"ኡማ ቲቪ " Tv
Kanalga Telegram’da o‘tish
ለበለጠ ወቅታዊ መረጃወችን ለማገኘት የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇 https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf
Ko'proq ko'rsatish2025 yil raqamlarda

46 270
Obunachilar
-1424 soatlar
-827 kunlar
-52630 kunlar
Postlar arxiv
ሰሞኑን አስተባብረን እንደ ሁልጊዜው ለአንድ መስጅድ ለረመዷን የሚደርስ ምንጣፍ ብናነጥፍ ምን ይመስላቹሀል ? ረመዷኑም እየቀረበ ስለሆነ የአላህ ባሪያወችም በመስጅዶች ይደምቃሉ ። የሚሳተፍ እስኪ?
👍 47❤ 8💯 6
Repost from "ኡማ ቲቪ " Tv
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ
ውድና የተከበራቹህ #የዳሩር ኡማ ቤተሰቦች በሙሉ የአላህ ሰላምና እዝነት በእናንተ ላይ ይስፈን ።
እንደሚታወቀው በየዓመቱ የተለያዩ መልካም ስራወችን ከእናንተ ጋር በመሆን እያከናወን እንገኛለን አልሀምዱሊላህ በቋሚነት ከምንሰራቸው ፕሮጀክቶች በዋናነት ከሚጠቀሱት የመስጅድ ምንጣፍ ድጋፍ ይገኝበታል ።
ላለፉት ሁለት አመታት በተለያየ ቦታ ከላይ የምትመለከቶቸውን ምንጣፎች አንጥፈን የአላህ ባሪያወች እየሰገዱበት ይገኛል ።
በአላህ ፍቃድ በእናንተ እገዛ ሰሞኑን #ለ3ተኛ ዙር የመስጅድ ምንጣፍ ለማንጠፍ የገቢ ማሰባሰቢያ እናደርጋለን በደንብ ተዘጋጁ ።
ዘንድሮ የተለያዩ መስጅዶች ላይ የምንጣፍ ችግር አለ ። ከሁሉም የባሰበትን ዘንድሮ የምናነጥፍ ይሆናል ። ምናልባት ይሆናል ብለን ያሰብነው መስጅድ የባሰበት ካለ ሀሳብ ስለሚቀየር የገቢ ማሰባሰቢያው ዕለት ከመከናወኑ በፊት ጥቆማ መስጠት ይቻላል ።
ጥቆማና ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት @faysul
ማሳሰቢያ ጥቆማ ስሰጡ የባሰበት ምንጣፍ የሌለው ➙ጁመዓ የሚሰገድበት➙የሀገሩ ትልቁ መስጅድ መሆን አለበት➙የአከባቢው ማህበረሰብ ደካማ መሆንም አለባቸው ።
የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ ።
https://t.me/darulOmah
https://t.me/darulOmah
❤ 19
እዚህ ምድር ላይ ምንም አይግረምህ
ለምን እንደማይገርም ታቃለህ
በጣም ተወጥሮ ሰውን አላስቀምጥ ያለ ሰው ተደብቆ ሲሄድ ታያለህ ። በጣም ሀብታም የነበረ ወርዶ ትመለከታለህ ። ወረደ ያልከው ትልቅ ደረጃ ደርሶ ትመለከታለህ ይመስልሀል እንጂ የጊዜ እንጂ የሰው ሀያል የለውም ።
👍 51❤ 13🙏 2
ያ ኢላሂ ...
መስጅዶች ውስጥ የቤት ኪራይ መክፈል አቃተን፣ ልጆቻችንን የምንመግባቸው አጣን... የሚሉ ድምፆች እየበረከቱ ነው። ኑሮው ብዞዎችን እየፈተነ ነው። የሰው ፊት መቆም ከብዷቸው በየቤታቸው በችግር የሚሰቃዩ ቤቱ ይቁጠራቸው። ከምንም ጊዜ በላይ እርስበርስ ልንተዛዘን የሚገባን ጊዜ ላይ ነን። በዙርያችን፣ ጎረቤቶቻችን ያሉበት ሀል ማወቅ ባለን ነገር መተጋገዝ ይገባናል።
አላህ ይሁነን!
🙏 105👍 35😢 28❤ 25
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከአምቢያ መስጂድ ወጣት ጀምአ ጋር በመተባበር ታላቅ የደአዋ ፕሮግራም አከናወነ።
የደአዋ ፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ ሙሐመድ ሸሪፍ እና የከፍተኛ ምክር ቤቱ ዋና ፀሀፊ ኡስታዝ ሺሐቡዲን ሼህ ኑራ እንዲሁም ሌሎች የስራ አስፈፃሚ አባላት እና የክፍለ ከተማው መጅሊስ አመራሮች ተገኝተዋል።
በደአዋው ፕሮግራም ላይ ኡስታዝ ሱልጣን ኸድር "የአላህ ጥበቃ" በሚል ርዕስ ለታዳሚው ትምህርት ያቀረቡ ሲሆን የአላህ ጥበቃ በተሟላ መልኩ አጠገባችን እንዲኖር ከወንጀል የፀዳ ህይወት ሊኖረን ይገባል ብለዋል::
ሌላኛው ደአዋ አድራጊ ኡስታዝ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ ሲሆኑ "የእምነት አስፈላጊነትን" በተመለከተ መልእክት አስተላልፈዋል::
እስልምና ተፈጥሮአዊ ዲን በመሆኑ ትዕዛዛቱም ከውስብስብ ሀሳቦች የፀዳ እና በግልፅነት ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ ገልፀዋል::
በዚህ የደአዋ ፕሮግራም ላይ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ኡስታዝ ሸሀቡዲን ሼህ ኑራ ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል::
ዋና ፀሀፊው በመልእክታቸው በዚህ አይነት የሰዎች ስብስብ ላይ ተገኝቶ ስለ እስልምና መስማት አስደሳች ነው በማለት ገልፀዋል::
ወጣቶች የእምነት ሀላፊነት ተረክበው እንዲሄዱ ከተፈለገ የእውቀትን አስፈላጊነት በተሻለ መልኩ መረዳት ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል::
በዲጂታል ዘመን ላይ እንደመገኘታችን ወጣቶች ዘመኑ በሚጠይቀው መንገድ እውቀትን ለሰዎች ለማስተላለፍ ጥረት ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለወጣቶች የሚሆን የተሻለ አደረጃጀት በቀጣይ ለመስራት በእቅድ ላይ ስለሆንን ወጣቱ የሚጠቀምበትን እድል ለመፍጠር ተቀራርበን መስራት አለብን ሲሉ ገልፀዋል::
ወጣቶቾን ለዲን በሚጠቅም መኩል ለማብቃት ይህን መሰል የእውቀት ማግኛ መንገድ አስፈላጊ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል::
በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ም/ፕሬዝዳንት ሼህ ሙሐመድ ሸሪፍ የተገኙ ሲሆን ወጣቶች ከብዙ አሳሳች ነገር ራሳቸውን አቅበው በዚህ መሰል የዲን ተግባር ላይ መሳተፍ መቻል ትልቅ እድል ነው ብለዋል::
ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ መጅሊስ ውጤታማ እንቅሰቃሴ እያደረገ መሆኑን አንስተው ወጣቱን ያሳተፈ ተግባር ላይ ጠንክረው እንዲሰሩ መልእክታቸውንም አስተላልፈዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ መጅሊስ ወጣቱን በእውቀት እና በአመራር ልምድ አሳድጎ ነገ ተቋም የሚመራበትን እድል እንዲያገኝ አስቦ እየሰራ ስለሆነ ወጣቶች ተቋማችሁን በቅርበት ሆናችሁ እንድታግዙት በማለት መልእክት አስተላልፈዋል::
በዝግጅቱ ላይ የአንቢያ መስጂድ እና የአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ በመስጂዱ በመገኘት የደአዋ ፕሮግራሙን ተከታትሏል::
❤ 29👍 5
Repost from "ኡማ ቲቪ " Tv
Photo unavailableShow in Telegram
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
አር-ሪሳላህ የቁርዐን ማዕከል ለሙስሊሙ ኡማ አስደሳች ዜናን ይዞ መጥቷል ።
በየትኛውም የእድሜ ክልል ላይ ለሚገኙ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ኢስላማዊ እውቀትን ከመሰረቱ በማስተማር ከዳር እስከ ዳር ተደራሽ ለማድረግ በእምነቱ ጠንካራ የሆነን ማህበረሰብ ለመፍጠር ዝግጅቱን ጨርሷል ።
በአማርኛ
በኦሮመኛ
በጉራጌኛ
በስልጢኛ እና በእንግሊዝኛ
ቋንቋዎች በኦንላይን ለማስተማር በምዝገባ ላይ ይገኛል።
በማዕከሉ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች
📌 ቃኢደቱ ኑራኒያህ ለጀማሪዎች
📌 የቁርዐንን እያዩ ለማንበብ ከመሰረታዊ የተጅዊድ ትምህርት ጋር
📌 ቁርአን ሂፍዝ ከተሟላ ሙራጅአ ጋር
📌የተርቢያ (የመልካም ስነምግባር ) ግንባታ እና ክትትል
📌 አጫጭር የአቂዳ የፊቂህ እና የ ሃዲስ ኪታቦች ይሰጣሉ
የትምህርት አሰጣጥ ሁኔታ
በመረጡት የሶሻል ሚድያ አማራጮች
- በዙም
- በቴሌግራም
- በዋትስ አፕ
- በኢሞ እንዲሁም በሌሎች አማራጮች ባሉበት ሁነው የእጅ ስልክዎን ብቻ በመጠቀም የሚሰጥ ይሆናል።
የቂርአት ሰአቶች
በሳምንት 6 ቀን
ከ ፈጅር ብኋላ እስከ 1:00 ሰአት
ከ 2:00 -6:00
ከ8:00 - አሱር
ከ አሱር ብኋላ እስከ መግሪብ
ከ ምሽቱ 2:00 - 6:00
☎️ ለበለጥ መረጃ እና ለምዝገባ
በ 0914696797 ወይም
በ 0717189395 ይደውሉ
📱በቴሌግራም ለማናገር
@A_Abuyasmin
❤ 8😡 1
Photo unavailableShow in Telegram
Great to see this!
ዘምዘም ባንክ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የተከፈለ ካፒታል ሚኒማ በሟሟላቱ እንኳን ደስ ያለን!
❤ 38👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
በሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን (ዶ/ር) የተመራው የአሊፍ ጀመኣ ልኡካን ቡድን በሀላባ ዞን የሚገነባውን ሱና ዩኒቨርሲቲ ጎበኘ!
- ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ፥ ታህሳስ 5/2018
በሸይኽ ሙሐመድ ሀሚዲን (ዶ/ር) የተመራው የአሊፍ ጀመአ ልኡካን ቡድን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የሚገነባውን ሱና ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በስፍራው በመገኘት ምልከታ አድርገዋል።
በጉብኝቱ ላይ ከአሊፍ ጀመአ የተወከሉ መነሻቸው ከሀገራችን ከሁሉም አቅጣጫ የሆነ በኸይር ስራ ላይ በመሳተፍ የሚታወቁ በርካታ ወንድሞች በዶክተር ሸይኽ ሙሐመድ ሀሚዲን እየተመሩ ወደ ዮኒቨርሲቲው የግንባታ ስፍራ ተገኝተዋል፡፡
በሀላባ ዞን መጅሊስ ሰብሳቢ ሸይኽ ሁሴን መሀመድ የተመራውና ኡለማዎች፣ መሻኢኾችን የመጅሊስ አመራሮችንና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ያካተተው የሀላባ ጀመአ ደመቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።
በጉብኝቱም ወቅት በርካታ ሀሳቦች የተንሸራሸሩ ሲሆን ለዩኒቨርሲቲው የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት ስፍራ ከታሪካዊ የበደኔ አካባቢ አቅራቢያ መሆኑ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ተገልጿል።
ከዩኒቨርሲቲው ግንባታ በተጓዳኝ የትምህርት ስራ በአስቸኳይ መጀመር እንደሚገባው ስምምነት ላይ መደረሱም ነው የተገለፀው። የአክፍሮት ሀይላት እንቅስቃሴን በመግታት ዲነል ኢስላምን ለሌሎች ለማዳረስ የዲን እውቀት ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል።
📎 ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ በስፍራው ተገኝቶ ያጠናቀረው ሙሉ የቪዲዮ ዘገባ እንደደረሰን የምናቀርብላችሁ ይሆናል፡፡
© ሀሩን ሚዲያ
❤ 18🙏 3
Photo unavailableShow in Telegram
"ዛሬ የሰለፎችን ዓቂዳ አጥብቆ የያዘ ሰው እንደ 'ካፊር' ወይም 'መጤ' ተደርጎ የሚፈረጅበት ዘመን ላይ ደርሰናል!"
"እስልምናን በ ወሕይ ሳይሆን በግሪክ ፍልስፍና (Philosophy) መነጽር የሚከተል መቷል"
"50 ኪታብ በራሴ ስም አወስዳለሁ"
ሲጠበቅ የነበረው የሸይኽ ሰዒድ አራጌ "አውኑ ረህማን" የተሰኘው መፅሐፍ ምረቃ ፕሮግራም ላይ ከተናገሩት!
#አፍሪካ_ቲቪ
#የህይወት_ጎዳና
❤ 55👍 6😡 1
Photo unavailableShow in Telegram
እነሱ ሲያሰለጥኑ የእነሱን እንቶ ፈንቶ ተግተው የእነሱ ካድሬ እንዲሆኑላቸው ነበር ያሰቡ ወንድማችን ሸይኽ ሰዒድ አራጌ ግን ጥሩ አላማ ብሩህ አስተሳሰብ ስለነበራቸው አጋጣሚውን ለትልቅ አላማ ተጠቅመውበታል
ሁል ጊዜ ፈር ቀዳጅ የሆነ ሰው ትልቅ ውለታ ነው ለታሪክ ትቶ የሚሄደው
ከዚህ ቡሀላ በየዘርፉ የዚህ አይነት ስራ መስራት አለብን ሀገር በቀል የሆኑ መፅሀፎችን ማዘጋጀት አለብን
ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ
የሸይኽ ሰዒድ አራጌ "አውኑ ረህማን" የተሰኘው መፅሐፍ ምረቃ ፕሮግራም ላይ ከተናገሩት!
#አፍሪካ_ቲቪ
#የህይወት_ጎዳና
❤ 35👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
"የዒልም መሰረት በማንበብ ነው የሚገኘው"
ይህ በሸይኽ ሰዒድ የተዘጋጀው "ዓውኑ ረህማን" የተሰኘው መፅሀፍ በቅርቡ የደረሰኝ ቢሆንም የተወሰነውን ያክል ለማንበብ ሞክሬ ነበር በብዙ መልኩ የተደመምኩባቸው ቁም ነገሮች አሉ ።
ሸይኽ ኢልያስ አህመድ
የሸይኽ ሰዒድ አራጌ "አውኑ ረህማን" የተሰኘው መፅሐፍ ምረቃ ፕሮግራም ላይ ከተናገሩት!
#አፍሪካ_ቲቪ
#የህይወት_ጎዳና
❤ 27💯 3👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኢስናድ የዲን አካል ነው, ኢስናድ ባይኖር ሁሉም ሰው የሻውን ይናገር ነበር
በዝግጅቱ ላይ የታደሙት ሸይኽ ኤልያስ አህመድ፣ ኢስናድ በኢስላም ውስጥ ያለውን ወሳኝ ሚና በማስረዳት፣ የእውቀት ምንጮችን በፅሑፍ በማዘጋጀት የቀደምት ሰለፎችን እምነት መጠበቅ ስለሚያስፈልገው ጉዳይ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሸይኹም "ኢስናድ የዲን አካል ነው፤ ኢስናድ ባይኖር ሁሉም ሰው የሻውን ይናገር ነበር"የሚለውን የአብደላህ ኢብኑ ሙባረክ ንግግርን በማውሳት ሰነድ ለሃይማኖታዊ ትምህርቶች እውነተኛነት እና ተዓማኒነት ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።
ኢስናድ የእውቀት ምንጭነቱን ለማረጋገጥ እና ከስህተት ለመጠበቅ የሚያስችል መሠረታዊ የዲን መርህ ነው።
የዚህ ዓይነቱ የእውቀት ቅብብሎሽ እና የፅሑፍ ዝግጅት መዳከም፣ ውሸት መልኩን ቀይሮ እንዲመጣ በር እንደሚከፍት ጠቁመዋል።
በተጨማሪም፣ በማህበረሰቡ ዘንድ የሚታወቁ የሃይማኖት የእምነት ርዕሶች እንደ የኺላፍ (የልዩነት) ርዕሶች እየተመሰሉ እንዲሰራጩ እንደተደረገ አውስተዋል።
እንደዚህ ዓይነቱ የእውቀት ዝግጅቶች ለሚነሱ ውዥንብሮችና የተዛቡ አመለካከቶች ዓይነተኛ መፍትሄ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።
እምነት ማለት የቀደምት ሰለፎች መንገድ እንደሆነ በማውሳት፣ ይህ እምነት የሚገነባውም በመረጃና በሰነድ የተደገፈ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
በመጨረሻም ሸይኽ ኤልያስ አህመድ፣ ኢስናድ የዲን መሠረት መሆኑን አብራርተው፣ በውሸት የሚመጡ ውዥንብሮችን ለመከላከል የቀደምቶችን እምነት የሚጠብቁና በመረጃ የተደገፉ እውቀታዊ መጻሕፍት መዘጋጀታቸው እና የእውቀት ቅብብሎሹ መቀጠሉ ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል።
#ሱና_ዩኒቨርሲቲ | #አወሊያ | #የእውቀት_ብርሃን | #ለትውልድ_አሻራ | #አብሮነት
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
❤ 33👍 5
የእውቀት ቅብብሎሽ እና የሰለፎች መንገድ አስፈላጊነት
ቀን: ታህሳስ 05, 2018 ዓ.ም.
ቦታ: አዲስ አበባ፣ አወሊያ መመረቂያ አዳራሽ
በሸይኽ ሰዒድ አራጌ "አውኑ ረሕማን" መጽሐፍ ምርቃት ላይ የቀረቡ ወሳኝ ምክሮች
በአወሊያ መመረቂያ አዳራሽ የተካሄደው የሸይኽ ሰዒድ አራጌ "አውኑ ረሕማን" መጽሐፍ ምርቃት ዝግጅት፣ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪካዊ ፈተናዎች እና የዒልም (የእውቀት) ቅብብሎሽ ወሳኝ ሚና ላይ ትኩረት አድርጎ ተካሂዷል። ዝግጅቱ በዋነኝነት የታሪካዊ ውዥንብሮችን (እንደ አህባሽ አጀንዳ ያሉትን) ለመመከት እና የእምነትን ንጽህና ለመጠበቅ የፅሑፍ ሥራዎች እና ኢስናድ (የሰነድ ሰንሰለት) ያላቸውን ወሳኝ ሚና አጉልቷል።
ፕሮግርሙ ላይ የተለያዩ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ የነበሩት ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን ዘህረዲንም በንግግራቸው፣ ዑለማዎች የቀደመውን የእውቀት ውርስ ለመቀጠል እና ለትውልድ ለማሻገር፣ በሀገር ቋንቋ የተለያዩ መጻሕፍትን በማዘጋጀት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አደራ አሳስበዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የታደሙት ሸይኽ ኤልያስ አህመድም በመረጃ እና በሰነድ የተደገፈ እውቀት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል። "ኢስናድ የዲን አካል ነው፤ ኢስናድ ባይኖር ሁሉም ሰው የሻውን ይናገር ነበር" የሚለውን የአብደላህ ኢብኑ ሙባረክን ንግግር ጠቅሰው፣ በመረጃና በሰነድ የተደገፈ እውቀት ብቻ ከውሸቶች እና የተዛቡ አመለካከቶች (የእምነት ርዕሶችን የኺላፍ ርዕስ አድርጎ ከማቅረብ) እንደሚከላከል አብራርተዋል።
ኡስታዝ አህመዲን ጀበልም በሰጡት አስተያየት፣ በሰለፎች አኗኗር (ሀያት) ላይ ብቻ ከማተኮር ጎን ለጎን፣ መሰረታዊ የሆነውን እምነታቸውን (አቂዳቸውን) ለመጠበቅ እና ትኩረት ለመስጠት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
በመጨረሻም፣ ዝግጅቱ ሁሉም ሙስሊሞች በተለይም ደግሞ ዑለማዎች የሰለፎችን ንጹሕ አቂዳ በመረጃ (ኢስናድ) ላይ ተመስርቶ እንዲያሰራጩና ለቀጣዩ ትውልድ በሀገር ቋንቋ የተሟላ የእውቀት ቅብብሎሽ አሻራ እንዲያስቀምጡ አሳስቦ ተጠናቋል።
#ሱና_ዩኒቨርሲቲ | #አወሊያ | #የእውቀት_ብርሃን | #እስልምና_እና_ዕድገት | #ለትውልድ_አሻራ | #አብሮነት
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ
❤ 24😡 2🙏 1
ወ/ት ለይላ ኑርሰቦን በተመለከተ ሰሞኑን የተለያዩ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የቆየ በመሆኑ፣ ጉዳዩን በተመለከተ ያለው መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል።
ወ/ት ለይላ ኑርሶቦ የተባሉ ዜጋችን በነብስ ማጥፋት ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው ለረዥም አመታት በፍርድ ሲታይ የቆየ መሆኑ ይታወቃል።
በዚሁ መሠረት ከተጎጂ ቤተሰቦች ጋር እርቅ በማውረድ የገንዘብ ካሣ በመክፈል ቤተሰብ ምህረት እንዲያደርግላቸው በሽምግልና ስምምነት ላይ ተደርሶ፣ ኮሚቴ በማቋቋም ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እርዳታ በማሰባሰብ የገንዘብ ካሣ ለተጎጅ ቤተሰቦች ተከፍሏል።
ይሁን እንጂ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ አግኝቶ፣ በቤተሰብ ደረጃ የተሰጠው ምህረት በፍርድ ቤት ተቀባይነት አግኝቶ ምህረቱ ተፈጻሚ ይሆን ዘንድ ኤምባሲያችን ከሚመለከተው የሳዑዲ መንግስት ተቋማት ጋር ሲያደርግ የነበረውን የቅርብ ክትትል አጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን እንገልጻለን።
©የኢትዮጵያ ኢንባሲ ሪያድ
❤ 34
اللهم اني تبرأت من حولي وقوتي ولجأت إلى حولك وقوتك ياحي ياقيوم..
👍 22❤ 11🥰 3💯 2
Photo unavailableShow in Telegram
የተመድ መረጃ
=========
በጋዛ ሰርጥ ከ140,000 በላይ ሰዎች በዝናብ ውሃ ተጎድተዋል፣ በጦርነቱ ሳቢያ በመቶ ሺዎች አልቋል፣ አስቸጋሪ በሆኑ ሰብአዊ ሁኔታዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ህይታቸው አልፈዋል።
ቤቶችና መሰረተ ልማቶች በስፋት ወድመዋል። ወረራው እስራኤል በነዋሪዎች ላይ ቀጣይ የሚጥለው የእርዳት ገደብ ገደብ ያስፈራል ይህ የህዝቡን ስቃይ የሚያባብስ ነው።
በተኩስ አቁም ስምምነቱ መሰረት ቤቶችን መልሶ መገንባትን እና ሰብአዊ አርዳታዎችን ያለ ገደብ መፍቀድ እንደሆነ አጉልቶ ያሳያል
ያበጠው የእስራኤል ኢብሪት በቅርቡ ይተነፍሳል
❤ 48😢 23
Photo unavailableShow in Telegram
#በኢራን የተደረገ አስገራሚ #ጥሎሽ
ዶክተሩ ሙሽራ ዶክተሯን ሙሽሪት በሚገርም ጥሎሽ አግብቷታል ጥሎሹ 313 ቀዶ ጥገና ለድሆችና ለችግርተኞች በነፃ ማድረግ ነበር።
❤ 145👍 48
