።
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
14/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 84👍 17👏 6
🔥#የድሮን_ጥቃት_ወግዲ_ቀጠና‼️
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ የድሮን ጥቃት ፈፅሟል::
ፀረ-አማራው የአብይ አህመዱ አገዛዝ ዛሬ ህዳር 14/2018 ዓ.ም ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ አብዩ ጎርባ የተባለች ታዳጊ ከተማ ላይ ባይራክታር ቲቢ2 (Bayraktar TB2) በተባለ ቱርክ ሰራሽ ድሮን ጥቃት የፈፀመ ሲሆን ጥቃቱ የተፈፀመው በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ነው::
የድሮን ጥቃቱ ከቀኑ 8:10 አካባቢ የተፈፀመ ሲሆን ጥቃቱ የተፈፀመበት ግለሰብ ሁኔታውን ሲገልፅ፦ ወትሮ እኔም ሆነ ባለቤቴ ቤታችንን አለቅም ነበር ዛሬ ማለዳ ግን አላህ በምክንያት ትረፍ ሲለኝ ባለቤቴ አባታቸው ስለታመሙ ጠይቀሻቸው ነይ አልኳትና ሄደች:: እኔም ለአጨዳ የደረሰ ጤፍ ስላለኝ እሱን ለማየት ወደ እርሻየ ሄድኩኝ ይላል በሁኔታው እየተገረመ:: በጥቃቱ ቤትና ንብረቱ ወድሟል::
ስለሆነም ድሮን በጣም የረቀቀ ቴክኖዎሎጂና ማጥቃት ያለበትን ለይቶ የሚያውቅ ቢሆንም የብልፅግናው አገዛዝ ግን በዚህ መልኩ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት በመፈፀም የታጠቀውን ፋኖን ሳይሆን የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ እየጨፈጨፈ ይገኛል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
14/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
1.40 MB
9.06 KB
2.12 MB
❤ 68💔 62👍 12😢 7
Photo unavailableShow in Telegram
🔥#ደብረብርሃን_ዩንቨርስቲ ‼️
ደብረብርሃን ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በአገዛዙ ኃይል (በፌደራል ፖሊስ ) በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ሁኔታ እየተደበደቡ ይገኛሉ ። ድምፅ ሁኑንን አገዛዙ እያሰቃየን ይገኛል ሲሉ የዩንቨርስቲው ተማሪዎች ለንስር አማራ በላኩት መልዕክት ገልፀዋል‼️
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
14/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
😢 88❤ 40👍 33💔 5
Photo unavailableShow in Telegram
🩸#መተከል_የደም_መሬት🩸
መተከል ቡለን ወረዳ ላይ 50 የሚደርሱ ንፁኋኖች ተገደሉ!
በቡለን ወረዳ ልዩ ስሙ በኩጂ በተባለ አከባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በፈፀሙት የጅምላ ግድያ 50 የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች መገደላቸው ተሰምቷል።
በአከባቢው የነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ከሁለት ቀናት በፊት አከባቢውን ለቀው ከመውጣታቸው ነው ጥቃቱ የተፈፀመው የሚሉት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ ታጣቂዎቹ ከአገዛዙ ሰዎች ጋር በመናበብ የፈፀሙት የጅምላ እልቂት ነው ብለዋል።
የጅምላ እልቂት ጥቃቱ የተከፈተው ትናንት ህዳር 13/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ ሲሆን፡ በዚህም እስካሁን ባለው 50 የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች ተገድለዋል፡ ቀሪው የሕብረተሰብ ክፍልም ሕይወቱን ለማትረፍ ሽሽት ላይ ነው ተብሏል።
በዚህ አከባቢ ከዓመታት በፊት የጅምላ ግድያ ተፈጽሞ የሰው ልጅ በግሬደር ታፍሶ የተቀበረበት ልብ ሰባሪ ክስተት አይዘነጋም።
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
14/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
💔 71❤ 48😢 9👍 7
🩸#መተከል_የደም_መሬት🩸
ዛሬ ግዛት አስፋፊው የኦህዴድ ብልፅግና ኃይል በስውር ያሠማራው በጃል ቃንቄ የሚመራው ሸኔ ኃይል በመተከል ቡለን ወረዳ ነዋሪ 42 በአማራ፣ በጉሙዝ እና በሽናሻ ህዝቦች ላይ ጭፍጨፋ ፈፅሟል።
የኦሮሚያ ክልል በቡለን ወረዳ ኩታገጠም በሆነው ወንበራ ወረዳ ሠፊ የፖለቲካ ሥራ ሢሠራ የቆየ ሲሆን ቡለን ወረዳ የሚኖረውን "የራሴ" ከሚሉት ውጭ ያለውን ነዋሪ ለማፅዳት ያለመ ጭፍጨፋ በጫካው ብልፅግና በኩል ዛሬ አስፈፅሟል።
ሀገርን ከጥፋት የማዳኛ በቸኛ መንገድ ፋኖነት ነውና መላው ጭቁን ህዝብ ከአማራ ፋኖ ጎን በመሰለፍ ሀገርንና ራስን ከጥፋት እንታደግ‼️
በግፍ ለተጨፈጠፉት ነፍስ ይማር‼️
#ዐንድ_አማራ‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
13/ዐ3/2018 ዓ.ም
@NISIREamhra
❤ 98💔 54👍 30😢 9🎉 7
