uz
Feedback
መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿

መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿

Kanalga Telegram’da o‘tish

☑ ከጥንት አባቶቻች በተቸረን ሰሎሞናዊ ጥበብ ተፈጥሮ ያበቃላቸው የእፅዋት መድሀኒቶችን በመጠቀም ክፉ ዓይነ ጥላ ፣ በቤተሰብ ወይም በዘር የሚተላለፉ መናፍስት መፍትሔዎቻቸው ይተነተናሉ። ☑ አድራሻ ቁጥር 1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ቁጥር 2 አ/አ አየር ጤና እንዲሁም በተለያዩ የክልል ከተሞች እንልካለን 📞#0918834904 📞#0915310455 መልዕክት ካለዎት @merigetaamedeberhan

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
118 341
Obunachilar
-16024 soatlar
-1 0107 kunlar
-4 57830 kunlar
Postlar arxiv
እንዲሁም የፅንሱን ደም በመጠጣት ልጁን ለራሳቸው ይገብራሉ፡፡ በተለይ የቤተሰባችን ባዕድ አምልኮ ካለ እንደ ዛርና ዓይነ ጥላ ያሉ መናፍስት ዘራችንን በማምከን ሴቷን ማኅፀኗን በመዝጋት፤ ብታረግዝም ፅንሱን በማጨናገፍ፤ ቢወለድም ጤናማ ያልሆነ ልጅ ለምሳሌ ንቃተ ኅሊናው የቀነሰ፣ የአእምሮ እድገት ውሱንነትና የአካል እድገት መዘግየት ያለበት፣ በተለይ ከተፈጥሮ  ውጭ የሆኑ ልጆች እንዲወለዱ በማድረግ ከፍተኛውን ሚና ይጫወታሉ፡፡ እኛም እነዚህን ክሥተቶች በሳይንሱ መንገድ በመረዳት ፈታኛችንን እንዳንዋጋ ቀድመን በሥጋ እውቀት ተመልተናል፡፡ ብናውቅም ከመረዳት ውጪ በጸሎት መዋጋትን ስለማንሻ የጨለማው ዓለም ገዢ ሰለባዎች እንሆናለን፡፡ እነዚህ የአጋንንት ፍላጻዎች እንዳይወጉን ስለ ትዳራችን ጤናማነት፣ ጽነስ ከመፈጠሩ በፊት በቡራኬ እንዲመጡ አብዝቶ መጸለይን ስላልቻልን፣ ልጀቻችንን መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸው ሳይሆን ርኩስ መንፈስ የተጠናወታቸው እንዲሆኑ እናደርጋለን፡፡ እኛ ወላጆች በመንፈሳዊ ሕይወት ዝለት፣ በጸሎት ድክመት ምክንያት በልጆቻችን ላይ የሕይወት ዘመን የመከራና የፈተና ጦስን እናወርሳቸዋለን፡፡ የዛር መንፈስ እየባሰ ሲመጣ በተለይ ደም የለመደ ከሆነ አባትና ልጅን፣ ልጅንና እናትን፣ ወንድምና እህትን፣ በማጣላት ደም ሊያፋስስ ይችላል፡፡ ደሙን እንደ በዓል ግብር ይጠቀምበታል፡፡ ስለዚህ ፅንስ ከአንድም ሁለቴ ሲጨናገፍ፣ በማሕፀን ውስጥ ሲጠፋ ዝም ብለን በየሕክምናው ከምንሮጥ ቆም ብለን ወደ ኋላ እናስብ፡፡ ብዙ ጊዜ የቤተሰቦቻችንን ጣጣ ችግሮቻችንና የችግሮቻችን መንስኤ ሆነው እናገኛለን፡፡ ስለዚህ ወደ ጠበሉ ወደ ጸሎቱ ፊታችንን መልሰን ወደ ፈጣሪ ብንማጸን መፍትሔ እናገኛለን ጤናማ ልጅ እንወልዳለን፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ  በሳይንሱ ስም የተሰጣቸው፣ ግን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በማኅፀን በአጋንንት ከመጨናገፍ ተርፈው ግን የአጋንንት ሰለባ ሆነው የተወለዱትን ልጆችን አጋንንት እንዴት ለከፋ ሕይወት እንደዳረጋቸው እግረ ብዕራችንን እንይ፡፡ ለምሳሌ በሕክምናው ‹‹ዳውን ሲንድረም›› የሚባልም ሕመም አለ፡፡ ይህም የእድገትና የአእምሮአዊ መዘግየትን የሚያስከትለው የዘረ መል ክሮሞዞም 21 ችግር ነው፡፡ ይህ ያልተለመደ የሕዋስ ክፍፍል ከክሮሞዞም 21 ተጨማሪ የዘረ መል (ንጥረ ነገር) ውጤት ሲመጣ የተከሠተ የዘር ቀውስ ነው፡፡ ዳውን ሲንድረም ያለባቸው ልጆች ከውልደታቸው ጀምሮ የተለያዩ ምልክቶች ይታይባቸዋል፡፡ እነርሱም ፡- የሰውነት ጡንቻ መልፈስፈስና አቅም ማጣት፣ ትንሽ ጭንቅላት፣ ትንሽ ጆሮ፣ ትንሽ አፍ፣ አጭር አንገትና ከአንገት ጀርባ ደግሞ ከመጠን ያለፈ የተረፈ ቆዳ፣ ሰፋፊ አፍንጫ ናቸው፡፡ የሕመሙ ምልክት ከዚህም ከፍ ሲል በቋሚነት የሚገለጥባቸው መንገዶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ፡- የዕውቀት ጉድለት፣ ከሌሎች ሰዎች ያነሰና ሾጠጥ ያለ ራስ ቅል፣ የልብ ሕመም፣ ጆሮአቸው ድምጽ መሰብሰብ አቅሙ አናሳ የሆነና የመስማት ችግር ያለበት፣ በሽታ የመከላከል አቅም ማጣት፣ በአፍ መተንፈስ፣ ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት፣ የእንቅልፍ ችግር ፣ የእይታ ችግር ወዘተ …ናቸው፡፡ እንዲሁም ኦቲዝም (Autism) የተባለውን ብንመለከት ኦቲዝም በማኅበራዊ መስተጋብር እና ግንኙነት ፣ እንዲሁም በተገደበ እና ተደጋጋሚ በሆነ ባሕርይ ተለይቶ የሚታወቅ የእድገት በሽታ ነው፡፡ ኦቲዝም ያለባቸው ወላጆች በልጆቻቸው ሕይወት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ ምልክቶችን ያስተውላሉ፡፡ ሌላው አልዛይመርን ብንመለከት አብዛኞቹ የሳይንስ ሊቃውንት በሰዎች ላይ አልዛይመር የሚከሠተው በአንጎል ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ የዘረ መላዊ ፣ የአኗኗር ዘይቤዎች እና አካበቢያዊ ምክንያቶች ውሕደት በመፍጠር እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ከአንድ በመቶ በታች የሆነው የአልዛይመር በሽታ የሚከሠተው በተወሰኑ ሰዎች ላይ በዘር ለውጦች ምክንያት ነው፡፡ ግን ዋና ዋና ምልክቶቹ የማስታወስ ችሎታ መቀነስ፣ ግራ መጋባት ፣ የአእምሮ ማሽቆልቆል፣ የመረዳት ችግር፣ በምሽት ሰዓታት ግራ መጋባት፣ መገለል፣ መርሳት፣ የትኩረት ማነስ፣ ትውስታዎችን አለመፍጠር፣ የተለመዱ ነገሮችን ለይቶ አለማወቅ፣ ጠብ መፍጠር፣ ብስጭት፣ ራስን በተገቢው መልኩ አለመንከባከብ፣ ትርጉም የለሽ ቃላትን መደጋገም፣ እረፍት ማጣት፣ እየተንከራተቱና ሲጠፉ መዋል፣ ሥነ ልቦናዊ ድብርት ወዘተ ናቸው፡፡ እነዚህ ከላይ ያየናቸው የሾተላይ የዳውን ሲንድረም፣ የኦቲዝም፣ የአልዛይመር  ምልክቶች ተብለው የተጠቀሱት በሙሉ ክፉ መናፍስት/አጋንንት፣ ዛር፣ ዓይነ ጥላ፣ ብዳ ወዘተ/ በሕፃናት እና በልጆች እንዲሁም በአዋቂዎች ላይ ሲያድሩ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው፡፡ አንዳንዱ ላይ መልክአ አጋንንት ተሥሎባቸው የሚወለዱ አሉ፡፡ ያ ማለት አስፈሪ ገጽታን ተላብሰው የሚታዩ፤ ሲያዩዋቸው የሚያሳዝኑ ሳይሆን የሚያስፈሩ ልጆች ሆነው ይታያሉ፡፡ አጋንንት ከሥጋቸው ሲዋሐዱ ራሱን በሰው ገጽታ ሲገልጽ ልጆቹ አስፈሪ ገጽታን እንዲላበሱ ያደርጋል፡፡ ዛር እና ዓይነ ጥላ የልጆች ፊት ላይ ሲቀመጥ እራሱን በመሳል እራሱን በመምሰል ከተፈጥሮ ወጣ ያለ ገጽታ እንዲኖራቸው ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ ችግሮች በጊዜ ከታወቁ በጸሎት፣ በጸበል በእምነት እና በቅብዓ ቅዱስ መፍትሔ እና ድህነት የሚገኝባቸው ናቸው እምነት ትእግስት ፅናት ላላቸው፡፡ ካልሆነ ግን ችግሩን እና በዚህ የተቸገሩትን ልጆች ይዞ መኖር ነው፡፡ ❤ 4ኛ/ መተት ፦ አንድ ሰው በአንድ ሰው በመቅናት የሚያደርገው የምቀኝነት የአጋንንት ሥራ ነው፡፡ መተት በትዳር ዕድል በልጅ በባል/በሚስት በመቅናት የሚደረግ ክፉ አሠራር ነው፡፡ በትዳር ላይ መተት ከተደረገ ፈጣን የባሕርይ ለውጥ ማምጣትና ሰላም ማጣት ከዛም እስከ መለያየት የሚደርስ መጠላላት በመሃላቸው ሊፈጥር ይችላል፡፡ ታዲያ ሁለቱም በተለይም የተጋቢዎች ወገን የአጋንንቱን አሠራር ባለመረዳት ፍቺን እንደ አማራጭ በማየት በችኮላ፣ ትዕግሥት በማጣት አጋንንቱን ይተባበራሉ፡፡ የቤተሰብ ጣልቃ መግባት ለአጋንንቱ ጥሩ ከለላ ስለሚሆንና ቤተሰብን በጐ በመሰለ ሐሳብ በመደገፍ ይገባባቸውና በእነርሱ አድሮ የመለያየትን ሥራ ይሠራል፡፡ የሚያሳዝነው ሁለቱ ተፋቺዎች ምክንያት ያለው በሚመስል ባልታወቀ ምክንያት ተለያይተው ሌላ ቢያገቡ ትዳራቸው ከድጡ ወደ ማጡ ነው የሚሆንባቸው፡፡ ቀድሞ አጋንንት ስላፋታቸው ሁለተኛው ትዳር ውስጥ ጣልቃ በመግባት ማበጣበጥ ሰላም መንሳት ይጀምርና ያለያያል፡፡ በዚህም ተፋቺው ‹ትዳር› የሚባለው ነገር ሲነሳ ግፍግፍ በማለት ለልጆቻቸውና ለወዳጆቻቸው የትዳርን መጥፎ ገጽታ ብቻ በመናገር ቤተሰብን ተጽዕኖ ውስጥ በመክተት ታናናሾችንና ልጆችን ‹ትዳር ከእርሷ ወዲያ ላሳር› በማለት ትዳርን እንዲፈሩ ፈርተውም እንዳያገቡ በማድረግ ቆሞ ያስቀራል፡፡ ለዚህ መፍትሔው በትዳር ያልተጠበቀ ክሥተት ሲፈጠር መጸለይና አባቶችን በጸሎት እንዲረዱ ማድረግ፣ በተቻለ አቅም ጠበል መጠመቅ፣ ችግሩን ማወቅና ለችግሩ መፍትሔ ማግኘት ይቻላል፡፡ ወዳጆቼ በትዳር በመቅናት የሚመተት መተት ልክ እንደ ዛር እና ዓይነ ጥላ ፅንስ ሊያጨናግፍ እና ፅንስን በማኅፀን ውስጥ ሊያጠፋ ይችላል፡፡ በተለይ እርጉዝ ሴት ሆና የመተት አጋንንት ከተላከባት በማሕፀኗ ውስጥ ያለውን ፅንስ ስለሚመታውና ስለሚያድርበት ፅንሱ ሊጨናገፍ እና ሊጠፋ ይችላል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
1
❤ #_የርኩሳን_መናፍስት_ፈተና_በትዳር_ሕይወት ❤ #_ክፉ_መናፍስት_በትዳር_እና_በሩካቤ_ሥጋ_ጣልቃ_መግባት ወዳጆች ሆይ ክፉ መናፍስት በትዳር ሕይወታችን፣ በሩካቤ ሥጋ ደስታችን እንዴት ጣልቃ እየገቡ እንደሚበጠብጡ እና እንደሚያናውጡ በዝርዝር እናያለን። እኔ ሳልሰለች የጻፍኩትን እናንተ ሳትሰለቹ አንብቡት። ❤ 1ኛ/ ዓይነ ጥላ ዓይነ ጥላ ገርጋሪ ምቀኛ ክፉ መንፈስ ነው፡፡ ይህ ክፉ መንፈስ አድብቶ በመተናኮል ዕድላችንን በመዝጋት እጃችን ገባ ያልነውን ነገር በማሳጣት ይተናኮላል፡፡ ዓይነ ጥላ አብረውን ከሚወለዱና ተወልደን ከጊዜ በኋላ ከሚጠናወቱን ክፉ መንፈስ አንዱ ነው፡፡ ዓይነ ጥላ ያለባቸው ባል ወይም ሚስት በትዳራቸው ሰላም፣ ፍቅር፣ መግባባት በመሃላቸው በፍጹም አይኖርም፡፡ በተለይ በሩካቤ ሥጋ አይስማሙም፣ አይጣጣሙም፣ አይግባቡም፡፡ የዓይነ ጥላ መንፈስ ተጠቂ ከሆኑ እንኳን ሩካቤ ሥጋን በመፈቃቀድ ሊፈጽሙ ቀርቶ አብሮ መተኛት መተቃቀፍ አይወዱም፡፡ መንፈሱ የባልን ሰውነት ወይም የሚስትን ሰውነት እንደ ባዕድ አካል በማሳየት እንዲቀፈው/እንዲቀፋት በማድረግ ምክንያት የሌለውን ጥላቻ በመሃላቸው ይዘራል፡፡ በሩካቤ ሥጋም ደስታ የሚባል ያሳጣቸዋል፡፡ ሩካቤ ሥጋን የሚፈጽሙት ስለተጋቡ ብቻ እንጂ ወደውና ፈቅደው አይደለም፡፡ ደመ ቀዝቃዛ ያደርጋቸዋል፡፡ ከትዳር በፊት ወደ ሕይወታቸው ሰተት ብሎ የገባው መንፈስ በትዳራቸው ውስጥ ራሱን በተለያየ ጠባይና መልክ በመግለጥ፣ ለትዳራቸው መበጣበጥ እና መናወጥ ምክንያት ይሆናል፡፡ በማግባታቸው የተበሳጨው ዓይነ ጥላ በትዳር ኑሮአቸው ውስጥ የበቀል መርዙን እየረጨ፣ ትዳሩን እያቀጨጨ ለፍቺ ይዳርጋል፡፡ ዓይነ ጥላ በትዳር ሕይወት ሰላም በመንሳት እና በሩካቤ ሥጋ ጊዜ ስሜት በማጥፋት፣ የሩካቤ ሥጋ ደስታን በማበላሸት የተካነ ስለሆነ የመንፈሱን ጠባይ አውቃችሁ ልትነቁበት እና በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ልትዋጉት እንዲሁም በቅዱስ ቁርባን ጸጋ ከሕይወታችሁ ልታርቁት ይገባል፡፡ ምክንያቱም መንፈሱ ሸፍጠኛና ከጠባይ ጋር የሚመሳሰል በመሆኑ የብዙዎችን ትዳር ለፍቺ አብቅቷል፡፡ ❤ 2ኛ/ ዛሮች፦ ከሁለት አንዳቸው ዛር እና የዛር ውላጅ፣ ወንድ ወይም ሴት ዛር ካለባቸው ትዳራቸው አደገኛ ችግር ውስጥ ይገባል፡፡ ዛሩ ስለሚቀና ባልና ሚስትን ለማተራመስ ኩርፊያን፣ ንትርክን ጭቅጭቅን፣ ብስጭትን፣ አለመግባባትን፣ አለመተዛዘንን፣ ጥላቻን እንደ ግብዓት በመጠቀም ፍቅርን በማቀዝቀዝ ትዳሩን በፍቺ መንገድ እንዲጓዝ ይዳርጋል፡፡ ባስ ሲልም ደም የለመደ ዛር ከሆነ ጸብ በማንሳት ደም ያፋስሳል ከተቻለም ነፍስ ያዋድቃል፡፡ ዛሩ በአባትና በእናት ላይ ካለ በግንኙነት ወቅት ከዘር ጋር በመዋሐድ በማኅፀን ከፅንሱ ጋር አድጐ በመወለድ ደባል ሆኖ ያድጋል፡፡ ዛር እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ በመውረድ ቤተሰብን በማፈራረስ ሰላማቸውን በመደምሰስ ቤተሰብን ይዘበራርቃል፡፡ ዛር ልጆች ከተወለዱ በኋላ በልጆች እእምሮ በማደር አእምሮአቸውን በመዝጋት ትምህርት እንዳይገባቸው በማድረግ ቤተሰብንና ተማሪውን ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ በዚህም ልጁ በቤተሰብ እንዲጠላ ያደርገዋል፡፡ ፍራቻን እያስተማረ ያሳድገውና በራስ መተማመኑን በማጥፋት ለቤተሰቡ ለሀገሩ ደንታ ቢስ በማድረግ ውድ ሕይወቱን በመውረስ ለራሱ ለጥፋት ዓላማ ይጠቀምበታል፡፡ ሌብነትን፣ ወንጀልን፣ ክፉ ሱስን፣ መጠጥን፣ ዝሙትን፣ ጠበኛነትን እና ነውጠኝነትን በማስለመድ ምግባረ ቢስነትን በማላበስ የእርግማን ትውልድ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ወላጆች ሆይ ልጆች የሚታነጹት በእናንተ መልካምና እኩይ መሠረት ላይ ስለሆነ ዛሬ እንደ ቀልድ የዘራችሁትን ነገ መከመር እስኪያቅታችሁ ድረስ ስለምታጭዱ ልትጠነቁና በእውነተኛው መንገድ ልትሄዱ ይገባል፡፡ ዛሬ ‹‹የተረገመ ያልተባረከ›› እያላችሁ የምትረግሙት ልጅ ትላንት የናንተ ወይም የቤተሰባችሁ ጠንቅ ተርፎት ነውና ልታዝኑላቸው ይገባል፡፡ የዛር መንፈስ አንዱ መጥፎ መገለጫው በዓል በመጣ ቁጥር ለምሳሌ በዘመን መለወጫ፣ በገና እና በትንሣኤ በዓላት የቤተሰቡን ደስታ ለማጥፋት እና ሰላም ለመንሳት የማይረባ እና ውኃ የማያነሳ አለመግባባትንና ጠብን ተጠቅሞ ቤተሰቡን በማተራመስ፣ የበዓሉን ዐውድ ያጠፋባቸዋል፡፡ ወዳጆቼ በባል ወይም በሚስት ላይ የራሳቸው  አልያም የዛር መንፈስ ካለ ካላወቁበት እና ካልነቁበት መቼም ቢሆን በዓል በመጣ ቁጥር መጣላታቸው፣ በዓልን በኩርፊያ ማሳለፋቸው አይቀርም፡፡ እንዲሁም ከሁለት አንዳቸው ላይ በሕመም ተመስሎ በመቀመጥ ለበዓል የደስታ መዋያ ያሰቡት ገንዘብ የሐኪም ቀለብ ያደርጋል፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩላችሁ በተለይ የወንድ ዛር በሴቷ ላይ ካለ ከባሏ ጋር ሩካቤ ሥጋ መፈጸም ቀርቶ አብሮ መተኛት እና ማውራት ያስጠላታል፡፡ ሌሊት ከባሏ አጠገብ ተኝታ በእንቅልፍ ልቧ የወንድ ዛሩ ይገናኛታል፡፡ በደመ ነፍስም በተኛችበት የሚጫናት፣ የሚነካት፣ ሰውነቷን የሚዳስሳት ሰው መሰል ነገር ይሰማታል፡፡ እንዲሁም ሴት ዛር በወንዱ ላይ ካለች በተለይ በስንፈተ ሩካቤ ይጠቃል፡፡ በሕልመ ሌሊትም እጅጉን ይመታል፡፡ ጠባዩ እየተቀያየረ በውኃ ቀጠነ ይጨቃጨቃል፣ እንደ ሕፃን ይነጫነጫል፡፡ ሚስቱ ታስጠላዋለች፡፡ አብሯት ቢተኛም ሩካቤ ሥጋ ለመፈጸም እጅጉን ይቸገራል፡፡ በባል ላይም ሴት ዛር ካለች በሚያውቃት እና በማያውቃት፣ በቤተሰብ እየተመሰለች ሌሊት በተኛበት ትገናኘዋለች፡፡ ❤ 3ኛ/ ፅንስን የሚያጨናግፉ እና በማሕፀን የሚገድሉ ክፉ መናፍስት/ሾተላይ ፦ ብዙዎች በተደጋጋሚ የፅንስ መጨናገፍ እና በማኅፀን ውስጥ የፅንስ መጥፋት ያጋጥማቸዋል፡፡ በተለይ በማኅፀን ውስጥ ፅንስ ሲጠፋ በሕክምናው ሾተላይ ተብሎ ስም ይሰጠዋል፡፡ ሕክምናው የሕክምናውን ጥበብ እንጂ የክፉ መናፍስቱን ተንኮል ስለማያውቅ ከቤተሰቦቻችን በወረስናቸው፣ በራሳችንም ባመጣናቸው የዛር መንፈስ እንዲሁም በዓይነ ጥላና እና በመተት በድግምት ፅንስ እንደሚጨናገፍ እና በማኅፀን እያሉ እንደሚጠፋ አያውቅም፡፡ ስለዚህ የተጨናገፈውና በማኅፀን የሚጠፋው ፅንስ ሁሉ ሾተላይ ይባላል፡፡ አጅሬም በሾተላይ ስም ራሱን ሰውሮ ሥራውን በገሃድ ይሠራል፡፡ በነገራችን ላይ ሕክምናው በተደጋጋሚ  ፅንስ የመጨናገፍ ችግር የሚገጥማቸውንና የፅንሱን የመጨናገፍ ምክንያት በውል የማያውቃቸውን ‹‹መንስኤው የማይታወቅ›› ወይም በሕክምናው ቋንቋ ‘አይድዮ ፓቲክ’ ይለዋል፡፡ በሕክምናው ሾተላይ የሚባለው አንዲት ሴት የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጌቲቭ /Rh-/ ሆኖ ከዚህ በፊት አር ኤች ፖዘቲቭ /Rh +/ የሆነ ደም  ወደ ሰውነቷ ሲገባ አር ኤች ፓዘቲቭ የሆኑ የደም ሕዋሶችን የሚያጠፋ ንጥረ-ነገር በደሟ ውስጥ ይመረታል፡፡ ይህ ንጥረ-ነገር አንዴ ከተመረተ በደሟ ውስጥ እስከ ሕይወት ፍጻሜ ድረስ ይኖራል፡፡ በዚህም በማኅፀንዋ ውስጥ የያዘችውን ፅንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ የተመረተው ንጥረ-ነገር ፅንሱን እንደ ባዕድ አካል ስለሚቆጥረው ያጠቃዋል ፅንሱም ይጠፋል በማለት ይገልጻል፡፡ ወዳጆቼ ከላይ እንዳየነው ሾተላይን ወደ መንፈሳዊው ዓለም ስናመጣው ፅንስን የሚያጨናግፍ እና በማኅፀን እንዳለ የሚያጠፋው የቅድመ አያቶቻችን፣ የአያቶቻችን፣ የእናት አባታችን ዛር እንዲሁም ዓይነ ጥላና እና መተት ድግምት ነው፡፡ አጋንንት፣ ሰይጣን፣ ዛር፣ ዓይነ ጥላ ፅንስን ተዋሕደው በማጨናገፍ ይታወቃሉ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
«በቃና ዘገሊላ ከብካብ ኮነ፣ ወሰማይኒ ረስዮ ወይነ፤» (በገሊላ አውራጃ በቃና መንደር ሰርግ ሆነ፤ውኃውንም ወደ ወይንነት ለወጠው።) ዮሐ ፪፥፩-፲፩ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገሊላ አውራጃ በዳዊት ከተማ በቤተልሔም ምድረ ኤፍራታ ተወልዶ በሠላሣ ዘመኑ በሠላሣ ዓመተ ምሕረት በፈለገ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ ሳይውል ሳያድር ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ጾመ ጸለየ፤ በጠላት ዲያብሎስ ተፈተነ። ፈተናውን ድል አድርጎ ሱባኤውን ፈጽሞ በወጣ በሦስተኛው ቀን ከእናቱ ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም እና ከቅዱሳን ሐዋርያቱ ጋር በመሆን በገሊላ አውራጃ በቃና መንደር በሰርግ ቤት ተገኝቶ ቤተ ከብካቡን በትምህርቱ በተአምራቱ ባረከ።  ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽን ድንቅ ተአምር በቃና ዘገሊላ ያደረገው በገዳመ ቆሮንቶስ ሱባኤውን ፈጽሞ በወጣ በሦስተኛው ቀን የካቲት ፳፫ ቀን ነው። ይሁንና አባቶቻችን ሊቃውንት «የውኃ በዓል ከውኃ በዓል ጋር መቀናጀት አለበት» በማለት በጥምቀት በዓል ማግስት ጥር ፲፪ ቀን እንዲከበር አድርገውታል። እኛም ይኽንኑ ቀን ጠብቀን በዓሉን በማክበር ላይ እንገኛለን። በቃና ዘገሊላ የተደረገው ይኽ ተአምር በዮሐንስ ወንጌል በምእራፍ ፪ ከቁጥር ፩-፲፩ ድረስ ተጽፎ ይገኛል። በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘውና በዚህ ስም ሊጠራ የቻለው አምላካችን፣ ጌታችንናመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍልበምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈጸመው ተአምርምክንያት መነሻነት ነው። ከቅዱስ መጽሐፍ ላይ ተጽፎ የሚገኘው ሙሉ ቃል እንዲህ ይላል፦ «በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ። የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው። ኢየሱስም። አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት። እናቱም ለአገልጋዮቹ። የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው። አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። ኢየሱስም። ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው። አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም። አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ። ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው። ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።» በቃና ዘገሊላ የተፈጸመው ይኽ ሰርግ ሙሽራ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድናስብና እንድናስታውስ ያደርገናል። ሚዜው የሙሽራው አገልጋይ ነውና መጥምቁ ዮሐንስ ሙሽራ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ መደሰቱንና ሊያገለግለው የተዘጋጀ መሆኑን ሲያስረዳ ፦ «ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ። እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።» ዮሐ ፫፥፳፱-፴ ይለናል። በቃና ዘገሊላ በሰርጉ ቤት ተገኝቶ ተአምሩን የጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ እና ከሐዋርያት ጋር አብሮ ነበርና አማላጅ እና ተማላጅ ማን እንደሆነ በልዩ ምሥጢር ተስተውሎበታል። ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ በተከታታይ ልዩ የሆነውን ብሥራት ሲያሰማ እንዲህ በማለት ጽፎልናል፦ በስድስተኛው ወር ማለትም መልአኩ ገብርኤል ካህኑ ዘካርያስን «ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።» ካለው በኋላ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በክብር ተገልጦ «ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ።» ብሏታል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በአብሣሪው መልአክ በቅዱስ ገብርኤል እንደተነገራት በእውነት ጸጋን የተሞላች ናትና በሰርግ ቤት የጎደለውን የጓዳውን ምሥጢር ተረድታ የሠርጉ ሥነ-ሥርዓት በሠመረና በተዋጣለት ሁኔታ እየተከናወነ ድንገት የወይን ጠጅ በማለቁ ተጨንቀውና ግራ ተጋብተው አስተናባሪዎቹ በታወኩበት ሰዓት የጭንቅ አማላጅ ናትና ወደ ልጅዋ ወደ ወዳጅዋ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ «ወይን እኮ የላቸውም»በማለት አሳስባ ባዶ የሆኑት የድንጋይ ጋኖች ውኃ ተሞልተው ጣፋጭ ወይን ጠጅ ተገኝቶባቸዋል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ«እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ። ፩ጢሞ ፫፥፲፮ በማለት እንደጻፈልን ከድንቅ በላይ ድንቅ በሆነ ተዋሕዶ በሥጋ መገለጡ ከእመቤታችን ተወልዶ ነውና በልደቱ ጊዜ አብራ እንደነበረችው እንዲሁ ደግሞ በሞቱ ጊዜ ከእርሱ እንዳልተለየች እንረዳለን። ይኽንንም ወንጌላዊው ዮሐንስ «ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።» ዮሐ ፲፱፥፳፭ በማለት በጻፈልን መልእክት ለማወቅ ችለናል። በመጀመርያ በልደቱ በኋላም በሞቱ ጊዜ አብራው የነበረች ቅድስት ድንግል ማርያም ዘመኗን በሙሉ በፍጹም  እንዳልተለየችው ተአምሩን በጀመረበት በቃና ዘገሊላም አብራው ነበረችና ዛሬ ትውልዱ ሁሉ የሚኮራበትን የአማላጅነት ሥራ በቃና ዘገሊላ ፈጽማለች። «አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ» በሚለው ቃል ብዙዎች ተሰናክለውበት ቢገኙም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አምልተውና አስፍተው ምሥጢራትን የነገሯቸው የተዋሕዶ ልጆች ግን በእናትና በልጅ መካከል ያለውን የንግግር ዘይቤ ተረድተው እውነቱን ሲመሰክሩ ይኖራሉ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ከእግዚአብሔር ተልኮ የመጣውን አብሳሪ መልአክ«እንደ ቃልህ ይደረግልኝ» እንዳለችው ኢየሱስ ክርስቶስም እመቤታችንን «ከአንቺ ጋር ምን አለኝ» (እንደ ቃልሽ ይሁን) በማለት ጥያቄዋን መልሷል፤ ምልጃዋን ተቀብሏል። «ጊዚዬ አልደረሰም» በማለት ቢናገርም ስለ እናቱ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ሲል የእናቱን ልመና ተቀብሎ ተአምራቱን ፈጽሟል። እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሳይነግሯት በልባቸው ያለውን የምታውቅ እናት ናትና የሰርጉ አስተናባሪዎችን ኃዘን ተመልክታ ከልጇ ከወዳጇ አማልዳ የጎደላቸውን እንደሞላች ለእኛም ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል ብላ በተፈጸመላት ቃል ጎዶሏችንን ትሙላልን። የሰዎችን ጭንቅ አውቃ ሳይነግሯት ያማለደች እናት ስሟን ጠርተው ለሚለምኗትማ የበለጠ ታደርጋለችና ሁላችንንም በተሰጣት ጸጋ ታማልደን። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
ደብተራዎቻችን Vs Psychiatry Psychiatry ከህክምና ዘርፎች አንዱ ሲሆን ትኩረት አድርጎ የሚሰራው የአእምሮ በሽታዎች ላይ ነው። ይህ የህክምና ዘርፍ ለመፈወስ ከሚሰራባቸው በሽታዎች መካከል፦ የመርሳት ችግር ፣ ከእውነታ ማፈንገጥ ፣ አስከፊ የፀባይ መለዋወጥ እና ከአስተሳሰብ ጋር ተዛማጅ የሆኑ በሽታዎች ተጠቃሽ ናቸው።    የምእራቡ አለም ምሁራን ይህን የህክምና አገልግሎት እንደ አንድ ዘርፍ ተቀብለው በዘመናዊ መንገድ መስጠት የጀመሩት ወደ ሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ነበር። በተለይ በጣም አስቸጋሪ ለሆኑ የአእምሮ በሽታዎች መድሃኒት ማግኘት የጀመሩት 21 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ቢሆንም አሁን ድረስ ፈዋሽ መድሃኒት ያላገኙላቸው በሽታዎች አሉ። ወደኛ ስንመለስ ደብተራ (ሊቃውንት) አያቶቻችን የአእምሮ በሽታዎችን መፈወስ የጀመሩት ከአምስት ሺህ ዘመናት በፊት አንስቶ ነው። አያቶቻችን ይህን የአእምሮ በሽታዎችን የመፈወስ ጥበብ ያገኙት ከኖህ አባታቸው ነው። በመፅሐፈ ኩፋሌ ላይ እንደተፃፈው የኖህ ልጆች የአእምሮ በሽታ አጥቅቷቸው ነበር። ኖህም ልጆቹን የሚፈውስበትን ጥበብ በፀሎት ጠየቀ። እግዚአብሔርም መለሰ! መድሃኒት የሚቀምምበትን እና ለዚሁ ህክምና አገልግሎት የሚውሉትን እፅዋትና ማዕድናትን ገለፀለት። ኖህ ያገኘውን ጥበብ በመጠቀም ልጆቹን ፈወሰ። ጥበቡ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሻገር ዘንድ በመፅሐፍ ፅፎ አለፈ። ይህን መፅሐፍ መሰረት አርገው ኢትዮጵያውያን ደብተራዎች መፅሐፍቱን በሁለት መልኩ ከፍለው ፃፏቸው። 1. የመጀመርያ እፀ ደብዳቤ ይሰኛል። 2. ሁለተኛው እንቁ አእባን ይሰኛል። እፀ ደብዳቤ፦ የሰባት መቶዎቹን እፅዋት ዝርዝር ፣ አቀማመማቸው፣ ለምን በሽታ ፈውስ እንደሚሰጡና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን የያዘ ነው።   እንቁ አእባን፦ እርሱ ደግሞ የማዕድናት ዝርዝሮችን የያዘ ሲሆን ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ ማእድናትን ዝርዝር መረጃ የያዘ ነው። ደብተራ አያቶቻችን በዚህ አላቆሙም ከላይ የጠቀስኳቸውን መፅሐፍት መሰረት አርገው የራሳቸውን ጥናትም በማካተት የተለያዩ የአእምሮ በሽታ መፈወሻ ጥበብ የያዙ የህክምና መፅሐፍትን አዘጋጁ። ከነኚህ መፅሐፍት መካከል ዋንኛዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦ ፩ኛ. መፍትሔ ሥራይ ( በስሩ ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ መፅሐፍትን አካቷል)                                                                                                ፪ኛ. መፅሐፈ አፍልሆ                                                                                                                                                                  ፫ኛ. መፅሐፈ ነድራ                                                                                                                                                                    ፬ኛ. መፅሔተ ሠለሞን ፭ኛ.መርበብተ ሠለሞን ፮ኛ.መጽሓፈ ባርቶስ..ወዘተ ናቸው። እነዚህ ሁሉ ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደተዘጋጁ አሁን ድረስ ያሉ ደብተራዎች ይናገራሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት እነኚህ የህክምና መፅሐፍት የማይፈውሱት የአእምሮ በሽታዎች የሉም። ዛሬ ድረስ ሳይንስ መድሃኒት ያላገኘላቸው የአእምሮ በሽታዎች በነኚህ መፅሐፍት ይፈወሳሉ። ያሳዝናል … እውነታው ይህ ቢሆንም ግን ይህን በደብተራ አያቶቻችን ጥረት ከዚህ ዘመን የደረሰው ይህ አገራዊ ህክምና በአገራችን “ዘመናዊ” ሀኪሞች “ባህላዊ” ተብሎ የተናቀ በማህበረሰቡም ” ጥንቆላ” ተብሎ ገሸሽ የተደረገ በመንግሥት ትኩረት ያልተሰጠው ጥበብ ነው። እውነታው ግን  ከላይ የጠቀስኳቸው መፅሐፍት እንዳለ በጀርመን ፣ በእንግሊዝ እና ፈረንሳይ ውስጥ በሚገኙ የህክምና የትምህርት ተቋማት ውስጥ ጥናት ይደረግባቸዋል። ከዚህም አልፎ በፈረንሳይኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተተርጉመው በትላልቅ ጥራዞችም ታትመዋል። ለማስረጃም በእጄ ላይ የሚገኙ አሉ። የዚህ ፅሁፍ መልእክት ሁለት ነው። ፩ኛ. ለበርካታ ሺህ ዘመናት አገራዊ የሆነውን ጥበብ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሻገር ታላቅ መስዋእትነት ለከፈሉት ደብተራ አያቶቻችን እውቅና መስጠት ሲሆን … ፪ኛ. በአገራዊ እውቀት ዙሪያ መነቃቃትን መፍጠር ነው። አገራዊ የሆኑ እውቀቶችን ከዘመኑ ጋር አስታርቀን ብንገለገልባቸው ምክሬ ነው። መርጌታ አምደብርሃን !
Hammasini ko'rsatish...
👍 7
ሊያደርስብን ይችላል፡፡ መተት እና የዓይነ ጥላ መንፈስ በልዩነታቸው መተት የሚከብድበት አንዱ መተት አጋንንት እራሱን መቀየር መቻሉ ነው፡፡ መተት በሆድ ውስጥ አውሬ ሆኖ ይቀመጣል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በሻይ፣በጠላ፣በሚሪንዳ መተት ተመትቶ ቢሰጠው ያንንም ቢጠጣ ወደ ሆዱ ከገባበት ቀን ጀምሮ ጤና ማጣት፣ህመም መሰማት ይጀምረዋል፡፡ ይህ በሚጠጣ ነገር ወደ ሆዱ የገባው መተት ሰውዬው ሳያውቀው ከቆየ፣ሥጋዊ በሽታም ከመሰለው በጊዜ ሂደት ሆዱ ውስጥ የገባው መተት እራሱን በመቀየር እባብ፣እንቁራሪት፣አይጥ ወዘተ ሆኖ ውስጡ ተቀምጦ ሥጋውን በመብላት ደሙን በመጠጣት ለከፍተኛ ጤና መታወክና ጉዳት ይዳርገዋል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ሊገድለውም ይችላል፡፡ ዛሬ ሆዳችንን እያመመን፣የሆድ ህመማችን ትልቅ ጭንቀት ፈጥሮብን በየ ሆስፒታሉ ሄደን መፍትሔ የምናጣው መተት ቢሆንስ? ምክንያቱም በመተት ወደ ሆድ ገብቶ ደዌና አውሬ ሆኖ የተቀመጠው ነገር በሕክምና ምርመራና መሣሪያዎች አይታይም ይሠወራቸዋል፡፡ ሴቶችም በመተት ማኅፀናቸው ላይ ደዌና አውሬ ሆኖ ይቀመጣል፡፡ እንደ ጽንስ ይገላበጣል፣እንደ አውሬ ይጮኻል፡፡ በሕመም ያሰቃያቸዋል ግን በሕክምና የሕመማቸው ምክንያት አይታወቅም መፍትሔም አይገኝም፡፡ እህቶቼ መተት ቢሆን ማን ያውቃል? ስለዚህ የመተት አጋንንት ውስጣችን ከገባ እራሱን እየቀያየረ የተለያየ በሽታ ይሆናል፡፡ በሚበላና በሚጠጣ ወደ ሆዳችን የገባው፣በቁሳቁስ ወደ እኛ የሰረጸው መተት ሆዳችንን ሊያሳምመን፣ለአእምሮ ሕመም/እብደት/ ሊዳርገን፣እጅ እግራችንን ሽባ ሊያደርገን፣ለወገብ ለልብ ወዘተ ሕመም ሊዳርገን ይችላል፡፡ መተትም አደገኛ የሚያደርገው ይህ ነው፡፡ ዓይነ ጥላ ሕይወታችንን የማጎሳቆል ሥራ የሚሠራው በስውር ነው፡፡ መተት ግን በግልጥ ነው፡፡ ዓይነ ጥላ በውስጣችን አሸምቆ ተደብቆ ከእኛው ጠባይ ጋር ተስማምቶ አድብቶ ነው የሚኖረው፡፡ መተት ግን ጥቃቱ የሚታይና ግልጥ ነው፡፡ የዓይነ ጥላ አጋንንት የሚጎዳን በጊዜ ሂደት ነው፡፡ መተት ግን በድንገት ነው፡፡ መተት ብዙ ጊዜ የተንኮለኞች የቅናት እና የክፋት እጅ ስለሆነ ተጠንቅቀን የምናመልጠው ሳይሆን በጸሎት የምንከላከለው ነው፡፡ አንድ አባት አንድ ወጣኒን ‹‹ልጄ ጀርባህ ላይ ግንድ ከሚጫንህና ሰው ከሚጫንህ የቱ ይሻልሃል›› አሉት፡፡ ወጣኒውም ብልህ ኖሮ ‹‹አባቴ ጀርባዬ ላይ ግንድ ቢጫነኝ ሰው ያወርድልኛል፤ሰው ከተጫነኝ ማን ያወርድልኛል›› አላቸው፡፡ ዛሬም በመተት ሰዎች ሕይወታቸውን ተጭነዋቸው የሚያወርድላቸው አጥተው ከቤሰተብ፣ከትዳር፣ከሥራ ተለይተው በየ ጸበሉና በየ ገዳሙ የሚንከራተቱትን ፈጣሪ ይቁጠራቸው፡፡ ወዳጆቼ ሰውና አጋንንት በማበር በመተት በዚህ ደረጃ የሚፈትኑን፣ሕይወታችንን የሚያበላሹት አንድም ለፈተና፣ለጸጋ፤ለክብር፤አንድም በእኛ የእውነተኛ አምልኮት ድክመት ነው፡፡ ሰማያዊ አምልኮት፣ጾም፣ጸሎት ስግደት በሌለበት ሕይወታችን በመተት አጋንንት ብዙ ነገር በማጣት ብንኖር ፈጣሪን ከመውቀስ እራስን መለስ ብሎ መፈተሹ አይከፋም፡፡ አስደናቂው ነገር የመተት እና የዓይነ ጥላ መንፈስ ሁለቱም ውስጣችን ካሉ ይተባበራሉ፡፡ አጋንንት ለክፉ ተግባራት እርስ በእርሳቸው ሲተባበሩ እኛ ግን ለመልካም ነገር እርስ በእርሳችን አንተባበርም፡፡ በተቃራኒው በምቀኝነት ጎራ ተሰልፈን አንዳችን ለአንዳችን ሕይወት መበላሸት ምክንያት እንሆናለን፡፡  የመተትም የዓይነ ጥላውም ሥራቸው፣ዓላማቸው ሕይወታችንን ማበላሸት ስለሆነ እራሳቸውን ላለማጋላጥ ተደብቀው ይኖራሉ፡፡ ደግነቱ ዓይነ ጥላው ከተጋለጠ፣መተቱም ይጋለጣል፡፡ አንዱ ሲያዝ አንዱም ይያዛል፡፡ ተወዳጆች ሆይ ትዕግስተኛው ኢዮብ ‹‹በምድር ላይ የሰው ሕይወቱ ብርቱ ሰልፍ አይደለምን›› ብሎናል፡፡ ስለዚህ በምድር እሰከ ኖርን ድረስ በሕይወታችን በአጋንንት ብርቱ ሰልፍ ሊገጥመን ስለሚችል አምልኮታችን በማጠንከር፣በጾም በጸሎት በስግደት በመበርታት  ልንዋጋ ይገባል፡፡ /ኢዮ 7÷1/ ‹‹ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል›› ት.ሆሴ 4÷6 ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› ት.ኢሳ 53÷8 ‹‹ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ድል ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው›› ምሳ 21÷31 እውቀታችንን ሰዎች በመተት/በአጋንንት/ ግፊት እና በቅናት እንዴት ይወስዱታል? የእኛን እውቀት ሰዎች በመተት ለራሳቸው ሊጠቀሙበት ይችላሉን? በአጋንንት ጥበብ እውቀታችን ወደ ሌላ ሰው ሊተላለፍ ይችላል? እውቀታችን መወሰዱን በምን እናውቃለን? ይቀጥላል …
Hammasini ko'rsatish...
መተት የመተት አጋንንት ከዓይነ ጥላ የሚለይበት እና አንድ የሚሆንበት! ተወዳጆች ሆይ ከዚህ በፊት በዓይነ ጥላ መንፈስ መግቢያ ላይ አጋንንት ዓላማቸው አንድ ቢሆንም በሥራ ድርሻቸው እና በተንኮል ተልዕኮአቸው የተለያዩ መሆናቸውን በሰፊው አይተናል፡፡ በዚህ ክፍል የመተት እና የዓይነ ጥላ አጋንንት አስገራሚ አንድነታቸው እና ልዩነታቸውን እናያለን፡፡ ይህን እንድታውቁ የምፈልገው ለግንዛቤ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ በአጋንንት ተንኮል ውስጥ ምን ያህል አጋንንታዊ ሱታፌ እንዳለው እንድትረዱና ሰው መልአክም ሰይጣንም የመሆን ሁለት ተቃራኒ ጠባይ በውስጡ እንዳለው እንድትገነዘቡና የፈተና ስልታቸውን እንድትሉ ነው፡፡ ወዳጆቼ ሰው የቅድስና ጠባይን ከተላበሰ ሥጋ ለበስ መልአክ መሆን ይችላል፡፡ ሰው የርኩሰትን ጠባይ ከተላበሰ ሥጋ ለበስ ሰይጣን መሆን ይችላል፡፡ በተለይ የለበሥነው ሥጋ የዕድቅ አደጋ ስለሆነ ከመልአካዊ ጠባይ ይልቅ ሰይጣናዊ ጠባይ በእኛ ሊታይ ይችላል፡፡ ለዚህም ነው ‹‹ሰው ሲከፋ ባለ ሁለት እግር አውሬ ይሆናል›› የሚባለው፡፡ መተት ከዓይነ ጥላ አጋንንት ጋር አንድ የሚያደርገው ሁለቱም የሰውን ልጅ ውድ ሕይወት ማበላሸት፣ውጥኑን፣እቅዱን ማኮላሸት ላይ ስለያተኩሩ ነው፡፡ መተትም ዓይነ ጥላም በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ጣልቃ በመግባት ሕይወትን ከማበላሸት እስከ ማጥፋት ይደርሳሉ፡፡ ሁለቱም አለን፣እጄ ገባ፣እርግጠኛ ነኝ በምንላቸው ነገሮቻችን ላይ የሚያደርሱብን ስውር ጥቃት አንድ ነው፡፡ መተት እና ዓይነ ጥላ በዕድላችን፣በእውቀታችን፣በትምህርታችን፣በእጮኝነት እና በትዳር ሕይወታችን እንዳንጠቀም ከጥንስሱ ጀምሮ እስከ ድግሱ ድረስ የመደንቀር፣የማበላሸት ሥራን ይሠራሉ፡፡ ሁለቱም አሉኝ በምንላቸው ነገሮች እንዳንጠቀም የመጠርቀም ሥራን ይሠራሉ፡፡ ሁለቱም ተስፋ በጣልንባቸው ከመቶ ፐርሰንት በላይ እርግጠኛ በሆንባቸው ነገሮቻችን ላይ፣አጋንንታዊ የበላይ በመሆን በግልጽና በስውር፣የማይታይ ምስማር በመሆን ጠስቀይ ይይዙብናል፡፡ ሲላቸው በራሳቸው ሲላቸው በሰው እያደሩ፣የእኛን ነገር ገና ከጅምሩ እየገረገሩ ያበላሹብናል፡፡ መተት እና ዓይነ ጥላ የሰው ልጅ ዳግም የማያገኝውን፣ተመልሶ የማይኖረውን ውድ ሕይወቱን በማባከን፣የያዘውን በማስጣል ብሎም በመንጠቅ አንድ ናቸው፡፡ መተት እና የዓይነ ጥላ አጋንንት የሚለያቸው ወይም አንድ የማያደርጋቸው ደግሞ አለ፡፡ ይህም መተት በደጋሚዎች ወይም በጠንቋዮች በመጎተት ሰውን የሚቆራኝ አጋንንት ነው፡፡ መተት በሰው እድል የሚቀና፣በሰው መልካም ሕይወት በብግነት የሚኖር ሰው በሚበላ በሚጠጣ፣በቁስ ወዘተ በማስደገም የሚያቆራኘው አጋንንት ነው፡፡ ዓይነ ጥላ በደጋሚዎች የሚጎተት አጋንንት አይደለም፡፡ እራሱን ችሎ፣ክፋቱን ተንኮሉን ጠቅልሎ ወደ ሰው ሕይወት የሚገባ አጋንንት ነው እንጂ በደጋሚዎች የሚቆራኝ አይደለም፡፡ ዓይነ ጥላ የሰውን ልጅ ከማኅፀን ጀምሮ በጽንስ ጊዜ በመቆራኘት አብሮ የሚያድግ፣የሰውን ሕይወት የሚያጠወልግ አጋንንት ነው፡፡ መተት ግን ድንገት ወደ እኛ ሕይወት በሰው ክፋት የሚመጣ አጋንንት ነው፡፡ ዓይነ ጥላ የማንም አጋንንታዊ ድግምት የማያዘው በራሱ የክፋት መንገድ የሚራመድ ክፉ መንፈስ ነው፡፡ በእርግጥ መተት ገና በማኅፀን ባለ ጽንስ ላይ ቢደገምም መተትን ወደ ሰው ሕይወት ለማስገባት ገፊ አካላት ያስፈልጋል፡፡ ዓይነ ጥላ ግን ዕድላችን ላይ በመቅናት ሰተት ብሎ የሚገባ ነው፡፡ መተት በሰው ቅናት የሚገባ አጋንንት ሲሆን ዓይነ ጥላ እራሱ መንፈሱ በእኛ በመቅናት የሚገባ ነው፡፡ ዓይነ ጥላ በውስጣችን ከገባ በኃላ እራሱን እየቀያየረ በሕመም እየተመሰለ ይቀመጣል፡፡ መተትም ውስጣችን ከገባ ደዌ ሆኖ ይቀመጣል፡፡ ልዩነታቸው ዓይነ ጥላ አንዴ ውስጣችን ከገባ እንደ ግል ይዞታው ተደላድሎ ይቀመጣል፡፡ መተት ግን ውስጣችን ከገባ በኃላ እድሳት የሚባል አጋንንታዊ ሥርዓት አለው፡፡ እድሳት ማለት አንድ ሰው ላይ በመልካም ነገሩ መተት ሲመተትበት፣የሚያስመትተው ሰው በደጋሚው ወይም በመታቹ በኩል ለአጋንንቱ ግብር ያቀርብለታል፡፡ ለምሳሌ ገንዘብ፣በግ፣ደም ወዘተ ያቀርባል፡፡ ይህንን ያስደገመ ቀን ያቀረበውን ግብር በየ ዓመቱ ሊያቀርብ አጋንንታዊ ውል ይገባል፡፡ ይህንን የሚያደርገው የሰውን እድል ስለወሰደ በዛም ስለሚጠቀምበት ከሰው የወሰደው ዕድል፣እውቀት፣የትዳር፣የሥራ እድል ወዘተ በአጋንንት ተጠብቆ እንዲቆይለት እንዲጠቀምበት የሚያደርገው ነው፡፡ ብዙ ጊዜ መተት የተመተተባው ሰዎች ከአጋንንቱ በቀላሉ መላቀቅ የሚያቅታቸው በአጋንንቱ እና በሚደገምበት ሰው መሃል ያለው አስደጋሚው ሰው በየዓመቱ ወይም በየወራቶቹ በተደገመበት ሰው ስም ለአጋንንቱ ስለሚገበር የተመተተበት ሰው ሲታደስበት አጋንንቱ እንደ አዲስ ወደ ውስጡ ይገባል፣ጤና ያጣል፣የጀመራቸው ነገሮች በአስገራሚና ለማመን በማያስችል ሁኔታ ይበላሻል ወዘተ፡፡ አንድ ሰው በተለይ መተት የተመተተበት ሰው መተቱ ሲታደስበት የሚያሳየው ጠባይ አለ፡፡ ይህም በድንገት ጭው የሚል ስሜት መሰማት፣ያለ ምክንያት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ መግባት፣መረበሽ፣መጨናነቅ፣ፍርሃት መሰማት፣የሆነ የማናውቀው ነገር ውስጣችን ሲገባ መሰማት፣እራስን ስቶ መውደቅ/ይህ መንፈሱ ውስጣችን ሲገባ ነው/ በጠራራ ፀሐይ ብርድ ብርድ ማለት፣ውልብ ብሎ ሰውነታችንን የሚከብድ ስሜት መሰማት፣በድንገት የልብ ምት መጨመርና ዝብርቅረቅ የሚል ስሜት መሰማት፣ከፍተኛ ድንገተኛ የሰውነት ድካምና የመክበድ ስሜት መሰማት፣ሰላም ማጣት፣ድንገተኛ የባሕርይ ለውጥ ማሳየት፣ያለ ምክንያት ብስጭት ብስጭት ማለት፣ማዞር መቅለሽለሽ፣ጭንቅላት እና ልብ ላይ ጭንቅ የሚል ስሜት መሰማት፣ጩኽ ጩኽ የሚል ስሜት ከውስጥ መግፋት፤እጮኛሞች እና ባለ ትዳሮች ከሆኑ ድንገት የማስጠላት እና የመጥላት ስሜት ውስጥ መግባት፣መሳደብ፣እንለያይ ማለት፣የትዳር አጋርንና ልጆችን መጥላት፣ያለ ጥፋት መምታት ወዘተ ሊከሰቱብን ይችላል፡፡ ስለዚህ የተመተተበት ሰው መተቱ ሲታደስበት እንኳን ለሰው ለራሱም የማያውቃቸው የሚይጨበጡ የባሕርይ ለውጦችን ያሳያል፡፡ ለምሳሌ በመጠጥ የተመተተበት ሰው በስንት ጸሎት እና ጸበል መጠጡን ከተወ የታደሰበት ቀን ንጉልያው እስኪዞር ድረስ ጠጥቶ ይሰክራል፡፡ በእጮኛውና በትዳሩ ላይ በመቅናት የተመተተበት ሰው ከሆነ የታደሰበት ቀን ከእጮኛውና ከትዳር አጋሩ እና ከልጆቹ ጋር ያለ ምክንያት ከፍተኛ ጠብ ውስጥ ይገባል፡፡ በእውቀቱ የተመተተበት ሰው ከሆነ የታደሰበት ቀን በዛን ሰሞን ደንዝዞ ፈዞ ይከርማል፡፡ በገንዘቡ የተመተተበት ሰው ገንዘቡ ከኪሱ ለመውጣት የሚያጨበጭቡ ይመስል ያለ ምክንያት ይወጣል፡፡ ግን በምን እንዳወጣው፣ገንዘቡን የት እንዳሰረሰው፣ምን ቁም ነገር ላይ እንዳዋለው አይውቅም፡፡ ሌላም ሌላ …. በአጠቃላይ እድሳት ማለት ከአጋንንቱ ጋር በሰው ሕይወት እና እድል ላይ ውል ማራዘም ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት በሰው ሕይወት ላይ በአጋንንት ስውር ምስጢር መቆመር ማለት ነው፡፡ ተወዳጆች ሆይ መተት ከዓይነ ጥላ አንዱ የሚለይበት መተት በምንበላው ምግብ፣ በምንጠጣው መጠጥ፣በምንለብሰው የውስጥ እና ውጭ ልብስ/በላብ በወዝ/  በምንይዘው ቁስ ወዘተ ስለሚደገም በቀላሉ ሕይወታችን ሊደረመስ፣ጤናችን ሊቃወስ ይችላል፡፡ ሌላው መተት ከዓይነ ጥላ የሚለይበት ምክንያት መተት አደገኛና ገዳይ መሆኑ ነው፡፡ ምንክያቱም መተት በመርዝ መልክ ሊሠራ ስለሚችል የተመተተበትን ምግብ የበላ ወይም መጠጥ የጠጣ ሰው በድንገት ሊሞት ይችላል፡፡ በተለይ ወደ ሆድ በሚገቡ ነገሮች አጋንንቱ በሰውነታችን ሕዋሶች በመሰራጨት፣ከፍተኛ ጉዳት
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
ተወዳጆች ሆይ መተት ከዓይነ ጥላ አንዱ የሚለይበት መተት በምንበላው ምግብ፣ በምንጠጣው መጠጥ፣በምንለብሰው የውስጥ እና ውጭ ልብስ/በላብ በወዝ/  በምንይዘው ቁስ ወዘተ ስለሚደገም በቀላሉ ሕይወታችን ሊደረመስ፣ጤናችን ሊቃወስ ይችላል፡፡ ሌላው መተት ከዓይነ ጥላ የሚለይበት ምክንያት መተት አደገኛና ገዳይ መሆኑ ነው፡፡ ምንክያቱም መተት በመርዝ መልክ ሊሠራ ስለሚችል የተመተተበትን ምግብ የበላ ወይም መጠጥ የጠጣ ሰው በድንገት ሊሞት ይችላል፡፡ በተለይ ወደ ሆድ በሚገቡ ነገሮች አጋንንቱ በሰውነታችን ሕዋሶች በመሰራጨት፣ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስብን ይችላል፡፡ መተት እና የዓይነ ጥላ መንፈስ በልዩነታቸው መተት የሚከብድበት አንዱ መተት አጋንንት እራሱን መቀየር መቻሉ ነው፡፡ መተት በሆድ ውስጥ አውሬ ሆኖ ይቀመጣል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በሻይ፣በጠላ፣በሚሪንዳ መተት ተመትቶ ቢሰጠው ያንንም ቢጠጣ ወደ ሆዱ ከገባበት ቀን ጀምሮ ጤና ማጣት፣ህመም መሰማት ይጀምረዋል፡፡ ይህ በሚጠጣ ነገር ወደ ሆዱ የገባው መተት ሰውዬው ሳያውቀው ከቆየ፣ሥጋዊ በሽታም ከመሰለው በጊዜ ሂደት ሆዱ ውስጥ የገባው መተት እራሱን በመቀየር እባብ፣እንቁራሪት፣አይጥ ወዘተ ሆኖ ውስጡ ተቀምጦ ሥጋውን በመብላት ደሙን በመጠጣት ለከፍተኛ ጤና መታወክና ጉዳት ይዳርገዋል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ሊገድለውም ይችላል፡፡ ዛሬ ሆዳችንን እያመመን፣የሆድ ህመማችን ትልቅ ጭንቀት ፈጥሮብን በየ ሆስፒታሉ ሄደን መፍትሔ የምናጣው መተት ቢሆንስ? ምክንያቱም በመተት ወደ ሆድ ገብቶ ደዌና አውሬ ሆኖ የተቀመጠው ነገር በሕክምና ምርመራና መሣሪያዎች አይታይም ይሠወራቸዋል፡፡ ሴቶችም በመተት ማኅፀናቸው ላይ ደዌና አውሬ ሆኖ ይቀመጣል፡፡ እንደ ጽንስ ይገላበጣል፣እንደ አውሬ ይጮኻል፡፡ በሕመም ያሰቃያቸዋል ግን በሕክምና የሕመማቸው ምክንያት አይታወቅም መፍትሔም አይገኝም፡፡ እህቶቼ መተት ቢሆን ማን ያውቃል? ስለዚህ የመተት አጋንንት ውስጣችን ከገባ እራሱን እየቀያየረ የተለያየ በሽታ ይሆናል፡፡ በሚበላና በሚጠጣ ወደ ሆዳችን የገባው፣በቁሳቁስ ወደ እኛ የሰረጸው መተት ሆዳችንን ሊያሳምመን፣ለአእምሮ ሕመም/እብደት/ ሊዳርገን፣እጅ እግራችንን ሽባ ሊያደርገን፣ለወገብ ለልብ ወዘተ ሕመም ሊዳርገን ይችላል፡፡ መተትም አደገኛ የሚያደርገው ይህ ነው፡፡ ዓይነ ጥላ ሕይወታችንን የማጎሳቆል ሥራ የሚሠራው በስውር ነው፡፡ መተት ግን በግልጥ ነው፡፡ ዓይነ ጥላ በውስጣችን አሸምቆ ተደብቆ ከእኛው ጠባይ ጋር ተስማምቶ አድብቶ ነው የሚኖረው፡፡ መተት ግን ጥቃቱ የሚታይና ግልጥ ነው፡፡ የዓይነ ጥላ አጋንንት የሚጎዳን በጊዜ ሂደት ነው፡፡ መተት ግን በድንገት ነው፡፡ መተት ብዙ ጊዜ የተንኮለኞች የቅናት እና የክፋት እጅ ስለሆነ ተጠንቅቀን የምናመልጠው ሳይሆን በጸሎት የምንከላከለው ነው፡፡ አንድ አባት አንድ ወጣኒን ‹‹ልጄ ጀርባህ ላይ ግንድ ከሚጫንህና ሰው ከሚጫንህ የቱ ይሻልሃል›› አሉት፡፡ ወጣኒውም ብልህ ኖሮ ‹‹አባቴ ጀርባዬ ላይ ግንድ ቢጫነኝ ሰው ያወርድልኛል፤ሰው ከተጫነኝ ማን ያወርድልኛል›› አላቸው፡፡ ዛሬም በመተት ሰዎች ሕይወታቸውን ተጭነዋቸው የሚያወርድላቸው አጥተው ከቤሰተብ፣ከትዳር፣ከሥራ ተለይተው በየ ጸበሉና በየ ገዳሙ የሚንከራተቱትን ፈጣሪ ይቁጠራቸው፡፡ ወዳጆቼ ሰውና አጋንንት በማበር በመተት በዚህ ደረጃ የሚፈትኑን፣ሕይወታችንን የሚያበላሹት አንድም ለፈተና፣ለጸጋ፤ለክብር፤አንድም በእኛ የእውነተኛ አምልኮት ድክመት ነው፡፡ ሰማያዊ አምልኮት፣ጾም፣ጸሎት ስግደት በሌለበት ሕይወታችን በመተት አጋንንት ብዙ ነገር በማጣት ብንኖር ፈጣሪን ከመውቀስ እራስን መለስ ብሎ መፈተሹ አይከፋም፡፡ አስደናቂው ነገር የመተት እና የዓይነ ጥላ መንፈስ ሁለቱም ውስጣችን ካሉ ይተባበራሉ፡፡ አጋንንት ለክፉ ተግባራት እርስ በእርሳቸው ሲተባበሩ እኛ ግን ለመልካም ነገር እርስ በእርሳችን አንተባበርም፡፡ በተቃራኒው በምቀኝነት ጎራ ተሰልፈን አንዳችን ለአንዳችን ሕይወት መበላሸት ምክንያት እንሆናለን፡፡  የመተትም የዓይነ ጥላውም ሥራቸው፣ዓላማቸው ሕይወታችንን ማበላሸት ስለሆነ እራሳቸውን ላለማጋላጥ ተደብቀው ይኖራሉ፡፡ ደግነቱ ዓይነ ጥላው ከተጋለጠ፣መተቱም ይጋለጣል፡፡ አንዱ ሲያዝ አንዱም ይያዛል፡፡ ተወዳጆች ሆይ ትዕግስተኛው ኢዮብ ‹‹በምድር ላይ የሰው ሕይወቱ ብርቱ ሰልፍ አይደለምን›› ብሎናል፡፡ ስለዚህ በምድር እሰከ ኖርን ድረስ በሕይወታችን በአጋንንት ብርቱ ሰልፍ ሊገጥመን ስለሚችል አምልኮታችን በማጠንከር፣በጾም በጸሎት በስግደት በመበርታት  ልንዋጋ ይገባል፡፡ /ኢዮ 7÷1/ ‹‹ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል›› ት.ሆሴ 4÷6 ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› ት.ኢሳ 53÷8 ‹‹ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ድል ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው›› ምሳ 21÷31 እውቀታችንን ሰዎች በመተት/በአጋንንት/ ግፊት እና በቅናት እንዴት ይወስዱታል? የእኛን እውቀት ሰዎች በመተት ለራሳቸው ሊጠቀሙበት ይችላሉን? በአጋንንት ጥበብ እውቀታችን ወደ ሌላ ሰው ሊተላለፍ ይችላል? እውቀታችን መወሰዱን በምን እናውቃለን? ይቀጥላል …
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
#የቤተሰብ ዛር ከቤተሰብ ወርዶ ለልጅ ልጅ የሚተርፍ የባዕድ አምልኮ የዛር መንፈስ ቁርኝት! #የዛር መንፈስ ማለት በአብዛኛው ጊዜ ፈቅደን ወደን ከ ፈጠረን አምላካችን ይልቅ ክፉ የዛር መንፈስ ያዘዝከኝን አደርግልሃለሁ ያዘዝኩህን አድርግልኝ ብለን ቃል በመገባባት ከራሳችን ጋር እንደንጉስ አክብረን የምናዋሃደው መንፈስ ሲሆን። #የዛር መናፍስት ከሰው ልጅ ማህበራዊ ኑሮ በመቆራኘት የሰው ልጅ ስጋውን ለብሰው ከደሙ ጋር ተዋህደው ህይወታቸውን የሚመሩ ረቂቃን መናፍስት ናቸው። #የዛር መናፍስ ከአያት እንዲሁም ከአባት እናቶቻችን ዘንድ  በደም ሐረጋችን በመውረድ ልጅን እንዲሁም የልጅ ልጅን ትልቅ ፈተና ውስጥ የሚጥሉ የከፉ መናፍስት ናቸው። #የዛር መናፍስት ከሰው ልጅ ጋር ከመላመዳቸው የተነሳ የየእለቱ የሰው ልጅ እንቅስቃሴ አብረው ስያከናውኑ ወዳልሆነ መንገድ ሲመሩ ሃገርንም ስያተራምሱ የሚኖሩ መናፍስት ናቸው። #የዛር መናፍስቶ የተለያየ ነገድ ሲኖራቸው በየአከባቢው እና በየሀገሩ የተለያዩ ስሞችን እራሳቸውን በሚገልጽ መንገድ በመጠራት ሲመለኩ ይኖራሉ። #የዛር መናፍስት የዓይነጥላ እና የመተት ምልክትን በመላበስ ራሳቸውን ደብቀው የሰው ልጅን በጥርጣሬ ከወዳጅ ዘመዶቹ እንዲጋጭ የማድረግ ብቃትም አላቸው። #የዛር መናፍስት በተለያዩ የጥበብ ሰዎች በተለያዩ አባዎራዎች በተለያዩ ባልቴቶች እንዲሁም በተለያዩ ህጻናቶች በመቆራኘት ስራቸውን ስያከናውኑ ይኖራሉ። #የዛር መናፍስት በ ተለያዩ መንገዶች ካልተገሰጹ እንዲሁም ካልተወገዱ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የመውረድ አቅም እንዳላቸው ሊቃውንት ያትታሉ። #የዛር መናፍስት ወደው ፈቅደው ላመለክዋቸው ሰዎች እና ልጆቻቸውን ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸውን በማመዘን ለተለያዩ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ችግር የሚዳርጉ መናፍስት ናቸው። #የዛር መናፍስት በሰዎች ዘንድ በመላክም ሌሎች ሰዎችን የማጥቃት ክህሎትም አላቸው። ይህ ማለት ጉዳዩ አድርግልኝ ላድርግልህ ነውና!በገቡት ቃል መሰረት የተለያዩ እንስሳት በመስዋዕትነት በማቅረብ ጠላታቸውን እንድያጠቃላቸው በታዘዙበት ቅጽበት የተላከበት ሰው በጸሎት እና በሕገ እግዚአብሔር ያልጸና እንደሆነ በዛር መናፍስት የመጠቃት እድሉ እጅግ ሰፊ ነው። #የዛር መናፍስት የሚፈጥሩት ችግር፦ ፦ትዳር እንዳትይዙ ትልቅ እንቅፋት ይፈጥራሉ። ፦በሰዎች ዘንድ መጠላትን ይፈጥራሉ። ፦የሰውነት ጠረን ፣የአፍ ጠረን፣- ሆድ ውስጥ መንፋት የመንቀሳቀሰ ምልክት ጨጒራን በመመሰል ትልቅ ሁከት ይፈጥራሉ። ፦ሴቶች ላይ የማህጸን ህመም፣የወገብ ህመም፣ ህልመ ሌሊት፣ፍራቻን በመጫር የህይወት ስጋት ይሆናሉ። ፦ወንዶች ላይ ህለመ ሌሊት፣ድክመተ ወሲብ እና ትዳር ማጣትን ያስከትላሉ። ፦ትልቅ የስራ ዕድል መዝጋት፣ብር አለመበርከት፣ማዛጋት ፣ማንጠራራት፣እጅ እና እግር ፓራላይዝድ አልያም ሸምቅቆ በመያዝ ችግር ይፈጥራሉ። ፦በስኳር፣በደም ግፊት ፣በሪህ በመመሰል የክኒን ሱሰኛ አድርገው ሲጫወቱብን ይኖራሉ። ፦ራስ ህመም፣በአስም፣በመካንነት ችግር ይፈጥራሉ። ፦በጣም የባሰ እንደሆነ ደግሞ ማስጎራት ፣አመድ ማስቃም ፣ጫት ፣ቡና ማሰኘት ፣የአልጋ ቁራኛ አድርገው ማሰቀመጥ የመሳሰሉት ችግሮች የመፍጠር ኃይል አላቸው። #የዛር መናፍስት እንዴት ከእኛ ዘንስ ማራቅ እንችላለን? #በመጀመርያ ወደ ቤተ አምልኳችን  በመሔድ የተለያዩ መፍትሔዎች በታላላቅ አባቶቻችን የ እግዚአብሔር መፍትሔ መሻት። #በመቀጠል በራስ ጊዜ ሳንሰለች በጸሎት በጾም በስግደት ስጋችንን በማድከም ያ ክፉ ያለውድ ከቤተሰብ የወረደቅ መንፈስ ማስወገድ እንችላለን። #ይህ ሁሉ አድርገው አማራጭ እና መፍትሔ ያጡ እንደሆነ በየአከባብያችሁ ወደሚኖሩ ከ እግዚአብሔር ዘንድ ጥበብ እና ፀጋ ወደተሰጣቸው አባቶች ጎራ በማለት የ እግዚአብሔር ቃልን በመጥራት የእጽዋቶችንም ኃይል በመጠቀም አስቸጋሪ እና አሰልቺ የሆነ የዛር መንፈስን እንገስጸው እናስወግደውም። 1ኛ መፍትሔ ጧት ጧት #ከበተሰብ የወረደ ዛርን እንዴት እናስወግደው? #የምድር እንቧይ ሥር ቀጠል #የደድሆ ሥር ቅጠል #የጭቁኝ ሥር ቅጠል #የፌጦ ፍሬ #የደማካሴ ሥር ቅጠል እነዚህ እጽዋቶች ሮብ እና ዓርብ በመቁረጥ አንድ ላይ በመጨቅጨቅ ጧት ጧት በአዲስ እቃ በመዘፍዘፍ ለ ፯ ቀን ያክል ሙሉ ሰውነትን  መታጠብ የዛር መንፈስ ያስወግዳል።እንዲሁም ሙሉ ግቢውን ጧት ጧት ለ ፯ ቀን መርጨት።ከራስ አልፎ ጎረቤት ላይ ቢኖርም ይወገዳል። 2ኛ መፍትሔ ማታ ማታ #ጤና አዳም ሥር ቅጠል #ቀጠጥና (የአህያ ጀሮ) ሥር ቅጠል #የጊዜዋ ሥር ቅጠል #የእንቧጮ ተቀጽላ ሥር ቅጠል እነዚህን በማድረቅ ከደረቁ በኃላ አንድ ላይ በማቀላቀል ማታ ማታ ሊተኙ ሲሉ ከተቀላቀለው በሾርባ ማንኪያ አንድ በመለካት በፍም እሳት ለ ፯ ቀን ሙሉ ሰውነትዎን እየታጠኑ መተኛት። ቤተሰብ ሙሉውን ይህ ድርጊት በየእምነቱ እጽዋቱ ላይ በመጸለይ ቢጠቀም ከፈጣሪው ዘንድ ሙሉ መፍትሔ ያገኛል። የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት ጠልሰም እና ጥቅማቸው በዚህ ጥበባዊ ድህረ ገጽ ይዳሰሳል። #አምደብርሃን ይትባረክ !!! #አድራሻችን_ቁ/1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከ አደባባይ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መሄጃ... #አድራሻችን_ቁ/2 አ/አ ከ አየር ጤና ወደ አለም ባንክ መሄጃ በ ቤተል መገንጠያ በኩል ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት  እንገኛለን 👉 የስራ ሰአት ከሰኞ -ቅዳሜ ከ2:30 እስከ 11:00 ሰአት  ለበለጠ መረጃ (ለሐሳብ አስተያየተዎ ) 📞#0918487073  📞#0920253444 📞#0918834904  ይደውሉልን ✅ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት @merigetaamedeberhan ✅ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት @mergetaamedeberhane ✅ፌስቡክ ገፃችን https://www.facebook.com/profile.php?id=100076378898155 ✅የቴሌ ግራም ቻናላችን https://t.me/mergeta_amdebrhan ✅የቴሌ ግራም ቻናላችን t.me/mergeta_amdebrhane ✳️የቲክቶክ ቻናላችን http://tiktok.com/@mergetaamdebrhan 👉 ❗️❗️እውቀቱ ሳይኖራቸው በተመሳሳይ ፅሁፍ ኮፒ እያደረጉ ከሚያጭበረብሩ ሌቦች ተጠንቀቁ ሌባው በዝቷል ❗️❗️
Hammasini ko'rsatish...
👍 7
#ሰላም #ፍቅር #ጤና ለእምየ ኢትዮጵያ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁን። ዛሬ ስለ ......................               #ፍርሃት               #ዓይነ ጥላ               #ድንጋጤ               #መንቀጥቀጥ እና መፍትሔዎቻቸው የምናይ ይሆናል።             #ፍርሃት እንዲሁም ዓይነ ጥላ ከልጅነት  ጀምሮ እስከ  እውቀት ስነ ልቦናዊ፣ማሕበራዊ፣እንዲሁም አካላዊ  ችግሮችን መፍጠር የሚችል በአብዛኛው ሰው የሚገኝ በሽታ ነው። #ፍርሃት ወይንም ዓይነጥላ የሚባለው ችግር በዙርያችን ባሉ ለሰዎች ቅርብ የሆኑ ቁራኛ ሁነው ሰዎችን ለማሰቃየት የተዘጋጁ ፣ህይወትን የሚያጨልሙ፣ በክፉ መናፍስቶች የሚከሰት በሽታ ነው። #ፍርሃት እንዲሁም መንቀጥቀጥ የአጋንንት ሴራ እንዲሁም የክፉ መናፍስት ተንኮል ከሰው ዘንዳ ያላቸው ቅናት እና ተንኮል የሚያንጸባርቁበት እንዲሁም የምያሸማቁቅበት ክስተት ነው። #የፍርሃት እና የዓይነ ጥላ ምልክቶች፦ብዙ ጊዜ አጋንንት በቅናት መንፈስ ሰዎችን በመተናኮል በየትኛውም መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎቻችን የዘወትር ፈተናዎች የሆኑት ጥንተ ጠላቶቻችን ውግያቸው እጅግ በረቀቀ ስልታቸው ከሰዎች ዘንዳ በመላመድ የየእለት ተግባራችንን በመላመድ እንዳናስተውላቸው ወጥመዳቸውን በማጥመድ ለብዙ ፈተናዎች ይዳርጉናል። ከዚህም የተነሳ የፍርሃት እና የዓይነ ጥላ መናፍስቶች የሚፈጥሯቸው ችግሮች ከስር በትንሹ አስቀምጫቸዋለሁ። የሰዎች ፍራቻ የስራ ፍራቻ የትዳር ፍራቻ የትምህርት ፍራቻ የመብረቅ ፍራቻ የወሲብ ፍራቻ የብቸኝነት ፍራቻ የአይጥ ፍራቻ የጭለማ ፍራቻ የእባብ ፍራቻ የእሳት ፍራቻ የሞት ፍራቻ.....ወዘተ #እነዚህ እና የመሳሰሉት ፍራቻዎች ትልቅ የስነ ልቦና ቀውስ መሆናቸውን የተለያዩ ምሁራኖች በተለያዪ መንገድ ግንዛቤ ሲሰጡ ይስተዋላል። ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ስንገባ ግን ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች የሚፈጥሩ ቀናተኞች  እንዲሁም የሰው ልጅ ወደ ፈጣሪው መቅረቡ የሚያንገበግባቸው ክፉ መናፍስት መሆናቸው አስረግጦ ያስረዳናል። #ውድ ቤተሰቦቼ በየእምነታችሁ ጽኑ ጊዜው የፈተና እና የመናፍስት ውግያ የበዛበት ዘመን ነውና!እምነታችሁም አጠንክሩ !መናፍስትንም መርምሩ!የጥልቁ ዓለም ተላላኪዎችንም አጋልጡ! #የፍርሃት መናፍስቶች፦ ወደ ቤተ ክርስትያን ፣ወደ ገዳም፣ወደ ጸሎት ቦታ ለመቅረብ በምትፈልጉበት ጊዜ ብዙ ፈተናዎች ሊደርስባችሁ ይችላልና ተስፋ አትቁረጡ። ለምሳሌ፦እንቅልፍ ማብዛት፣ድብርት፣የወር አበባ፣ህልመ ለሊት፣ፍርሃት፣ጭንቀት የመሳሰሉት ምልክቶች ሊታዩባችሁ ይችላል እና በጸሎት ያሸንፉ። #ዓይነ ጥላ እና የፍርሃት መናፍስት፦ አእምሮን በመቆጣጠር ፣የልብ ምትን በመጨመር፣ የሆድ ሽብር በመፍጠር፣የሆድ ቁርጠት በማብዛት፣የእግር እና እጅ ቁርጥማት፣የወገብ ሕመም፣የወር አበባ ማብዛት፣ከፍተኛ የራስ ህመም በመፍጠር ትልቅ ማሕበራዊ ቀውሶችን ሊፈጥሩ ይችላሉ ። #ጸሎት #ስግደት #ንስሀ #እምነት #ጥበብን በማጠንከር ፍርሃትን ዓይነ ጥላን ማስወገድ እንችላለን እና በእምነታችን እንጠንክር። #ጥበባዊ የፍርሃት እና የዓይነ ጥላ መፍትሔዎች #የምድር እንቧይ ሥር #የአቶች ሥር #የሴት ቀስት ሥር #የሐረግ ሬሳ ሥር #እነዚህን ዕጽዋቶችን በንጽህና አድርቀው አድቅቀው በመፍጨት እንዲሁም ነፍተው በትንሿ የሻይ ማንኪያ ከሁሉም አንድ አንድ በመለካት በንፁሕ ሩብ ኪሎ ማር በመለወስ ጧት ጧት ለ ሰባት ቀን ይውሰዱ። ፍርሃትዎ ይጠፋል የዓይነ ጥላ መናፍስትንም ያስወግዳል። ተፈትኖ ያለፈ የአባቶች ሁነኛ ጥበብ ነው። እንዲሁም ከዚህ በፊት የላኩላችሁ በከርቤ ዕጣን ተጸልዮ ማታ ማታ የሚታጠንም ትልቅ መፍትሔ የሰጣቸው ሰዎች ምስክር ናቸውና። ሳምንቱን አብራችሁ ማታ ማታ ተጠቀሙ። #አምደብርሃን ይትባረክ !!! #አድራሻችን_ቁ/1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከ አደባባይ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መሄጃ... #አድራሻችን_ቁ/2 አ/አ ከ አየር ጤና ወደ አለም ባንክ መሄጃ በ ቤተል መገንጠያ በኩል ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት  እንገኛለን 👉 የስራ ሰአት ከሰኞ -ቅዳሜ ከ2:30 እስከ 11:00 ሰአት  ለበለጠ መረጃ (ለሐሳብ አስተያየተዎ ) 📞#0918487073  📞#0920253444 📞#0918834904  ይደውሉልን ✅ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት @merigetaamedeberhan ✅ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት @mergetaamedeberhane ✅ፌስቡክ ገፃችን https://www.facebook.com/profile.php?id=100076378898155 ✅የቴሌ ግራም ቻናላችን https://t.me/mergeta_amdebrhan ✅የቴሌ ግራም ቻናላችን t.me/mergeta_amdebrhane ✳️የቲክቶክ ቻናላችን http://tiktok.com/@mergetaamdebrhan ‼️ማስጠንቀቂያ የምፅፈውን ኮፒ በማድረግና አስመስለው ድምፃቸውን የሽማግሌ በማስመሰል መሪጌታ ነኝ እያሉ የሚያጭበረብሩ ሌቦች ስላሉ በተቻላችሁ ሀቅም ጥንቃቄ እንድታደርጉ ለማሳሰብ እወዳለሁ !!!
Hammasini ko'rsatish...
👍 2 1😢 1
#ቡግር ማጥፍያ እንሆ! #ኢትዮጵያ ታበፅሕ እደዊሃ ለእግዚአብሔ! ✔ብጉር እንዴት ይከሰታል? የተለያዩ የብጉር አይነቶች ቢኖሩም በጣም የተለመደው ግን በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚከሰተው ነው። ለአቅመ አዳም እና ሄዋን ስንደርስ የሆርሞናችን መጠን ይጨምራል በተለይ ቴስቴስትሮን! ይህ የሆርሞን ለውጥ የቆዳችን ዕጢ ብዙ ዘይት(ሴበም) እንዲያመርት ያደርገዋል። በቆዳችን ቀዳዳ የሚወጣው ዘይት ዋናው ጥቅሙ ቆዳችን ጤናማ ወዝ እንዲኖረው ማድረግ ነው። ብጉር የሚጀምረው ዘይት ከሞቱ የቆዳ ሴሎች ጋር ይቀላቀልና የቆዳችንን ቀዳዳ ይዘጉታል በዚህ ውህደት ውስጥ ባክቴሪያ ያገባና ያድጋል። ይህ ውህድ ከጐን ወዳለው የቆዳ ስጋ በማፈትለክ እብጠት፣ መቅላት እና መግል ይፈጥራል። #የሚከተሉት ብጉርን የሚያባብሱ ሁኔታዎች ናቸው፦ ※ ቆዳን የሚፈገፍጉ/የሚፈትጉ ነገሮች ለምሳሌ፦ ቀበቶ፣ ታይት፣ ሄልመንት፣ እጅ ላይ የሚታሰሩ ነገሮችና የመሳሰሉትን መጠቀም። ※ የፀጉርና ቆዳ መጠበቂያ ውጤቶች በተለይ በውስጣቸው የምያሳክክ ንጥረ ነገር የያዙ ※ ፊትዎን ዘወትር/በተደጋጋሚ መታጠብ እና ፊትዎን ሲታጠቡ በጣም ማሸት። ※ ሸካራ ሳሙና መጠቀም እና በጣም የሞቀ ውሃ መጠቀም እንዲባባስ ያደርገዋል። ※ ጭንቀት ሲኖር ※ ፊትን በተደጋጋሚ መንካት ※ ላብ በብዛት ሲያልበን ※ በፊት ላይ በዛ ያለ ፀጉር መኖር የፊት ቆዳ ዘይት/ቅባት እንዲኖረው ያደርጋል። ※ አንዳንድ መድሃኒቶች መውሰድ ※ በዘይት እና ኬሚካል ማምረቻዎች አካባቢ መስራት ※ አትሌቶችና ሰውነታቸውን የሚገነቡ ስፓርተኞች ስቴሮይድ ስለሚወስድ በብጉር የመጠቃት ዕድል አላቸው። ✔ የብጉር መከላከያ መንገዶች ብጉርን መከላከል አይቻልም ነገር ግን እንዳይባባስ የሚወሰድ እርምጃዎችና ጥንቃቄዎች አሉ ከነዚህም መካከል፦ ※ በዝግታ ወይም በጣም ሳይሹ መታጠብ ለቆዳዎ ጤንነት አስፈላጊ ነው። በጣም ማሸት፣ መጥረግ፣ መፈተግ ወይም መፈግፈግ ተገቢ አይደለም። ※ በጣም እንዳያልብዎ መጠንቀቅ። ላብ እንዲያልበን የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ካደረግን በኋላ ወዲያው መታጠብ። ※ ፀጉርዎ ቅባት ካለው ወይም ከበዛበት መታጠብ። ※ አንዳንድ የፀጉር መንከባከቢያ ምርቶችን መጠቀም ማቆም ለምሳሌ፦ ጄል፣ ክሬምና የመሳሰሉት ※ ፊትዎን ቶሎ ቶሎ ከመንካት መቆጠብ ※ ለስላሳ የኮተን ልብሶችን መጠቀም በተለይ ከቆዳ ጋር ንክኪ ያላቸው። ※ ከቅባት እና ኬሚካል ጋር ያለዎትን ግንኙነት መቀነስ/ማቆም ለምሳሌ ፔትሮሊየም። #የቆየ ብጉርንም ጭምር መፍትሔ #ነጭ ሽንኩርት ተልጦ ተፈጭቶ ግማሽ የሾርባ ማንኪያ! #የዝግባ ፍሬ ተፈልቅቆ ቅባቱን አውጥተው ፈጭተው ግማሽ የሾርባ ማንኪያ #ሁለቱም ውህድ በአንድ ሎሚ ውኃ አሽቶ ፊት ታጥቦ መቀባት ከዛ በኃላ ከ 3 ሰዓት በኃላ መታጠብ የቆየ ከሆነ አንድ ቀን እየዘለሉ ለ 3 ሳምንት ይጠቀሙ ብዙም ካልቆየ ከሳምንት እስከ ሁለት ሳምንት ይጠቀሙ ይድናል። የዝግባ ፍሬ ካላገኙ በሁለቱም ብቻ ማድረግ ይችላል። ሽንኩርቱ ተፈጭቶ በሎሚ ውኃ ታሽቶም መተቀም ይችላል። አምደብረሃን! #አድራሻችን_ቁ/1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከ አደባባይ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መሄጃ... #አድራሻችን_ቁ/2 አ/አ ከ አየር ጤና ወደ አለም ባንክ መሄጃ በ ቤተል መገንጠያ በኩል ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት  እንገኛለን 👉 የስራ ሰአት ከሰኞ -ቅዳሜ ከ2:30 እስከ 11:00 ሰአት  ለበለጠ መረጃ (ለሐሳብ አስተያየተዎ ) 📞#0918487073  📞#0920253444 📞#0918834904  ይደውሉልን ✅ቴሌግራም መልክት @merigetaamedeberhan ✅ቴሌግራም መልክት @mergetaamedeberhane ✅ፌስቡክ ገፃችን https://www.facebook.com/profile.php?id=100076378898155 ✅የቴሌ ግራም ቻናላችን https://t.me/mergeta_amdebrhan ✅የቴሌ ግራም ቻናላችን t.me/mergeta_amdebrhane ✳️የቲክቶክ ቻናላችን http://tiktok.com/@mergetaamdebrhan ‼️ማስጠንቀቂያ የምፅፈውን ኮፒ በማድረግና አስመስለው ድምፃቸውን የሽማግሌ በማስመሰል መሪጌታ ነኝ እያሉ የሚያጭበረብሩ ሌቦች ስላሉ በተቻላችሁ ሀቅም ጥንቃቄ እንድታደርጉ ለማሳሰብ እወዳለሁ !!!
Hammasini ko'rsatish...
👍 5 1