uz
Feedback
ATC NEWS

ATC NEWS

Kanalga Telegram’da o‘tish

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA ለመልዕክት 👇🏻 @mujaabot For Advertisement👇🏿 @atcads

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
127 423
Obunachilar
-6624 soatlar
-2667 kunlar
-76830 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
#DillaUniversity በዲላ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው ፕሮግራም የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመማር አመልክታችሁ ተቀባይነት ያገኛችሁ አመልካቾች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 09 እና 10/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ ➫ በህክምናና ጤና ሳይንስ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ (ሆስፒታል ግቢ) ሬጅስትራር ፅ/ቤት ➫ በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ በኦዳያኣ ግቢ ዋና ሬጅስትራር ህንፃ ቁጥር 609 ➫ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ ነባሩ ግቢ ሬጅስትራር ፅ/ቤት ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒውን፣ ➫ የቅርብ ጊዜ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ➫ Official Transcript ለዲላ ዩኒቨርሲቲ በፖ.ሳ.ቁ. 419 ወይም በኢ-ሜይል አድራሻ registrar@du.edu.et ማስላክ፣ ➫ በመንግሥት ስፖንሰር የተደረጉ ከሆነ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርብዎታል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#DebarkUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር á‹°á‰Łáˆ­á‰… ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም እንዲሁም በቅጣት ህዳር 29/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ትምህርት የሚጀምረው ህዳር 29/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3×4 የሆነ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ፣ ብርድ ልብስ እና á‹¨áˆľá–áˆ­á‰ľ ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር በዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤታማነት ላይ ጥናት እያካሔደ ነው፡፡ ጥናቱ በሦስት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ይፋ እንደሚደረግ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡ መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል። እስከ 250 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች በዓመት ሁለት ጊዜ የሚሰጠውን ፈተና እየወሰዱ መሆኑን የገለፁት መሪ ስራ አስፈጻሚው፤ ፈተናው ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት መቅሰም የሚጠበቅባቸውን ክህሎት እና እውቀት ለመፈተሽ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል። የመውጫ ፈተናውን ውጤታማነት በመገምገምና በቀጣይ መሰራት ያለበትን ሥራ በመለየት የአፈጻጸም ወጥነትን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ጥናት በቀጣይ ሦስት ወራት ተጠናቆ ይፋ ይደረጋል ብለዋል። #ኢዜአ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#UnityUniversity ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፍላጎትና ብቃት ያላቸው መምህራን እና አሰልጣኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ➤ የሥራ መደብ፦ መምህራን እና አሰልጣኞች ➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 24 ➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ➤ የሥራ ልምድ፦ ከ2-5 ዓመት ➤ የሥራ ቦታ፦ አዲስ አበባ፣ አዳማ እና ደሴ የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ አርብ ህዳር 05/2018 ዓ.ም የምዝገባ ቦታ፦ ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች CV እና የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒውን በመያዝ አዲስ አበባ ገርጂ የዩኒቨርሲቲው የሰው ሃብት አስተዳደር ቢሮ ወይም ቡራዩ የዩኒቲ አካዳሚ በአካል በመቅረብ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#JinkaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 10 እና 11/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ለምዝገባ ስትሔዱ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው እንዲሁም አንሶላ እና ትራስ ጨርቅ መያዝ ይኖርባችኋል። ትምህርት ህዳር 15/2018 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ዩኒቨርሲቲዎች በለብለብ እያስተማሩ ተማሪዎችን ማስመረቃቸውን እንዲያቆሙ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሳሰቡ፡፡ የዩኒቨርሲቲዎቹ ስኬት መለካት ያለበት ባስመረቁት ተማሪ ብዛት ሳይሆን፣ በተማሪዎቻቸው ብቃት ሊሆን እንደሚገባ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡ 34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ ነው፡፡ ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለመፍጠር ጥራት ያለው ትምህርት መስጠት የግድ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ በኋላ ለተማሪዎቻቸው ዲግሪ ሲሰጡ ያሰለጠኗቸው ተመራቂዎች ከሌላው ዓለም ጋር መወዳደር እንደሚችሉ ማረጋገጥ ሲችሉ ብቻ ሥራቸውን ተወጥተዋል ማለት እንደሚቻል ሚኒስሩ ገልፀዋል፡፡ በቅርቡ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ በተደረገ ምልከታ ትምህርት ማስተማር ያልጀመሩ ዩኒቨርሲቲዎች መኖራቸውን  አረጋግጠናል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ዩኒቨርሲቲዎች ይህን “እንዝህላልነት“ ሊቆጣጠሩ ይገባል፣ “መምህራን ገብተዋል ወይ፣ ማስተማር ጀምረዋል ወይ? ይህን መቆጣጠርና ማስተካከል ይኖርብናል“ ብለዋል፡፡ #ShegerFM ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#RayaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 22 እና 23/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#GambellaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 15 እና 16/2018 ዓ.ም  መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አራት 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ ዲጂታል መታወቂያ፣ ➫ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#BahirDarUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 11 እና 12/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። የምዝገባ ቦታ፦ ➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች - ግሽ አባይ ግቢ ➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች - ዘንዘልማ ግቢ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አራት 3x4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#JigjigaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ከህዳር 05-08/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ8-12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ስምንት ፓስፖርት መጠን የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ልብስ፡፡ ህዳር 09/2018 ዓ.ም ለአዲስ ገቢ የሪሚዲያል ተማሪዎች ገለጻ የሚሰጥ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ቀን ትምህርት ህዳር 10/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#WerabeUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ወደ ፊት የሚገለጽ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ እስከዛ ድረስ ጉርድ ፎቶግራፍ ተነስታችሁ በ https://ssms.wru.edu.et/sp አማካኝነት ወደ ሲስተም ከጥቅምት 30/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 05/2018 ዓ.ም እንድታስገቡ ተብሏል፡፡ የምታስገቡት ጉርድ ፎቶግራፍ ጥራት ባለው ስማርት ስልክ የተነሳችሁት መሆን ይኖርበታል፡፡ ፎቶው ወደ ሲስተሙ ከገባ በኋላ ተቀባይነት እስከሚያገኝ ድረስ Waiting for Approval የሚል ምላሽ ሲስተሙ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ተቀባይነት ካገኘ Approved ፤ ተቀባይነት ካላገኘ Rejected የሚል ምላሽ ሲሰተሙ የሚሰጥ ሲሆን Rejected የተባለው ፎቶግራፍ በሌላ ጥራት ባለው ጉርድ ፎቶግራፍ መቀየር ይኖርብዎታል፡፡ ለበለጠ መረጃ፦ 0925139032 / 0712595832 መኪ 0913737976 / 0717737976 ሀሺም ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#DambiDolloUniversity በ2018 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ትምህርታችሁን በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለመከታተል ያመለከታችሁ የምዝገባ ጊዜው በአንድ ሳምንት መራዘሙን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡ በዚህም፦ ➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ማስገቢያ ቀን፦ ህዳር 09/2018 ዓ.ም ➫ የትምህርት ክፍያ መክፈያ የመጨረሻ ቀን፦ ህዳር 09/2018 ዓ.ም ➫ የኦንላይን ምዝገባ የሚጀመርበት ቀን፦ ህዳር 10/2018 ዓ.ም ➫ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን፦ ህዳር 11/2018 ዓ.ም (ለመደበኛ) እና ህዳር 13/2018 ዓ.ም (ለእረፍት ቀናት መርሐግብር ተማሪዎች) ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#MoLS የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለፌደራል ግብርና፣ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በ16 የሥራ ዘርፎች በወጣው ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ ላይ ለተመዘገባችሁና ለቀጣዩ ዙር ቃለ-መጠይቅ በስልክ ቁጥራችሁ አጭር የፅሑፍ መልዕክት የደረሳችሁ አመልካቾች ከህዳር 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት ከታች በተቀመጠው የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ቅደም ተከተል በተመደባችሁበት ቀን እና ሰዓት የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዛችሁ አዲስ አበባ ወሰን አካባቢ አሰለፈች መርጊያ ሆቴል አጠገብ ባለው የብየዳ ማዕከል እንድትገኙ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡ የቀጠሮ ቀን እና ሰዓት፦ ሰኞ ጠዋት 3:00 A-B ሰኞ ከሰዓት 8:00 B-D ማክሰኞ ጠዋት 3:00 D-H ማክሰኞ ከሰዓት 8:00 H-M ረዕቡ ጠዋት 3:00 Me-Si ረዕቡ ከሰዓት 8:00 So-Y ሐሙስ ጠዋት 3:00 Yo-ሰ ሐሙስ ከሰዓት 9:00 ሰ-ነ አርብ ጠዋት 3:00 አ-ወ አርብ ከሰዓት 3:00 ዘ-ፈ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% ባነሰ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% ባነሰ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#KabridaharUniversity በ2018 ዓ.ም ቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 08 እና 09/2018 ዓ.ም እና ምዝገባ ህዳር 08 እና 09/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬቶች ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ስምንት 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገበት ነው። - ትምህርት ሚኒስቴር ‌‎የሚከለሰው ስርዓተ ትምህርት በ2018 ዓ.ም ዩኒቨርስቲ የገቡ ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል። ስርዓተ ትምህርቱን የመከለስ ሥራ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ተልዕኮ መሰረት ባደረገ መልኩ እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ገልፀዋል። የቀድሞዎቹ ስርዓተ ትምህርቶች ዘመኑን ያልዋጁና ከዘመኑ ጋር በአግባቡ ያልተቃኙ በመሆናቸው ክለሳው ማስፈለጉን መሪ ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል። የሚከለሰው ስርዓተ ትምህርት ምሩቃን ሥራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ትምህርት ፕሮግራሞች ዴስክ ኃላፊ ተስፋዬ ነገዎ ገልፀዋል።‎ እስካሁን በሁለት ዙሮች 55 የትምህርት ፕሮግራሞች ተከልሰዋል የተባለ ሲሆን፤ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ከ80 የሚበልጡ ፕሮግራሞች እንደሚከለሱ ተገልጿል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርፕሮፐርቲስ ⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል። ⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል። 📍 ሊሴ ገ/ማርያም ባለ 1 መኝታ 👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000                  ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000) 👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000                  ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500) ባለ 2 መኝታ 👉 78 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,970,000                  ቅድመ ክፍያ = 10% (897,000) 👉 99ካሬ ሙሉ ክፍያ = 11,385,000                 ቅድመ ክፍያ = 10% (1,138,500) ባለ 3 መኝታ 👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000                    ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000) 👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000                    ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000) 📍 አያት (ፈረስ ቤት) ባለ 2 መኝታ 👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000                  ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000) ባለ 3 መኝታ 👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000                    ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000) 👉 121 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 11,495,000                    ቅድመ ክፍያ = 10% (1,149,500) 👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000                    ቅድመ ክፍያ = 10% (1,570,000) 📍 ተክለሐይማኖት (ሱማሌ ተራ) ባለ 3መኝታ 👉 110ካሬ ሙሉ ክፍያ = 12,100,000ብር                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,210,000) ብር 📍ሀይሌ ጋርመንት ባለ 3መኝታ 👉 139ካሬ ሙሉ ክፋያ =14,595,000 ብር            ቅድመ ክፋያ 10%= (1,459,500ብር) ⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን! +251936650128 +251994495655
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#BoranaUniversity በ2018 ዓ.ም ቦረና ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 03 እና 04/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
በክረምት ሥልጠና ከተካተቱ 110 ሺሕ መምህራን መካከል 70 በመቶዎቹ የብቃት ምዘና ፈተናውን አልፈዋል ተባለ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ታስቦ ላለፉት 2 ዓመታት በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተሰጠውን የመምህራን የክረምት ስልጠና ከተሳተፉ 110 ሺሕ የ2ኛ ደረጃ መምህራን መካከል፤ 70 በመቶዎቹ የብቃት ምዘና ፈተናውን ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። መምህራኖቹ በማስተማሪያ ይዘት፣ በትምህርት መስክ ዕውቀት፣ በማስተማር ሥነ-ዘዴ እና በዲጂታል ክህሎት ዙሪያ የወሰዱትን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና በጥሩ ውጤት ማጠናቀቃቸውን የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ 85 በመቶ የሚሆኑ የትምህርት ቤት አመራሮችም በተመሳሳይ ከማለፊያ ነጥቡ በላይ አስመዝግበዋል ብሏል፡፡ በትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ የትምህርት ልማት ዘርፍ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር)፤ በተለይ ከ2016 ክረምት ጀምሮ የመምህራን ስልጠና ትኩረት በሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት ላይ ተጨባጭ ብቃት እንዲያዳብሩ ማገዝ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በሥልጠናው መምህራንን ብቻ ሳይሆን የትምህርት ቤት አመራሮችን አቅም እንዲያጎለብቱ ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን አብራርተዋል። ይህን የክረምት ስልጠና በመጀመሪያው ዓመት ከ52 ሺሕ በላይ እንዲሁም በሁለተኛው ዓመት ደግሞ ከ62 ሺሕ በላይ መምህራንን በአጠቃላይ ከ110 ሺሕ በላይ መምህራን የወሰዱት ሲሆን፤ አብዛኞቹ መምህራን እና አመራሮች የተሰጣቸውን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና በጥሩ ውጤት አጠናቀዋል ተብሏል፡፡ የማለፊያ ነጥብ ያላገኙት 30 በመቶዎቹ መምህራን በቀጣዩ የክረምት የትምህርት ዘመን በድጋሚ ሥልጠናውን ወስደው ለፈተና እንደሚቀመጡ መሪ ሥራ አስፈጻሚው ለአሐዱ አስታውቀዋል።
Hammasini ko'rsatish...