uz
Feedback
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

Kanalga Telegram’da o‘tish

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
166 319
Obunachilar
-1724 soatlar
-227 kunlar
-430 kunlar
Postlar arxiv
​​በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን፡፡ ✞✞✞ ✞ ጥቅምት ፳፯ (27) ✞ ✞✞✞ እንኳን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል:: ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ:: በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: 7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን ተናገረ:: ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: +በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: 11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው:: ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም:: በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል:: © ዝክረ ቅዱሳን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
295🕊 18
በዘመናት የሸመገለ በዘመናት የሸመገለ ክብርን ሁሉ የጠቀለለ እንደ ጌታ ኧረ ማን አለ እንደ እግዚአብሔር ኧረ ማን አለ
አዝ
ጥሎብኛል መጎናጸፊያ ለይቶኛል ከስጋ ጥድፊያ በሰው ሚዛን ክብርን ማይለካ እውነተኛ ጌታ ነው ለካ
አዝ
ደመና ነው መንኮራኩሩ ነበልባል ነው ዙፋን መንበሩ መሰወሪያው አይደረስም በማንም ሞት አይከሰስም
አዝ
ቀን ዘመናት ሁሉ ሲያረጁ አዲሶቹ ዘምነው ሲጃጁ ጌታ አዲስ ነው ሁሌ ማለዳ ፍቅር ያዘንባል ከልቡ ጓዳ
አዝ
መካኒቱን በልጅ ባረከ ኃይለኛውን አንበረከከ ለምስጊኖች ስለሚራራ በኢየሱስ ልባችን ኮራ ዘማሪ እስጢፋኖስ ሳህሌ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
በዘመናት_የሸመገለ_ክብርን_ሁሉ_የጠቀለለ_እደጌታ_እረ_ማን_አለ_እደ_እግዚአብሔር_እረማን_አለ128k.m4a4.99 MB
181🥰 8🕊 3🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
ጥቅምት ፳፮ /26/
‎ ‎በዚች ቀን ጌታችን ከመረጣቸውና በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ አጋንንትንም ያወጡ ዘንድ ሥልጣንን ከሰጣቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ቅዱስ ሐዋርያ ጢሞና በሰማዕትነት አረፈ። ‎ ‎ይህም ቅዱስ ጢሞና ሰማያዊ ሀብትን መለኮታዊ ኃይልን ገንዘብ አድርጎ በሽተኞችን ፈወሳቸው አጋንንትም ተገዙለት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ በምድር ሳለ አገለገለው። ወደ ሰማይም ከዐረገ በኋላ ሐዋርያትን አገለገላቸው በሃምሳኛው ቀንም ጰራቅሊጦስ በወረደ ጊዜ የአጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከእርሳቸው ጋር ተቀበለ። ‎ ‎ከዚህም በኋላ ሰባት ሁነው ከተቆጠሩት ዲያቆናት ጋር ሐዋርያት ሾሙት እነርሱ መንፈስ ቅዱስን ዕውቀትንም የተመሉ እንደሆኑ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ምስክር ሁኖአል። ‎ ‎በዲቁና አገልግሎትም ጥቂት ከአገለገለ በኋላ ብልቃ ከሚባል አገር በስተምዕራብ በሆነ ስብራ በሚባል አገር ላይ ኤጲስ ቆጶስነት ሾሙት በውስጧም ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሃይማኖት አስተማረ ከዮናውያንና ከአይሁድም ብዙዎችን አጠመቃቸው። ‎ ‎የዚያች አገር ገዥም ይህን በሰማ ጊዜ ቅዱስ ጢሞናን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይቶ በእሳት አቃጠለው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። ‎ ‎ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️ ‎
Hammasini ko'rsatish...
239🕊 14🥰 6
ወደ ምስራቅ እዩ ወደ ምስራቅ እዩ ወደ ፀሐይ መውጫ ድንግልን ክበቧት እንበል ሃሌ ሉያ ለአምላክ እናት ለአዛኚት እልል እንበል እንዘምርላት/2/ አዝ ወገኖች ተነሱ እናታችን መጣች ስሟን ስንጠራ መቼ ትቀራለች የተከዘን ልታፅናና ነይ ስንላት ትመጣለችና አዝ የጽጌው ማኃሌት መዝሙሩ ሲጀመር ማርያም ትመጣለች በደመና በአየር ንዒ ስንል በሳዕታት ልትባርከን ትመጣለች በእውነት አዝ ፍልሰታ ሲጀመር ቃል ኪዳን ገብታለች የሌሊት ውዳሴን ንዒን ትሰማለች ህጻናቱን በበረከት ልትጎበኝ ትመጣለች በእውነት አዝ በፍፁም ቸርነት እንዲምረን ጌታ በአማላጅነትሽ ሁኚልን መከታ እናታችን አለኝታችን እንድናለን ድንግል አንቺን ይዘን አዝ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ እስመ ዝንቱ ዑራኤል እስመ ዝንቱ ለዓለም ብርሐን     ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
6082726593_1.mp38.25 MB
101🥰 7🕊 3🔥 2
ጥያቄ❓ከመመለስዎ በፊት የእለቱን ስንክሳር ይመልከቱ። ለምትሳተፉ ለሁላችሁ ቃለ ሕይወት ያሰማልን። በዚች ቀን ታላቅና ክቡር  የሆነ አቢብ የተባለ መስተጋድል አባ ቡላ አረፈ።Anonymous voting
  • ‎ሀ. እውነት ‎
  • ለ. ሐሰት
0 votes
91🥰 5
አቤቱ ጉልበቴ ሆይ አቤቱ ጉልበቴ ሆይ  እወድሃለሁ /2/ አንተ ካሻገርከኝ  ሁሉን አልፋለሁ /2/
አዝ
ክንድህን እንዳላየሁ ኃይልህን እንዳላየሁ ሲመሽና ሲነጋ ዘወትር እጨነቃለሁ አንተ ግን ለሰላሜ ለእረፍቴ ቆመሃል ያዘነውን ልቤን ውስጤን አሳርፈሃል
አዝ
ሁልጊዜ ጠያቄ ነኝ መልስ የለኝም ጌታዬ አንተ ግን መፍትሄ ነህ ስደክም ለብቻዬ አይዞህ ስትል ስማውኝ ቃልህ ሲናገረኝ ዘወትር አምላኬ ነህ የማትተወኝ
አዝ
የብርቱዎች አምላክ ነህ  አውቃለሁ የእኔ ጌታ ለደካማው አንተ ነህ ኃይሉን ምታበረታ የተሸከመኝ ክንድህ ዝሎ አያውቅም ፍፅም የማምለጫ አለት ነህ ለነፍሴ ዘላለም
አዝ
በፈረሰው ግድግዳ  ሙሉ ሆነህ ቆመሃል ባለቀስኩኝ ጊዜ ጉልበቴን አግኝተሃል ልናገረው በሰው ፊት ሌላ ምን እከፍላለሁ አይነ ስውር ነበርኩኝ  ዛሬ ግን አይቻለሁ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
6082726593_1 (31).mp35.21 MB
166🥰 12
ጥቅምት ፳፭/25/
‎ ‎ በዚች ቀን ታላቅና ክቡር  የሆነ አቢብ የተባለ መስተጋድል አባ ቡላ አረፈ። ‎ ‎ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብርሃም  የእናቱም ‎ስም ሐሪክ ነው። እነርሱም ልጅ በአጡ ጊዜ የተባረከ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ በጾም በጸሎት ተወስነው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ የእግዚአብሔርም መልአክ በሕልም ተገለጠላቸውና ፍሬ የመላበትን ዘለላ ሰጣቸው። ‎ ‎ይህም ቅዱስ በተፀነሰ ጊዜ በቤታቸው አጠገብ ታላቅ ዛፍ በቀለ በቅጠሉም ላይ በሮማይስጥ ቋንቋ ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ በጽዮንም አድሮ የሚኖር የያዕቆብ ፈጣሪ ያከበረው የሚል ጽሑፍ ነበረበት። ‎ ‎ በተወለደም ጊዜ ክርስትና ሳያስነሡ ዓመት ሙሉ አኖሩት እመቤታችን ማርያምም ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለሰለባስትርዮስ ተገልጣ ወደ አብርሃም ቤት ሒዶ ሕፃኑን እንዲአጠምቀው አዘዘችው። አጠመቀው ስሙንም ቡላ ብሎ ሰየመው ‎ ‎ሕፃኑም ገና ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ ከሀዲ መኮንን ተነስቶ በብዙ አሰቃየው የመላእክት አለቃ ሚካኤልም መጥቶ አዳነው ያለ ጉዳትም ጤነኛ አደረገው። ‎ ‎ዕድሜውንም ፈጽሞ ከዚሀ ዓለም የሚወጣበት ጊዜ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ በእጁ ልዩ የሆኑ አክሊሎችን የሚያበሩ ልብሶችንም ይዞ ተገለጠለትና እስከ ዐሥር ትውልድ የሚያስምር ቃልኪዳን ተቀበለ። ይህንም ብሎ  በደረቱም ላይ አድርጎ ወደ አየር አወጣው ፡ ፡ የመላእክትንም ምስጋና በሰማች  ጊዜ ነፍሱ  ከሥጋው ተለየች ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ገባች። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️ ‎
Hammasini ko'rsatish...
244🕊 13😍 9🥰 4
አሳስቢ ምድር አሳስቢ ምድር ተጨንቃለች የሞት ጣር ይዟት ታነባለች አሳስቢ ለጻድቃን አይደለም ምልጃሽ ነው ዕረፍቷ ለዓለም!
አዝ
ሞት አዳምን ወግቶት ሲሰደድ ሲወጣ ከገነት አይቶሻል መጽናናቱ ሆነሽ አዳኙን ቤተልሔም ወልደሽ።
አዝ
ነሽ ዳግማዊ ሰማይ ያበራሽ የጽድቅንም ጸሐይ ማር በይው በቀኙ እንዳለሽ ይፈወስ ዓለሙ በምልጃሽ።
አዝ
ነይ ባርኪን በእጆችሽ ድንግል ሆይ በደመና ሆነሽ አድኚኝ እንድኖር በእቅፍሽ ፍቅርሽን ልቤ ላይ አትመሽ።
አዝ
ሰጥቶ እጁን ለነውር ርቋል ትውልዱ ከክብር ያብርደው ሞትና ጥፋቱን ድንግል ሆይ ማልጅልን ንጉሡን። ዘማሪት መቅደላዊት 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
6082726593_1 (28).mp37.67 MB
170🕊 10🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጥቅምት ፳፬ /24/
‎ ‎በዚች ቀን መስተጋድል መነኰስ አባ አብላርዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ጋዛ  ከሚባል አገር ነው። ወላጆቹም አረማውያን ናቸው የዮናናውያንንም ትምህርታቸውንና ፍልስፍናቸውን አስተማሩት ሰውነቱ ለጥበብ ማደሪያዋ እስከሆነ ድረስ በዕውቀቱ ከጓደኞቹ በላይ ሆነ። ‎ ‎ ከዚህም በኋላ ለጥበብ ትምህርት ወደ  እስክንድርያ ሔዶ በዛው የክርስትናን ተምሮ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ወደ አባ እንጦንዮስም ሔዶ መንፈሳዊ የሆነ ጥምቀት ተጠመቀ ከዚያም መንኵሶ የትሩፋትን ሥራ እየተማረ በእርሱ ዘንድ ብዙ ወራት ኖረ። ‎ ‎ወላጆቹም እንደሞቱ በሰማ ጊዜ ሒዶ የተዉለትን ገንዘባቸውን ሁሉንም ወስዶ ለድኆችና ለችግረኞች መጸወተ ከዚህም በኋላ ከሶርያ ገዳማት ወደ አንዱ ገዳም ገባ በዚያም በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት በመትጋት ፍጹም ገድልን ተጋድለ በየሰባት ቀን እስቲመገብ ድረስ ምግቡም የዱር ሣር ነበር። ‎ ‎እግዚአብሔርም ሀብተ ትንቢትን ሰጥቶት ልቡናው ብሩህ  ሆነ  ድንቆች ተአምራትንም  የሚያደርግ ሆነ ኤጲፋንዮስንም ያመነኰሰውና ለደሴተ ቆጵሮስም ኤጲስቆጶስ እንደሚሆን ትንቢት የተናገረለት እርሱ ነው። ‎ ‎የዚህም አባት መላ ዕድሜው ሰማንያ ዓመት ነው፡ከክርስትናውና ከምንኵስናው በፊት ዐሥራ ሰባት ዓመት በምንኵስናም ስልሳ ሦስት ዓመት ነው።ክብር ይግባውና እግዚአብሔርንም ካገለገለ በኋላ በሰላም አረፈ። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️ ‎
Hammasini ko'rsatish...
234🕊 11
የጽዮን ደጆች የጽዮን ደጆች ቅኔ ተሞሉ ለድንግል ክብር እልል እያሉ እንደ ነጭ እንቁ የሚያበራ አርፈናል ስሟን ስንጠራ/2/
አዝ
ኃይልን ለሚያደርገው ለተወዳጅ ስምሽ  የዜማ እቃችንን አነሳን ልጆችሽ  ማህተመ ቡራኬሽ በልባችን አለ  አፋችን ማርያም ሲል ጭንቃችን ቀለለ
አዝ
የምስጋና ጥበብ የቅኔ ሃብት ፀጋ ከደጃፍሽ መጥተን ገዛን ያለ ዋጋ ጥልቁን ወጥተነዋል በትከሻሽ ሆነን ፅዮንን በእልልታ በዜማ ሸፍነን
አዝ
ጠቢባን ምክራቸው ታየ ተሰውሮ ምስጢር ተገለጠ በህፃናት አእምሮ ቤተልሔም ሰማች የብስራቱን ዜማ ፍቅር ተለቀመ ከእግዚአብሔር ከተማ
አዝ
ከአሸናፊው ልጅሽ ከክርስቶስ ጋራ እንደ ዘበት ወጣን የሞትን ተራራ ፍሬሽን ቀምሰነው ልቦናችን ረጋ ሰላም ነው ከእንግዲህ አንኖርም ስንሰጋ
አዝ
ጠቢባን ምክራቸው ታየ ተሰውሮ ምስጢር ተገለጠ በህፃናት አእምሮ ቤተልሔም ሰማች የብስራቱን ዜማ ፍቅር ተለቀመ ከእግዚአብሔር ከተማ ዘማሪት ቅድስት ምትኩ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
Yetsiyon-Dejoch-የጽዮን-ደጆች.m4a8.49 MB
126🕊 4🔥 2🥰 2
እርሱን ስሙት እርሱን ስሙት እርሱን ልጄን ስሙት እርሱን ስሙት አንድያዬን ስሙት ይሞላል ወይናችሁ አይጎድልም ጓዳችሁ
አዝ
ቃሉ የታመነ ታምር የሚሠራ ይሞላል በቅጽበት ባዶውን እንስራ ስሙን ከታመነ ከጸና ልባችሁ አያልቅም ፈጽሞ ወይኑ ከጓዳችሁ ቢልም እንድዬ ጊዜዬ ገና ነው ወይኑ ከማድጋው ፍፁም እስኪያልቅ ነው
አዝ
በኤልሣ ማሠሮ የንበረ ያጨው ኤልሻዳዩ ጌታ መካከላችሁ ነው አትለፉት እርሱን ጠየቁት ሂዱና አያፍርም ፊታችሁ ወይኑ አልቆ በቃና ቢልም እንድዬ ጊዜዬ ገና ነው ወይኑ ከማድጋው ፍፁም እስኪያልቅ ነው
አዝ
ፅድቅ ያለቀበትን የልባችሁን ጋን በቃሉ እያጠበ አዲስ ወይን ይሞላል ዓለም ይፈወሳል ስትቀዱ ከጋኑ ከአእምሮ በላይ ነው በስሙ ታመኑ ቢልም እንድዬ ጊዜዬ ገና ነው ወይኑ ከማድጋው ፍፁም እስኪያልቅ ነው
አዝ
የአዲሱ ኪዳን አዲስ የወይን ጠጅ እንዴት ይጠመቃል ዶኪማስ በአንተ ደጅ ጠብቅ ቀራንዮ ሙሽራው ይነግሣል ዓለም የሚጠጣው ደም በዚያ ይፈሳል ቢልም እንድዬ ጊዜዬ ገና ነው ወይኑ ከማድጋው ፍፁም እስኪያልቅ ነው ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
6719386377 (1).mp36.43 MB
169
Photo unavailableShow in Telegram
ጥቅምት ፳፫ /23/
በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ኀምሳ ሁለተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ አረፈ። ይህም አባት ከመኑፍ አገር ከታላላቆች ተወላጆች ወገን ነው ወላጆቹም ብዙ ገንዘብ ያላቸው ነበሩ ታናሽም ሁኖ ሳለ አባትና እናቱ ትተውት ሲሞቱ ድኃ አደግ ሆነ አንድ እግዚአብሔርንም የሚወድ ሰው አሳደገው። አድጎ በጐለመሰም ጊዜ የወላጆቹን ገንዘብ ሁሉንም ወስዶ ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወተ ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወጥቶ ከአንድ ጻድቅ ሽማግሌ ሰው አባት ዘንድ መነኰሰ በበጎ ገድል ሁሉ እየተጋደለ ኖረ። ይህም ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ መናፍቃንን የሚገሥጻቸው ሆነ ሕዝቡንም ከአባቶቻቸው፤ በተቀበሏት በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ አስተማራቸው ከቅዱሳት መጻሕፍትም ለእነርሱም ሥውር የሆነውን ተርጕሞ ያስረዳቸዋል ያስገነዝባቸዋልም በትምህርቱና በጸሎቱም እንዲህ ጠበቃቸው ጌታችንም በእጆቹ ብዙዎች ተአምራትን አደረገ ያማረች ገድሉንም ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም በፍቅር አረፈ። መላ የሕይወቱም ዘመን ሰባ ስምንት ነው ከምንኵስና በፊት ሃያ ዓመት በምንኵስና ተጋድሎ ሠላሳ ዘጠኝ ዓመት በሊቀ ጵጵስና ሹመት ዓሥራ ዘጠኝ ዓመት ኖረ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
170🕊 8🥰 5😍 1
በከመ ምህረትከ ከአስሩ አንዱ ድንገት ቢጠፋባት ድሪሟን ፍለጋ ሴቲቱ ተነሳች ቤቷን ስታፀዳ አብርታ መብራቷን ከቆሻሻ መሃል አየችው ድሪሟን      ያድሪም እኔ ነኝ በቃልህ ማልገኝ በቤትህ ውስጥ ሆኜ በቤትህ ማታውቀኝ ከቆሻሻ መሃል ከምታገኛቸው አገልጋዮች መሃል እኔነኝ ዋነኛው በከመ ምህረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ
አዝ
የሰበከውን ቃል በህይወቱ ነዋሪ የጠፋው ርሱ ነው ሞልቷል ተናጋሪ በክፉ ስራዬ በኔ ተነቅፈሃል የስም ብቻ አገልጋይ መች ያስደስትሃል      ቅርብ ነው አንደበቴ ልቤ ግን የሸሸ ማንነቴ ባዶ በቃልህ ያልታሸ ዛሬ አስተካክለኝ ልታነፅ በቃልህ በእኔ አይሰደቡ ቅን አገልጋዮችህ በከመ ምህረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ
አዝ
ሀገሪቱ ረስታ መጎብኘቷ ወራት እንባህን አፍስሰህ ለሷ አለቀስክላት ዛሬ ብትመጣ በልቤ ከተማ አዝነህ ታለቅሳለህ በእኔ ምግባርማ      በመቅደስህ መሃል ድፍረቴ የበዛ ልቤ ለአለም እንጂ ለአንተ ያልተገዛ የስም ብቻ አገልጋይ መሆኔን ታውቃለህ ድሮስ ከእኔ አይነቱ ምንስ ታገኛለህ በከመ ምህረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ
አዝ
የቃኤል መሠዋዕት ከመቅደስህ ገብቶ አንድነት ተረስቶ ሁሉ ተለያይቶ እንክርዳዱን መሠዋዕት ቁራ በትኖታል ፍቅር አልባ መሠዋዕት መች ያስደስተሃል       ይቁም በመቅደስህ መሸጥ መለወጡ አፊንና ፊንሃስ ከመቅደስህ ይውጡ ሳሙኤልን መሠል ቅን አገልጋዮችህ በመቅደስህ ይብዙ ተናገር ይበሉህ በከመ ምህረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ አምላካችን ሆይ እንደቸርነትህ ነው እንጂ እንደበደላችን አይሁን/3/ ዘማሪ አቤል ተስፋዬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
6082726593_1 (27).mp37.64 MB
175
Photo unavailableShow in Telegram
ጥቅምት ፳፪ /22/
በዚህች ቀን ብልህ ጥበበኛ የሆነ ቅዱስ ወንጌላዊ ሉቃስ በሰማዕትነት አረፈ። ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስም ከተገደሉ በኋላ በሮሜ ሀገር የሚያስተምር ሆነ በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ ለምእመናን መልእክትን ይጽፍ ነበር። ጣዖት አምላኪዎች ከአይሁድ ጋር በመስማማት አንድ ግምባር ፈጠሩ በንጉሥ ኔሮን ፊት ቁመው ጮኹ ይህ ሉቃስ ብዙዎች ሰዎችን በሥራዩ ወደ ትምህርቱ አስገባቸው። ንጉሥ ኔሮንም ወደ ፍርድ አደባባይ ሉቃስን እንዲአቀርቡት አዘዘ። በኔሮንም ፊት ቀርቦ በቆመ ጊዜ ንጉሡ በሥራይህ ሕዝቡን የምታስት እስከመቼ ነው አለው ቅዱስ ሉቃስም እኔ ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያው ነኝ እንጂ ሥራየኛ አይደለሁም ብሎ መለሰለት። ንጉሥ ኔሮንም እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይቺን እጅህን እኔ እቆርጣታለሁ ይህንንም ብሎ የቀኝ እጁን እንዲቆርጡ አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ ንጉሥ ሆይ እኛ የዚህን ዓለም ሞት እንደማንፈራ እወቅ ነገር ግን የጌታዬንና የፈጣሪዬን ኃይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይሃለሁ። ይህንንም ብሎ የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደ ቀድሞዋ ደኅነኛ አደረጋት። በኋላ ለያት በዚያም የነበሩ አደነቁ የሠራዊት አለቃውና ሚስቱ ብዙዎችም ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ቁጥራቸውም አራት መቶ ሰባ ሰባት ነፍስ ሆነ ንጉሡም ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
235🕊 16🥰 15🔥 3
እኛ ግን ስላንቺ የነገስታት ንጉስ ፈጣሪን ወልደሽ እንዴትስ መመስገን ማርያም ይነስሽ ዓለም ለማመስገን እውነቱ ቢከብደው እኛ ግን ስላንቺ ምንለው ብዙ ነው/2/
አዝ    
ከሰማያት መጣ የሚደነቅ ክብር ሰማን ከገብርኤል ለአንቺ ሲነገር እውነቱን ለማወቅ ዓለም ምን ጋረደው የሕይወቱን ምግብ ከማነው ያገኘው እኛ ስለገባን ጸጋና ክብርሽ እጅጉን አብዝተን ማርያም ወደድንሽ/2/
አዝ
ማንም ሠው ለእናቱ ክብር እንደሚሻ ለአንቺ ያለን ፍቅር የለው መጨረሻ ስንዘምር ስንጠራሽ ዓለም ብዙ ቢለን የገባንን እውነት እንዲያይ ወደድን እኛ ስለገባን ጸጋና ክብርሽ እጅጉን አብዝተን ማርያም ወደድንሽ/2/
አዝ
ዝም የሚል አንደበት የለንም ለክብርሽ በደማችን ሰርጿል ስምሽና ፍቅርሽ ፀሀይን ስላየ ዓለም ደስ ካለው አንቺን ለማመስገን ስለምን ከበደው እኛ ስለገባን ጸጋና ክብርሽ/2/ እጅጉን አብዝተን ማርያም ወደድንሽ/2/
አዝ
ከቶ በሠው ልማድ ፍጹም ያላየነው እናት ሆኖ ድንግል አንቺን ነው ያየነው ገና ብዙ ብዙ ብዙ ቃላት አለን ማነው ከማመስገን ማነው የሚያስተወን እኛ ስለገባን ጸጋና ክብርሽ እጅጉን አብዝተን ማርያም ወደድንሽ/2/                  ዲያቆን አቤል መክብብ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
6082726593_1 (26).mp37.32 MB
146🥰 4🕊 4🔥 1
በኃጢያት ያደፈ በኃጢያት ያደፈ ሆኗል ሰውነቴ አብቂኝ ለንስሀ አማልጅኝ እናቴ
አዝ
በኃጢያት ያደፈ በሐጢያቴ ብዛት በኃጢያት ያደፈ ልቤ ሲታወር በኃጢያት ያደፈ ተብትቦ ሳይጥለኝ በኃጢያት ያደፈ የሐጢያቴ ድር በኃጢያት ያደፈ በጣጥሰሽ ጣይልኝ በኃጢያት ያደፈ የሐጢያቴን ወጥመድ በኃጢያት ያደፈ ድንግል ሆይ አስታርቂኝ በኃጢያት ያደፈ አርቂኝ ከዚህ ጉድ አዝ በኃጢያት ያደፈ መቆም አቅቶኛል በኃጢያት ያደፈ በደሌ በዝቶብኝ በኃጢያት ያደፈ እማፀንሻለሁ በኃጢያት ያደፈ ልመናዬን ስሚኝ በኃጢያት ያደፈ ሐጢያቴን መሸከም በኃጢያት ያደፈ እኔ አልቻልኩምና በኃጢያት ያደፈ እናቴ ሆይ ስሚኝ በኃጢያት ያደፈ ድንግል በፅሞና
አዝ
በኃጢያት ያደፈ ነገ ዛሬ እያልኩኝ በኃጢያት ያደፈ  ቀጠሮ ሳበዛ በኃጢያት ያደፈ ዘመኔ ሲፈፀም በኃጢያት ያደፈ ሁሉም እንደዋዛ በኃጢያት ያደፈ  የመዳን ቀን አሁን በኃጢያት ያደፈ እንደሆነ ዛሬ በኃጢያት ያደፈ አስታውሽኝ እናቴ በኃጢያት ያደፈ እንዳላጣ ፍሬ ሊቀ መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
6719386377.mp34.84 MB
231🥰 4🔥 3🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
‎ጥቅምት ፳፩ /21/
‎ ‎በዚችም ቀን የነቢይ ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ ። ይህም የእስራኤልን ልጆች የሚያስተምርና የሚገሥጻቸው ነበር ስለ ክርስቶስም በኢየሩሳሌም መኖርና ማስተማር ትንቢት ተናገረ ። ደግሞም ስለ መከራው በሐዋርያትና በሰባ ሁለቱ አርድእት በሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ላይ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ እንዲህ ሲል ተናገረ። ‎ ‎ከዚህ በኋላ በሥጋዊ በደማዊ ሰው ሁሉ ከመንፈሴ አሳድርበታለሁ ሴቶች ልጆቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ ትንቢትን ይናገራሉ አለቆቻችሁ ሕልምን ያልማሉ ጎልማሶቻችሁም ራእይን ያያሉ ። ሁለተኛም እንዲህ አለ ያን ጊዜ ከተራራው ማር ከኮረብታውም ወተት ይፈሳል በቤተ እግዚአብሔር አጠገብ ካሉ ከይሁዳ አገሮች ሁሉ ምንጩ ከላይ ወደታች ይፈሳል ። ‎ ‎ሙታን በሚነሡ ጊዜ ስለሚሆነው የፍርድ ሰዓት እንዲህ አለ ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ የከዋክብትም ብርሃናቸው ይጠፋል ። የትንቢቱንም ወራት አድርሶ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ ። ‎ ‎ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️ ‎
Hammasini ko'rsatish...
228🕊 15🥰 11
ያንተ ልሁን ብቻ ያንተ ልሁን ብቻ  ባይቀናም ጉዞዬ ያንተ ልሁን ብቻ  ባይሞላም ጓዳዬ ያንተ ልሁን ብቻ  ባይሰምርም መሻቴ ለጥያቄዬ መልስ  ቀን አለህ አባቴ
አዝ
እጠብቅሃለው አላጉረመርምም መፃጉን አይቼ ከቶ አላማህም ትመጣለህ ጌታ አታጥፍም ቃልህን አትዘገይም አንተ ታውቃለህ ስራህን ታማኝ ነህ የማትከዳ የማይለውጥህ ዘመን በእምነት ልከተልህ በምልክት ሳይሆን/2/
አዝ
ለይስሐቅ ስም ሆነው የሳራ ፈገግታ ቤቷ ተከደነ በዘላለም ደስታ ነገር ስትለውጥ ስትቀይር እንዲህ ነው ውብ ታደርገዋለህ ሁሉንም በጊዜው ታማኝ ነህ የማትከዳ የማይለውጥህ ዘመን በእምነት ልከተልህ በምልክት ሳይሆን/2/
አዝ
አባትነትህን  ከዓለም ያስበለጡ ምልክት ሳይሹ በእምነት ተለወጡ ማድጋውን ሳይሆን ፍቅርህን እያዩ መከራን ታግሰው ከፍ ብለው ታዩ ታማኝ ነህ የማትከዳ የማይለውጥህ ዘመን በእምነት ልከተልህ በምልክት ሳይሆን/2/
አዝ
የኔ ያልኩት ነገር ከእጄ  ቢበተን ተስፋ ያደረኩት ሁሉ ከንቱ ቢሆን እኔ አላማርርም ለአመፅ አልነሳ አንተ የሰጠኽኝን አንተ ስትነሳ ታማኝ ነህ የማትከዳ የማይለውጥህ ዘመን በእምነት ልከተልህ በምልክት ሳይሆን/2/ ዲ/ን ብስራት ተሾመ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
6082726593_1 (25).mp314.60 MB
159🥰 9
ጥያቄ❓ከመመለስዎ በፊት የእለቱን ስንክሳር ይመልከቱ። ለምትሳተፉ ለሁላችሁ ቃለ ሕይወት ያሰማልን። ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤልሳዕ ከ----------ነገድ ነው።Anonymous voting
  • ‎ሀ. ብንያም ‎
  • ለ. ሌዊ‎
  • ሐ ይሁዳ‎
  • መ. ይሳኮር
0 votes
110🕊 20
Photo unavailableShow in Telegram
ጥቅምት ፳ /20/ ዳግመኛም በዚህች ቀን የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ የሆነ የታላቅ ነቢይ የኤልሳዕ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። እርሱም አሜሁላ ከሚባል አገር ከይሳኮር ነገድ ነው ብዙ ትንቢትን ተናግሮአል ብዙ ተአምራትንም አድርጓል። የኢያሪኮም ሰዎች ኤልሳዕን ጌታችን እንደምታያት የዚች አገር ኑሮዋ ያማረ የተወደደ ነው የአገሩ ውኃ ግን ክፉ ነው ሴቶች ሲጠጡት ይመክናሉ አሉት ኤልሳዕም ጨው ጨምራችሁ አዲስ ሸክላ አምጡልኝ አላቸው እነርሱም አመጡለት ። ኤልሳዕም ወደ ውኃው ምንጭ ሒዶ ያንን ጨው በውስጡ ጨመረውና እግዚአብሔር እንዲህ አለ እርሱን ከመጠጣት የተነሣ የሚሞት እንዳይኖር የሚመክንም እንዳይኖር ይህን ውኃ ለውጥኩት አለ አላቸው ። ከዚያችም ቀን በኋላ ኤልሳዕ እንደተናገረ እስከ አሁን ድረስ ያ ውኃ ተለወጠ። የዚህ የነቢይ ኤልሳዕ ተአምራቱ ብዙ ነው የሶርያውን ሰው ንዕማንን ከለምጹ ያነጻው እርሱ ነው ሁለት ሙታንን አንዱን በሕይወት ሳለ ሌላውንም ከሞተ በኋላ አስነሥቷል። የትንቢቱንም ወራት ፈጽሞ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Hammasini ko'rsatish...
266🕊 17🔥 2🥰 1