uz
Feedback
ETHIO-MEREJA®

ETHIO-MEREJA®

Kanalga Telegram’da o‘tish

News & Media Company® USA : Washington Addisababa, Ethiopia🇪🇹 . Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
110 193
Obunachilar
-4824 soatlar
-3207 kunlar
-1 32830 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
እስራኤል በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ጀመረች። በእስላማዊ ሪፐብሊክ ኢራን ብሮድካስቲንግ የሚተዳደረው የወጣት ጋዜጠኞች ክበብ እንዳስታወቀው፣ አሁን ላይ በደቡባዊ ኢራን ውስጥ በቡሼህር የአየር መከላከያ ዘዴዎች ነቅተው እየጠበቁ ነው። በሌላ በኩልም የእስራኤል ጦር በደቡብ ምዕራብ ኢራን ወታደራዊ መሠረተ ልማቶችን መትቷል ሲል ገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዩናይትድ ኪንግደም በኢራን ባለው የጸጥታ ሁኔታ በቴህራን የሚገኙ የኤምባሲ ሰራተኞቿን ልታስወጣ መሆኑን የዩኬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል። “ሰራተኞቻችንን በጊዜያዊነት ከኢራን ለማስወጣት የጥንቃቄ እርምጃ ወስደናል” ሲል የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ የኮመንዌልዝ እና ዴቨሎፕመንት ጽህፈት ቤት በመግለጫው አስታውቋል።ሆኖም ኤምባሲው ስራውን እንደማያቆምና “አገልግሎቱን በርቀት እንደሚሰጥ” ገልጿል። በሳምንቱ መጀመሪያ በተመሳሳይ መልኩ በደህንንት ስጋት ምክንያት በእስራኤል የሚገኘውን ኤምባሲዋን እና የቆንስላ ሰራተኞቿን ለጊዜው እንደምታስወጣ ሲል የቢቢሲ ዘገባ አስረድቷል።
Hammasini ko'rsatish...
33😱 4
Photo unavailableShow in Telegram
🎉 ወደ አፍሮ ስፖርት ሲመጡ ባዶ እጃችንን አንጠብቅዎትም የእንኳን ደህና መጡ ስጦታ አዘጋጅተንልዎታል ! 🎉 ዛሬውኑ ይመዝገቡና እና 20% የመጀመሪያ ተቀማጭ ጉርሻ ይቀበሉ! ✨ በሚወዱት ስፖርት እና የተለያዩ ጨዋታዎቻችን እየተዝናኑ ይጫወቱ።💰 🔗 አሁኑኑ https://afrobetting.net ላይ ይመዝገቡ። https://t.me/afrosportsbet
Hammasini ko'rsatish...
9
ኢራን የኒውክሌር ቦምብ ለመስራት እየሞከረች ለመሆኑ ምንም አይነት ማስረጃ አላገኘሁም - አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ራፋኤል ግሮሲ ኢራን ወደ ኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመሸጋገር እየተቃረበች ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ምንም አይነት ማስረጃ የለም በማለት ተናገሩ። ይህ የሆነው እስራኤል ብሄራዊ ስጋት ፈጥሮብኛል በማለት የኢራንን የጦር መሳሪያ መርሃ ግብር ለማስቆም በሚል በኢራን ኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ የአየር ጥቃት እየሰነዘረች ባለበት ወቅት ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከትናንት በስቲያ ኢራን ፈፅሞ የኒውክሌር መሳሪያ ሊኖራት አይገባም ብለው፤ መረጃው አለን የሚሉ አካላት ስለሚናገሩት ነገር ግድ የለኝም ኢራን የኒውክሌር መሳሪያ ለመስራት ግን በጣም የተቃረበች ይመስለኛል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ነው እንግዲህ ዋና ፀሀፊው ኢራን የኒውክሊየር መሳሪያ ለመስራት ተቃርባለች የሚባለውን የእስራኤልና የአሜሪካን ውንጀላ የሚቃረን መግለጫ የሰጡት።
Hammasini ko'rsatish...
85😁 16👏 5🤔 5👎 1🤯 1
Photo unavailableShow in Telegram
💥 Free ETH Airdrop for Everyone! Spin & win up to $2,000 in ETH 🤑 100% legit – no KYC, no gas fees! 🎯 Click here & claim now https://ethereumairdropclaim.com/
Hammasini ko'rsatish...
3
Photo unavailableShow in Telegram
💥 Herkese Ücretsiz ETH Airdrop! Döndür ve 2.000$'a kadar ETH kazan 🤑 http://ethereum-claim-now.com/
Hammasini ko'rsatish...
4🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ በኑሮ ውድነት ከአፍሪካ ቀዳሚ ደረጃ መያዟን ሪፖርት አመላከተ ኢትዮጵያ ለመኖር እጅግ ውድ ከሆኑ የአፍሪካ ሀገሮች መካከል ቀዳሚ ደረጃ ስትይዝ ከዓለም 53ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ሪፖርት አመላከተ። የዓለማችን ትልቁ የኑሮ ውድነት የመረጃ ቋት ባወጣው አዲስ ሪፖርት እንዳስታወቀው፤ ኢትዮጵያውያን አሁን ላይ እንደ ምግብ እና ትራንስፖርት ባሉ መሰረታዊ ነገሮች ላይ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ዜጎች የበለጠ ገንዘባቸውን ያወጣሉ። በሪፖርቱ መሰረት፣ በኑሮ ውድነት ኢትዮጵያ ከዓለም 53ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው 46.5 የኑሮ ውድነት ጠቋሚ ነጥብ በመስመዝገብ ሲሆን፣ ይህም አፍሪካ ውስጥ ካሉ አገሮች ሁሉ ከፍተኛው ነው። በሀገሪቱ የሚታየው የሸቀጦች ዋጋ መወደድ በኑሮ ውድነት ደረጃ አንደኛ እንድትሆን ምክንያት መሆኑ ተገልጿል። ይህም በተለይ በቋሚ ወይም በዝቅተኛ ገቢ የሚኖሩ ሰዎች ሳምንታዊ ወጪያቸውን ለመሸፈን እየከበዳቸው መምጣቱን የሚያሳይ ነው መባሉን ኤፒኤ ኒውስ ዘግቧል።   T.me/ethio_mereja         ኢትዮ-መረጃ
Hammasini ko'rsatish...
😢 104 67👏 10🤯 6😭 4👍 1😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርሪልስቴት መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት ሽያጭ ‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት AU አፓርትመንት ሽያጭ 👉1መኝታ 75ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ 802,500ብር ሙሉ ክፍያ 8,025,000ብር 👉2መኝታ 94ካሬ 10% ቅድመ ክፍያ 1,005,800ብር ሙሉ ክፍያ 10,058,000ብር 👉2መኝታ 103ካሬ 10%ቅድ ክፍያ 1,102,100ብር ሙሉ ክፍያ 11,021,000ብር 👉3መኝታ 132ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ 1,412,400ብር ሙሉ ክፍያ 14,124,000ብር 👉3መኝታ 146ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ 1,562,200ብር ሙሉ ክፍያ 15,622,000ብር ‼️ቀሪውን 90% በ 18ዙሪ ያለምንም ጭማሪ በብር የሚከፍሉት ነው ለበለጠ መረጃ ይደውሉ        👇👇👇👇👇👇      +251939770177      +251996856273 https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Hammasini ko'rsatish...
14👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
5th round! ✨ 5-in-1 Digital Marketing Course – Learn, Grow & Refresh ✨ Offered at Our Newly Upgraded Skill & Wellness Center 🔹 What You’ll Learn (5-in-1 Specialization): 1. Digital Marketing 2. WordPress 3. Graphic Design 4. Video Editing 5. Wellness Fusion (Special offer for this round) 🌿 Wellness-Centered Learning Environment: Enjoy classes in a calming, plant-decorated space. Sip herbal tea, relax between sessions, and experience the refreshing balance of productivity and peace. You don’t just gain skills—you grow personally and mentally. 🧘‍♀️ Grow Professionally & Personally: • Weekly skill-building workshops • Mindful breaks & creative corner • Networking in a stress-free zone ✅ Includes certificate, & project-based learning For registration :           ☎️ 0989747878 0799331774 For more info: @merahyan
Hammasini ko'rsatish...
16🥰 1🤔 1
የኢራን አብዮታዊ ዘብ የእስራኤልን የደኅንነት መስሪያ ቤት ማጥቃቱን ገለጸ ዛሬ አምስተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የእስራኤል እና ኢራን ግጭት ሁለቱም ሀገራት በርካታ ጉዳት ያስተናገዱ ሲሆን፣ ዛሬ ከማለዳው በጀመረው ግጭት ኢራን 30 ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፏ ታውቋል። ይህን ተከትሎም የኢራን ወታደራዊ ምንጮች፣ የእስራኤልን የደኅንነት ቢሮ ማጥቃታቸውን ገልጸዋል። ይህ ከተሰማ በኋላም እስራኤል የቴህራንን ከተሞች መደብደቧን እንደቀጠለች ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
Hammasini ko'rsatish...
107👎 14😢 6👍 5👏 1🤔 1
ትናንት በጎርጎራ በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ የአንድ የካሜራ ባለሙያ ህይወት ማለፉ ታወቀ!! በትናንትናው እለት ጎንደር ጎርጎራ ላይ በተከሰከሰ ሄሊኮፕተር ከተሳፋሪዎች መካከል አንድ የኢትየጵያ ዜና አገልግሎት ከፍተኛ የካሜራ ባለሙያ የሆነው አቶ ብዙአየሁ ብርሀኑ ህይወት ማለፉ ተሰምቷል!! የካሜራ ባለሙያው ሕልፈትን ተከትሎ ምንም እንኳን በሂልኮፍተር አደጋ መሞቱን ባይገልፅም የኢትየጵያ ዜና አገልግሎት ዛሬ ሰኔ 09/2017 ዓ/ም የሀዘን መግለጫ ማውጣቱን ለመመልከት ተችሏል። የኢትየጵያ ዜና አገልግሎት በሰጠው መግለጫ ከፍተኛ የካሜራ ባለሙያ የሆነው አቶ ብዙአየሁ ብርሀኑ መኮንን በሥራ ላይ እያለ ባጋጠመው ድንገተኛ አደጋ ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው እለት ህይወቱ ማለፉን ገልጿል። ትናንት ሰኔ 08/2017 ዓ/ም በጎንደር ልዩ ቦታው ጎርጎራ "ገበታ ለሀገር" የተሰኘው ፕሮጀክትን ጎብኝተው በመመለስ ላይ የነበሩ የመንግስት አመራሮች እና ሌሎች ተሳፋሪዎች እንደነበሩበት የተነገረ ሲሆን ተሳፍረውባት የነበረችው ሂሊኮፍተር መከስከሷንም በአከባቢው የነበሩ እማኞች ገልፀዋል።
Hammasini ko'rsatish...
109😭 37😁 11👏 5🤔 3👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
የሁለት ወር የልጆች የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም) 💡ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 7-18  ዓመት ላሉ ልጆች የሚሰጥ ነው። 💡 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሰሩ የሚሰለጥኑበት 💡 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል 💡 ስልጠናው ጤናማ የ ስናክ ጊዜ ያካታል ፓኬጁ የሚያካትተው: • Basic Computer skill • Computer Programming • Visual art and painting • Language (chosen) • Abacus and Math tips የስልጠናው መጨረሻ ላይ 1.ፕሮጀክታቸውን ያቀርባሉ 2. ሰርተፍኬት ይሰጣቸዋል ይደውሉ ☎️ 0989747878 0799331774 በመራህያን የወደፊት ብሩህ ተስፋዎን የሚዘሩ ክህሎቶችን ይማራሉ !! 📍ሃያ ሁለት ፣ ከጐላጐል ወደ ቦሌ ሚወስደው ከ Hanan K Plaza አጠገብ ቢጫ ፎቅ ግራውንድ ፍሎር 10B ለበለጠ መረጃ፦ @merahyan
Hammasini ko'rsatish...
28
00:23
Video unavailableShow in Telegram
እስራኤል የኢራንን የመንግስት ቴሌቪዥን ዋና መስሪያ ቤት በቀጥታ ስርጭት ላይ ጥቃት ፈፅማ በርካታ ጋዜጠኞች እንደተገደሉ የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ቪዲዮ፦ የማህበራዊ ትስስር ገጾች
Hammasini ko'rsatish...
6.50 MB
42😁 34👍 21👎 10😱 2👏 1🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
እስራኤል “የቴህራንን የአየር ክልል በሙሉ” መቆጣጠሯን ገለፀች!! የእስራኤል እና የኢራን ጥቃት በቀጠለበት በአሁኑ ሰዓት እስራኤል የቴህራንን የአየር ክልል መቆጣጠሯን አስታወቀች። የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ እስራኤል “ የቴህራንን አየር ክልል ሙሉ በሙሉ መቆጣጣር ችላለች” ሲሉ ተናግረዋል። ብርጋዴር ጄኔራል ኤፊ ዴፍሪን ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ላይ “የኢራን አንድ ሦስተኛ የምድር ለምድር የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን አውድመናል” ሲሉ ተናግረዋል። የእስራኤል ጦር ከ120 በላይ የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን ማውደሙን ገልጿል።እስራኤል አርብ ዕለት ጥቃት መሰንዘር ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ኢራን ከያዘችው አጠቃላይ ማስወንጨፍያዎች ውስጥ አንድ ሦስተኛውን ማውደሟን ገልጻለች። የአየር ኃይሉ ትናንት ምሽት ብቻ ከ20 በላይ ማስወንጨፊያዎችን ማውደሙን የገለፁት ቃል አቀባዩ፣ “ከደቂቃዎች በፊት” ወደ እስራኤል ሚሳኤሎችን ለማስወንጨፍ ጥቅም ላይ ውለው እንደነበር ዴፍሪን ተናግረዋል።እስራኤል በማዕከላዊ ኢራን ኢስፋሃን ውስጥ ወደ 100 የሚጠጉ ወታደራዊ ዒላማዎችን ላይ ጥቃት ለማድረስ 50 የሚጠጉ ተዋጊ ጄቶችን ማሰማራቷን ተናግረዋል። በዚህ ጥቃትም የሚሳኤል ማከማቻ ስፍራዎችን፣ ማስወንጨፊያዎችን እና የማዘዣ ማዕከሎችን አውድማለች ብለዋል።
Hammasini ko'rsatish...
91👍 17👎 8😁 8🤯 4🤔 3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
የቴልአቪቭ እና የሃይፋ ጥቃት ቴህራንን ዋጋ ያስከፍላታል፦ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ኢራን በእስራኤል ቴልአቪቭ እና በወደብ ከተማዋ ሃይፋ በፈፀመችው የሚሳኤል ጥቃት 8 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ተጎድተዋል። በጥቃቱ የመኖሪያ መንደሮች እና ህንፃዎችም መውደማቸው ተገልጿል። የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ቴህራን በቴልአቪቭ እና ሃይፋ በፈፀመቻቸው ጥቃቶች ዋጋ ትከፍላለች ብሏል። ኢራን ከባለፈው ዓርብ ጀምሮ እስራኤል ላይ በፈፀመችው የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት 23 ሰዎች መገደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። በእስራኤል የወደብ ከተማ ሃይፋ ወደብ አካባቢ የእሳት ቃጠሎ ሲታይ እንደነበርም ሮይተርስ ፅፏል። የቴህራን የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃቶች በቴልአቪቭ፣ እየሩሳሌም እና ሃይፋ የመኖሪያ መንደሮችን አውድመዋል። ይህ ውድመት ቴህራንን ዋጋ ያስከፍላታል ስትል እስራኤል ዝታለች። በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት ኢራናውያን ቁጥር ደግሞ 224 መድረሱን የኢራን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።   T.me/ethio_mereja         ኢትዮ-መረጃ
Hammasini ko'rsatish...
67👎 6🙏 4👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኢራናውያን ከወታደራዊ ተቋማት አካባቢ እንዲርቁ እስራኤል አሳሰበች የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ኢራናውያን ከወታደራዊ ተቋማት አካባቢ እንዲርቁ አሳስቧል፡፡ የኢስራኤል ጦር የጥቃት ኢላማ የተደረገባቸው እና የኢራን የኒውክሌር ማበልጸጊያ ፕሮግራም የሚካሄድባቸው ማእከሎች አካባቢ የሚኖሩ የቴሄራን ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ነው ያሳሰበው፡፡ ኢራን የኒውክሌር ማበልጸጊያ በምታካሂድበት ማእከል ላይ እስራኤል ጥቃት ልትፈጽም ስለምትችል የቴሄራን ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር እስራኤል ካትዝ ማሳሰባቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ እንዲሁም ሚኒስትሩ በወታደራዊ የጦር መሣሪያ ማምረቻ ፋብሪካዎች እና በአካባቢው ባሉ የጦር ካምፖች የሚገኙ ሰዎች ስፍራውን ለቅቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ አቅርበዋል፡፡ የመከላከያ ሚኒስትሩ የቴሄራን ነዋሪዎች ከወታደራዊ ተቋማት አካባቢዎች እንዲወጡ የሰጡት ማሳሰቢያ በኢራን ላይ ጫና ለመፍጠር ያለመ ሊሆን እንደሚችልም ተገልጿል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
108😁 9🤯 4👏 3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የሁለት ወር የልጆች የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም) 💡ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 7-18  ዓመት ላሉ ልጆች የሚሰጥ ነው። 💡 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሰሩ የሚሰለጥኑበት 💡 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል 💡 ስልጠናው ጤናማ የ ስናክ ጊዜ ያካታል ፓኬጁ የሚያካትተው: • Basic Computer skill • Computer Programming • Visual art and painting • Language (chosen) • Abacus and Math tips የስልጠናው መጨረሻ ላይ 1.ፕሮጀክታቸውን ያቀርባሉ 2. ሰርተፍኬት ይሰጣቸዋል ይደውሉ ☎️ 0989747878 0799331774 በመራህያን የወደፊት ብሩህ ተስፋዎን የሚዘሩ ክህሎቶችን ይማራሉ !! 📍ሃያ ሁለት ፣ ከጐላጐል ወደ ቦሌ ሚወስደው ከ Hanan K Plaza አጠገብ ቢጫ ፎቅ ግራውንድ ፍሎር 10B ለበለጠ መረጃ፦ @merahyan
Hammasini ko'rsatish...
24
የኢራን የሚሳኤል ጥቃት በእስራኤል መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመት ማድረሱ ተገለፀ ***** ኢራን አርብ ዕለት በሰሜናዊና በማዕከላዊ እስራኤል ላይ የፈፀመችው ከባድ የሚሳኤል ጥቃት በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመት ማድረሱ ተገልጿል፡፡ የእስራኤል ወታደራዊ እርምጃ ተከትሎ ኢራን በእስራኤል ከተሞች ላይ በሁለት ዙር ከ150 በላይ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል መተኮሷ ተዘግቧል፡፡ የእስራኤል የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት፤ በጥቃቱ ቢያንስ 10 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል፡፡ በጥቃቱ ከ100 በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውም ቢቢሲ የእስራኤል የአገር ውስጥ የመገናኛ ብዙኃንም ጠቅሶ ዘግቧል። ስካይ ኒውስ የኢራንን ወታደራዊ ምንጮች ዋቢ በማድረግ እንደዘገበውም፤ ኢራን በፈፀመችው ጥቃት እያንዳንዳቸው 80 ሚሊዮን የሚያወጡ የእስራኤል ኤፍ35 ተዋጊ ጄቶችን መትታ መጣሏን ገልጻለች፡፡ እስራኤል በበኩሏ በፈፀመችው ጥቃት በቴህራን የነዳጅ ማከማቻ መጋዘን ላይ ውድመት ማድረሷን አስታውቃለች፡፡ እስራኤል ኢራንን ለመምታት ከተጠቀመችባቸው 100 የጦር ጄቶች መካከል እጅግ ዘመናዊ የሆኑት አዲር የሚል ስያሜ የተሰጣቸው እነዚህ ኤፍ35 ጄቶች እንደሚገኙበት ተነግሯል፡፡ የጦር አውሮፕላኖቹን ወደ ግዳጅ ለማሰማራት በሰዓት ለያንዳንዳቸው ከ44 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግም ነው የተገለፀው።
Hammasini ko'rsatish...
82👎 8🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
እስራኤል በመላው ዓለም የሚገኙ ኤምባሲዎቿን ዘጋች ** እስራኤል በኢራን ላይ የፈፀመችውን ጥቃት ተከትሎ በመላው ዓለም የሚገኙ ኤምባሲዎቿንና የቆንስላ ፅህፈት ቤቶቿን በጊዜያዊነት ዘግታለች። የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው ተለዋጭ መልእክት እስኪሰጥ ድረስ በመላው ዓለም የሚገኙ የእስራኤል ኤምባሲዎችና የቆንስላ ፅ/ቤቶች ተዘግተው ይቆያሉ ተብሏል፡፡ በውጭ ሀገራት የሚገኙ እስራኤላውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ማሳሰቡን ዘገባው አክሏል። የእስራኤል ጦር በኢራን ላይ በፈፀመው የአየር ጥቃት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የኒውክሌር ጣቢያዎች እና ወታደራዊ ኢላማዎችን መምታቱ ተነግሯል፡፡   T.me/ethio_mereja         ኢትዮ-መረጃ
Hammasini ko'rsatish...
67👍 51😱 7🤔 6🥰 5
Photo unavailableShow in Telegram
ጥንቃቄ❗️ በኢትዮጵያ የተገኘው የኤምፖክስ ቫይረስ ዝርያ "ከፍተኛ የሞት መጠን" እና "ሥርጭት" ያለው መሆኑ ተገለጸ ከአንድ ወር በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባው የኤምፖክስ (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) ቫይረስ ዝርያ "ከፍተኛ የሞት መጠን" የሚያስከትል እና በከፍተኛ መጠን የሚሠራጭ እንደሆነ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቁ። ከሁለት ሳምንት በፊት በበሽታው ሕይወቱ ያለፈው አንድ ወር እድሜ ያለው ሕጻን እንደሆነም ተቋማቱ ገልጸዋል። የጤና ሚኒስቴር እና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ይህንን ያስታወቁት ትናንት ረቡዕ ሰኔ 4/2017 ዓ.ም. ምሽት ባወጡት 'ወቅታዊ ማብራሪያ' ነው። ግንቦት 16 ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ የተረጋገጠው ኤምፖክስ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 18 ሰዎችን መያዙን የተቋማቱ መረጃ ያመለክታል። በበሽታው ከተያዙት ሰዎች መካከል አምስቱ "ሙሉ ለሙሉ" ማገገማቸውን መግለጫው ያስረዳል። የኤም ፖክስ ( Mpox) መተላለፊያ መንገዶቹም ፦ - የቅርብ ንክኪ፣ - በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የሚኖር የእጅ መነካካት፣ - በቫይረሱ የተያዘ ሰው የሚጠቀምባቸው ቁሳቁሶችን መጠቀም እና የፊት ለፊት የትንፋሽ ግንኙነት ናቸው። የኤም ፓክስ በሽታ ምልክቶቹ ፦ ° ከፍተኛ ትኩሳት፣ ° ራስ ምታት፣ ° የጀርባ ሕመም፣ ° የሰውነት ዕጢ እብጠቶች፣ ° ለመተንፈስ መቸገር፣ ° በሰውነት ክፍል ጎልተው የሚታዩ ሽፍታዎች ሲሆን ምልክቶችም ህመምተኛው በቫይረሱ ከተያዘ ከ5 እስከ 21 ቀናቶች ውስጥ የሚታዩ ናቸው። መከላከያ መንገዶች ፦ ° በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነቶችን  መገደብ ፣ ° እጅን በሳሙና መታጠብ፣ ° በበሽታ የተያዘ ሰው የሚጠቀምባቸውን ቁሳቁሶች በጋራ አለመጠቀም።   T.me/ethio_mereja         ኢትዮ-መረጃ
Hammasini ko'rsatish...
81👍 23😱 5🤯 2🤔 1
#Mpox በሽታ በአማራ ክልል በሁለት ሰዎች ላይ የኤም ፖክስ (Mpox) ቫይረስ መገኘቱን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በኤም ፓክስ (Mpox) በሽታ የተያዙ ሁለት ሰዎች መገኘታቸውን ገልፀዋል። በባህር ዳርና በመተማ ከተሞች በተገኙት ሁለቱ ሰዎች በተወሰደው ናሙና በኤም ፖክስ (Mpox) መረጋገጡን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ተገቢውን ህክምና እየተሰጣቸው መሆኑን አክለው ገልፀዋል። የኤም ፖክስ ( Mpox) ቫይረስ በቫይረስ የሚተላለፍ በሽታ ነው። መተላለፊያ መንገዶቹም ፦ - የቅርብ ንክኪ፣ - በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የሚኖር የእጅ መነካካት፣ - በቫይረሱ የተያዘ ሰው የሚጠቀምባቸው ቁሳቁሶችን መጠቀም እና የፊት ለፊት የትንፋሽ ግንኙነት ናቸው። የኤም ፓክስ በሽታ ምልክቶቹ ፦ ° ከፍተኛ ትኩሳት፣ ° ራስ ምታት፣ ° የጀርባ ሕመም፣ ° የሰውነት ዕጢ እብጠቶች፣ ° ለመተንፈስ መቸገር፣ ° በሰውነት ክፍል ጎልተው የሚታዩ ሽፍታዎች ሲሆን ምልክቶችም ህመምተኛው በቫይረሱ ከተያዘ ከ5 እስከ 21 ቀናቶች ውስጥ የሚታዩ ናቸው። መከላከያ መንገዶች ፦ ° በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነቶችን  መገደብ ፣ ° እጅን በሳሙና መታጠብ፣ ° በበሽታ የተያዘ ሰው የሚጠቀምባቸውን ቁሳቁሶች በጋራ አለመጠቀም። አቶ በላይ በዛብህ ለህብረተሰቡ ባስተላለፉት መልዕክት " የኤም ፓክስ በሽታ ተገቢው ህክምና ከተደረገ በቶሎ የሚድን በሽታ ሲሆን የግል ንፅህናን በመጠበቅና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ በሽታውን መከላከል ይቻላል " ብለዋል።
Hammasini ko'rsatish...
50👍 4