uz
Feedback
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

Kanalga Telegram’da o‘tish

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
44 133
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
-22730 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
በጋምቤላ ክልል የማህፀን በር ካንሰር ክትባትን በተመለከተ በተማሪዎች ዘንድ የተዛባ አመለካከት መኖሩ ተነገረ በክልሉ የማህፀን በር ካንሰርን ለመከላከል  ጥረት ቢደረግም በተማሪዎች ዘንድ ስለ መከላከያ ክትባት አስፈላጊነት የተዛባ አመለካከት መኖሩ የጋምቤላ ጤና ቢሮ አስታውቋል።የማህፀን በር ካንሰር በሴቶች እንዲሁም በማህበረሰቡ ዘንድ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የሚመለከታቸው አካላት ትብብር እንደሚያስፈልግ የክልሉ ቢሮ አስታውቋል። ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም ለእምነት ተቋማት መሪዎች እና ለሌሎች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ከጉዳዮ ጋር በተገናኘ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል።በክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶች እና ህፃናት ዳይሬክተር አቶ ኡጁሉ ኡሞድ የማህፀን በር ካንሰር የማህበረሰብ ጤና እክል ከመሆን በተጨማሪ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ባለድርሻ አካላት በትብብር እንዲሰሩ አሳስበዋል። የክልሉ ጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድም አገኘሁ በላይነህ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ስለ ማህፀን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት አስፈላጊነት ግንዛቤ ቢኖርም የተወሰኑ ተማሪዎች የተዛባ መረጃ አላቸው ።የትምህርት አመራሮች እና መምህራን የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንደሌለው ለታዳጊ ሴቶች ማስገንዘብ እንደሚኖርባቸው ገልፀው ሚናቸው ሊጠናከር ይገባል  ነው ያሉት። ትምህርት ቤቶች እና የሀይማኖት ተቋማት ከመደበኛ አገልግሎቶቻቸው ጎን ለጎን ስለ ማህፀን በር ካንሰር አስከፊነት እና ስለ ክትባቱ አስፈላጊነት ግንዛቤ መስጠት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።በአሁኑ ወቅት በክልሉ ዕድሜያቸው 9 ዓመት ለሆናቸው ታዳጊ ሴቶች ከማህፀን በር ካንሰር በሽታ ለመከላከል የመከላከያ ክትባት እየተሰጠ እንደሚገኝ ቢሮው ገልጿል። በቅድስት ደጀኔ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
5👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
መረጃ ከመቀሌ የትግራይ የጸጥታ ኃይሎች አባላት የጊዜያዊ አስተዳደሩን ቢሮ መክበባቸውን ለቢቢሲ ትግርኛ ገልፀዋል። የትግራይ የጸጥታ ኃይሎች አባላት “የደመወዝ ክፍያ ዘገየ” በሚል ቅሬታቸውን መሳሪያዎቻቸውን ይዘው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ህንፃን ከበውታል። የአርሚ 31 ጦር 71 አባላት ትናንት ረቡዕ ምሽት ከአራጉሬ (እንደርታ) አካባቢ ወደ መቀሌ መጥተው አመፅ እንዳስነሱ ታውቋል። ዛሬ ጠዋት የአስተዳደር ህንፃውን ከበውታል። ከዚህ በተጨማሪ የ “አርሚ 31  ኮር 312 ክፍለ ጦር  ረመፅ የሚባለው ዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም 5:05 የመሳሪያ ማስቀመጫ መጋዘን በመስበር ትጥቃቸውን በመታጠቅ ከነሩበት ቦታ ወደ መቀሌ በመገስገስ ላይ መሆናቸውን ምንጮች ጠቁመዋል። የፌደራል መንግሥቱ በጀት በወቅቱ ባለመልቀቁ በትግራይ ክልል ደመወዝ በወቅቱ መክፈል እንዳልተቻለ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲሁም ህወሃት በተናጠል ለፌደራል መንግስቱ ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል። #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
😁 15 5🤣 3🤔 1
በመጨረሻ ከ9 ዓመት የኩላሊት እጥበት በኃላ ሜላት የኩላሊት ንቅለ ተከላ ተደረገላት የ9 ዓመት ስቃይ ፍጻሜ - የአርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም የልግስና ውርስ ዛሬም ሕያው ሆኗል! ቱርክ/አዲስ አበባ - (ህዳር 25 ቀን 2018) - ታዋቂው አርቲስት ጋሽ ፍቃዱ ተክለማርያም ከ9 ዓመታት በፊት ያሳዩት ታላቅ ሰብዓዊነት ዛሬ ላይ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘቱ ተነገረ። አርቲስቱ በኩላሊት ህመም ተይዛ ለነበረችው ወጣት ሜላት አሰፋ ያደረጉት ልግስና፣ ወጣቷ ቱርክ በሚገኝ ሆስፒታል በተሳካ ሁኔታ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንድታደርግ መንገድ ከፍቷል። *"እኔ እድሜዬ ገፍቷል፤ ከእኔ ይልቅ እሷ ትታከም" በማለት ለእርሳቸው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ከተሰበሰበው የሕክምና እርዳታ ገንዘብ ላይ ለሜላት አሰፋ በማካፈል ታላቅ ሰብዓዊነትን አሳይተዋል። * ሜላት አሰፋ ይህንን የገንዘብ ድጋፍ ተከትሎም ቢሆን ለተለያዩ ምክንያቶች ንቅለ ተከላውን ማከናወን ሳትችል ቀርታ፣ ለዘጠኝ ተከታታይ ዓመታት በኩላሊት እጥበት (Dialysis) ላይ በመቆየት ስትታገል ቆይታለች። የንቅለ ተከላው ስኬት የተረጋገጠው በቱርክ በሚገኘው Acıbadem Hospital ሲሆን፣ ወጣቷ በአሁኑ ወቅት ጤንነቷ ተረጋግቶ በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። Melat Melina Assefa እንኳን ደስ አለሽ Via Awoke Tesfu Ayalew 🌴🌴🌴
Hammasini ko'rsatish...
👍 32 23🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ትራምፕ በሶማሊያ ስደተኞች ላይ የሰጡትን አፀያፊ ያሉትን ንግግር ውድቅ አደረጉ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ውስጥ በሚኖሩ የሶማሊያ ስደተኞች ላይ የሰጡትን አፀያፊ አስተያየት ውድቅ እንዳደረጉ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል።ትራምፕ በበርካታ ሀገራት ላይ አሉታዊ አስተያየቶችን ሰጥተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ በኢኖቬሽን ጉባኤ ላይ ባደረጉት ምላሽ ከመስጠት ይልቅ "በቀላሉ ወደ ፊት መሄድ ይሻላል" ሲሉ መናገራቸዉ ተሰምቷል። ሶማሊያውያን በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ይዘርፋሉ ግን ለሀገራችን አስተዋጾ የላቸዉም፡፡ ምንም የሚያዋጡ አይደሉም።በሀገራችን እንዲኖሩ አልፈልጋቸውም። አገራቸውንም በምክንያት አይጠቅምም ፤እኛ ደግሞ በአገራችን አንፈልጋቸውም፤" ሲሉ አክለዋል።በተጨማሪም “በአንድ ወይም በሌላ መንገድ መሄድ እንችላለን እናም ወደ አገራችን ቆሻሻን መውሰድ ከቀጠልን በተሳሳተ መንገድ እንሄዳለን” ብለዋል ። እ.ኤ.አ. በ2016 ለፕሬዝዳንትነት ከተወዳደሩበት ጊዜ ጀምሮ፣ ትራምፕ ወደ አሜሪካ የሚገቡትን በተለይም ከአንዳንድ ሀገራት የሚመጡ ስደተኞችን በመተቸት እና በአብዛኛው በወንጀለኞች የተደራጁ መሆናቸውን በመግለጽ ይታወቃሉ።የሚኒሶታ ገዥ የሆኑት ቲም ዋልዝ የአካባቢውን የሶማሊያ ነዋሪዎች አሞካሽተው ትራምፕን ወቅሰዋል፡፡ “ወደዚህ የመጡትን የእርስ በርስ ጦርነትን ሸሽተው ነዉ፣ ሚኒሶታና ይህችን አገር የተሻለ የሚያደርጋት ንቁ ማህበረሰብ ፈጥረዋል” ሲሉ ተናግረዋል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
20😁 2
በተጭበረበረ ሰነድ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ የወሰዱ መንጃ ፍቃዳቸው ተሰረዘ የአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ባለስልጣን በተቋሙ ከሚሰጣቸዉ በርካታ አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ የውጭ መንጃ ፍቃድ ቅያሬ አገልግሎት ነዉ ። በአዋጅ ቁጥር 1074/2010 መሰረት ያቀረበው የውጭ መንጃ ፍቃድ ሰነድ ትክክለኛነቱ በሚመለከታቸው አካላት ሲረጋገጥና የሰጠው አገር የኢትዮጵያን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ በተመሳሳይ መልኩ የሚቀበል መሆኑ ሲረጋገጥ ምትክ የሚሰጣቸው መሆኑን እንደሚደነግግ የባለስልጣኑ መረጃ ያመለክታል ። በዚህ መሰረት የተጭበረበረ ሰነድ በማቅረብ የመንጃ ፍቃድ ቅያሬ አገልግሎት ያገኙ ግለሰቦች መንጃ ፍቃዳቸው ተሰርዞ በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ በመሰራት ላይ እንደሚገኝ እና በቀጣይም ተቋሙ ህገወጥነትን የመከላከል ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል ። በሰመሀር አለባቸው #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
17😁 6👏 2
የዛሬውን ተጠባቂ ጨዋታ ማን ያሸንፋል?Anonymous voting
  • አርሰናል
  • ብሬንትፎርድ
  • አቻ
0 votes
👍 14🔥 6 3👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
የቀድሞ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ሃላፊ ሞገሪኒ በማጭበርበር እና በሙስና ወንጀል ተከሰሱ የቀድሞ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ሃላፊ ፌዴሪካ ሞገሪኒ እና ሌሎች ሁለት ሰዎች በግዥ ማጭበርበር እና በሙስና ፣በጥቅም ግጭት እና ሙያዊ ሚስጥራዊነትን በመጣስ ክስ እንደቀረበባቸው የአውሮፓ የህዝብ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ረቡዕ እለት አስታውቋል። ሶስቱ ግለሰቦች በአውሮፓ ህብረት የማጭበርበር ምርመራ ማክሰኞ እለት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ምርመራው በሂደት ላይ እያለ አሁን ከእስር መለቀቃቸውን ዘገባዎች አመላክተዋል። ሌሎቹ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በብሩጌስ በሚገኘው የአውሮፓ ኮሌጅ ከፍተኛ ባልደረባ እና የአውሮፓ ኮሚሽን ከፍተኛ ባለሥልጣን እንደሆኑ ታዉቋል። ሶስት ምንጮች ለሮይተርስ እንደተናገሩት ከታሳሪዎቹ መካከል አንዱ የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት ስቴፋኖ ሳንኒኖ ናቸው።ሞገሪኒም ሆነ ሳንኒኖ አስተያየት አልሰጡም። "ሁሉም ሰዎች ጥፋተኛ ሆነው በቤልጂየም የህግ ፍርድ ቤት ጥፋተኝነታቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ ንፁህ እንደሆኑ ይገመታል" ሲል የአውሮፓ የህዝብ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት አስታዉቋል።የታሰሩት በብራሰልስ በአውሮፓ ህብረት ዲፕሎማሲያዊ አገልግሎት፣ በአውሮፓ ኮሌጅ በርካታ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናትን በሚያስተምር ብሩገስ የሚገኝ ከፍተኛ ዩኒቨርስቲ  እና በተጠርጣሪዎች ቤት ውስጥ የተደረገውን ወረራ ተከትሎ ነው። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
8
ራቅ ባሉ የገጠር አካባቢዎች ላይ እየተሰራ ባለው የኤሌክትሪክ ዝርጋታ መጠን ነዋሪዎች  በአቅም  እና በግንዛቤ እጥረት ምክንያት ተጠቃሚ እየሆኑ አይደለም ተባለ የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጸሃይ ሃይል እንደ ሀገር ያለው አቅም ከፍተኛ ቢሆንም ተግባራዊ እየተደረገ ያለው በጣም  ውስን እና ጅማሬው ላይ መሆኑን  በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጥላሁን ብርሃኑ  በተለይ ለብስራት  ሬዲዮ ተናግረዋል።እንደ ተቋም ሶስት ፕሮጀክቶች ላይ እየተሰራ ሲሆን ይህም በአለም ባንክ  ፋይናንስ 12  ቀበሌዎችን  የማገናኘት እቅድ ተይዞ 11 የሚሆኑትን  ማገናኘት ተችሏል። ሁለተኛው በአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ ድጋፍ  20 ቀበሌዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ዘጠኙን ማገናኘት የተቻለ ሲሆን 11 የሚሆኑት  በኮንስራሽን ላይ ይገኛሉ ። የመጨረሻው ፕሮጀክት በዓለም ባንክ ተባባሪነት 100 ከተሞችን የማገናኘት እቅድ መሆኑን 83 ለሚሆኑት ዝርጋታው የተጠናቀቀ መሆኑን እና በአጠቃላይ ከ 6ሺ በላይ የገጠር አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸውልናል። ኃላፊው አክለውም በሚፈሰው ሀብት መጠን ደንበኞች ተጠቃሚ እየሆኑ እንዳልሆነ ይህም የሆነው አካባቢዎቹ ከከተሞች የራቁ መሆናቸው፣  የአቅም ውስንነት እና የግንዛቤ እጥረት ዋና ዋና ምክንያት ሲሆኑ ይህም በሚጠበቀው ልክ ተጠቃሚ እንዳላደረጋቸው ተገልጿል፡፡የኤሌክትሪክ  አገልግሎትን በፍጥነት ለበርካቶች   ለማዳረስ ከመንግስት በተጨማሪ  የግሉ ዘርፍ እና ማህበረሰቡ ትኩረት ሰጥተው መሳተፍ እንዳለባቸው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጥላሁን ብርሃኑ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
8😁 4🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ሩሲያ ለረዥም ጊዜ ግጭት እየተዘጋጀች ነው ሲል ኔቶ አስታወቀ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ኔቶ ዋና አዛዥ ማርክ ሩት ሩሲያ "የእኛን መከልከል ምን እንደሚመስል መሞከሯን ቀጥላለች" እናም "እውነተኛ እና ዘላቂ አደጋዎች ያጋጥሙናል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ሩት በመቀጠልም ሩሲያ የአየር ክልላችንን በጄት እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥሳለች፣ ሰላይ መርከቦችን ወደ ውሃዋ አካል ልካለች ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ እነዚህ ድርጊቶች “በግዴለሽነት የተሞሉ እና አደገኛ ናቸው” ሲሉ አክለዋል።ሩሲያ ከቻይና፣ ሰሜን ኮሪያ እና ኢራን ጋር “ህብረተሰባችንን ለማወክ እና ዓለም አቀፍ ህጎችን ለመበጣጠስ” በቅርበት እየሰራች ነው፣ እናም “ለረጅም ጊዜ ግጭት እየተዘጋጀች ነው” ሲሉ አክለዋል።ሩት የኔቶ ሀገራት የመከላከያ ኢንቨስትመንታችንን እያጠናከሩ ነው ብለዋል ።አክለውም ዩክሬን "የእኛን ድጋፍ ከምንጊዜውም በላይ ትፈልጋለች" ምክንያቱም ክረምት እየመጣ ነዉ ደግሞም የሩሲያ ጥቃቶች እንደቀጠለ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ቭላድሚር ፑቲን እና የዩናይትድ ስቴትስ ተደራዳሪዎች የዩክሬን የሰላም ስምምነትን በማረጋገጥ ላይ አንድ ለውጥ ማምጣት ያቃታቸው እንደሚመስል ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡የሩሲያ ባለስልጣናት ውይይቱ "ገንቢ" ነበር ነገር ግን "ምንም ስምምነት" ላይ አልተደረሰም ብለዋል፡፡የኔቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሰላማዊ ድርድር ላይ ለመወያየት በብራስልስ ተገናኝተዋል፡፡ቀደም ሲል ፑቲን የአውሮፓ የሰላም ስምምነት ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም ሲሉ ተናግረው "ከአውሮፓ ጋር አንዋጋም ነገር ግን አውሮፓ ከእኛ ጋር መዋጋት ከፈለጉ አሁን ዝግጁ ነን" ብለዋል፡፡ በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
10😁 6
Photo unavailableShow in Telegram
የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የምግብ አምራች እና አገልግሎት የሚሰጡ 10 ተቋማትን አሸገ የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በምግብና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር በማዕከል እና በ11ዱ ቅርንጫፍ በህዳር ወር በ3ሺህ407 ተቋማት ላይ ቁጥጥር አከናውኗል፡፡ በተደረገው ቁጥጥር  110 ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን ከነዚህ መካከል 99 ተቋማትን የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው  10 ተቋማትን ደግሞ በጊዜያዊነት ታሽገዋል፡፡ 1 ተቋም ደግሞ የብቃት ማረጋገጫው እንዲሰረዝ ተደርጓል ሲሉ የባለስልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። የታሸጉት ቤቶች የምግብ አገልግሎት ሰጪ (ሬስቶራንት) እና የምግብ አምራች ማለትም እንጀራ መጋገሪያ እና የምግብ ዘይት ማምረቻ ተቋማት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ትምባሆ በማስጨስ እና የሀይጅን እና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ክፍተቶች በተደጋጋሚ ባለማስተካከል እና  የጤና ብቃት ማረጋገጫ ሳይዙ በመስራታቸው ተቋማቶቹ ላይ እርምጃ ሊወሰድ ተችሏል፡፡ በቀጣይ በርካታ ስራዎች ለመስራት የቀጣይ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በተለይም የቁጥጥር ስራው ስጋት ተኮር በሆነ መልኩ ለመስራትና ለህዝብ  ጤና አስጊ ሁኔታዎችን ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት በትኩረት ይሰራል ሲሉ የባለስልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
3
ከ11 ዓመታት በፊት የጠፋውን የማሌዥያ አየር መንገድ አዉሮፕላን ሚስጥር ለመፍታት ፍለጋው ቀጠለ የጠፋውን የማሌዢያ አየር መንገድ በበረራ ቁጥሩ ኤም ኤች 370 የሚታወቀዉን አዉሮፕላን ፍለጋ የቀጠለ ሲሆን ከአለም ታላላቅ የአቪዬሽን ሚስጥሮች አንዱን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በዚህ ወር መጨረሻ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታዉቋል።አውሮፕላኑ ቦይንግ 777 ሲሆን 227 ተሳፋሪዎችን እና 12 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. መጋቢት 8 ቀን 2014 ከማሌዢያ ዋና ከተማ ኩዋላ ላምፑር በመነሳት ወደ ቻይና ቤጂንግ ያቀና ሲሆን ወዲያዉ ከራዳር እይታ ተሰዉሯል፡፡የትራንስፖርት ሚኒስቴር ረቡዕ እለት በሰጠው መግለጫ "ፍለጋው አውሮፕላኑን የማግኘት ከፍተኛ እድል እንዳላቸው በተገመገሙ የታለሙ ቦታዎች ላይ ያተኩራል" ብሏል። ሚኒስቴሩ እንደገለፀው ዳግም የፍለጋ ጥረቱ መጀመር የማሌዢያ መንግስት በአደጋው ለተጎዱ ቤተሰቦች ምላሽ ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያጎላ ነው ማለቱን የበርናማ የዜና ወኪል ዘግቧል። በበረራዉ ላይ ከነበሩት መንገደኞች መካከል 2/3ኛው ቻይናውያን ሲሆኑ የተቀሩት ከማሌዢያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ አውስትራሊያ እንዲሁም ከሌሎች ሀገራት የተዉጣጡ ተሳፋሪዎች ነበሩ።የበረራ መርማሪዎች አውሮፕላኑ ለምን እንደጠፋ እንደማያውቁ በ495 ገፆች ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዉ ከአውሮፕላን አብራሪዎች ውጪ ሌላ አቅጣጫ እንዲቀይር ተደርጓል ሲሉ ግምታቸዉን ያስቀምጣሉ።የሳተላይት መረጃ እንደሚያሳየው አውሮፕላኑ የበረራ አቅጣጫዉን በመቀየር ወደ ደቡብ አቅጣጫ በመብረር ደቡባዊው የህንድ ውቅያኖስ በማቅናት ነዳጁ አጥቶ ተከስክሷል ተብሎ ይታመናል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
21😢 6😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
በባህል ህክምና መፍትሄ በማጣት ወደ ጤና ተቋም ከመጡት 468 ህፃናት 50 በመቶ የሚሆኑት እግር እና እጃቸውን እንዳጡ ተነገረ በኢትዮጵያ በተለያዩ አጋጣሚዎች የመውደቅ አደጋ አጋጥሟቸው ወደ ባህል ህክምና ሄደው መፍትሄ በማጣታቸው ወደ ጤና ተቋም ከሚመጡት 468 ህፃናት ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት እግር እና እጃቸውን እንደሚያጡ ተገልጿል። ወደ ጤና ተቋማት  ከመጡት 468 ህፃናት በአካላቸው ላይ የተለያዩ የጎንዮሽ ጉዳት እንደሚያጋጥማቸው እና ወደ ጤና ተቋም ከመጡት ውስጥም 5.6 በመቶ የሚሆኑት እግር እና እጃቸውን ለማጣት ተገደዋል ሲሉ ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት   የኢትዮጵያ የአጥንት እና መገጣጠሚያ ሀኪሞች ማህበር ፀሀፊ  ዶ/ር ንጉሱ ገብረዮሀንስ ናቸው ።ህፃናት ከትልቅ ሰው አንፃር ሲታዩ አምስት እጥፍ እግር እና እጃቸውን ለማጣት የተጋለጡ  መሆናቸውን ገልፀዋል። የጉልበት ፣የክርን እና ሌሎች የመገጣጠሚያ አጥንቶች መድረቅ እድላቸውም ከፍተኛ እንደሆነ እና በእነዚህ ችግሮችም  ህይወታቸው  እስከማለፍ ድረስ እንደሚያደርሳቸው  ተናግረዋል።በቦሳድ የጥናት ፕሮጀክት ውስጥ  570 የባህል ህክምና ባለሞያዎች (ወጌሾች) ተሳትፈዋል። በዚህም የወጌሽነት ጥበቡ ወይም አቅሙ ተሰጥቷቸው  የሚሰሩ እንዳሉ ሆነው በአብዛኛው ግን ምንም አይነት ስልጠና ያላገኙ ፣በራሳቸው ከቤተሰብ የተማሩ እና በድንገት ከሰው አይተው አገልግሎቱን የሚጀምሩ ናቸው። በባህል ህክምናው በኩል ያሉትን ክፍተቶች ለመሙላት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ወጌሻ ማነው የሚለውን ለመፍታት ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል ተብሏል። በተጨማሪም በትክክል ወጌሾችን የሚገልፅ ወይም ማነው የሚለውን  የሚፈታ ሰነድ ማዘጋጀት እና ወጌሾች ስልጠናውን በወሰዱት ልክ እየሰሩ ነው ወይ የሚለውን  በየጊዜው መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ ዶ/ር ንጉሱ ገብረዮሀንስ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
10😢 8💔 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
በጦርነት በምትታመሰው ምያንማር የአደንዛዥ እጽ ምርት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ተሰማ በማያንማር የሚገኘው የኦፒየም ፓፒ እርሻ በ10 ዓመታት ዉስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ምርቱ በጦርነት በምትታመሰዉ ሀገር ውስጥ በሁሉም ክልል እየጨመረ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።የተባበሩት መንግስታት የመድሀኒት እና የወንጀል ፅህፈት ቤት (UNODC) ባደረገው የቅርብ ጊዜ የምያንማር ኦፒየም ጥናት ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ17 በመቶ የጨመረ ሲሆን ይህም ከ 45,200 ሄክታር ወደ 53,100 ሄክታር ደርሷል። በአፍጋኒስታን የጦርነቱን መርገብ ተከትሎ ምርቱ ቢቀንስም ምያንማር በዓለም ታዋቂ የህገወጥ ኦፒየም ምንጭ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የመድሀኒት እና የወንጀል ፅህፈት ቤት አስታዉቋል፡፡የደቡብ ምስራቅ እስያ እና የፓስፊክ ውቅያኖስ የድርጅቱ ተወካይ ዴልፊን ሻንትዝ "ይህ በእርሻ ላይ ያለው ትልቅ መስፋፋት ባለፉት ዓመታት የኦፒየም ኢኮኖሚ ምን ያህል እንደገና እንደተቋቋመ ያሳያል እናም ለወደፊቱ ተጨማሪ እድገትን ያሳያል" ብለዋል ። እ.ኤ.አ. በ2024 እና 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ በምያንማር በእርሻ መሬት ምርቱ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፣በኦፒየም አመራረት መካከል ያለው ልዩነት በሀገሪቱ እያደገ በመጣው አለመረጋጋት ምክንያት ነው ሲል ድርጅቱ ገልጿል፡፡ "ግጭት እና የደህንነት እጦት እየተባባሰ መምጣቱ" ገበሬዎች ከዚህ ቀደም የሚያመርቱትን ሰብላቸውን በመተዉ ከፍተኛ የኦፒየም ምርት ለማምረት ፊታቸዉን አዙረዋል፡፡ በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
6
በአማራ ክልል ባለፋት ሶስት ወራት 166  ተንቀሳቃሽ ቅርሶችን መመዝገብ እንደተቻለ ተገለፀ ለተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ እየተጋለጡ የሚገኙ የቅርሶችን ደህንነት ለመጠበቅ ለቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ጥገና ከማድረግ ባለፈ ቅርሶችን የመመዝገብ ስራ መስራቱን የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል። የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አበበ እምቢአለ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በ2018 በጀት ሩብ ዓመት  የቅርሶችን ደህንነት ለመጠበቅ በቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ላይ ምዝገባ በማድረግ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲያገኙ የማድረግ ስራ ተሰርቷል።በዚህም በክልሉ የሚገኙ 166  ተንቀሳቃሽ ቅርሶችን መመዝገብ ተችሏል ብለዋል ። እንደዚሁም 11 የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶችን መመዝገብ እንደተቻለ ገልፀው 4ሺህ 2መቶ ለሚሆኑ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች የክትትልና የቁጥጥር ስራ ተከናውኗል።ከዚህም ባሻገር በቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ዙሪያ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መከናወኑን አቶ አበበ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።የቅርሶችን ደህንነት በመጠበቅ ስራ ስድስት የወሰን ክለላ የተደረገላቸው የአርኪዎሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ስፍራዎች መኖራቸውንም አክለዋል። በቅድስት ደጀኔ #ዳጉ_ጆርናል
Hammasini ko'rsatish...
9👎 3