uz
Feedback
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

Kanalga Telegram’da o‘tish

Journalist-at-large

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
133 804
Obunachilar
+224 soatlar
-1627 kunlar
-57230 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ ህዝቡ ካለችው ላይ ቀንሶ ወገኔን ላግዝ ብሎ ሲነሳ "ከድርጊትህ ታቀብ" የሚል አሳፋሪ እና አሳዛኝ የሆነ አካሄድ ነው። ትግራይ ውስጥ የተራቡ ወገኖቻችንን ለመደገፍ 50 ሺህ ብር በመሠረት ሚድያ ስም አግዛለሁ፣ ሁላችንም ትብብር በማድረግ ሰብዓዊነታችንን እና የመተጋገዝ ባህላችንን እናቆይ። @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
👍 549 217😢 87🙏 54😁 24🤔 11😱 9
ግልፅነትን እና ሌብነትን 'ሙሉ በሙሉ ያጠፋል' በሚል በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የተጀመረው ካሜራ ሌላ የሌብነት ስልት ይዞ መጥቷል። ከስራ ሰዓት ውጪ ካሜራውን ቢሯቸው አስረክበው ይመጣሉ፣ ከስራ ውጪ አልስተናገድም ያለ ነጋዴን ደግሞ በነጋታው ካሜራ አርገው መጥተው ስቃይ ያበላሉ። በተመሳሳይ አንዳንድ የቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ሰራተኞች የሙስና ተግባር በመሠረት ሚድያ ሲጋለጥ ለትንሽ ሳምንታት ጋብ ካለ በኋላ ከሰሞኑ እንደ አዲስ እየጀመሩ ነው፣ ከሰሞኑ በምስል እና ቪድዮ የተደገፈ ተከታታይ መረጃ ይቀርባል። እንዲህ ያለውን ችግር በቴክኖሎጂ ማገዝ ይቻል ይሆን እንጂ ሙሉ በሙሉ መፍታት ይከብዳል፣ ዋናው ስራ ግብር ሰብሳቢዎቹ እና የጉምሩክ ሰራተኞቹ ጭንቅላት ላይ ስራ መስራት እና ጉቦኛውን ደግሞ በደንብ መቅጣት ነው። እስከዛው ቢያንስ ነጋዴው የራሱን ካሜራ ደረቱ ላይ ገጥሞ ስራውን እንዲሰራ ምክሬ ነው፣ መስረቅ የለመደን ባንዴ ማስቆም ይከብዳል። https://www.meseretmedia.org/p/11
Hammasini ko'rsatish...
319👍 129😢 104😁 66🤔 15😱 7🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
My new story out in The Howard County Beacon. I spent time with Chef Alba exploring how food connects culture, memory, and community here in Maryland. Take a look 👇 https://www.thebeaconnewspapers.com/howard-county/
Hammasini ko'rsatish...
👍 163 82😁 12🙏 5😱 1
ያልታደለ ግብስብስ የመንግስት ሚድያ ሆኖ እንጂ ጋምቤላ ክልል አሁን ላይ እየተከሰተ ካለው የዜጎች ግድያ እና መፈናቀል ውጪ ሌላ ዋና ጉዳይ ሀገር ውስጥ አልነበረም። ታጣቂዎች እንካፍንጫቸው ታጥቀው ለመገዳደል እየተመሙ ይገኛሉ፣ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ጭምር ገብተው ህዝቡን እየጨረሱ ነው። ትኩረት ለጋምቤላ ክልል! https://www.meseretmedia.org/p/636
Hammasini ko'rsatish...
😢 561👍 78 61😱 22🤔 13🙏 9🕊 7
Photo unavailableShow in Telegram
የወዳጄ የተስፋዬ ወልደዮሐንስ ሀይሌ “የተደለዙ ገጾች” መፅሐፍ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ለኢትዮጵያ ለገበያ ይቀርባል፣ አማዞን ላይ ደግሞ በዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል ⤵️ https://a.co/d/9q7qJpY
Hammasini ko'rsatish...
👍 113 34🙏 7😁 4
#YouTube ከሰሞኑ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር በኢሚግሬሽን ዙርያ አዳዲስ ለውጦችን ማድረጉን ወይም ሊያደርግ ማሰቡን እያስታወቀ ይገኛል። ታድያ ይህ ለውጥ ለኢትዮጵያውያን እና ለትውልደ ኢትዮጵያውያን ምን ይዞ ይመጣ ይሆን? በዚህ ዙርያ የመሠረት ሚድያ በርካታ ተከታታዮች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በአሜሪካን ሀገር የኢሚግሬሽን የህግ ባለሙያ ከሆነው ጠበቃ ሙሉአለም ጌታቸው ጋር ሰፋ ያለ ውይይት አድርገን ነበር፣ ይከታተሉት። https://youtu.be/Iowexmd_OtQ?si=G2NWB0EzdGfCWKBy
Hammasini ko'rsatish...
149👍 48🙏 17😁 2
ከሰሞኑ መንግስት ቆፍጠን ያሉ እርምጃዎችን ሲወስድ እየተመለከትን ነው። በተለይ አንድ ሰሞን አይነኬ የሚመስሉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ጥብቅ የምርመራ ፋይል እየተከፈተ ነው። ጥሩ ሲሰራ ማመስገንም ይገባልና በርቱ ልንል እንወዳለን 🙏🏽 @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
👍 1 570 327🙏 130😁 24🕊 23🤔 16😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
አንድ አጭር ክትትል አረግን። መሠረት ሚድያ ላይ ከሚቀርቡ የመልካም አስተዳደር፣ የሙስና እና ህዝብ ላይ የሚደርሱ በደሎች ዘገባዎች መሀል በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ 65 ፐርሰንት ገደማው በሚመለከተው አካል ምላሽ ተሰጥቶበታል፣ ወይም ምላሽ ለመስጠት ሙከራ ተደርጓል (ለማሳያ አንድ የዛሬ ዘገባን ይመልከቱ: https://www.meseretmedia.org/p/2aa) አንድ የመንግስት ሀላፊ በቅርቡ "አንዳንዴ ታበዙታላችሁ እንጂ ሚድያችሁ ስራዎችን ለማስተካከል እየጠቀመን ነው" በሚል የተናገሩት ለዚህ ይመስላል። 'ታበዙታላችሁ' የሚለው ያው subjective ነው 🙃 ታድያ በእንዲህ አይነት የሁሉንም በር ቀስ በቀስ በሚያንኳኳ የመልካም አስተዳደር ችግር ዙርያ ትኩረት ተደርጎ ዜና ሲሰራ ካድሬው "ተቃዋሚ" የሚል ስም ለመለጠፍ ይሯሯጣል፣ መሠረት ሚድያ ግን ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል። በዚህ ሊንክ የመሠረት ሚድያ የፕሪሚየም አባል በመሆን ስራውን የበለጠ ለማስፋት እና በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ቋንቋዎች ስራ ለመጀመር እያደረግን ያለውን ዝግጅት ይደግፉ ⤵️ https://meseretmedia.substack.com/30pcoff
Hammasini ko'rsatish...
476👍 238🙏 23😁 19🕊 10🤔 5😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
ፅዳትም ሆነ ልማት ለራስ ነው... ነገር ግን እነዚህን ተግባራት በሁለት ቀን ውስጥ ያልፈፀመ ነዋሪ በአዋጅ እንደሚቀጣ ደብዳቤው ይጠቅሳል፣ ይህ ስፍራ ደግሞ ጡረተኞች በብዛት የሚኖሩበት አካባቢ ነው። ጥድፊያው ለምድን ነው? ይህን ሁሉ ለማድረግ ነዋሪው ሁሉ አቅም አለው ብሎ የወሰነውስ ማነው? - ራዲየስ ማፅዳት - ኮምፖስት ወይም ቀዝል ማዘጋጀት - ያረጁ ዛፎችን እና አበባዎችን መከርከም - ከርብ ስቶን መስራት እና ጥቁር በቢጫ ቀለም መቀባት - በተሰሩ ከርብ ስቶኖች ውስጥ አበባ መትከል - ቆሻሻ በአይነት መለየት እና ለፅዳት ማስረከብ - አጥሮችን ግሬይ ቀለም መቀባት - ካሜራ ማስገባት - ወል ማውንት ማውጣት... @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
😢 342 124🤔 54😁 40👍 24😱 12🙏 10🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
#የኢሚግሬሽንነገር በትናንትናው እለት መሠረት ሚድያ አዲሱ የኢሚግሬሽን ዌብሳይት መስራት እንዳቆመ አንድ መረጃ አጋርቶ ነበር። በደቂቃዎች ልዩነት ውስጥ ኢሚግሬሽን በፌስቡክ ጉፁ ላይ ማንኛውም ፓስፖርት ፈላጊ www.immigration.gov.et ላይ መመዝገብ እንደሚችል እና ዌብሳይቱ እንደሚሰራ ምላሽ ሰጠ። ማንም ሊንኩን ከፍቶ ማረጋገጥ እንደሚችለው ዌብሳይቱ ዛሬን ጨምሮ ለበርካታ ቀናት መስራት አቁሟል፣ በርካቶችም እየተንገላቱ ይገኛሉ። በአካል ለሚሄድ እና ጉቦ እስከ 35,000 ብር ለከፈለ በውስጥ ይሰራሉ። ዌብሳይቱ በርካታ ሺህ ዶላሮች ወጥቶበት ዱባይ ባለ ካምፓኒ የተሰራው ነው። ይህ ለረጅም ግዜ የቆየ ዝርፊያ አሁንም ቀጥሏል፣ በተቋሙ የሚቀርቡ ሪፖርቶች ግን ሁሉ ነገር የተስተካከለ እና ዜጋ በአሰራሩ ተደስቶ እንደሚወጣ ነው። ቢያንስ 'እንዴት የማይሰራ ዌብሳይት ይሰራል ተብሎ ይለጠፋል?' የሚለው ጥያቄ መልስ የለውም። @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
👍 748 188😢 112😁 71🤔 37🙏 18😱 11🕊 7
Photo unavailableShow in Telegram
ከሰሞኑ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲሰራጭ የነበረው ቪድዮ እጅግ አሰቃቂ እና በክቡር የሰው ልጅ ላይ የተፈፀመ ነውር ነው፣ ማንም ሁሌም ሊያወግዘው የሚገባ ተግባርም ነው። የቪድዮውን መውጣት ተከትሎ ይህ ምስል ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲሰራጭ ቆይቷል። ምስሉ “እውነት እያደረች ትጠራለች ተደብቃ አትቀርም! የጨካኙ የብልፅግና ድራማ በማስረጃ ተጋልጧል” የሚል ጽሁፍም ይዟል። ይህም በጭካኔ ድርጊቱ የመንግስት እጅ እንዳለበት ህዝብን ለማሳመን የተደረገ ሙከራ እንደሆነ አንዳንዶች ሲገልፁ ተስተውለዋል። ይሁንና ምስሉ በ AI የተፈበረከ ሀሰተኛ ምስል እንደሆነ SynthID Detector በመጠቀም አረጋግጠናል። ለዝርዝሩ የኢትዮጵያ ቼክ ዘገባን ያንብቡ: https://tinyurl.com/fake-ai-image @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
👍 382 146😢 42😁 28🤔 10😱 4🕊 4🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
Hammasini ko'rsatish...
😢 108 19🙏 12👍 5😱 5😁 4🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
መሠረት ሚድያ በአርሲ ዞን ውስጥ የማርበርግ ቫይረስ እንደተከሰተ ለሰራው ዘገባ የአካባቢው ባለስልጣናት "ውሸት ነው" የሚል ምላሽ ከሰጡ በኋላ ከታች የሚታየውን አበረታች የሆነ ምላሽ ለቲክቫህ ሰጥተዋል፣ መረጃውን እንደ ጥቆማ በመውሰድ እየተጠቀሙበትም እንደሆነ ተናግረዋል። ውሸት ነው የሚለው ግዜውን ጠብቆ መታወቁ አይቀርም። በሚድያው በሽታው ተከስቶበታል በተባለው አካባቢ ናሙና የመውሰድ እና ግንዛቤ የማስጨበጫ ስራ ከተሰራ ግን ሌላው ትርፍ ነው። የሚድያም ሚና እሱ ነው!
Hammasini ko'rsatish...
454👍 254😁 47🙏 31😢 15🤔 9😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
Join us now! Be part of the conversation ⤵️ መሠረት ሚድያ ተደራሽነቱን ለማስፋት የሚያደርገው ጥረት አካል የሆነው የፕሪሚየም አባልነት የ30% ቅናሽ ክፍት ተደርጓል፣ ይህን ሊንክ በመጠቀም አሁኑኑ ይቀላቀሉ። አንድም ሀገራዊ መረጃ አያምልጥዎ! https://meseretmedia.substack.com/30pcoff
Hammasini ko'rsatish...
136👍 38😁 36
ከሰሞኑ እየተዛመተ ባለው የማርበርግ ቫይረስ ዙርያ ግልፅነት የሌለው አካሄድ የበርካታ ሰውን ህይወት አደጋ ላይ ይጥላል! መሠረት ሚድያ በጂንካ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ከዘገበ ከስድስት ቀናት በኋላ ጤና ሚኒስቴር ማረጋገጫ ሰጠ፣ አሁንም እንደ አርሲ ባሉ አካባቢዎች ሰዎች ህይወታቸው እያለፈ መሆኑን የጤና ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው። መረጃውን በፍጥነት ለህዝብ ይፋ አርጎ ሰው እንዲጠነቀቅ ማረግ አይሻልም? በሽታው ገባባቸው በተባሉ አካባቢዎች ልየታ እስከሚደረግ ማንም ሰው እንዳይገባ እና እንዳይወጣ መደረጉ መልካም ቢሆንም ይህን ክስተት 'ገፅታ እንዳያበላሽ' በሚል መደበቁ በሰው ህይወት መቆመር ነው። እነዚህ ከታች ስማቸው የተቀመጠ ሰዎች በአርሲ ሶን አሰኮ ወረዳ ሁሉቆ ቀበሌ ውስጥ ብቻ ህይወታቸውን እንዳጡ በመሠረት ሚድያ የተረጋገጡ ናቸው: 1. አሜ ሙሳ 2. ሳኒ አህመድ 3. አብራሒም ሃሚዶ 4. አብዱረማን በያን 5. ሙሃመድ አብዲ አብዱላ 6. ሙለታ ኢብሮ 7. ሆሴና ሙሜ 8. ህፃን መይሙና ሳና አህመድ 9. ህፃን ማሪፋ ሙሃመጥ 10. በጥሪያ ከማል ሙሜ እና 11./አሺረፋ አደም የመሠረት ሚድያን ዘገባ ያንብቡ: https://meseretmedia.org/marburg-virus
Hammasini ko'rsatish...
😢 406 161👍 57🤔 16🙏 15😱 11😁 7
Photo unavailableShow in Telegram
የቲክቶክ ተሰላፊ ባልሆንም አንዳንዴ ጎራ እላለሁ፣ ባለፉት ጥቂት ቀናት ግን አንዱ ተጠቃሚ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን እዚህ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ለማቅረብ እንኳን በሚቀፍ እጅግ አፀያፊ ስድብ ሲሳደብ ሰማሁ። አፀያፊ ስድቡ እንደ ፌስቡክ ባሉ ፕላትፎርሞች ላይ ቀርቦ ቢሆን አንድ ቀን አይቆይም፣ ቲክቶክ ግን ቁጭ ብሎ እየተመለከተ ነው፣ ይህ ደግሞ ተቀባይነት የለውም። በፍፁም! ለሚመለከተው የቲክቶክ የአፍሪካ ቡድን ጉዳዩን በግሌ በኢሜይል ዛሬ አሳውቄያለሁ። ሁሉም ሀይማኖት፣ ብሄር፣ የፖለቲካ አስተሳሰብ ሳይለይ እንዲህ አይነት ፀያፍ ጥቃቶችን ሪፖርት ያድርግ። ወደፊትም በየትኛውም ሀይማኖት ላይ እንዲህ አይነት ድርጊት ሲፈፀም ህዝብ ተባብሮ ሊያዘጋ ወይም ኮንተንቱን ሊያስወርድ ይገባል። @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
🙏 1 471👍 383 255😁 41🕊 23🤔 10😢 6😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
'የወባ ወረርሽኝ ከ50 በመቶ በላይ ቀነሰ' የሚል አስገራሚ መረጃ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዴኤታው ለመንግስት ሚድያ ተናገረዋል። ይህ መረጃ የወጣው እንደ ዳውሮ ዞን ባሉ አካባቢዎች በአሁኑ ሰአት በየቀኑ በደርዘን የሚቆጠር የሰው ህይወት እየጠፋ ባለበት እና ሆስፒታል እና ጤና ጣቢያ ሞልቶ ሰው በየዛፍ ስር ተኝንቶ በሚታከምበት ወቅት ነው (ዝርዝሩን ያንብቡ: https://tinyurl.com/5wt7s29m) የአለም ጤና ድርጅት የቅርብ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያ ለአመታት የወባ ወረሽኝን በመከላከል ዙርያ ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች እየተሸረሸሩ አሁን ላይ ከ7.3 ሚልዮን በላይ የወባ ተጠቂዎች መመዝገባቸውን ነው፣ ይህም የዛሬ ሁለት አመት ከነበረው እጥፍ ገደማ ማለት ነው። ሰው ሲሞት ውሸት ነው፣ ወባ ሲከሰት እየጠፋ ነው፣ ህዝብ ሲራብ ምርት ጨምሯል፣ እገታ ጨምሯል ፀጥታው አስተማማኝ ነው... ከእውነት ጋር እንዲህ የተጣላን ሆነን መቅረታችን ያሳዝናል። ሁለት ማስረጃዎች ⤵️ https://www.doctorswithoutborders.org/latest/unprecedented-surge-malaria-cases-ethiopia#:~:text=More%20than%207.3%20million%20malaria,with%20previous%20and%20ongoing%20conflict. https://www.nytimes.com/2024/10/25/health/malaria-ethiopia-deaths-cases.html#:~:text=Global%20Health-,Malaria%20Is%20Surging%20in%20Ethiopia%2C%20Reversing%20a%20Decade%20of%20Progress,an%20alarming%20spread%20of%20cases. @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
😢 478👍 172 122😁 20🙏 10🤔 6🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
የእለት ጉርስ ለማግኘት የሚንከራተቱ ወጣቶች ከየመንገዱ ካለፍላጎታቸው እየታፈሱ የት እየተወሰዱ እንደሆነ የዛሬ ዓመት ገደማ ይህን አስፍሬ ነበር፣ መሠረት ሚድያም በምርመራ ዘገባዎቹ በተደጋጋሚ ሲጠቁም ነበር። ቢቢሲ አማርኛ ዛሬ ባወጣው መረጃ መዳረሻቸውን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን በመንግስታዊው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መርማሪዎች የተደረሰበትን አሳዛኝ የልጆቹን ሁኔታ ዳስሷል። እውነት አንዳንዴ ለግዜው ብትደበቅም መውጣቷ አይቀርም። የቢቢሲን ዘገባ ለማንበብ: https://www.bbc.com/amharic/articles/c74jrydd1vko?fbclid=IwdGRzaAOAZ61jbGNrA4BnqWV4dG4DYWVtAjExAHNydGMGYXBwX2lkDDM1MDY4NTUzMTcyOAABHpY2BelnU6mYkaIPuxmZ0t913CGOUnAWf_dbZZgb2ogXQNkSvD7ucKe44dzA_aem_Vt4a6vS40R1M2XEciTCECQ @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
283😢 194👍 68🕊 8🙏 7😁 3🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሊደገም፣ ሊደጋገም የሚገባው አሰራር! መሠረት ሚድያ ላይ በቅርቡ የወጣ አንድ በከፊል የተሳሳተ መረጃ ነበር፣ መረጃውን ለማስተባበል ደግሞ ዜናው ላይ በስህተት ከተጠቀሱት ሁለት ግለሰቦች አንደኛዋ ከጠ/ሚሩ ጋር የጎንደር ጉብኝት ላይ እንዲሳተፉ ተደርገው ፎቶው ዛሬ በጠ/ሚር ቢሮ እና በመንግስት ሚድያዎች ላይ ተለቋል። ይህ ብልሀት የተሞላበት እና በማስረጃ የተደገፈ ማስተባበያ በውጭ አለም በስፋት የሚሰራበት እና እሰረው፣ አሳደው ከሚለው በሀገራችን ከተለመደው የተለየ ነው፣ ወደፊትም ስህተቶች ሲኖሩ ሊደገም የሚገባው ስልት ነው። መሠረት ሚድያም እርምቱን ዛሬ አውጥቷል። ለመሠረት ሚድያ በጠ/ሚር ቢሮ ደረጃ እንዲህ ምላሽ መሰጠቱ የሚድያውን ተደራሽነት፣ ተሰሚነት እና እድገት ጠቋሚ ነው። ከዚህ በፊት በዚህ ደረጃ ለአንድ ወይም ሁለት የውጭ ሀገር ሚድያዎች ምላሽ ሲሰጥ አስታውሳለሁ። ይሁንና መሠረት ሚድያን በዚህ መልኩ የሚከታተሉት ከሆነ ሌሎች በሚያቀርባቸው እንደ መብት ጥሰት፣ ሙስና እና የዜጎች የዕለት ተዕለት ተማፅኖ እና እሮሮዎች ዙርያም በተመሳሳይ በከፍተኛ የመንግስት ደረጃ ምላሽ ቢሰጥበት መልካም ነው እላለሁ። #መሠረትሚድያ @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
👍 700 311😁 127🤔 26🕊 14🙏 7
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ እንግዲህ ባሳለፍነው ሳምንት 25 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በአርሲ ሐገረ ስብከት ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉ፣ ትናንት ተጨማሪ 5 ሰዎች በተመሳሳይ እንደሞቱ ለወጣው መረጃ ማርከሻ መሆኑ ነው። የሀይማኖት አባት እና የሀገር ሽማግሌ ንፁሀን ህዝብ ሲጨፈጨፍ ሀዘኑን ገልጾ፣ ድርጊቱን አውግዞ እንዲሁም ወደፊትም እንዳይደገም ከህዝብና መንግስት ጋር ይመክራል እንጂ በሚጨፈጨፍ ህዝብ እንዲህ አይሳለቅም። ይህ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ግድያቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ከማድረግ ውጪ ሌላ አላማ ያለው አይመስልም። This is truly sad! @EliasMeseret
Hammasini ko'rsatish...
😢 1 002👍 172 123😁 26🕊 12🤔 9