ETHIO-MEREJA®
Kanalga Telegram’da o‘tish
News & Media Company® USA : Washington Addisababa, Ethiopia🇪🇹 . Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot ✔
Ko'proq ko'rsatish2025 yil raqamlarda

110 243
Obunachilar
-5724 soatlar
-3197 kunlar
-1 31530 kunlar
Postlar arxiv
ለሚሰጡት አገልግሎት ጉቦ የጠየቁ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የቄራዎች ድርጅት የሚሰጠውን አገልግሎት ለማግኘት የሄዱ ተገልጋዮችን ገንዘብ የጠየቁ ሁለት ተጠርጣሪ አመራሮች ፣ 1ኛ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰይድ እንድሪስ ከማል እና 2ኛ ምክትላቸው አቶ እድሪብሳ ማሞ ገንዘብ ካላመጣችሁ አገልግሎት አታገኙም በማለት ፤ እንግልት ሲፈጠሩ ቆይተው በደረሰ ጥቆማ በዛሬው ዕለት ከተገልጋይ ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ተገልጋዬች ተከታትለዉ ለሰጡት ጥቆማ እያመሰገንን ፣ በቀጣይም ሙስናን ለመከላከል በሚደረገው ትግል ከጎናችን በመሆን መተባበራችሁን እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርብለን ሲል የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል ።
እንደዚህ አይነት የሙስና ተግባራትን ሲመለከት ለ ከንቲባ ጽ/ቤት የሙስና ወንጀል ጥቆማ ተቀባይ በመጠቆም ሙስናን የመከላከል ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ እናሳስባለን ብሏል ።
❤ 55👍 15👏 9
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአማራ ክልል የተቋሙ ሰራተኛ ታገቶ ከተወሰደ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በስራ ላይ የነበረ የተቋሙ ሰራተኛ አቶ ሆነልኝ ፋንታሁን ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ታግቶ ከተወሰደ በኋላ በተፈጸመበት ድብደባ እና ኢ-ሰብዓዊ ኣያያዝ ምክንያት ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ህይወቱ ማለፉን አስታወቀ።
ማህበሩ ትላንት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ አቶ ሆነልኝ ፋንታሁን ነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከደባርቅ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጨነቅ አካባቢ በሰብአዊ አገልግሎት ላይ ተሰማርቶ ባለበት ሁኔታ ነበር የታገተው ብሏል።
ማህበሩ በአከባቢው በተቋሙ የሰብአዊ ድጋፍ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ዶ/ር ተፈራ አሰፋና አቶ አደላደላው ይግዛው የተባሉ ሌሎች ሁለት ሰራተኞቹ ከዚህ አሳዛኝ ክስተት መትረፋቸውን ጠቁሟል።
❤ 59😭 34😢 9🥰 6👍 3😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
መንግስት የተጨማሪ እሴት ታክስ መጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል ወሰነ
የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ፖሊሲ መመሪያ ኃላፊ አቶ ሙላይ ወልዱ ለኢቢሲ እንደገለጹት፤ የገንዘብ ሚኒስቴር በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል ወስኗል፡፡
ነባሩ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ከምጣኔ ውጭ ሌሎች ማሻሻያዎችን በማካተት ከ3 አስርት ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ በ2017 በጀት አመት ስራ ላይ መዋሉን አቶ ሙላይ ገልፀዋል፡፡
የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከነበረው ከ12 በመቶ በላይ ድርሻ በየዓመቱ በተከታታይ እየቀነሰ ከ7 በመቶ በታች መድረሱን የጠቀሱት ኃላፊው፤ ከዚህ ጠቅላላ ቅናሽ 44 በመቶው የተጨማሪ እሴት ታክስ ድርሻ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡
መጣኔው አሁን ካለበት 15 በመቶ ከፍ እንዲል ማድረግ ጫናው ተጨማሪ እሴት ታክስ በአግባቡ የሚከፍሉት ላይ እንዲባባስ በማድረግ የታክስ አስተዳደር ወይም የታክስ ህግ ተገዥነት ችግሩ ሊባባስ እንደሚችል በጥናት መረጋገጡን ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡
በዚህም በማሻሻያው መሰረት በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑን ነው የገለፁት፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች ውስጥ የሚመደብ ሆኖ በፍጆታ የሚጣል፣ ቁጠባንና ካፒታልን የሚያበረታታ ከተጠቃሚው የሚሰበሰብ ታክስ ነው፡፡
❤ 24
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአንቾራጌ አላስካ አየር ማረፊያ ተገናኝተው እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል።
በአየር ማረፊያው በርካታ የጦር ጀቶች የታዩ ሲሆን፣ ጥበቃውም ከበድ ያለ እንደሆነ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ነው።
በአላስካ አየር ማረፊያ በዘተጋጀላቸው ቀይ ምንጣፍ ላይ ሆነው እጅ ለእጅ ከተጨባበጡና የፎቶ ግራፍ መነሳት ስነ-ስርዓት አከናውነዋል።
ከዚህም በኋላ ዓለም በጉጉት ወደሚጠብቀው ውይይት ያመሩ ሲሆን፤ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑም ተዘግቧል።
የልዑካን ቡድናቸው ይዘው ወደስብሰባው ስፍራ የገቡት ፕሬዚዳንቶቹ በዩክሬን ጉዳይ ላይ እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
❤ 116👍 33🤯 7👎 5🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኦሮሞ_ነፃነት_ሠራዊት የአሜሪካን የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት ተቀበለ፤ ተፈፅመዋል በተባሉ ወንጀሎች ላይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት( ኦነሠ) በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ የወጣውን የ2024 የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርት በመቀበል በሪፖርቱ የተገለጹ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ ዓለም አቀፍ አካል እንዲመረመሩ ጥሪ አቀረበ። በተጨማሪም አሜሪካ ለኢትዮጵያ መንግስት የምትሰጠውን ድጋፍ እንድታጤነውም አሳስቧል።
ኦነሠ ነሐሴ 7 ቀን 2017 በወጣው መግለጫ፤ ሪፖርቱ “ባለፉት ሰባት ዓመታት ሕዝባችን የኖረውን እውነት፣ ስርዓታዊ ሽብር፣ በመንግስት የተቀናጀ ጭካኔ እና ስር የሰደደ አለመከሰስን ዳግም አረጋግጧል” ብሏል።
ኦነሠ በሪፖርቱ በተወሰነ ቦታ ብቻ መጠራቱን በተመለከተም፤ እንደ ሮይተርስና ዋሽንግተን ፖስት ያሉ ገለልተኛና ተዓማኒ የሆኑ የሚዲያ ተቋማት ያደረጓቸው ምርመራዎች፤ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ፈፀመው ተብለው ከተገለጹ ወንጀሎች መካከል አብዛኛዎቹ የተፈጸሙት በመንግስት ኃይሎች ወይም በመንግስት ድጋፍ በሚሰጣቸው ቡድኖች መሆኑን አረጋግጠዋል ብሏል።
አክሎም በተከሰሰበት ወንጀሎች ላይ መርመራ እንዲደረግ ከገለልተኛ አካላት ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።
❤ 69😁 16👍 4🥰 1👏 1🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢዜማ ገዥው ፓርቲ “የራሱን ድክመቶች ችላ ብሏል” ሲል ወቀሰ፤ ተጠያቂነትን እንዲቀበል እና የፕሪቶሪያው ስምምነት አለመፈጸምን እንዲፈታ ጠየቀ!!!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ገዥው ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በቅርቡ ያወጣው መግለጫ “የራሱን ድክመቶች ወደ ጎን ችላ ያለበት” እና “ለተጠያቂነት ያለውን ዝቅተኛ ተነሳሽነት ያሳየበት” ነው ሲል ወቀሰ።
የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ባወጣው መግለጫ “ታሪካዊ ጠላቶች” እና “የውስጥ ባንዳዎች” ሲል የጠራቸው አካላት ኢትዮጵያን ለማተራመስ አዲስና የተቀናጀ ሙከራ እያደረጉ ነው ሲል ከሷል።
ፖርቲው “ከጥቂት ዓመታት በፊት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የገጠመንን ጦርነት በአሸናፊነት ተወጥተናል” ያለ ሲሆን፤ “ወታደራዊ ድላችንን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ቋጭተናል። ዳሩ ግን ይፈልጉት የነበረው የተራዘመ ጦርነት በስምምነቱ የተጨናገፈባቸው ጠላቶቻችን ሌሎች ስልቶችን ወደ መሞከር ገብተዋል” ብሏል። እነዚህ ኃይሎች “ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ” ሲንቀሳቀሱ ነበር ሲል ገልጿል።
ይህን የገዢው ፓርቲ መግለጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል የነበረውን ጦርነት ለማስቆም እና የፕሪቶሪያ ስምምነትን በመፈረም ረገድ የኢትዮጵያውያንን “የጋራ አስተዋጽዖ” እና የስምምነት ድንጋጌዎችን በማሟላት ረገድ የታዩ ድክመቶችን ችላ ብሏል ሲል ወቅሷል።
ኢዜማ “ለሁከትና ብጥብጥ ተጠያቂው የውጭ ጠላቶች” ናቸው የሚለውን የገዥው ፓርቲ መግለጫ በመተቸት የመንግስት የአስተዳደር ብልሽቶች እና ግልጸኝነት አለመኖር ውጥረቶች እንዲባባሱ ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸውን አመልክቷል።
❤ 91👎 21👍 12😁 8👏 7
Photo unavailableShow in Telegram
🌺ተጨማሪ 100 ሪሴለሮችን እንፈልጋለን።
ከቤትዎ ሆነው በነፃ በኦንላይን ከኛ ጋር ይስሩ!!!
እቃዎችን በተለያዩ የኦንላይን አማራጮች
ከኛ በኦንላይን በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ያግኙ፣
በቴሌግራም፣ በፌስቡክ፣ በማርኬትፕሌስ፣ በቲክቶክ፣ በኢንስታግራም፣ በራስዎ በማስተዋወቅ እቃዎችን መሸጥ ይችላሉ።
ይህን የሪሴለሮች Private ግሩፕ👇 አሁኑኑ ተቀላቀሉ
https://t.me/+4tK-v7Py8Mo3YTJk
https://t.me/+4tK-v7Py8Mo3YTJk
https://t.me/+4tK-v7Py8Mo3YTJk
Contact 👉 @Addisekachat
JOIN አድርገው አብረውን መስራት ይጀምሩ!
❤ 19😁 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
🌺ተጨማሪ 100 ሪሴለሮችን እንፈልጋለን።
ከቤትዎ ሆነው በነፃ በኦንላይን ከኛ ጋር ይስሩ!!!
እቃዎችን በተለያዩ የኦንላይን አማራጮች
ከኛ በኦንላይን በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ያግኙ፣
በቴሌግራም፣ በፌስቡክ፣ በማርኬትፕሌስ፣ በቲክቶክ፣ በኢንስታግራም፣ በራስዎ በማስተዋወቅ እቃዎችን መሸጥ ይችላሉ።
ይህን የሪሴለሮች ግሩፕ ነው። ተቀላቀሉ👇
https://t.me/+4tK-v7Py8Mo3YTJk
Contact 👉 @Addisekachat
JOIN አድርገው አብረውን መስራት ይጀምሩ!
❤ 12
የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ የ2018 ዓ/ም የትምህርት የጊዜ ሰሌዳን ለክልል ትምህርት ቢሮዎች አሳውቋል።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተገኘው መረጃ ትምህርት ሚኒስቴር በላከው የዓመቱ የትምህርት ካላደር ፦
- እስከ ነሐሴ 30/2017 ዓ/ም የአዲስ እና ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ይካሄዳል።
- መምህራን በትምህርት ቤታቸው ተገኝተው ሪፖርት የሚያደርጉበት ጊዜ ነሐሴ 19/2017 ዓ/ም ነው።
- መስከረም 5/2018 ዓ/ም የመጀመሪያው ቀን የመጀመሪያ መደበኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ (day one class one) የሚጀምርበት ቀን ነው።
- ከጥር 18 እስከ ጥር 22 / 2018 ዓ/ም የአንደኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና የሚሰጥበት ነው። ከጥር 25 እስከ 29 ትምህርት ቤቶች ዝግ ይሆናሉ።
- የካቲት 2/2018 ዓ/ም የሁለተኛ ሴሚስተር መደበኛ ትምህርት ይጀምራል።
- ከሰኔ 1 እስከ 5/2018 ዓ/ም የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ይሰጣል።
- ከሰኔ 8 እስከ 12/2018 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ይሰጣል።
- የሁለተኛ ሴሚስተር ፈተና ከሰኔ 15 እስከ 19/2018 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።
- የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 15 እስከ ሰኔ 26/2018 ዓ/ም ድረስ ለመስጠት ታቅዷል።
(የ2018 ዓ/ም የትምህርት ጊዜ ሰሌዳ ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ)
❤ 72👎 11👏 1🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
🌺100 ሪሴለሮችን እንፈልጋለን።
ከቤትዎ ሆነው በነፃ በኦንላይን ከኛ ጋር ይስሩ!!!
እቃዎችን በተለያዩ የኦንላይን አማራጮች
ከኛ በኦንላይን በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ያግኙ፣
በቴሌግራም፣ በፌስቡክ፣ በማርኬትፕሌስ፣ በቲክቶክ፣ በኢንስታግራም፣ በራስዎ በማስተዋወቅ እቃዎችን መሸጥ ይችላሉ።
ይህን የሪሴለሮች ግሩፕ ነው። ተቀላቀሉ👇
https://t.me/+4tK-v7Py8Mo3YTJk
Contact 👉 @Addisekachat
JOIN አድርገው አብረውን መስራት ይጀምሩ!
❤ 22👍 4😱 1🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ፍርድ ቤቶች ከነሀሴ 1 ጀምሮ በከፊል ዝግ ሆነዋል
በ2017 ዓ.ም በፌደራል ፍርድ ቤቶች በርካታ አፈጻጸሞች የተመዘገቡበት እንዲሁም ከመዝገብ አፈጻጸም አኳያ በዓመቱ ለ187ሺህ 55 መዛግብት ዕልባት ለመስጠት በዕቅድ ተይዞ ለ109 ሺህ 347 መዛግብት ዕልባት በመስጠት የዓመቱ አፈጻጸም 101.7 በመቶ መድረሱ ተገልፆል።
ይህ አፈጻጸም ለፍርድ ቤቶች ተይዘው ከነበሩ ዕቅዶች አንጻር ሲታይ በጠቅላይ ፍ/ቤት 22,690 መዛግብት ታቅደው 18ሺህ951 መዛግብት ዕልባት በማግኘታቸው አፈጻጸሙ 83.5% ፣ ለከፍተኛ ፍ/ቤት 23ሺህ165 መዛግብት ታቅደው 25ሺህ 987 መዛግብት ዕልባት በማግኘታቸው አፈጻጸሙ 112.1%፣ ለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 141ሺህ 200 መዛግብት ታቅደው ለ145ሺህ 409 ዕልባት በመስጠት አፈጻጸሙ 103% መድረሱ ተገልጿል።
የፌደራል ፍርድ ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 38 መሰረት ዳኞች የሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ዉስብስብነትን ግምት ውስጥ በማስገባት በቂ እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው ታምኖበት በየዓመቱ መጨረሻ ለተከታታይ ለ2ወራት ማለትም ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 30 በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ በተደነገገው መሰረት ከነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በከፊል ዝግ ይሆናሉ፡፡
ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩበት የሁለት ወራት ጊዜ በባህሪያቸዉ አስቸኳይ የሆኑና ጊዜ የማይሰጡ በዜጎች መብትና በሀገር ልማት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩትን አቤቱታዎች እንዲሁም ለዉሳኔ የደረሱ መዛግብትን መርምሮ ውሣኔ የመስጠት አገልግሎቶች የሚቀጥሉ ይሆናል ።የሰበር አጣሪ ችሎቶች በመደበኛ ጊዜ የሚሰራዉን አጣርቶ ዉሳኔ የመስጠት ስራን ከነሐሴ 1ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ በመደበኛ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት ይቀጥላሉ።
❤ 65👍 10👏 2🤔 2👎 1
Repost from TgId: 1424013175
🔔ዋጋ Price ➤ 49,900ብር
🔅የ 2 አመት የጽሑፍ ዋስትና እና
🔅ከ 21+ አመት በላይ ልምድ
ሞዴል Model M74
21ኛ አመታችንን እያከበርን ለውሱን ግዜ የልዩ ቅናሽ ተጠቃሚ ይሁኑ።
📍 አድራሻችን
🏠 በቅሎ ቤት • ግሎባል ፊት ለፊት • አልፋ ሕንፃ
• 0911445604
• 0979426642
• 0979420042
❤ 11👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
🎬 Video Editing Course at Merahyan Skill Center
የቪዲዮ ኤዲቲንግ ሥልጠና ምዝገባ ጀምረናል
Master the art of video editing with Adobe Premiere Pro!
•Schedule- Saturday and Sunday
•Project based
•Will start in August 9
Very Few spot left!
Call to Register:
0989747878 /
0799331774
For more :
@merahyan
Learn. Grow. Refresh
❤ 26👍 2🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
የአፍሪካ_ህብረት ተልዕኮ ከ50 በላይ አል-ሸባብ ታጣቂዎች በደቡባዊ ሶማሊያ መገደላቸውን አረጋገጠ!!
የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ(አውሶም) በሶማሊያ የመንግስት ኃይሎች የሚደገፉት ወታደሮቹ ባሳለፍነው አርብ በደቡባዊ ሶማሊያ በባሪሬ ከተማ በተካሄደ ከባድ ውጊያ ከ50 በላይ የአል-ሸባብ አባላትን መግደላቸውን አስረጋገጠ።
አውሶም ከሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በሰጠው መግለጫ፤ “በባሪሬ በተልዕኮው ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል” የሚሉ የሚዲያ ዘገባዎችን አስተባብሏል።
"አውሶም ኃይሎቹ ከሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ኃይሎች (SNAF) ጋር በመተባበር የባሪሬ ከተማን መልሶ ለመቆጣጠር ሐምሌ 25 ቀን ጥቃት መጀመሩን ግልጽ ማድረግ ይፈልጋል" ሲል የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ(አውሶም) ገልጿል። አውሶም ይህን ያለው፤ አል-ሸባብ በባሪሬ በተካሄደው ከባድ ውጊያ የአፍሪካ ህብረት ንብረት የሆኑ የታጠቁ ሰዎች ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን እና የአውሶም ወታደሮች ማፈግፈጋቸውን መግለጹን አስመልክቶ በገዳዩ ላይ ምላሽ ሲሰጥ ነው።
“የጋራ ወታደራዊ ዘመቻው ለአሸባሪው ቡድን ከፍተኛ ኪሳራ አስከትሏል፣ ከ50 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች ሲገደሉ ሌሎች በርካቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል” ሲል የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ(አውሶም) ማስታወቁን ዥንዋ ዘግቧል። ከሞቃዲሾ በስተደቡብ ምዕራብ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ባሪሬ ከተማ፤ በሸበሌ ወንዝ ዳርቻ ከሚገኙ ስትራቴጂካዊ አካባቢዎች አንዷ ነች።
❤ 65👍 12🤔 6🥰 4
Photo unavailableShow in Telegram
ጀርመንኛ ቋንቋ ስልጠና
A1, A2, B1 and B2 and C1 Level
🌟 Enhance Your Skills with Our Upcoming German Language Training! 🌟
•አዲስ ቋንቋ መማር ለምትፈልጉ
•የጋብቻ ፕሮስስ ጀርመን ኤምባሲ መጀመር ላሰባችሁ
•የስራ ፕሮስስ ለመጀመር ያሰባችሁ
የ ጎተ (Goethe) ፈተና ለማለፍ ዝግጁ እናደርጋቹሃለን!
•Online or Inperson
To register:
☎️
0989747878
0799331774
ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan
❤ 24👍 3👏 2😱 1
ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ የሚያስተላልፉ ወኪሎች ይፋ ሆኑ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተቀማጭነታቸውን አሜሪካ ያደረጉና በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፉ የሃዋላ ተቋማትን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
ባንኩ ፈቃድ ያላቸውና ቁጥጥር የሚደረግባቸውን የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች መጠቀም ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና ለአሸባሪዎች የሚደረግ ድጋፍን ለመከላከል ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል።
በአንጻሩ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ሥርዓት ታማኝነት ለመቀነስና የገበያ ምንዛሪ ዋጋን ለማዛባት በማለም በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ የሚልኩ መኪሎች መኖራቸውን አመልክቷል፡፡
በተጨማሪም በውጭ ሀገራት ከሚገኙ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ አባላት የተሰበሰበን ገንዘብ ሕገ ወጥ ተግባርን ለመደገፍ የሚውሉና ገንዘብ በማሸሽ ተግባር ላይ የተሰማሩ አስተላላፊዎች መለየታቸውን ነው ያስገነዘበው፡፡
በዚህ መሰረትም፡-
1. ሽገይ የገንዘብ ማስተላለፊያ ወኪል ( Shgey Money Transfer)
2. አዱሊስ የገንዘብ ማስተላለፊያ ወኪል (Adulis Money Transfer) USA)
3. ራማዳ ፔይ (Ramada Pay (Kaah)
4. ቲኤኤጄ የገንዘብ ማስተላለፊያ ወኪል (TAAJ Money Transfer)
የተሰኙ የሃዋላ ተቋማት ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ እንደሚያስተላልፉ ተጠቁሟል፡፡
የወኪሎችን እንቅስቃሴ ለመመርመር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን የጠቀሰው ባንኩ ÷ ምርመራውን አጠናክሮ በመቀጠል ተገቢ ርምጃ እንደሚወስድ አስገንዝቧል፡፡
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ ፈቃድ በሌላቸው የገንዘብ ማስተላለፊያ ወኪሎች ገንዘባቸውን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ከመላክ እንዲቆጠቡም አሳስቧል፡፡
በእነዚህ ወኪሎች በኩል የተላከ ገንዘብ ሊወረስ እንደሚችል እና ከተላከ በኋላ ለተፈለገው አካል ስለመድረሱ ምንም አይነት ዋስትና እንደሌለም አመልክቷል።
በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ እና አስተማማኝ መንገዶችን በመጠቀም ገንዘባቸውን እንዲጠብቁም አስገንዝቧል፡፡
ሕጋዊ የገንዘብ ማስተላለፊያ ወኪሎችን ሙሉ ዝርዝር ከታች በተቀመጠው የብሔራዊ ባንክ ድረ ገጽ ላይ ማግኘት እንደሚቻልም ባንኩ ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመልክቷል፡፡
❤ 88😁 17🤔 4😱 4👏 2🤯 2
Photo unavailableShow in Telegram
ግብፅ እና አሜሪካ በውሃ ደህንነት እና ቁልፍ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙርያ መከሩ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ ከግብጹ አቻቸው ባድር አብደላቲ ጋር በግብጽ የውሃ ደህንነት ዙርያ እንዲሁም በመካከላኛው ምስራቅ ሰላማን ለማስፈን በሚደረጉ ጥረቶች እና ቁልፍ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አስታወቀ።
ሚኒስትሮቹ ረቡዕ ሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ ላይ ሩቢዮ፤ “ግብፅ በሐማስ ተይዘው የነበሩ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ላሳየችው ጽኑ ድጋፍ” ለአብደላቲ ምስጋና አቅርበዋል ሲል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስነብቧል።
በተጨማሪም በሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር ስለሚደረገው ሽግግር አስፈላጊነትም ተወያይተዋል ሲል መስሪያ ቤቱ አክሎ ገልጿል።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባድር አብደላቲ ስብሰባውን አስመልክቶ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ ከአሜሪካ አቻቸው ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነትን በማጠናከር፣ ቁልፍ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች እና በግብፅ የውሃ ደህንነት ዙርያ መምከራቸውን ገልጸዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች ውይይቱን ያካሄዱት በጋዛ ስላለው ረሃብ አስመልክቶ ከሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች በኩል የሚደረጉ ጥሪዎች እየተበራከቱ በመጡበት በአሁኑ ወቅት ነው።
❤ 50👍 3😱 1😢 1🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የአገር ውስጥ ባንኮች ለሚጠብቃቸው ጠንካራ ፉክክር ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ማሳሰቢያ ተሰጣቸው
ብዙ የውጭ ባንኮች የውጭ ባንኮች የኢትዮጵያን የባንክ ዘርፍ መቀላቀላቸው የማይቀር በመሆኑ ለሚጠበቀው ጠንካራ ውድድር፣ የአገር ውስጥ ባንኮች ራሳቸውን ማዘጋጀት እንደሚኖርባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አሳሰቡ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ አቢሲኒያ ባንክ ከወረቀት ነፃ አገልግሎትን በይፋ ባስጀመረበት ፕሮግራም ላይ፣ የባንክ ዘርፍ እስካሁን ከነበረው በተለየ ውድድርና ፉክክር ይካሄድበታል ብለዋል፡፡
የባንክ ኢንዱስትሪው በሁሉም የአገልግሎት መሥፈርቶች ዘመናዊና ተወዳዳሪ እንዲሆን ግድ የሚልበት፣ ይህንንም የበለጠ አሁናዊ የሚያደርገው ሁለት ምክንያቶች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡አንደኛው ኅብረተሰቡ ከባንኮች የተሻለ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚፈልግ በመሆኑ፣ በተለይ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች ክፍት እንዲሆን ከመፈቀዱ ጋር በተያያዘ ጠንከር ያለ ውድድር ስለሚኖር እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
‹‹ብዙ የውጭ ባንኮች ፈቃድ እየጠየቁና ማመልከቻ እያስገቡ ነው፡፡ የውጭ ባንኮች መግባታቸው እርግጥ በመሆኑ፣ ወደድንም ጠላንም በሒደት በጣም ተወዳዳሪና የፉክክር ዘርፍ መሆኑ አይቀርም፤›› ያሉት ገዥው፣ የአገር ውስጥ ባንኮችም ይህንን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
❤ 82👎 7👍 6🤯 2
አቶ ዳውድ ሙሜ በድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው አለፈ።
በኦሮሚያ ቱርዝም ቢሮ ምክትል ኮሚሽነር እና የኢኮ ቱሪዝም ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳውድ ሙሜ ዛሬ በደረሰባቸው መኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል።
የሥራ ባልደረቦቸው አቶ ሀብታሙ አቶምሳ እንደተናገሩት አቶ ዳውድ ዛሬ ሀምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በአንድ ጀንበር ሰባት መቶ ሚሊዮን ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ኮሚሽኑን ወክለው የተወሰኑ ሰራተኞችን፣ አባገዳዎችን እንዲሁም ሁለት ልጆቻቸውን ይዘው ነበር ችግኝ ለመትከል በማለዳ ወደ አዳማ የሄዱት።
ችግኝ ተከላውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ አዲስ አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ ልዩ ቦታው " ጎጌቻ " ወንዝ ድልድይ ላይ አቶ ዳውድ፤ ልጆቻቸው እና አንድ የመስሪያ ቤታቸው ባልደረባ ሰው የነበሩበት መኪና ተገልብጦ የአቶ ዳውድ ሙሜ ህይወት አልፏል።
በመኪናው ውስጥ የነበሩ ሁለቱ የአቶ ዳውድ ልጆች ፤ሾፌራቸው እና አንድ የስራ ባለደረባቸው ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል መሄዳቸውን አቶ ሀብታሙ አክለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አቶ ዳውድ ሙሜ ከምዕራብ ሀራርጌ ጭሮ ከተማ ከንቲባ እስከ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ፤ በኦሮምያ ክልል የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ውስጥ በዳሬክተርነት ፤ የኦሮምያ ክልል የኮሚኒኬሽን ኃላፊ እና ህይወታቸው እስካለፈበት ድረስ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮምሽን ምክትል እና የኢኮ ቱርዝ ሀላፊ ሆነው ስያገለግሉ ነበር።
" ለቱሪዝም ባላቸው ልዩ ፍቅር በኦሮምያ ክልል ሆነ በፌደራል ደረጃ የፓርኮች ልማት፤ የዱር እንስሳት እንክብካቤ፤ የቱሪስት መዳረሻዎችን ማልማት እና ማስተዋወቅ ላይ ጥናቶችን ያደረጉ፤ ለቱሪዝም ልማት ያላቸውን የሰጡ እውቅ ባለውለታ ነበሩ " ሲሉ የሥራ ባልደረባቸው አቶ ሀብታሙ ገልፀዋቸዋል።
❤ 71😢 68👏 9👍 6😱 3👎 2
Repost from TgId: 1424013175
Photo unavailableShow in Telegram
🔔ዋጋ Price ➤ 69,900ብር
🔅የ 2 አመት የጽሑፍ ዋስትና እና
🔅ከ 21+ አመት በላይ ልምድ
ሞዴል Model M110
ለዋጋ መረጃና ሌሎች ምርቶቻችን የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
👇 👇 👇
t.me/AlphaFurniture
📍 አድራሻችን
🏠 በቅሎ ቤት • ግሎባል ፊት ለፊት • አልፋ ሕንፃ
Beklo Bet • Infront of Global Hotel • Alpha Building
• 0911445604
• 0979426642
• 0979420042
❤ 21
